Ayu ze Habesha - Official @ayuzehabeshaoficial Channel on Telegram

Ayu ze Habesha - Official

@ayuzehabeshaoficial


ጥቆማ‼️
በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ፣በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ‼️‼️
#Ayu-zehabesha-official
ለማስታወቂያ እና ጥቆማ ለመስጠት 👉 @ayulaw0
#Ayuzehabesha #አዩዘሀበሻ #Ayu #አዩ #ዘሀበሻ #Ethiopianews #Ayuzehabeshanews #Zehabesha #AyuzehabeshaOficial

Ayu ze Habesha - Official (Amharic)

አዩ፣ ዘሀበሻ የሚመጣው ልዩ የቴሌግራም እርምጃ አዲስ መረጃ እና መረዋንድያን እንዲሆኑ በነጻ ያስገኙት ማህበረሰብ ነው። ከውጭ በከተሞች ያሉት ጥቆማዎች፣ ታመነጅ እና እስከ ስራ ሠይጣዊ መረጃ የሚሰጥ ስልጠና አይሁኑ። በእነዚህ ውሃብታም ከሚጠቀሙት ተጠሞች እና ተመሠረተዋል ያሉበት ስልጠና ለመስጠት ለፈጣን የምንሰጣቸው፣ እናቶች እና እንስሳት ተነበቡ። ጥቆማዎችን ወይም መረከቦችን እንዴት በትልቅ ይተላለፋል? ከእውነት ውስጥ ተመልከቱ ማህበረሰብ እና እድዎታልን? ስንት ጥረት እንዳልያስገባት ስልጠና እንግዳለን? አስተያየቶችዎ የቴሌግራም አባላት ለሆኑ በሥራዎ በጣም ሁኔታዎችን በያዘ በርክታ እና በርክታ እንዴት መረጃ ማስተማር።

Ayu ze Habesha - Official

16 Nov, 09:17


ጦርነቱ በቅርቡ ሊያበቃ ይችላል
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት በቅርቡ ሊቆም እንደሚችል ተናገሩ
የዶላንድ ትራምፕን መመረጥ ተከትሎ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው ድጋፍ ሊቆም እንደሚችል በመጠቆም የራሺያ እና ዩክሬይን ጦርነት በቅርቡ መቆሙ አይቀርም ሲሉ ለአንድ የዩክሬን ሚዲያ ተናግረዋል።
"ጦርነቱ በይፋ መቼ ይቆማል"? የሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው " ጦርነቱ መቼ እንደሚቆም የተቆረጠ ቀን ባይኖርም፣ነገር ግን በቅርቡ መቆሙ አይቀርም "ሲሉ መልሰዋል።
ዶናልንድ ትራምፕ ዘለንስኪ ወደ አሜሪካ እየመጣ ቢሊዮን ዶላር አፍሶ የሚሄድበት ዘመን ያበቃል ማለታቸው ይታወሳል።

Ayu ze Habesha - Official

16 Nov, 09:10


ቤተመንግስት ተገኘ የተባለው ወርቅ ከተሸጠ የመንግስት አካላት ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው እናት ፓርቲ ገለፀ‼️

ፓርቲው ባወጣው መግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት “ባደረግነው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪ.ግ. ወርቅ ኮሚቴ አቋቁመን ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገብተናል” በሚል ያቀረቡት ገለፃ ላይ ለህዝብ ማብራርያ እንዲሰጡ ጠይቋል።

"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግልጽ አይደለም" ያለው ፓርቲው "ከእርሳቸው ወደ ሥልጣን መምጣት አስቀድሞ ለ44 ዓመታት ደርግ እና ኢህአዴግ ሲመሩ ይህ የተጠቀሰው ወርቅ ከእይታ ተሰውሮ ተደብቆ የተገኘ አዲስ ግኝት ወይንስ የአገር ቅርስ በመሆኑ ለጥፋት እንዳይጋለጥ ተጠብቆ የቆየ ነው?" የሚለው ምላሽ እንደሚፈልግ ገልጿል። 

