የግጥም ህይወት በስራህን እና ቀላል እውቀትን የሚቀረቡ ፥ እና ስነ ፅሁፍ አፍቃሪያንን በተለያዩ ግጥም እና ስነ ፅሁፍን መሰረት በአብታም አዘገጃጀቱ ላይ ነው። ኑ ለግጥም ቅንብለትን መልስ በሌንቶን መኖር ይችላሉ። ጆይን ከሆነ ለወዳጅ ፣ ለጓደኛ ፣ ለዘመድ ሼር ለማድረግ እና ለቀናት የሚከሳበትን ቻናሉ ማስታወቅ ይችላሉ። አናት @Mersha_9119
13 Nov, 11:00
08 Nov, 18:33
03 Nov, 18:50
03 Nov, 15:00
02 Nov, 12:34
29 Sep, 15:35
ገል እና አበባ
"""""""""
[ በረከት_ዘውዱ ]
ለዘመናት ያህል ሳይኖረው ሰባራ
ብዙ ሰው ያበላ ብዙ ወጥ የሰራ
የገል ድስት ነበረ
በቆይታ ብዛት ድንገት ተሰበረ
ከስብራት ወዲያ
ማገልገል ቢሳነው ልክ እንደ በፊቱ
ከውጪ ተጣለ ደጃፍ ሆነ ቤቱ
ከዳጃፍ እንዳለ
ይተክዝ ነበረ አልጠቅምም እያለ
አላወቀምና
ከላዩ የሚኖር አበባ እንዳለ
የሰባራውን ገል ሀዘን ያስተዋለ
የሚያምረው አበባ እንዲህ ተናገረ
" እባክህ ሸክላ ሆይ
አበቃልኝ ብለህ አትዘን ለአፍታ
መኖሪያ ሳይኖረኝ የማርፍበት ቦታ
ካንተ ተጠግቼ
መኖር ጀምሬያለሁ ህይወትን ድጋሚ
አይደለሁም አትበል ለኔ'ስ ነህ ጠቃሚ "
እያለ ነገረው
ይህን እንደሰማ ገል እንባ አበሰ
ደስታው ተመለሰ
ከመሰበር ወዲያ መጥቀም በመቻሉ
የአንድ ውብ አበባ መኖሪያ መሆኑ
ዳግም ተስፋ ሰጠው ከሀዘኑ ተፅናና
በሰባራው በኩል
ድጋሚ ታየችው ዓለም ሙሉ ሆና
እንዲህ ነው አንዳንዴ
አበቃልን ብለን
ተሰበ'ርን ብለን ተስፋ ባጣን ጊዜ
ዙሪያችን ሲከበብ በሀዘን ትካዜ
የህይወትን ትርጉም ፈልገን ስናጣ
ተሰብረህም ቢሆን
አኑረኸኛል ሚል ምስክር ሲመጣ
ይገርማል ይደንቃል
ለካ'ስ
ለመኖር ያነሰ ለማኖር ይበቃል
@amharic_poet11 Sep, 05:27
11 Sep, 04:26
03 Sep, 17:01
03 Sep, 04:59
02 Sep, 07:33
26 Aug, 15:59
አንድ ሰውዬ በጣም ትልቅ አዋቂ ከሆኑ ሰው ምክር ፍለጋ ይሄዳል
እንዳገኛቸውም "ምክር ፈልጌ ነበረ አላቸው "
አዋቂውም ምክር መስጠት የዘወትር ስራቸው ነበርና
" ስለ ምን ? " ሲሉ ጠየቁት
ሰውየው በእሺታቸው እየተደሰተ
" በህይወቴ ምንም ነገር መያዝ አልቻልኩም ምንም የኔ የምለው ነገር የለም " አላቸው
አዋቂውም " ከምክሬ በፊት አንድ ማድረግ ያለብህ ነገር አለ ምታደርገውም ነገር ሁለት ህጎች አሉት ብለው " ነገሩት
ሰውየም የሚያዙትን በደስታ እንደሚፈፅም ነገራቸው
አዎቂውም " ትዕዛዙ ይኸው ነው ከዚህ ከሚታየው የበቆሎ ማሳ ውስጥ የፋፋውን ወይም ትልቁን በቆሎ ታመጣለህ ፣
ማሳው ሶስት ክፍሎች አሉት ከመጀመሪያው ክፍል አልፈህ ከሄድክ መመለስ አትችልም ሁለተኛው ደግሞ ባዶ እጅህን ከማሳው መውጣት አትችልም " አሉት
ሰውዬውም በመጀመሪያው ማሳ ትልልቅ በቆሎውችን አገኘ ነገር ግን ሌላኛው ማሳ ውስጥ ከዚህ የተሻለ ሊኖር ይችላል ብሎ በማሰብ የመጀመሪያውን የማሳ ቦታ አልፎ ሄደ ፣ በቀጣዩም ክፍል መካከለኛ በቆሎውችን አገኘ አሁንም ወደ ፊት የተሻለ ሊኖር ይችላል ብሎ በማሰብ ሁለተኛውንም ክፍል አልፎ ሄደ ፣ በሶስተኛው ክፍል ግን እንጭጭ ወይም ትንንሽ በቆሎዎችን ብቻ አገኘ
ወደ ኋላ እንዳይመለስ አንደኛው ህግ ወደ ኋላ እንዲመለስ አይፈቅድም ባዶ እጁን ከማሳው እንዳይወጣ ሁለተኛው ህግ ባዶ እጅ ከማሳው መውጣትን አይፈቅድም ስለዚህ እንጭጩን በቆሎ ይዞ ከማሳው ወጣ
አዋቂውም " ከመጀመሪያው ማሳ ትልልቅ በቆሎዎች ነበሩ ፣ ከሁለተኛውም ማሳ መሀከለኛ በቆሎዎች ነበሩ ለምን ከነሱ አላመጣህም ? " ብለው ጠየቁት
ሰውየውም " ከነሱ የበለጠ የተሻለ አገኝ ይሆናል ብዬ ነው ሁለቱንም ማሳዎች አልፌ የሄድኩት በህጉ መሠረት ባዶ እጅ መመለስ ስለማይቻል ነው ይህን እንጭጭ በቆሎ ይዤ የመጣሁት " አላቸው
22 Aug, 04:54
10 Aug, 17:37
05 Aug, 17:41