Ethiopia Check @ethiopiacheck Channel on Telegram

Ethiopia Check

@ethiopiacheck


ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

Ethiopia Check (Amharic)

ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል። ኢትዮጵያ ቼክ ማህበራዊ ሚድያ እና መደበኛ ሚድያዎች የተወደዱ ተጠቃሚዎችን ለመስጠት የሚፈልጉ ነው። ይህ ቼክ በማህበራዊው እና መደበኛው ሚድያው ላይ እና የተለያዩ መረጃዎችን በመጠበቅ እና በአንድ ሚኒስቴር ላይ፣ ኢትዮጵያውያን ለአንድ ሚኒስቴርው እና ሊጠቀም ሲገድዳቸው ገልጿል። ምሳሌዎችን እና ኢትዮጵያ እግር እና ውድ ጉዳይን በተመለከተ የሚወክሉ ኢትዮጵያውያን ስለ እነሱ ያለውን እና እነሱን ለማስቀመጥ እና ማግኘት ያላቸውን መረጃዎች ምንም ማለት የለም።

Ethiopia Check

09 Dec, 14:17


#MondayMessage ዜጋታት ሓበሬታ ናይ ምርካብ መሰሎም ንምርግጋጽ እጃም መንግስቲ እንታይ ክኸውን ኣለዎ?

ኮምፒዩተራትን ሞባይል ስልኪታትን ምምዕባል ካብ ዝጅምራሉ ግዜ ኣትሒዙ ክሳብ እቲ ኢንተርነት ዝዓበየሉ ግዜ ቅርፅን ዋሕዝን ሓበሬታ እናተቐየረ መጺኡ ኣሎ።

እዚ ክፍለ ዘመን ድማ ብዓብይኡ ብርክት ዝበሉ ቴክኖሎጂካዊ ምዕባለታትን ዋሕዚ ሓበሬታን ዝርኣየሉ ዘሎ ብምዃኑ ናይ ሓበሬታ ዘመን ተባሂሉ’ዩ ዝጽዋዕ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/the-right-to-access-information-and-the-responsibility-of-a-government-%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/

Ethiopia Check

06 Dec, 15:20


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. ቴሌግራም የህጻናት ወሲብ ብዝበዛን የሚያሳዩ ይዘቶችን ከፕላትፎርሙ ለማጽዳት ከኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን ጋር ስምምነት ማድረጉን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን የህጻናት ወሲብ ብዝበዛን የሚያሳዩ ይዘቶችን ከኢንተርኔት በማስቀገድ ረገድ ብዙ ቀዳሚ ተቋም መሆኑ ይነገራል። በስምምነቱም ቴሌግራም ይዘቶቹን ቀድሞ ለመለየትና ለማስወገድ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችንና ልምዶችን ያገኛል ተብሏል። ከዚህ ጋር በተገናኘ ሸጋ የተባለ የድረገጽ ሚዲያ ከቀናት በፊት ባስነበበው የምርመራ ዘገባ የኢትዮጵያውያን ሴቶችን እርቃን ምስሎች የሚያሳዩ ይዘቶች በቴሌግራም በስፋት እንደሚሰራጩ ያሳየ ሲሆን ጉዳዩ ባለፉት ቀናት የቲክቶክ መንደር ዋና መነጋገሪ መሆኑ ይታወቃል።

2. በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እስካሁን የስርጭት መጠናቸው አነስተኛ መሆኑን ሜታ በትናትናው ዕለት አስታውቋል። በፈረንጆቹ 2024 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ በተደረጉ ምርጫዎችን በተመለከተ በፕላትፎርሞቹ ከተሰራጩ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችም በሰውሰራሽ አስተውሎት የተሰሩት ድርሻ ከ1% በታች መሆኑን ገልጿል። ይዘቶቹን ለመለየትና ለማስወገድም እንዳልከበደው አብራርቷል።

3. ሜታ በሙከራ ደረጃ ያስጀመረውን ቅጣትን በትምህርት የመቀየር አሰራር ለሁሉም የፌስቡክና የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ማስፋቱን በትናትናው ዕለት አስታውቋል። አሰራሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖሊሲ ጥሰት ፈጽመው የአካውንት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተጠቃሚዎች አጭር ትምህርታዊ ፕሮግራም በመከታተል ቅጣታቸውን እንዲሰረዝላቸው የሚያደርግ ነው። ሆኖም አሰራሩ ተደጋጋሚ ወይም ከባድ የፖሊሲ ጥሰት የሚፈጽሙትን አይመለከትም ተብሏል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች:

-ቆየት ያሉ ልጥፎችን ለማሰስ የሚረዳ መገልገያን በአፋን ኦሮሞ አስተዋውቀናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2522

-የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን የግዙፍ ኤርፖርት ፕሮጀክትን ያሳያሉ ተብለው የተጋሩ ምስሎችን አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2524

-የሴራ ትንታኔን መሰረት አድርገው ስለሚሰራጩ ሀሠተኛ መረጃዎች በትግርኛ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2525

ኢትዮጵያ ቼክ

Ethiopia Check

06 Dec, 15:07


#Explainer ግጉይን ጭብጢ ዘይብሉን ሓበሬታ መን’ዩ ናብ ብዙሓት ክባጻሕ ዝገብር?

ኣብዚ እዋን፡ ብርክት ዝበሉ ሰባት ብዝተፈላለዩ መድረኻት ማሕበራዊ ሚዲያ ዝቐርቡ ትሕዝቶታት ከም ዝከታተሉ ይገልፁ።

መዓልታዊ ፌስቡክ ወይ ካልኦት ኣማራጺታት ብምጥቃም ድማ ሓገዝቲ’ዮም ዝብሉዎም ሓበሬታት ከም ዝረኽቡን ብስሩዕ ማዕከናት ሓበሬታ ዝቐርቡ ዜናታት ምክትታል ከም ዝገደፉዎ ይዛረቡ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/the-role-of-conspiracy-theory-in-misinformation-%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/

Ethiopia Check

03 Dec, 15:00


#FactCheck እነዚህ ምስሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን የግዙፍ ኤርፖርት ፕሮጀክትን ንድፍ አያሳዩም

ከሰሞኑ በርከት ያሉ የፌስቡክ እና ኤክስ (ትዊተር) ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን ሜጋ ኤርፖርት ፕሮጀክት ያሳያሉ ያሏቸውን ምስሎች እያጋሩ ይገኛሉ።

ለምሳሌም ‘FastMereja.com’ የሚል ስም ያለው እና ከ860 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ” ሲል በስክሪን ቅጂው የሚታዩትን ሶስት ምስሎች አጋርቷል።

ይህን የፋስት መረጃ ልጥፍም ከ40 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው አጋርተውታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምስልን በምልሰት መፈለጊያን በመጠቀም በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት በስክሪን ቅጂው የታችኛው ክፍል የሚታዩት ሁለት የኤርፖርት ንድፎች በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የኢንቾን ኤርፖርት ንድፍ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችሏል።

የኢንቾን ኤርፖርት ንድፎች በተለያዩ ጊዝያት ሲጋሩ የቆዩ ሲሆን ከንድፎቹ የተወሰኑትን በነዚህ ማስፈንጠሪያዎች መመልከት ይቻላል፡ https://www.gensler.com/projects/incheon-international-airport እና https://www.koreaherald.com/view.php?ud=20191119000078

በሌላ በኩል በስክሪን ቅጂው የላይኛው ክፍል የሚገኘው ምስል ‘GSAAN’ በተሰኘ ድረ-ገጽ የተጋራ ሲሆን ተቋሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚገነባው ሜጋ ኤርፖርት የቅድም ዲዛይን እና ማስተር ፕላን ጽንሰ-ሐሳብ አገልግሎት መስጠቱን ጠቅሷል፡https://www.gsaan.us/ethiopia-new-airport-logistics-industry-park-project-study-report/

ይሁን እንጂ ‘GSAAN’ ድረ-ገጽ ላይ የተጋራውን ንድፍ ከሌላ ምንጮች ማረጋገጥ አልቻልንም። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚያስገነባው ሜጋ ኤርፖርት ከዳር አል ሀንዳሽ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ጋር የቴክኒካል፣ የአርክቴክቸር፣ የኢንጅነሪንግ እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ስምምነት መፈራረሙን ባለፈው ነሐሴ 2016 በድረ-ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቆ ነበር፡ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-signs-a-contract-with-dar-al-handasah-to-develop-a-mega-airport-city

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ በዳር አል ሀንዳሽ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ይፋ የሆነ የሜጋ ኤርፖርቱ ንድፍ እንደሌለ ተመልክተናል።

በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገነባ የተነገረው ሜጋ ኤርፖርት በአመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

02 Dec, 12:22


#MondayMessage Feesbuukii irratti maxxansawwan buleeyyii akkamiin salphaatti barbaannee argachuu dandeenya?

Taatee yeroo dhiyootti mudate dhoksuuf jecha maxxansawwan Feesbuukii turan wabeeffachuun mala namoonni odeeffannoowwan sobaa tamsaasan irra deddeebiin itti fayyadaman ta’aa jira.

Guutuusaa dubbisuuf geessituu kana cuqaasaa: https://ao.ethiopiacheck.org/home/facebook-search-tools-to-learn-about-who-posted-what-feesbuukii/

Ethiopia Check

29 Nov, 14:24


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1.ተጽእኖ ፈጣሪ ናይጄሪያውያን አርቲስቶችን ያካተተ ጥምረት በሀሠተኛና በተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ዙሪያ ንቃት ለመፍጠር ያለመ እንቅስቃሴ መጀመሩን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ጥምረቱ ናይጄሪያውያን ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች መለየት እንዲችሉ ትምህርታዊ ንቅናቄዎችን ያደርጋል የተባለ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎችንም ተጠያቂ የማድረግ ትልም እንዳለው ተገልጿል። ጥምረቱ #FWDWithFacts የሚል ሃሽታግ ይጠቀማል ተብሏል።

2. የአውስትራሊያ ፓርላማ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ህግ በዛሬው ዕለት ማጽደቁን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ታዳጊዎችን ከማህበራዊ ሚዲያ “ጉዳት” ለመጠበቅ ያለመ ነው የተባለው ህግ ተፈጻሚነቱ ከ12 ወራት በኋላ ይጀምራል ተብሏል። ህጉን የሚተላለፉ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እስከ 32.5 ሚሊዮን ዶላር እንደሚቀጡም ተደንግጓል።

3.በስሩ ከ320,000 በላይ ጋዜጠኞችን ያቀፈው የአውሮፓ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ከመጭው የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያ ወር መጨረሻ ጀምሮ ኤክስ/ትዊተር የተባለውን የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም እንደሚያቆም አስታውቋል። ፌደሬሽኑ የማህበራዊ ሚዲያውን ባለቤት በፀረ-መደበኛ ሚዲያነት የከሰሰ ሲሆን ኤክስ “የሴራ ተንታኞች፣ የዘረኞችና የአክራሪ ቀኝ ዘመሞች” መናህሪያ ሆኗል ሲል ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። በቅርቡ ዘጋርዲያን ጋዜጣን ጨምሮ በርከት ያሉ ተቋማትና ግለሰቦች ተመሳሳይ ምክን ያት በመጥቀስ ኤክስን መጠቀም ለማቆም መወሰናቸውን ማስታወቃቸው ይታወቃል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች

-የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመቀነስ ጋዜጠኞች ምን ማድረግ ይችላሉ፧ የሚል መልዕክት አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2515

-ወቅታዊ መረጃዎችን በምንከታተልበት ወቅት ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ የሚያስረዳ ጽሁፍ በትግረኛ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2516

-ድምጽ ማቸገን ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለ? ለሚሉት ጥያቄወች ምላሽ የሚሰጥ ማብራሪያ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/2517

-እንዲሁም ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል? ለሚሉት ጥያቄወች ምላሽ የሚሰጥ ማብራሪያም አጋርተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

29 Nov, 14:12


#Explainer ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል?

የአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከ3.4 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎችን ማስተናገዱን እና በዚህም ከ2.41 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በትናንትናው ዕለት አስነብቦ ነበር። ለመረጃውም በምንጭነት የክልሉን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጠቅሷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች ክልሎችም እንዲህ ያሉ ቁጥሮችን በየጊዜው ሲናገሩ ይደመጣል። ይህን የተመልከቱ ሰዎች ቁጥሮቹ መጋነናቸውን በመጥቀስ አስተያየታቸው ሲሰጡ የሚታይ ሲሆን ለኢትዮጵያ ቼክም የአጣሩልን ጥያቄዎች ይመጣሉ።

- ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል?

የተመድ የዓለም ቱሪስም ድርጅት (UNWTO) የቃላት መፍቻ ጎብኝ ወይም ዕንግዳ (visitor) ከአንድ አካባቢ ወደሌላ አካባቢ የሚጓዝ፤ በሄደበት አዲስ አካባቢ ከአንድ ዓመት በላይ የማይቆይ፤ ጉዞውም ከቅጥር ውጭ ለንግድ፣ ለጉብኝት፣ ለግል ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ይዘረዝራል።

ተጓዡ በሄደበት አካባቢ ከአንድ ቀን በላይ ከቆየ ቱሪስት (tourist) ሊባል እንደሚችል የሚበይነው ድርጅቱ ከአንድ ቀን በታች ወይም በደርሶ መልስ ወደመኖሪያቸው የሚመለሱትን ሽርሽር አድራጊዎች (same-day visitor or excursionist) ይላቸዋል። ጎብኝ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተጓዦችን ያጠቃልላል።

ከጎብኝዎች የሚገኝ ገቢ ደግሞ ጎብኝው በአካባቢው በቆየበት ጊዜ  ለምግብ፣ ለምኝታ፣ ለአስጎብኝ፣ ለትራንስፖርት፣ ለስጦታ ዕቃዎች መግዣ ወዘተ ያወጣል ተብሎ የሚገመተው ወጭ ላይ መሰረት እንደሚያደርግ  የዓለም ቱሪስም ድርጅት የቃላት መፍቻ ያስረዳል።

- የአማራ ክልልን በሩብ አመቱ የጎበኙት እነማናቸው? ገቢውስ ከምን ተገኘ?

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በሩብ አመቱ ክልሉን ጎበኙ ያላቸውን ዋና ዋና ተጓዦችን ዘርዝሯል። በቢሮው የቱሪዝም ልማት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ አዳም በግሸን ደብረ ከርቤ በዓል አከባበር ብቻ አንድ ሚሊየን ሃይማኖታዊ ጎብኝዎች ወደ አካባቢው መጓዛቸውን የገለጹ ሲሆን በሰሜን ሸዋ የሚገኙ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ መስህቦችን ለመጎብኘትም  በየሳምንቱ መጨረሻ የእረፍት ቀናት ከአዲስ አበባ በርካታ ጎብኚዎች እንደሚመለጡ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከነሐሴ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚከበሩት የሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል፣ የመስቀል፣ የግሸን ደብረ ከርቤ በዓላትና ሌሎች ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላትንም አስረድተዋል።

ከጎብኝዎቹ መካከልም 6,328 የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ከጎብኝዎች ተገኘ የተባለው ገቢ የተሰላው አንድ የውጭ ወይም የሀገር ውስጥ ጎብኝ  እንደ አካባቢው ሁኔታ በቀን ለመኝታ፣ ለምግብ፣ ለአስጎብኝ፣ ለጫማ ማስዋብና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያወጣው ታስቦ መሆኑ ቢሮው ባጋራው መረጃ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

28 Nov, 14:45


#Explainer ድምጽ ማቸገን (voice cloning) ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለን?

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች ፈጣንና የማያቋርጥ እድገት ለሰው ልጆች በርከት ያሉ ዕድሎችን ይዘው ስለመምጣታቸው በተደጋጋሚ ሰምተናል፣ በአንጻሩ ቀላል የማይባሉ ጉዳቶችን እያስከተሉ ስለመሆናቸውም አድምጠናል።

ለምሳሌም በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሚፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እና ጽሁፎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን በማባባስ ረገድ በመጫዎት ላይ ያሉትን አሉታዊ ሚና መጥቀስ ይቻላል።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/disinformation-threats-posed-by-voice-clones-and-how-to-combat-them/

Ethiopia Check

28 Nov, 14:21


#Explainer ቅኑዕ ሓበሬታ ንምርካብ ክትገብሩዎም ዝግባእ ጥንቃቐታት

ሰባት ካብ ቀረባ ግዜያት ናብዚ ማሕበራዊ ሚዲያ ከም ቀንዲ ምንጪ ሓበሬታን ፍልጠትን ገይሮም ይወስዱዎ ከም ዘለው ይፍለጥ።
ኣብዚ እዋን ድማ ኣብዞም መድረኻት ትኽክለኛ ወይ ቅኑዕ ሓበሬታ ንምርካብ ኣፀጋሚ ዝኾነሉ ኣጋጣሚታት ከምዘሎ ንዕዘብ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/how-to-identify-reliable-information-%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/

Ethiopia Check

25 Nov, 10:33


#የሰኞመልዕክት የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመቀነስ ጋዜጠኞች ምን ማድረግ ይችላሉ?

አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቀን ከቀናት በፊት በተለያዩ መርሐግብሮች ተከብሮ ውሏል። በዕለቱም በአስቸጋሪ የስራ አውድና ከባቢ ውስጥ ሁነው መረጃ የሚደርሱ ጋዜጠኞች ታስበው ውለዋል። ኢትዮጵያ ቼክም ለሙያ እና ለስነምግባር መርሆች ታምነው ማህበረሰባቸውን ያገለገሉ ጋዜጠኞችን ያመሰግናል!

ሆኖም የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶች ስርጭት ከፍተኛ ምስቅልቅል እየፈጠረ ባለበት በዚህ ወቅት የጋዜጠኞች ሚና መረጃን ከመዘገብም በላይ መሆን አለበት ብለን እናምናለን። በዚህ አኳያም ጋዜጠኞች ዘርፈ ብዙ አስተዋጾ ማበርከት ይችላሉ።

ጋዜጠኞች በቅድሚያ ማድረግ የሚችሉት በጎ አስተዋጾ የሙያ እና የስነምግባር መርሆችን በጥብቅ ማክበርና መፈጸም ሲሆን ይህም የሀሠተኛ መረጃን እና የጥላቻ መልዕክቶች ስርጭት በመቀነስ ረገድ የማይተካ ሚና አለው። ጋዜጠኞች ለሙያና ለስነምግባር መርሆችን በከፍተኛ ደረጃ ተገዥ በመሆን ዘገባቸው ትክክለኛ፣ ርዕታዊ፣ ከሀሠተኛ መረጃ የጸዳ፣ አካታችና ከጥላቻ መልዕክት የራቀ መሆኑን ማረጋገጥ የዕለት ስራቸው መሆን ይገበዋል። በተጨማሪም ግልጽነት የተሞላበት የዘገባ ሂደትን ማስፈን፣ ስህተት ሲፈጠር ቀጥተኛና ፈጣን ዕርምት መስጠት ከተከታታዮች ጋር የሚኖረውን የመተማመን ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።

በሌላ በኩል ጋዜጠኞች የመረጃ ማጣራት ስራን በመስራት እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን በማጋላጥ በጎ ተጽኖ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም በሚሰሩባቸው የሚዲያ ተቋማት የመረጃ ማጣሪያ ዴስክ በማቋቋም፣ የአየር ሰዐት ወይም የህትመት ቦታ በመመደብ፣ የግል የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን በመጠቀም እንዲሁም ገለልተኛ ከሆኑ የመረጃ አጣሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት መከወን ይችላሉ።

በተጨማሪም ጋዜጠኞች የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን መለየት፣ ማጣራት እና ማጋለጥ እንዴት እንደሚቻል የሚያስተምሩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ፕሮግራሞችን በመስራትም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። ይህንንም የመረጃ ማጣራት ዘዴዎችና ቴክኖሎጅዎች በመማር እንዲሁም ባለሙያዎችን በመጋበዝ በቀላሉ መስራት የሚቻል ነው።

የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ከአሉታዊ ይዘቶች አንጻር የክትትልና የቁጥጥር ስራቸውን ጠበቅ እንዲያደርጉ በመወትወት እንዲሁም የህግ አውጭና ፈጻሚ አካላት የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕቶች በተመለከተ የሚያወጧቸውን ህጎችና ፖሊሲዎች ጉድለታቸውን በመፈተሽ እንዲሁም በትክክለኛ አግባብ መፈጸማቸውን በመከታተል በጎ ተጽኖ ማሳረፍ ይቻላል።

ጋዜጠኞች እነዚህንና ሌሎች የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭትን የሚቀንሱ ተግባራትን እንደሙያ ግዴታቸው በመቀበል በየዕለቱ መተግበር ከቻሉ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለን እናምናለን።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

22 Nov, 17:26


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

(ኀዳር 13፣ 2017)

https://ethiopiacheck.org/home/ethiopia-checks-friday-round-up-stories-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab/

Ethiopia Check

20 Nov, 13:07


#FakeAccountAlert Akkaawuntii X (Tiwiitaraa) sobaa maqaa Obbo Jawaar Mahaammadiin baname irraa of yaa eegnu!

Akkaawuntiin X (Tiwiitaraa) sobaa maqaa Obbo Jawaariin baname odeeffannoowwan garagaraa qoodaa akka jiru hubanneerra.

Akkaawuntiin maqaa ‘Jawar Muhammad’ jedhufi hordoftoota 380 ol qabu kun ji’oota darban keessa odeeffannoowwan heddu maxxanseera.

Odeeffannoowwan akkaawuntichi tibbana qoode keessaa tokko immoo ergaa baga gammaddanii mootummaan Itoophiyaa dhiyeenya kana Pirezidaantii Somaalilaand ta’anii kan filaman Abdiraahmaan Mohammad Abdullaahiif dabarse ni argama.

Maxxansa kana keessatti akkaawuntichi bifa safuun ala ta’een Pirezidaantii Somaaliyaa kan ta’an Hasan Sheek Mohaammud qeeqee jira.

Obbo Jawaar gama isaaniitin akkaawuntiin kun kan isaanii akka hintaane akkaawuntii Tiwiitaraa isaanii sirrummaan isaa mirkanaa’e fi hordoftoota kuma 349 ol qaburratti beeksisaniiru.