እናት ፓርቲ በመግለጫው በጠ/ሚኒስትሩ የተጠቀሰው ወርቅ በቤተ መንግሥት አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ወይንም ለነገሥታቱ ከውጭ አገራት መንግሥታት የተበረከቱ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከሆኑ እነዚህ ወርቅ ተብለው በወርቅ ዋጋ የሚገመቱና ተመዝግበው በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጡ ባንኩም አግባብነት አለው ባለው ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም ብሏል።

ይህን መሰል የአገር ቅርስ ወደ ተራ ወርቅነት ተለውጦ መልኩን እንዲቀይርና በወርቅም ሆነ በሌላ መልኩ ተሸጦ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በአጠቃላይና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በተለይ የጋራ ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው በመረዳት ከዚህ መሰል የጥፋት ሥራ እንዲታቀቡ እናት ፓርቲ በጽኑ ያሳስባል በማለት መግለጫውን አጠቃሏል።

@Esat_tv

Ayu ze Habesha - Official

15 Nov, 04:28


የደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች መምህራን የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ሥራ እንዲጀምሩ አስገዳጅ መመሪያ እንደወጣባቸው ገለጹ::

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሚገኙ መምህራን የጸጥታ ችግር ወደአለባቸውና ወደተመደቡባቸው የገጠር ት/ቤቶች ሄደው ሥራ እንዲጀምሩ በአካባቢው ባለሥልጣናት አስገዳጅ መመሪያ እንደወጣባቸው ገለጹ፡፡
መምህራኑ የተመደቡባቸው ቀበሌዎች በፌደራል መንግሥቱ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት የሚካሄድባቸው በመኾናቸው ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ ተናግረዋል፡፡ እንዳይቀሩ ደግሞ ወደምድብ ቦታቸው ካልሄዱ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡ መምህራኑ በዚህ መሃል ችግር ላይ መውደቃቸውን አመልክተው የጸጥታው ሁኔታ እስኪስተካከል መንግሥት ችግራቸውን እንዲረዳላቸው ጠይቀዋል፡፡
የአማራ ክልል መምህራን ማኅበር በመምህራኑ ስለተነሳው ቅሬታና ስጋት መረጃ እንዳለው ጠቅሶ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ አካላት የመማር ማስተማሩ ሂደት ከጸጥታ ችግር የጸዳ እንዲሆን በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

@VOA

Ayu ze Habesha - Official

15 Nov, 04:27


በተለምዶ ትፍታ የሚባለውን ወንጀል ተሽከርካሪን በመጠቀም ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የስርቆት እና የቅሚያ ወንጀል የሚፈፅሙ ናቸው ተብሏል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሳሪስ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ላይ ምራቅ በመትፋት እና ምራቁን የተፉት ባለማወቅ እንደሆነ ተናግረው ይቅርታ በመጠየቅ ምራቁን ከግለሰቡ ላይ የሚጠርጉ በመምሰል ከኪሱ ውስጥ ሞባይል ስልክ ሰርቀው በተለምዶ “ትፍታ” የሚባለውን ወንጀል ፈፅመው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-B41536 አ.አ በሆነ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ተሰውረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል አባላት ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩት እነዚህ ተጠርጣሪዎች በድጋሚ ወደ ለገሃር አካባቢ በመምጣት ተመሳሳይ ወንጀል ለመፈፀም ሙከራ አድርገው ሲያመልጡ የክትትል አባላቱ ቸርችል ጎዳና አካባቢ በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ለወንጀል ተግባር የሚጠቀሙበት ተሽከርካሪ ሲፈተሽ አራት ሞባይል ስልኮች ተገኝተዋል። ከእነዚህ ስልኮች መካከል አንዱ የህጻናት ፎቶ በእስክሪኑ ላይም የሚገኝ ሲሆን በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚል ግለሰብ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መስጠት እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

        ኢትዮ-መረጃ

Ayu ze Habesha - Official

15 Nov, 04:25


⚠️Somalia

ሶማሊያ በመማሪያ መፅሀፍቷ የኢትዮጵያን መሬት ወደ ራሷ አካተተች


ሶማልያ በመማሪያ መፅሐፍቶቿ ላይ የኢትዮጵያን ግዛቶች በራሷ ግዛት ስር ማካተቷ ተሰማ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ‹የሕልውና ስጋቴ ናት› በማለት በመማሪያ መፀሰሐፍቷ ላይ አስፍራ ተማሪዎቿን እያስተማረች ነው፡፡ ለዚህም የመማሪያ መፅሕፍቷን እንደገና መከለሷን ኢንሳይድ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

