በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት @teklesawirossundayschool Channel on Telegram

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

@teklesawirossundayschool


ተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት
በ1957 ተመሰረተ።
ይህ በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው::የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት ስርዓት ዶግማ ቀኖና ትውፊት በጠበቀ መልኩ መንፈሳዊ ማዕዶችን ሳቢና ለየት ባለ መልኩ እናቀርብላችኋለን ።https://youtube.com/channel/UCMgN4_

ተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት (Amharic)

ተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት የ1957 ዓ.ም በእያወቀ ምንጩን እናመሰግናለን። ይህ በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው እና መላኩን ይፈጥራል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ስለ እምነትእና ስለ ስልጠና ውስጥም ተወካዮችን በቀጥታ መንፈሳዊ ማዕዶች እና ሳቢን ለማያወጣና ለማቀርብ መልኩ እንዲሆን እናቀርብላችኋለን። የቴሌግራም ቻናልን ለመዋጣት እና በተጨባጮለው ገጽ መረጃ እንዲያቀርብ አጋሜጦ እንዲሆን መልኩን ለመፅሀፍ በማሰብ እናቀርብላችኋለን።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

19 Jan, 18:56


. እግዚአብሔርን አመስግኑ

የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በታላላቆቹ አድባራት ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን በደማቁ የተከበረ ሲሆን ታቦታተ ህጉ ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ገብተዋል። የአድባራቱ ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ስብሐት ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ አማረ በበዓሉ ላይ ላገለገሉ ካሕናት ፣ የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ፣ በብዙ ለደከሙ የአጥቢያው ወጣቶች እና ለጸጥታ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው በዓሉ በጸሎት ተፈጽሟል።

በነገው ዕለት የቃና ዘገሊላ በዓል ታቦታተ ህጉ ከየመንበረ ክብራቸው ተነስተው በደማቁ የሚከበር ሲሆን ሁላችንም በመቅደሱ እንድንገኝ ከወዲሁ መንፈሳዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

ከበረከተ ጥምቀቱ ይክፈለን። ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

18 Jan, 18:38


ዜና ዕረፍት

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የሱራፌል ጸጋዬ አባት አርፈዋል።

ቀብር ነገ 11/05/2017 ዓ,ም በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን 4 : 00 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።
በመሆኑም የቻልን ስልክ እየደወልን ወንድማችንን እንድናጽናና ይሁን።

አድራሻ :- 090246 5721

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

18 Jan, 13:16


በፍስሐ ወበሰላም ፣ ወረደ ወልድ ውስተ ምጥማቃት

የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን ታቦታተ ህግ በክቡር አባታችን መልአከ ስብሐት ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ አማረ ፣ በሊቃውንት ፣ ካሕናት ፣ ዲያቆናት ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች ፣ በአጥቢያው ወጣቶች እና በማኅበረ ምዕመናን ታጅበው ወደ ባህረ ጥምቀቱ ጉዞ ጀምረዋል።

መልካም የከተራ በዓል

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

18 Jan, 09:53


የደብራችን የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ታቦታተ ሕጉ ወደ ጥምቀተ ባሕር የሚሄዱበት የጉዞ መስመር

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

17 Jan, 15:47


በከተራ ዕለት የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብሮ ወንዝ መውረድ ስለምንድ ነው ?

የጥምቀት አከባበር በሀገራችን ኢትዮጵያ ታቦት ተሸክሞ ወንዝ ወርዶ የክርስቶስን በዓለ ጥምቀት ማክበር የተጀመረው በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሲሆን ይበልጥ ተጠናክሮ በሜዳና በውኃ ዳር ማክበር የተጀመረው በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ( ከ 530 - 544 ዓ.ም ) እንደ ሆነ ይነገራል

ጥር 11 ቀን ጠዋት ወደ ወንዝ ወርደው ማታ ወደ መንበረ ክብራቸው እንዲመለሱ ይደረግ ነበር ከዚህም በኋላ በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውናና በስብከተ ወንጌል ተግተው ያገለግሉ የነበሩ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገር እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል ።

ንጉሥ ላልይበላ ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለየብቻቸው በተናጠል ሲፈጽሙት የነበረውን ክብረ በዓል አስቀርቶ በምትኩ በአንድ አካባቢ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት ተሰባስበው በአንድ ጥምቀተ ባሕር እንዲያከብሩ ትዕዛዝ አስተላልፏል ይህም ተግባራዊ በመኾኑ የበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት ቅንጅትና ድምቀት ባለው ሁኔታ እንዲከበር አድርገዋል

በዚህም ምክንያት ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሁሉ ታቦተ ሕጉ ወደ ጥምቀተ ባሕሩ በሚወርድበት ጊዜና ከጥምቀተ ባሕር ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ ፣ አጅቦ እንዲመለስ አዋጅ ነግረው በአዋጁ መሠረትም ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ታቦተ ሕጉን በማጀብ በሆታና በዕልልታ እንዲያከብር ተደርጓል ።

በመንፈሳዊነታቸውና በደራሲነታቸው የሚታወቁ መጻሐፍትን በመጻፍ ሥርዓትን በመደንገግ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ውለታ ያበረከቱ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ ሀገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በአዋጅ ወሰኑ ።

ታቦታተ ሕጉ በወጡበት ቦታ የማይመለሱበት ምክንያት ብዙ ምስጢር አለው የመጀመሪያው « ምድር በኪደተ እግሩ ተቀደሰች » እንዲል ያልተባረከ መሬት እንዲባረክ ነው ።
ሁለተኛው ደግሞ ያላየው እያየ ያልሰማው እየሰማ ሥርዓቱን አይቶ እንዲያምን ሃይማኖት እንዲሰፋ ነው ።
ሦስተኛ ነቢያት በመጡበት እንዳይመለሱ ሥርዓት ነበረና በዚያ ልማድ ነው አራተኛ ሰብአ ሰገል ጌታን ካገኙ በኋላ በመጡበት ቦታ አልተመለሱምና የዚያ ምሳሌ ነው።

ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና ክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ  ወስነው ነበርና አከባበሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ አድማሱም ብሔራዊነትን እየያዘ መጥቷል ።

ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በዕልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ። ሊቃውንቱም እንዲሁ ለበዓሉ የሚስማማውን ቃለ እግዚአብሔር እያደረሱ ያድሩ ጀመር ። #እንኳን_አደረሰን

በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኅኒት መድኅኔዓለም
አብያተ ክርስቲያን የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

17 Jan, 05:29


#ጾመ_ገሃድ

ጾመ ገሃድ /ጾመ ድራረ ጥምቀት/

ጾመ ገሃድ [ ጋድ ] ፦ የቃሉ ትርጕም "ገሃድ" ሲል መገለጥ ፥ " ጋድ " ሲል ለውጥ ማለት ነው። ይኸውም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ነው። አንድም ጋድ ተብሎም ይጠራል ፤ ጥምቀት ረቡዕ ፣ ዓርብ ቢውል በዚያ ለውጥ ማግሰኞና ሐሙስ ይጾማልና።

ጋድ [ ጾመ ድራረ ጥምቀት ] ፦ ይህ ጾም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው። የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነ የጥምቀት ድራር [ ዋዜማ ] ጾም ነው።

የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ዕለት በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማግሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል። በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ይከናወንልናል።

የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ ፣ ማግሰኞ ፣ ሐሙስ ከሆነ ጾም ነው ፤ በአጋጣሚ ደግሞ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል። ሆኖም ጥምቀት በየትኛውም ዕለት ቢውል በየዓመቱ ሁልጊዜ የጥምቀትን ዋዜማ እስከ ዕርበተ ፀሐይ እንጾም ዘንድ አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ይሆን ዘንድ ሥርዓትን ሠርተውልናል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

16 Jan, 14:51


ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ከ1 ሺህ 4መቶ በላይ ለሚሆኑ ዲያቆናትና ቀሳውስት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።

በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከ1 ሺህ 4መቶ በላይ ለሚሆኑ ዲያቆናትና ቀሳውስት ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል ከነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 3 መቶ የአብነት ደቀ መዛሙርት የዲቁና፣1 መቶ 60 ቀሳውስት የቅስና እንዲሁም 6 መነኮሳት ደግሞ የቁምስና ሥልጣነ ክህነት ተቀብለዋል።

ብፁዕነታቸው ዛሬ ሥልጣነ ክህነትን ላገኙት ካህናት ባስተላለፉት አባታዊ መልእክታቸው እንዳሉት በጾም፣በጸሎት፣በስግደት እና በምጽዋት ለሚመሯቸው ምእመናን ምሳሌና አርአያ መሆን አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪነትም ክህነት የተቀበሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት ስለክብረ ክህነት፣ስለአምስቱ አዕማደ ምሥጢራትና ስለ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን ወስደዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በሀገረ ስብከታቸው በሚገኙ በተለያዩ አድባራትና ገዳማት የመደቧቸው የአብነት መምህራን ላፈሯቸው ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ከሌሊት ሰባት ሰዓት ጀምረው ሥልጣነ ክህነት ሲሰጡ አድርዋል።

ዘገባው፡- የአቡቀለምሲስ ሚዲያ ነው፡፡

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Jan, 09:40


ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤ የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነው፡፡

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤

በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን  ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ ባለመጠፋፋት፣ ባለመቀላቀል፣ ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣ አንድ ክዋኔ፣ አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክብር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡

በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው  ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም ኣምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኖኣል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቶአታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጐልብተን፣ በሥነ-ምግባር ኣምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡

የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡
ጠቡ ፣ ጥላቻው፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ  ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን ኣላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤ የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኖአል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡    

በመጨረሻም፡-

በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

      አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Jan, 05:19


በጌታችን ልደት ከሰይጣንና ከአጋንንት በስተቀር ያልተደሰተ ፍጡር ያላመሰገነ አካል አልነበረም በተለይ የልደቱን በዓል ከመላእክትና ከእረኞች ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት ያከበሩት እነማን እንደነበሩ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ሲል ይነግረናል

ተራራዎች ተደስተው ኮረብቶችና የዱር ዕፀዋት ደስ ብሏቸው በቅርንጫፎቻቸው ያጨበጭባሉ ፤ ዛሬ በቤተ ያዕቆብ ለዘለዓለም የሚኖር የዓለም መድኀኒት ወልድ ተወልዶላቸዋልና ። ›› በማለት ተራሮች ፣ ኮረብቶች ፣ ዕፀዋትና አራዊት ስለልደቱ ምስክርነት በመስጠት ማንም እንዳልቀደማቸው ሊቁ ተናግሯል ፡፡

ስለዚህ እኛም ኦርቶዶክሳውያን ከልደቱ በረከትን እናገኝ ዘንድ በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህን ስርዓተ ማኅሌት በስንበት ትምህርት ቤታችን እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Jan, 07:10


ሌላ ቦታ ቀጠሮ እንዳይኖራችሁ !!!

ልክ የዛሬ ሳምንት ጥር 4 ቀን 2017 ዓ,ም ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ ሰንበት ት/ቤታችን ታሪኩን የሚቀይር አገልግሎቱን የሚያሰፋ የሁላችንን ርብርብም የሚጠይቅ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል። ምንድን ነው የሚለውን በቀጣይ እናሳውቃለን።
በዚህ ዕለት ብፁዓን አበው ፣ የሀገረ ስብከት እንግዶች የሚገኙበት ክንውን ላይ የታሪኩ ባለቤት ለመሆን አደራ ለመቀበል ሁላችንም ተጋብዘናል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Jan, 06:56


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ስደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የተክስሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

“ በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድር ሰላምም ለሰው ልጆች !

