የካቲት 7/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ አመት የዕቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት የሚካሄደው ግምገማ ዋና ዓላማ የባለስልጣኑ 15 የትኩረት አቅጣጫዎች ከውጤት እና ከተገኙ በጎ ተፅህኖዎች አንፃር በጥልቀት ተገምግሟል።
የጥራት ስራን ባህል ማድረግ እንደሚገባ እንዲሁም ለማቹሪቲ ሌቭል ስሪ የተሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ዋና ዳይሬክተሯ ያሳሰቡ ሲሆን በተለይ ስራዎች በዕቅድ ተመስርቶ እየተገመገመ መሰራት ዋነኛ ትኩረታችን መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
የቅኝትና የቁጥጥር ስራችን የተቀናጀ ሊሆን ይገባል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ በሕገወጥ የወባ መድኃኒቶች ቁጥጥር ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች መልካም መሆኑን ገልፀው የትምባሆ ስራ ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ረገድ መጠናከር እንዳለበትና ስራዎችን አረጋግጦ ከመመዘን አንፃር እያንዳንዱ የስራ ኃላፊ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ በፋይዛ አባቢያ የቀረበ ሲሆን ህብረተሰቡን የቁጥጥር ባለቤት ለማድረግ ፣ቅልጥፍናና ውጤታማነትን ለማሻሻል፣ የምግብ ደህንነት ቁጥጥርን ለማጠናከር፣ የመድኃኒት ደህንነት፣ጥራት፣ፈዋሽነት እና አግባባዊ አጠቃቀም ቁጥጥርን ለማሻሻል በተቀመጡ 15 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት በዋና ዋና መለኪያዎች ሲመዘኑ አበረታች ውጤት ተገኝቷል፡፡
በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያና የመልካም አስተዳደር አፈፃጸም ላይ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