Dilla University Official @dprd9 Channel on Telegram

Dilla University Official

@dprd9


University of the Green Land

Dilla University Official (English)

Are you looking for a reliable source of information about Dilla University? Look no further than the 'Dilla University Official' Telegram channel! This channel, with the username @dprd9, is the go-to place for all the latest news, updates, and announcements from the University of the Green Land. Dilla University is known for its commitment to excellence in education and research, and this official channel is dedicated to keeping students, faculty, staff, and alumni informed about the university's activities. Whether you are a current student looking for information about class schedules and campus events, a prospective student interested in learning more about the university's programs, or an alumni wanting to stay connected with your alma mater, this channel has got you covered. By joining the 'Dilla University Official' Telegram channel, you will have access to a wealth of information, including important announcements, upcoming events, links to academic resources, and much more. You will also be able to interact with other members of the university community, share your thoughts and experiences, and stay connected with the latest developments on campus. Don't miss out on this valuable resource! Join the 'Dilla University Official' Telegram channel today and stay informed about everything happening at the University of the Green Land. Whether you are a current student, an alumni, a faculty member, or simply interested in learning more about this prestigious institution, this channel is the perfect place to connect with the Dilla University community. Join us now and be a part of the conversation!

Dilla University Official

14 Nov, 12:34


#የተራዘመ_የውድድር_ማመልከቻ_ጊዜ ማስታወቂያ

Dilla University Official

12 Nov, 14:36


#Reminder

ለመካከኛ አመራርነት የወጣው ክፍት የኃላፊነት ቦታዎች ማመልከቻ ጊዜ የሚጠናቀቀው በቀን #5_03_17 ዓ.ም (ሐሙስ) መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://[email protected]

Dilla University Official

09 Nov, 18:54


#በምርምርና_ቴክኖሎጂ_ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዘርፍ ስር ባሉ ክፍት የኃላፊነት መደቦች ለመወዳደር ያመለከታችሁ መምህራንና ተመራማሪዎች ከዚህ በታች በቀረበው ማስታወቂያ አግባብ የስልታዊ እቅዳችሁን #ሶፍት_ኮፒ በማስታወቂያው ላይ በተገለጹት አድራሻዎች እንድትልኩ ተጠይቃችኋል።

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://[email protected]

Dilla University Official

09 Nov, 15:17


#ማስታወቂያ
#ለዲላ_ዩኒቨርሲቲ_አስተዳደር_ሰራተኞች_በሙሉ

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች ደልዳይ ኮሚቴ የሰራተኞችን ድልድል ያጠናቀቀ በመሆኑ በቀን 02/03/2017 ዓ.ም ከ8:00 ጀምሮ በነባሩ ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ በሚሰጠው ገለጻና አጠቃላይ ውይይት እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://[email protected]

Dilla University Official

08 Nov, 17:49


የተስፋ ጥሪ
https://youtube.com/watch?v=4rFUqBFYa40&si=ueCIUrrnVoCtdQpN

Dilla University Official

07 Nov, 17:54


በዶመርሶ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር መንደር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ዲዩ፣ ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (ህዓግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት በይርጋጨፌ ወረዳ ለዶመርሶ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር መንደር ሰራተኞችና የአከባቢው የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

የማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የዶመርሶ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር መንደር የተቋቋመው በአካባቢው ያለው የቡና ምርት በእርጅና እና በወቅቱ ተከስቶ በነበረው ውርጭ ምክንያት የቡና ምርትና ምርታማነት በመቀነሱ ከወረዳው አስተዳደር እና ከማህበረሰቡ በቀረበው ጥሪ እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ተካልኝ አያይዘውም ዲላ ዩኒቨርስቲ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር መንደር የቡና እና የእንሰት ችግኞችን እያዘጋጀ ለአከባቢ ማህበረሰብ ሲያደርስ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው በተፈጠረው የስራ እድልም በርካታ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ አስገንዝበዋል።

አቶ ተካልኝ አክለውም፤ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር መንደሩ ለአካባቢው ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ብሎም ለአለም ሀብት በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ ሊጠብቀውና ሊንከባከበው ይገባል ብለዋል።

#ለዝርዝሩ👇
https://www.facebook.com/share/p/18TjoSVguS/

Dilla University Official

06 Nov, 13:10


#Miss_it_not

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
ዛሬ ምሽት ከዜና ሰዓት ቀጥሎ እንዳያመልጦት

https://web.facebook.com/fanabroadcasting/videos/891096442731414

Dilla University Official

06 Nov, 06:30


#ማስታወቂያ
#ለዲላ_ዩኒቨርሲቲ_መምህራንና_ተመራማሪዎች

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት #የኃላፊነት_ቦታዎች መምህራንና ተመራማሪዎችን አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል።

ፍላጎቱ ያላችሁ መምህራንና ተመራማሪዎች #ከዛሬ_ጀምሮ_ባሉት_ሰባት_ተከታታይ የስራ ቀናት #ፕሬዚዳንት_ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ እንድታመለክቱ ተጋብዛችኋል።

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://[email protected]

Dilla University Official

05 Nov, 16:04


በፀጥታና ድህነት ዙሪያ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄደ

ዲ.ዩ፣ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በተቋሙ የፀጥታና ደህነት ዙሪያ የተቋሙ የጥበቃ ሰራተኞችን፣ የግቢውን ፌደራል ፖሊስ አባላት ተወካዮችን፣ የአከባቢውን የፀጥታና የፍትሕ አካል ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተካሂዷል።


ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በውይይት መድረኩ ባደረጉት ንግግር እንደ ሀገር የተጀመረውን የትምህርት ሪፎርም ለማሳካት የሚያስችል የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ታስቦ አጠቃላይ የአካዳሚክና አስተዳደር ሰራተኞች የውይይት መድረክ ተካሂዶ እንደነበር አውስተው ከውይይት መድረኩ በተገኙ ግብአቶች መሰረት በሰራተኞች የተነሱ ጥያቄዎችን እና የተሰጡ አስተያየቶችን በአጭር፣ መካከለኛ እና በረዥም ጊዜ እቅድ በመያዝ አበረታች ስራዎች በመከናወን ገልጸዋል።

በሰራተኞች ውይይት ከተነሱ ጉዳዮች የፀጥታና ድህነት ጉዳይ አንዱና ዋነኛው ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ በመሆኑ የዛሬው የውይይት መድረክ መዘጋጀቱን ነው ክቡር ፕሬዝዳንቱ የገለፁት።

ዶክተር ኤልያስ አያይዘውም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል፣ የተቋሙን ሀብትና ንብረት ለሚፈለገው ዓላማ ብቻ እንዲውል ለማድረግ የፀጥታ አካላት የተቀናጀ ስራ የማይተካ ሚና እንዳለው አምነው ስራቸውን በቅንነትና በትጋት የሚወጡ አብዛኛው የዩኒቨርስቲው የጥበቃ ሰራተኞች እንደመኖራቸው ሁሉ በተቃራኒው ተቋሙን የሚጎዳና የጥበቃ ሰራተኞችን ስም በሚያጎድፍ ተግባር የሚሳተፉ ጥቂቶች አባላት በመኖራቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዩኒቨርስቲው የሚገደድበት ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን አስገንዝበዋል።

#ለዝርዝሩ👇
https://www.facebook.com/share/p/DnPz76FQ8MsbZGci/