የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ @stgeorge_gibi_gubae Channel on Telegram

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

@stgeorge_gibi_gubae


ከመ/ገ/ጽ/ቅ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤት ጋር በመሆን

☞ ዘወትር ረቡዕ ከ10:00 - 11:30
☞ በመ/ገ/ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ

መንፈሳዊ ትምህርት የምንማማር ሲሆን ይህንን የተማሪዎች ጊቢ ጉባኤ አገልግሎት ለማጠናከር የተከፈተ የቴሌግራም ማኅበር ነው።

@YeGibi_Gubae
✞ ኢንኅድግ ማኅበረነ ✞
አንድነታችንን አንተው

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ (Amharic)

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ የናታንያ ታላላ ቤተ ክርስቲያን እና አስብዓኝ ህጻን የግብፅ ጉባኤ ናት። ዘወትር ረቡዕ ከ10:00 - 11:30 በላይ በመሆን ከእምባብሮች ጋር ማኅበረነት ያለው ህይወትና እናቶችን መንፈሳዊ ትምህርት የመጀመሪያ ስራ መቼም የተማርከዉን አገልግሎት ለማጠናከር በዚህ ጉባኤ ነፃ ቴሌግራም ማኅበርን ማጠናከር በመሸጥ እናቴ ለኢንኅድግ መኅበሩን ማስተዳደርና ማድረግ ይችላሉ። የእጅግ ገጽ ታሪካዊ እና መረጃውን ለንብረት በገዛ አካሂዳ ያገለገላል። ከልጆች ለተለይም እናንተ ምስጋና ሞግዳ የግብፅ ጉባኤን ለመጀመሪያ ስራ ቢጠቅም ሠፈር እና በቀን ሚሊሻውያንን ለናትናት። ለጠቅላላነቱ በሰንበታቴስ ከተማሪዎቹን በመተንከባቢ ለመግዛትና ለመቅጠር ከርስዎን እንደሚያከናውነው እባኮቅናችሁ።

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 20:11


የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ pinned «ሰላም እንዴት አመሻችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደሚታወቀው የጉባዔያችን መርሐግብር ቀን ከረቡዕ ወደ አርብ መቀየሩ ይታወሳል። ስለሆነም ቀጣይ ጉባዔያችን የሚሆነው ቀጣይ ሳምንት አርብ 13/03/2017 ሲሆን በነገው አርብ ምንም አይነት የጉባኤ መርሐግብር አይኖርም። ነገር ግን መዝሙር ጥናት የምታጠኑ አገልጋዮች እና አዲስ ማገልገል የምትፈልጉ ተማሪዎች በነገው አርብ እለት ጥናት የሚኖር መሆኑን እናሳውቃለን።…»

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 19:29


ሰላም እንዴት አመሻችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደሚታወቀው የጉባዔያችን መርሐግብር ቀን ከረቡዕ ወደ አርብ መቀየሩ ይታወሳል። ስለሆነም ቀጣይ ጉባዔያችን የሚሆነው ቀጣይ ሳምንት አርብ 13/03/2017 ሲሆን በነገው አርብ ምንም አይነት የጉባኤ መርሐግብር አይኖርም።
ነገር ግን መዝሙር ጥናት የምታጠኑ አገልጋዮች እና አዲስ ማገልገል የምትፈልጉ ተማሪዎች በነገው አርብ እለት ጥናት የሚኖር መሆኑን እናሳውቃለን።
መልካም ምሽት።

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 20:45


“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። .. ቀይና_ነጭ አበባ የሚመስል ልጅሽን ታቅፈሽ ከደስተኛው ገብርኤልና እንዳንቺ ርኅሩኅ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ።” — “ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ፤ ተመየጢ ወንርዓይ ብኪ ሰላመ። ... እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ጸዓዳ ወቀይሕ፥ .. ምስለ ገብርኤል ፍሱሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።” (መኃ. 7፥1፤ ማኅሌተ ጽጌ)

እንደምታውቁት ዛሬ በጽጌ ወራት የሚቀርበው ምስጋና (ማኅሌተ ጽጌ) መጠናቀቂያው ነው። ማኅሌቷን ስትቆሙ ያለውን የነፍስ እርካታ እንዲኽ ነው ብዬ በቃል ልገልጽላችኹ አልችልም፤ በቃ ሔዳችኹ እዩት። እንደ ወንድምነቴ ልምከራችኹ። እስከዛሬ ማኅሌቷን የቆማችኹ ዛሬን እንዳትቀሩ! እስከዛሬም ያልቆማችኹ የዛሬው እንዳያመልጣችኹ!