በውጪ ሀገር ፣ በዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ከሰ / ት / ቤታችን ርቃችሁ የምትገኙ የሰ / ት / ቤታችን አባላት በሙሉ እንኳን ለ 2017 ዓ.ም ለጌታችን ለመደኃኒቲችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሠላም በጤና አደረሳችሁ አደረስን አሜን ፡፡

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Jan, 13:20


ለ 50 ወገኖች የበዓል እንኳን አደረሳችሁ ስጦታ ተበረከተ።

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ 50 አቅመ ደካሞች ወገኖቻችን የበዓል እንኳን አደረሳችሁ ስጦታ መርሐግብር አከናውኗል። ልገሳው በሰንበት ትምህርት ቤቱ የምግባረ ሰናይ ክፍል በኩል የተደረገ ሲሆን ለእያንዳንዱ አቅመ ደካማ 3 ሊትር ዘይት እና 3 ኪሎ ዱቄት ልገሳ ተደርጓል።

የእንኳን አደረሳችሁ ስጦታው ለተወሰኑ አቅመ ደካሞች ቤታቸው ድረስ በመገኘት የተበረከተ ሲሆን ሰንበት ት/ቤት ውስጥም ተገኝተው ልገሳውን የተቀበሉ አሉ።

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ለአባላቱ እና ለመላው የተዋሕዶ ልጆች መልካም የልደተ እግዚእ በዓል እንዲሆንላቹ ይመኛል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Jan, 09:26


በኢግዚብሽን ማዕከል በተካሄደው 10ኛ ዙር ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል ሰንበት ት/ት ቤታችን ተሳተፈ

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባህል ፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቤተ መጽሐፍት የመረጃ ሀብቶች ማሰባሰብና ማደራጀት ቡድን ጋባዥነት በአዲስ አበባ ኢግዚብሽን ማዕከል "ንባብ  ለሰላም ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የንባብ ፌስቲቫል ላይ የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ተሳትፏል። ፌስቲቫሉ ለ3 ቀናት የተከናወነ ሲሆን በዚህም ፌስቲቫል ሰንበት ት/ት ቤቱ በሐውልተ ስምዕ ቤተ መጸሐፍትና ወመዘክር ክፍል ተወክሎ ዝግጅቱን ታድሟል። በፌስቲቫሉም ቤተክርስቲያን ከጥንት እስከ አሁን የተገለገለችባቸውን ልዩ ልዩ ጥንታዊ መጸሐፍትን እና በቅርብ የታተሙ መንፈሳዊ መጸሐፍትን በማቅረብ ለታዳሚው ያስጎበኘ ሲሆን ስለመጽሐፍቱ አገልግሎት ማብራሪያ ተሰጥቷል። ተያይዞም ስለ ቤተመጸሐፍቱ አገልግሎት ትንታኔ አቅርቧል።

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በዚህ ፌስቲቫል ላይ እንዲሳተፍ እና ልምድ እንዲቀስም እድሉን ላመቻቸለት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባህል ፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከልቡ ያመሰግናል።

ቤተ መጸሐፍቱን በመደገፍ ድርሻችንን እንወጣ

ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት
ታኅሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም.

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Jan, 04:33


ወርኃዊው የባለ ትዳር ጉባኤ የፊታችን እሑድ ታኅሣሥ 27 ቀን 2017 ዓ,ም ይከናወናል።
ከ3:30 ጀምሮ በአለቃ በዛብህ አዳራሽ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Jan, 09:32


ዜና ዕረፍት

የደብራችን ትጉህ አገልጋይ የሆነው ሊቀ መዘምራን ዘርይሁን ወርቅነህ አባት አባ ወርቅነህ ተሰማ ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።

አረጋዊው አባት አባ ወርቅነህ ከወጣትነት እድሜያቸው ጀምሮ እስለ ዕረፍታቸው ድረስ ከሚወዷት ደብራቸው የማይለዩ ጸሎተኛ ፣ እንደ ልበ አምላክ ቅዱስ ደሰዊት እግዚአብሔርን በበገና የሚያመሰግኑ መዝሙረኛ ጉረቤት መንደሩ የሚወዳቸው አስታራቂ ሽማግሌ ነበሩ። የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በአባታችን ዜና ዕረፍት የተሰማውን ሐዘን ይገልጣል። እመ አምላክም ለወንድማችን መጽናናቱን ታድለው ዘንድ ይመኛል።

ቀብራቸው ዛሬ ከቀኑ 9:00 ላይ በማኅደረ ስብሐት ልደታ ይከናወናል።

የአበታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን።

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

29 Dec, 11:45


ቅዱስ ፓትርያርኩ የቅዱስ ገብርኤል በዓልን
በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
አክብረው በሰላም ወደ መንበረ ክብራቸው ተመለሱ።
+++++++++++++++++++++++++++++++

ታኅሣሥ ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""""""
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ ፲ የልዑካን ቡድን ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በማክበር ዛሬ ከቀትር በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ እና የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከድሬዳዋ ሲነሱ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ሀርጲ ቡህና ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር የክብር አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተኮለሃይማኖትም የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጅዋር፣ም/ከንቲባ አቶ ሀርጲ ቡህ እንዳሁም የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የከተማው የጸጥታ ሀይሎችና የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት እንዲሁም መላው የድሬዳዋ ነዋሪ ሕዝብ ላደረገላቸው የክብር አቀባበልና አሸኛኘት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድሬዳዋ ከተማ የምንወዳት ከተማችን ነች ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ነባር ባህሏን ጠብቃ፣እንግዳ አክባሪነቷን አጽንታና ሰላሟን አስጠብቃ የቀጠለችው ሰላምን የሚሹና የሚሰብኩ፣ሰላምን በተግባር የሚኖሩና ለሰላም ተግተው የሚሰሩ የመንግሥት አመራሮች ስላሏት መሆኑን ጠቁመው ይህን ሰላማዊ ሕይወት በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት በማሳካት ደረጃ በአቶ ከድር ጅዋር የሚመራው የመንግስት መዋቅር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላለው ምስጋና ሊቸረው ይገባል ብለዋል።

በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራው የልዑካን ቡድን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ፣ጸሐፊና ካህናት አቀባበል አድርገውለታል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

28 Dec, 05:21


እንኩዋን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ::

ታህሳስ 19 በዚህች ቀን… ንጉሡ ናቡከደነፆር የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው ። ለወርቁ ምስል ሁሉም እንዲሰግድ እንዲንበረከክ አዘዘ ሁሉም ሰገደ ተንበረከከ ከእነዚህ ሦስት የልዑል እግዚያብሔር ብላቴናዎች በቀር ስማቸው ሲድራቅ ሚሳቅና አብደናጎም ይባላል፤ ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሦስቱን ብላቴናዎች ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው። "አምላኬን አለማምለካችሁ፥ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? እንግዲውስ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? "ብሎ ተናገራቸው።

ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም እንዲህ ሲሉ መለሱለት " ንጉስ ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ደግሞም ያድነናል! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን እንኳን አማልክትህን እንደናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንደማንሰግድ እወቅ" አሉት። የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፥ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፤ እርሱም ተናገረ፥ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት እና እሳቱ ይጥሉአቸው ዘንድ አዘዘ፤ የዚያን ጊዜም እነዚህ ብላቴናዎች ከነልብሳቸው ከነመጐናጸፊያቸው ታስረው እሳት ውስጥ ተጣሉ ።

ናቡከደነፆር አሟሟታቸውን ሊመለከት ቆመ ወደ እሳቱም ተመለከተ አራት ሰዎችም በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ አየ ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም። "ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?" ብሎ ተናገራቸው ። እነርሱም። "ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው" ብለው መለሱለት።እርሱም "እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል" ብሎ መለሰ። ይህም ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡ ናቡከደነፆር ድምጹን ከፍ አድርጎ ከእሳቱ እንዲወጡ ተጣራ የራሳቸው ጸጉር አልተቃጠለም ልብሳቸውም እንዲሁ ናቡከደነፆር ከዚህ በኃላ እንዲህ ሲል እግዚያብሔርን አመሰገነ “በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ” ትንቢተ ዳንኤል 3፡ 1- 30

ከሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ረድኤትና በረከት ያሳትፈን፡፡

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

27 Dec, 05:32


    ለጉዞ ሲመጡ እነዚህን ነጥቦች እንዳይዘነጉ

ታኅሣሥ 20 2017 ዓ,ም ወደ እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤልና ቅዱስ ኤልያስ ቤ/ክ በተዘጋጅው መንፈሳዊ ጉዞ ላይ ለሚሳተፉ አባላት አጭር  መንፈሳዊ መልዕክት።

1➙ በጉዞው የምንሳተፍ አባላት በሙሉ ክርስቲያናዊ አለባበሳችን መምጣት አለበት።

2➙ የመነሻ ሰዓት 2:00 ስለሆነ ሁላችንም ሰዓቱን አክብረን ቀደም ብለን መገኘት ይኖርብናል

 3➙ የመኪና መቆሚያ ቦታ ከመድኃኒዓለም  ቤ/ክ ጀርባ ዋርካው ጋር ይሆናል

4➙ የተቆረጥነውን የጉዞ ትኬት ይዞ መገኘት መርሳት የለብንም።

5➙ ሰንበት ት/ቤቱ ባወጠው መርሐግብር መሠረት ጉዟችንን አጠናቀን እንድንመለስ የበኩላቹን ትብብር ማድረግ እንዳለብን አንዘንጋ።

እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎታችንን ይባርክልን።

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Dec, 17:31


ቅዱስ ፓትርያርኩ በድሬዳዋ ደብረ
መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን
የተሰራውን ሁለገብ ሕንጻ መረቁ።
******

ታኅሣሥ ፲፯ ቀን ፳፻፲ ወ፯ ዓ.ም
******
ድሬዳዋ -ኢትዮጵያ
===========
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የድሬዳዋ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ወበዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ያሰራውን ሁለ ገብ ሕጻ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች ጋር በመሆን መረቁ።

በቤተክርስቲያኑ ቅጽረ ጊቢ የተገነባው ሕንጻ ባሁለት ወለል ሲሆን ለሁለገብ አገልግሎት እንዲውል ታስቦና ሙሉ ወጪውም በዲያቆን ኢንጂነር መላኩ ተስፋዬ ተሸፍኖ የተሰራ መሆኑ በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።በመጨረሻም ደብሩ ሁሉንም የካቴድራል መስፈርቶች አሟልቶ የሚገኝ ስለሆነ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ካቴድራል ተብሎ እንዲጠራ ያቀረበትን ጥያቄ ቅዱስነታቸው ተቀብለው አጽድቀውታል።

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ ጉዞ በነገውም እለት የሚቀጥል ይሆናል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Dec, 09:39


የሰንበት ት/ቤታችንን 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤልና ቅዱስ ኤልያስ ቤ/ክ የምናደርገው ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ 3 ቀናት ብቻ ቀርተውታል። ቦታዎች እየሞሉ ነው እርስዎ ትኬት ካልያዙ ይህ ታሪክ እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ይቁረጡ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Dec, 03:29


በቡፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን
የቅዱስ ገብርኤል በዓልን ለማክበር ወደ ቁልቢ ደብረ
ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
++++++++++++++++++++++
ታኅሣሥ ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ ፲ የልዑካን ቡድን ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል በዓል ለማክበር ፣በበዓሉ ላይ የሚገኙ ምዕመናንን ለማስተማር፣ቃለ በምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ለመስጠት ዛሬ ማለዳ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል።

የልዑካን ቡድኑ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅንና መምሪያ ኃላፊዎችን የሚያካትት ነው።ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎችም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለልዑካን ቡድኑ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ እና የልዑካን ቡድኑ ድሬዳዋ አውሮፕላን
ማረፊያ ሲደርሱ በብፁዕ አቡነ በርተሎሚዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በአቶ ከድር ጁዋርና በካቢኔ አባለቱ፣ በሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ በካህናትና በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል።

በድሬዳዋ ቆይታቸውም በድሬዳዋ ገብረ መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የተሰራው ሁለገብ ሕንጻ ይመርቃሉ፣በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ ጌቴሴማኒ ጠባባት ገዳም ሕጻናት ማሳደጊያ በመገኘትም ታዳጊዎችን በመጎብኘት ትምህርተ ወንጌል፣ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚሰጡ ይሆናል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Dec, 08:20


#አራት_ቀናት_ብቻ

በ ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ቆይታዎ ካፈሩት ወዳጅ ጋር እንዲህ ያሉ ኹነቶችን አብሮ መካፈል ታሪክ ነው። የጋራ ትዝታንም ያተርፋሉ። ደግሞ ይህ የሚሆነው በሰንበት ት/በለትዎ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉ ላይ ነው።
ታዲያ የዚህ ታሪክ አካል ለመሆኑ የጉዞ ትኬት መቁረጥዎ ወሳኝ ነው። አራት ቀናት ብቻ ነው የቀሩን አሁኑኑ ይቁረጡ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Dec, 11:49


. #የጉዞ_ትኬትዎን_ይዘዋል?

