ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤 @filimon6 Channel on Telegram

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

@filimon6


፡ እኔ እምኖረው በራሴ ህግ ነው…ከፍታን አልፈልግም ዝቅታንም አልፈራም 🤎
✍🏽 ደብዳቤዎች 🖤
✍🏽 ግጥሞች 🖤
✍🏽 ወጐች 🖤
✍🏽 መጣጥፎች 🖤
✍🏽 አባባሎች ይቀርባሉ 🤎
otherchannle 👉🏽 🖤 @filimonhappy 🖤
Cross 👉🏽 🥀 @itsmehappy 🥀

እግዛብሔር እምትወዱትን ህይወት ይስጣቹ :(

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤 (Amharic)

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤 በተወሰነው መልኩ የእርስዎ መረጃ ለሁሉም ለናንተ ድምፅ። ይህ ቡድንን የሚሰጥ መረጃ ነው፣ ዛሬ ትልቅ ምግብ ቴሌግራም አልገባም። ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤 ከኦሮሞ ሃይሌ ቴሌግራም መርጠዋል። እናም አትበል፣ የሚቀመጠውን ቃሊቲ የሚያግኙ ሓዲስፎን አለን። ስለዚህ ከአንደኛውን መልእክት ለመጠቀም ከቡድን።

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

13 Apr, 05:09


:)
አንዳንዴ …የሆነ ስሜት አለ ልንነገርውም ሆነ ልንፅፈው የማንችለው ስሜት… እግዛብሔር የለ ቀን ሁሉም መልካም ይሆናል።

መቼ ትመጫለሽ?…👩🏽

🖤 @filimon6 🖤
🌘 @itsmehappy 🌘

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

11 Apr, 18:02


ለሰው ሄደህ ችግርህን አትንገረው…እሱም ችግር አለበት …ለፈጣሪ ግን ደጋግመህ ንገረው መፍትሄም ያላው እሱ ጋር ነው…🖤

🎬🍿🥤 Follow Me On 🎬🍿🥤👇🏾

Tiktok👇🏾
tiktok.com/@itsmefilimon
Facebook👇🏾
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090684465271
Telegram👇🏾
https://t.me/+aHnwEiTMkp9iMjhk
Instagram👇🏾
https://instagram.com/filimonhappy?igshid=ZDdkNTZiNTM=

          

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

07 Apr, 17:08


፡  ጊዜ ይጠይቅሀል…ለሱ መልስ አዘጋጅ !

   እመነኝ አሁን ያለው ነገር በሂደት ያልፋል…የሆነ አያልፍም ብለህ እርግጠኛ የሆንክበትም ሳይቀር ያልፋል…አይቀየሩም ያልካቸው ሰዎች ተቀይረው ታገኛቸዋለህ ተቀይረውም ብቻ ሳይሆን ከፍተው ታገኛቸዋለህ…እመነኝ! አሁን ያለህ ብርታት እና ጥንካሬ ያኔ አይኖርም ከተቀመትክበት እንኳን መነሳት እስኪያቅትህ ትደክማለህ…ያኔም ህይወት ጥያቄዎን ታቀርብልሀለች…ለምን እንዲ አደረክ? እና ለምን ደሞ እንዲህ አላዳረክም? ብላ…ያኔ ማሰብ ትጀምራለህ…

   ስለዚህም…አሁን ነገ ይሆናልና ስለ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ስለ ነገም መልስ አዘጋጅ…መልካም ህይወት 🖤

           ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ

                   🖤 @filimon6 🖤
               🥀 @itsmehappy 🥀

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

31 Mar, 10:18


፡ ለፍቅር የተፀፈ ደብዳቤ ቁጥር 1321 🖤

፡ ሰለምወድሽ ነበር እምትወጂኝ ወይስ ስለምትወጂኝ ነበር እምትወጂኝ…አብረሺኝስ እያለሽ አብረሺኝ ነበርሽ?…ወይስ እኔ ጋር ሆነሽ ሌላ ቦታ ነበርሽ?…

🖤 @itsmehappy 🖤

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

20 Mar, 15:10


፡   ከተዘነጋው ማስታወሻ 📓

   አንዳንዴ በጣም ትናፍቂኝ የለ…አንዳንዴ ሳላስበው ስለ አንቺ ማሰብ እጀምር የለ…አንዳንዴ ያሳለፍነው ሁሉ ትዝ ይለኝ የለ?…አሁንም ቢሆን እየሞከርኩ ነው…