የሶማልያ መንግስት ሶማልያውያን ታዳጊዎች እና ህፃናት ኢትዮጵያ የህልውና ስጋት እና የሶማሊያ ታሪካዊ ጠላት እንደሆነች እንዲያምኑ በትምህርት ቤት ልጆች ላይ ማስረፅ ጀምሯል። ይህንን ትርክት ለመደገፍ የሞቃዲሾ አስተዳደር ለመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የታሪክ እና የጂኦግራፊ መማሪያ መፅህፍትን ከልሷል፡፡

እነዚህ የተሻሻሉት የታሪክ መማሪያ መፅሃፍት በኢትዮጵያ እና ሶማልያ መሀል ጥላቻ እና ቁርሾን የሚፈጥሩ ምእራፎች የተካተቱበት ነው፡፡ በተጨማሪም የተሻሻለው የጂኦግራፊ መማሪያ መፅህፍት የኢትዮጵያን መሬት በሶማሊያ ግዛት ውስጥ እንዲካተት እና እንዲጠቀለል አድርጎ ነው ያሻሻለው፡፡ በሶማልያ ግዛት ስር እንዲካተት የተደረገው የኢትዮጵያ መሬት አብዛኛው የሶማሌ ክልል ክፍል ነው፡፡

ይህም የሶማልያ ታዳጊ ትውልድ የዚያድ ባሬ ‹የታላቋ ሶማልያ› ትርክት በውስጣቸው ለማስረጽ ታልሞ የተደረገ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

Ayu ze Habesha - Official

14 Nov, 15:41


አልሸባብን የማዳከም ስራ እንደሚቀጥል  የኢትዮጵያ መንግስት ገለፀ

በሶማሊያ የሚገኘውን አሸባሪ ቡድን አልሸባብ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥጋት እንዳይሆን "በየትኛውም ሁኔታ አሸባሪ ቡድኑን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል" ሲል የኢትዮጵያ መንግሥስት አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠራዊት በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆኑን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማስታወቋን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም ሲጠየቁ ነው ይህንን ያሉት።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ "የማይነጣጠሉ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም" ያሉት ቃል አቀባዩ የሶማሊያ ማንግሥት ይፋ ላራመደው አቋም አልሸባብን እናዳክማለን ከማለት በቀር ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተካረረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ «የባሕር በር  እውቅና» የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን በሂደት ላይ መሆኑ ሲገለጽ በአንድ በኩል፣ አልሸባብን በመዋጋት ለዓመታት የጋራ ግብ እና ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሆድና ጀርባ አድርጎ ከቃላት ያለፈ የዲፕሎማሲ ቁርቁስ ውስጥ ከቷቸዋል።

Ayu ze Habesha - Official

14 Nov, 15:41


በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ‼️

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ያለሙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ሕዝባዊ ስልፉ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች እየተደረገ ሲሆን፤ በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች 'ሰላምን ለማጽናት የበኩላችንን እንወጣለን'፣ 'በሰላም እጦት ምክንያት የህዝቡ ስቃይ ሊቆም ይገባል'፣ 'ወደ ሰላም መመለስ መሰልጠን ነው' የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

@Esat_tv

Ayu ze Habesha - Official

14 Nov, 15:41


የድሮን ጥቃት!
በመንግስት የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ነው”- ኢሕአፓ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ “የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት ቢሆንም በሚያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር የዜጎች ህይወት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደቅጠል እያረገፈ ይገኛል” ብሏል፡፡

ኢሕአፓ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህገመንግሥቱን የመንግሥት አካላት ራሳቸው ካላከበሩት እንዴት ሊያስከብሩት ይችላሉ “በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደረጉት ግድያዎች ይቁሙ” ሲል አሳስቧል፡፡

እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከመዘገብ ቢቆጠቡም በውጪ የመገናኛ ብዙሀን ጭምር ጥቃቱ መፈጸሙን እየገለጹ መሆኑን እና ፓርቲውም አጣርቻለሁ ያለውን በየክልሉ የደረሱትን ጥቃቶች አስታውቋል፡፡

