መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF @menzu_m Channel on Telegram

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

@menzu_m


ምንዳዬና ምንዳችሁ ይበዛ ዘንድ ወደዚህ ቴሌግራም ቻናል በገባችሁ ቁጥር በነብያችን(ﷺ) ላይ ሰለዋት አዋርዱ በብዕርህ✍️
መጣራት ባትችል በሰው ብዕር ተጣራ
ሰሉ ዐለ ነቢ💛

✍️Temam Al hadra

ለበለጠ መረጃ በዚህ አናግሩኝ
👇👇👇
@al_hadraw

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF (Amharic)

እንኳን ደህና መጣህ! ይህ ቴሌግራም ቻናል የሚሆን ነው በገባችሁ። መንዙማ ሀድራ ከ'እንቅስቃሴ' ማህበረሰብ መሆን እና ዋጋችሁን ለማድረግ፣ ባደረገው ተለዋዋጮ ደስታ ከዚህ መንዙማ ሀድራ PDF ከሚቀጥለው ገፅ ጋር ተጋበዙ። አዲስ መረጃዎችን እና ተጨማሪ መጽሀፉን ለመመልከት ከዚህ አገራችንን ይጎብኙ። የመንዙማ ሀድራ እናቴሌግራም ቻናል በዚሁ አረንጓዴ የከበሬ ታሪክ ነኝ። በዚህ ቻናል ለመጠቀም እና በቻናል የበጎ መረጃዎች ለመረጃዎቹ እና ለማንበብ የሚመኖባትን መጽሀፍ ከሚከብርበት ቀጥር ማድረግ ይችላል። ከዚህ ገንዘብም አድምጡ፣ እባኮትን እና ጠቃሚ በሙሉ ጠንቅቁ። ጥሩ ግምት ለምንጮኹህ በቴሌግራም ቻናል ላይ እንዳደረገ ከመመለስ ባህል በተነበበው መንዙማ ቻናል ላይ፣ የዩኪዎችን ለትንሽ የመረጃ መረጃዎችን በመቀነብ እና መልሱን በመስተጠበቁ እና ለምንጠባቡ ራስ መቶን በራስ ለመጠቀም ይህ ቴሌግራም ቻናል በገለጹ መዘናና መጠበቅ አድርገዋል። በቻናል ገፅ ውስጥ የመንዙማ ሀድራን በግዛቱ እና ሌሎችን ታሪኮች ለማየት የእውነት ምንድኑ እንደሆነ እናወራለን።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

27 Jan, 20:44


አላሁመ ባሪክ ለና ፊረጀብ ወሻዕባን ወበሊግና ረመዷን ?!

~ የ11 ወራት መንቀዥቀዥን ገታ አድርጎ ከራስ ጋር ንግግር እናደርግ ዘንድ የተመቸው ፤

~ በሌሎቹ ወራቶች ስንደክም ከርመን ረመዳን ኑ እዚህ ጋር አረፍ በሉ የሚለን ዓይነት የእዝነቱ ወር ፤

~ ልክ እንደ መዲና ከተማ ከሁሉም ተለይታ ስክን እንዳለቺው ከወራት በተለየ ሁኔታ ስክነትን የተላበሰ ስክን የሚያደርገው ወር ፤

~ "ኡፍፎይ ረመዷን ገባልን" የምንልለት ተናፋቂና ተወዳጅ ወር ፤

~ ዓመት ሙሉ የተዛባ የሌሊት እንቅልፋምነታችንን በንቁነት የሚያስተካክልልን ወር ፤

~ መስጠትን ፣ መተዛዘንን ፣ ዝምድና መቀጠልን ፣ ምላስ መሰብሰብን ፣ ዓይን መስበርን ፣ ረሃብና ጥማት መልመድን ፣ ውሸት መተውን እነዚህና መሰል ብዙ በጎ ተግባራትን የምንቀስምበት የምንለማመድበት ወር ፤
~ በአጠቃላይ ዓመታዊ ሰርቪሳችንን የምናደርግበት ወርሃ ረመዷን ላይ ነው ። ጥሩ ሰርቪስ ተደርገን « ኧረ - መዳን » ልንል ጥቂት ሳምንታት ቀርቶናል ።

በረመዳኑ ታጥበን ተቀሽረን በውስጡ ለዓመታት አጭደን በዐፊያ ስንጨርሰው በመሄዱ እያዘንን ባገኘነው ረክተን « ኧረ - መዳን» የምንልበት ወርሃ ረመዷን እነሆ ከፊታችን ተደቅኗል ።

አላህ ደርሰው ከሚጠቀሙት ያድርገን 🤲🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

27 Jan, 17:19


የነብዩ መሃመድ صلى الله عليه وسلم ኢስራ ወልሚራኢጅ ሃይማኖታዊ ጉዞን ምክንያት በማድረግ የሚካሄድ የዳዓዋ ስነስርዓት ከሚኖረው ሃይማኖታዊ ፋይዳ ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከተማ ተካሄዷል።


ዘንድሮው የተካሄደው የዳዓዋ ስነስርት ከስካሁኑ ልዩ የሚያደርገው ከ400 በላይ የጎረቤት ሃገር ሱዳን የዕምነቱ ተከታዮችና ኦለማዎች መገኘታቸው መሆኑንም በመጠቆም ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ተሳታፊዎች በአንድ ተገኝተው ሥነስርዓቱን በመታደማቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች እንዳሉት የመውሊድ ፕሮግራም መዘጋጀቱ ነብዩ ሙሃመድ በታላቁ የረጀብ ወር ሚስጢራዊ ጉዞ በማድረግ ከአላህ ጋር በመገናኘት ታዓምራትን ያዩበትን ዕለት ለህዝበ ሙስሊሙ ለማስታወስና ለሀገርና ለህዝቡ ጾሎት የሚደረግበት መሆኑን ተናግረዋል።

የረጀብ ወር የመውሊድ በዓል በመከባበር እና በአንድነት የሚከበር በመሆኑ ይህ እሴት ተጠናክሮ ለትውልድ እንዲሽጋገር ማስቻል ይገባል::

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

27 Jan, 13:30


ሺሊላ ሺሊላ ሺሊላ ሺሊላ
ያ ኸይረ ኸልቂላህ ሺሊላ ሺሊላ
ያሻፊዐል ኸልቂ ዒንደላህ
ሙሀመድ ያማሊሀል ወጅሒ ጁድ ቢላህ💚💚

አላ ያ አስያዲ አላ ያ አሰያዲ
ኢዛ ማጀዝቱሙ ቢዲያሪል ሐዲ
በሊጉሁም ሰላመን ሚና
ሙሀመድ ያ ማሊሀል ወጅሒ ጁድ ቢላህ 💚💚

ያ አዮሀ ራሚ  ያ አዮሀ ራሚ
ቢሰህሚ ሁቢሂ ቁሉበል ኪራሚ
ጁድ ለሁም ቢል ዊሳሊል አህና 
ሙሐመድ ያ መሊሀል ወጅሂ ጁድ ቢላህ💚💚💚

ሐቢቡን መሕቡቢ ሐቢቡን መሕቡቢ
ቢሀዋኡ ቀልቢ አበደን መጅዙቢ
ፈመታ ሱሩሪ ወልሀና
ሙሐመድ ያ ማሊሀል ወጅሂ ጁድ ቢላህ😢💚💚💚

ፈከይፈ ኢኽቲያሊ ፈከይፈ ኢኽቲያሊ
ኢዛማ ሰደኒ ዘንቢ አን ዊሳሊ
ያ ጡለ ጀፋኢ ወል ዐና
ሙሐመድ ያ ማሊሀል ወጅሂ ጁድ ቢላህ😢💚💚💚

ያ ሲረል ውጁዲ ያ ሲረል ውጁዲ
ያ ከሒለል ዐይኒ ቢኢሥሚዲል ጁዲ
ያጋየተል  ቀስዲ ወል ሙና
ሙሐመድ ያማሊሀል ወጅሂ ጁድ ቢላህ💚💚💚

ያ በድረ ተማሚ ያ በድረ ተማሚ
ያመን ሀመት ቢሂ አርዋሁል  ኪራሚ
ወከም ቢሂ ሰቡን ተገና
ሙሐመድ ያማሊሀል ወጅሂ ጁድ ቢላህ💚💚💚



ሙሀመድ ያማሊሀል ወጂ ጁድቢላ


መደዱ ማረከኝ በልጅነት ደርሶ
አልቻልኩኝምና ለመተው ጨርሶ
የኔ ጉዳይ ብሶ ከሌላ
ሙሀመድ የኔ ጉዳይ ብሶ ከሌላ
መድሁን ጀምሪያለው ፊት በልጅነት
በሁቡ እየኖርኩኝ
በሁቡ ልሙት
አርጉኝ ጎረቤት በጀና ሙሀመድ አርጉኝ
ጎረቤት በጀና
መደዱእየመጣእንዴትልመክተ ው
አልቻልኩኝምና ብፈልግም ልተው
ብዬ ልወትውተው ሺሊላ ሙሀመድ ብዬ
ልወትውተው ሺሊላ
ባርያዎቿን ይዛ ነቢን ስትጎትት
ተሳበላት እንጂ መች አስለቀቃት
ሁቡ አቃጥሏት ገንፍላ
መሀመድ ሁቡ አቃጥሏት ገንፍላ
ነገ በጀነት ሆነን አብረንሆ
ከአስያ ከመርየም ሲሰረግልሆ
እናዚምልሆ ሰለላ
ሙሀመድ እናዚምልሆ ሰለላ
ወይ አንቱን አላየዉ ያነቢ ያነቢ
ወይም አላደኩኝ ቤተሰብ ቀርቤ
ተቃጠለ ደሜ ጉድ ፈላ
ሙሀመድ ተቃጠለ ደሜ ጉድ ፈላ
አንቱን ልጥራሁ እነጂ
ደግሜ ደግሜ
እያልኩኝ ሺሊላ የአበል ቃሲሜ
ይመርልኝ ስሜ በሌላ
ሙሀመድ ይመርልኝ ስሜ በሌላ
እጣኑን ሲያጨሰው
እንዳለው ባሩዴ
ነቢን ልበላቸው
አንቱ ኖት ፓውንዴ
ሙራዴ ያ ዛዴ ጁድቢላ
ሙሀመድ ሙራዴ ያ ዛዴ ጁድቢላ
በቃኝ ብዬ ነበር ቀለሜን ሳነሳ
እንዴት ላወድስህ እያለኝ ዋክሳ
ባክህ ስጠኝ ካሳ ያ መውላ
ሙሀመድ ባክህ ስጠኝ ካሳ ያ መውላ
ያንከራትተኛል እኔስ ተገድጄ
በትንሹም ቢሆን ነብዬን ቀስጄ
እባክህ ወዳጄ ተው ዱላ
ሙሀመድ እባክህወዳጄ ተው ዱላ
መደድ የሚባለው ሲገባለት ሀድራ
መረቀነ መሰል ወይ ተጋባ ግራ
ወይም አያሰራ ሊያበላ
ሙሀመድ ወይም አያሰራ ሊያበላ
አንተኮ ቃዲር ነህ የፍአሉ ማኢሻ
ማጣትን አንስተህ አሳምር ማኢሻ
ሀድልንም እንደሻህ ላግላ
ሙህዬ ሀድልንም እንደሻህ ላግላ
ያኛው ሰው እንዳለው አላያ አዝያዴ
ነቢን ልበላቸው ማንአለኝ ከንግዲ
ተሸበረ ሆዴ ጉዴ ጉድ ፈላ
ሙህዬ ተሸበረ ሆዴ ጉድ ፈላ
ሙሀመድ
ያማሊሀል ወጂ ጁድቢላ
ሀቢቢ
ያማሊሀል ወጂ ጁድቢላ
ሙሀመድ
ያማሊሀል ወጂ ጁድቢላ
ሰይዲ
ያማሊሀል ወጂ ጁድቢላ

@Menzu_m
👆👆Joine

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

27 Jan, 06:43


ምንም አይነት ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎት ባልነበረበትና በማይታወቅበት ዘመን አንድ ሰው አንድ ሙሉ ሌሊት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከመካ ተነስቶ ቁድስ ደርሶ ተመለሰ ተብሎ ቢነገር የሚታመን ነገር አልነበረም
ለዚህ ነበር በወቅቱ ወደ እስልምና ገብተው የነበሩ
አዳዲስ ሰዎች ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ያደረጉትን ይህንን ጉዞ አምኖ ለመቀበል የተሳናቸው :
የቁረይሽ ሙሽሪኮችና ባላባቶች ይህንኑ ዜና በሰሙ ጊዜ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ለማሳጣትና ለማዋረድ የማይገኝ እድል ያገኙ ስለመሰላቸው ጮቤ ረገጡ
ክፍተትን ለስህተት ለመጠቀም ያላቸው አቋም አጂብ ነው ሚያስብለው
በነገሩ ለመሳለቅና ለማሾፍ ወደ አቡበከር (ረ.ዐ)
ዘንድ ሄዱ እንደደረሱም ለ አል ሲዲቅ አሏቸው ፦
"አቡበከር ሆይ ! ጓደኛህ የሚዘላብደውን ሰምተሀልን?" አሉ ከዚያ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በኢስራ እና ሚዕራጅ ስላደረጉት ጉዞ የተናገሩትን ነገሯቸው
አቡበከርም (ረ.ዐ ) "በእርግጥ እንዲ በሏል? አሉ '
"አዎ! አዎ ብሏል አሏቸው " አቡበክርም (ረ.ዐ)
"በእውነት ይህንን ብሎ ከሆነ እውነትን ተናግሯል አሉ ።"
ቁረይሾችም ይህንን አምነህ ትቀበላለህ!" ሲሉ ደግመው ጠየቋቸው ።" ከዚ የበለጠ ነገር ቢናገሩም አምናቸዋለሁ ሲሉ መለሱላቸው 🥺 መገን ያንቱስ ...."ወደ እርሳቸው እንሂድ አሉ ።
ወደ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ ) ዘንድ እንደደረሱም ስለ ኢስራ እና ሚዕራጅ የተከተለውን ሁሉ በዝርዝር ነገሯቸው ።"አቡበክርም እንዲህ አሉ :- እውነት ተናግረዋል ! እውነት ተናግረዋል ! እርሶ የአላህ መልዕክተኛ መሆንዎን እመሰክራለው ።"
ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) "አቡበከር ሆይ ! አንተ እውነተኛ ነህ ።"አሏቸው
መገን የሲዲቅስ ወላሂ 🥺🥺

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 23:06


አል ኢስራ                  ወል ሚራጅ
★ዛሬ ከባድ ለይል ነች ስንት ድንቃ ድንቅ ነገር የታየባት ለይለተል ሚራጅ
                                 #የቡራቁዋ ናፍቆት
                                #አስፈሪ ነገር የታየበት
                               #ደስታ የታየበት
                              #የመጥፎ ስራ ድርጊት የታየበት
                             #የጥሩ ስራ ምንዳ የታየበት
                            #ምላስ የምታመጣው በላ የታየበት
#50 ሰላት ወደ #5 ሰላት የተደረገልን ነብያችን (ሰ ዋ ወ) #9 ግዜ ተመላልሰው እንዲቀነስልን አድርገዋል #50 ሰላት ኡመትህን አይችልም ብለው ሂድና አስቀንስ አሉ ነቢ ሙሳ (ዓ ወ) የነቢ ሙሳም (ዓ ወ)ውለታም የታየበት ለይል ነው ጉዞው አያልቅም።

ሲዲቂዩም ሲድቅ የተባለበትን ማዕረግ ያገኝበት ለይል ነች ። እኔም ሲዲቅነትን ነይቼ ነው ሁሌም የማድረው በዚች ለይል

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 23:04


ሰኞ ተወለዱ ፣ በሰኞ ኢስራ ወል ሚዕራጅ (ወደ ሰማይ) ወጡ ፣ በሰኞ ወደ መዲና ተሰደዱ ።

የዛሬውም ለይሉ ለሰኞው ገጥሞልናል ። ኸይር የተባለ ነገር ሁሉ በዚሁ ለሊት የሚገጥመን ይሁን ...!