ወደ እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤልና ቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን የምናደርገው መንፈሳዊ ጉዞ #5_ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እርስዎ ዝግጁ ነዎት? ትኬቱንስ ቆርጠዋል?
እንግዲያዎስ ዛሬውኑ ቦታ ሳይሞላብዎ ትኬቱን በጅዎ ይያዙ
👉 በሰንበት ት/ቤቱ ንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ
👉 በጽሕፈት ቤት እና
👉 በቤተ መጻሕፍቱ ያገኙታል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Dec, 11:18


ውድ የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት አባላትና አንባብያን የቃለ እግዚአብሔር ዕድምተኞቻችን እንኳን ለመጀመሪያ ዓመት ቅጽ 1፥ ቊጥር 3 ዲጂታል መጽሔት ጽሑፋችን በሰላም አደረሰን!

በዚህች የታኅሣሥ ወር የቅዱሳን ሃይማኖት "ቊጥር 3" ዲጂታል መጽሔት በሰባት የጽሑፍ ዐምዶችና በ23 ገጻት አሰናድተን፥ አቅርበንላችኋል።

ጽሑፋቱ በዋነኝነት የጌታችን በዓለ ልደትና ተያያዥ ሰሞንኛ በዓላት ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው።

አንብባችሁ ለመንፈሳዊ ሕይወት ስንቅ የሚሆን ዕውቀት እንደምትገበዩበት ተስፋ እናደርጋለን።

            እነሆ፥ መጽሔቷ!

    1ኛ ዓመት፥ ቅጽ 1፥ ቊጥር 3።
      ወርኀ ታኅሣሥ፤ 2017 ዓ.ም።


      ስለምታነቡልን እናመሰግናለን!

     "ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ እንትጋ!"

    ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
    እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ!

           መልካም ንባብ!

🔖 አዘጋጅ፡-

   በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና
ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም አብያተ ክርስቲያን፡፡
            የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት፤
ኪነ ጥበብ ክፍል፤ የጽሑፍ ዝግጅት ንኡስ ክፍል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

23 Dec, 07:55


“ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወዳል፣ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል"መጽሐፈ ምሳሌ 17 ፣ 17

እውነተኛ ወዳጆች እምነት የሚጣልባቸው ናቸው። እርስ በርስ እንደሚቀራረቡ ወንድማማቾች በተለይ በችግር ጊዜ አንዳቸው ለሌላው ታማኝነትና አሳቢነት ያሳያሉ።
እኔም በሰ/ት/ቤት መኖሬ ከሰጠኝ ጥቅም አንዱ በሕይወቴ ሁሉ ከጎኔ የቆሙ ብዙ ወንድሞች እና እህቶችን አፍራቻለው፡፡

እናም የፊታችን ታኅሣሥ 20 - 2017 ዓ,ም የ60ኛ ዓመት ምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚካሄደው የሰንበት ት/ቤታችን መንፈሳዊ ጉዞ ላይ ልደትዬ ከሰጠችኝ ወዳጆቼ ጋር እጓዛለሁ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

20 Dec, 14:20


ዜና ዕረፍት

የሰንበት ት/ቤታችን  አባል የሆነው  የወንድማችን የዲ/ን  ሀረጉ ዲሳሳ    ወንድሙ  በዛሬው ዕለት ዐርፏል የቀብር  ሥረዓቱ ነገ  6:00 ሰአት ላይ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ይፈጸማል
የመኖሪያ አድራሻ :-  ከኮካ አደባባይ መቶ ሜትር ወደ 25 ቀበሌ ክበብ ገባ ብሉ
ስልክ ቁጥር :- 0913133576
የወንድማችንን ነፍስ ከቅዱሳኖቹ  ጎን ያሳርፍልን እመ አምላክ የቤተሰቡን የልብ ሐዘን ታቅልልን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ያድልልን ።
እሑድ 12:00 ሰአት በመኖሪያ ቤታቸው የማጽናኛ መርሐ ግብር የምናከናውን ይሆናል

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

20 Dec, 10:27


ውድ የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት አባላትና የመጽሔታችን አንባብያን
የቃለ እግዚአብሔር ዕድምተኞቻችን እንኳን ለኻያኛ (20) ዓመት ቅጽ 1፥ ቊጥር 1 ልዩ ዕትም መጽሔት ዝግጅታችን በሰላም አደረሰን፥ አደረሳችሁ!

      የጥር ወር የቅዱሳን ሃይማኖት ልዩ ዕትም፥
     መጽሔታችንም፥ በቅርቡ ታትማ ለንባብ ትበቃለች!


               ይጠብቁን!

     20ኛ ዓመት፥ ቅጽ 1፥ ቊጥር 1፥
ልዩ ዕትም፥ ወርኀ ጥር፤ 2017 ዓ.ም።


      ስለምታነቡልን እናመሰግናለን!

🔖 አዘጋጅ፡-

   በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና
ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም አብያተ ክርስቲያን፡፡
            የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት፤

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

18 Dec, 07:29


#challenge #ከወዳጆቼ_ጋር_እኔም_እጓዛለሁ

"ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጅ አለ"መጽሐፈ ምሳሌ 18 ፣ 24

እንዲል ጠቢቡ በሰንበት ትምህርት ቤት መኖር ከሚሰጥን ጥቅም አንዱ  በእያንዳንዱ የሕይወት መስመር ላይ ከኛ የማይለዩ የሕይወት ዘመን ወዳጆችን ማግኘት ነው።
እናም የፊታችን ታኅሣሥ 20 - 2017 ዓ,ም የ60ኛ ዓመት ምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚካሄደው የሰንበት ት/ቤታችን መንፈሳዊ ጉዞ ላይ እናታችን ከሰጠችኝ ወዳጆቼ ጋር እጓዛለሁ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

17 Dec, 10:08


#challenge #ከወዳጆቼ_ጋር_እጓዛለሁ
.             " # ኑ በመንፈሳዊ ጉዞ በረከትን ፣ ፍቅርን ፣አንድነትን እንውሰድ "
.        ▃▃▃▃▃  ▃▃  ▃▃ ▃ . .

በእያንዳንዱ የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ  የምታወያየው ፤ አቅጣጫ የሚመራህ ቤተሰብ የምታደርገው ሰው አታጣም። ደስታህ አስደስቷቸው ሳቅህን አብረው የሚስቁ ፤  "ከተዋለደ የተዛመደ" እንዲል የደስታ ተካፋይ ዘመዶችን ታፈራበታለህ። ሐዘንህን እስክትረሳ ድረስ ከጎንህ ሆኖ የሚያጽናና ወዳጅ ታገኝበታለህ።

ሰንበት ትምህርት ቤት በራስ መተማመንን የምትገነባበት በልጅነት ኃላፊነት መወጣትን የምትለምድበት ፣ በሰው ፊት የመናገር ጥበብን የምትማርበት ተቋም  ነው። ሰንበት ተማሪነት የሰው ሀብታም መሆን ፣ የመንፈስ ቅዱስ እህቶችን ወንድሞችን የሚገኝበት ነው። በቤተ ክርስቲያን በኩል የሚፈጠር ወዳጅነት ሌላ ቦታ ከሚፈጠሩ ወዳጅነቶች ይለያል። እዚህ ወሬውም ጨዋታውም እሳቤውም በዋናነት በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ያመዝናል ያ ደግሞ ለእኛ ጠቃሚ እና ዎጋ ያለው ነው ።
60ኛ ዓመት በተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉዞ ታህሳስ 20 እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እመጣለሁ!!!!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

16 Dec, 18:16


በተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ቆይታዎ እንዴት ያለ ባልንጀራ አፈሩ ማንስ ወዳጅ ሆነዎ ?

የሰንበት ተ/ቤታችንን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ታኅሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ,ም ወደ እንጦጦ ርዕሰ አድባራት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤልና ቅዱስ ኤልያስ ገዳም የሚካኤደውን መንፈሳዊ ጉዞ በማስመልከት ከነገ ጀምሮ " #ከወዳጆቼ_ጋር_እኔም_እጓዛለሁ #challenge " ተዘጋጅቷል ስለዚህ ሁላችሁም በሰንበት ት/ቤት ቆይታችሁ ማንን ወዳጅ እንዳፈሩ እንዴት ያለ ባለንጀራ እንዳገኙ በተመጠነ ጽሑፍና በገላጭ ፎቶ አያይዘው ይላኩልን። እኛም እንለጥፈዋለን።

https://vm.tiktok.com/ZMk2h5XSn/

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

15 Dec, 13:20


የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤትን 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተከናወነ።

ዛሬ ማለትም ታኅሣሥ 6 ቀን 2017 ዓ,ም የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳና የበጎ አድራጎት መርሐ ግብር ደስ በሚል መልክ ተለናውኗል።

በደም ልገሳው መርሐ ግብር ላይ 60 አባላት ክቡር የሆነውን ደማቸውን በመለገስ የተሳተፉ ሲሆን በበጎ አድራጎቱም ሥራውም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሆን መባ ይዘው የመጡ አባላት አሉ ሆኖም ግን ጧፍ እጣን ሻማና ዘቢቡ ከታሰበው አንጻር በበቂ ሆኔታ ስላልተሰበሰበ ወደፊትም ባሉ ጊዜያት ይዞ መምጣት እንደሚቻል ተገልጧል።

በስተ መጨረሻም የሰንበት ት/ቤቱን ጥሪ ተቀብላችሁ በጎውን ነገር ላደረጋችሁና ላስተባበራችሁ የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በእግዚአብሔር ስም ምስጋናውን ያቀርባል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Dec, 19:55


ዜና ዕረፍት

የሰንበት ት/ቤታችን  አባል የሆነው  የወንድማችን የወንደሰን ቢራራ አባት  በዛሬው ዕለት ዐርፈዋል የቀብር ስነ ሥርዓታቸው ዛሬ  ህዳር 27/03/ ቀን 2017  ዓ,ም
ጋሸና ኢየሱስ ቤተክርሰቲያን ተፍፅሟል

የመኖሪያ ቤት አድራሻ ፦ ቦሌ ቡልቡላ ልዩ ሰሙ ቀይ አፈር (ኤርፓረት ጀርባ)
ስልክ - +251913067602

የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳኖቹ  ጎን ያሳርፍልን እመ አምላክ የቤተሰቡን የልብ ሐዘን ታቅልልን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ያድልልን ።

ተክለ ሳዊሮሰ ሰንበት ትምህርት ቤት

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Dec, 07:11


የደም ልገሳ መርሐ ግብር

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት 60ኛ ዓመቱን ከሚያከብርባቸው መርሐ ግብራት መካከል ታኅሣሥ-6 ቀን 2017 ዓ,ም የሚያደርገው የደም ልገሳና የበጎ አድርጎት መርሐ ግብር አንዱ ነው።

ደም መለገስ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት መታደግ ነው። በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮም የተከለከ አይደለም። እናም የምንችል ሁሉ በዚህ በጎ ስጦታ ተካፋይ ሆነን ለወገኖቻችን እንደርስላቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Dec, 13:23


የቀን ለውጥ ተደርጓል !!