ፓርቲው አጣርቻለው ባለው መሰረት ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች የሟቾችን ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን እና ጥቃት ከተፈጸመባቸው ውስጥም ነፍሰጡሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት አመላክቷል፡፡

በመሆኑም  “ወደፊት ትውልድ እንዲከፍል በብድር በመጣ የጦር መሳሪያ ንጹሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄድ አግባብነት የለውም”፤ መንግሥት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ለማለት እንደዚህ ያለውን ሁኔታ በዝምታ ማስቀጠል አይችልም ሲል ኮንኗል፡፡

ኢሕአፓ  መንግሥት በተለይ የጦርነት አውድማ በተደረጉት በአማራ፣በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝና በደቡብ ክልሎች  ዉስጥ የሚደረገውን ህገመንግሥቱን እየጣሱ ያሉትን፣ መንግሥት መር የዜጎች ግድያዎችን በጥብቅ ማውገዙን እና   ጦርነቶቹ አሁኑኑ ይቁሙ ሲልም አሳስቧል፡፡

Ayu ze Habesha - Official

14 Nov, 07:46


አቶ ጃዋር መሀመድ ስለ አፈሳው የተናገሩት‼️

ካለፈው አመት ጀምሮ በኢትዮጵያ በታጣቂ ሃይሎች የሚፈጸመው የአፈናና የአፈና ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።  እነዚህ ወንጀሎች ብዙውን ጊዜ መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት የሚፈጸሙ ቢሆንም፣ የመንግሥት ኃይሎች ከተለያዩ ታጣቂዎች ጋር በመሰባጠር ትርፉን በመካፈል ላይ መሆናቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ይባስ ብሎ ደግሞ አሳሳቢ አዝማሚያ ታይቷል፡ የመንግስት አካላቶች አሁን ለብር ተብሎ የሚፈጸመውን አፈና በግልፅ እያረጋገጡ ነው።  እየተካሄደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት፣ መንግሥት ወታደራዊ ግዳጁን ለመሙላት እየታመነ ነው።  መጀመሪያ ላይ ቀዳሚ ኢላማው ያልደረሰው ወጣት፣ በተለይም ከቀያቸው ርቀው የሚሰሩ የቀን ሰራተኞች ነበሩ።  ይሁን እንጂ ትኩረቱ በቅርቡ ከሀብታም ቤተሰቦች ወደ ወጣቶች ተዘዋውሯል.

የአካባቢው የጸጥታ ባለስልጣናት ወጣቶችን ከትምህርት ቤት ወይም ከማህበራዊ ስፍራዎች ሲመለሱ እያሰሩ ወደ ጊዜያዊ እስር ቤቶች በግዳጅ እያጓጉዟቸው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።  የተያዙት ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች መጓጓዝን በመጠባበቅ ላይ እያሉ፣ ደላሎች ወደ ቤተሰቦቻቸው በመቅረብ ከፍተኛ ክፍያ እንዲከፍሉ ልጆቻቸውን ለማስፈታት ያቀርባሉ።  እነዚህ ክፍያዎች እንደ ቤተሰቡ ሀብት ከ100,000 እስከ 500,000 ብር ይደርሳል።  ባለሥልጣኖች እና ደላሎች የቤተሰብ ገቢ መረጃን ከባንክ እና ከግብር መዝገቦች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ፣ ይህም የታለመውን የመክፈል አቅም ለመገምገም እና ምን ያህል እንደሚፈልጉ ለመወሰን ያስችላቸዋል።  በእጃቸው ያሉት ገንዘብ የሌላቸው ከጓደኞቻቸው ለመበደር ተገድደዋል.  ቀጣዩ ተጎጂ ከመሆን በመፍራት ብዙ ወጣቶች ትምህርታቸውን እና ስራቸውን ትተው ተደብቀዋል።

ይህ አፈሳ በሩቅ የገጠር መንደሮች ብቻ የተገደበ አይደለም።  በዋና ዋና ከተሞች  ያሉ ቤተሰቦች አሁን ዋና ኢላማዎች ሆነዋል።  ይህ ከመላው ሀገሪቱ በወጡ ዘገባዎች ላይ የተመሰረተ ብቻ አይደለም - እኔ በግሌ የማውቀው ቤተሰብ ከጥቂት ቀናት በፊት ልጃቸውን ለማስፈታት 300,000 ብር መክፈል ነበረባቸው።  የኑሮ ውድነቱ ሊቋቋመው በማይችልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ ምዝበራ ጨካኝነት ነው።

የግዳጅ ግዳጅ መግባቱ ራሱ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው።  በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አሳዛኝ ነው!

