መሬት ላይ ስወድቅ ህመሙ ቢበረታም ከህመሙ በላይ ውስጤ ገብቶ ያሳመመኝ ከኤቤጊያ የወጡት አስነዋሪ ቃላት ነበሩ ውጤን በጣም ተሰማኝ።
ሰምሃል እና ኪያር ሊያረጋጉኝ ቢጥሩም ምንም ለውጥ አልነበረኝም ኪያ ሲቸግረው ሮጦ ሄዶ ዶክተሯን ይዟት መጣና ከወደቅኩበት መሬት አንስተውኝ አልጋው ላይ አስተኙኝ ነርሷ ቁስሉን ድጋሚ አፀዳችው እያፀዳችው ፊቴን በእጄ ሸፍኜ አለቅሳለው። እያስለቀሰኝ የነበረው ህመሙ ሳይሆን የኤቤጊያ ንግግሮች ነበሩ ቁርጥ ቁርጥ እያሉ አእምሮዬ ውስጥ ይመላለሱ ጀመር "እኔ ውደደኝ ሙትልኝ አልኩህ፣ ጀዝባ ሁንልኝ ብዬሃለው እኔና አንተ እኮ አንመጣጠንም ፍቅር ምናምን የሚሉት እንቶፈንቶ አይገባኝም፣ ለመሆኑ ረስህን አይተኽዋል...የኤቤጊያ ድምፅ ራሴን እስኪያመኝ ድረስ አእምሮዬ ውስጥ እያቃጨሉ ነበር።
ነርሷ ከሄደች በኃላ ሰምሃል ወደኔ መጥታ እጄን እያሻሸችኝ ይቅርታ በጣም ናዲ እንዲ ታደርጋለች ብዬ አልጠበቅኩም ነባር በጣም ይቅርታ ይዣት መምጣት አልነበረብኝም አለች የኔ እንባና ሃዘን እየተጋባባት። ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ በእንባ የራሰው ፊቴን በመዳፌ እየጠረግኩ። በቃ አታልቅስ አይዞህ እሺ ናዲ እኔ አናግታለው አለ ኪያ እልህ ይዞት።
የተፈጠረውን ነገር ለማስረሳት ይመስል ሰምሃል ወይ ረስቼው ቁርስ አምጥቼላቹሃለው ያው ቤት ያፈራውን አለች ፈገግ እያለች ያው አንተ ጉሉኮስህን ትጠጣለህ ኪያ ይበላል ባይሆን ስትድን ውጪ ጋብዝሃለው አለችኝ የሰምሃል አባባል ፈገግ አስባለኝ ኪያ እየተጣደፈ በፌስታል ያመጣችውን ምሳቃ ከፍቶ ቶሎ ቶለ ይደፍቅ ጀመር ሁለታችንም የኪያርን አበላል አይተን ተሳሳቅን። ኪያ ሁኔታችንን አይቶ ምን ትገለፍጣለህ ለሊቱን ሙሉ አንተን ስጠብቅ ፃሜን ነው ያደርኩት አለኝ ወደኔ እያየ። ለግዜውም ቢሆን ከኤቤጊያ ጋር የተፈጠረውን ነገር ረሳሁት።
ኪያ በልቶ ከጨረሰ በኃላ ትንሽ እንዳወራን ሰምሃልን ወደውጪ ይዟት ወጣ እሚያወሩት አይሰማኝም ቀስ እያሉ ይንሾካሾካሉ እኔም እሚሉትን ለመስመት ጆሮዬን ወድሬ ለመስማት ጣርኩ። ትንሽ ቆይተው ገቡ ኪያር ወደኔ መጣና በቃ ናዲ ዛሬ ከሰሙ ጋር ትሆናለህ እሺ እኔ programming exam ስላለኝ ልሂድና ላጥና ላንተም አስፈቅድልሃለው የተፈጠረውን ነገር ለጋሽ አሴ እነግራቸዋለው ይፈቅዱልሃል አለኝ እሺታዬን ከሰማ በኃላ ተሰናብቶኝ ሄደ።
ከሰምሃል ጋር ብቻችንን ቀረን ምን እንደማወራት ግራ ገባኝ በመሃል ዶክተሯ መጣችና ዝምታውን ሰበረችው ሁሉንም ነገር አይታ ከጨረሰች በኃላ ዛሬስ ተነስተህ ተራመድክ አለችኝ አይ አልተራመድኩም ስላት ተነስተህ ወክ አድርግ ትንሽ አለችኝና ሄደች። ሰምሃል ልታግዘኝ ተነሳች ከአልጋው ላይ ደግፋኝ ከተነሳው በኃላ እንደትናንቱ ኮሪደሩ ላይ ወክ አድርገን ተመልሰን ገባን። አልጋዬ ላይ ተቀምጬ ስልኬን ሳይ ሚስኮል አገኘው ታላቅ እህቴ ነበረች መልሼ ደወልኩላት ሰላም ከተባባልን በኃላ ትንሽ አውርተን የተፈረውን ነገር ለእናትና አባቴ እንዳትናገር አስጠንቅቂያት ነገርኳት በጣም ደነገጠች አሁኑኑ ተነስታ ወደናዝሬት እንደምትመጣ ነገረችኝና ተሰነባበትን።
አሁንም ከሰምሃል ጋር ምን እንደማወራ ግራ ገባኝ ወሬ ለማስጀመር ያክል እስኪ ስለራስሽ ንገሪኝ አልኳት። ሰሙ ፈገግ እያለች ምን እነግርሃለው ማወቅ የምትፈልገውን ጠይቀኝ አለችኝ። ምን እንደምጠይቃት ግራ ገባኝና ዝም አልኩ። ከሰአታት በኃላ እህቴ እየሮጠች እኔ ወዳለሁበት ክፍል ዘው ብላ ገባች በአንዴ ክፍሉን ወከባ በወከባ አደረገችው ግን እሷ ብቻ አልነበረም የመጣችው እኔትና አባቴም አብረዋት ነበሩ ሲገቡ ሳያቸው ደነገጥኩ እህቴን በቁጣ አየኃት።
ጤንነቴን በደምብ ካረጋገጡ በኃላ ጭቅጭቅ ያዝን ሰምሃል ሁሉንም ነገር ዝም ብላ እያየች ነበር ቅር ያላት ትመስላለች። ከብዙ ጭቅጭቅ በኃላ ትምህርቴን አቁሜ ዊዝድሮው ሞልቼ ወደ አዲስ አበባ እንድመለስ ተወሰነ።
ይቀጥላል...
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot