የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) @ethzema Channel on Telegram

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

@ethzema


ኢዜማ ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎች መብት የተከበረባት፣ ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ሰላማዊ እና የበለፀገች ሀገር እንድትሆን የሚሠራ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነው።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) (Amharic)

ኢዜማ የሁሉም ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ወደ ማኅበረሰብ እና ለሌሎች ፊልምግንሽንስ ወደ ሡ፡ጊኒፉልናይሊንክ በተመሳሳይ ማህበረሰብ አሉት። በእዚህ መሠረት ዜጎችን ወደ ማኅበረሰብ እንዴት ማገልግ ይችላሉ? ለአሁኑ ኢዜማ ኢትዮጵያ የድሮ የቴሌገርልድ አዳዲስ ዜጎችን ሊሞክ የሚችል እና ከልክ፣ ከፍላጎች፣ ከመድላትና ከቅ። እንቅስቃሴ ተገኝታ ይኖርብናል። ለአሁኑ ኢዜማ በዚህ ቅ። ተጨማሪ ዜጎችን ለመዳን የሚገባልን እና እንደሚታዘዙበት ለመስማት። እንደዚህ እንሴንፕዉሽሬ ለማቀበር ይህን ቅ። ቴሌገሪልᏴክ እዚህ ይጫኑ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

08 Feb, 04:30


የመርኃግብር ማስታወሻ!!

የውይይት መድረክ

የመወያያ ርዕስ: አሁናዊ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት በኢትዮጵያ

የመነሻ ሐሣብ አቅራቢ: ዶ/ር ዳዊት በለው (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ ) ፖሊሲ ጥናት እና ምርምር መምሪያ ኃላፊ)

ቀን: ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 01/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00 ሰዓት

ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

04 Feb, 09:01


የ #ኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በዝክረ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ መርኃግብር ላይ የነበራቸውን ወዳጅነት እንዲህ አስታውሰዋል፤ እንዲሁም በዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ አጭር የሕይወት ታሪካቸው ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

01 Feb, 14:04


ዝክረ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ መርኃ ግብር ተከናወነ
የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት የተገኙ ሲሆን የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በመርኃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም የኢዜማ አካዳሚ መፅሐፍ ቤትን ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ ቤተ- መፅሐፍት ተብሎ እንደሚሰየም አሳውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

01 Feb, 05:12


የመርኃግብር ማሥታወሻ!

ዝክረ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ

ቀን: ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00

ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

30 Jan, 04:55


https://youtu.be/gWWKICB7-wk?si=-PxYWsaWBenFIhSN

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

22 Jan, 04:49


የመርኃግብር ማሥታወሻ!!

የበይነ መረብ ውይይት ከ #ኢዜማ አመራሮች ጋር

በቀጣይ ስለሚኖረው ሀገራዊ ምርጫ
አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን (የኢዜማ ም/መሪ)

በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ

አቶ ኢዮብ መሣፍንት (የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ)

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ)

ቀን: January 25/2025 (ጥር 17/2017 ዓ.ም.)

ሰዓት: ከምሽቱ 2:00

በአሜሪካ፣ ካናዳ እና አከባቢዎቹ: 12:00 PM ET / 9:00 AM PT

በአውሮፓ: 18:00

Zoom Meeting ID: 816 5104 2191
Passcode: 314670

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

18 Jan, 05:52


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ እና ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

13 Jan, 04:34


"“መንግሥት ሰላምን የሚያረጋግጥ የፖለቲካ መፍትሄ መፈለግ አለበት”

ሐሮሌ ዮሴፍ (የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል


በኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የምትዘጋጀው የዜጎች ልሳን መጽሔት ቅጽ 02_ቁ: 09 ትኩረቷን በሰላም ላይ አድርጋ የተሠናዳች ሲሆን የወሩን እንግዳ ጨምሮ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ታሥነብበናለች፤ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ሙሉውን ይዘት ያንብቡ።

https://drive.google.com/file/d/12de9lx4BgvoqpdLfzEW40cECS8s_WK9V/view?usp=drivesdk

#ኢዜማ
#የዜጎች_ልሳን

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

09 Jan, 16:40


የፕሮፌሰር በፍቃዱ ቀብር ነገ ቀን በዘጠኝ ሰዓት ቀራንዩ መድሀኒዓለም ነው።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