አላሁመሰሊ ወሰለም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 19:31


27 halkan Rajab
Israa’elii fi Miraaj (الإسراء والمعراج 

• Hiikaa: Israa’ii jechuun imala ajaa’ibaa Nabi Muhammad (صلى الله عليه وسلم) Kaaba (Makkaa) irraa gara Masjiida Qulqulluu (Beital Makdis/Yerusalem) halkan tokkotti fedha Rabbiitiin imale jechuudha.  Mi'raj imala isaanii gara samiitti fi sanaa oli tasisani jechuudha
• Hiika: Imalli kun taatee dinqisiisaa Islaamummaa keessatti gatii guddaa qabuudha.  Imala kana keessatti Nabiyyiin (صلى الله عليه وسلم) Rabbiin waliin wal argan;  Salata (Kadhannaa) dabalatee ajaja adda addaa argataniiru. Nu fidanidha
• Xumura irratti: Israa’ii fi Mi’raaj humna Rabbii fi sadarkaa addaa Nabi Muhammad (صلى الله عليه وسلم) kan mul’isudha.

27 halkan Rajab

• Hiika: Halkan 27ffaan Rajaab halkan Israa’ii fi Mi’raaj akka ta’e amanama.  Halkan kuni islaamummaa keessatti halkan qulqulluu waan ta’eef Muslimoonni Rabbi kadhachuu, salaata irratti hirmaachuun fi Qur’aana qara’uun dabarsu🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 15:31


ይህች የለይለቱል ኢስራእ ወልሚእራጅ ለሊት ነቢ ﷺ ያዘነ ቀልባቸው የታጠበበት ለሊት ናት። 💚 የኛም ያዘነ ቀልብ በዚች ለሊት ይጠብልን🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 14:16


ኢስራእ ወልሚዕራጅ ነው እናም በዚህ ለሊት ለይል የሚደረገው ተወዳጅ ዚክር
سبحان الذي اسرى بعبده
የሚለው ነው
ቢያንስ 100 ጊዜ አልያም ከዛ በላይ
.....
اللهم صل على خير العباد
محمد الهادي الى الرشاد
شفيع الورى في يوم المعاد

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 13:39


"አንዳንድ መሻይኾች የረጀብን ወር ክብደት በመመልከት ሻዕባን ላይ ለመጣ ሀጃ ቀጣይ አመት ረጀብ ይምጣና ..ብለው ያቆዩት ነበር" አሉኝ ሸሁ
በዚህ አይነተ እኛ ምን ተጠቀምንበት?🥺 ኢንሻአላህ ዛሬ ለይሉ በዱአ እንበርታ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 12:35


የዛሬው ለይል በዱአ እንበርታ🤲

ዛሬ የኢስራና ሚዕራጅ ሌሊት ነው፤ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ሌሊቱን አስመልክቶ ሢራዎች ይቀራሉ። ሰለዋቶች ይደረጋሉ፣ በሕብረት አማኞች ተወሱላቶችን ያከናውናሉ። በሐገራችንም በተለያዩ መስጂዶች ላይ እነዚህ መንፈሣዊ ክንውኖች ይደረጋሉ።

የኢስራእና ሚዕራጅ ታላቁ ትሩፋት ሰላት ነው። ሰላት ለአማኞች ሚዕራጅ ነው። ሰላታችን የሚዕራጅ ያህል ምጥቀት የሚያስገኝልን መንፈሳዊ ሽልማት ነው።

ኢስራእ ማለት የአላህ መልእክተኛ በቡራቅ ላይ ኾነው ካሉበት ወደ ቤይተል መቅዲስ (ዐቅሷ) ያደረጉት ጉዞ ሲኾን፥ ከበይተል መቅዲስ (ቁድስ) ወደ ሰማየ ሰማያት ያደረጉት ጉዞ ደግሞ ሚዕራጅ ይባላል።

በፈለስጢን ምድር ያለችው ዐቅሷ የሰማይ በር ብለው ይጠሯታል። በሰላት ወደ ሰማይ በር የምንቃረብ ያድርገና! 🤲🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 11:07


"አንዳንድ መሻይኾች የረጀብን ወር ክብደት በመመልከት ሻዕባን ላይ ለመጣ ሀጃ ቀጣይ አመት ረጀብ ይምጣና ..ብለው ያቆዩት ነበር" አሉኝ ሸሁ
በዚህ አይነተ እኛ ምን ተጠቀምንበት?🥺

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 09:50


በሚራጁ ለሊት በለይለተል ኢስራ በቡራቅ ላይ
ሆኖ💚{ﷺ}ጅብሪል እየመራ ተጠርተዋል ብሎ ከጀሊሉ ሀድራ ሰላት" ይዘው መጡ ያላህን አደራ!!{ﷺ}

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 08:31


ታላቁ ጉዞ
እንኳን አደረሳቹ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 08:03


ዛሬ እሁድ ( ረጀብ ቀኑ 26) ለይሉ ደግሞ 27 ነው “ኢስራእ ወልሚዕራጅ” ለሊት ነው ብዙ ተዓምር የታየበት ለይል ነው ። በአላህ ፈቃድ ቀጣይ ሳምንት የሻዕባን ወር ይገባል ዱአ እንወጥር🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 07:57


ኢስራዕ እና ሚዕራጅ ሲነሳ ምንድነው የሚያጅባችሁ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

26 Jan, 07:51


ኢስራእ ወል ሚዕራጅ ረጀብ 27 እንኳን አደረሳችሁ ዛሬ አመሻሹን በዱአ እንበርታ🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

25 Jan, 09:53


ህዝበ ሙስሊሙ ሚስጊን አይደል?... በሀጂ ሙፍቲ ጊዜ የሀጅ ገንዘብ 78ሺ እና 80 ሺ ሆኗል ሲባል የፌስቡክ ኡስታዞች <<እንዴት እንደዚ ይሆናል የህዝበ ሙስሊሙን ብር ሊግጡት ነው>> ምናምን ምናምን ወዘተ....የሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስን ስም ከገንዘብ ጋር አያይዘው ብዙ ቆሻሻ ነገሮችን ፅፈው ሁጃጁን አስጩኸውት ነበር... ይሁን እስቲ አሁን ደግሞ  እናንተ ግቡበት ብሎ መንግስት ሁሉን ጠቅልል ሰጣቸው.... የ ሀጁን ገንዘብ በዕጥፍ ደርበውት ከግማሽ ሚሊኒየን 625ሺ ብር አድርገውት እርፍ አሉ😊🤭

መገን ጠንካራው መጅሊስ......መጅሊስን ካልሰጣቹሁን እያሉ ሲጮሁ የነበሩበት አንዱ እና ዋነኛውኮ የሁጃጆች ገንዘብ ይቀነስ በሚል ነበር😊

ደርሶ እስኪመለስ ድረስ የቤተሰቡን ቀለብ ችሎ ለ ሀጅ ደግሞ 625ሺ ብር የሚከፍለው ትርፍ ገንዘብ ያለው አንድም  ሀብታም የለም!!...በርግጥ ኡስታዞቹ ይኖራቸዋል.. ተራው ምዕመን ግን በጭራሽ.😂😂.. እመኑኝ ዘንድሮ ማንም ላይ ሀጅ አይወጅብም😊

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

25 Jan, 07:27


የዘንድሮ ሀጅ በእግር ነው ምንጓዘው ተዘጋጁ

እንጂ ማነው 625ሺ ብር ከፍሎ ምሄደው😊🤭

በእግር መሄድ ምትፈልጉ ቶሎ እኔ ጋር ተመዘገቡ ቦታ ሳይሞላ😊😊

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Jan, 19:09


ሰይዲ ለጊዜያዊውም ሆነ ለዘላቂው ህይወት ሁሉ ችግሩን ከነ መፍትሔው አስተምረውን እንጂ አልተለዩንም ። ከጓዳ እስከ ስልጣን ማማ ያለውን ሁሉ አሳይተዋል ። ስለ ነፍስ ፣ ስለቤተሰብ ፣ ስለ ህዝብ ሁሉ እንዴት እንደሚኖር ኖረው አሳይተውናል ። የእርሳቸው ዑመት ሆኖ የሰሩትን ለመስራት ከታቀቡት ለመታቀብ የጣረ በፍፁም አልሰነፈም ። ህመም ችግሩ ፣ መዛል መድከሙ ቢያስመነዳው እንጂ ሌላ አይደለም ። እንደርሱ ያለ ብርቱ ፣ እንደርሱ የታደለ አንድም የለም ። የእርሱ ዑመት መሆን በራሱ የነብያት ምኞት ነው ። በዱኒያ ይህን የመሰለ ስጦታ አልተሰጠንም ። በአኺራም የእርሱን ምልጃ ማግኘት ለዑመቱ የተሰጠ ነው ። አኗኗራቸውን በዱኒያ ምልጃቸውን በአኺራ እንዲወፍቀን ታላቁን ሰው የእርሱን ተወዳጅ ለኛ ለቸረን አላሁ ተዓላ እንጠይቀዋለን ። እርሱም መላዕክቶቹም በሚያወሱት ሙሐመድ ላይ ሰለዋት ማብዛት የአላህ ትዕዛዝ የእርሱም ሱና ነው ።  ሰለዋትን እንጂ አድርጌዋለው አድርጉት አላለንምና በተቻለን ሁሉ በእርሱ ላይ ሰላት ሰለዋትን እናብዛ ።

ተማም አል ሀድራ በአንቱ ላይ ይህን ያህል  ሰለዋት አድርጓል ከሚል ከአላህ ወደ ረሱል ዓለይሂ ሰላም ከሚተላለፍ መልዕክት የተሻለ መልዕክት ይኖር ይሆን  ? ምንም !

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Jan, 19:00


« ቀልብያ ሲቆሽ አማን ሲዳከም
ሙሐመድ ብለህ በሃድራው ታከም»

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Jan, 16:39


ውድድሩ አሁንም ጀምሯል

በስራዬ ደስተኛ የሆናችሁ ቤተሰቦቼ እስኪ በዚህ የፌስቡክ ሊንክ ግቡና ላይክና ኮሜንት አድርጉልኝ 👇👇👇

https://web.facebook.com/vijai.naiker/posts/9132874240123436?comment_id=980371330813276&cft[0]=AZXosMu_CanEx4nYQnaeCMIErc8OJYudxC3370CDBIKTzYhLQkvn0JskJspaBf6hk1KjFLfb2nhGHDk2n_Pt_o55ODPwFr41MyWROV9hHYf6LVNGOjRuLDiLLzMqhQKGdxaJM_lHGKwoBb1HWRKQN-KVCrazMCYcU5uImNBj3UAKvTD0Fz2EfO_xxNuZOlAC7KA&tn=R]-R

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Jan, 08:39


ኢናሊላህ ወኢና ኢላሂ ራጅኡን 😭

انا لله وانا اليه راجعون
አስታወሳችሁት ከቀናት በፊት የዚህን ታዳጊ ህፃን ሕይወት እንታደግ ዘንድ በተለያዩ ማሕበራዊ ሚድያ ላይ በህክምና ወጪ ቤተሰቦቹን  እናግዝ ዘንድ ጥሪ ማቅረባችን ይታወሳል። እነሆ በእናንተ ቅን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ትብብር አስፈላጊው የሕክምና ወጪ ተመልቶ ነበር ግን አላህ የፈለገው ነገር ሆነ😢
አናንተ ኢትዮጵያዊ ደጋግ ልቦች አላህ ኸይር ሥራችሁን ይቀበላችሁ፤ በልጅ ማጣትም አይፈትናችሁ😢

በጣም የሚያሳዝን ነው ወላሂ።አላህ ለቤተሰቡ እና ለሁላችሁም ሰብሩን ይስጣችሁ። ማሜ ነገ በቂያም ለቤተሰቡ ሸፈዓ ይሁናችሁ።

አልፋቲሓ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Jan, 08:20


ያላንቱ ነኝ🌹እኔ ከንቱ
ምን💚ልበል አጠረኝ...እኔ..✍️ቀለም 🥁👏
صَلَّى اللَّهُ عَلَا םבםב_ﷺ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Jan, 07:44


ረቢዕ ቢን ሐይሰም
"አንድም ሰው ላይ ነውሩን ስታወጣ አላየንህም" አሏቸው
"በራሴ ደስተኛ አደለሁም እንዴት የሰዎችን ነውር ለማውጣት ጊዜ ይኖረኛል?!" ብለው መለሱ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Jan, 07:21


ከሮጠ ይልቅ ከአሏህ ጋር የቆመ ይበልጣል🙌

ጁምዓ ሙባረክ💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Jan, 23:50


በረጀብ ወር በመጨረሻው ጁምዐ ዕለት ላይ ለጁምዐ ሶላት በሚደረገው ኹጥባ በሁለተኛው የኹጥባ ወቅት ላይ ፦

ኹጥባ አድራጊው ሁለተኛውን ኹጥባ እያደረገ ለሙዕሚን ሙዕሚናት ዱዐ በሚያደርጉ ጊዜ ፦(أحمد رسول الله محمد رسول الله) [አህመድ ረሱሉላህ ሙሀመድ ረሱሉላህ] ሰላሳ አምስት ጊዜ ያለ ገንዘብ ከእጁ ላይ በጭራሽ አይጠፋም።

የሚባለውም በውስጥ ነው
___
📚كتاب كنز النجاح والسرور

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Jan, 21:16


እንደዛሬ ሰዎች ተሰባስበው "ሰለዋት" ለማድረግ ሳይሳቀቁና ሳይፈሩ የሚሉበት የድሮ የአባቶች ጊዜ "ተንቢህ አልአናም" የተሰኘውን የሰለዋት ኪታብ እየተዋሱ በእጃቸው ጽፈው ትልቁ ንብረታቸው አድርገውት በየዕለቱ፣ በየሐሙሱ፣ ለዐቂቃው፣ ለዱዓው፣ ለመውሊዱ፣ ለለቅሶው በመጠቀም የሕዝባቸውን ኢማን በሚገባ ይጠብቁበት ነበር። ዛሬ ዐረብኛ ማንበብ በመቻላችን በምንደነቅበት ጊዜ ጽድት ብሎ ታትሞ በየመደብር እየተሸጠ በግለሰብ ኾነ በመስጂዶች ውስጥ ተሰባስቦ በሰለዋት ለመደሳሰት አለመታደል ከየት የመጣ መጤ ነገር ይኹን?! ከአባቶቻችን ከወረስናቸው መልካም የዲን እሴቶች ሠንሰለት መቋረጥ እኮ ነው ከባዱ "ቢድዓ" ማለት። በተገላቢጦሽ የነብያት ወራሽ ዑለማ አባቶች ጠብቀውና ተንከባክበው ያቆዩትን ተጅሪባ (ልምድ) በማይኾኑ መጤዎች መተካት ፋሽን ኾነና ሰለዋት ተሰባስቦ ለማለት መተፋፈር ያዝን!

ይህን የተሞኘንበትን ጊዜያት ቀዷ በማውጣት ያህል ወደ ሰለዋት መመለስ ይገባናል፣ አባቶች በየመንደሩ ያደረጉትን ዱዓ፣ የቀሩትን ሰለዋት የመለስን ዕለት ነው ትልቁ ስኬት ማለት!

ይህን በግለሰብ ደረጃ እንለማመድ!

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

አላህ ይወፍቀና🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Jan, 21:06


ከሰለዋት አለ ነቢይ ጥቅሞች ....
ሰውየው የረሳውን ነገር ያስታውሰዋል
ድህነትን ያስወግዳል
ቀልብን ያጠራል
ሀጃን ያወጣል
ወንጀልን ያስምራል
የአሏህን ራህመት ለማግኘት ሰበብ ነው.....................

