ክፍል ( 2 )
፨ መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በተለያዩ ስሞችና ምሳሌዎች ተገልጿል ። ከእዚህ መካከል ጥቂቶቹን በዝርዝር እንመልከት ፦
1/ መንፈስ ቅዱስ ፦ መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል
፨ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥመቁ ዩሐንስ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ በወረደ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ሊመሰክር ተገለጠ ።
" ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ። መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ።"
ዮሐ 1:32)
2/ መንፈስ ቅዱስ ፦ የእግዚአብሔር መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል ።
፨ ሐዋሪያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጆችን ባህሪና የሕይወት ዘይቤ ለመግለፅ በጻፈው መልዕክቱ ላይ መንፈስ ቅዱስን "የእግዚአብሔር መንፈስ " በማለት ገልጿል ። የአማኞች ወይም የእግዚአብሔር ልጆች መለያቸው በመንፈስ ቅዱስ መመራታቸው ነው ።
" በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።" ሮሜ 8:14)
3/ መንፈስ ቅዱስ ፦ የጌታ የክርስቶስ መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል ።
፨መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ መንፈስ ነው ። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው የመንፈስ ቅዱስን ሙላት አልተካፈለም ማለት ነው ። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አማኞች የክርስቶስን ባህሪ እንዲላበሱ እርሱን እንዲመስሉ ያደርጋል ።
" የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።" ሮሜ 8:9
" ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።" 2ኛቆሮ 3:17
4/ መንፈስ ቅዱስ ፦ የእውነት መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል።
፨ የመንፈስ ቅዱስ አንዱና ትልቁ ስራው አማኞችን ወደ እውነት መምራት እና ክርስቶስን እለት እለት በሕይወታቸው መግለጥ እንዲሁም እርሱን መተረክ ነው።
" ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤" ዮሐ 15:26)
5/ መንፈስ ቅዱስ ፦ አጽናኝ ተብሎ ተጠርቷል።
በዚህ አለም ክርስቶስ መስሎ መኖር ምንም ከባድ ቢሆን እንኳ የተቀበልነው መንፈስ ሁሉን የሚያስችል ከሁኔታዎች በላይ ሆነን እንድንኖር አቅም የሚሰጥ ነው ። በሚገጥመን መከራ ሁሉ የሚያጽናና ፣የሚያስተምር ታላቁ ተፋችን የሆነውን እመጣለው ያለንን ጌታ ኢየሱስን እንድንጠብቅ የሚያሳስበን መንፈስ ቅዱስ ነው ። መንፈስ ቅዱስ ያላፅናናው በምንም አይፅናናም !
" አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።" ዮሐ14:26)
6/ መንፈስ ቅዱስ ፦ በርግብ ሀምል ተገልጧል።
፨ እግዚአብሔር እንድንከተል፣እንድንሰማው ያዘዘን ኢየሱስን ብቻ ነው ።
ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ። ማቴ 3፥16-17
7 / መንፈስ ቅዱስ ፦ በእሳት ሀምል ተገልጧል።
" እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤" ማቴ 3:11
እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። ሐዋ 2፥3-4
8 / መንፈስ ቅዱስ ፦ በነፋስ ሀምል ተገልጧል።
" ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።"
ዮሐ 3:8
9 / መንፈስ ቅዱስ ፦ በእግዚአብሔር ጣት ተገልጧል።
" እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።" ሉቃ 11:20
" እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።" ማቴ 12:28
10/ መንፈስ ቅዱስ ፦ በእግዚአብሔር እስትንፋስ ተገልጧል።
በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥
በቍጣውም መንፈስ ያልቃሉ። ኢዮ 4፥9
@gospelisjesua
@pastorayalew