ሌሊት ከሚባለው ማኅሌተ ጽጌ እና ከሰቆቃወ ድንግል አንድ አንድ ክፍል ላስነብባችኹ።

“ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፥ ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፥ ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ_ጽጌ_ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፥ ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡” — “ንጹሕ የተዓምርሽ ቀስት (5 ቀስተ ደመና የማርያም መቀነት) እንደ ብር ገንቦ ጌጥ፥ በአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ዐይነት በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፥ የሰማይና የምድር ንግሥት ኾይ! የተወደደ የጽጌ ምስጋና ተፈጽሟልና፥ የቀጣዩን ዓመት ምስጋና በሰላም አቅርቢልን።” — (ማኅሌተ ጽጌ)

የእመቤታችንን ስደት ሳስብ የእመቤታችን እምነት እጅግ ይደንቀኛል። ልጇ አምላክ እንደኾነ እያወቀች እየተራበች የእህልን ፈጣሪ፥ እየተጠማች ውኃን የፈጠረውን ‛እውን አምላክ ነው?’ ብላ አለማሰቧ ያስደንቀኛል። ልጇን ይዛ ሄሮድስ ልጇን እንዳይገድልባት ወደግብጽ ስትሸሽ ‛አምላክ ባይኾን ነው እንጂ እንዴት ሄሮድስ ያሳድደዋል?’ ብላ አምላክነቱን አለመጠራጠሯ አያስደንቅም? እርሷ ግን በሐዘን ልቧ እየደማም አምላክነቱን አንዳች አልተጠራጠረችም። አኹን ግን የስደቷ ወራት አብቅቶ ወደሀገሯ ልትመለስ ነውና ደራሲው ‛ናሁ ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር’ አለ፤ አንድም ወርኃ ጽጌ አልፏልና።

ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ባሳተሙት 'መጽሐፈ ቅኔ' ላይ የተመዘገበው የመልአከ ፀሐይ ቴዎድሮስ ጥንታዊ ቅኔም ይኽን ያስገነዝበናል፤ “ማርያም ዘኢትፈርህ ሐሜተ፥ ፍርፋራተ ኅብስት ሰአለት በፍና እንዘ ትፀውር ኅብስተ።” — “ሐሜትን የማትፈራው ማርያም [የሕይወት] እንጀራን_ተሸክማ በመንገድ ላይ የእንጀራን ፍርፋሪ ለመነች።

ወተመይጠት ማርያም ሀገረ እስራኤል አቡሃ፥ ነቢራ በግብጽ አርብዓ ወክልዔተ አውራኀ፥ እንዘ ይሰግዳ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፥ እምይእዜሰ ነገፍኩ ላሓ፥ ለእምየ በእትወታ ረኪብየ ፍስሐ።” — “ማርያም በግብጽ 42 ወር (3 ዓመት ከ6 ወር) ቆይታ፥ የጢሮስ ድንግል በምስጋና እየሰገዱለት፥ ወደአባቷ ሀገር ወደእስራኤል ተመለሰች፥ ከዛሬ ጀምሮ በእናቴ መመለስ ደስታን አግኝቼ፥ ለቅሶን_ተውኹኝ” — (ሰቆቃወ ድንግል)

ሰቆቃወ ድንግል'ን ('የድንግል ለቅሶ'ን) ካነበባችኹት (እኔም ሙሉውን አላነበብኩትም ግን እንዲኹ አይቼዋለኹ) ደራሲው አንባቢው የእመቤታችንን ሐዘን አብሯት እንዲካፈል አድርጎ የጻፈው ነው፤ እርሱም በእንባ ኾኖ እንደጻፈው እንዲኽ ሲል ጽፏል፤ “.. ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፥ ወይሌ ወላሕ ለይበል ዘአንብቦ፥ ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኵለሄ ረከቦ፥ ርእዮ ለይብኪ ዐይነ ልብ ዘቦ። — .. ያነበበው ኹሉ ወዮ ይል ዘንድ የድንግል ማርያምን ለቅሶ በእንባ ቀለም ነጠብጣብ እጽፋለኹ፥ ዐይነ ልቡና ያለው ሰው እንደ እሷ፥ ኃዘንና መሰደድ ቢደርስበት አስተውሎ (እሷን እያሰበ) ያልቅስ።” እንዲኽ ብሎ በጻፈበት ወደሀገሯ ስትመለስ ደግሞ ‛በእናቴ መመለስ ደስታን አግኝቼ ለቅሶን ተውኹኝ’ አለ። ወደኛ እናምጣው። ግን መች ይኾን ወደአሥራት ሀገሯ ወደኢትዮጵያ ተመልሳ እንደደራሲው የኃዘን እንባችን ቆሞ የደስታ እንባን የምናነባው? መች ይኾን እንድትሰደድ ካደረግንበት ልባችን ተመልሳ ገብታ ሕይወታችን በእርሷና በልጇ በረከት የሚሞላው?

እኛም ከሊቃውንቱ ጋር አብረን እንዲኽ እንበላት፤ “ከእሴይ ወገን የተገኘሽ የመድኃኒት አበባ ማርያም_ሆይ፥ ከጻድቃን አንደበት የተገኘ ያለኝ ምስጋና ይበቃኛልና፥ ከኃጢአተኛ አንደበት ምንም አያስፈልገኝም አትበይ።”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር! ይቆየን!



https://t.me/SSC_kidme_gibi_gubae



https://t.me/StGeorge_Gibi_Gubae

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 20:12


Channel photo updated

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

11 Nov, 05:10


የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ pinned «»

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

06 Nov, 15:21


አምንስቲቲ ሙኪርዬ አንቲ ፋሲልያሱ

ረቡዕ ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም
 

የካቴድራል፣ ቅ/ማርያምና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ጊቢ ጉባኤ የ2017ዓ.ም. 

        Join and share👇
   @StGeorge_Gibi_Gubae