09 Jan, 14:26


በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል 24 አባል የሆኑት ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ጥር 01/2017 ዓ.ም. በሞት ተለይተውናል፡፡
ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ ከፓርቲው ቅድመ ምሥረታ አንስቶ በኢዜማ ፖሊሲዎች ዝግጅት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉ እንዲሁም በሀገር አቀፉ የ 2013 ምርጫ ኢዜማን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መወዳደራቸው ይታወቃል።
በአባላችን ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እና ጓዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

07 Jan, 03:34


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

15 Dec, 17:47


የኢዜማ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ግርማ ሰይፉ የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በስኬት እያከናወኑ ነው።

ግርማ ሰይፉ ይመሩት የነበረው የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት የዘንድሮው የኢትዮጵያ የጥራት ድርጅት ተሸላሚ በመሆን በትናንትናው እለት በቤተመንግሥት በተካሄደ ሥነሥርዓት ላይ የሪፐብሊኩ ፕሬዝደንት በተገኙበት የከፍተኛ አድናቆት ሠርተፊኬት ተቀብሏል:: ይህም የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በውጤታማነት እየተወጡ መሆኑን ያመለክታል።

ግርማ ሰይፉ የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በስኬት፣ በሕግ አግባብ እና ከሌብነት በፀዳ መልኩ እየተወጡ በመሆኑ ኢዜማ ያለውን አድናቆት እየገለፀ፤ አሁን ኃላፊነት በተቀበሉበት የከተማ ውበትና አረንጏዴ ልማት ቢሮ የህዝብ እና የሀገርን ጥቅም ባስከበረ መልኩ በተለመደው ትጋትዎ እንዲያገለግሉ መልዕክቱን ከአደራ ጋር ያስተላልፋል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

04 Dec, 15:36


የዓለም አጠቃላይ ሁኔታ እና የሀገራችን ፖለቲካ (የውይይት መነሻ ሐሣብ በ #ኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ) ክፍል 2

https://youtu.be/GLoXLNU1g2A?si=LJrwLPFf0RHSyA87m

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

30 Nov, 08:47


ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም. መደረግ የጀመረው የኢዜማ የተለያዩ አመራሮች ውይይት በዛሬው ዕለት መደረጉን የቀጠለ ሲሆን የኢዜማ ድርጅታዊ ቁመና በሚል ርዕስ የፓርቲው ም/መሪ ዮሐንስ መኮንን የውይይት መነሻ ሐሣብ እያቀረቡ ይገኛሉ።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

28 Nov, 04:30


የኢትዮጵያ ሀገራችን ታሪክ መጥፎም ይሁን ጥሩ የሁላችንም ታሪክ አካል መሆኑን እንቀበላለን፡፡

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

27 Nov, 04:30


የ #ኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ክፍል 2 ይመልከቱ።

https://youtu.be/1wxYLYY1cZw?si=Qt2uvint7MPL2eSz

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

23 Nov, 09:35


ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም. መደረግ የጀመረው የኢዜማ የተለያዩ አመራሮች ውይይት የሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ዕይታ በሚል ርዕስ በዛሬው ዕለት መደረጉን የቀጠለ ሲሆን የመነሻ ሐሣቡን የፓርቲው የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ግርማ ሰይፉ እያቀረቡ ይገኛል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

23 Nov, 06:01


ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም. ሀገር፣ ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ በሚል ርዕስ በፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መነሻ ሐሣብ አቅራቢነት የተጀመረው ተከታታይ ውይይት በተመሣሣይ የብሔራዊ ሥራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ብሔራዊ ኦዲት ኮሚቴ፣ የሕገ ደንብ ተርጓሚና አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ የትይዩ ካቢኔ አባላት እና የመምሪያዎች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዛሬ ሕዳር 14/2017 ዓ.ም. የሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ዕይታ በሚል ርዕስ ውይይቱ ቀጥሎ ይደረጋል።

የመጀመሪያውን የውይይት መድረክ መነሻ ሐሣብ ክፍል አንድን ለመመልከት የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) በመጫን ይመልከቱ።

https://youtu.be/-crxQBaJND8?si=XmhyPW0HrrKvIShc

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

19 Nov, 08:36


ኢትዮጵያን እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር እስከተቀብልን ድረስ አንድ ሕዝብ ያደርገናል፤ የቋንቋና የባሕል ብዝኃነታችን ደግሞ የብዙ ማኅበረሰቦች ሀገር ያደርገናል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