@Esat_t

Ayu ze Habesha - Official

23 Oct, 12:38


" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው ፦

" የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡

ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክክል መምራት ይጠበቅበታል፡፡

ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡

እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡

ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅርና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡

ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡

በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት ? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡

ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡

በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ "

Ayu ze Habesha - Official

22 Oct, 05:39


ከሰዓታት ርብርብ በኋ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በሄሊኮፍተር ጭምር ተደጋጋሚ የውሃ ርጭት መደረጉ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው (6:00) አካባቢ በሰጡት አጭር ማብራሪያ " አሁን ላይ እሳቱን በቁጥጥራችን ስር አድርገናል ፤ የማጥፋትና የመልቀም ስራ ነው የሚቀረን እጅግ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ እዚህ ላይ ባይገታ በጣም ብዙ ቦታ ፣ ሰፊ አካባቢዎች ላይ እሳቱ ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ከዚህ የበለጠ ሃብትም ይወድም ነበር " ብለዋል።

በመርካቶ ሸማ ተራ ከምሽቱ 1:00 የጀመረው የእሳት ቃጠሎ አሁን ላይ (9:00)ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል።በሄሊኮፍተር ጭምር በተደጋጋሚ በተካሄደ የውሃ ርጭት መቆሙ ተነግሯል።

Ayu ze Habesha - Official

20 Oct, 20:17


እስራኤል በሂዝቦላህ የስለላ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ላይ ጥቃት ፈጸመች‼️

ሦስት የቡድኑ ከፍተኛ አዛዦችንም ገድያለሁ ብላለች

እስራኤል በቤይሩት በሚገኘው የሂዝቦላህ የስለላ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት እና በምድር ውስጥ በሚገኘው የጦር መሳሪያ ማምረቻ ጥናት ማዕከል ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።

የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ በተዋጊ ጄቶቹ ሦስት የሂዝቦላህ አዛዦችን መግደሉን አረጋግጧል።

ኮማንደሮቹ የተገደሉት በዋና መሥሪያ ቤቱ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ወይንስ በተለያዩ አካባቢዎች በተወሰደ እርምጃ የሚለው ጉዳይ በመግለጫው በግልጽ አልተጠቀሰም።

ሂዝቦላህ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

Ayu ze Habesha - Official

16 Aug, 15:42


🅰lert ‼️
ከአዲስ አበባ-ሸዋሮቢት-ደሴ ዋናው መስመር ልዩ ስሙ ጉዶበረት፣ጣርማበር፣ደብረሲና ዝቅ ብሎ ሾላ ሜዳ በሚባሉ አካባቢዎች ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል።
አሁን ላይ የተኩስ ልውውጡ ቆም ያለ ቢሆንም ውጊያ በባህሪው ተለዋዋጭ ስለሆነ በዚህ መስመር ጉዟችሁን ለማድረግ ያቀዳችሁ የመንገዱን ደህንነት አጣርታችሁ ብትጓዙ ይመከራል(አዩዘሀበሻ)።
====================

Ayu ze Habesha - Official

13 Aug, 07:59


#ዕለታዊ : የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጨመረ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

መግዣው ወደ 102.9899 ፤ መሸጫው ደግሞ 113.2889 ሆኗል።

ፓውንድ ስተርሊግም መግዣው 125.5507 ፤ መሸጫው 138.7004 ደርሷል።

ዩሮም ጨምሮ መግዣው ወደ 112.5577 ፤ መሸጫው 123. 8134 ገብቷል።

አንዱ የኩዌት ዲናር 321.2233 መግዣ ፤ 354.8592  መሸጫ ተቆርጦለታል።

የUAE ድርሃምም 28.0428 ተገዝቶ ፤ በ30.8471 ይሸጣል ተብሏል።

በግል ባንኮች ደግሞ የአንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ከ103 ብር አንስቶ እስከ 119 ብር ደርሷል።

