በመድረኩ ባለፉት 6 ወራት በማዕከልና በክፍለከተማ 193 ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ ታቅዶ 217 ግንባታዎችን ማከናወን እንደተቻለ የተመላከተ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም 88 የፕሮጀክት ቅድመ ዝግጅት ጥናት እና 155 ዲዛይን ዝግጅት በማከናወን የዲዛይን ክትትልና ቁጥጥር አሰራርን ማሳደግ እንደተቻለም ተጠቅሷል።
ተያይዞም በጊዜ ማዕቀፉ 204 ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ለማሳተፍ ታቅዶ 360 ማከናወን እንደተቻለም በቀረበው ሪፖርት ተጠቁሟል።በተጨማሪም በዘርፉ ለ26,756 ዜጎች የቋሚና ጊዜያዊ የስራ-ዕድል መፍጠር እንደተቻለና 3,574,883,794.64 ብር የገበያ ትስስር መፈጠሩም በመድረኩ ቀርቧል፡፡
የከተማዋን የግንባታ ጥራት ከማረጋገጥ አንፃር ለ3,515 የግንባታ ግብዓት ናሙናዎችን በራሱ ላብራቶሪ ፍተሻ እንዳከናወነ እንዲሁም ለ8902 አይነቶች የዋጋ ተከላ ጥያቄ ምላሽ እንደተሰጠም ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል 162 የፕሮጀክት ክዋኔና ፋይናንሺያል ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ 295 ፕሮጀክቶች ላይ ማከናወን መቻሉ እንዲሁም በ20 የተለያዩ ርዕሶች ለ1,888 የስራ ተቋራጮች ፣አማካሪ ድርጅቶች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የተዋንያኑን ዓቅም መገንባት እንደተቻለ የቀረበው ሪፖርት ያሳያል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ባቀረቡት ማጠቃለያ ቢሮው በዕቅድ የያዛቸውን ተግባራቱን ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንደቻለ ጠቅሰው ከዚህም በተጨማሪ በኮሪደር ልማት ክንውኑ እና የፕሮጀክት ፋይናንሺያል ድርድር በማድረግ እንደ ከተማ ከፍተኛ ወጪዎችን በማስቀረት ረገድ የነበረውን ስኬት አስረድተው በመጨረሻም የቢሮውን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫና የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል።
ጥር 13/2017 ዓ/ም