Odeeffannoon akkaawuntii sobaa irratti qoodames akkaawuntii isaanii isa sirriirra akka hinjirre mirkaneessineerra. Akkaawuntiin X Obbo Jawaar Mahaammad inni sirriin geessituu kanaan argama: https://x.com/jawar_mohammed?s=21&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

Gama biraatiin akkaawuntiin X sobaa maqaa nama siyaasaa kanaan ALI Waxabajjii 2016 baname ji’oota muraasa darban keessatti odeeffannoowwan 390 ol qooduu isaa ilaallee jirra.

Akkaawuntiiwwan fi fuulawwan miidiyaalee hawaasaa sobaa maqaa namoota fi dhaabbilee beekamootiin banaman odeeffannoowwan sobaa fi dogongoraaf nusaaxiluu waan danda’aniif ofeeggannoo yaa taasifnu.

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

19 Nov, 13:41


#FactCheck የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የመኪና መገጣጠሚያ ሲያስመርቁ ያሳያል ተብሎ የተጋራው ቪዲዮ የተሳሳተ ነው

ከ7 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘UNO’ የሚል ስያሜን የሚጠቀም የቲክቶክ አካውንት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የመኪና መገጣጠሚያ ሲያስመርቁ ያሳያል ያለውን ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ቪዲዮውም በድምሩ ከ12,000 በላይ ግብረ-መልሶችን ያገኘ ሲሆን በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሰው ፕሬዝደንት መንግስቱ ናቸው ብለው ያመኑ በርካታ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡም ተመልክተናል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሰው ፕሬዝደንት መንግስቱ አለመሆናቸውን አረጋግጧል። በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሰው በጋና የሚገኝ አሳንቲ ብሔር ባህላዊ ንጉስ ሲሆኑ የንግስና ስማቸውም ዳግማዊ ኦቶሙፉ ናና ኦሲ ቱቱ (Otumfuo Nana Osei Tutu II) ነው።

ንጉሱ ከንግስናቸው በተጨማሪ የኩዋሜ ኑኩሩማህ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር በመሆንም ያገለግላሉ።

ከላይ የተጋራው ቪዲዮ የተቀረጸውም ዳግማዊ ኦቶሙፉ ናና ኦሲ ቱቱ ከሶስት ቀናት በፊት ዞንዳ የተባለን በጋና የሚገኝ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በጎበኙበት ወቅት ነበር። ትክክለኛውን ቪዲዮ ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል:
https://vm.tiktok.com/ZMhnCy44V/

ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

18 Nov, 16:38


#FactCheck የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከሰሞኑ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” እንዳሉ ተደርጎ የተጋራው መረጃ አዲስ አይደለም

‘Somali Soldier’ የሚል ስም ያለው የኤክስ (ትዊተር) አካውንት የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ብለዋል ሲል ከሰሞኑ በተደጋጋሚ መረጃ አጋርቷል።

መረጃው የዋና ጸሃፊውን ምስል እና ንግግራቸው ያረፈበት የስክሪን ቅጂም በውስጡ ይዟል።

‘Somali Soldier’ የኤክስ አካውንት ጉቴሬዝ ይህን ንግግር መች እንደተናገሩ ወይም በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው እንዳጋሩ ምንም አልጠቀሰም።

ኢትዮጵያ ቼክ በመረጃው ዙሪያ ባደረገው ማጣራት መረጃው ንግግሩ የተደረገበትን ቀን ሳይጠቅስ አሳሳች በሆነ መልኩ መጋራቱን ተመልክቷል።

ጉቴሬዝ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ያሉት ከሰሞኑ ሳይሆን ከሁለት ዓመታት በፊት እኤአ ጥቅምት 17፤ 2022 ሲሆን ይህን ያሉትም በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ተከስቶ የነበረውን ጦርነት በማስመልከት ነበር።

ዋና ጸሃፊው በወቅቱ ያጋሩት የኤክስ (ትዊተር) መልዕክትም መዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://x.com/antonioguterres/status/1582082186337202176?s=46&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

ስለዚህም ‘Somali Soldier’ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ዋና ጸሃፊው አሁን እንደተናገሩ በማስመሰል ያቀረበው መረጃ አሳሳች እና ያልተሟላ ነው።

የተሟላ መረጃ ሳያካትቱ እና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ መረጃዎች ለሀሰተኝ እና የተሳሳተ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ።

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

18 Nov, 08:55


#MondayMessage ዘረባ ፅልኣትን ናይ ሓሶት ሓበሬታን ኣብ ምቁፅፃር ግዳ ትካላት ማሕበራዊ ሚዲያ እንታይ ክመስል ይግባእ?

ኣብዚ እዋን ኣብ ማሕበራዊ ሚዲያታት ዝርአ ዝርግሐ ናይ ሓሶት ሓበሬታን ዘረባ ፅልኣትን ኣዝዩ ከም ዝወሰኸ ይፍለጥ።

ይኹን’ምበር ነዞም ነገራት ባይታ ዝህቡ ዘለው ኵባኒያታት ማሕበራዊ ሚዲያታት እኹል ናይ ምቁፅፃር ስራሕቲ ብዘይምስራሕ ይንቀፉ። እዚ ብፍላይ ኣብ ኢትዮጵያ ብሰፊሑ ይርኣይ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/the-roles-and-responsibilities-of-social-media-companies-in-countering-hate-speech-and-disinformation-%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab/

Ethiopia Check

15 Nov, 15:19


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. ቲክቶክ በፈረንጆች ሁለተኛ ሩብ ዓመት በኬንያውያን ተጠቃሚዎች የተጫኑ 360,000 ይዘቶችን ማንሳቱን አስታውቋል። በተመሳሳይ 60,000 አካውንቶችንም መሰረዙን ገልጿል። ቲክቶክ ባስነበበው የሩብ ዓመት ሪፖርቱ ከተነሱት ይዘቶች አብዛኞቹ ሀሠተኛ መረጃንና ልቅ ወሲብን ያሰራጩ ናቸው ብሏል። ከተሰረዙት አካውንቶች መካከል ደግሞ 90% ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የሚጠቀሙባቸው ሆነው በመገኘታቸው መሆኑን ገልጿል። ኬኒያ ከወራት በፊት ቲክቶክ የየሩብ ዓመቱን ሪፖርት እንዲያቀርብ መጠየቋ ይታወሳል።

2. አንጋፋው የብሪቲሽ ዕለታዊ ጋዜጣ ዘ-ጋርዲያን ኤክስ የተሰኘውን የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም ማቆሙን አስታውቋል። ጋዜጣው በድረገጹ ባስነበበው መግለጫ ኤክስን አሉታዊ ይዘቶች የበረከቱበት “መርዛም” ፕላትፎርም ሲል ገልጾታል። ከጋርዲያን በተጨማሪም የስፔኑ ላ ቫንጋርዲያ ጋዜጣም ኤክስ የሀሠተኛ መረጃ አሰራጮችና የሴራ ተንታኞች የገደል ማሚቶ (echo chamber) ሆኗል የሚል ምክንያት ከሰጠ በኃላ ፕላትፎርሙን መጠቀም እንደሚያቆም ገልጿል።

3. በተመሳሳይ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን (Reporters Without Borders) ኤክስ የተሰኘውን የማህበራዊ ሚዲያ ሀሠተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል መክሰሱን አስታውቋል። ቡድኑ በፈረንሳይ ሀገር በሚገኝ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ኤክስ ከተቋሙ አንጻር የተሰራጨን ሀሠተኛ መረጃ ተደጋጋሚ ሪፖርት ቢቀርብለትም አለማንሳቱን ያትታል። ቡድኑ ክሱን ያቀረበው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ለማሳየት መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስነብቧል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-የማህበራዊ ሚዲያ ድርጅቶች በጥላቻ ንግግር እና በሃሰተኛ መረጃ መቆጣጠር ላይ ያላቸው ሚና ምን መምሰል አለበት በሚለው ጉዳይ መልዕክት አስተላልፈናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2502

-ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑን ወታደራዊ ኮንቮዮች ያሳያል ተብሎ የተጋራን ፎቶ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2503

-‘’የድሮ ፎቶ’’ እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስልንም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2504

-ቴክኖሎጂን በመጠቀም ‘በሰአታትእ ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ መረጃንም ተመልክተናል: https://t.me/ethiopiacheck/2505

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

14 Nov, 17:18


#HealthCheck ቴክኖሎጂን በመጠቀም ‘በሰአታት' ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ አሳሳች ነው

“በሦስት ሰአታት ውስጥ የስኳር ህመምን ከነዘርማንዘሩ ማጥፋት ተችሏል” የሚል መረጃ በቲክቶክና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

እነዚህ ‘ET Smart Care’ በሚል የቲክቶክ አካውንት እየተሰራጩ የሚገኙ የህክምና መረጃዎች “የክሩስፐር ጂን ኤዲቲንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሦስት ሰአት ውስጥ የስኳር ህመምን ከነዘር ማንዘራቸው ማጥፋት ተችሏል። እውነት ነው ከነዘር ማንዘራቸው ማጥፋት ችሏል” ሲል ይደመጣል።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/health-professionals-advised-against-misleading-information-about-diabetes-treatments-circulating-on-social-media-%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8c%83/

Ethiopia Check

13 Nov, 19:37


#FactCheck "የድሮ ፎቶ" እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስል

'አበበ ቶላ ፈይሳ' የተባለ ፌስቡክ ላይ ከ158 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ "የድሮ ፎቶ እያወጣህ እንደ አዲስ የምትለጥፍ ከሆነ..." በሚል ያሰራጨው ምስል እንዳለ ተመልክተናል።

ግለሰቡ በዚህ ልጥፉ ላይ ከትናንት ጀምሮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲንሸራሸር የነበረው የፋኖ ሀይሎች አመራር የሆነው የዘመነ ካሴ ምስል "ዓመት የሞላው" መሆኑን ገልጿል።

ይህን ያሳያሉ ያላቸውን እና የፋኖ አመራሩን ፎቶ አምና፣ ማለትም እአአ በ2023 የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አጋርተውት ነበር ያላቸውን ምስሎች አያይዟል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ማጣራት እንዲያደርግ ጥያቄ የቀረበለት ሲሆን እኛም በዚህ ዙርያ ፍተሻ አርገናል።

በዚህ ዙርያ ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የድሮ እንዲመስሉ '2023' የሚል ዓመት በፎቶሾፕ ቅንብር እንደገባባቸው ተመልክተናል። ቅንብሩ ሲሰራም የፌስቡክን ዲዛይን በማይመስል መልኩ ተጣሞ እና ከዲዛይን ውጪ ክፍተት ኖሮበት ሆኖ እንደተሰራ መመልከት ይቻላል።

ከዚህም በተጨማሪ መረጃውን አጋርተዋል ወደተባሉት የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች በመሄድ ምርመራ ያደረግን ሲሆን "የአርበኛ ዘመነ ካሴ የዕለቱ መልዕክት" ከሚለው ፅሁፍ ጋር ተጋርቶ የነበረው ሌላ የፋኖ አመራሩ ምስል መሆኑን ለማየት ችለናል።

በዚህም ምክንያት 'አበበ ቶላ ፈይሳ' በተባለው ግለሰብ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና በቅንብር የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ከአውድ ውጪ ከሚቀርቡ፣ በቅንብር ከሚሰሩ እና ተጋነው ከሚሰራጩ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

13 Nov, 13:11


ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑን ወታደራዊ ኮንቮዮች ያሳያል ተብሎ የተጋራው ፎቶ ከሌላ ቦታ የተወሰደ ነው

ከ15,700 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Demekech’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የኤክስ/ትዊተር አካውንት ብዛት ያላቸው ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን የሚያሳይ ፎቶ ማጋራቱን ተመልክተናል።

በፎቶው ላይ የሚታዩት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑ መሆናቸውን ገልጿል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ የጎግል ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች መገልገያን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው ፎቶ ከሩዋንዳ የተወሰደ መሆኑን አረጋግጧል።

በፎቶው ላይ የሚታዩት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ሲሆን እአአ በታህሳስ ወር 2021 ዓ.ም በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተፈጠረን ውጥረት ተከትሎ ሩዋንዳውያንና ዩጋንዳውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስፋት ሲያጋሩት ነበር።

ይህንንም የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመከተል መመልከት ይቻላል:

https://web.facebook.com/share/p/15VXLLitQP/

https://web.facebook.com/share/p/15m5CFiBCd/

በተጨማሪም በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚነበበውን የሰሌዳ ቁጥር ያነጻጸርን ሲሆን የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት የሚጠቀምበት መሆኑን አይተናል።

ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ፎቶዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

11 Nov, 03:29


#EthiopiaCheck የሰኞ መልዕክት

የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ድርጅቶች በጥላቻ ንግግር እና በሃሰተኛ መረጃ መቆጣጠር ላይ ያላቸው ሚና ምን መምሰል አለበት?

የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየበዛ መቷል፡፡ ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች የሚወጡባቸው የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች በቂ የሚባል የመቆጣጠር (moderating) ስራ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሰሩ አይታዩም።

እነዚህ ድርጅቶች በመጀመሪያ የተመሰረቱ ጊዜ በሚዲያቸው ላይ ለሚወጡ ጽሁፎችም ሆነ ማንኛውም አይነት ነገሮች ተጠያቂነታቸውን ከራሳቸው ላይ አንስተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰዎች ማንኛውንም አይነት መረጃዎችንም ሆነ ዜና የሚያገኙት በነዚህ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ ብቻ እየሆነ መቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ድርጅቶችም ከብዙ ጫናዎች በኋላ በተወሰነ መልኩ በሚዲያዎቻቸው ላይ የሚወጡትን መረጃዎች አርተፊሻል ኢንተለጀንስን እና የሰው ሀይልን በመጠቀም መቆጣጠር ጀምረዋል፡፡

ሆኖም ግን የሃሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች የመብዛታቸውን ያክል እነዚህ ድርጅቶች ሃላፊነት ወስደው ሲሰሩ አይታዩም፣ በተለይ የፖለቲካ ይዘት ባላቸው ጽሁፎች ላይ፡፡ የሚያንማር መንግስት በሮህንጊያ ሙስሊሞች ላይ ያሰራጨው የሃሰተኛ መረጃ ያስነሳውን ከፍተኛ እልቂት እንደ ምሳሌነት መመልከት እንችላለን፡፡

በሃገራችንም ደግሞ በተለይ ከ2015 አ.ም ጀምሮ በሚታዩት የተለያዩ አለመግባባቶች እና ግጭቶች ጀርባ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ የሚወጡት የሃሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች ግጭቶቹን ከሚያባብሱት ውስጥ ናቸው።

የእነዚህ ሚዲያዎችን ቸልተኝነትን አስከትሎ በአለማችን ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት በማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ የሚወጡትን መረጃዎች በተለይም የፖለቲካ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች የሚቆጣጠሩበት መመሪያዎችን አውጥተዋል። እነዚህ መመሪያዎችን ካወጡ ሃገራት መካከል አውስትራሊያ እና ሲንጋፖር ይገኙበታል።

ኢትዮጵያም በቅርቡ ያጸደቀችው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ውስጥ ለተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ኃላፊነቶችን አስቀምጣለች።

ህጉ “ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠርና ለመግታት ጥረት ማድረግ አለበት። ድርጅቱ የጥላቻ ንግግርን ወይም የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ጥቆማ ሲደርሰው በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ ይህን መሰል መልዕክቶችን ወይም ንግግሮችን ከአግልግሎት አውታሩ ሊያስወግድ ይገባል” ይላል።

ነገር ግን መንግስት እንደዚህ አይነት ህጎችን/መመሪያዎችን አውጥቶ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚወጡትን መረጃዎች በሚቆጣጠሩበት ጊዜ የሰዎችን የመናገር መብትን ሲጋፉ እናያለን።

እንደ መፍትሄ ልናያቸው ከሚገቡ አስተያየቶች መካከል:

1. በእነዚህ ድርጅቶች ድህረ ገጽ ላይ የሚወጡትን እያንዳንዱን መረጃዎች የሚከታተሉ ሰዎች (content moderators) በብዛት መቅጠር ያስፈልጋቸዋል። አሁን ከሚጠቀሟቸው ከነሱ ውጪ ያሉ ድርጅቶች (outsourced companies) ይልቅ በየሃገሩ ሰዎችን መቅጠር አለባችው። እነዚህም የሚቀጠሩት ሰዎች የሃገሩን ባህል እና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች መሆን ይኖርባቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ከ7 ሚሊየን ሰዎች በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚ ባለባት ሀገር እና በብዙ ቋንቋዎች በሚጻፍባት ሃገር ላይ በብዛት መረጃዎችን የሚከታተሉ ሰዎች (content moderators) መቀጠር አለባቸው።

2.  እነዚህ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ደግሞ ቢያንስ በመረጃ የተረጋገጡ ሃሰተኛ መረጃዎችን ከአውታራቸው ማውረድ ይኖርባቸዋል።

3. እንዲሁም ትክክለኛ ገፆችን ማረጋገጥ (verify ማድረግ) እና ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን የመዝጋት ሀላፊነታቸውንም ሊወጡ ይገባል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

08 Nov, 14:57


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባነት በተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል። የቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ከከተማው ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የተማሪዎች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ለውጤት ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያት በመሆኑን አስታወቀዋል። ሃላፊው “በተለይም ቲክቶክ ቶታሊ ልጆችን ቀምቶናል” በማለት የተናገሩ ሲሆን “እነዚህን ሶሻል ሚዲያዎችን ባን ካላደረግን (ካልዘጋን ተማሪዎችን) አስተምረን ዳር እናደርሳልን ከባድ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

2. ዋትስአፕ የሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች (reverse image search) አገልግሎትን በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የቴክኖሎጅ ዘገባዎችን የሚሰራው ቴክራዳር በሳምንቱ አጋማሽ አስነብቧል። የሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች አገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በዋትስአፕ የሚመለከቱትን ፎቶ ትክክለኛነት በቀላሉ ለማወቅ ይረዳቸዋል ተብሏል። አገልግሎቱን ለማግኘት ፎቶውን መከፈት ቀጥሎም ቁልቁል የተደረደሩትን ሶስት ነጥቦችን መንካት ከዚያም ሰርች ኦን ዌብ (search on web) የሚለውን አማራጭ ብቻ መንካት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

3. ካናዳ የቲክቶክ ቢሮዎችን መዝጋቷን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ይሁን እንጅ ካናዳዊያን የቲክቶክ መተግበሪያን መጠቀም መቀጠል ይችላሉ ተብሏል። ካናዳ እርምጃውን የወሰደችው ከብሔራዊ ደህነንት ስጋት ጋር በተገናኘ መሆኑ ተገጿል። ቲክቶክ ውሳኔውን የተቃወመ ሲሆን ወደ ፍርድ ቤት ሂጀ እሟገታለሁ ብሏል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች ሊንኮች:

- አልጎሪዝሞች እንዴት የመረጃ አጠቃቀማችንን መልክ እንደሚያስይዙ በሰኞ መልእክታችን በትግርኛ ቋንቋ አቅርበናል: https://tig.ethiopiacheck.org/home/tackling-echo-chambers-and-filter-bubbles-how-algorithms-shape-our-social-media-news-feeds-%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/

-ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ መወሰኑን በመግለጽ የተሰራጨን ‘ደብዳቤ’ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2497

-በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የሚዲያ ዳሰሳ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2498

- ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው የተባለ ግለሰብ ያሰራጫውን ምስልም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2499

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

08 Nov, 13:40


#FactCheck ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው የተባለ ግለሰብ ያሰራጨው ሀሰተኛ ምስል

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ዛሬ የሰራውን ዘገባ በማንሳት "ስትዋሹም እየተናበባችሁ" በማለት ግለሰቡ መረጃ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዜናው የተጠቀመበት ምስል በትግራይ ጦርነት ወቅት ትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመበት መሆኑን በመጥቀስ ይህን ያሳያል ያለውን ምስል ከቢቢሲ ዘገባ ጋር በማመሳከር አቅርቧል።

"ውሸትን እንደትግል መሳሪያ መጠቀም የነበረ፣ ያለና የሚኖር ሃቅ ነው። ነገርግን ፕሮፓጋንዳ ሳይንስ እና የላቀ ጥበብ የሚሻ እንጂ  ተዘርፍጠ'ው የሚሰሩት ቀላል ስራ አይደለም" ያለው ረዳት ፕሮፌሰሩ አክሎም "በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ከሁለት ዓመት በፊት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የዋለን ምስል ተጠቅሞ ፕሮፓጋንዳ መስራት አንድም ፕሮፓጋንዳን መናቅ ሁለትም ጅላንፎ'ነት ስለሆነ ማስተካከያ ልታደርጉና ተናባችሁ ልትዋሹ ይገባል" በማለት 77 ሺህ ገደማ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፁ ላይ መረጃ አጋርቷል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ማጣራት ያደረገ ሲሆን ግለሰቡ ያሰራጨው ምስል በቅንብር የቀረበ እና ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ማየት ችለናል።

ትግራይ ቴሌቭዥን በወቅቱ፣ ማለትም ኦክቶበር 24/2022 ባወጣው ዘገባው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት የተጠቀመውን ምስል ሳይሆን ሌላ የድሮን ጥቃትን ያሳያል የተባለ መሆኑን ማየት ችለናል (ምስሉ ላይ በስተቀኝ አያይዘነዋል)።

ስለዚህ ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዘገባው የቆየ የትግራይ ምስል እንደተጠቀመ አድርጎ ያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጠናል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

06 Nov, 13:45


#MediaMonitoring ኣብ ትግራይ ዝርከቡ ተመዛበልቲ መሊኦም ናብ መረበቶም ተመሊሶም ድዮም?