(ዕለታዊ የባንክ ምዛሬ ከላይ ተያይዟል)

(ነሐሴ 7/2016 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Ayu ze Habesha - Official

13 Aug, 07:59


ህወሃት በመቀሌ ሰማዕታት አዳራሽ ለዛሬ ጠዋት 3:00 ለመጀመር ያቀደውን ጉባኤ ምክንያቱ ባይገለፅም ለከሰዓት 9:30 አዛውሮታል።👇

ትናንት አመሻሽ ላይ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሃት ጉባኤውን እንዳያካሂድ ማሳሰቡ ይታወሳል።

Ayu ze Habesha - Official

12 Aug, 05:26


የሩሲያ የቅርብ አጋር የሆነችው ቤላሩስ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር አስጠጋች

የዩክሬን ድሮኖቸ የአየር ክልሏን እንደጣሱባት የገለጸችው ቤላሩስ ተጨማሪ ወታደሮችን ከዩክሬን ወደምትዋሰንበት ድንበር ልካለች።
https://bit.ly/4cpeykZ

Ayu ze Habesha - Official

10 Aug, 05:57


የአማራ ፋኖ በወሎ የድርጅቱን አርማ (Logo) ይፋ አደረገ!

የአማራ ፋኖ በወሎ አዲሱን የድርጅት አርማ በዛሬው ዕለት ማለትም ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ የሚሰጣቸውን መግለጫዎች፣ ተጋድሎዎች እና ድርጅታዊ የጋራ መግለጫዎች በድርጅቱ አርማ ተደርገው እንደሚወጡ መግለፅ እንፈልጋለን!

ማስታወሻ:-

ባለፉት ጊዜያት ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የአማራ ፋኖ በወሎ እና የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ የሚሉትን ሁለት ስሞች በተለዋዋጭ በመጠቀማችን ምክንያት አንዳንድ ሚዲያዎችና ደጋፊዎቻችን ላይ ግራ መጋባት እንዳለ ተገንዝበናል::

ስለሆነም እዝ የሚለዉን ቃል የምንጠቀምበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት በመዋቅራችን ስር ያለን አንድ እዝ በመሆኑ እንጂ ድርጅታችን ወደፊት ሁለትና ከዛ በላይ እዞች ሊኖሩት ስለሚችል የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ የሚለውን ስያሜ ድርጅታችን አይጠራበትም::

በተጨማሪም እዝ የሚለው አደረጃጀት የወታደራዊ አደረጃጀትን ብቻ እንጅ የፖለቲካ የትጥቅ ትግል ለሚያደርግ ድርጅት የሚውል ስያሜም አይደለም::

ስለዚህ ሁሉም የሚዲያ አካላት እና አጠቃላይ ህዝባችን የድርጅታችን ስያሜ "የአማራ ፋኖ በወሎ" መሆኑን ተገንዝቦ ከዚህ ድርጅታዊ መግለጫ ከተሰጠበት ቀን ነሃሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን ስያሜ ብቻ መጠቀም እንዳለባችሁ እናሳስባለን::

ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ሕዝብ

የአማራ ፋኖ በወሎ
ወሎ(ቤተ-አምሐራ)፣ አማራ፣ ኢትዮጲያ
ነሃሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም

Ayu ze Habesha - Official

29 Jul, 09:46


#Breaking‼️#Update‼️
መንግስት የብርን የውጭ ምንዛሪን የመግዛት አቅሙን ከ15 እስከ 20 በመቶ ለማዳከም(devaluate)
ለማድረግ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅቶች ጋር ተስማማ👇👇
ኢትዮጵያ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓትን ተግባራዊ ልታደርግ ነው‼️
🔴 ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች  የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች “ለተወሰኑ ጊዜያት”  ይደረጋል ተብሏል