              🥀  @filimon6 🥀

           ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

19 Mar, 09:01


🎬ፊልሞች ላይ ካየናቸው ብዙ ምርጥ የፍቅር ጥንዶች መካከል እነዚህ አራቱ ይጠቀሳሉ…ለእኔ five feet apart ላይ ያሉት ይበልጥ ይመቹኛል…?🍿

🎬 Titanic 🛳
🎬 After 👩‍❤️‍👨
🎬 Twilight 🐺
🎬 Five Feet Apart 👩‍❤️‍💋‍👨

🎬🍿🥤 Follow Me On 🎬🍿🥤👇🏾

Tiktok👇🏾
tiktok.com/@itsmefilimon
Facebook👇🏾
https://www.facebook.com/profile.php?id=100090684465271
Telegram👇🏾
https://t.me/+aHnwEiTMkp9iMjhk
Instagram👇🏾
https://instagram.com/filimonhappy?igshid=ZDdkNTZiNTM=

           🍿 @filimonmovies 🍿

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

16 Mar, 14:48


፡ አንዳንዴ በጣም ትናፍቂኝ የለ…አንዳንዴ ሳላስበው ስለ አንቺ ማሰብ እጀምር የለ…አንዳንዴ ያሳለፍነው ሁሉ ትዝ ይለኝ የለ?…አለልሽ አደል አንዳንዴ የሆነውን ሁሉ ሳስብ እሚያደርገኝን ያሳጣኝ የለ…
 
  እንቺስ ግን…አንዳንዴ ትዝ እልሽ ይሆን?…አንዳንዴስ ስላለፍነው እና ስላሳለፍነው ታስታውሺ ይሆን…አንቺስ ግን እናፍቅሽ ይሆን?…በርግጥ መልሱን ልቤ ያ ውቀዋለው…አልናፍቅሽም!🥺

          እየሄድኩ ነው…ወዴት ግን እኔጃ…

✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

16 Mar, 11:26


፡  የአንድ አለም ሁለት ሰዎች 🖤

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 18:13


፡ በተራመጅ ዓለም ምንም ቋሚ ነገር የለም…ሁሉም እየመጣ ይሄዳል…እማይሄድ እሚመስለውም ይሄድና ይረሳል…እኔም ለዚች ምድር እንግዳ መሆኔን አልዘነጋም…ነገር ግን ስኖር ደስተኛ ሆኜ ነው መኖር እምፈልገል…የራሴ ህገ መንግስት ያለኝ እና በራሴ እምነት ብቻ የምኖርም ሰው ነኝ…በአንድ ነገርም አምናለው ጥሩ ሁን ጥሩ እንዲገጥምህ በሚለው…🖤

        ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🎬

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 17:42


🍃🍃

እየጠጣሁ እዘፍናለው🌧...

ሁሉም ሱቆች ተዘግተዎል… ዛፎችም በርዶቸዎል መሰለኝ አይነፍሱም ደርቀዎል … አርቄ ቤትም ደረስኩ…ብዙ ሰው የለም…

👨🏼 @filimonhappy 👨🏼
🕰 @itsmefilimon 🕰

🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 17:42


ዛሬ ቆየት ካሉ ደብዳቤዎች ጥቂቶቹን ልጋብዛቹ 🖤

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 17:42


:)
ለፍቅር የተፀፈ ደብዳቤ 👫

አሁንም ቢሆን እኔ አለሁ…ያለሁት ግን አንቺ እንደምታውቂኝ እንደ ድሮ ሆኜ አደለም…አሁን ላይ ድክመቴ በዝቶዎል…አፌና ምግባሬ ለየቅል ሆኖዎል…

🌷 @filimonhappy 🥀
🤴🏾 @itsmefilimon 🤴🏾

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 17:42


:)
በህይወት መንገድ ላይ…

መተኛት እፈልጋለው…አይኔን ጨፍኜ በውስጤ ምንም ሳላስብ እረጅም ሰዕት መተኛት እፈልጋለው ግን አንዳንዴ አልችልም…ያለፈው እና እሚመጣው ነገር ያሳስበኛል…