የፊታችን እሑድ ኅዳር 29 ሊደረግ የነበረው የበጎ አድራጎትና የደም ልገሳ መርሐ-ግብር በአገልግሎት መደራረብ ምክንያት የቀን ለውጥ ተደርጎበት ታኅሣስ -6 2017 ዓ,ም ሆኗል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Dec, 10:17


የፊታችን እሑድ ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ,ም ወርኃዊው የባለትዳሮች ጉባኤ ይካሄዳል።
ተጋባዥ መምህር መ/ር ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ናቸው።
ከ3:30 ጀምሮ እንጠብቅዎታለን

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Dec, 13:22


https://youtu.be/qc-sRKdxum4?si=uKHMb5a42-dS2XBn

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Dec, 10:59


ለኦርቶዶክሳውያን ጸሓፍያን!

"ኑ! በተሰጥዎት የመጻፍ ጸጋ ቤተ ክርስቲያንን ያገልግሉ!"

ለጽሑፍ አዘጋጆችና ጸሓፍያን የተዘጋጀ የዐምደኝነት ጥሪ!

በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና
ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም አብያተ ክርስቲያን።
    የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት፤
በኪነ ጥበብ ክፍል፤ የጽሑፍ ዝግጅት ንኡስ ክፍል።

📌 ለሰንበት ት/ቤታችን አባላት፤
📌 ለደብራችን አገልጋይ ጸሐፍት፤
📌 ለአኃት ሰንበት ት/ቤት ጸሓፍያንና ደራስያን፤

በሙሉ መንፈሳዊ ጽሑፍ በመጻፍ በዐምደኝነት ማገልገል የሚችሉበትን መድረክ አመቻችተናል።
የዐምደኝነት ጥሪውን ተቀብለው በተሰጥዎት ጸጋ ያገልግሉ!

📜 ዐምደኛ ለመሆን

👉 መንፈሳዊ ጽሑፍ የመጻፍ ፍላጎትና አቅም ያለው፤
👉 የሥነ ጽሑፍ ዘዴ ሥልጠናን ሳያቋርጥ መሠልጠን የሚችል፤

🗓 የምዝገባ ጊዜ፦ ከኅዳር 23 እስከ ታኅሣሥ 12

🔴 ለመመዝገብ

ከታች ባለው ስልክ ቊጥር ደውለው ይመዝገቡ!
- 0902462572

🔴 የዐምደኞች ቅበላ ስብሰባ

🔖 ቀን፦ ታኅሣሥ 13 (እሑድ)፤
🔖 ሰዓት፦ ከምሽቱ 11፡00 - 1፡30፤
🔖 ቦታ፦ ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ላይ።

"ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ እንትጋ!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Nov, 10:37


https://vm.tiktok.com/ZMhc7nrdt/

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Nov, 18:42


የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በሥጋ የተለዩትን አባሎቹን በጸሎተ ፍትሐት አሰበ።

የተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት ቤት በሥጋ የተለዩትን አገልጋይ እህት ወንድሞችን ጸሎተ ፍትሐት በማድረግ አስቧል። የደብሩ ካህናት ፣ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት እና ምዕመናን በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐቱ በመድኃኔዓለም ዐውደ ምሕረት የተከናወነ ሲሆን በተጨማሪም የጧፍ ማብራት ስነ ሥርዓት ተከናውኗል።

እግዚአብሔር አምላክ በሞተ ሥጋ የተለዩንን እህት ወንድሞቻችንን ነፍሳቸውን ከቅዱሳን ሕብረት ይጨምርልን። ያገለገሏት እመቤት ለነፍሳቸው ምልጃ ትቁምልን። በአገልግሎት ያለነውንም ክርስቶስን መስለን የምንኖርበትን ሕይወት ያድለን።

ኅዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም.

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

21 Nov, 05:21


https://vm.tiktok.com/ZMhWWJ8Cb/

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

20 Nov, 18:49


የ60ኛ ዓመት ሁለተኛው መርሐ ግብር
           የጸሎተ ፍትሐት ጉባኤ

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በሕይወተ ሥጋ የተለዩ አባላቱን ኅዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በጸሎተ ፍትሐት  ያስባል።
መጽሐፍ  "ለሞተ ሰው አረፈ ነገር ግን ነፍሱ ታርፍ ዘንድ ተዝካር አውጣለት" መ. ሲራክ 38: 23 እንዳለው ሰንበት ት/ቤታችንም የ60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሏን ምክንያት በማድረግ የልጆቿን ነፍስ አምላክ በደጋጎቹ እቅፍ ውስጥ ያኖር ዘንድ ይህን ታላቅ የጸሎተ ፍትሐት ጉባኤ አዘጋጅቷል።

ሰዓት - ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ - በመድኃኔዓለም ዐውደ ምሕረት

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

20 Nov, 09:45


https://vm.tiktok.com/ZMhWjfVhT/

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

20 Nov, 09:00


ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ጠላት የሚታደገን የነፍሳችን ጠበቃ የሕይወታችን ዋስትና መሆኑን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር ‹‹ ለነፍስ ሁሉ ነጋዲ ስለሆነው ስለሚካኤል ብለህ አቤቱ ከክፉ ጠላት አድነን ። ›› በማለት ዘምሯል ።

‹‹ ነጋዲ ›› ሲል በዚህ ዓለም የሚነግድ ሰው ያገሩን ምርት ወስዶ የውጭውን ሀገር ምርት እንደሚያስመጣ ሁሉ ቅዱስ ሚካኤልም የሰውን ጸሎትና መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር አድርሶ ፤ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ቸርነት ወደ እኛ የሚያመጣ የነፍስና የሥጋ መጋቢ ነው ።

አንድም በዚህ ዓለም የሚነግድ ሰው በተሰጠው መክሊት ወጥቶ ወርዶ እንደሚያተርፍ ቅዱስ ሚካኤልም በተሰጠው የቃል ኪዳን መክሊት ከአብ ዙፋን እየገባ እየወጣ እያማለደ ነፍሳትን ያተርፋል ፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቃል ለማለት ነው ።

እኛም የሐዲስ ኪዳን ምዕመናን የተባልን ከእግዚአብሔር ዘንድ ምህረትን ቸርነትን እንዲያመጣልን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን ሥርዓተ ማኅሌት በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህ ስርዓተ ማኅሌት በሰንበት ትምህርት ቤታችን እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል ። #መልካም_በዓል

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

19 Nov, 08:21


ኑ! በተሰጥዎት የመጻፍ ጸጋ ቤተ ክርስቲያንን ያገልግሉ!

ለጽሑፍ አዘጋጆችና ጸሓፊያን የተዘጋጀ የዐምደኝነት ጥሪ!

በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና
ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም አብያተ ክርስቲያን።
    የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት፤
         በተውኔትና ኪነ ጥበብ ክፍል፤
         በጽሑፍ ዝግጅት ንኡስ ክፍል፤
ለጽሑፍ አዘጋጆችና ጸሓፊያን የተዘጋጀ የዐምደኝነት ጥሪ!

በሰንበት ት/ቤቱ መንፈሳዊ ሰሌዳዎችና ዲጂታል እንዲሁም በሚታተሙ መጽሔቶችና በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ (Social Media) ላይ በዐምደኝነት ማገልገል የሚችሉበትን መድረክ አመቻችተናል።

የዐምደኝነት ጥሪው ቀድመው ለሚመጡ 20 ሰዎች የሚያገለግል ሲሆን በአፋጣኝ እድልዎን ይጠቀሙ!

📜 ዐምደኛ ለመሆን የሚያስፈልግ መስፈርት

👉 1) የሰንበት ት/ቤቱ አባልና የደብሩ አገልጋይ የሆነ፤
👉 2) መንፈሳዊ ጽሑፍ የመጻፍ ፍላጎትና አቅም ያለው፤
👉 3) በሰንበት ት/ቤቱ የሚሰጠውን ተከታታይ መንፈሳዊ ኮርስ ተከታትሎ የጨረሰ፤
👉 4) ወደፊት በሰንበት ት/ቤቱ የሚሰጠውን የሥነ ጽሑፍ ዘዴ ሥልጠና ሳያቋርጥ መሠልጠን የሚችል፤

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት አሟልተው መመዝገብ የሚችሉ 20 ሰዎች ብቻ ናቸው!

🗓 የምዝገባ ጊዜ

ማስታወቂያው ከወጣበት ኅዳር 10 እስከ 16 ነው።

🔴 ለበለጠ መረጃና ምዝገባ

ከታች ባሉት ስልክ ቊጥሮች ደውላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ፦

- መ/ር ድንበሩ፦ 0919903376
- ቢታንያ፦ 0902462572
- አዳም፦ 0945580710

🔖 የዐምደኞች ቅበላ ስብሰባ

📌 ቀን፦ ኅዳር 17 (ማግሰኞ)፤
📌 ሰዓት፦ ከምሽቱ 12፡00 - 1፡50፤
📌 ቦታ፦ በሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት።

"ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ እንትጋ!"

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

17 Nov, 12:12


ይህን ሁሉ ላከናወነ ለድንግል ማርያም ልጅ እግዚአብሔር አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው የሰንበት ትምህርት ቤታችሁንን 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ኅዳር 7 20 17 ዓ.ም ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ ።

የሰንበት ትምህርት ቤታችሁን ጥሪ አክብራችሁ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ለማክበር በዕለቱ ተገኝታችሁ በደመቀና ባማረ መልኩ በፍቅር በደስታ እንድናከብር ስላደረጋችሁ የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ትልቅ ምስጋናና አክብሮቱን ያቀርባል ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

16 Nov, 11:35


https://www.youtube.com/live/0CDZsl8_ORw?si=N5Gczyg8xEgPV7tf

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

16 Nov, 04:14


የጥሪ ካርዱ አልደረሰንም ብላችሁ እንዳትቀሩ

እርሱ እናንተን ለማክበርና ለማስታወሻነት የተዘጋጀ እንጂ መግቢያ አይደለም!! ስለዚህ ሁላችንም በሰዓታችን ቀድመን እንገኝ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

15 Nov, 13:31


በተለያዬ የዓለም ክፍል ያላችሁ ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትና ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ የነገው የአንድነት ጉባኤያችን ከ7:30 ጀምሮ በ ሰንበት ት/ቤታችን የ Youtube ቻልም https://youtube.com/@lidetateklesawiros-4216?si=oJZ-2ZItqdf8-A82 በቀጥታ ስርጭት ስለሚተላለፍ  እንዴትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

15 Nov, 13:19


ነገ ታሪካችንን በፎቶ እናስቀራለንና ቀድመው ይምጡ

የአንድነት መርሐ ግብራችን አንድ ቀን ያልሞላ ጊዜ ቀርቶታል። እኛም ዝግጅታችንን አጠናቀን እናንተን እየጠበቅን ነው። ይህን የሰንበት ት/ቤታችንን የ60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ሁላችንም ለታሪክ እናስቀረው ዘንድ በግልም በጋራን የፎቶ መነሳት መርሐ ግብር ስላለ በተቻለን መጠን ከጉባኤው መጀመሪያ ሰዓት ቀደም ብለን እየተገኘን ማስታወሻችንን እናስቀር ዘንድ በልዑል እግዚአብሔርስም እንጠይቃለን።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

15 Nov, 05:59


❝  ኢንኅድግ ማኅበርነ ፤ ማኅበራችንን አንተው ❞
ዕብ 10 : 25

አንድ ቀን ብቻ ቀረው

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

14 Nov, 12:29


በ2004 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የመስቀል በዓል ወረብ ያቀረቡ ወንድም እህቶቻችን ቅዳሜ ኅዳር 7 በድጋሜ ወረብ ሊያቀርቡ ተዘጋጅተዋል። እናንተስ በጉባኤው ለመታደም ጊዜውንና ነጭ ልብሶን አዘጋጅተዋል?