14 Nov, 04:40


ዜግነትን መሠረት ባደረገ ሀገራዊ ዕይታ አንፃር ሲታይ፤ #ኢዜማ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሕዝብ ነው ብሎ ያምናል። ይኽ ሕዝብ በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በእምነቱ፣ በፆታው ወዘተ ሳይፈረጅ እያንዳንዱ ግለሰብ በዜግነቱ በአንድ ላይ ሲሰባሰብ  የፈጠረው ሕዝብ ነው።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

12 Nov, 08:59


#የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባለፉት 6 ዓመታት ሀገራችን ስላለፈችበት ፖለቲካዊ ሁነት ከሉዓላዊ ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ክፍል ሁለት (2) ቆይታ ይመልከቱ

https://youtu.be/bT6q1hkfS8E?si=f3wuwL0l_T3GMJyg

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

05 Nov, 08:26


አለመረጋጋት ምንጩ በጠራ የፖለቲካ መስመር ላይ መቆም ያልቻለው፤ አቋምም ሆነ አቅም የሌለው የብልፅግና አመራር ነው! ሲል መንግሥትን ተጠያቂ ባደረገበት መግለጫ አንስቷል።

በመቀጠልም የሥምምነቱ አንደኛ ዓመት መሙላት ተክትሎ ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም. አንድ ዓመት የሞላው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ከምን ደረሰ? ሲል ባወጣው መግለጫ “መንግሥት ከዚህ ቀደም ቅራኔዎችን በውይይት ለመፍታት ከተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ካደረጋቸው ስምምነቶችና የውይይት ሙከራዎች በተሻለ መልኩ የፕሪቶሪያው ስምምነት ለሕዝብ በይፋ የተገለጸ መሆኑ መልካም የሚባል ጅማሮ” መሆኑን ገልፆ “አፈጻጸሙ ላይ ግን በመንግሥት በኩል በታየ ዳተኝነት እና ግልጸኝነት መጉደል እንደ ሥምምነቱ መፈጸም አለመፈፀሙን፣ ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚያመላክቱ መረጃዎች በአግባቡ ሲቀርቡ አለመመልከታችን ሲብስም በተለያየ ጊዜ የሕወሓት አመራሮች በተለያዩ መድረኮች ላይ የሚያሰሙት  ግጭት ቆስቋሽ እና ተጨማሪ ውጥረቶችን የሚያጭሩ ገለፃዎችን መንግሥት ዐይቶ እንዳላየ በዝምታ ማለፉን እና ማብራሪያ አለመስጠቱ ስንመለከት ሥምምነቱ በተባለው መልኩ ከመፈጸም ይልቅ “በተቃራኒው እየሄደ ይሆን?” የሚያስብል ስጋት ውስጥ ይጥላል።” ሲል ስለ ሥምምነቱ ግልጽ መግለጫ እንዲሰጥ የጠየቀ ሲሆን መንግሥት በሆደ ሰፊነት እና ሥምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ነገሮችን አስገዳጅ እና በጥብቅ እንዳልሔደባቸው ባወጣው መግለጫ ገልጿል። 

ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም. የሕወሓት ታጣቂዎች በአላማጣ እና አከባቢው የኃይል እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ፓርቲያችን በደረሰው መረጃ መሠረት መንግሥት ጦርነት የሚጎስመውን የሕወሓት ስብስብ በፕሪቶሪያው ሥምምነት መሠረት ትጥቅ እንዲፈታ በማድረግ ሕግ እና ሥርዓት እንዲያስከብር በአፅንዖት እንጠይቃለን! ሲል ባወጣው መግለጫ “ዛሬም ይህ በክህደት ተወልዶ በክህደት ያረጀ ስብስብ ለሰላም የተዘረጋለትን እጅ በመርገጥ ለሥምምነት እግሩን እየጎተተ እያንዳንዱን ቀን በሴራ ሲያሳልፍ ተው ሊባል ይገባል፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩን ሙሉ ለሙሉ በሆደ ሰፊነት ለሕወሓት ለቀኩለት የሚለው ገዢው ብልጽግና ፓርቲም ይህን ባለ ማግሥት ውጤቱ ግን እንደታሰበው ለሰላም ሲሰራ ስለማይታይ በአስቸኳይ አማራጭ የማስገደጃ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ሊገነዘበው ይገባል” ሲል መንግሥት እንደሥምምነቱ አለመፈጸሙ የበለጠ አደጋ ይዞ እንደመጣ ለማሳወቅ ሞክሯል።