ብቀዳም ቤት ፅሕፈት ኣመሪካ ብምኽንያት ካልኣይ ዓመት ኣብ መንጎ ህወሓትን መንግስቲ ኢትዮጵያን ኣብ ፕሪቶሪያ ዝተፈረመ ውዕሊ ዘላቒ ምቁራፅ ተፃብኦታት ኣብ ዘውፅኦ መግለፂ ክሳብ ሕዚ ንዝተርኣዩ ምዕባለታት ከም ዝንእድ ጠቒሱ ነይሩ።

ምስዚ ብዝተሓሓዝ ኣብ ትግራይ ተዅሲ ደው ምባሉ ዝያዳ ክንእድ ከሎ “ተመዛበልቲ ናብ ገዝኦም ተመሊሶምን መሰረታዊ ኣገልግሎታት ናብ ንቡር ተመሊሶምን’ዮም” ክብል እቲ መግለፂ ሓቢሩ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/media-monitoring-about-the-recent-controversy-regarding-idps-in-tigray-region-%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad/

Ethiopia Check

01 Nov, 15:10


#FactCheck ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ መወሰኑን የሚገልጽ ‘ደብዳቤ’ ሀሰተኛ ነው

ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ እንደተወሰነ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

በቀን 18/2/2017 እንደተጻፈ ተደርጎ እየተጋራ የሚገኘው ይህ ደብዳቤ የትምህርት ሚኒስቴር አርማ እና የሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) “ፊርማ” አርፎበታል።

ደብዳቤው በመንግስት ይሰጥ የነበረው አቅም ማሻሻያ ፕሮግራም በበጀት እጥረት ምክንያት መቋረጡን እና ለፕሮግራሙ ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩና የመንግስት ከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ነጥብ ሲያመጡ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ያትታል።

ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነት እንዲያጣራ ከተከታዮቹ ጥቆማዎች የደረሱት ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ መረጃ አግኝቷል።

በዚሁ መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር እና የሚንስትሩን ስም እና “ፊርማ” ይዞ እየተሰራጨ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን ከት/ት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የትምህርት ሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) “ሀሰተኛ መረጃ ነው” በማለት ደብዳቤው ትክክለኛ አለመሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በደብዳቤው ላይ አጠራጣሪ የሆኑ የአፃፃፍ ሁኔታዎችን የተመለከትን ሲሆን በፎቶፎረንሲክስ መስል መመርመሪያ መሳሪያ ባደረግነው ማጣራትም ደብዳቤው ተመሳስሎ የተሰራ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶችን ተመልክተናል።

ተመሳስለው የሚሰሩ ሀሰተኛ ደብዳቤዎች ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣ ሲሆን ታማኝ ባልሆኑ ምንጮች የሚሰራጩ መሰል ደብዳቤዎችን አምነን ከመቀበላችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

31 Oct, 11:51


#MediaMonitoring የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር እንደተከለከለ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነ አየር መንገዱ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናገረ

በርካታ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማልያ ኦንላይን ሚድያዎች ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል ውስጥ እንዳይበር መከልከሉን እየዘገቡ ይገኛሉ።

እንደ 'Eritrean Press' ያሉ እነዚህ ሚድያዎች ለዚህ ክስተት አስረጂ ነው ያሉትን ማስረጃ ባያቀርቡም ጉዳዩ አየር መንገዱ በቅርቡ ወደ ኤርትራ እንዳይበር ከመታገዱ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አመላክተዋል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ማብራርያ ጠይቋል።

"አየር መንገዳችን አሁንም በኤርትራ አየር ክልል እየበረረ ነው፣ መረጃው የተሳሳተ ነው" ብለው አንድ ከፍተኛ የአየር መንገዱ ሀላፊ መረጃ ሰጥተውናል።

"በኤርትራ አየር ክልል ለመብረር አሁንም ፈቃድ አለን፣ ይህ ፍቃድ እንደተነሳ ምንም አይነት ከኤርትራ አልደረሰንም" ብለው ያስረዱት ሀላፊው ከበፊቱ የተቀየረ ነገር እንደሌለ ጠቁመዋል።

ይሁንና Flight Radar 24 የተባለው የበረራ መከታተያ ድረ-ገፅ እና መተግበርያ አንዳንድ አውሮፕላን የኤርትራን አየር ክልል በመተው በሱዳን በኩል እየበረሩ እንደሆነ በ X ላይ ምላሽ ሰጥቷል።

ይሁንና በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አየር መንገዱ አሁንም በረራውን በኤርትራ የአየር ክልል እያደረገ እንደሆነ የሚያሳዩ የስክሪን ቅጂዎችን እያጋሩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

31 Oct, 10:33


#FactCheck ጠ/ሚር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት መዳረሻነት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ስለመሆኗ ስላነሱት ሀሳብ ጥናቶች ምን ይላሉ?

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዛሬው የፓርላማ ውሏቸው ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መሀል ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ነበር።

"በአፍሪካ ውስጥ የፈለገው ያህል የሚድያ ፕሮፖጋንዳው ቢስፋፋም ኢትዮጵያን የሚያክል ለኢንቨስትመንት ምቹ የሚባል ሀገር እምብዛም የለም" በማለት የተናገሩት ይህም ከመሬት አጠቃቀም፣ የኢነርጂ አቅርቦት እንዲሁም ዝቅተኛ የብልሹ አሰራር/ጉቦኝነት መኖርን አንስተዋል።

በዚህ ዙርያ በአፍሪካ በየአመቱ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሆኑ መዳረሻዎችን በማውጣት የሚታወቀው ግዙፉ RMB ግሩፕ ያወጣውን ጥናት እንመልከት።

የዘንድሮው (እአአ የ2024) የተቋሙ ጥናት እንደሚያሳየው ሲሸልስ ቀዳሚዋ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገር ስትሆን በምክንያትነት የተቀመጠው ሳቢ የኢንቨስትመንት አሰራር፣ የህዝብ እድገት እና የተረጋጋ ኢኮኖሚ ናቸው።

በሁለተኝነት የተቀመጠችው ሞሪሺየስ ስትሆን ሀገሪቱ ደግሞ በፈጠራ፣ በኢኖሚ ነፃነት፣ በጥሩ መልኩ በሚመራ የኢንቨስትመንት ሴክተር እና ከፍ ባለ የነፍስ ወከፍ ገቢ ተመራጭ ሆናለች።

ከሶስት እስከ አምስት ያለውን ቦታ የያዙት ደግሞ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ናቸው።

RMB የግዙፉ የደቡብ አፍሪካው ፈርስት ራንድ ግሩፕ የኮርፖሬት እና ኢንቨስትመንት ባንኪንግ (CIB) ቅርንጫፍ ሲሆን ሪፖርቱን በዚህ ሊንክ መመልከት ይቻላል: https://www.rmb.co.za/where-to-invest-in-africa-2024

በዚህ ዙርያ አለም አቀፍ ሚድያዎች ዘገባዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን የፋይናንስ ዜናዎችን በማውጣት የሚታወቀው ብሉምበርግ የሰራውን ዜናም መመልከት ይቻላል: https://www.bloomberg.com/news/articles/2024-08-06/island-nations-top-egypt-as-best-african-investment-destinations?embedded-checkout=true

ከዚህ ተቋም በተጨማሪ የሌሎች ሁለት ድርጅቶችን ጥናት የተመለከትን ሲሆን ኢትዮጵያ እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ያላት እንጂ አሁን ላይ በአንደኝነት ተመራጭ ከሚባሉ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች አንዷ መሆኗን አያሳዩም።

በዚህም ምክንያት ይህን በፓርላማ የቀረበ ንግግር ተጋኖ የቀረበ መሆኑን ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

28 Oct, 11:54


#MondayMessage Maalummaafii maloota ittisaa duulawwan odeeffannoo sobaa bifa qindaa’een adeemsifaman

Babal’achuu itti fayyadama miidiyaa hawaasaan walqabatee duulli odeeffannoo sobaa bifa qindaa’een taasifamu (coordinated disinformation campaigns) galmoota siyaasaa, diinagdee fi hawaasummaa milkeessuuf dhimma itti bahamaa jira.

Guutuusaa dubbisuuf geessituu kana cuqaasaa: https://ao.ethiopiacheck.org/home/mondaymessageodeeffannoo/

Ethiopia Check

25 Oct, 13:24


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።አቶ ታዲዮስ ታንቱ በሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም “የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል” ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።


2. ሊንክድኢን ለ55 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች የአካውንት ትክክለኛነት ማረጋገጫ (account verification) መስጠቱን አስታውቋል። ሊንክድኢን ማረጋገጫውን በብዛት መስጠት የጀመረው በተለይም በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚፈበረኩ ምስሎችን በመጠቀም የሚከፈቱ አካውንቶች ስጋት ስለፈጠሩበት መሆኑን ገልጿል። እንዲህ ባሉ አካውንቶችም ለመለየት እስከሚያስቸግር ድረስ ሀሠተኛ ባለሙያዎች (fake experts) እና ሀሠተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት መታየታቸውን ጠቅሷል። ሊንክድኢን የአካውንት ማረጋገጫ የሰጣቸው ተጠቃሚዎች ቁጥር ከሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ሲነጻጸር ከፍተኛ ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ 100 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱ ተገልጿል።

3. ከሶስት ሰዎች ሁለቱ በኢንተርኔት አማካኝነት በሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮች ተጠቂ መሆናቸውን አንድ ጥናት አሳይቷል። የተመድ የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) አይፒኤስኦኤስ (IPSOS) ከተባለ ተቋም ጋር የሰሩት ይኸው ጥናት ፌስቡክ እና ቲክቶክ የጥላቻ ንግግር በስፋት ከሚሰራጭባቸው ፕላትፎርሞች ቀዳሚዎቹ መሆናቸውን አሳውቋል። ጥናቱ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ምርጫ በሚደረግባቸው 16 ሀገሮች የተካሄደ ሲሆን ህንድ (85%)፣ ባንግላዴሽ (84%) እና ደቡብ አፍሪካ (79%) የጥላቻ ንግግር በስፋት የሚሰራጭባቸው ሀገሮች ናቸው ተብለዋል።


በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-ቆየት ያሉ ይዘቶችን ለመፈለግ የሚረዳ መገልገያ የሚያስተዋውቅ ጽሁፍ አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2485

-የፋኖ ሀይሎች ሚሳኤል የታጠቀ ድሮን በአማራ ክልል መተው ጣሉ” በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ ቪድዮን አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2486

-በጅማ አየር ማረፊያ ፎቶ የተነሳው እቃ ጫኝ አውሮፕላን በተመለከተ የተጋራን መረጃ ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2488

-የብሪክስ አባል ሀገራት ስራ ላይ እንዲውል የጸደቀ የገንዘብ ኖት ተብሎ በተሰራጨ መረጃ ላይ ማብራሪያ አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2490

ኢትዮጵያ ቼክ

Ethiopia Check

25 Oct, 12:24


#FactCheck ምስሉ ላይ የሚታየው 'የገንዘብ ኖት' የብሪክስ አባል ሀገራት ስራ ላይ እንዲውል የጸደቀ የገንዘብ ኖት አይደለም

ምስሉ ላይ የሚታየው እና የተወሰኑ የብሪክስ አባል ሀገራት ባንዲራ ያረፈበት 'የገንዘብ ኖት' ባለፉት ሁለት ቀናት በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

አንዳንድ ምስሉን ያጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎች ደግሞ “የብሪክስ አባል ሀገራት ዶላርን የሚገዳደር የገንዘብ ኖት ይፋ አደረጉ” ከሚል መረጃ ጋር ምስሉን እጋርተዋል።

የብሪክስ አባል የሆነችው ‘የኢትዮጵያ ባንዲራስ ለምን በኖቱ ላይ አልተካተተም?’ የሚል ጥያቄ ሲነሳም ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክም የገንዘብ ኖቱን ትክክለኛነት እንዲያጣራ ከተታዮቹ ጥቆማዎች ደርሰውታል።

በዚሁ መሰረት ምስሉ የሚታየውን “የገንዘብ ኖት” በተመለከተ ባደረግነው ማጣራት ኖቱ በብሪክስ አባል ሀገራት ጥቅም ላይ እንዲውል በይፋ የታወጀ ወይም የጸደቀ የገንዘብ ኖት እንዳልሆነ አረጋግጠናል።