የኅዳር 7 ሰው ይበለን🙏

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

14 Nov, 04:27


"እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው ..... በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ" ራእይ 7፥9

የሰንበት ት/ቤታችንን የልደት ቀን ለማክበር ነጭ ለብሰን እንገኛለን።  ዝግጁ ናቹ?

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

13 Nov, 09:16


#እንኳን_አደረሳችሁ

ኅዳር 7 20 17 ዓ.ም ከ ቀኑ 7 ፡ 30 ጀምሮ የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል መከበር ይጀምራል በዕለቱም

✞ ብፁዓን አበው ሊቃቃነ ጳጳሳት ይገኛሉ

✞ ቃለ ወንጌል በተጋባዥ መምህር

✞ በልዩ መርሐ ግብራችን ደግሞ ( የሊቃነ መናብርት ወግ )

✞ በተጋባዥ ዘማርያን ዝማሬ

✞ በ2004 ዓ.ም . የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ ወረብ ያቀረቡ አባላት በዕለቱ በወረብ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።

✞ እንዲሁም ሌሎች መርሐ ግብራት በዕለቱ ተዘጋጅተው ይጠብቆታልና ወዳጅ ዘመዶትን ይዘው እንዲገኙ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

13 Nov, 04:53


ሦስት ቀናት ብቻ ቀርተውናል ዝግጁ ናችሁ?
ምናልባት እስካሁን የጥሪ ካርድዎን ወስደው ካልሆነ በሰንበት ት/ቤቱ ቤተ መጻሕፍትና የንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ በመሄድ አሁኑኑ በእጅ ያስገቡ።
መቼም በዕለቱ ስንመጣ በነጭ አልባሳቶቻችን ደምቀን መሆኑን አንረሳም አይደል?

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

13 Nov, 04:43


የሰንበት ት/ቤታችን ፍሬ የሆኑት ቀሲስ ሃብታሙ ሃብተሥላሴ ከአሜሪካ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት።

ለተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት አባላት ለሆናችሁ በሀገር ውስጥ በአገልግሎት ላይ ያላችሁ እንዲሁም በስራ በትምህርት በኑሮ ምክንያት በተለያየ ቦታ የምትገኙ እናት አባቶቼ እህት ወንድሞቼ እንኳን ለሰንበት ትምህርት ቤታችን 60 ኛ አመት የምስረታ በአል አደረሳችሁ :: በዚህ ዘመን ላለን ክርስቲያኖች የሰንበት ትምህርት ቤት ውለታ ተነግሮ እና ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም :: ከልጅነት እስከ እውቀት ሃይማኖት ከምግባር የተማርንባት ከሊቃውንት አባቶቻችን ጋር የተዋወቅንባት በጸሎት የተጉ በመንፈሳዊ ሕይወት የበረቱ ክርስቲያኖችን ያየንባት በምክርና በጸሎታቸውም የተጠቀምንባት ትጉህ የሆኑ ቤተሰቦች ያፈራንባት ቤታችን ናት :: እግዚአብሔር ፈቅዶልን በዚህ ዘመን ያለን የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትም ዘመኑን በመዋጀት ታዳጊ ሕፃናትን እና ወጣቶችን በማስተባበር በማስተማር የአባቶችን መንገድ በማሳየት እና እንዲከተሉም  በማድረግ ለቤተክርስቲያን መልካም  ትውልድ መፍጠር ይጠበቅብናል ለዚህም የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን::

በመጨረሻም በመጪዎቹ አመታት የሚከበረውን የሁላችን መገኛ መሰብሰቢያ የሆነችውን የታላቋን ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበትን 100ኛ አመት ሁላችንም ልጆቿ ካለንበት ተሰብስበን ከሊቃውንቱ ከካህናቱ ከዲያቆናቱ ከሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እንዲሁም ከማህበረ ምእመናኑ ጋር በህብረት በመዘጋጀት በአሏን ለማክበር እንዲያበቃን የእመቤታችንን መልካም ፈቃዷ ይሁንልን::

በአካል ከሀገር ብንርቅም ኅዳር 7 በሰንበት ትምህርት ቤታችን ማህበራዊ ድረ ገፅ መርሃ ግብሩን እንከታተላለን ::

እንኳን አደረሳችሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

12 Nov, 19:36


ዛሬ ምሽት በኅዳር -7  የሰንበት ት/ቤታችን የምሥረታ በዓል የአንድነት ጉባኤ ላይ ያሬዳዊ ዜማ(ወረብ) የሚያቀርቡት በ2004 ዓ.ም.  የመስቀል ደመራ በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ ወረብ አቅራቢ ከነበሩ አባላቶቻችን ጋር ዝግጅት ኮሚቴው አጭር ቆይታ ያደረገ ሲሆን የሰንበት ት/ቤቱም መልእክት በም/ሊቀመንበራችን መ/ር ኤልያስ አባተ ተላልፎ የወረብ ጥናቱ ( ክለሳው ) ተጀምሯል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 19:12


አርማው ( Logo ) በተለያዩ መገልገያዎች ላይ ሲያርፍ የሚኖረው ገጽታ በጥቂቱ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 18:58


በሎጎ ላይ ያሉት ቀለማት ምንን ይወክላሉ?

ሀ➙ ሰማያዊ፡- ቤተክርስቲያን በሥዕላቶቿ ላይ ሰማያዊ ቀለም የምትጠቀመው ቅዱሳኑ ሰማያዊውን ሀብት ገንዘብ ማድረጋቸውን ፣ ዓለማዊነትን ድል አድርገው ሰማያውያን መሆናቸውን ለማመልከት ነው። ሰማያዊ ቀለም እምነትን መታመንን ይወክላል። ከዚህ በመነሳት ሰንበት ት/ቤት እያስተማረች ልጆቿን ወደ መንፈሳዊነት የምትመራ ሀገራቸው በሰማይ እነሱም ሰማያውያን እንደሆኑ የምታስተምር በመሆኗ ቀለሙ ተመርጧል። በተጨማሪም ሕይወታቸውን እስከ መስጠት ለቤተክርስቲያን ክብር የቆሙ ብዙ አባላት ያፈራች ሰንበት ት/ቤት ናትና እስከ ፍጻሜው ለታመኑ አባላትን ለማሰብ ቀለሙ ተመርጧል።

ለ➙ ቢጫ፡- ይህ ቀለም እውነተኛነትንና ብርሃንነትን ይገልጻል፡፡ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” እንዲል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና ማዕረግ ላይ የደረሱትን ቅዱሳንን “እውነተኞችና የዓለም ብርሃን ናችሁ” ስትል በራሳቸው የብርሃን አክሊል በቢጫ አድርጋ ትሥላለች፡፡ ሰንበት ት/ቤትም እነዚህ የዓለም ብርሃን የሆኑትን ቅዱሳንን የምትሰብክ የምትገልጽ ልጆቿም እነሱን እንዲመስሉ እያለማመደች የምትቀርጽ ናትና ቀለሙን ተጠቅመናል። ቢጫ ተስፋ ነው ሰንበት ት/ቤታችንም ዓለሙን እየዋጀች ለብዙ ትውልድ እስከ ፍጻሜው የምትኖር ተቋም መሆኗን ይገልጻል።

ሐ➙ ነጭ፡- የድል አድራጊነት፣ የንጽሕና እና የፍጹምነት ምሳሌ ነው፡፡ ቅዱሳን ዓለምንና ምኞቱን ድል ያደረጉ ልበ ንጹሐን በመሆናቸው ነጭ ልብስ ለብሰው ይሣላሉ፡፡ መለኮታዊ ክብርንም ያሳያል ለዚህም በደብረ ታቦርና በትንሣኤ ሥዕሎች ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነጭ ልብስ ለብሶ ይሣላል፡፡  በብዙ የተፈተነችው ሰንበት ት/ቤታችን ሁሉን ፈተና ድል አድርጋ የጸናች ልጆቿንም ወደ ንጽሕና የምታቀርብ ናትና ቀለሙ ሊመረጥ ችሏል

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 18:54


ሎጎው ምን ምን ነገሮችን አካትቷል?

1ኛ➙ የሁለቱ ቤተክርስቲያናት ሕንጻ

የሁለቱን ደብራት ማለትም ከፊት የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እንዲሁም ከኋላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እንዲኖሩ ተደርጓል። የልደታ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ከፊት የተደረገው በምስረታ ከመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስለሚቀድም ሲሆን የልደታ ደብር ከመቃኞ ቤቷ ጀምሮ በ1916 ዓ.ም እንዲሁም የመድኃኔዓለም ደብር ደግሞ በ1939 ዓ.ም. መመስረታቸውን ይጠቁማል።

2ኛ ➙ የጳጳስ ቆብ (አስኬማ)

አስኬማው የደብራችን የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም መሥራችና ሰንበት ት/ቤታችንም በስማቸው የተሰየመባቸው አቡነ ሳዊሮስን የሚጠቁመን ሲሆን እኚህ አባት በኢትዮጵያ ምድር ጵጵስናን በ1922 ዓ.ም. የተቀበሉ ለመሆናቸው ማሳያ ነው። (በ1921 ዓ.ም. የተሾሙት አባቶች ግብጽ ሄደው ጵጵስናውን እንደተቀበሉ ልብ ይለዋል) አቡነ ሳዊሮስ ግን በበአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና የእስክንድርያው ፓትርያክ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት በጥር 1 ቀን 1922 ዓ.ም. ጵጵስና በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተቀብለዋል።

3ኛ ➙ የተዘረጋ (የተገለጠ) መጽሐፍ

ከአስኬማው በታች የተገለጠ መጽሐፍ ቅዱስ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱሱ ወይም ቅዱስ ወንጌሉ መዘርጋቱ ወንጌል ሁሌ በቦታ ሳይወሰን በ7ቱም ቀናት የሚሰጥበት ሰ/ት/ቤት መሆኑን ያመለክታል። በአካልም በርቀትም ሁሌ ቃለ እግዚአብሔር የሚሰጥበት ሰንበት ት/ቤት ናትና መጽሐፍ ቅዱሱ እንዲገለጥ ተደርጓል።

4ኛ➙ በግእዝና በአረብኛ ቁጥር የተገለጸ 1957 እና ፲፱፻፶፯ የሚል አኀዝ እናያለን ይህ ቁጥር ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት የተመሠረተበትን ዓመት የሚገልጽ ሲሆን ሰንበት ት/ቤታችን ኅዳር 7 ቀን 1957 ዓ.ም. እንደተመሠረተ ይገልጻል።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 17:02


በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከዚህ በኋላ የሚጠቀምበትን የመለያ ምልክት ( Logo ) በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት 30 2017 ዓ.ም. በይፋ አስመረቀ ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰንበት ት/ቤቱ አዲስ ባስተዋወቀው መለያ አርማ ላይ ያሉት ምልክቶች የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ቅዱስ ወንጌል እና የጳጳሳት አስኬማ ተካተው ይታያሉ ።

በመጨረሻም ከዚህ በኋላ የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት የሚጠቀመው አርማ ይህንን እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 13:40


ቀንዎን ያስተካክሉ

ልንገናኝ ሰባት ቀን ብቻ ቀርቶናል

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 12:31


ታላቅ የምሥራች
በይዘት ዝግጅቱ መንፈሳዊ የሆነ ባማረና በተለየ መልኩ በተውኔትና ኪነ ጥበብ ክፍል ፤ የጽሑፍ ዝግጅት ንኡስ ክፍል እየተዘጋጀ በየወሩ የሚቀርብ ዲጂታል መጽሔት ይዘንላችሁ መተናል !