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

19 Jan, 07:16


ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎቱ ተቋረጠ

ቲክቶክ ከደቂቃዎች በፊት በአሜሪካ መስራት አቁሟል።

ከቻይና መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለው በአሜሪካ መንግስት ክስ የቀረበበት የቲክቶክ ዋና ድርጅት ባይት ዳንስ ማስተካከያ እንዲያደርግ ወይም የድርጅቱን የአሜሪካ ቅርንጫፍ ለአሜሪካ ኩባንያዎች እንዲሸጥ ተጠይቆ ነበር።

ቲክቶክ አገልግሎቱ ለ175 ሚልዮን አሜሪካውያን ዛሬ ቢቋረጥም ሰኞ እለት ወደ ስልጣን የሚመጡት ዶናልድ ትራምፕ እገዳውን እንደሚያስቆሙት ይጠበቃል።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

18 Jan, 20:51


ከፌስቡክ መንደር 100ሺ ብር ውድድር አሸናፊ አድርጉኝ

ውድድሩ ሪአክቱ እና ኮመንቱ እኩል መሆን አለበት ወይም ኮመንቱ መብለጥ አለበት የሚል ሕግ አለው።  ሪአክት ስታደርጉ ሪፕለይ ላይ መኮመትም አትርሱ አንዱ መስፈርት እሱ ነው

ላይክ ከዛም ኮሜንት በማድረግ አበረታቱኝ  ውድድሩ ልገባደድ ነው።

ፌስቡኩ ገፅ ይኸው በዚህ ሊንክ 👇  ገባ ገባ በሉና ለይኩ🙄

https://www.facebook.com/share/18dRHAKSpM/

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

18 Jan, 19:00


አላህዬ🤲ቶሎ አክብረንና አገር ጉድ ይበል 🙌

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 20:41


ለኡስታዝ ሀሰን ታጁ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ በኮሜንት አንድ ወንድማችን መውሊድ አክባሪ በመሆኑ የደረሰበትን እንግልት በፅሁፍ አጋርቷል።

ክቡር ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር እድሪስ እውነት 7 ምድር ቢቀ-በር መውጣቱ አይቀርም:: ውሸት ሰባት ሰማይ ቢወጣ መውረዱ አይቀርም::

ህግ እና መንግስት ባለበት ሀገር እንዳሻቸው ህግን ሲጥሱና በሰላማዊ መንገድ በህግ ጥላ ስር የሚኖሩትን ዜጎችን በጠራራ ፀሃይ ሲበድሉ የሚሳይ ደርዘን መረጃ እያለ የህግ አካላቱ #ጆሮ_ዳባ ልበስ መሆናቸው የሚያስተዛዝብ ነው።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 20:25


ቲክ ቶክ ከነገ በስቲያ ከአሜሪካ ሊሰናበት ይችላል
***

ቲክ ቶክ ከነገ በስቲያ (እሁድ) ከአሜሪካ ሊሰናበት እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክ ቶክ እንዲሸጥ አሊያም አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ የተዘጋጀውን ሕግ ደግፏል፡፡

ስለ እግዱ አተገባበር ዝርዝር መረጃዎች አለመውጣታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ቲክ ቶክ ለአሜሪካ ገዥ የማይሸጥ ከሆነ መተግበሪያው በሀገሪቱ የሚኖረው የአገልግሎት የመጨረሻ ቀን እ.አ.አ ጥር 19 ቀን 2025 (እሑድ) እንዲሆን ቀነ ገደብ ተቆርጦ ነበር፡፡

ባይት ዳንስ በተባለው ካምፓኒ የሚተዳደረው መተግበሪያው አሜሪካ ውስጥ ከ170 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡

የካምፓኒው ባለቤት ዣንግ ይሚንግ ከቻይና ዜግነቱ ጋር ተያይዞ ቲክ ቶክ የአሜሪካ መንግሥት የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው በሚል ሲያሟግት ቆይቷል፡፡

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 20:20


በዓለም ላይ ቲክቶክ ከነገ ወዲያ (እሁድ)ይዘጋል ተብሏል እዚህ መንደር ያላችሁ ቲክቶከሮች ምን ትላላችሁ😊😊

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 20:10


ራሱን አግቶ ከቤተሰቦቹ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ🤭

ምን ይባላል አሁን😊🤭 እስቲ ምን ትላላችሁ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 19:34


ፌስቡክ ይኸው በዚህ ሊንክ 👇 ገባ ገባ በሉና ለይኩ🙄

https://www.facebook.com/share/18dRHAKSpM/

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 19:25


ከፌስቡክ መንደር 100ሺ ብር ውድድር አሸናፊ አድርጉኝ

ውድድሩ ሪአክቱ እና ኮመንቱ እኩል መሆን አለበት ወይም ኮመንቱ መብለጥ አለበት የሚል ሕግ አለው። ሪአክት ስታደርጉ ሪፕለይ ላይ መኮመትም አትርሱ አንዱ መስፈርት እሱ ነው

ላይክ ከዛም ኮሜንት በማድረግ አበረታቱኝ 48 ሰዓት ይቆያል ውድድሩ።

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 17:53


እኔ እንዳለሁ አለሁ
አንቱ እንደምን አለሁ
ስጠራሁ እየዋልኩ ስጠራሁ አድራለው
አሽሩኝ ጌታዬ ቀልቤን ታምሚያለሁ
ዘልቃችሁ እስክታዩኝ መጠበቅ ይዣለሁ 💚

አጊሱና ቢላህ🙌

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 14:56


ባህር ኪያ💛

አረ እናንተ ሆዬ ሰው አይድንም ታሞ
ያምናው በሽታዬ አገረሸ ደግሞ 💚
ከጎራው ላይ ሆኖ ይላል ወዲህ በል
ቶሎ አክብረንና አገር ጉድ ይበል 🙌💚

አጊሰኒ

ያሰሪአን ቢልከራማ ያሸፊአን ቢሰላማ አጊሰና ያኑርሁሴን

አቢዮ አማና🙌

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 14:32


ከታዋቂ እና ከአውቃ ሰው መሃል ያለው ልዩነት አስረዱኝ😊

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

17 Jan, 09:39


ጁምዐ ሙባረክ
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ “ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛል

الّلهُمَّ صَلِّ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ
وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِأَجْمَعْيْنَ

📿صلو عليه صلاوات ربي وسلامه عليه📿

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

16 Jan, 22:09


የአላህ እዝነትና በረከት ለይለቱል ጁምአ በቴሌግራም በሰለዋት በምታስውቧት ውድ ሙሂቦች ላይ ይውረድ 🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

16 Jan, 21:44


ሰለዋት የ ድህነትን ማስወገጃ ነው
አንቱን አወድሶ የደኸየም አላየን

ያ ረሱለላህ (ﷺ)

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

16 Jan, 21:34


#ኸሚስ_አመሻሹን🤲🤲

#ረጀብ🥰
" የዚህን የረጀብ ወር በረካ እንዲሰጠን አላህን እንጠይቃለን ...
ከዚህ በረካ ውስጥ በየጊዜው የሚጨምር ኑር ልብ ውስጥ መፈንጠቅ ነው
ይሀን በረካ ደሞ ካገኘክ ቀጥሎ ያለው ወር - ሻዕባን- ላይ ትደሰታለህ ሻዕባን ወር ላይ ደስታን ካገኘክ ደሞ ረመዳን ላይ ደስታክ ሙሉ ይሆናል በያንዳንዷ ለሊት አላህ ጋር ክብርና ደረጃን ትጎናፀፋለክ.. ገበያና ንግድ ለሚፈልግ ፤ መጨረሻ የሌለው መገበያያትን ለሚያውቅ ፤ ዘውታሪን ግብይት ለሚያውቅ እነዚህ ወራት የገበያና የትርፍ ጊዜያት ናቸው
አላህ ከዚህ የአጅር ንግድ፤ ወደ አላህ የመቅረብ ንግድ ፤ የደስታ ንግድ ፤ ቸር ከሆነው ጌታችን ምህረትን የማግኘት ንግድ ድርሻችንና ትርፋችንን አተልቆ ይስጠን🤲

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

11 Jan, 04:08


ጠዋት ከእንቅልፍክ ስትነሳ ፈጣሪህን ማመስገን በፍፁም አትርሳ ምክንያቱም እርሱ በየቀኑ አንተን መቀስቀስ አልረሳምና

አልሀምዱሊላህ ዓላ ኩሊ ሃል

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 19:37


https://youtu.be/DLM_r7QJo2E?si=QnWA7rt_pFBvLun8

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 19:24


መች የእኛ ንግግር ይገባቸዋል😊🤭
አፉ በሉኝ

አበቃሁ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 19:17


የጫት ትልቁ ጥቅሙ እራስህን ለማድመጥ ምላስህን ይለጉምልሃል:: ችግሩ ግን ልክ ከራስህ ጋር ልትደማመጥ ስትጀምር ምር-ቃናው ብን ይላል:: I am not ቃሚ:: አንድ ሰው ከቃመ ከማኪያቶ ምርቃና ብዙም አያሳልፈው:: ኳድሮ አብርተህ ሞተር ካስነሳህ በሗላ ደጋግሞ ቁልፍ መምታት ሞተሪኖ ማቃጠል ነው:: አንዴ በስሱ ተረክ ካደረግኸው ባትሪው እራሱ ቻርጅ ያደርጋል:: ይህም assፈላጊ ከሆነ ብቻ ነው::

ያለ አደብ ከቃምከው ሰሀራ በረሃ መሃሉ ላይ ወደብ ትፈልጋለህ:: አሸዋው የተንጣለለ ውቅያኖስ ስለሚመስልህ😊🤭

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 18:58


ከጫት ቃሚ ጋር ቀጠሮ ስትያያዙ ተጠንቀቁ:: እርሱ ከጫት ጋር መቼም የማይፈርስ ቋሚ ቀጠሮ አለው:: ቃሚ before and after ጸባይ ስላለው ከቃሚ ጋር ስትነጋገሩ ከኮሚቴ ጋር እንደምትነጋገሩ አስቡ:: አንድ ቃሚ ብዙ ሰው ነው:: ከየትኛው ጋር እንደተነጋገርክ አስብ:: ለስምንት ሰዓት ሲቀጥርህ አልፈለገህም ማለት ነው:: ገና ሲቀጥርህ ተሰርዟል😂

መቃሚያ የለው ሰው ብቻ ነው ንግግራችን የምገባው😊🤭

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 18:51


ቃሚ ሆነህ ለማግባት ስታስብ ላትተወው ነገር የምትጨቃጨቅህን ሳይሆን መቃሚያ ጉዝጓዝህን ተሸክማ የምትዞረዋን አግባ😊🤭

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 18:36


መቃሚያየን አሞኛል ዱዓ አድርጉልኝማ
ቃሚዎች😊😊

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 18:08


ከፌስቡክ መንደር ኸበር
አልሃምዱሊላህ አሁን ላይ የፌስቡክ ገፃችን ለሚሊዮኖች ተደራሽ እየሆነ ይገኛል።

ሀበሻን አስከብረው የኖሩ ትልልቅ ሳዳቶችን በሚድያ ለአለም እናስተዋውቃለን ሀድራቸውን እናሳያለን የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መውሊድ ዳር እስከዳር እናደምቃለን የአባቶቻችንን ፈለግ እናስቀጥላለን።

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 17:02


ከቻልክ ዝረፍ የፍቅር ቅኔ
ወይም እብድ ሁን እንደኔ
አትከልክለኝ ካጣህ ወኔ
እኔው ልስከር ተወኝ ደህኔ ማለት አሁን ነውስ🤭

ደዋም ደዋም ብለናል💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 16:03


ተናፍቅው ወር

በቢሊዮን የዓለም ሙስሊም በፍቅር የሚጠበቀው
ረመዷን ከረም 1 ወር ከ15 ቀን ቀረው አላህ በሰላም ያድርሰን😭🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 05:52


#የረጀብ_መደድ

ረጀብ ወር የአላህ ራሕመት የሚንቧቧበት ነው። እንደ ቀልድ አንድ ሳምንት አለቀ። ከሚወርደው የራሕመት የበረካ ማዕድ ምን ያህል ተቋድሰን ይኾን። እነዚህ ውድ የሚባሉ ቀናት በጣም ነው የሚሄዱት። መረጃ በማስተላለፍና መረጃ በመሰብሰብ ተጠምደናል። በዚህም የመረጃ ችግር እንደሌለብን ግልጽ ኾኗል። ሐላልና ሐራምን ሰዎች ከሞላ ጎደል አውቀዋል፣ ባይማሩ ራሱ ሕሊናቸው የተከለከለና የተፈቀደን ነገር በግልጹ ይነግራቸዋል። ሌላውኛው ቀመር ደግሞ በኑሮ ሒደት ውስጥ ሁሉም ነገር ሐላል ነው፤ ሐራም ሲቀር። (የሁሉም ነገር መሠረት ሐላል ነውና!) ሐራም የምንላቸው ነገሮች ግልጽ ከመኾናቸው የተነሳ ቆጥረን ኹላ ልንጨርሳቸው አለያ አጠቃለን ልንጨርሳቸው እንችላለን።

  የሰው ልጅ በዚህ ልክ እምነቱ ቀልሎ ነገሮች በነጻነት እንዲያከናውን ገርቶለት ሲያበቃ ነፍሲያና ሸይጣን ከዚህ ሐቅ እንዲዘናጋና (ጘፍላ) ውስጥ እንዲገባ ያደርጉታል። የምናያቸው መዘናጋቶች፣ በእምነት ስም የሚሰሩ ደባዎችና ሴራዎች ኹሉ ወደ ሐቅ ዓለም (የሩሕ ዓለም) እንዳንመለስ የሚያደርጉ ማዘናጊያዎች ናቸው። የእምነቱን መሠረታዊ ፍቁድ ነገሮች እንድንጣረስ ያደርጋሉ ይህ ካልሆነ ሐራምን እንድንሰራ ያለማምዳሉ ከዚህ ካለፍን በእምነት ውስጥ በሚፈጠሩ የነፍሲያ ችግሮች ((የዝና፣ ገንዘብ፣ ስሜት) ጣጣዎች ውስጥ እንድንገባ ያደርጉናል።

ከእነዚህ ኹሉ ጣጣዎች በግለሰብ ደረጃ ለመዳን የፈለገ ሰው በሰለዋት ኃይል ባርነትን ይለማመድ። ሰለዋት ከመረጃ በዘለል የማዕሪፋ ዕውቀትን (አላህን የማወቅ) ይከፍታል።

ዕለቱ ጁምዓ ነው። የካህፍን ምዕራፍ በዕለቱ ደግጋሞ ማንበብ አልያ ማዳመጥ ይወደዳል። በምዕራፉ ውስጥ ያሉት ዋና ሁለት ተዋኒያን ሰይድና ሙሳ እና ሰይድና ኸድር ውስጥ ብዙ እንማራለን። ሰይድና ሙሳ ታላቅ ነብይ ናቸው። ሰይድና ኸድር ደግሞ ፍጹም የኾኑ የአላህ ባርያ ናቸው።

ባርያ መኾን ምድር ላይ ካለ ከየትኛውም ማዕረግ በላጭ መኾኑን የምንማርበት ምዕራፍ ነው። ይህንን ደግሞ የመልእክተኞች ኹሉ ቁንጮ የኾኑ ሰይዲ ወቁድወቲ ነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከንግስና ባርነትን መርጠው አሳይተውናል። በማግኘት፣ በመቆጣጠር፣ የሰዎች ላይ የበላይ በመኾን የሚገኝ እረፍት የለም። በዚህ ውስጥም ውስጥን ማዳን ከባድ ነው። በማጣት፣ ባርነትን ለአላህ በማጽደቅ፣ ከእርሱ ጋር በመኾን የሚገኘው ክብር ግን ኃይል ነው።

ረጀብ ነው ኢስቲግፋር እናብዛ፣ ጁምዓ ነው በሰለዋት እንበረታ ካህፍን በማንበብ ከዋሻው ውስጥ ጥቂት ማዕሪፋን ለመውሰድ እንጣር።

ጁምዓ ሙባረክ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

10 Jan, 03:58


ድንገት ጠዋት ከእንቅልፋቹ ስትነሱ አንዱ አግራቹ ለሴኮንዶች አልታዘዝም ቢላቹ ምን እንደምትሆኑ አስቡት እስኪ🤔😢 እናመስግን።

አልሀምዱሊላህ ዓላ ኩሊ ሃል🤲

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

09 Jan, 23:40


ሎሳንጀለስ!!