እንደ ሥምምነቱ አለመፈጸሙ ሌላው ይዞ የመጣው ችግር በመግሥት እና ሕ.ወ.ሓ.ት መካከል ሊፈጸሙ ሲገባቸው ያልተፈጸሙ ብቻ ሳይሆን በሕወሓት ባለሥልጣኖች መካከል ስለ ሥምምነቱ ያላቸው ምልከታ የተለያየ መሆን እና የሥልጣን ሽኩቻ የፈጠረው የእርስ በእርስ ግጭት በትግራይ ማኅበረሰብ እና በአከባቢው ላይ ሊያስከትለው የሚችለው ችግር ያሳሰበው ፓርቲያችን ነሐሴ 07/2016 ዓ.ም. የፕሪቶሪያው ሥምምነት አለመከበሩ ዛሬም ለዜጎች ስጋት መሆኑ ቀጥሏል! ሲል ባወጣው መግለጫ “በኢዜማ እምነት በተለይ የፕሪቶሪያው ሥምምነት በአግባቡ አለመከበሩ በክልሉ ለሚስተዋለው ሥር የሰደደ ስጋት፣ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም ይላል፡፡ የፕሪቶሪያው ሥምምነት በተያዘው ዝርዝር ዕቅድ መሠረት አለመፈጸሙን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የመሣሪያ አይነት እና ቁጥር በፖለቲካ ኃይሎች እጅ ባለበት ሁኔታ፣ የሀሳብ ልዩነትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በውይይት መፍታት በማይታወቅበት ብሎም መንግሥት እና ፓርቲ የመለየት ምንም የረባ ልምድ በሌለው ፖለቲካችን ውስጥ ሕዝብ የሚያስተዳድር ፓርቲ በውስጡ ያሉ መካረሮች ዳፋው ለሰፊው ሕዝብ እንደሚተርፍ ትላንታችንን ዞር ብሎ ማየት በቂ ነው፡፡” ሲል በተደጋጋሚ የፕሪቶሪያው ሥምምነት እንዲፈጸም ወትውቷል።

አሁንም መንግሥት ይሄንን ሥምምነት በቶሎ በመፈጸም የተከፈለው መሥዕዋትነት እውነትም ለሀገር አንድነት እንደሆነ እንዲያሳይ፣ እንደ ሥምምነቱ አለመፈጸም በትግራይ ክልልም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈጥረው ስጋት ቀሪ እንዲያደርግ እና የፕሪቶሪያ ሥምምነት ተደርጎ ሰላም ሰፍኗል ከሚል ባሻገር ሥምምነቱ መሬት ወርዶ የመከራው ቀጥተኛ ገፈት ቀማሽ ለሆኑት ወገኖቻችን የብርሀን ቀን እንዲወጣ የፌደራል መንግስቱ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ደጋግሞ ማሳሰብ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
ጥቅምት 26/ 2017 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

04 Nov, 14:30


#የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባለፉት 6 ዓመታት ሀገራችን ስላለፈችበት ፖለቲካዊ ሁነት ከሉዓላዊ ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ

https://youtu.be/Rif0U_sJrCs?si=vJ0AQUrIH_uuzxTk

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

04 Nov, 05:04


#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

29 Oct, 09:06


የ #ኢዜማ ግብ


በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት ተገንብቶ፣ የዜጎች ሉዓላዊነት የተረጋገጠበት፤ ዜጎች በቋንቋ፣ በዘር፣ በሐይማኖት፣ በፆታ ወይንም በማንኛውም የማንነት መገለጫ መድሎ የሌለባት፤ ለዜጎቿ ምቹ እና በሌሎችም
የምትመረጥ ሀገር ማድረግ ነው።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

25 Oct, 04:42


የ #ኢዜማ ርዕይ

“ኢትዮጵያ ሀገራችን የእያንዳንዱ ዜጋዋ ፖለቲካዊ፣ ሰብአዊ እና የምጣኔ ሀብት መብቶች የተከበሩባት፣ ማኅበራዊ ፍትሕ የሰፈነባት፣ በዜጎቿ ጽኑዕ አንድነት ማዕቀፍ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና እምነቶች ሳይበላለጡ በነፃነት የሚስተናገዱባትና የውበቷ መገለጫ ብቻ የሆኑባት፣ ሰላምና መረጋጋት የተረጋገጠባት፣ በላቀ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና የተጎናጸፈች፣ ሁሉም ዜጎቿ የሚኮሩባት ታላቅና ገናና ሀገር ሆና ማየት ነው።”

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

24 Oct, 15:05


"አሁናዊው የምሥራቅ አፍሪካ ጂኦፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ሚና"

👉 አቅራቢ: ኃ/መለኮት ተ/ጊዮርጊስ (የ #ኢዜማ ትይዩ ካቢኔ አባል)

👉 ቀን: ቅዳሜ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም.