አንብባቹ ለመንፈሳዊ ሕይወት ስንቅ የሚሆን ዕውቀት እንደምትገበዩበት ተስፋ እናደርጋለን ።

መጽሔቷን ኅዳር 1 ቀን እንደሚለቀቅ ስናበሥር በታላቅ ደስታ ነው !

በተጨማሪም ለ 2 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው መንፈሳዊ የኬብሮን ሰሌዳ ጽሑፍ በድጋሚ ወደ አገልግሎት መመለሱን ልናሳውቅ እንወዳለን !

           ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 05:36


ሁልጊዜም በወሩ መጨረሻ እንደምናደርገው ጥቅምት 30 ቀን ወርኃዊው የሰንበት ትምህርት ቤታችን የጸሎት መርሐ ግብር 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ዋና አዳራሽ ( ጎልጎታ አዳራሽ ) ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ ካህናት አባቶች በተገኙበት ይካሄዳል።

በእለቱም የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የሚወክል አርማ ( ሎጎ ) የሚመረቅ ሲሆን ሁላችንም ሳንቀር ከመጥምቀ መለኮት ረድኤት በረከትንና የሰንበት ት/ቤት ቤታችንንም መለያ የሆነውን አርማ አብረን እንድንመርቅ ሌሎች ወንድም እህቶቻችንን ጋብዘንም እንገኝ ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Nov, 13:38


ዘማሪ ዘሩባቤል ሀብታሙ እባላለው
ወደ ተክለሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት በህፃንነት እድሜ 1993 -1994 የህፃናት ኮርስ ተማሪ የነበርኩ ሲሆን በረብሻው ምክንያት ሰንበት ተማሪዎች ሲወጡ እንደ ገና እንደ አዲስ 1995 ህፃናት ክፍል ገብተን ኮርስ መማር ጀመርን ሰንበት ትምህርት ቤቴ ለኔ ልዩ ናት ብዙ ከባድ ጊዜያትን አሳልፋለች በወቅቱ አገልግሎት ለኔ ከባድ ቢሆንም  አይምሮዬ ሚያርፍባት ለነፍሴ እርካታን የማገኝባት  የውስጤን ለፈጣሪዬ የምነግርባት እናቴም አባቴም ሆና ከክፉ ከልላ ያሳድጋ የሳለፈችኝ ለአገልግሎት ብቁ ያደረገችኝ ሰንበት ትምህርት ቤቴ ለኔ ልዩ ናት ዛሬም ለብዙ ረጅም አመታት በመዝሙር ክፍል አስጠኚነት በአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶችም አገልግሎት በመስጠት እናም በየአድባራቱ የአውደምህረት ዝማሬ አገልግሎት በመስጠት እንዳገለግል ብርታት ሞገስ ሆናኝ እያገለገልኩ እገኛለው ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤቴ እንኳን ለ60ኛ አመትሽ አደረሰሽ
    የታላቁ አባት -የሳዊሮስ ፍሬ
    እጅግ ደስ ይበልሽ- አብበሻል ዛሬ
    በእልልታ- እንዘምር ለስምሽ
    ለልጆችሽ- አንቺ ክብራችን ነሽ
ህዳር 7 ለኔ የቀደሙ ታላላቆቼን አገልጋዮች እንዲሁም አብረውኝ ሲያገለግሉ የነበሩ ህፃናት ማእከላዊያን ወንድም እህቶቼን ማገኝበት የአገልግሎት ጊዜአችንን ምናወሳበት  ልምድ ምንወስድበት ምንማማርበት ልዩ መርሀ ግብር ነውና በፍጹም አልቀርም

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Nov, 12:13


ተ ፈ ጸ መ ፡ ማ ኅ ሌ ተ ፡ ጽ ጌ
የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጉርጉር የሆነ ንጹህ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው እነሆ የተወደደ መልካም ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ የሰማይ የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በእቅፍሽ እንዲጠጋ በእርሱ አማጽኝ
እያልን የመጨረሻውን ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በአንድ ልብ በአንድ ቃል እኛ ምዕመናን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህን ሥርዓተ ማኅሌት የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤታችን እንደሚከተለው አዘጋጅቶ አቅርቧል ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

07 Nov, 18:45


የሰንበት ትምሀርት ቤታችንን አገልግሎት በተመለከተ አሁን #በማኀበረ #ቅዱሳን #ቲቪ መርሐ ግብር እየተላለፈ ነው እንድትመለከቱ ጋበዝናችሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 18:45


ሙሉቀን መለሰ እባላለሁ

የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ከወጣትነቴን ጀምሮ ተምሬ ያለፍኩበት አገልግዬ ያደግኩበት ቤቴ ነው። በዚህ በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውስጥ በመዝሙር ክፍል በሀዘንና ደስታ እንዲሁም በድራማና ስነ ጽሑፍ ክፍል አገልግያለሁ።
አሁን ላለሁበት ሕይወቴም ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከተችልኝ ፣ የተማርኩባት ፣ ያደግኩባት ፣ የተገለገልኩባት በውስጤ ያለች የእምነት ቤቴ ናት። ይህን መርሐ ግብር ያዘጋጃችሁ ለእናንተም ምስጋናየ ይድረሳችሁ።
 
እናም 60ኛ ዓመቷን በማክበሯ ፈጣሪን እያመሰገንኩ በዓሉን አሁን ካሉት አገልጋዮችና እኛም ካለንበት ተሰባስበን ለማክበር ኅዳር 7 አልቀርም።

ክብር ለተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት
ሙሉቀን መለሰ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 16:13


የጥሪው ካርድ ደርሶዎታል?

እንግዲያውስ በሰንበት ት/ቤቱ የንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ ወይም በቤተ መጽሐፉ ይሂዱና አሁኑኑ ይውሰዱ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 12:27


ለኅዳር - 7 ቀጠሮዎን ያስተካክሉ

ቅዳሜን ከሰዓት ከእኛ ጋር መሆንዎን አይዘንጉ!!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 11:47


ኃይለሚካኤል ዑስማን እባላለሁ

በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኅኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ ተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት ከ15 ዓመት በላይ አባል ስሆን የፊታችን ቅዳሜ ህዳር ሰባት 60ኛ ዓመቱን አብረን እንገናኝ ስል ጥሪዬን አስተላለፋለሁ ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 07:56


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
እነሆ የበዓሉን ሥርዓተ ማኀሌት ከሊቃውንቱ ጋር አብረን እናመሰግን ዘንድ እንዲህ አቀረብንላችሁ
ሰናይ በዓል🙏🏻

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 06:12


ዮሴፍ የሺወንድም እባላለሁ።

ወደ ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት  በጉብዝናዩ ወራት ነው ለመገልገል እና ለማገልገል የተጠራሁት።ከቀዳማይ እስከ ራዕባይ ክፍል ትምህርት ተከታትያለሁ ይህም መዝሙር ክፍል ,ምግባር ሰናይ ክፍል , ፅዳት ክፍል ,የነዳያን መርሀ ግብር እና ሌሎችም አገልግሎች በረከት አሰገኝተውልኛል በትዳርና በልጆች ተባረካለሁ።እንኳን 60ኛ ዓመት አደረሰን አደረሳችሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Nov, 19:53


https://vm.tiktok.com/ZMh4FQfje/
Download TikTok to enjoy more posts. This post is shared via TikTok: https://vm.tiktok.com/ZMh4FcYtQ/

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Nov, 14:38


ነጋሽ መሀተቡ እባላለሁ  
ሰንበት ት/ት ቤቴ የኔ የማንነቴ መሰረት የእውቀት ገበያዩም ናት ህዳር 7 በመገኘት 60ኛ አመቷን አከብራለሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Nov, 06:10


"እግዚአብሔር ተከተሉኝ ያለው ከእኛ የሚፈልገው እርዳታ ኖሮ ሳይሆን እሱን መውደዳችን ሙሉ ሰው እንደሚያደርገን ስለሚያውቅ ነው።"
                               ቅዱስ ሄሬኔዎስ
እኔ ዮሐንስ ደሳለኝ እባላለሁ።
ባለፉት 20 መልካም ዓመታት እግዚአብሔርን እንዳውቀው ለስሙ እንድዘምር በስሙ እንዳስተምር ሕይወቴ ሕይወት፣ኑሮዬን ኑሮ  ያደረገችልኝ የምኖርለት ዓላማ እንዲኖረኝ ያደረገችኝ እውቀትን ከምግባር ጋር ይዤ እንድሄድ ያደረገችኝ ተክለሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤቴ ናት ።
   ከእናት ልጅ በላይ በስስት የሚያዩ ወንድሞችና እህቶች ያሉባት፣ በሀዘንም በደስታም ቀድመው የሚደርሱ መልካም ሰዎች የሚፈጠሩባት ቤተክርስቲያንንም ሆነ ሀገር የሚወዱና የሚቆረቆሩ በነጻ ያገኙትን በነፃ መስጠት የሚችሉ የቤተክርስቲያን ልጆች የተሰበሰቡባት
ሰንበት ት/ቤት ናት።
     ማንኛውንም የቤተክርስቲያንን ልጅ ሰንበት ት/ቤት መጥቶ እንዲማር የምጋብዘው ያገኘሁትንና የሚያገኘውን ስለማውቅ ነው።
    እግዚአብሔርን በጽኑ የምለምነው እስከ ሽምግልና እስከ መጨረሻው እቅታ በቤቱ እንድተከል ወደኋላ እንዳላፈገፍግ፣ በያዝኩት እንድፀናና፣ በሰንበት ት/ቤቴ ውስጥ እየተማርኩና እያስተማርኩ እኖር ዘንድ ነው።
   እኛን ለዚህ ክብር ያበቃችን ሰንበት ት/ቤታችን 60ኛ ዓመትዋ ኅዳር 7 ስለሚከበር ሁላችሁም እንድትገኙ በትኅትና እጠይቃለሁ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Nov, 16:50


#የአፋልጉን_ማስታወቂያ

የሰንበት ት/ቤታችን አባልና የቀድሞ ሥራ አመራር የሆነችው የልዑል አባት ከቤት እንደወጡ ስላልተመለሱ ይህን መልእክት በመጋራት በፍለጋው እንድንተባበር በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
አቶ ታደለ ገብረመድኅን ሃይሉ ይባላሉ። እድሜ 77 አርብ 22/02/2017ዓ.ም. ጠዋት ከመኖሪያ ቤታቸው ሃና ፉሪ ኮንዶሚንየም እንደወጡ አልተመለሱም። በወቅቱ የለበሱት ልብስ ቡናማ ኮት፣ ባርኔጣና  ኤርገንዶ /ነጠላ ጫማ ሲሆን የእንጨት ከዘራም ይዘዋል።መታወቂያ ያልያዙና የመርሳት ችግር ስላለባቸው እባካችሁ አፋልጉን።
ቤተሰቦቻቸው (0946877789፣0913718151፣013613083)