አሜሪካ ሀያልነቷን ለማሳየት የጋዛ ህፃናት ላይ እሳት ስታዘንብ የሀያሎች ሁሉ ሀያል የሆነው አላህ እሳት እያዘነበባት ነው
እስቲ የፈጣሪን ጉልበት ቲየው።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

09 Jan, 23:05


ሰለዋት አውርዶ ህመሙ ያለቀነሰ ጭንቀቱ ያልተወገደለት አንድም ሰው አልሰማንም ። ከሰለዋት በመራቅ ግን ጭንቀት እና ህመሙ የበዛበት እንዳለ ለማወቅ ግን ሩቅ መሄድ አይጠበቅብንም እኛው ራሳችን ምስክር አለን ።

እስኪ ከህመምም ከጭንቀትም ትንሽ አረፍ እንበል ።

አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ወሸፊኢና ﷴﷺ💚💚 ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

09 Jan, 21:33


ኸሚስ አመሻሹን ዱአ ጀባታዬ🤲

የኢማንን ካባ የምንደርብበት የረጀብ ለይል አላህ ያድርግልን
ሀጅም ኡምራም ከተጠሩት ባሮቹ ያድርገን🤲

የነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን የእውነተኛን መውደድ የምንወዳቸው ያድርገን አብረን የምንቀሰቀስ አብረን ጀነት ጎረቤት የምንሆን ከሀገራቸው የምንሞት አላህ ያድርግልን

በዱንያ በአኼራም ከውርደት ነጃ የተባልን ያድርገን🤲

ሀገራችንን አማን መሻሂኮቻችን ረጅም እድሜ ለእኛም መዘየርን መጠቀምን ይስጠን🤲

ዱዐ አድርጉልን ላሉንም ላላሉንም ሙራዳቸውን ከሙራዳቸው በላይ ጭንቀታቸው ፈረጃ የሚያገኙበት ያድርግልን በኔ የጎደለውን አላህዬ ይሙላበት🤲

ሱብሀነ ረቢከ ረቢ ኢዘቲ አማ የሲፉን ወሰላሙን አለል ሙርሰሊነ ወልሀምዱሊላሂ ረቢል አለሚን
ያአላህ ያ አዚዝ ያ ከሪም
×3

ቢኢዝኒላህ ቢጃሂ ነቢዩነል ከሪም

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መልካም የኢባዳ ለይል ይሁንልን🤲

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

08 Jan, 15:52


አህባሽ ነህ ? ብለው ለሚጠይቁ ለአንዳንድ ወሃቢያዎች ምላሽ፦
------------ ------- ----- --
☞ ይህን ጥያቄ ብዙዎቻችን በሰፈር፣ በዩንቨርሲቲ፣ በኮሌጅ እና በኢንተርኔትም እንጠየቃለን ።

አንዳንዱ አህባሽ የሚባል ሀይማኖት የለም ይላል። አንዳንዱ ደግሞ አህባሽ ማለት የሀበሻ ሰው ማለት ነው ይላል። አንዳንዱም የዜግነት ስም እንጂ ሀይማኖት ስም አደለም ይላል። አንዱን ጠይቄው አዎ ፈረንጅ አይደለሁም፣ ሀበሻ ነኝ አለኝ። ሁሉም ትክክል ናቸው፣ ማንንም እኔ አልነቅፍም፣ ግን መልሱ መሆን ያለበት እንዲህ ነው።

አህባሽ ማለት ምን ማለት ነው ? ብለህ መልስህ እራሱን ጠይቀው። እሱ በሚመልስልህ መልስ መሠረት ተነስተህ መልስለት።

አህባሽ ብለህ "ወሃቢዮች" በውሸት ያጠፉትን ስም ከፈለክበት ማለትም (ቁረአን የጅብሪል ቃል ነው... እስከ መጨረሻው) ተብሎ የተዋሸባቸውን ከሆነ፣ እኔ ከዚህ የራኩ ነኝ፣ አህባሽ አይደለሁም።

አህባሽ ብለህ ግን የነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታይ የነብዩ ወዳጅ፣ የሰሃቦች፣ የሰለፎች፥ የኸልፍ ዑለማኦች ተከታይ፤ እንዲሁም የሐበሻው ጀግና ሼህ አብዱሏህ አልሐረሪይ አል ሀበሺይ (ረሂመሁሏህ) ተማሪ ማለትህ ከሆነ አዎ.. አዎ.. አዎ አህባሽ ነኝ፤ የሀበሻው ሼህ ተማሪ ነኝ፤ የጥንት ዑለሞች፤ የነ አንይ፣ የነ ዳንይ፣ የነ ጀበርቲ፣ የነ አብሬት፣ .. ወዳጅ ነኝ። ዐቂዳዬም የሙስሊሞች ዐቂዳ አሏህን ከአምሳያ ማጥራራት ነው። የነቢየ ወዳጅ፣ መውሊድን ማክበሬ አህባሽ ካስባለኝ አዎ.. አዎ አህባሽ ነኝ።

በዚህም ጉዳይ የሀበሻው ጀግና ሼኽ አብዱሏህ አል-ሀበሺይ እንዲህ ሲሉ ተነግረዋል፦ «እኛ ከ250 አመት በፊት የመጠውን ዲን አይደለም ምንከተለው፤ እኛ የነቢዩ፣ የሷሓቦች፣ የሰለፎች እና ታላላቅ የኸለፍ ዑለማኦች ተከታይ ነን፤ እኛ ከአህሉ ሱና ወልጀማዓ ከፊሉ ነን እንጂ ከኛ ውጭ አህሉ ሱና የለም አንልም» ።

በመቀጠልም ይህን የፈለክበት ከሆነ ጥያቄህን አስተካክል፤ አህባሽ ነህ ሳይሆን ሀበሽይ ነህ ወይ ? ብለህ ጠይቅ፤ በአረበኛው ቋንቋ መሠረት ሀበሽይ ለነጠላ ሲሆን አህባሽ ለብዙ ቁጥር ነው! እኔ ሀበሽይ "የሀበሻው ጀግና የሼህ አብዱሏህ" ተማሪ ነኝ እንጂ አህባሽ አደለሁም።

በመጨረሻም ላስረዳህ የምፈልገው፤ ይህ ስያሜ የመጣው ከወዳጅ ሳይሆን ከጠላት የመጣ ስያሜ ነው። እነሱ ለውርደት ነበር የለጠፉብን፣ ግን እኛ እንኮራበታለን። በተለይም እኛ ሀበሾች (የሀበሻ ተወላጆች)። ምክንያቱም ይህ ስያሜ በመጀመሪያ የተነሳው በሊባኖስ እና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት ነበር። እነሱ የሀበሻው ሼይኽ ተማሪዎች በማለት ለውርደት ነበር የተጠቀሙት፣ በመጨረሻም ይህ የኩራት ስያሜ ሆኖ ቀረ። አሁን ሊባኖስ ሀገር ሄደህ ሀበሺይ ነህ ካልከው በኩራት አዎ ይላል።

ለምሳሌ፦ ሼኽ ሆነህ የዲን ትምህርት እያስተማርክ ليس كمثله شيء ካልክ፤ ሀበሺይ ትባላለህ። በየመንገዱ እና በየሰፈሩ አሏህን መሳደብና በዲን ማፌዝን ሰምተህ ይህን በመሰለ ኩፍር ስታስጠነቅቅ ካየህ ሀበሺይ ነው ትባላለህ። ይህን ጉዳይ ለሼይኻችን ሲነግሯቸው ደስ አላቸውና «አልሐምዱ ሊሏህ፤ ለአሏህ ምስጋና ይገባው፤ በተከበረው የቁርኣን አንቀፅ እንድንታወቅ ላደረገን፤ አልሐምዱሊሏህ በሐቅ እንድንታወቅ ላደረገን» አሉ።

አኛም አልሐምዱሊሏህ.. አልሐምዱሊለሏህ.. አልሐምዱሊሏህ.. እንላለን።

የሼይኽ ሙሪድ ነኝ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Jan, 21:59


እነሆ ረጀብ

ለዚች ቀን ሲባል የታሰረ ቢፈታ የወደቀ ቢነሳ የተጣላ ቢታረቅ የታረዘ ቢሰነቅ የተከፋ ቢስቅ የተጨቆነ ቢካስ የተበላሸ ቢታደስ ደስታ ካፅናፍ አፅናፍ ቢናፈስ ምኞቶች ሁሉ ቢሳኩ እንኳን ለኔ ስጦታዬን ለማመስገኛ በቂ አይሆንም ነበር

የአንዳንድ ሰዉ መወለድ ለአንዳንድ ሰዉ ልክ እንደ እስትንፋስ ነዉ
አልሃምዱሊላሂ ረቢል አለሚን 🙏

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Jan, 21:47


የሰለዋት ኃይል

ሰለዋት በየትኛውም ሁኔታችን ውስጥ ያለ ጠንካራ መሠረታችን ነው። ሰለዋት ዚክር ነው፣ ሰለዋት መድሐኒት ነው፣ ሰለዋት ዱዓም ነው፣ ሰለዋት በአጠቃላይ ነብያዊ ኃያል ድምጽ ነው። ሰለዋት ላይ የተጠመደ ሰው የሚያጣው ልባዊ እርካታ የለም። ሰለዋት የተደበቀ ሐጃን ማውጪያ ስልት ነው። ይህ ነብያዊ ድምጽ ከፍ ሲል በውስጣችን ያለ ተውሒድ ይፋፋል፣ አምልኮዎች ይገራሉ፣ መረዳቶች ይመጣሉ፣ መንፈሳዊ በረከቶች ይሰፋሉ። በተቃራኒው ነብያዊ ድምጽ (ሰለዋት) ሲቀንስና በልኩ ከእኛ ከራቀ የእምነት መረጃዎች ውስጣችን ኢማን ለመዝራት ሩቅ ይኾናል፣ መንፈሳዊ ልምምዶች ትክክለኛ ትርጉማቸውን ያጣሉ፣ የተለያዩ ድምጾች እኛ ልብ ውስጥ ይገዝፋሉ።

ለዚህ ነው በእያንዳንዱ ዚክሮቻችንና ዱዓዎቻችን ውስጥ የዓለሙን ኑር ላይ ሰለዋት የምናወርደው። በየዕለቱ የሰለዋት ዊርዳችንን እናጠናክር፤ መንገዳችን ላይ ለሚገጥመን ብዥታም መፍትሔ የምናገኝበት ነው።

አላህ ይረዝቀን 🤲🤲

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Jan, 14:40


የእከሌ ልጅ ባንቱ ላይ ሰለዋት አውርድዋል
ተብሎ ስምህ የዓለማት ነቢይ ﷺ ፊት መነሳቱ ምን ያማረ ነው!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Jan, 03:31


አንተ ጠዋት ተነስተህ ፊትህን ስትታጠብ አንደኛው በተመሳሳይ ሰዓት ኩላልቱን ይታጠባል።

አልሀምዱሊላህ ዓላ ኩሊ ሃል🤲

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Jan, 00:45


አዝናለሁ😢 ያ ረሱለላህ ﷺ ሰው ሁሉ በዱኒያ ቢዚ ሆኗል።

ሸረሪቷና እርግቧ እንኳን አንቱን አልረሱም።
ራሳቸውን ለአንቱ ፊዳእ ለማድረግ ከፊት ነበሩ እኛ ግን የት ነን😢

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 23:25


ነቢ ላይ ሰለዋት ስታወርድ እንደራስህ ቀድር ነው አላህም ባንተ ላይ ሲያወርድ እንደራሱ ቀድር ነው።

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 22:56


ወቅቱ ረጀብ ነው ያአላህ ወር ነው ዱአ ወጥሩ ብዙዎች ሀጃ አሉብን 🤲🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 22:00


አብሬት ሀሪማ💛💛


(አባባ በወእዝ እንዲህ አሉ የአብሬት
መውሊድ ሲቃረብ #በሙሪዱ ላይ ምንም
የሌለበት ሀጃ ልክ እንደ ንብ ይጭንበታል
አሉ በዛ ሃጃ ተውጦ ከቀረ ከሃጃው ጋር
መቼም አይላቀቅም ነገር ግን እምቢ ብሎ
ትቶት ወደ አብሬት መጥቶ መውሊዱን
አውጥቶ ሲሄድ ልክ ከአን ለምየኩን
አርጎ ሃጃውን ምንም እንዳልነበረ አርጎ
ይጠብቀዋል አሉ ስለዚህ ነቃ ነቃ በሉ
መቅረት ማይቻልበት መውሊድ😍🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 21:32


#comand post🤔 አብሬት ለምንሄድ ሰዎች🤞

®እኛ እብድ ይምንላቸው ሰዎች
®እኛ ድሀ ብለን የምናስባቸው ልብሳቸው የተራቆቱ የተቀደደ ልብስ የለበሱ የማናውቃቸው የአሏህ ባርያዎች
®እንዲሁም ገሪባ ጃዚብ የሆኑ ሰዎችን ከመተናኮል ከመስደብ ከመናቅ ሀታ ለኛ የማይመስል ነገር እንኳን ቢያደርጉ በፋፁም መናገር እንደሌለብን ነው👐

®ሌላው ደግሞ ኒያችንን አጥርተን ሴቷ ወንዱን ወንዱ ደግሞ ሴቷን ከጅሎ ሣይሆን አሏህና ነቢን ብቻ ቀስድ አድርገን ከልባችን ጥርት ያለ ኒያ አድርገን እንሂድ👐

#ሼር አድርጉት

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 21:26


አባናዬ ተጋበዙልኝ💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 21:20


#አብሬትዬ

ገና ወር ሲቀረው ነው ሩሄ ጀሰዴን ጥሎ ወደ እዚህ ወደ ፍቅር ወደ ሰላም ወደ ደስታ ወደ መደድ መንደር አብሬት የሚገሰግሰው እና የፊታችን ቅዳሜ ረጀብ ጀሰዴን ከሩሄ ላገናኝ ወደ አባና የሩህ ሸኀና ሀገር እኮበልላለሁ እንዳትቀሩ ሁላችሁም ተጠርታቹሀል 🥰🥰
እዚህ ቁጭ ብለህ ዝባዝንኬ ከምቀባጥር በሰው ወሬ ከምትነዳ እነ እከሌ አሉ ጠሉ ብለህ ከምትጠላ እራስህ መጥተህ ቦታውን አይተህ ወስን እርግጠኛ ነኝ ልትወደው እንደምትችል
አብሬትን በመታደም እንጂ በወሬ አትረዳውም ሀላስ 👐
💚

ኢንሻአላህ እኔም ዘንድሮ እዚህ ቦታ እገባለሁ በአላህ ፊቃድ

ጥሪያችን ይድረስ ብለናል

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 21:04


ሺሊላ አበራ ሙዜ
አሁን ትንጠራ ባሸን ይፈዜ
አባና አበራ ሙዜ አሁን ትንጠራ ባሸን ይፈዜ

አባ ዘንድሮ ጥሩኝ ያንቱ ሀሪማ አስገቡኝ🤲🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 20:52


የምክር ስንቅ ✍️

ስለ አብሬት መውሊድ ከሰማሁት

ኸይር ነገር አስበህ ከሄድክ ጥሩ ምንዳ አግኝተህ ትመለሳለህ አቃቂር አልያም ሸ*ር  አስበህ የሄድክ ጊዜ ያሰብከውን ታገኛለህ ታያለህም ስለዚህም ኒያህን አስተካክለህ ሂድ ጥሩ ነገር ታያለህ ተጠቅመህም ትመጣለህ ይባላል ኒያ እንሳምር።

በተረፈ በዚህ መውሊድ አላህንና ነቢን ብሎም አካቢሮቹን ምናገኝበት ይሁንልኝ እላለው

ሁሉም ሙሪድ እንደሚለው #አብሬት አናዠ ተብላሸ  እላለሁ
ይህቺን ቃል እዛ ስትገባ ነው ምትረዳት።

ኢንሻአላህ በአላህ ፊቃድ እዛው እንገናኛለን::

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Jan, 19:55


ይህ ውብ መስጂድ የት ሀገር ነው ይገምቱ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Jan, 23:46


የእከሌ ልጅ ባንቱ ላይ ሰለዋት አውርድዋል
ተብሎ ስምህ የዓለማት ነቢይ ﷺ ፊት መነሳቱ ምን ያማረ ነው!