👉 ሰዓት: ከቀኑ 8:00

👉 ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት

👉 አዘጋጅ: የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ

👉 ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

21 Oct, 04:35


የ #ኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በተለያዩ ወቅታዊ እና የፓርቲው ጉዳዮች ላይ ከአሻም ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገዋል፤ የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይመልከቱ

https://youtu.be/T17lZVp8Oec

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

18 Oct, 15:00


የ #ኢዜማ ም/መሪ ዮሐንስ መኮንን ሀገራችን በማካሔድ ላይ በምትገኘው የሀገራዊ ምክክር ሒደት ላይ ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ

https://youtu.be/HG8tLhJHE3s?si=z8oEvoX8HqoQZ-Dቆይታን

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

04 Oct, 15:16


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የኢሬቻ በዓልን ለምታከብሩ በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል።

partiin lammiilee itiyophiyaa haqaa hawaasummaaf lammiilee ayyaana irrechaa kabajaan hundaaf baga nagaan geessan jechaa ayyaanni kun kan nagaaf jalaala akka isiniif ta'u hawwina.

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

02 Oct, 08:42


ህዝባዊ በዓላት የፖለቲካ መድረክ ሊሆኑ አይገባም!

ፓርቲያችን #ኢዜማ በመርኆዎቹ ካስቀመጣቸው መሠረታዊ ሐሳቦች መካከል አንዱ “ኢትዮጵያ ልንንከባከበው የሚገባን ባለ ብዙ ባሕል፣ ታሪክ እና ቅርስ ባለቤት የሆነች ሀገር መሆኗን ከልብ እናምናለን” የሚል ነው። እነዚሕን ባሕል፣ ታሪክ እና ቅርሶች በተሻለ ደረጃ ለመጠበቅ ለማቆየት እና ለማጎልበት የመንግሥት፣ የማኅበረሠቡ እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት መሆኑን እና እነዚህም የጋራ ማንነት ለመፍጠር ያላቸውን አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ አንዳች ጥርጥር የለውም።

እነዚህ የጋራ ማንነትን በመፍጠር ሚናቸው ከፍተኛ የሆኑ ባሕሎችን በእኩል መንከባከብ እና ማሳደግ ተገቢ እና የሚበረታታ ነው። ነገር ግን ሀገራችን ባላት ስሁት ፌደራላዊ የመንግሥት ስሪትን በመንተራስ መሠል ባህሎችን የጋራ ማንነት ማጠንከሪያ ምሰሶዎች ከማድረግ ይልቅ የፖለቲካ ውግንና እና ትርፍ መሸቀጫነት ለማድረግ ሲሞከሩ ማየት የሚያሳዝን ነው፡፡ ልንከባከባቸው ልናሣድጋቸው እና በደማቅ ሁኔታ ልናከብራቸው ከሚገቡ ባሕሎች መካከል አንዱ በቅርብ ቀን የሚከበረው ኢሬቻ መሆኑን ኢዜማ ያምናል።

መንግሥት ከባሕል፣ ታሪክ እና ቅርሶች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዋነኛ ኃላፊነቱ የሆነውን እነኚህን ለማሳደግ፣ ለመጠበቅ እና ለማጎልበት የሚረዱ የሕግ ማዕቀፎችን እና ፖሊሲዎችን ማውጣትና መተግበር፣ ግንዛቤ መፍጠር እና ለቅርሶቹ አስፈላጊውን ጥበቃ ማድረግ እንዲሁም ባሕሎቹ ሲከበሩ ያለምንም ስጋት ተከብረው እንዲጠናቀቁ የጸጥታ እና ደኅንነት ሥራን መሥራት ብቻ ነው። ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይም ኢሬቻን በማክበር ሒደት በመንግሥት መዋቅሮች እና በመንግሥታዊ ኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ ባለሥልጣናት ባሕሉ ካለው ሕዝባዊ እሴት ባፈነገጠ መልኩ ባሕሉን ከሕዝቡ ባለቤትነት ነጥቆ ፖለቲከኞቹ ዋነኛ አጋፋሪ ሆነው መምጣታቸው በሌሎች ዘንድ የመገለል እና የስጋት ስሜት ይፈጥራል። ገዢው ፓርቲም በዚህ መልኩ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚመስል መልኩ መንቀሳቀሱ ተገቢ አይደለም ብለን እናምናለን።