ኖቱ በጉባኤው ለራሽያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተሰጠ ሲሆን አሁን ስራ ላይ የሚውል ኖት ሳይሆን አምሳያ ወይም ሞዴል ነው።

ይህን “የገንዘብ ኖት” በተመለከተ ስለ ብሪክስ ወቅታዊ መረጃዎችን በማቅረብ የሚታወቀው ‘BRICS News’ ጨምሮ በርካት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡ https://x.com/bricsinfo/status/1849149567549210829?s=46&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ እና

https://x.com/sputnikint/status/1849149063234556366?s=46&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

ላለፉት ሶስት ቀናት በራሸያ ካዛን በተካሄደው 16ኛው የብሪክስ አመታዊ ጉባኤ ከ20 በላይ ሀገራት መሪዎች መሳተፋቸው እና የስብስቡ አባል ሀገራት በጋራ ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ ገንዘብን በተመለከተ ዝግ ስብሰባ መካሄዱም ተዘግቧል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

23 Oct, 14:46


#FactCheck በጅማ አየር ማረፊያ ፎቶ የተነሳው እቃ ጫኝ አውሮፕላን ለዓለም የምግብ ፕሮግራም አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ነው

ከ22,000 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Amhara News Service’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የትዊተር አካውንት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከትናት ወዲያ በስህተት መቶ የጣለው ኢሉሽን እቃ ጫኝ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በጅማ አየር ማረፊያ ታይቶ ነበር የሚል መረጃ ማጋራቱን ተመልክተናል። 

ከመረጃው ጋርም ሁለት ፎቶዎችን ያያየዘ ሲሆን በአንዱ በጅማ አየር ማረፊያ የቆመ ኢሉሽን አውሮፕላን ይታያል። ይህንንም ከድንበር ዘለል የመሳሪያ ዝውውር ጋር አገናኝቶታል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ በፎቶው ላይ ባደረገው ማጋጣራት በጅማ አየር ማረፊያ ቆሞ የሚታየው አውሮፕላን ለዓለም የምግብ ፕሮግራም አገልግሎት (World Food Program) ይሰጥ የነበር መሆኑን አረጋግጧል።

ፎቶግራፉ የተጋራውም የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከመጀመሩ ከዓመታት በፊት እአአ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ሲሆን በአውሮፕላኑ ጎን ላይ ውሃ ሠማያዊ ቀለም ያለው የአለም ምግብ ፕሮግራም አርማ ይታይበታል። 

ይህንንም ማስፈንጠሪያውን በመከተል መመልከት ይቻላል: https://www.instagram.com/p/BjKG3XrjizQ/?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

ፎቶውን ያነሳውና በኢንስታግራም ገጹ ያጋራው ሰው የአለም ምግብ ፕሮግራም አርማ የሚታይበትን አውሮፕላን የሚያስዩ ፎቶዎችን ከጅማ በተጨማሪ በጋምቤላ አየር ማረፊያ በማንሳት በኢንስታግራም ገጹ ያጋራ ነበር (https://www.instagram.com/p/B7Lf_AbpKOL/?igsh=YzljYTk1ODg3Zg%3D%3D) ።

የጅማ እና የጋምቤላ አየር ማረፊያዎችን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በደቡብ ሱዳን ለሚያደርገው የምግብ እደላ ለዓመታት ይጠቀምባቸው እንደነበር ይታወቃል።

ለምሳሌ በፎቶዎቹ ላይ ከሚታዩትና የመለያ ቁጥሩ EW-355TH የሆነውን አውሮፕላን እአአ በ2014 ዓ.ም ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ (UNICEF Ethiopia) በፍሊከር ገጹ አጋርቶት ነበር።

አውሮፕላኑ በደቡብ ሱዳን  ለሚገኙ ተረጅዎች ከአየር ላይ የሚጣል ምግብ ከጋምቤላ አየር ማረፊያ እየጫነ መሆኑም ፍሊከር ላይ ይነበብ ነበር: https://www.flickr.com/photos/unicefethiopia/15898594070

በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምንመለከታቸውን መልዕክቶች ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት ትክክለኛ መሆናቸውን እንመርምር።

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

23 Oct, 14:38


#FactCheck “የፋኖ ሀይሎች ሚሳኤል የታጠቀ ድሮን በአማራ ክልል መተው ጣሉ” በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ ቪድዮ የቆየ ነው

ሰሞኑን በፋኖ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ተመቶ የወደቀን የጦር ድሮን ያሳያል በሚል አንድ ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ይገኛል።

ይህ የስክሪን ቅጂው (screenshot) ላይ የሚታየው ቪድዮ አማራ ክልል ውስጥ እንደተቀረጸ በመጥቀስ ካጋሩት መካከል ደጎሞ በኤክስ (ትዊተር) ከ159 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘Bashir Hashi Yussuf’ የሚል ስም ያለው አካውንት ይገኝበታል፡ https://x.com/BashirHashiysf/status/1848176849576194085?t=aw7ptfy0vZz5VjSzf21aMg&s=19 

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/factcheckdroneamhara%e1%8b%b5%e1%88%ae%e1%8a%95/

Ethiopia Check

21 Oct, 15:49


#MondayMessage ቆየት ያሉ ይዘቶችን ለመፈለግ የሚረዳ መገልገያ

በቅርብ የተከሰተ እውነታን ለመደበቅ ቆየት ያሉ ይዘቶችን ማጣቀሻ ማድረግ አሁን አሁን እየተለመደ የመጣ ሀሠተኛ መረጃን የማሰራጫ ስልት መሆኑን ብዙዎቻችን ታዝበናል።

ለምሳሌ በቅርቡ የተነሳን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ለማስተባበል ያሰበ ሰው ከዓመታት በፊት በእከሌ ገጽ ተጋርቶ ነበር በማል ብቅ ሊል  ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/mondaymessage%e1%89%86%e1%8b%a8%e1%89%b5/

Ethiopia Check

18 Oct, 16:16


https://ethiopiacheck.org/home/fridayroundup%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%a5/

Ethiopia Check

17 Oct, 14:03


#ScamAlert የካናዳ መንግስት ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል አመቻቸ በማለት ከሚፈጸም የማጭበርበር ድርጊት እንጠንቀቅ

የውጭ ሀገር የስራ እድሎችን እናመቻቻለን በሚል የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ ይገኛሉ።

እንደ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ያሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ፈጣን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች ደግሞ መሰል የማጭበርበር ድርጊት ለሚፈጽሙ አካላት አመቺ ሁኔታን ፈጥረዋል።

እነዚህ አካላት በግልጽ የስልክ ቁጥሮችን እና የባንክ ሂሳብ ቁጥሮችን በማጋራት የተሻለ ገቢ እና ህይወትን ተስፋ በማድረግ ወደነሱ የሚሄዱ ግለሰቦችን ያጭበረብራሉ።

ከሰሞኑም “የስራ ማስታወቂያ” የሚል ርዕስ ያለው እና የካናዳ መንግስት ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል እንደሰጠ፤ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንም ስልክ በመደወል እንዲመዘገቡ የሚያሳስብ ደብዳቤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል።

ይህ ደብዳቤ የሁለቱ ሀገራት ባንዲራ፤ ‘CANADA EMBASSY’ የሚል አራት ማዕዘን “ማህተም” እንዲሁም የቃላት እና ይዘት ግድፈት ያለበትና ሀሰተኛ መሆኑ የሚያስታውቅ ክብ ማህተም አርፎበታል።

ኢትዮጵያ ቼክ መሰል የማጭበርበር ድርጊቶችን በተመለከተ በተለያዩ ወቅቶች መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በማጣራት ለተከታዮቹ ሲያቀርብ ቆይቷል።

በካናዳ መንግስት የተመቻቹ የስራ እድሎች እና ቪዛ ሎተሪ በሚል በግለሰቦች ስልክ ቁጥር እና የቴሌግራም አድራሻዎች አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችም ከዚህ በፊት ከሰራንባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።

በወቅቱ ኢትዮጵያ ቼክ ከካናዳ ኤምባሲ መረጃን ጠይቆ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈጸሙ በርካታ የማጭበርበር ድርጊቶች መኖራቸውን እና ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና መሰል መረጃዎችን በደንብ መመርመር እንዳለባቸው ኤምባሲው ገልጾ ነበር።

በተጨማሪም ኤምባሲው ሰዎች የሀገሪቱን ኢሚገሬሽን ፕሮግራሞች በተመለከተ ሁልጊዜ ትክክለኛ የሀገሪቱን ድረ-ገጾች እና ማህበራዊ ትስስር ገጾችን እንዲመለከቱ መክሯል።

በዚሁ መሰረት “የካናዳ መንግስት ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል ሰጠ” በሚል እየተጋራ የሚገኘው ደበዳቤ ላይ ባደረግነው ማጣራት ደብዳቤው በራካታ የጽሁፍ ግድፈቶች ያለበት፤ ግልጽ ያልሆነ እና አጠራጣሪ “ማህተሞች” ያረፉበት መሆኑን ተመልክተናል።

በተጨማሪም የካናዳ ኢሚግሬሽን፤ ስደተኞች እና ዜግነት ተቋም ድረ-ገጽን የተመለከትን ሲሆን “ለ10 ሺህ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የስራ እድል መሰጠቱን” የሚገልጽ ምንም አይነት መረጃ አለመኖሩን አረጋግጠናል፡ https://www.canada.ca/en/immigration-refugees-citizenship/news.html

የተቋሙን ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የኤክስ (ትዊተር) አካውንትም የሀገሪቱን ኢሚግሬሽን ጉዳዮች የሚመለከቱ መረጃዎችን በየጊዜው የሚያጋራ ቢሆንም ስለ “10 ሺህ የስራ እድሉ” ምንም አይነት መረጃ አለማጋራቱን አረጋግጠናል፡ https://twitter.com/CitImmCanada?s=20&t=9JlcTQWzQhB6JyFrFKtJrQ

ስለዚህ አጓጚ የስራ እድሎችን እንደ ማታለያ በማቅረብ ለሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች እንዳንጋለጥ ህጋዊ መንገዶችን እንምረጥ፣ እንዲሁም ትክክለኛነታቸው የተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን እንደ መረጃ ምንጭ እንጠቀም።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

16 Oct, 16:47


#FactCheck በደሴ ከተማ የተደረገን የተቃውሞ ሰልፍ ያሳያል ተብሎ የተጋራው ቪዲዮ የቆየ ነው

ከ6,350 በላይ ተከታዮች ያሉትና 'Abu' የሚል ስያሜ ያለው የቲክቶክ አካውንት በትናትናው ዕለት ፋኖን የሚደገፍ ሰልፍ በደሴ ከተማ ተካሄደ የሚል መልዕክት የሚነበብበት ቪድዮ ማጋራቱን አይተናል።

በተመሳሳይ 'Tilaye' የሚል ስም የሚጠቀምና ከ2,837 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት በበኩሉ ተመሳሳይ ቪዲዮ በመጠቀም ዛሬ ጠዋት መንግስትን የሚቃወም ሰልፍ በደሴ መደረጉን የሚገልጽ መረጃ ማሰራጨቱን ተመልክተናል።

በተጨማሪም ሌሎች የቲክቶክ እና የትዊተር አካውንቶች ይህው ቪዲዮ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ታዝበናል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በመጋራት ላይ የሚገኘው ቪዲዮ ከአመት ከወር በፊት የተቀረጸ መሆኑን አረጋግጧል። በወቅቱ ቪዲዮው በኢቢሲ ተጋርቶ የነበረ ሲሆን አላማውም "በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገሮችን ለማውገዝ" እንደነበር በኢቢሲ ዘገባ ተገልጾም ነበር።

ትክክለኛውን ቪዲዮ ለመመልከት ይህን ማስፈንጠሪያ ይከተሉ: https://youtu.be/AyzxjfEYtzE?si=PW-j_MbtRigfscPb

በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምንመለከታቸውን ቪዲዮዎች ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት ትክክለኛ መሆናቸውን እንመርምር።

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

14 Oct, 21:05


#ImageCheck “የሶማሊያ መንግስት ለአልሸባብ አንድ ሄሊኮፕተር ሙሉ መሳርያ ሰጠ” ከሚል መረጃ ጋር ተያይዞ የተጋራው ምስል አሳሳች ነው

የሶማልያ መንግስት በአገሪቱ ለሚንቀሳቀሰው አልሸባብ ታጣቂ ቡድን የጦር መሳሪያ ሰጠ የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርቷል።

ለምሳሌም ይህ ከ11 ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘Habtish Gurmu’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ጉዳዩን ከአንድ የጦር ሄሊኮፕተር ምስል ጋር በማያያዝ አቅርቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/somaliaalshabab%e1%88%88%e1%8a%a0%e1%88%8d%e1%88%b8%e1%89%a3%e1%89%a5/

Ethiopia Check

14 Oct, 15:32


#MondayMessage ኣብ እዋን ዞባውን ዓለምለኻውን ምዕባለታት ዝፍጠር ዝርግሐ ግጉይ ሓበሬታ ብኸመይ ንብድሆ?