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Jan, 20:17


🤲አላህ ካልፈቀደ ተኝተን ለመንቃት አቅም የሌለን

ደካማ ......ፍጥረቶች እኮ ነን❗️

ደህና እደሩ 🥺

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Jan, 20:13


ማንም እናት ከሰይዳችን ﷺ ♥️ በላይ ምርጥ ልጅ አልወለደችም።

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Jan, 19:37


እደግመዋለሁ
አድናቂህን እንዳታገባ:: <<ዊህ አንተ ነህ እንዴ>>? ትልሃለች:: ስታደንቅህ በነበረችበት ወቅት እንደሰው የምትፈሳና የምታገሳ አይመስላትም:: ስለዚህ ወይ ከገጠር ወይ ከማይታወቅ ጀማዓ ይዘህ ና:: ድንቅ መሆንህን እየተረዳች ስትመጣ እያደነቀችህ ትኖራላችሁ::

ሸይኽ ጫሊን የማያውቅ የዚህ ገጽ አንባቢ አይኖርም:: በዘመናቸውም ድንቅ ነበሩ:: ሴቱ ሁላ ሸይኽ ሲያልፍ ጎንበስ ብሎ ነው:: አንዱ ወዳጅ ቆንጆ ልጁን አንስቶ ጀባቸውና አገቡ:: የሌሊት ጭለማው ሄዶ ጠዋት ትክ ብላ አየቻቸውና "ሰው ሁላ ሸይኽ ጫሊ እያለ የሚያብድልሁ አንቱ ነሁ?" አለቻቸው

መልሳቸው ትንሽ ገራሚ ነው:: ይለፈን::

ምን ድንቅ ምን ጀግና ብትሆን ዝናርና ቀበቶ የሚያስፈታ ሀጃ ላይ መውደቅህ አይቀርም:: ያው ያስገምትሃል:: ፑ😊😂

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Dec, 21:39


መካ እና መዲና #ካፊር ሄደበት
ያንቱ ወዳጅ ቀረ ገንዘቡ ጎሎበት አሉ ሸሆቹ

መገን ነቢ
በሀበሻ የሚገኙ ሙስሊሞች ነቢን በማወደስ በሌላው አለም ካሉ ሙስሊሞች እጅግ ይልቃሉ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Dec, 21:23


የቁባ አባ😍

ሼሆቹ የጉራጌ ማሕበረሰብ ከመብራቅ አምላኪነት ወደ ሀቂቃው ዲን እስልምና እንዲገባ ያደረጉ ትልቅ የአሏህ ባሪያ ወልይ ናቸው 🙌

አባ ደዋም💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Dec, 21:20


አሏህ የቁባን አባ ባይሰጠን ኖሮ
ይሄኔ ቦዥ ለመብረቅ ሰጋጅ ትሆን ነበር🤔
ሺሊላ የቁባ ጌታ አለብን ብዙ ውለታ🤲

ተናፍቂ 15 ቀናቶች

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Dec, 21:14


ለአላህ በሚስጥር ያንሾካሾክነው ሀጃ በዛሬው ለይል ይውጣ😢🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Dec, 21:10


የዘመናችን ሰው እንደ ማማ ነው ከሆዱ እየከዳ ካፉ ግጥም ነው የዘመናችን ሰው እወደው እጠላው ቸገረኝ እንዴት ነህ ይለኛል ምሶ እየቀበረኝ

(ሼህ አደም ደርቃ)

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Dec, 15:09


ኢናሊላሂ ወኢና ዒለይሂ ራጂዑን😢

#የዲን ታጋዩ ወንድማችን ሳዳት ያሲን ዛሬ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ወደ አኼራ ተሻግሯል።
ወንድማችን ያሳለፍነው እሁድን በጋብቻ ተጣምሮ ነበር
የሚያሳዝነው ግን 2 ቀን እንኳን ሳያድር ለዛ ቆራጭ የሆነው ሞት መጣ!
የአሏህ ውሳኔ ነውና ምን ይደረጋል።
ሙሽራው ወንድማችን አሏህ በጀነት ይሞሽርህ።
አይ ዱንያ😢

"ሁላችንም ፍቲሃ እንቅራለት"

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

24 Dec, 11:16


መገርገቢያ💛

አጊሰኒ

ያሰሪአን ቢልከራማ ያሸፊአን ቢሰላማ አጊሰና ያኑርሁሴን

አቢዮ አማና💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 23:01


ሺሊላ ሺሊላ

የመንዙማ PDF ጀባ ብያለሁ እንግዲህ በዱአችሁ ንከሱኝ🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 22:21


🍁 ሴቷ ማዲህ .......

🍂 አንዲት ሴት ኩበት እየለቀመች መንዙማውን እንዲህ እያለች ታንጎራጉራለች

አወየው ነቢ ፣ አወየው ነቢ
ሙሀመድ ነቢ ሰላም አለይክ እየለች ስትመድህ

🍂 ጌታው ሰይድ ጫሌ ሰሞት ብድግ አሉና ማነች ይቺ የሴት ማዲህ ዝም በይ በሏት አሉ። እርሷም ሰማችና እንዲህ አለች።

🍂 እኛ አርግዘነዎት: እኛ ወልደነዎት
አኛ አጥብተነዎት
ቃልቻ ዝም በል ነቢ የኛ ነዎት ፣አለች።

🍂 ጫሌም አረገኝ ወደየት ወሰደችው አሉና ወንድን ወንድ ሲመድኽው ነው ሚያምረው ብለን እንጂ ሌላ አይደለም አሏት። እሷም

🍂 ወንድነት ሲጠቀም: ሴትነት ሲጎዳ
እንገናኛለን አረደል በይዷ ሜዳ አለቻቸው።

🍂 እሳቸውም አረ በኸለቀሽ አረ እንደዛ አይደለም የዛሬን አፉ በይኝ ብለው ዱስቱር አሉ።

🌹 የሴቶች ሀድራ ስትሰሙ ሁሉ ለምትንጫጩ አደብ ብለናል።


አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ወሸፊኢና ﷴﷺ💚💚 ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 21:06


ሺሊላ ሺሊላ👏👏

ሀያት ኡስታዝና😘
ተቃጠለ ደሜ ጉድ ፈላ ሙሐመድ ተቃጠለ ደሜ ይህ መንዙማ PDF በአረብኛ ጀባ እላችኋለሁ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 21:00


ሺሊላ ሺሊላ👏👏

ተቃጠለ ደሜ ጉድ ፈላ ሙሐመድ ተቃጠለ ደሜ ሚለው መንዙማ PDF ጀባ እላችኋለሁ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 20:53


ሺሊላ ሺሊላ የሚለውን መንዙማ PDF ትፈለጋላችሁ

እስቲ 50 Ract አድርጉልኝ እለቃለሁ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 20:47


በአህያ ላይ ተጉዟል በኬሻ ላይ ተኝቷል
ከድሆች ጋ ኖሯል ደረቅ የገብስ ቂጣ በልቷል

ነገር ግን የአለም ንጉስ ነው የኔ ነቢ 😥

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 20:41


ጫት ለመቃም የራሱ መቃም አለው:: ካልሆነ ግን ይቅምሃል😊

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 12:35


ደረሰ አብሬትዬ መውሊድ

#የዘንድሮውን አብሬት መውሊድ መቅረት አይታሰብም ኢንሻአላህ እኔም በአላህ ፊቃድ አብሬት መውሊድ ላይ እገኛለሁ የአብሬት ሙሪዶች በዱአችሁ ንከሱኝ አላህ ያገናኘን 🤲

አሸይኹና አብሬት የኛ የዲኑ ጋሻ
ጠራጊ ነበሩ የቀልብን ጠቀርሻ
ሀድራቸው ነበረ የኢማን ማደሻ
አባና ነበሩ የሁሉም መሸሻ
ይስጠን ትልቅ ድርሻ ረቡነል ኩበራ

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

23 Dec, 12:26


አብሬት የነቢን መውሊድ በረጀብ የሚያወጡበት አንዱ ምክንያት ነቢ ﷺ የተፀነሱትና ከውልደታቸው በፊት ቀድሞ ብስራቱ የተጀመረበት በረጀብ ወር ስለሆነ ነው አላህ ያድርሰን🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

22 Dec, 15:14


አልሃምዱሊላህ

113ኛው የቃጥባሬ መውሊድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ
ስነ- ስርዓቶችች በድምቀት ተከበረ አልሃምዱሊላህ አላህ የዓመት ሰው ይበለን።

ታህሳስ 12/13/2017 ዓ.ም(ወልቂጤ)
በቀቤና ልዩ ወረዳ የሚገኘው ጥንታዊውና ታሪካዊ የቃጥባሬ መውሊድ ለ113ኛ ጊዜ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርአቶች በአማረ መልኩ ተከብሯል የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከሀገር ውጭ የመጡ እንግዶችም ተገኝቷል።

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 20:05


#ላንድም ሶለዋት ማውረድ ይሁን ሰበብ የሚሆንህ ሰው ጋር ተቀማመጥ!!💚💙

አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወዚድ ወባሪክ ዐለይህ ወዐላ አሊሂ ወሷህቢህ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 19:58


ሰፕርይዝ 1

ንገራቸዋለው ኢንሻአላህ ሌላው በቅርቡ አብረን እናያለን።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 19:42


ታህሳስ 6

መውሊድ ለሀገር ሰላም እና ለ አንድነት
   በነብዩ ፍቅር እና በ ዑለሞቻችን መንገድ   ህያው ነን
ታህሳስ 6-2017- በ 6ኪሎ ስብሰባ ማዕከል ልዩ የመውሊድ  ዝግጅት  ከ ታላላቅ መሻይኾች ሙህራኖች ዳዒዎች እንዲሁም ማዲሆች የሚገኙበት ድንቅ ዝግጅት ።
አዘጋጅ የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር (ነጃሺ ኢስላማዊ ማህበር)‼️

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 19:04


#ታህሳስ_6_2017

#በ6ኪሎ_ስብሰባ_ማዕከል
#መዉሊድ_ለሀገርሰላም_እና_ለአንድነት_በነብዩፍቅር_እና_በዑለሞቻችን_መንገድ_ህያዉነን

ታላቅ ሰፕርይዝ ይጠብቃቸዋል

ለዓለም ደምቀን_የምንታይበት_ቀን አላህ በሰላም ያድርሰን🤲 የውሸት ጊዜም ኢንሻአላህ ያበቃል::

የነቢ ﷺ መውሊድ ዘንድሮ ተባባሰን።

ቪድዮ ከስራ እለቃለሁ አውርዱት::

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 18:49


ታህሳስ 6

ምስጥሩን ልንገራችሁ አሁን ተዘጋጁ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 15:54


አሏህ ጠላቶቻችንንም ሃብታም ያድርግልን
በራሳቸው መሽጉል ያድርግልን ☝️🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 15:02


#ሕመምን_መውደድ

ኢማም ጁነይድ (ቀደሰላሁ ሩሓሁ) እንዲህ ይላሉ ፦

« ሪዷ (ፍጹም ወድዶ መቀበል) ማለት እኛ ላይ የደረሱትን አደጋዎች (ችግሮች፣ሕመሞች) ልክ እንደጸጋዎች መመልከት መቻል ማለት ነው።»

ሰይድና ሩሚ (ቁዲሰ ሲረሁ) በተለያዩ መልእክቶቻቸው ውስጥ በሕመም በኩል ወደ ውስጣችን ብርሀን እንደሚሰርጽ ይነግሩናል። ይህ ማለት ችግር እንዲነካን መመኘት ማለት ሳይኾን በቀናት መካከል ችግር እኛን መንካቱ የማይቀር መኾኑንና እነዚህ የሚነኩን ሕመሞች ውስጥ በትዕግስትና የነካንን ነገር ወድዶ በመቀበል አላህን ማግኘት እንደሚቻል የሚጠቁመን መልእክት ነው።

የምንኖርበት የኑሮ ውጣ ውረድ፣ የገጠመን የብቸኝነት ችግር፣ ያለማግባት፣ ከጥንድህ ጋር ያለመስማማት፣ የልጅህ ባህርይ ችግር፣ የሥራ ማጣትህ፣ ያለማግባት፣ ያለመውለድ .....ሁሉም ሰው የሚነካው ችግር ሁሉ በራሱ ፈተና ነው።

ሰይድና ሩሚ ሌላ ቦታ ሲያክሉ "አንተ ማለት የወንጀሎችህ ድግግሞሽ ውጤት ነህ" ይላሉ። እያንዳንዱ ወድቆ የመመነሳት ታሪካችን ሳይቀር የዚሁ ፈተና አካል ነው።

ያጣናቸውና አጣናቸው የምንላቸው ነገሮች ኹሉ ስናገኛቸው ደግሞ በሌላ ገጽ ፈተና ኾነው መቀጠላቸው አይቀሬ ነው።

የምትናፍቀው ትዳር ከአመታት በኋላ አግብተህ ፈተና ኾኖ ሕይወት ይቀጥላል። የምትናፍቀው ገንዘብ ከሆነ ጊዜ በኋላ አግኝተኸው የፈተና ማዓት ጎትቶ ይመጣብሃል። ይህ የኾነው አገሩ ዱንያ በመኾኑ ነው። በዚህች ዓለም ውስጥ ማግኘትም ኾነ ማጣት፣ ምቾትም ኾነ እንግልት ገጻቸው ይለያይ እንጂ ፈተና አለባቸው። ዱንያ ውስጥ እየተፈኑ መማር፣ እየተፈተኑ ብርሃን ማግኘት የአማኞች ዕጣ ነው።

በዚህች ዓለም ውስጥ "ደስተኛ መኾን" ግዴታ አይደለም። በደስታ ውስጥ ውስጣዊ ሰላም ከሌለ ደስታው ጎዶሎ ነው። በሐዘንና መከፋት ውስጥ ውስጣዊ ሰላም ካልለ ተፈላጊው እርሱ ነው። ሰዎች ሲያዝኑ እምባቸው ሞቃት ነው፣ ሲደሰቱ እምባቸው ቀዝቃዛ ነው። እናታችን መርየም የተከፋችና ያነባች ጊዜ አላህ እምባዋን በተቃራኒው ቀዝቃዛ አደረገላት።

ይኸው ነው! እያለቀስን እየተከፋን ሕይወትን እንቀጥላለን ግና ለቅሶኣችን ለሰዎች ሳይኾን የሚቀርበው ለአላህ ብቻ ነው። በሕይወት ውጣውረድ የሚገጥመንን ስሞታ ኹሉ ለፍጡራን አንናዘዝም፣ ከእነርሱም አንጠብቅም መጠቀብም ማሶመትም የሚገባን ለአላህ ብቻና ብቻ ነው።

ልክ እንደ ሰይድና ያዕቁብ፣ የልጅ መጥፋት ከባድ ፈተና ነው፣ ሐዘንና ስቃያቸውን ያቀረቡት ግን ከአላህ ብቻ ነው፣ ከሰው የጠበቁት ክፍያም ኾነ ደሞዝ የለም። አላህ እኛ ላይ የወሰነውን ወድዶ መቀበል (ሪዷ) ማለት ይህ ነው።

አላህ ያስረዳና 🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 10:54


#የረቡዕ_መጅሊስ_ወግ
#አወሊያዎቹ

ይህ ሰአት ዱዓ ተቀባይነት የሚገኝበት ወቅት ነው። ረቡእ በዝሁር እና ዐሥር መካከል ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው በሐዲስ መጥቷል። ከእያንዳንዱ ቀናት ጀርባ በርካታ ምሥጢሮችን የተረዱ ዓሊሞች ቀናቱን ከፋፍለው ዱዓና ሰለዋቶች በማደረግ ዘመን የሚበትነውን ጘፍላ መርታት ችለዋል።

በመጅሊስ ኒያ ሥራ ላይ ላላችሁ፣ እንዲሁም ተመችቷችሁ ዱዓ ለተቀመጣችሁ ሰዎች የሁለት አውሊያዎችን ገጠመኝ ላወጋችሁ ወደድሁ።

በቅርብ ዘመን ግብጽ ውስጥ የነበሩት ኢማም ሻዕራዊ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) መዲና ዚያራ በማድረግ ላይ ሳሉ የሰይዲን ዶሪሕ ተበሩክ ሲያደርጉ አንድ ሹርጣ (ፖሊስ) መጥቶ ይህ "ቢድዓ" ነው ብሎ ይከለክላቸዋል። አውሊያ መች የክርክር ናዳ ውስጥ ይገባል። ብዙ ካስረዱት በኋላ እንኳን እርሳቸውን በከበበው ነገር ቀርቶ አንተ እዚህ ኺድማ ላይ ባለኸው እንኳን እባረካለሁ ብለው ሰውነቱን አሻሽተው በረካውን ወሰዱ። :-D  (ዝርዝር ጭውውታቸውን ከዚህ ቀደም አጋርቼው ነበር።)

አይ ዑለማ! ልባቸው ሰፊ ነው፣ ከማይረዳቸው ሰው እንኳን መወሰድ ያለበትን ያውቃሉ። ፖሊሱ እምነቱን በተዳረዳው ልክ ነበር ግና ያላየው ዕይታ ነበር እርሱን አስተማሩት ምን አልባትም ልቡን ጠረጉለት

****

አንጋፋዊው ዛሒድ የነበሩት ኢብራሂም ቢን አድሀም (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ጊዜ ወደ ሻም ጉዞ ሲያደርጉ የገጠማቸውን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ በመንገድ ላይ ሳለሁ ውሃ ጠማኝና አንድ ፍየል ጠባቂ እረኛ ስመለከት ተጠጋሁና እንዲህ አልኩት፦ የሚጠጣ ወተት ወይም ውሃ ይኖርሀል?
እንዲህ አለ፦ የትኛው ቢመጣልህ ትወዳለህ?
"ውሃ" ስል መለስኩ። በያዘው ልምጭ መሬቱን ሲወጋው ውሃ መፍለቅ ጀመረ! በጣም ተገረምኩ።
"አትገረም ጠጣ" አለኝ። ውሃውን ጠጣሁት ከበረዶ የቀዘቀዘ ከማር የጣፈጠ ውሃ ነበር። እያየሁት ቆሜ ቀረሁ። ከዚያም ይህ እረኛ እንዲህ አለኝ፦ « ኢብኑ አድሀም አንድ ባርያ አላህን ከታዘዘ ሁሉም ነገር ይታዘዘዋል።»

ምንጭ፦ [ሲየር ኢዕላም አኑበላእ ወሒሊየቱ አልአውሊያ]

አላህ የአውሊያዎችንና የዑለማዎችን ቀድር ያሳውቀና 🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

04 Dec, 10:44


#ዶክተር_ሸይኽ_አሕመድ_ዐጁር
ወደ #ሸይኹል_ኢስላም_ሸይኽ_ዐብዱሏህ_አል_ሀረርይ ረድየሏሁ ዐንሁ ሲመጡ የ12 አመት ልጅ ነበሩ ከዛኔ ጀምረው በሸይኻችን በተገቢው መንገድ ተኮትኩተው ያደጉ ትንታግ ናቸው። ሸይኻችንም ከሙራድ ካደረሱ በኋላ
"فأما أحمد أنا عنه راضي"
ሲሉ በአጭር ቃል ገልፀዋቸዋል።... አዎ ተማሪ ማለት መምህሩ እሚፈልገው ቦታ ደርሶ የሚታይ ነው!
ሸይኽየው ዶክተሩን በዚህ መልኩ የመግለፃቸው ሚስጥር የሚገለጥልህ የዶክተሩን
"حسن التعامل بين الناس"
የሚባል ኪታባቸውን የዳሰስከው ከሆነ ነው... ይህን ኪታብ #ፕሮፌሰር_ሸይኽ_ጧሪቅ_አል_ለሓም أ.د الشيخ طارق اللحام በሚገባ ተንትነውታል ... ኪታቡ ህይወትን መስመር ለማስያዝ ወሳኝ ነው በተለይ ደግም ለጧሊበል ዒልም ታላቅ ስንቅ ነው። ከዩቲውብ አውርዳችሁ በመከታተል አሊያ ደግሞ ተለቂ ከወሰደው ሰው በመማር ህይወታችሁን አሳምሩበት።
የዶክተሩን ዱሩሶች መከታተል ለሚፈልግ
👇👇

https://www.facebook.com/ProjectsAssociation ቻናል ማግኘት ይችላል።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

03 Dec, 22:15


የተከበረው ወር 🌙
87 ቀናት ብቻ ቀርተውታል
አላህ ደርሰዉ ከሚፆሙት ያድርገን 🤲አሏህ በስላም ያድረስን😍👌

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

03 Dec, 17:31


ታህሳስ 6

ታላቅ ሰፕርይዝ ይጠብቃቸዋል

ለዓለም ደምቀን_የምንታይበት_ቀን አላህ በሰላም ያድርሰን🤲 የውሸት ጊዜም ኢንሻአላህ ያበቃል::

#ሼር_አድርጉት

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

03 Dec, 13:36


ፍልቅልቁ ዮርዳኖሳዊው ፈርጥ #ዶክተር_ሸይኽ_ማዚን_ዐብዱረሕማን_ሷሊሕ_ጛኒም
الشيخ الدكتور مازن غانم
በ1972 በሀገሪቱ ዋና ከተማ "አማን" የተወለዱ ሲሆን ዑሉሙል ቁርኣን ወተፍሲሪህ፣ኡሱሉዲን ወፉሩዒህ እና አተሰውፉል ኢስላሚይ በሚባሉ ፊልዶች ድግሪያቸውን፣ማስተርሳቸውን እና ዶክትሬታቸውን በጥሩ ሁኔታ አጥንተዋል። #ከታላቁ_ኢማምና_ሙጅተሂድ_ሸይኽ_ዐብዱሏህ_አል_ሀረርይ ዘንድም በሚገባ ተምረዋል።
#ሰዪዲ_ሸይኽ_ማዚን_ጛኒም ወደ #ሸይኹል_ኢስላም_ሸይኽ_ዐብዱሏህ_አል_ሀረርይ ዘንድ እንዴት መጡ? ...
በጊዜው የዮርዳኖስ ሙፍቲ ወደ ነበሩት #ሸይኽ_ኑሕ_አል_ቁዷት ዘንድ በመሄድ "ሸይኺ ሸይኽ ዐብዱሏህ አል ሀረርይ ስለሚባለው ሰው ምን ትላላችሁ? አንዳንዶች ሲያወግዙት፣ሲሰድቡት፣ሲያፌዙበትና ሲዋሹበት እመለከታለሁ አንዳንዶች ደግሞ ታላቅ ዓሊም ነው፣የሐዲስ ሊቅ ነው ሲሉ እሰማለሁ እንደሚባለው አይነት ዓሊም ከሆነ ደግሞ እኔ ከእርሱ ዒልምን መማር እፈልጋለሁ" በማለት ይጠይቃሉ። የዚህን ጊዜ ሙፍቲውም(ሸይኽ ኑሕ አል ቁዷት) {"እንዴታ ተማርበት እንጂ እኔም ሶሪያ በነበረት ወቅት ሐዲስ ተምሬበታለሁ።ሸይኽ ዐብዱሏህ ማለት እኮ ኢማም፣ሓፊዝ እና ሙጅተሂድ ነው። በእኔ የህይወት ዘመን ከእርሱ የበለጠ በዒልም፣በጥንቁቅነት፣በዙህድም ሆነ በተቅዋ አይቼ አላውቅም።"} በማለት ምስክርነታቸውን ይሰጧቸዋል ... ከዛም ሸይኽ ማዚን ጛኒም እንዲህ ይላሉ "#ከሸይኽ_ኑሕ_አል_ቁዷት ይህን ምስክርነት ከሰማሁ በኋላ ዒልምን ለመማር ወደ ሸይኽ ዐብዱሏህ አል ሀረርይ ጉዞየን ቀጠልኩ" ... ።

አሕሰንተ ያ ሸይኽ ማዚን አዎ እንዲህ ነው የተማሪ አደቡ ስለ አንድ ሰው ውዳሴም ሆነ ውግዘት ስሰማ የተማርከው ዒልም ሰውየውን ለመመዘን በቂ ካልሆነ በጭፍን አይኬድም እውነታውን ከተገቢ ሰው በመጠየቅ መረዳት የተማሪ ወጉ ነው።

رحمك الله يا شيخ نوح القضاة
ورحمك الله يا معلم التوحيد يا هرري
وحفظك الله يا شيخ مازن غانم

#ወዳጆቼ ከሸይኽ ማዚን ተግባር የምንረዳው ነገር ያለ ይመስለኛል። በአሁኑ ስዓት ስለ መውሊድ አሊያ ደግሞ ስለ ተወሱል ወይም ስለ ተንዚህ ሲያወራ የሰማነው ሁሉ የአህሉ ሱናህ ተከታይ ነው ማለት አይደለም። ማንነቱን የማናውቀው ሰው የሚናገረው ነገር [ዲን ነው] ብለን ከመቀበላችን በፊት ማንነው? ሰንሰለቱስ የት ድረስ ነው? ብለን ከተገቢ ሰዎች ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ራሱን ወደ አሻዒራና ማቱሪዲያህ ያስጠጋ ሁሉ ሆኗል ማለት አይደለም። አልሐምዱሊሏህ በሚዲያው ዓለምም ጥርት ያለ ዒልምን የሚያስተላልፉ በርካታ መሻይኾችን አሏህ ሰጥቶናል እዛም እዛም መደናበር አያስፈልግም።

ወደ ዋናው ርዕስ ስንመለስ የእኒህን ወርቅየ ሸይኽ ደርስ በፔጃቸው እየገባችሁ ተከታተሉ። አትቦዝኑ ዐቅለኛ ስራ አይፈታም።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

02 Dec, 20:22


እስከ መች በፎቶ ብቻ😥

ከትንሽ እስከ ትልቅ አዋቂም ጃሂል:
በፍቅሩ ተይዞ በናፍቆቱ በግኗል:
ኢሳም ተመኝቶ ሙሳም ለምኗል:
ኢልያስና ኸድር አመታት ጠይቀዋል:
አደም ተወስሎ ምህረትን አግኝቷል:
ኸድርና ኢልያስ በነቢዬ ﷺ ፍቅር ከላይ ተሹመዋል:
እኛ በምን ስራችን ይሄን ክብር አገኘን?
ኡመቱ አድርጎ ከሁሉ አበለጠን:
አልሀምዱሊላህ ምስጋና ይድረሰው ይሄን ላደለን:
ያንን ውብ በመናም ማየትን ፍቀደን:
እዝነትህ ሰፊ ነው ጌትዬ አታሳፍረን:
መዲና ከረውዷው መሄድን ወፍቀን ዘንድሮ።

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

02 Dec, 20:06


በውስጥ መስመር የተሰጠኝ አስተያየት አላህ ያክብራችሁ በዚሁ መስመር ላይ አላህ ያበርታን🙏

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

02 Dec, 19:58


ስህተትን ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ እባካችሁ ጀዛኩሙል'ሏህ ኸይራ

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

22 Nov, 14:40


የተሳካ ማጨት + የተሳካ ጋብቻ + የተሳካ ዱኒያ + የተሳካ ትዳር + ፍሬው ያማረ ዘር  ለሰላዋት ወዳጆች በሙሉ

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

21 Nov, 16:50


ኸሚስ አመሻሹን 💛

ነቢ ሰለዋትህን እየጠበቁ ነው 💚

ያላገባም ያገባል፣ ያገባም ይወልዳል፣ የወለደም ይጦራል
የታመመ ሁሉ ይድናል! ያጣ ሁሉ ያገኛል! ብቻ ደስታ በደስታ ይሆናል ብቻ በሰለዋት እንበርታ

የተሳካ ማጨት + የተሳካ ጋብቻ + የተሳካ ዱኒያ + የተሳካ ትዳር + ፍሬው ያማረ ዘር  ለሰላዋት ወዳጆች በሙሉ

ጊዜው ደስታን ባይሰጥም አላህ ደስታ እና ወቅቱ ጥሩ እንድያርግልን በዱአህ  በሰለዋት መበርታት ነዉ አሏህ ይሄን ጊዜ ያሳልፈን

አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ወሸፊኢና ﷴﷺ💚💚 ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

21 Nov, 16:36


#ለይለቱል ጁሙዐህ

اللَّهمَّ صلِّ صلاةً كاملةً، وسلِّم سلامًا تامًّا، علىٰ نبيٍّ تنحلُّ به العقدُ، وتنفرجُ بهِ الكُرَبُ، وتُقْضَىٰ بهِ الحوائجُ، وتُنالُ بهِ الرَّغائبُ، وحسنُ الخواتيم، ويُسْتَسْقىٰ الغمامُ بوجههِ الكريم، وعلىٰ آلهِ.
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ወሸፊኢና ﷴﷺ ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

21 Nov, 12:36


ሰሉ ዐለ ነቢ💛

ሰለዋት የገራልህ ሰው ከሆንክ ከነቢ ጋር ያለህ ኔትወርክ እንዳልተቋረጠ እወቅ

አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ወሸፊኢና ﷴﷺ ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

21 Nov, 12:31


ኸሚስ ሙባረክ

"ሰለዋትን አትቁጠሩ ይልቁን እስትንፋሳችሁ በሙሉ ሶለዋት አድርጉ"

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

21 Nov, 12:28


ወደ መጅሊስ በድርድር ለመግባት ያሰፈሰፉ ሰዎች የመጅሊሱ ወንበር የሚታያቸው❗️😒

ተደራድረውና ተመራርጠው የገቡት ለራሳቸው ፏፏ ከማለት ውጪ እስኪ ከመወሰድ ያተረፉትን መስጂድ እና ከመታሰር ያዳኑትን አንድ ሰው ንገሩኝ❗️

ለማንኛውም ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን እንዳሉት ስልጣን የሚያዘው በኮሮጆ እንጂ በመናጆ ስላልሆነ ለምርጫው መዘጋጀቱ ምርጥ አማራጭ ነው ለማለት ነው❗️🙏

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 21:36


ይህም እዚህችው የቴሌግራም ቻናሌ ተከታይ ነው መዲና ከተማ ነው ያለው መገን መታደል💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 21:34


የፌስቡክ ወዳጄ መዲና ነው ያለው መገን መታደል Muaz Shemsu

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 21:12


ነቢ ﷺ ይጥሩኝ እስቲ💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 21:11


ይገርማችኋል ማሕበራዊ ሚድያ ማወቃቸው ወንድም እና እህቶቼ መዲና ከተማ እንደ ጉድ እየሄዱ እኔ ብቻ ነኝ የቀረሁት😥🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 21:07


ወላሂ እኔ እንጃ ብቻ ዘንድሮ ልቤ መዲና ብቻ ነው የሚለኝ እስቲ በዱአችሁ🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 20:19


አልቀርም እኔማ አልቀርም እኔማ
አልቀርም እኔማ አልቀርም እኔማ
ነብየን ዚያራ መዲና ከተማ💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 20:19


መዲነቱል ሙነወራ💙

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 20:18


መዲነቱል ሙነወራ💙

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 15:55


አልሃምዱሊላህ

አንድ ወዳጄ ስሜን በመጥራት ነቢን ﷺ ዘይሮልኛል ኢንሻአላህ እኛንም እዚህ መንደር አላህ ይወፍቀን🤲 ነቢ ﷺ ይጥሩን💛

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 13:23


ረመዷን 100 ቀን ቀረው
ከቁጥር ሳንጎድል እንደውም ከቁጥር ጨምረን
አሏህ በሰላምና በጤና ያድርሰን🤲

አህለን ያረመዷን::

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

20 Nov, 13:12


#የረቡዕ_መጅሊስ_ወግ
#አወሊያዎቹ

ይህ ሰአት ዱዓ ተቀባይነት የሚገኝበት ወቅት ነው። ረቡእ በዝሁር እና ዐሥር መካከል ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው በሐዲስ መጥቷል። ከእያንዳንዱ ቀናት ጀርባ በርካታ ምሥጢሮችን የተረዱ ዓሊሞች ቀናቱን ከፋፍለው ዱዓና ሰለዋቶች በማደረግ ዘመን የሚበትነውን ጘፍላ መርታት ችለዋል።

በመጅሊስ ኒያ ሥራ ላይ ላላችሁ፣ እንዲሁም ተመችቷችሁ ዱዓ ለተቀመጣችሁ ሰዎች የሁለት አውሊያዎችን ገጠመኝ ላወጋችሁ ወደድሁ።

በቅርብ ዘመን ግብጽ ውስጥ የነበሩት ኢማም ሻዕራዊ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) መዲና ዚያራ በማድረግ ላይ ሳሉ የሰይዲን ዶሪሕ ተበሩክ ሲያደርጉ አንድ ሹርጣ (ፖሊስ) መጥቶ ይህ "ቢድዓ" ነው ብሎ ይከለክላቸዋል። አውሊያ መች የክርክር ናዳ ውስጥ ይገባል። ብዙ ካስረዱት በኋላ እንኳን እርሳቸውን በከበበው ነገር ቀርቶ አንተ እዚህ ኺድማ ላይ ባለኸው እንኳን እባረካለሁ ብለው ሰውነቱን አሻሽተው በረካውን ወሰዱ። :-D (ዝርዝር ጭውውታቸውን ከዚህ ቀደም አጋርቼው ነበር።)

አይ ዑለማ! ልባቸው ሰፊ ነው፣ ከማይረዳቸው ሰው እንኳን መወሰድ ያለበትን ያውቃሉ። ፖሊሱ እምነቱን በተዳረዳው ልክ ነበር ግና ያላየው ዕይታ ነበር እርሱን አስተማሩት ምን አልባትም ልቡን ጠረጉለት

****

አንጋፋዊው ዛሒድ የነበሩት ኢብራሂም ቢን አድሀም (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ጊዜ ወደ ሻም ጉዞ ሲያደርጉ የገጠማቸውን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ በመንገድ ላይ ሳለሁ ውሃ ጠማኝና አንድ ፍየል ጠባቂ እረኛ ስመለከት ተጠጋሁና እንዲህ አልኩት፦ የሚጠጣ ወተት ወይም ውሃ ይኖርሀል?
እንዲህ አለ፦ የትኛው ቢመጣልህ ትወዳለህ?
"ውሃ" ስል መለስኩ። በያዘው ልምጭ መሬቱን ሲወጋው ውሃ መፍለቅ ጀመረ! በጣም ተገረምኩ።
"አትገረም ጠጣ" አለኝ። ውሃውን ጠጣሁት ከበረዶ የቀዘቀዘ ከማር የጣፈጠ ውሃ ነበር። እያየሁት ቆሜ ቀረሁ። ከዚያም ይህ እረኛ እንዲህ አለኝ፦ « ኢብኑ አድሀም አንድ ባርያ አላህን ከታዘዘ ሁሉም ነገር ይታዘዘዋል።»

ምንጭ፦ [ሲየር ኢዕላም አኑበላእ ወሒሊየቱ አልአውሊያ]

አላህ የአውሊያዎችንና የዑለማዎችን ቀድር ያሳውቀና

✍️ Best kerim

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

19 Nov, 16:40


የሆነ ሰው……………

"አንዴ ብቻህን ላናግርህ ፈልጌህ ነበር"
  ብሎህ ያውቃል? ምን ዐይነት ስሜት ነው የሚሰማህ??