በተለይ ለባሕሉ ተብሎ በተለያዩ አካባቢዎች ከተቋማት እና ከንግዱ ማኅበረሠብ በድጋፍ ስም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ደብዳቤ የንግድ ማኅበረሠቡን በሚያስጨንቅ እና ከአቅም በላይ የሆነ ከፍተኛ አስገዳጅ የገንዘብ መዋጮ መጠየቅ ማኅበረሠቡን ከፍተኛ ምሬት ውስጥ በመክተት ባሕሉን በስጋት እንዲመለከተው እያደረገ ይገኛል።

የባሕሉ ባለቤት የሆነው ሕዝብም ተቋማትን እና ግለሰቦችን አስጨንቃችሁ መዋጮ በመሰብሰብ በዓሉን አድምቁልኝ አይልም፤ ይህንንም ሕገወጥ ተግባር የሚጠየፈው መሆኑን አንዳች ጥርጥር የለንም። በመሆኑም የየትኛውንም ማኅበረሠብ ባሕላዊም ሆነ ሃይማኖታዊ በዓል ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ባሕሉን መበረዝ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ይህን መሰል የአደባባይ ክብረ በዓላት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት መጠቀምን ፓርቲያችን ፍፁም የሚያወግዘው ነው።

በመሆኑም በንግዱ ማኅበረሠብ ላይ እየተደረገ ያለውን ተጠያቂነት የሌለበት ሕገወጥ ጫናን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ ድርጊቶችን መንግሥት በቶሎ እንዲያቆም እያሳሰብን መንግሥት ባሕሎችን ጠንቅቆ ለሚያውቀው ማኅበረሠብ በመመለስ መሠረታዊ ስንል ከላይ የጠቀስናቸውን ኃላፊነቶቹን ብቻ በቅጡ እንዲወጣ እንጠይቃለን።

መስከረም 22/2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

28 Sep, 06:17


የመርኃግብር ማሥታወሻ!

"የኮሪደር ልማቱ ከከተማ ልማት እና ከሕግ አንፃር ሲዳሰስ"


👉 አቅራቢዎች:

ዮሐንስ መኮንን (የ #ኢዜማ ም/መሪ)

እዮዔል ሰለሞን (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ኃላፊ)

👉 ቀን: ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 18/2017 ዓ.ም.

👉 ሰዓት: ከቀኑ 8:00

👉 ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት

👉 አዘጋጅ: የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ

👉 ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

27 Sep, 14:15


የመርኃግብር ማሥታወሻ!

"የኮሪደር ልማቱ ከከተማ ልማት እና ከሕግ አንፃር ሲዳሰስ"


👉 አቅራቢዎች:

ዮሐንስ መኮንን (የ #ኢዜማ ም/መሪ)

እዮዔል ሰለሞን (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ኃላፊ)

👉 ቀን: ነገ ቅዳሜ መስከረም 18/2017 ዓ.ም.

👉 ሰዓት: ከቀኑ 8:00

👉 ቦታ: ስታዲየም አከባቢ በሚገኘው የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት

👉 አዘጋጅ: የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ

👉 ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

26 Sep, 15:11


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ)

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

25 Sep, 08:33


"የኮሪደር ልማቱ ከከተማ ልማት እና ከሕግ አንፃር ሲዳሰስ"


👉 አቅራቢዎች:

ዮሐንስ መኮንን (የ #ኢዜማ ም/መሪ)

እዮዔል ሰለሞን (የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ኃላፊ)

👉 ቀን: ቅዳሜ መስከረም 18/2017 ዓ.ም.

👉 ሰዓት: ከቀኑ 8:00

👉 አዘጋጅ: የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ

👉 ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

17 Sep, 07:40


የሐዘን መግለጫ

በፖለቲካው ዓለም እና በመምሕርነት ሙያ ለሀገራቸው አዎንታዊ አስተዋፅዖ በማድረግ የሚታወቁት የኢትዮጵያ ሶሻል ዴማክራቲክ ፓርቲ ሊ/መንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በዛሬው ዕለት መስከረም 07/2017 ዓ.ም. በሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ሰምተናል።

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ሀገር በጽኑ በምትፈልጋቸው ጊዜ ምሁራን እምብዛም በማይደፍሩት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስከመጨረሻው ሕቅታ ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በሚያምኑበት አስተሳሰብ ያገለገሉ ጉምቱ ፖለቲከኛ ነበሩ።

ፓቲርያችን #ኢዜማ በፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ሞት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለትግል አጋሮቻቸው በቶሎ መጽናናትን ይመኛል።

የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