ግጉይ ሓበሬታ ማለት ናይ ሓሶት ትሕዝቶ ኮይኑ ዘይተፈጸሙ ነገራት ብምምሃዝ ወይ ኣብ ሓቀኛ ፍጻመታት ዝተመርኮሱ ግን ከኣ ካብ ዓውዲ ወጻኢ ብምውሳድ (ከም ስእልታት ናይ ሓደ ሕሉፍ ፍጻመ እዋናዊ ኣምሲልካ ምቕራብ ወይ ቪድዮታት ካብቲ መበቆላዊ ትሕዝትኦም ዝተፈለየ ትርጉም ክሕዙ ብምግባር ተመስሪሖም ብዝቐርቡ ቪድዮታት) ዝቐርብ እዩ።

እዚኦም ብብዝሒ ኣብ መድረኻት ማሕበራዊ ሚዲያ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ኤክስ፣ ዩትዩብን ካልኦትን ንረኽቦም። ዝርግሐ ግጉይ ሓበሬታ ኣብ መንግስታዊን ናይ ውልቂን ሚዲያታት’ውን ክርአ ይኽእል እዩ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/mondaymessage%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/

Ethiopia Check

11 Oct, 19:50


#FactCheck ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከአማካሪነታቸው እንደተነሱ ተደርጎ ተቀናብሮ የተሰራጨው ምስል ሀሰተኛ ነው

ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች የጠ/ሚር አብይ አህመድ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከዛሬ ጥቅምት 1/2017 ጀምሮ ከስራቸው እንደረሰናበቱ የሚገልፅ ምስል ሲሰራጭ ተመልክተናል።

በጠ/ሚር አብይ በዛሬው እለት እንደተፈረመ በማስመሰል የተቀናበረው ይህ ምስል ከፍተኛ ኤዲቲንግ ተደርጎበት እና ታህሳስ 1/2016 የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ከስራ ሲሰናበቱ የተሰጣቸውን ደብዳቤ መልሶ በማቀናበር የተሰራ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል (ለንፅፅር ምስሉን ይመልከቱ)።

በተለይ የደብዳቤው ቀን እና ቁጥር የተፃፈበት ስፍራ ላይ ከፍተኛ የፊደል ቅርፅ መጣረዝ እና ከቅርፅ መውጣት የሚታይበት ሲሆን ይህም በቅንብር ሲሰራ የነበረውን ሂደት አመላካች ነው።

በተለይ ከሰሞኑ በርካታ በቅንብር የሚቀርቡ ምስሎች ሚድያዎችን፣ የመንግስት ተቋማትን እንዲሁም በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን እያሳሳቱ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለየን።

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

11 Oct, 17:07


#FactCheck ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ሆነች በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሚድያዎች፣ የግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች “ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ሆነች” የሚል መረጃ አጋርተዋል።

ይህን መረጃ ያጋሩት ሚድያዎች እና ግለሰቦች እንደ መረጃ ምንጭነት የተጠቀሙትም ኢን ኦን አፍሪካ (IOA) የተሰኘ ድረ-ገጽ ነው፡ https://www.inonafrica.com/ 

ይህ በደቡብ አፍሪካ እአአ በ 2007 ዓ/ም የተመሰረተ ተቋም በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቅ ነው።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ እየተሰራጨ የሚገኘውን መረጃ በተመለከተ የኢን ኦን አፍሪካን ድረ-ገጽን እንዲሁም የማህበራዊ ትስስር ገጾቹን የተመለከተ ሲሆን የተባለው ሪፖርት በድርጅቱ የመረጃ ቋቶች ላይ እንደሌሉ አረጋግጧል።

እየተጋራ በሚገኘው ስክሪን ቅጂው የላይኛው ክፍል ላይ የሚገኙ ጽሁፎች እና ምስሎች ከተቋሙ ትክክለኛ ድረ-ገጽ ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ሪፖርቱ ግን ትክክለኛው የ ‘IOA’ ድረ-ገጽ ላይ እንደሌለ አረጋግጠናል።

በተጨማሪም ከመረጃው ጋር እየተጋራ የሚገኘው የስክሪን ቅጂ የፊደል አቀማመጥ/ፎንት ስህተቶች የሚታዩበት መሆኑንም ተመልክተናል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መረጃውን በፌስቡክ ገጹ ካጋራ ከሰዓታት በኋላ መልሶ ማጥፋቱንም ተመልክተናል።

ከሰሞኑ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ ስክሪን ቅጂዎች በስፋት እየተሰራጩ እና በርካቶችን ለስህተት እየዳረጉ ይገኛሉ። በመሆኑም መሰል ስክሪን ቅጂዎችን አምነን መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

11 Oct, 13:36


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. "በአፍሪካ ውስጥ የተዛባ መረጃን እና የተሳሳቱ መረጃዎችን መከላከል፣ ተግዳሮቶች፣ ፈጠራዎች እና ስትራቴጂካዊ ምላሽ" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ መረጃ ማጣራት ጉባዔ በጋና አክራ ከተማ ተካሄደ። በጉባዔው ከ30 በላይ የአፍሪካ አገሮች የተወጣጡ 50 የመረጃ አጣሪ ተቋማት ተሳትፈውበታል። ኢትዮጵያ ቼክም በጉባዔው ተገኝቷል። በጉባዔው ሀሰተኛና የተዛባ መረጃዎች ሰዎች ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኙ የሚፈጥሯችው ተግዳሮቶች ለመቀነስ የህዝብ በሚዲያ አጠቃቀም ትምህርት ግንዛቤ ማሳደግ፣ የመረጃ ማጣራት ሂደቶችና አቅም ማጎልበት፣ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ለመቀነስ ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር መተባበር የተመለከቱ ውይይቶች ተደርገዋል። እንደ እአአ ከጥቅምት 9 - 10 ቀን 2024 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የተካሄደውን ጉባዔ ያሰናዳው አፍሪካ ቼክ (Africa Check)፣ ከፋክት ስፔስ ዌስት አፍሪካ እና ከዱባዋ አምፕሊፋይንግ ትሩዝ ጋር በመተባበር ነበር።

2. ቲክቶክ በርካታ የይዘት አስተናባሪ ሠራተኞቹን (Content Moderators) በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ሊተካ መሆኑን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት አስነብቧል። ሰዎችን በቴክኖሎጅ በመተካት ሂደቱም ከ500 በላይ ሠራተኞች እንደሚቀነሱ ተገልጿል። የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት አስተናባሪ ሰዎችን በሰውሰራሽ አስተውሎት የመተካት እንቅስቃሴው ሀሠተኛ መረጃዎችንና የጥላቻ ንግግሮችን ከአውድ አንጻር የመረዳት ክፍተትን ይፈጥራል የሚሉ ድምጾች በብዛት እንደሚደመጡ ይታወቃል።

3. ብራዚል በኤክስ/ትዊተር ላይ ጥላው የነበረው እግድ ማንሳቷን አለም አቀፍ ሚዲያዎች በሳምንቱ አጋማሽ ዘግበዋል። የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕግዱ ያነሳው ኤክስ የ5.1 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት መክፈሉን ተከትሎ ሲሆን በተጨማሪም ሀሠተኛ መረጃ ያሰራጫሉ የተባሉ በርካታ አካውንቶችን መዝጋቱንና የሀገሪቱ ዜጋ የሆነ ቋሚ ተወካይ መቅጠሩ ተገልጿል። ኤክስ እአአ በ2022 ብራዚል በተደረገው ምርጫ ሀሠተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የተባሉ አካውንቶችን እንዲዘጋ በሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ትዕዛዝ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ዕግድ ተጥሎበት እንደነበር ይታወቃል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-በቀድሞዋ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ላይ የቀረበን አነጋጋሪ ፅሁፍ የተመለከተ መረጃ አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2470

-የጥላቻ መልዕክት የሚያደርሰውን ጉዳት የሚያስቃኝ ጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2471

-የሞቱ ወታደሮች በቃሬዛ ወደ ሄሊኮፕተር ሲወሰዱ የሚያሳይ ቪዲዮን አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2472

-ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጨ መረጃም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2474

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

10 Oct, 14:35


#FactCheck ይህ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጨ መረጃ የተሳሳተ ነው

ትናንት ምሽት አንድ የጦር ሜዳ መገናኛ ሬዲዮን የሚያሳዩ ሁለት የስክሪን ቅጂዎች (screenshots) በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲዘዋወሩ ነበር።

አንደኛው የስክሪን ቅጂ 'Tigray Press’ የሚል ስም ካለው የፌስቡክ አካውንት እንደተወሰደ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን የጦር ሜዳ ሬዲዮው እአአ ታህሳስ 23/2020 ዓ.ም በአካውንቱ እንደተጋራ ያሳያል።

በአንጻሩ ሁለተኛው የስክሪን ቅጂ  'አስረስ ማረ ዳምጤ' የሚል ስም ባለው የፌስቡክ አካውንት ከደቂቃዎች በፊት እንደተወሰደ ያስነብባል።

እነዚህ የስክሪን ቅጅዎች በስፋት ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲጋሩ ተመልክተናል። ምስሎቹን ካጋሯቸው ሰዎች መካከልም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ ቼክ ሁለቱ ስክሪን ቅጂዎች ተወሰዱ የተባሉባቸውን የፌስቡክ ገጾች በተመለከተ ማጣራት አድርጓል።

'Tigray Press' የተባለው የፌስቡክ ገጽ እአአ ታህሳስ 23/2020 ዓ.ም የወታደራዊ ሬዲዮ የሚያሳይ ይዘት አጋርቶ እንዳልነበር ተመልክተናል። ለዚህም ‘ሁ ፖስትድ ዋት’ (Who Posted What) የተባለውን የቆዩ ፖስቶችን መፈለጊያ መገልግያ ተጠቅመናል።