ፍራቻ፣ ድንጋጤ፣ ስጋት፣ ዐስር ዐይነት ሀሳቦች አእምሮህ ውስጥ ይርመሰመሳሉ ኣ?

  ለምን ፈለገኝ?፣ ምን ሊጠይቀኝ ነው?፣ ስለ ምን ሊያወራኝ ነው?፣፣፣ የመሳሰሉ ሀሳቦች ይመላለሱብሃል።

በአጠቃላይ…………
  ለአፍታም ቢሆን መንፈስህ ይረበሻል!!


እንግዲያውስ አላህ የቀጠረንን አስታውስ፦
📖{وَكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا}
{የቂያማ ቀን ሁላቸውም ለየብቻ ሆነው ይመጣሉ።}

  ጓደኛ የለ፣ ቤተሰብ የለ፣ ወዳጅ ዘመድ የለ፣ ከኻሊቀ ሰማዋቲ ወልአርድ ጋ ብቻህን ቆመህ ት ጠ የ ቃ ለ ህ ።
   አስበነው ተዘጋጅተናል ወይ???

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

19 Nov, 16:29


እንደሰለዋት ዓለ ነቢይ ﷺ የጣፈጠ ሀያት ይሁንላችሁ አመሻሹ ወዳጆቼ 🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 21:16


ቃጥባሮች እንዲህ ነበሩ!

ሰውዬው ጌቶች አቡል ጀበልን የመግደል አላማ ሰንቆ ወደ ተቀመጡበት መጅሊስ መጣ።ተደብቆ ቦታውን ያመቻቸ ጊዜ ሸሽጎ የያዘውን ክላሽ አወጣ።ቃታውንም ሳበው። የዚህኔ አጠገባቸው የነበሩት ኻዲሞቻቸው ከጥይቱ ቀድመው መውላዬ ፊት ተሰደሩ።መሳሪያው ተተኮሰ።ሑለት ለጋ ወጣት ሙሪዶች(ሱፍያን እና ፈድሉ) ለመውላዬ ፊዳ ሆነው ተሰዉ።መውላዬንም ጨረፍታ ነክቷቸው…ሆስፒታል ተወሰዱ።ብዙ ነገርም ሆነ።ሰውዬውም አመለጠ።

ዓመታት አለፉ! አንድ ቀን መጅሊስ በተቀመጡበት አንድ የተቸገረ የኔ ቢጤ መጥቶ ምፅዋት ጠየቀ።ከባድ ጉዳት እንደደረሰበትም አስረዳ።መቸገሩን ሲያወራ ሰምተው መውላ አቡል ጀበል ሩህሩህ ልባቸው ክፉኛ አዘነ።ለተሰበሰበው ህዝብም እንዲህ የሚል ትዕዛዝም ሰጡ

«ዛሬ እያንዳንድህ! በኪስ ቀርቶ፣የሚስትህም መቀነት ቢሆን ፈትተህ፣ያለህን ኬትም ፈልገህ አምጣና ስጥ!»

በመጭሻም ከረጢት ሙሉ ገንዘብ ተሰበሰበ።እሳቸውም ለሹፌራቸው መኪና እንዲያነሳ አዝዘው ሰውዬውን እስከ መድረሻው ድረስ እንዲሸኘው አደረጉ።

ከቆይታ በኋላ ምዕመኑ ጠየቀ፥" እንዲህ ያዘናቹለት ሰው ማን ቢሆን ነው??" ……ሻለቃ አቡል ጀበልም መለሱ፦

«ያኔ እኔን ለመግደል መጥቶ ሱፍያንና ፈድሉን የገደለብን ሰውዬ ነው»

ገዳይንም እንኳን ቢሆን የተቸገረ ጊዜ ከመርዳት አልቦዘኑም።

የነገር ጥጉ ይሔው ነው!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 20:52


አንቱን ከያዝን አንሸሽም ጀምበር እያለች ቢመሽም
መላዬ (ﷺ) 💛💚💙

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 20:19


📍በቀን ክፈለ ጊዜ ላይ የሚተኙ ሶስት የእንቅልፍ አይነቶች አሉ እነሱም
(ሀይሉላ ፣ ቀይሉላ እና ዐይሉላ) ይባላሉ።

1 ሀይሉላ / حيلولة
ጠዋት ከፈጅር ቦሃላ የሚተኛ እንቅልፍ ነዉ ።
الحيلولة : هي النوم بعد صلاة الفجر وهي تحول بينك وبين رزقك.
📌 በሰዉዬዉ እና በርዝቁ መሀል መጋረጃ/ግርዶሽ ትሆናለች ፣ ዱኒያዊም ሆነ አኺራዊ ብዙ ማግኘት እና ማትረፍ የሚችል ነገር ታስመልጠዋለች ።
📌ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂወሰለም) አላህ ለህዝባቸዉ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ዉስጥ በረካ እንዲያደርግላቸዉ ዱዓ አድርገዋል ፣ ሁሌ በዚህ ሰዓት የሚተኛ ሰዉ ይሄ ዱዓም እንዳመለጠዉ ነዉ።

2 ቀይሉላ / قيلولة
ከዱሃ ሶላት ቦሃላ ወይም ከ ዙህር ሶላት ቦሃላ ለተወሰነ ደቂቃ ጋደም የምትባል እንቅልፍ ናት።

القيلولة : هي النوم بعد صلاة الضحى او بعد صلاة الظهر لمدة 30 دقيقه وهي مفيدة للصحة الجسم للتقوية على العبادة.
📌ለአካል ጤና እጅግ በጣም ጣቃሚ ነዉ።
📌ኢባዳ ላይ ኢንዲያጠናክረዉ ነይቶ የተኛ ሰዉ አጅር ያገኝበታል ።
📌ሶሃባዎች እና በርካታ አኢማዎች ይተኟት ነበረ።

3 ዐይሉላ /عيلولة
ከ አሱር ሶላት ቦሃላ የሚተኛ እንቅልፍ ነዉ።
العيلولة: هي النوم بعد صلاة العصر وهي تسبب علة للجسم والنفس وضيق لصدر.
📌በዚህ ጊዜ መተኛት የተከለከለ መሆኑ እና እጅግ በጣም የጠላ መሆኑን በሰሂህ ሀዲስ ተዘግበዋል ፣ የሚያስተኛዉ በቂ የሆነ ምክንያት/ዑዝር ከሌለዉ በቀር ።
📌በጤናችንም ላይ ለበሽታ ሰዉን ያጋልጣል
📌ለጭንቀት እና የሀሳብ ጥበት ላይ ሰዉን ይጥላል።

እኔ ከ10 አመት በላይ ቀይሉላ የመተኛት ልምድ አለኝ 😁ብዙ ነገርም አትርፌበታለሁኝ።

እናንተስ በዬትኛዉ ሰዐት ላይ የመተኛት ልምድ ነዉ ያላችሁ? ምን ምንስ ታዝባቹሃል?

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 20:07


ነቢያችን 💚(ﷺ)💚ተጨንቀዉ ሳለ
አላህ በድንገት ፍረጃቸዉ
በዛች ለይል ይሁንበት አላህ ሁላችንንም ይፈርጀን
ያ ረብ አሚንንን🙏💌

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 20:02


ወንድም ሀጃ ይወጣል ይላሉ አላህ የሀቂቃ ወንድም ይስጠን🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 19:50


የሰለዋት ጥቅም💛

ከአንዲት እህት እንደተዘገበው...

" በህልሜ ጨለማ ክፍል ውስጥ ሆኜ መውጫ አጥቼ ጨንቆኛል .. በእንደዛ ጭንቀት ውስጥ እንዳለው ስደናበር እንደ ድንገት ጣቴ ላይ ካለ ቀለበት ትልቅ አልማዝ ነገር በርቶ ታየኝና የነበርኩበትን ክፍል ወገግ አድርጎ አበራልኝ .. መውጫውንም በር አይቼ ስወጣ ... ከእንቅልፍ ነቃው..ነገር ግን ስነቃ ጣቴ ላይ የነበረው ከመተኛቴ በፊት 500 ግዜ ሰለዋት ያወረድኩበት የቀለበት ተስቢህ ነበር .."

አሏሁመ ሰሊ ወሰሊም በባሪክ ዐለይሂ ወዐላ ኣሊሂ ወሰሕቢህﷺ☺️

እሳቸው ﷺ ላይ ሰለዋት በማውረድ ከብዙ አይነት ጨለማ እንወጣለን:: ከብዙ አይነት እጣዎችና እድሎችም ጋር እንገናኛለን::

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 19:28


ነቢ ﷺለበሽታችን መድሀኒት ናቸው አላህ ደሞ አሻሪ

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 19:27


ሰለዋት የ ድህነትን ማስወገጃ ነው
አንቱን አወድሶ የደኸየም አላየን ያረሱለሏህ💛

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 18:26


"ሰይዳችንﷺ መልካም የሆነን ተስፋ ይወዱ ነበር።
ብዙ ጊዜም:-"አብሽር!" ይሉ ነበር።"
በረሱል ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት የማይከፍተው በር የለም!!

إن الصلاة على النّبي وسيلة
فيها النّجاة لكلِّ عبدٍ مُسْلِمِ
صلّوا على القمر المُنير فإنّه
نورٌ تبدّا في الغمام المُظلِمِ
— ابن الجوزي
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا ونبينا وحبيبنا محمد ﷺ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 18:23


#ከሰለዋት_በረከት

ሐሙስ ምሽት ጀምሮ ብዙ ሰዎች ሰለዋት ስለማድረግ ይተዋወሳሉ። ይህ በጣም መልካም ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከመደበኛ የሰለዋት ዊርዶች ውጭ በምሽቱ በምን አይነት መልኩ ነው ሰለዋት ማውረድ እንዳለብንም ማስቀመጥ አለብን። በቁጥር ባይገደብ እንኳን የተወሰኑ ደቂቃዎች ለሰለዋት መቀመጥን ማስለመድ አለብን። በተለይ በአከባቢያችሁ ከመግሪብ እስከ ኢሻ የሰለዋትና ሲራ መጃሉሶች ያሉበት ቦታ ስታገኙ መሐደር (መቀማመጥ) አለባችሁ። እርግጥ በየቦታው ይህን ታላቅ ስብስብ አስቀርተውብናል። ኾኖም በያለንበት ቦታ በተናጠል ብንል መልካም ነው። በሕብረት ለሰለዋት መጃሊሶች መቀማመጥ ግን አይደለም ሰዎችን መላእክቶችን የሚያስቀና ታላቅ ተግባር እንደኾነ በሐዲስ ቁልጭ ብሎ የመጣ ነገር ነው። በሕብረት ቤቶቻችንን እና መሳጂዶችን በሰለዋት ማስጌጥ የልብ ስፋትን፣ በረከትና የውስጥ ሰላምን የሚያስገኝ ውብ ሥርኣታችን ነው።

ሁሉም በዚህ ጥሩ ስራ መሳተፍ አለበት።

አላህ ይወፍቀን

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 18:20


ኸሚስ አመሻሹን

የማይቻል ነገር ይመስል ነበር ነገር ግን መሀን ለሆነች እንስት ልጅ የሰጠህ ጌታ ነህ!
ምንም ሰበብ እና መንገድ አልነበረም ነገር ግን ባህሩን ከፋፍለህ መንገድ አደረግከው!
ጥያቄ፡- ‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ›› መልስ የለውም
ነገር ግን አንድም ወንድ ሳይቀርባት በሴቷ ማኅፀን ውስጥ ነፍስን ዘርተህ ፈጥረህ የእንዴታ ጥያቄውን በሙዕጂዛህ አጠፋኸው!
ሊሆን የማይችል ነገር ነበር ነገር ግን ገና በአንቀልባ ያለን ልጅ እንዲያወራ ምላሱን አገራህለት
ከሚወዱት አካል መራቅ ቀልብ ላይ እንደተሰካ እንጨት ይጠዘጥዛል ነገር ግን መሞቱን በማስረጃ ያረጋገጠን አባት ዘንድ ልጁን መለስክ !!
ሲደክመኝ እና ስሰለችም አንተን መለመኔን መተው እና ፍላጎቶቼን ከልቤ ማስወገድ እፈልጋለሁ ነገር ግን ያረብ ሙዕጂዛዎችህ ኃይልህ እና ችሎታህ ደጃፍህ ዘንድ ያስቀረኛል !!
ይቺን አያም ያስታውሰኛል
" إِنَّمَا أَمْرُهُ إِذَا أَرَادَ شَيْئًا أَن يَقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ "🖤
ሰሉ አለ ነቢ😘
አለይኩም ቢዱዓ🤲

✍️Temam Al hadra

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

07 Nov, 18:10


ኸሚስ አመሻሹን

አላህ ለ1 ባሪያው ሐጃውን ሊያወጣለት ሲፈልግ ሰላት ዓለ ነቢይ ﷺ ያገራለታል 💚

አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ወሸፊኢና ﷴﷺ💚💚 ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

06 Nov, 17:46


ቃጥባሬ ሀድራ

በዓለም ሸንጎ ለይላ ተብላ
ልቤን ማረከች ገብታ ተዱላ አቃጠለቺኝ በዜማ አግላ
እኔም ወደድኳት ማንም ቢጠላ ከዚ በኋላ አሷ ነች ውዴ

ለመላው የሀገራችን የሙስሊሙ ዑማ መውሊድ ታዳሚዎች በሙሉ!
የዘንድሮው የቃጥባሬ ሐድራ መውሊዳችን ታኅሣሥ 12 & 13/ 2017 (( ጀማዱ ሣኒ 17 ና 18/ 1446)) የሚከበር መሆኑ ተገልጿል።
አሏህ በሰላም አድርሶ በሀቂቃው ከሚሀድሩት ያርገን።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Nov, 17:00


እንኳን አደረሳችሁ ቃጥባሬ መውሊድ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Nov, 16:49


ለመላው የሀገራችን የሙስሊሙ ዑማ መውሊድ ታዳሚዎች በሙሉ!
የዘንድሮው የቃጥባሬ ሐድራ መውሊዳችን ታኅሣሥ 12 & 13/ 2017 (( ጀማዱ ሣኒ 17 ና 18/ 1446)) የሚከበር  መሆኑ ተገልጿል።
አሏህ በሰላም አድርሶ በሀቂቃው ከሚሀድሩት ያርገን።

ኢንሻአላህ ማንም እንዳይቀር።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Nov, 15:31


እሺ አሁን ይህን ምን ይሉታል ስልኬ ማታ ቻርጅ አድርጌ ጠዋት ሲነሳ 101% ፔርስንት ብሎኛል😂🙄

እስኪ ፈትዋ ስጡበት🤭

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Nov, 15:04


ልብህ እንዲለሰልስ ከፈለግክ ድሃን መግብ የየቲምን ራስ ዳብስ የቲምን እርዳ ::

ረሱል ❴ﷺ❵ 💜

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

05 Nov, 14:50


ሰዎች ዘንድ አንጋፋ ተመስጋኝ ሆኖ አላህ ዘንድ ግን የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የሌለው😥ስንት ሰው አለ🤔

አላህ ሙስተአን🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

03 Nov, 20:05


#ሱፍይነት
አንድ ወዳጅ ወደ ሸህ ሙህይዲን ኢብኑ አረቢይ ይመጣና እንዲህ ይላቸዋል፦
ሰወች የኛን መንገድ አይቀበሉትም
እሳቸውም እንዲህ አሉት፦ አንድ ሰው ይሄን መንገድ ለማወቅ ማስረጃ ከጠይቀህ
የማርን ጥፍጥና እንዴት አወቅክ በለው፣ በመቅመስ ነው ያወቁት ካለህ ሱፍይነትም በመቅመስ ካልሆነ ሊታወቅ አይችልም ብለህ መልስለት አሉ  ።
፦ዳር ላይ ሁኖ የበሀርን ጥልቀት መለካትአይቻልም
፦የዚክረን ጥፍጥና ያልቀመሰ ሰው አብዝቶ ሊዘክር አይችልም
፦የሰለዋትን ጥፍጥና ያልቀመሰ ሰው አብዝቶ ሰለዋት ሊያወርድ አይችልም
፦የቁርአንን ጥፍጥና ያልቀመሰ ሰው አብዝቶ ቁርአን ሊቀራ አይችልም
፦አንድ ሀዲስ ከተማርክ ሁለት ሀዲስ የተማረን አክብር
፦ለጌታህ ታዛዥ ካልሆንክ አብዝተው የሚታዘዙ ሰወችን አትዝለፍ
፦ያንተን ጉድለት የተሟላላቸው ሰወችን በማውገዝ ልትሸፍነው አትችልም
፦አንተ ዱንያን የምትወድ ከሆነ ዱንያን የተዉ ሰወችን አትጥላ
፦በስራ የበለጡህን ሰወች በምላስ ልትበልጣቸው አትሞክር
፨ትንሽ ከሆንክ ትንሽ ነኝ በል ታድጋለህ፨

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

03 Nov, 16:05


ነቢ ﷺ «እኔም ብሆን በስራዬ ሳይሆን በራህመቱ ነው ጀነት የምገባ» ብለዋል። 1 ሰለዋት ስታወርድ 10 ራሕመት ታገኛለህ። በ1ዱ ራህመት ብቻ ጀነት መግባት ትችላለህ። 💚

اللهم صلِّ على سيدنا محمد 🌺

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

03 Nov, 15:59


ፊዳከ አቢ ወኡሚ
"(አባትና እናቴ ለእርስዎ ፊዳ ይሁኑ)" እያሉ
በሬ አርደው ፊዳ ማድረግ ከበዳቸው።
ወሬ ብቻ 🤨

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

02 Nov, 19:59


ኡሙ ሲብያን የምትባል ህፃናትን የምታጠቃ ሴት ጂኒ አለች። ልጅ ሲወለድ በቀኝ ጆሮው አዛን በግራ በኩሉ ኢቃም ካልተባለበት ልጁ በዚች ጂኒ አዛ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው።

ሳይወለድ በፊትም ወላጆቹ በግንኙነት ወቅት "አሏሁመጀኒብና አሽ ሸይጧን ወጀኒቢ ሸይጧን ማ ረዘቅተና" ካላሉ የሚወለደው ልጅ ለሸይጣን ቅርብ ይሆናል።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

02 Nov, 13:59


ውስጣቹ ያለው ብዙ ነገር ነው።

ከላይ ግን...

"ደህና ነኝ !" "አልሐምዱሊላህ" 🤲 ትላላቹ አደል?

ወላሂ ነው ምላቹ ምስጋናችሁን አታቋርጡ።

ምንም የገዘፈ ሐጃ ቢገጥማቹ ጌታቹን አታማሩ።

አንድ ቀን ሁሉም ይስተካከላል 💚

አልሐምዱሊላህ 🤲

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

02 Nov, 13:52


ሀኪም አልሻም መዳኛ
ስሙ ሆኗል የኔ ሺፉ
💚💚💚"مُحمد ﷺ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

01 Nov, 19:26


የሉጥ ህዝብን ሉጥ በውስጣቸው እያሉ አላህ ሲቀጣቸው ለነቢ ኡመት ግን ምንም እንኳ ቢክዱና ቢያምፁም «አንተ በውስጣቸው እያለህ (ኡመትህን) አልቀጣቸውም» አላቸው።
ለሳቸው ሲል ካፊሩን እንኳ አልቀጣም አለ 💚

ለሳቸው ሲል ከሀዲ ካልቀጣ አንተ የምትወዳቸውንና ሰለዋት የምታወርድባቸውስ? አላህ አንተን ለመቅጣት ምን ያህል ሀያእ ያደርጋል ብለህ ታስባለህ?

اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ💚

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

01 Nov, 19:00


ጓደኛ አታብዛ!!

የሁሉም ሰው ጓደኛ ከሆንክ አስታውስ አንተ የራስህ ጠላት ነህ።ብዙ ጓደኛ ኖሮት ለራሱ በቂ ጊዜ የሚሰጥን ሰው ፈልግ፣ ያ7ኘውን ሰው በሙሉ ጓደኛ እያደረ7 የተጠቀመን ሰው ፈልግ፡፡ በፍፁም አታገኝም፡፡ የጓዷኛ ብዛት ችግር እንጂ ምንም የሚጠቅምህ ነገር የለውም፡፡ ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት ገደብ አብጅለት፡፡ በሰው ተከበህ ለራስህ ጠላት ከምትሆን ብቻህን ቀርተህ ለራስህ ወዳጅ ብትሆን ይሻላል፡፡ ጫወታው ጓደኛ ባበዛ ሳይሆን ጥራት ያላቸው ካንተ ባህሪና ማንነት ጋር የሚሔዱ፣ የሚጠቅሙህና የሚረዱህ ጥቂት የልብ ጓደኞችን ማፍራት ነው፡፡ ከራሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የማይወድ ሰው የጓደኞቹ ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ባይፈልግም እንኳን ሁሌም ራሱን የሚያገኘው እነርሱን ለማስደሰት ሲጥር ነው፡፡ ብቸኝነትን ይፈራልና እየተጠቀሙበትም ቢሆን ጎጂ ጓደኝነት (toxic friendship) ውስጥ ለረጅም ጊዜ ይቆያል፡፡ ጓዷኝነት ካልጠቀመህ ብዛቱ ምን ያደርግልሃል? በዙሪያህ ብዙ ሰው ካለ በዋናነት የምታቃጥለው የራስህን ውድ ጊዜ ነው፡፡

ራስህን ታደግ! እርግጥ ነው ለብቻ መጓዝ ከባዱ ፖዞ ነው ነገር ግን ከእርሱ በላይ የሚያጠነክርህ ነገር የለም፡፡ በጫጫታና በአላስፈላጊ ድራማ መከበብ ማንንም ነፃ አውጥቶ አያውቅም፡፡ብዙ ጓደኛ ስላላቸው በሰዎች የሚወደዱ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዛ ጓደኞቼ የሚሏቸው ሰዎች እንደሚወዷቸው ለማረጋገጥ በደስታቸውና በሃዘናቸው ጊዜ የሚሰማቸውን ስሜት ማስተዋል ቢችል ብዙ ያተርፋል፡፡ ምቀኛም ሆነ ሌባ ከሩቅ አይመጣም፡፡ አብዝቶ የሚያውቅህ፣ የቅርብ ጓደኛዬ ነው አመነዋለሁ የምትለው ሰው ስለሚቀናብህ ብቻ ከጀርባህ ምን ሊሰራብህ እንደሚችል አታውቅም፡፡ ብዙ ጓደኛ ሲኖርህ ችግር አያጣህም፡፡ የእያንዳንዳቸውን ችግር ለመቅረፍ ስትሞክር የራስህ ችግር ሊያሰምጥህ ይደርሳል፡፡ ለእነርሱ ስትሯሯጥ ራስህን ትረሳለህ፣ ምናልባትም ባላሰብከው መንገድ ልትጠፋ ትችላለህ፡፡ በአንድም ሆነ በሌላ የማይጠቅምህ ጓደኝነት እየጎዳህ ነው ማለት ነው፡፡

ጓደኛ አታብዛ፣ በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች ቀንስ፡፡ ከእነርሱ የምታገኘውና ለእነርሱ በምትሰጠው ነገር ላይ ግንኙነትህን መስርት፡፡ በፍፁም ትርጉም አልባ ግንኙነት ውስጥ ተሳስተህ እንኳን እንዳትገባ፡፡ ጓዷኝነት የህይወት አቅጣጫህን ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል፡፡ በጓደኛህ ትጠፋለህ በጓደኛህ ትድናለህ፡፡ በክፏ ቀን የሚዷርስህ ጓዷኛህ ነው፣ ደስታህንም እንደራሱ ደስታ የሚደሰትልህ እርሱ ነው፡፡ ከባድም ቢሆን ጓደኛህን በአግባቡ ምረጥ፡፡ ከቻልክ ቁጥራቸውን ቀንስ፣ የጋራ ነገር ከሌላችሁና የማያተርፍልህ ከሆነ ጓዷኝነቱ ይቅርብህ፡፡ ማንም ትርፍ አልባ ግንኙነት የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ አንተ ለራስህ ካላወቅክ ማንም መጥቶ የሚጠቅምህን ሊነግርህ አይችልም፡፡ በመሰለህ መንገድ ሳይሆን በሚጠቅምህ ትክክለኛ መንገድ ተጓዝ፡፡ የይሉኝታ ተጠቂ አትሁን፡፡ አንዳንዴ ጓደኛህን ምንም ያህል ብትወድውም ወደ ጥፋት መንገድ እየመራህ ከሆነ አንድም ለራስህ ብለህ ሌላም ራስህን አድነህ ዳግም ተመልሰህ እርሱን ታድነው ዘንድ እያዘንክ ትተወዋለህ፡፡ የምታውቀውን ሰው በሙሉ ጓደኛ ለማድረግ አትሞክር ይልቅ በቅድሚያ የራስህ ጓደኛ ሁን፡፡ በየትኛውም መንገድ ጥራትን እንጅ ብዛትን አትፈልገው ይቅርብህ፡፡ ጓደኛ ማለት አንተ በለለህበት አንተን ሆኖ የሚገኝልህ ሰው መሆኑን አትርሳ!! አሏህ የልብ ወዳጅ መልካም ጓደኛ ይስጣችሁ፡፡


ድንቅ ምሽት ይሁንልን!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

28 Oct, 20:56


ሰበር ዜና || የአለም የዳዕዋ አሚር መዉላና ሸይኽ ሰአደ የአለም የሀበሻ ጉባኤ(ኢጅቲማዕ) በየሁለት አመቱ እንዲሆን ወሰኑ

ዘንድሮ በሚሊኖች ከ130በላይ ሀገራት በታደሙበት የዳዋ ስብሰባ (ኢጅቲማ) ለሶስተኛ ግዜ በቡታጅራ መደረጉ የሚታወስ ነዉ ።በዚህ መሠረት የአለም የዳእዋ አሚር የሆኑት ሸይኽ ሰአደ በሀበሻ የሚደረገዉ አለም አቀፍ ሀይማኖታዊ የዳአዋ ጉባኤ በየሁለት አመቱ እንዲደረግ መወሰናቸዉ ለማወቅ ተችሏል ።

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

28 Oct, 20:25


እ ና መ ሰ ግ ና ለ ን
T H A N K Y O U

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

የዘንድሮውን አለም አቀፍ ኢጅቲማዕ መርሐግብር በከተማዋ እንዲዘጋጅ ከመፍቀድ ጀምሮ የአለም ዳዕዋ ተብሊግ አሚር ሸይኽ ሰአድን ጨምሮ ከ 130 የአለም ሀገራት የተውጣጡ ጀመአዎችን አደባባይ ወጥተው በመቀበል ላሳዩት የሀበሻን የእንግዳ ተቀባይነት በሀበሻ ሙስሊሞች ስም ከልብ እናመሠግናለን !!
.... በናንተ በጎ ምግባር ሰበብ ሀገራችን በአለማቀፍ ደረጃ ከፍ ብላ ታየች !! እኛም በናንተ ኮራን !! አስተዳደራዊ ስኬታቹ ከፍታ ላይ ይዋል !!!

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Butajira City Communication Office

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

28 Oct, 20:24


እ ና መ ሰ ግ ና ለ ን
T H A N K Y O U
የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት

የዘንድሮውን አለም አቀፍ ኢጅቲማዕ መርሐግብር በሰላም እንዲጠናቀቅ ሰላም ከማስፈን ጀምሮ የአለም ዳዕዋ ተብሊግ አሚር ሸይኽ ሰአድን ጨምሮ ከ 130 የአለም ሀገራት የተውጣጡ ጀመአዎችን አደባባይ ወጥተው በመቀበል የሀበሻን የእንግዳ ተቀባይነት እሴት በማስመስከርዎ በሀበሻ ሙስሊሞች ስም ከልብ እናመሠግናለን !!

.... በከተማዋ በነበረን ቆይታ እጅግ ሰላም የሰፈነበት ማህበራዊ እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ በመኖሩ እያንዳንዱ የኢጅቲማዕ ተካፋይ ንብረቱ እና ደህንነቱ ሳይጓደል በሰላም ፕሮግራማችንን አጠናቀን ተመልሰናል !! በዚህም እኛ የሀበሻ ሙስሊሞች በናንተ የፀጥታ ስራ ኮርተንባቿል !!

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

28 Oct, 20:24


እ ና መ ሰ ግ ና ለ ን
T H A N K Y O U
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ማህበር

ቀለም ብሔር ጎሳ ሳይለይ ከአንድ ሚሊየን በላይ የአለምን ህዝብ ያሰባሰበው የዘንድሮውን አለም አቀፍ ኢጅቲማዕ መርሐግብር እንዲሳካ እምነት ሳትለዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና የማቴሪያል ድጋፋችሁን ከመስጠት አልፎ የኢጅቲማዐውን ሜዳ መጠለያ እና ማረፊያ ዳስ ግንባታ ላይ በጉልበት እና ነፃ የሙያ አገልግሎታቹን በመስጠት
.....እንዲሁም የአለም ዳዕዋ ተብሊግ አሚር ሸይኽ ሰአድን ጨምሮ ከ 130 የአለም ሀገራት የተውጣጡ ጀመአዎችን አደባባይ ወጥታቹ ላደረጋቹት ልዩ አቀባበል ላሳያችሁት የሀበሻን የእንግዳ ተቀባይነት እሴት በሀበሻ ሙስሊሞች ስም ከልብ እናመሠግናለን !!

.... በናንተ በጎ ምግባር ሰበብ ሀገራችን በአለማቀፍ ደረጃ ከፍ ብላ ታየች !! እኛም በናንተ ኮራን !! ወጣትነታቹን ይባርክልን !! ሁሌም ክበሩ

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Butajira City Communication Office

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

28 Oct, 18:32


አለማቀፍ ኢጅቲማዕ በዚህ መልኩ ታድመናል አልሃምዱሊላህ

መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

28 Oct, 18:21


አልሃምዱሊላህ

ከቡሌ ሆራ ከተማ አለማቀፍ #ኢጅቲማ በቡታጅራ ከተማ ላይ ለመታደም ከሄዱት በጥቅቱ በፎቶ ላሳያችሁ።
አልሃምዱሊላህ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ላስጨረሰን🙏

ለሚቀጥለውም በሰላም ያድርሰን 🙏

ኢጅቲማ ቡታጅራ 14/02/2017

2,713

subscribers

1,341

photos

37

videos