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Nov, 04:02


ፍቅሩ ቁምቢ እባላለሁ

ሙሉ እኔነቴ የሰንበት ትምህርት ቤቴ ውጤት ነው።

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ሰንበት ት/ቤቴ ያደኩብሽ ፊደል ቆጥሬ ሀሁ የተማርኩብሽ፤ ክፉውን ከደግ የለየውብሽ፤ ትግስት ከትህትና ጋር የተማርኩብሽ፤ መከባበር ማክበር የሰነኩብሽ፤ እናት አባት እህት ወንድም ማክበርን ያየሁብሽ፤ ለስጋዪም ለነፍሴም ችግር መልስ የማገኝብሽ ቤተክርስቲያኔ ነሽ እና  ግርሞ ሞገስ ያለሽ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም  እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት #የተክለ_ሳዊሮስ_ሰንበት#ት/ቤት ተብዪ  የኖርኩብሽ ያለሁብሽ አሳዳጊዬ እናት ቤቴ እንኳን ለ60ኛ ዓመት አደረሰን አደረሳችሁ ።

ህዳር ሰባት አልቀርም በሰላም ያገናኘን።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Nov, 18:00


ይሁንሰላም አስራት እባላለሁ

ውለታሽን አልረሳውም !
በዚያች አዳራሽ በ90ዎቹ በፕሪፓራቶሪ ት/ቤት ግቢ ጉባኤ ተማሪነት የተጀመረው አገልግሎት እነሆ አሁን ላለሁበት መሠረት   የሆነችኝ የተክለሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት ነች ። ቤተክርስቲያንን ያወቅሁባት፣ አምላኬን የተረዳሁባት፣ እንደሰጠችኝ ያልሰጠኋት፣ ያለስስት እንደቸረችኝ ያልሆንኩላት፣ ነገር ግን በሄድኩበት የማነሳት የምዘክራት ሰ/ት/ቤቴ ውለታሽን አልረሳውም ። እነሆ 60 ዓመታትን በትውልድ ቅብብሎሽ፤ እግዚአብሔር ይመስገን ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Nov, 07:25


ቀለሙ እጅጉ አባላለሁ

እንኳን ለሰንበት ትምህርት ቤታችን 60ኛ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሰን እግዚአብሔር ቢፈቅድ ህዳር 7 ቀን በፍቅር እንገናኛለን የዚያ ሰው ይበለን  አሜን

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Nov, 03:46


ኅዳር -7 አልቀርም
 ዘማሪት ሰርካለም ታምራት እባላለሁ

ወደ ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በልጅነት እድሜ ነው የተጠራሁት  ማዕከላውያን እና ወጣት ክፍል ላይ በኪነጥብ ክፍል ለረጅም ግዜ ደገሞ በመዝሙር አስጠኚነት አገልግያለሁ  እጅግ መልካም ዘመናትን በአገልግሎ አሳልፊያለሁ ።
የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ለእኔ ሰው እንድሆን  እናት ቤተክርስቲያኔን እንዳውቃት ሀገሬ ኢትዮጵያን እንዳከበራት እግዘብሔርን መፍራት እና ትህዛዙን እንዳከበር አስተምራኛለች።
   ህዳር 7 እግዚአብሔር ፈቅዶ ሁላችንንም ያገናኝን!!!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Oct, 18:29


ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚያም ዲያቆን ሆኖ ተሾሟል፤ ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ገማልያል በተባለ መምህር ትውፊትን፣ ኦሪትንና ነቢያቱን ተምሯል፡፡ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስብከት ወቅትም እርሱ በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ፤ ደቀ መዝሙሩም ሆነ፤ ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አደረገው፤ አጋንንትም ተገዙለት፡፡ (የሐዋ.፭፥፴፬፣፮፥፭-፲)

በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት መካከል የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትም ወንግልን ሰብኳል፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ፈተና ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰባት ዲያቆናት ሲመርጡ አንዱ እርሱ ነበር፡፡ የስድስቱ ዲያቆናት አለቃና የስምንት ሺህ ማኅበር መሪ ሆኗል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህውን ማኅበረ እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት እየጠፋች ወንጌል ደግሞ እየሰፋች ሄደች፡፡ (የሐዋ.፮፥፬)

ቅዱስ እስጢፋኖስም የእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል ያደረበትና ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ታምራትን የሚያደርግ ሰው ስለነበር በዚያን ጊዜ አይሁድ በምቀኝነት ተነሡበት፤ ከእርሱ ጋርም ክርክር ገጠሙ፤ ነገር ግን ሊያሸንፉት አልቻሉም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበታልና በፈጣሪ ኃይል አሸነፋቸው፡፡

ከዚህም በኋላ በሐሰት ምስክር ‹‹ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› በማለት ወነጀሉት፤ እርሱ ግን ስለ እውነት መሰከረ እንጂ በጀ አላላቸውም፤ ሊቀ ካህናቱም በጠየቁት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር አምላኩ መሰከረ፤ በመጨረሻም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ፡፡ አባቶቻችሁ ከነቢያት ያሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፡፡ በመላእክትም ሥርዐት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም፡፡›› በዚህም ተበሳጭተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ በዚህም ምስክሩን ፈጽሞ የሰማዕታት አክሊልን በጥር ፩ ቀን ተቀዳጅቷል፤ በዚህም ቀዳሜ ሰማዕታት ይባላል፡፡(የሐዋ. ፯፥፶፩-፶፫)

አይሁድ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለማጥፋት ቀንተው ሲገድሉት ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ክርስትናን ለማጥፋት እነርሱን ሰበብ አድርጎ ለሞቱም ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ክርስትናን ለማጥፋት ጠላት በሰዎች ላይ እያደረ ክርስቲያኖችን ያስገድላል፤ ያስጨፈጭፋል፤ እንዲሁም ያሳድዳል፡፡ በየጊዜውም በተለያዩ ክፍለ ሀገራት በጅምላ የሚጨፈጨፉት ሕፃናት፣ አረጋዊያን እንዲሁም ወጣቶች ምንም በማያውቁት ምክንያት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመናገራቸው ሳቢያ፣ ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓላትን በማክበራቸውና ባህላቸውን ለማስጠበቅ በመፈለጋው ብቻ ነው፡፡ እነዚህ እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የጠላት ተገዢ ከመሆናቸው ባሻገር ለራሳቸውና ለሌሎች ጥፋት መንሥኤ በመሆናቸው እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሐሰተኞችን በመቃወም ለእውነት መመስከር ይገባናል፡፡ ለዚህም በሃይማኖት ጸንቶ መኖር ይጠበቃልና እንጽና!

የቅዱስ እስጢፋኖስ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Oct, 14:31


አቤኔዘር ገዛኸኝ እባላለሁ [አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ]

በተክለሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ለ6 ዓመታት በመማርና በሕጻናት እና ማዕከላውያን ክፍል ለሚማሩ በአባላትና ግንኙነት ክፍል ዋና ተጠሪ በመሆንም በአገልግሎት አሳልፌያለሁ።

ሰንበት ትምህርት ቤቴ አሁን ላለሁበት የእምነት ጥንካሬ እና ከሰዎች ጋር በቀላሉ ለመግባባት እንዲሁም ከአንዳንዶች ጋርም ስለ ሃይማኖቴ በእውቀት እንድመሰክር በቂ እውቀት አስጨብጣኛለች።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሕዳር 7 ለሰንበት ትምህርት ቤቴ 60ኛ ዓመት ልደቷን ለማክበር እገኛለሁ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Oct, 07:38


ሲስተር ደስታ ከበደ እባላለሁ

ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤቴ እንኳን ለ60 ኛ ዓመት አደረሰሽ። የእውቀት ቤቴ በሁለት በኩል የተሳለ ቢላ ሆነን እንድንኖር ያደረገችን እናታችን።

ለ75ኛ ዓመትዋም ያድርሰን። 

ኅዳር ሰባት ቀን እንኳን መቅረት ማርፈድ በማይቻልበት ቀን ለመገናኛት ያብቃን

ኅዳር 7 እመጣለሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Oct, 06:04


በዚህ በዘመነ ጽጌ መከራዋንና ልቅሷን የሚያወሳ ‹ ሰቆቃወ ድንግል › የሚል ድርሰት ከማኅሌተ ጽጌ ጋር አብሮ ይዘመራል ፤ ‹ ሰቆቃወ ድንግል › ማለት የድንግል ልቅሶ ሰቆቃ ማለት ነው :: ››

እመቤታችን በልጇ ምክንያት ብዙ መከራ አይታለች ፤ በተለይ በስደቷ ወራት እንደዚህ ነው በማይባል በቃል ሊገለጥል በማይችል መሪር ዕንባ አፍሳለች ።

ሰቆቃወ ድንግልን የደረሰው አባ አርከ ሥሉስ የሚባል መናኝ ሊቅ እንደሆነ ሊቃውንት ይናገራሉ አባ አርከ ሥሉስ እመቤታችን በሦስት ዓመት ከመንፈቅ ውስጥ በስደቷ ወራት የደረሰባትን ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራ የዘገበበት ቅኔ ለበስ ምስጋና ነው ፡፡

‹‹ መከራሽን ስቃይሽን ምነው ለእኔ ባደረገው ›› እያለ በመከራዋ ለመሳተፍ በመመኘት ለእመቤታችን ያለውን ልባዊ ፍቅሩንና አክብሮቱን የገለጠበት አሳዛኝና መሳጭ ድርሰት ነው ::

አባ አርከ ሥሉስ በስደቷ ጊዜ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክቶ ‹ ሰቆቃወ ድንግል › በሚለው ድርስታቸው እንዲህ አለ ‹‹ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ፤ ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ቀርቶ ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር ። ›› በማለት መከራዋ እንዲህ ነው የማይባል በቋንቋ የማይገለጥ ጽኑዕ እንደነበር ተናግሯል ።

ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ ከሀገርሽ ከይሁዳ ወጥተሽ እንደ ጠፋች በግ በምድረ በዳ በተቅበዘበዝሽ ጊዜ ከጽጌ ረዳ አበባ ይልቅ የሚቀላ የፈትሽ ደም ግባት በቀን ሐሩርና በሌሊት ቁር ጠቆረ ። ጡቶችሽ በበጋ የፀሐይ ሐሩር ደረቁ ፤ ሕፃንሽ ወተትን አጥቶ በለቅሶ እስኪጮኽ ድረስ ያን ጊዜ የምታጠጪው እፍኝ ውኃ አላገኘሽም ። ሆድሽ መብልንና መጠጥን በማጣት ተጣበቀ ፣ ብርቱ የኾነ መንገድን በመኼድ የለመለሙ እግሮችሽ ተንቋቁ ተላላጡ ጉልበቶችሽ ከረኀብና ከጥም ብዛት የተነሣ ደከሙ ። ›› ሲል ስለመከራዋ ጽናት መሪር ስለነበረው ልቅሶዋ ተናግሯል ፡፡

ስለሆነም የእመቤታችንን መከራና እንግልት ስደቷን እያሰብን በሥርዓተ ማኅሌቱ በአንድ ልብ በአንድ ቃል እኛ ምዕመናን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህን ሥርዓተ ማኅሌት የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤታችን እንደሚከተለው አዘጋጅቶ አቅርቧል ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Oct, 04:16


ስመኝ ወ/ዮሐንስ እባላለሁ

ክርስትና ተነስቼ ያደኩባትና የተዳርኩባት ደብራችን ማ/ስ/ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እና ሰንበት ት/ቤቴ በሕይወቴ እጅግ ልዩ ትርጉም አላቸው። ከሕጻንነ ጀምሮ በቃለ እግዚአብሔር ኮትኩታ በምግባር አንጻ ቤተክርስቲያን ማፍቀር: ሰውን መውደድና ለሥራ መትጋትን ያስተማረችኝ የዛሬ ማንነቴ ያሠመረችልኝ ሰንበት ት/ቤት ናት።