🌷 @filimonhappy 🌻
💬 @itsmefilimon 💬

👵🏾 እማ እወድሻለው 👵🏾

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 17:42


:)
🖤 አንድ ቀን 🖤

እነርሱም አንገታቸውን ደፍተው…"እነርሱ አይኖሩም በቃ እነሱ የነበሩ ናቸው…አሁን የፍርድ ሰዕት ደርሷዎል መሄድ አለብን ብለው ከፍተውት የነበረውን ሰማይ በቃል ብቻ ዘጉት…ዘጉት

🍁 @filimonhappy 🌹
🌷 @itsmefilimon 💐

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 17:42


:)
እብዶች ነበርን…

"ዝም ብሎ ከሄደ ሰው ይልቅ እመጣለው ብሎ የሄደን ሰው መጠበቅ ይከብዳል" እኔ እና አንቺ እብዶች ነበርን አማንኤል ያልሄድን መድሀኒት እና ኪኒን የማንጠቀም…

🤵 @filimonhappy 👰
👰 @itsmefilimon 🤵

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

15 Mar, 17:42


:)
የፊሊሞን ደብዳቤ📖 (ቁጥር 117)…

ዛሬ እኮ እንደትላንት አደለም…ዛሬ አዲስ ቀነ ነው…ብዙ ነገሮችአልፈዎል…አሁች ላይ ብዙ አዲስ ነገሮች አሉ …እኔም እንደድሮው አደለሁም…

🕯 @filimonhappy 🕯
💐 @itsmefilimon 🌻

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

07 Mar, 18:04


፡      ይቅር በለኝ 🙏🏽

    ከረጅም ጊዜ ቡኋላ ነው ዛሬ ደጀ ሰላሙን ስረግጥ…እውነት ነው በዓለም ተሸንፌ እና አለምን መስዬ ከራኩኝ ቆይቻለው…በርግጥ ያ ህይወት ሰላም የለውም…እሩጫውም ያደክማል…የሀጥያት መረቡም ሰፊ ነው…

   አቀርቅሬ ወደ ውስጥ ገባሁ…አማትቤም ወደ ውስጥ ገባሁ…ብዙ ነገሮቹ አልተቀየሩም…አሁንም አለምን ሽሽት የመጡ ብዙዎች ናቸው…አሁንም ስለ ነብሳቸው ስጋቸውን የሚያደክሙሙ አላፎች ናቸው…አሁንም ቢሆን ለመማር ያጐነበሱ ብዙዎች አሉ…አልፊያቸው አንድ ጥላ ስራ ቁጭ አልኩ…መፀለይም ጀመርኩ…

   አቤቱ ይቅር በለኝ…አንተ ፊት የሚያቀርብ ኢምንት እንኳንስ ስንቅ ባልሰፍርም…ስለ ድንግል ማርያም  ብለህ ይቅር በለኝ…ስለ ቅዱስ ስምህ ብለህ የንስሀውን መንገድ ምራኝ…ይገበኛል እንደ እኔ ይቅር ያልከው እና የታገስከው የለም…ከቃል በላይ በደሎችን በድያለው…እምነቴን ረስቼ መዋል በማይገባኝ ውያለው…

   ያቀረቀርኩትን አንገቴን ቀና አድርጌ የመውጫውን መንገድ መሄድ ጀመርኩ…አደራህን መመለሻዬን አታርቅብኝ…የልቤን መሻት ሙላልኝ…

         ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ
🖤 @filimon6 🖤

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

07 Mar, 13:57


፡   የከፋው ሰው ደብዳቤ ከሚለው…🖤
 
   ያለፈውን ማሰብ ስጀምር አንዳንዴ ይጨንቀኛል…እምደርገውንም ያሳጣኛል…አንዳንዴ ጩህ…አንዳንዴ ደሞ የእየበረረ እሚሄድ መኪና ውስጥ ግባ ይለኛል…እንዳላስብም እማላደርገው ነገር የለም…
🖤 @filimon6 🖤

ፊሊሞን የማርያም ልጅ 🖤

27 Feb, 06:15


፡  አይሽ! …ቀን ይለዋወጣል…የነበረውም ሁሉ እንዳለነበር ይሆናል…ዘላለምም እሚባል ነገር የለም…በምንም ነገርም እርግጠኞች መሆን አንችልም…የሆነው ቢሆንም ግን እኔ እና ቤቴ አሁንም እየጠበቅንሽ ነው…

      ✍🏽  ፊሊሞን የ የማርያም ልጅ 🖤