የኢትዮጵያ መንግስት “በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት” ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሆነ አስታወቀ። ውሳኔው በመንግስት ቁጥጥር ሲከናወን የቆየውን የውጭ ምንዛሬ ግብይት “በገበያው አማካኝነት እንዲበየን” የሚያደርግ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ እሁድ ማምሻውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል። አሁን በስራ ላይ በሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት፤ ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ54 ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ገዝተው በ58 ብር ከ64 ሳንቲም ገደማ ይሸጣሉ። በተለምዶ "ጥቁር" እየተባለ በሚጠራው ትይዩ ገበያ በአንጻሩ፤ ይህ የምንዛሪ ተመን ከእጥፍ በላይ ልዩነት አለው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት፤ ውሳኔው “በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል ይረዳል” ብሏል። የውጭ የምንዛሪ ተመን ስርዓት በገበያው ፍላጎት መሰረት ሲከወን፤ “የገቢ እና የወጪ ሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን ዋጋ ከገበያ እውነታዎች ጋር እንዲጣጣም ያስችላል” ያለው መንግስት፤ “በክፍያ ሚዛን ላይ ያለውን አለመመጣጠንም ለማስተካከል ይረዳል” የሚል ተስፋውን ገልጿል።

የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓትን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ በሚያደርጋቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች እና እርምጃዎች “ተጋላጭ” የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በመግለጫቸው አመልክተዋል።  “ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሊያስከትሉ ከሚችሉት የአጭር ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመጠበቅ አስፈላጊ የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች ለተወሰኑ ጊዜያት ይደረጋሉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አስፍረዋል።  በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚከተለውን ጭማሪም መንግስት በከፊል እንደሚደጉም አብይ ገልጸዋል።  #ኢትዮጵያኢንሳይደር #አዩዘሀበሻ
==≠===============≠===

Ayu ze Habesha - Official

14 May, 14:42


Channel photo updated

Ayu ze Habesha - Official

15 Apr, 16:20


Update‼️
በዚህ ሰዓት የራያ አላማጣ ነዋሪዎች ወደ ቆቦ ለመሰደድ መገደዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀውልኛል። እቃቸውን ጭነው ወደ ቆቦ የገቡ ሰዎች በርካታ ናቸው ብለዋል። የህወሓት ታጣቂዎች አላማጣ ዙሪያ መጠጋታቸውን ተከትሎ እንዲሁም  ሚሊሻው እና ከተማ አስተዳደሩ ከአቅም በላይ ሆኖብናል በማለታቸው ምክንያት ታጣቂ ቡድኑ ማታ ሊገባ ይችላል በሚል  በርካታ የአላማጣ ነዋሪዎች ወደ ቆቦ ሸሽተዋል ብለዋል(አዩዘሀበሻ)።
========================
ጥቆማ👇
👉የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaoficial
http://t.me/ayuzehabeshaoficial

Ayu ze Habesha - Official

15 Apr, 12:48


ከትናንት በስተያ ምሽት ኢራን ወደ እስራኤል ካስወነጨፈቻቸው የባሊስቲክ ሚሳኤልዎች ውስጥ አንዱ በጆርዳን አዋሳኝ በሚገኘው በሙት ባህር (dead sea) ዳርቻ ወድቆ ተገኝቷል።
አዩዘሀበሻ
========================
ጥቆማ👇
👉የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇
http://t.me/ayuzehabeshaoficial
http://t.me/ayuzehabeshaoficial

Ayu ze Habesha - Official

14 Apr, 06:54


በተፈራው መሰረት  ኢራን  በእስራኤል ላይ  ከፍተኛ  የሆነ  የሚሳኤልና የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ጥቃት ከፍታለች ።  ቀይ ባህርና ሜድትራኒያን   ቀጠና ውጥረት ውስጥ ገብቷል  ።  በቀጥታ  ስርጭቶች እየታየ እንዳለው  እስራኤል እንዲሁም  አጋሮቿ እንግሊዝና አሜሪካ   የኢራንን  ጥቃት  ሙሉ በሙሉ  ኢላማቸውን ከመምታት እንዲከሽፉ መከላከል  እየተቻላቸው  አይደለም ። 

ጆ ባይደን ኢራን ላይ ያለንን  ጦር መሳሪያ በሙሉ እንጠቀማለን ሲሉ የዛቱ ሲሆን    ይህንንም  ተከትሎ  ዓለም  ለኒውክሌር  ጦርነት  ከምንግዜውም በላይ ቀርባለች  ሲሉ   ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየዘገቡ ይገኛሉ።

Ayu ze Habesha - Official

08 Apr, 17:52


ዛሬ በሳዑዲ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል!

ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

2,632

subscribers

2,356

photos

201

videos