በሰንበት ት/ቤቴ በሕጻናት ክፍል በኪነጥበብ ክፍል ተውኔትና ሥነጽሑፍ በወጣት በትምህርት እና በአባላትና ግንኙነት ውስጥ በተለያዩ ንዑስ ክፍላት እንዲሁም በትምህርት ክፍል፣ በከፍተኛ ት/ት ማስተባበሪያ፣ በምግባረ ሰናይ ክፍላት በሰብሳቢነት ኋላም dየሰ/ት/ቤቴ ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን ፍቅረ ቢጽንና ቤተክርስቲያንን ማወቅ ከታላላቆቼ እየተማርኩ ያቅሜን በአገልግሎት ተሳትፌያለሁ። በተጨማሪም ሰ/ት/ቤታችንን በመወከል በደብራችን በቴክኒክ ኮሚቴ በሙያዬ በጥቂቱ አገልግያለሁ እጅግም የብዙ ብዙ በረከት ተቀብያለሁ አሁንም በሕጻናትና ማዕከላውያን ክፍልና በታዘዝኩበት ላይ እሳተፋለሁ።
በሰንበት ት/ቤቱ  አገልግሎት ተሸናፊ የዱላ ቅብብል ተጫዋቾችን ይመስል በ60 ዓመታት የሚጠበቅብንን ፍሬ ያላፈራን ለፊዎች ብንሆንም፡ ተጨማሪ የቤተክርስቲያን ወገን የሚሆን ትውልድ የምናፈራበት ዘመን እንዲሰጠን ይህችን ዓመት ጨምርልን በማለት ሁላችንም በያለንበት ሰ/ት/ቤታችንን በጸሎት እንድናስባት አደራ እላለሁ።

ኅዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም. እናታችን ቤት በቸር ያገናኘን!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 18:52


ዜና ዕረፍት

የሰንበት ትቤታችን  አባል የሆነችው  እህታችን  ገነት አሻግሬ  ወንድሟ  በዛሬው ዕለት ስላረፉ ነገ ማለትም  ቅዳሜ በማኅደረ ስብሐት ቅድሰት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በሚካሄደው የቀብር ስነ ሥርዓት ላይ እንድንገናኝ ይሁን

የቀብር ሰዓት 9:00 ሰዓት
የቀብር ቀን ቅዳሜ 16/02/2017 ዓ ም
የቀብር ቦታ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ
የመኖሪያ አድራሻ  የቀድሞ ካርል አደባባይ
ቴሌ ፊት ለፊት 
የማጽናኛ መርሐ ግብር እሑድ በ17 2017ዐ.ም. ይካሄዳል።
ስልክ ቁጥር 0972222604

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 17:51


.               ሆነልኝ ይመር  እባላለሁ

ሰንበት ት/ቤቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ማለትም ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ እያስተማረችኝ በሰርዓተ ቤተክርሰቲያን  ያደኩባት ተክለ ሳዊሮሰ ቤቴ ናት ።

በሰንበት ት/ቤት ቆይታዬ  በአባላትና ግንኙነት ክፍል ፣ በቤተ መፃሐፍት (ሲጀመር በማደራጀት) እንዲሁም በኪነጥበብ ክፍሉ  በፀሐፊነት  በመዝሙር ክፍል በኮሚቴ  በመሳተፍ የድርሻዬን አበርክቻለሁ ። አሁንም ደግሞ ሰንበት ት/ቤቴን ለማገልገል በተቻለ መጠን ለማገልገል እጥራለሁ ።
ከእኞ ጋር በቀደመው ግዜ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ሲጀመር የነበሩ አባላትን ለማየት በጣም ጓግቻለሁ

የ60ኛ አመት ልደቷን ለማክበር ኅዳር 7 እገኛለሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 14:37


ሕዳር - 7 አይቀርም
    ሙሉዓለም እሸቱ እባላለሁ
በተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት በህፃናት, በማዕከላዊያን እንዲሁም በወጣት እድሜዬ በዋናነት በመዝሙር ክፍል እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ በውስጥ ግንኙነት ክፍል አገልግያለው
  አሁን ላለሁበት ጊዜዬ ማንነቴ እኔነቴ የተመሰረተው በሰንበት ት/ቤቴ ባገኘሁት የመገልገል ዕውቀት ነዉ በውጪውም አለም ማለትም ከሰ/ት/ቤት ውጪ ባለኝ ግንኙነት የመግባባት,የመረዳት ,የመሰማት ሞገስ, ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ የሆኑ ማንነትን እንዳልደፍር ገደብ እንዲኖረኝ በልጅነት የተቀረፀ ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን እውቀቶችን አግኝቻለው በመጨረሻም በትዳር በልጆች  የመባረክ በመልካም እህት ወንድሞች የመከበብ የህይወት ትርጉም እንዲኖረኝ የተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤቴ የእምነት መሰረቴም ናት። የሰ/ት/ቤቴን 60ኛ ዓመት ለማክበር በመብቃቴ እድለኛ ነኝ የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆኖ ለመገናኘት ያብቃን ህዳር -7 በፍፁም አይቀርም!!!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 11:44


ዲ/ን አሸናፊ ጌታቸው እባላለሁ

በተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በእግዚአብሔር ቸርነት  ከአገልግሎት ማዕዱ በረከት ተቋዳሽ ነኝ ። ሰንበት ትምህርት ቤቴ ስለ እምነቴ የተማርሁባት ,ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ትውፊቷን ያወቅሁባት , በእምነትም በህይወትም የቀኑ እና የተመሰገኑ ወንድሞችን እና እህቶችን ያገኘሁባት ቤቴ ናት። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ኅዳር ፯  ተገናኝተን ፷ኛ ዓመት የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የምስረታ በዓል እናከብራለን እግዚአብሔርንም እናመሰግናለን ።

ኅዳር 7 እመጣለሁ!!!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 08:01


ዘለቃሽ ወ/ሚካኤል (ዜድ) እባላለሁ

በተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ማገልገል ከጀመርኩ ረዥም ጊዜ ሆኖኛል። የአውደ ምሕረት ጉባኤ ከእናቴ ጋር ስካፈል ማስታወቂያ ሰምቼ ነው ሰንበት ት/ቤት የተመዘገብኩት ከዛም እስከ ራብዓይ ተምሬ ተመርቄአለሁ። በሰንበት ት/ቤት ቆይታዬ በአርድእት ክፍል በምግባረ ሰናይ ክፍል አገልግያለሁ እንዲሁም በማኅቶተ ሕጻናት ረዳት መምህርት በመሆንም አገልግያለሁ። የሰንበት ት/ቤቴ 50ኛ ዓመት ሲከበር ትጉ አገልጋይ እኔ ነበርኩ የተሸለምኩት። ሰንበት ት/ቤቴ በተለየ መልኩ ለኔ መኖሪያዬ አምላኬን መገናኛ የነፍሴን እረፍት ማግኛ ብዙ ወዳጅ ያፈራሁባት ከዓለም ፈተና የምድንባት መሸሸጊያዬ ናት። 60ኛ ዓመቷን ከበፊት አገልጋዮች እና አሁን ካሉት አገልጋዮች ጋር በመሆን ለማክበር ተዘጋጅቻለሁ።

ኅዳር 7 እመጣለሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 07:01


በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት pinned «ሰላም ውድ የትክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት አባላት ኅዳር - 7 2017 ዓ,ም, ለሚኖረን ጉባኤ ይህ መጠይቅ ይጠቅመናልና በመሙላት ይተባበሩን።

፨ ኅዳር- 7 በሚካሄደው የሰንበት ት/ቤታችን የ60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ልዩ ጉባኤ ላይ ይመጣሉ?
»

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 04:13


ከልጅነት አንስቶ እስከ ጉልምስና
እየመገብሽ ያሳደግሽኝ የዕውቀትን መና

የተሸሸግሁብሽ ከዓለሙ ክፋት
በጉዞዬ ሁሉ የጠበቅሽኝ ከእንቅፋት

ቀዳማይ ፣ ካልዓይ ፣ ሣልሳይ ፣ ራብዓይን የቆጠርኩብሽ
ምሥጢራቱን ፣ ሥርዓቱን ፣ አንድምታውን ያወቅሁብሽ
እርስ በእርስ መፋቀርን በአግባቡ ተማርኩብሽ

መቅደሱንም አሳየሽኝ
ቅዳሴውን ማሕሌቱን ሰዓታቱን ቁም እያልሽኝ
ስደክም የሚያበረቱ እህት ወንድሞችን ሰጠሽኝ

አመሰግንሻለሁ እናቴ
በኮልታፋ አንደበቴ
የመንገዴ አመላካች የማንነት መሠረቴ

ጊዜ ልጓም የለውም ይነጋል ደግሞም ይመሻል
ውጣና ውረዱን አልፈሽ ዛሬ እኔ ጋር ደርሰሻል
በሳዊሮስ ስም ተተክለሽ በማኅደረ ስብሐት ጸድቀሻል
በብዙ ተጋድሎና ትጋት ስድሳኛውን ዓመት ደፍነሻል

እኔም  ከታላቆቼ አደራውን ተቀብያለሁ
ኅዳር ሰባትንም ደግሞ አልቀርም ቃል እገባለሁ
ሌሎች መርሀ ግብራትም አሉ በንቃት እሳተፋለሁ

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Oct, 19:05


ሄኖክ ፀጋዬ እባላለሁ

በቅድሚያ ለሰንበት ት/ ቤታችን 60ኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ ሰንበት ት/ቤት የተቀላቀልኩት በልጅነት እድሜዬ ነው በህፃናት መዝሙር ክፍልና ብዙውን ጊዜ ደግሞ በኪነጥበብ ( በድራማ ክፍል) ከምወዳቸው ወንድሞቼ ጋር አገልግያለሁ ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በድራማው ገኖ የታየበት ወቅት ነበር መቼም የልደትን ድራማ ያየ የማያስታውስ አይኖርም በተለያዩ የአዲስ አበባ አድባራት አውደ ምህረት ላይ ሳይቀር ተዘዋውረን አገልግለናል በህይወቴ ትልቁን ነገር ያገኘሁበት ቤቴ ነው ነፍሱን ከቅዱሳኑ እቅፍ ያድርገውና አባቴ አብርሽንና እስካሁንም አብረውኝ ያሉ ወንድሞቼን ያገኘሁበት ቤቴ ነው በነፍስ ብቻ ሳይሆን በስጋም ብዙ ነገር ያገኘሁበት መሰረቴ ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ነው ታዲያ ይህን ሁሉ ያገኘሁበትን እስከዛሬም ከቤቱ እንዳልጠፋ መሰረት የሆነኝን እንዴት ልረሳ እችላሁ ህዳር 7/2017 እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በፍፁም አልቀርም ለቀኑ ያብቃን በድጋሚ ለ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Oct, 16:10


ታምራት ደጀኔ እባላለሁ

የተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት ለእኔ ማንነቴ ናት ሌላ ማንነት የለኝም ከህጻንነት ጊዜ ጀምሮ በህጻናት ክፍል፣በማዕከላውያን እንዲሁም በወጣት ክፍል በተለያዩ አገልግሎቶች በልደትዬ ቤት ኖርያለሁ። በሱስና በተለያዩ የኃጢአት ወጥመዶች የምንፈተንበትን የእሳትነት እድሜዬን ሰ/ት/ቤቴ ሽፍን፣ክልል አድርጋ አሳልፋኛለች በታዳጊ ክፍል በስነ-ጽሑፍና መዝሙር በወጣት ክፍል በአዲስ አባላት ተቀባይና በውስጥ ግንኙነት  በሰብሳቢነት ፤በመርሐግብር ዝግጅት፣በሀብት አስተዳደር እና  በልማት ክፍላት በጸሐፊነትና በሥራ አስፈፃሚነት አገልግያለሁ አሁንም እያገለገልኩና እየተገለገልኩኝ ነው።

ሰ/ት/ቤቴ ማንነቴን የሠራች፣አስተሳሰቤን የቀረጸች መጪውን ዘመን የምታመለክተኝ መንገድ መሪዬ ናት ስለሆነም 60ኛ ዓመቷን ስታከብር እገኛለሁ።

ኅዳር 7 እመጣለሁ