በተጨማሪም ምናልባት በዛኑ ቀን የተጋራና ኤዲት የተደረገ ይዘት ይኖር ይሆን በማለት ምልከታ ያደረግን ቢሆንም ትግራይ ፕሬስ በተጠቀሰው ቀን ያጋራው ምንም ነገር አልነበረም።

በተጨማሪም የሪቨርስ ኤሜጅ ሰርች (Reverse Image Search) መተግበሪያዎችን በመጠቀም ለማሰስ የሞከርን ሲሆን ምስሉ በተጠቀሰው ወቅት የትም ቦታ ተጋርቶ ማግኘት አልቻልንም።

በተጨማሪም የወታደራዊ ሬዲዮው ምስል በትግራይ ፕሬስ ተጋርቶ ነበር ብለው የሚከራከሩ ወገኖች ወደ ይዘቱ የሚያደርስ ምንም አይነት ማስፈንጠሪያ አላያያዙም።

በአንጻሩ ሁለተኛውን የስክሪን ቅጅ ተጋራበት በተባለው አካውንት አሁንም ይታያል። ብሎም ምስሉ ትክክለኛ መሆኑን የሚያጠናክሩ ተጨማሪ ምስሎችና ቪድዮን ወደ አካውንቱ በመሄድ መመልከት ይቻላል።

ይህም የመጀመሪያውን ስክሪ ቅጅ ትክክለኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ መሆኑን ያሳያል።

በአሁኑ ጊዜ  እንዲህ ያሉ የስክሪን ቅጂዎችን ለመፈብረክ ቀላል ሲሆን ሀሠተኛ ስክሪን ቅጂዎችን ወደሚፈበርኩ መተግበሪያዎች በመሄድ ማምረት እየተለመደ መጥቷል።

ስለሆነም በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምንመለከታቸውን ስክሪን ቅጅዎች ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት ትክክለኛ መሆናቸውን እንመርምር።

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

09 Oct, 15:05


#FactCheck ይህ የሞቱ ወታደሮች በቃሬዛ ወደ ሄሊኮፕተር ሲወሰዱ የሚያሳይ ቪዲዮ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀረጸ አይደለም

ከ600 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Astuka ከሐረር’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የኤክስ/ትዊተር አካውንት የሞቱ ሰዎችን በቃሬዛ ተሸክመው ወደ ሄሊኮፕተር የሚወስዱ ወታደሮችን የሚያሳይ ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል። አካውንቱ ቪዲዮው ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀረጸ መሆኑን ለማስረዳት ሲሞክር ታዝበናል።

ቪድዮው ሙሉ እይታ እንዳይኖረው ከፊል ይዘቱ በጽሁፍ የተሸፈነ ቢሆንም ከ11,000 በላይ ጎብኝዎችን መሳቡንም አይተናል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጋራው ቪድዮ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀረጸ አለመሆኑን አረጋግጧል። ቪዲዮው የተቀረጸው በደቡባዊ ሊባኖስ ሲሆን በቃሬዛ ወደ ሄሊኮፕተር ሲወሰዱ የሚታዩትም በሂዝቦላ የተገደሉ ስምንት የእስራኤል ወታደሮች ናቸው።

ቪዲዮውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከቀናት በፊት ለዘገባ የተጠቀመበት ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል መመልከት ይቻላል: https://www.youtube.com/watch?v=ZRWocGEqwWY

ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

07 Oct, 13:24


#MondayMessage Miidhaawwan haasaa jibbiinsaa fi tarkaanfilee fudhachuu dandeenyu

Haasaan jibbiinsaa taatee haaraa ta’uu baatus babal’achuu teekinoloojiiwwan qunnamtii ammayyaan deeggaramuun babal’achaa jira.

Haasaan jibbiinsaa namoota dhuunfaa akkasumas gareelee gidduutti jibbiinsifii loogiin akka uumamu taasisa.

Guutuusaa dubbisuuf geessituu kana cuqaasaa: https://ao.ethiopiacheck.org/home/mondaymessagehaasaajibbiinsaa/

Ethiopia Check

05 Oct, 12:35


"ፅሁፉ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም"- የፕሬዝደንት ፅ/ቤት

በዛሬው እለት ከአንድ ሰአት በፊት የተረጋገጠ (verified የሆነ) የፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ላይ አንድ አነጋጋሪ ፅሁፍ ቀርቦ ነበር።

ፅሁፉ "እነ ጥላሁን ገሠሠ: ቴዲ አፍሮ: አሊ ቢራ:ማህሙድ አህመድ..ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው::"የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው:መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው"ይላል ማህሙድ "ዝምታ ነው መልሴ"ን ሲያዜም::ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" የሚል ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን በተመለከተ የፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑትን አቶ ፍቃዱ ሰቦቃን አነጋግሯል።

አቶ ፍቃዱ በሰጡት ምላሽ "የፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ኦፊሴላዊ አካውንት አለ፣ እኛ አስተያየት መስጠት የምንችለው በእሱ ዙርያ ነው። የተባለው ፅሁፍ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ ፅሁፍ አሁን ላይ በርካታ ግብረ መልሶችን እና አስተያየቶችን እያስተናገደ ሲሆን ኢትዮጵያ ቼክ ይህን መረጃ እስካጠናቀረበት ደቂቃ ድረስ አካውንቱ ላይ ይገኛል።

ፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴን በቀጥታ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

04 Oct, 17:21


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. ግዙፉ የቴክኖሎጅ ኩባንያ ሜታ በቀላሉ ቪዲዮና ድምጽ መስራት የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት መገለገያን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። ይህ ሙቪ ጄን (Movie Gen) የሚል ስያሜ የተሰጠው መገልገያ በጽሁፍ የቀረበን ሀሳብ በፍጥነት ወደ ተንቀሳቃሽ ምስል መቀየር የሚችል ሲሆን ማጀቢያ ሙዚቃና ድምጽም ማምረት ይችላል ተብሏል። መገልገያው ለሲኒማ ኢንዱስትሪ በእጅጉ እንደሚጠቅም የተነገረ ቢሆንም ለሀሠተኛ መረጃ ስርጭት የመዋል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን የተመለከቱ አስተያየቶችም በመሰጠት ላይ ናቸው።

2. በመጭው ታህሳስ በጋና የሚደረገው ምርጫ በሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ተጽኖ ስር እናዳይወድቅ ጋዜጠኞች ከፍተኛ ሀላፊነት አለባችሁ ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት አሳስበዋል። በ28ኛው የጋና ጋዜጠኞች ዓመታዊ የሽልማት መርሐግብር ላይ የተገኙት ፕሬዝደንት አኩፎ-አዶ ሀሠተኛና የተዛባ መረጃ በዴሞክራሲ ምርጫ ስርዐት ላይ የደቀነውን ስጋት አስታውሰው ጋዜጠኞች “የዕውነት ዘብ” እንዲሆኑ መክረዋል።

3. ሜታ በማህበራዊ ፕላትፎርሞቹ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቀነስ ከባንኮች ጋር በሙከራ ደረጃ የጀመረው መረጃ የመለዋወጥ አሰራር ውጤት እንዳመጣለት በሳምንቱ አጋማሽ ባስነበበው መግለጫ አስታውቋል። ካምፓኒው የሙከራ አሰራሩን ከስድስት ወራት በፊት በዩኬ ከሚገኙ ባንኮች ጋር መጀመሩን ገልጾ በዚህም በማጭበርበር ድርጊት ላይ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ከ20,000 በላይ አካውንቶችን ማስወገድ መቻሉን አብራርቷል። በሜታ ስር የሚተዳደሩት ፌስቡክና ዋትስአፕ የማጭበርበር ድርጊት በስፋት ከሚፈጸምባቸው የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ከቀዳሚዎቹ እንደሚመደቡ ጥናቶች ያሳያሉ።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-በሰው ሰራሽ አስተዉሎት የተፈበረኩ ምስሎች የፈጠሩትን ስጋት የሚዳስስ ጽሁፍ አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2462

-የግብጽ ሚዲያዎች በታላቁ የሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በማለት ያሰራጩትን መረጃ ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2463

-በአርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ ህልፈት ዙርያ የተሰራጨን ሀሠተኛ መረጃ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2464

-ተመሳስለው የሚከፈቱ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ለመለየት የሚረዱ ነጥቦችን አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2465

-ታዋቂውን ሲኒማቶግራፈርና ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማውን (ሶሚክ) ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈተ ሀሠተኛ የፌስቡክ አካውንት ያሰራጨውን የማጭበርበር ድርጊት አጋልጠናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2466
-ከቪዲዮ ጌም ተወስዶ የተጋራን ቪድዮም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2467

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

Ethiopia Check

02 Oct, 13:51


#FactCheck Viidiyoon ‘xayyaara daangaa qilleensa Itoophiyaa keessatti rukkutamee kufe agarsiisa’ jechuun qoodame kun dogongora

Fuulli Feesbuukii maqaa ‘Digital Qeerroo’ jedhu fi hordoftoota kuma 76 ol qabu viidiyoo xayyaarri “diinaa” daangaa Itoophiyaa seene rukkutamee wayita kufu agarsiisa jedhe qoodee jira.

Guutuusaa dubbisuuf geessituu kana cuqaasaa: https://ao.ethiopiacheck.org/home/fakevidiogameitoophiyaa/

Ethiopia Check

30 Sep, 17:53


#ScamAlert የታዋቂውን ሲኒማቶግራፈርና ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማውን (ሶሚክ) ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈተ ሀሠተኛ የፌስቡክ አካውንት

የታዋቂው ሲኒማቶግራፈርና ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማውን (ሶሚክ) ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈተ የፌስቡክ አካውንት መኖሩን ተመልክተናል።  ይህ ‘Sewmehon Yismaw’ የሚል ስም የሚጠቀም አካውንት ለፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ፊልም ላይ የሚሳተፉ አዳዲስ አጃቢና ረዳት ተዋንያንን እንፈልጋለን የሚል ማስታወቂያ በማስነገር ላይ መሆኑንም አስተውለናል።

“ከአሁን በፊት ምንም ስራ ላይ ያልተሳተፉ አዳዲስ ተዋንያን” ብቻ እንደሚፈልጉ የሚያስነግረው ይህ አካውንት ፍላጎት ያላቸው ተመዝጋቢዎች ፎቶ እና አጭር ቪዲዮ በቴሌግራም እንዲልኩ ይጠይቃል። በርካታ ሰዎችም እውነት እንደመሰላቸው ተረድተናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ ሰውመሆን ይስማውን ያነጋገረ ሲሆን ከላይ የተጠቀሰው የፌስቡክ አካውንት የእርሱ አለመሆኑንና የተጋራው መረጃም ሀሠተኛ መሆኑን አስታውቋል። ይህ ሀሠተኛ አካውንት በሚያጋራቸው የተሳሳቱ መረጃዎች መቸገሩን የገለጸው ሰውመሆን ምንም አይነት የተዋናይ ምልመላ አለመጥራታቸውንና በቴሌግራም የሚላኩ ፎቶዎችና ቪዲዮዎችም ወደእነርሱ የሚደርሱ አለመሆናቸውን ተናግሯል።

የሰውመሆን ይስማው ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: https://www.facebook.com/somickk

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ  አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራሳችንን እንጠብቅ!

@EthiopiaCheck