ETHIO CHELSEA 🇪🇹 @eth_chelsea Channel on Telegram

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

@eth_chelsea


ስል CHELSEA በየደቂቃው ትኩስ ትኩስ መረጃዎች የሚያገኙበት !

➠| ስለ ቼልሲ ትኩስ መረጃዎች
➠| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
➠| የዝውውር ዜናዎች

ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅት የታላቁ ክለብ ቼልሲ ቻናል ነዉ።

Admin -: @swefer_n
@BEN_21_s

🇪🇹 ETHIO CHELSEA (Amharic)

ኢትዮ ቼልሲ ከተናገር የሚሰራ አገር ሲሆን ስለ ሼልሲ ትኩስ መረጃዎችን በተከተለው ታሳሚ ሰዓቱ ቼልሲ ቻናል ይጠናቀቅ አለብን። ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ፣ የዝውውር ዜናዎች እና እናይትስዞም፣ ኢትዮ፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ፣ አድማስ፣ የሚንፀባረቅት የታላቁ ክለብ ቼልሲ ቻናል ነዉ። ለበኩሉን ተጨናነል።

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

07 Jan, 22:07


📌 10,000 ተከታዮች 💙💙🥳                                                                                           
  

ውድ የዜና ቼልሲ ቤተሰቦች ከተከፈተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ 10ሺ በላይ ተከታዮች ማፍራት ችለናል ከልብ እናመሰግናለን 🙏💙

አሁንም አብሮነታችሁ አይለየን ቤተሰብ ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን 💙💙💙

📍HERE WE GO SOON TO 50k



SHARE~@ET_ZENA_CHELSEA
SHARE~
@ET_ZENA_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

07 Jan, 20:23


🟥 አርሰናል ከ ኒውካስል ዩናይትድ ⬛️

የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ በ ነፃ በስልኮዎ ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ(JOIN) የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉ

https://t.me/addlist/17z-JmLyi2U4ZGY0

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

07 Jan, 04:57


እንኳን አደረሳቹ ለመላው ክርስትና ተከታዬች በሙሉ

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 19:14


የዝውውር መስኮቱ ቀስ በቀስ መጋጋል ጀምሯል!

ብዙ ማጠብቋቸው ፊርማዎች እና ሚለቁ ተጫዋቾች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል!

ምን አልባት ቻናላችንን በስህተት ወይም በሌላ ምክንያት mute ያደረጋችሁ የኢትዮ ቼልሲ ቤተሰቦች unmute በማድረግ ትኩስ ትኩስ መረጃዎች በቀላሉ እንዲደርስዎ ያድርጉ።

🔹 ኢትዮ-ቼልሲ

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 18:44


የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን አዲስ ማሊያ ይፋ ተደርጓል። ከ10 ስንት ትሰጡታላቹ እስኪ

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 18:23


ቼልሲዎች በክሪስታል ፓላስ በውሰት ላይ ባለው ትሬቮህ ቻሎባህ ላይ የማስታወሻ አማራጭ አላቸው።

ሰማያዊዎቹ በቤኖይት ባዲያሺሌ እና በዌስሊ ፎፋና ላይ ጉዳት አጋጥሟቸዋል እና ጨዋታውን ቅዳሜ እለት ከንስሮቹ ጋር የጀመሩት የ18 አመቱ ጆሽ አቼምፖንግ በመሀል ተከላካይነት ነው።

ወጣቱ ወደ ኤንዞ ማሬስካ የመጀመሪያ ቡድን ቡድን ካደገ በኋላ ቶሲን አዳራቢዮዮ እና አክሴል ዲሳሲ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ሲቀመጡ የአቼምፖንግ የመጀመርያው የፕሪሚየር ሊግ ጅማሮ ነበር።

የቼልሲ ውሳኔ በቻሎባህ ሊታሰብበት የሚችለውን ውሳኔ በዌስሊ ፎፋና ጉዳት ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

ማሬስካ የ24 አመቱ የመሀል ተከላካይ ባለፈው ሳምንት ለቀሪው የውድድር ዘመን ከሜዳ እንዲርቅ ወስኖታል ነገርግን ለተጫዋቾች ቅርበት ያላቸው ምንጮች ቶሎ ሊመለስ እንደሚችል ተናግረዋል።

የፓላሱ ስራ አስኪያጅ ኦሊቨር ግላስነር ቻሎባህ በሴልኸርስት ፓርክ 1-1 መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ወላጅ ክለቡ ሊመለስ እንደሚችል ተጠይቀዋል።

"በቤንች ላይ ዲሳሲ እና ቶሲን እንዳሉ አይቻለሁ" አለ ግላስነር።

"ከሁለት ጋር ብትጫወት [ተጨማሪ] እንደምትፈልግ አላውቅም። አንሴልሚኖ ተመልሶ እንደሚመጣ እያነበብኩ ነበር ስለዚህም አምስት [የመሃል ተከላካዮች] አላቸው።

"ስምንት እንደሚያስፈልጋቸው አላውቅም። ምን እያሰቡ እንደሆነ አላውቅም። ትሬቮህ ለእኛ በጣም ጥሩ እየሰራልን ነው እና ከእሱ ጋር እቅድ እያወጣን ነው።"

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 18:01


🔵🇦🇷 የመጀመሪያ ቀን በኮብሃም ዛሬ ለአርጀንቲና የመሀል ተከላካይ አሮን አንሴልሚኖ በቼልሲ ከቦካ ጁኒየር የውሰት ጥሪ በኋላ።አንሰልሚኖ ከወኪሉ ዲያጎ ሜሪኖ ጋር በልምምድ ሜዳ ይገኛል።

Fabrizio Romano

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 17:36


ቻናላችን ዜና ቼልሲ ዜናን በጥራት ወደ እናንተ ለማድረስ የአድሚን እጥረት አጋጥሞታል እናም ቻናላችን አዳዲስ 2 አድሚኖችን መጨመር ይፈልጋል የአድሚንነት መስፈርት ~ ኦንላይን ብዙ ሰዐት መገኘት የሚችል እና ዜና በጥራትና በፍጥነት ማድረስ የሚችል መሆን አለበት እንዲሁም ለቻናሉ እድገት የሚለቀቁ ማስታወቂያዎችን delet ማረግ የሚችሉ ልምድ ያለው አድሚን inbox 👇
@BIRUKISM

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 16:03


ሰማያዊዎቹ 💙💙

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 13:49


ቼልሲዎች ማርክ ጉሂን ከክሪስታል ፓላስ ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸው ተዘግቧል ።

[ Fabrizio Romano ]

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 13:02


🔜 ቀጣይ ጨዋታ | Next Match

የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ 3ኛ ዙር መርሃ ግብር

     ቼልሲ ከ ሞርካምብ

🗓 ጥር - 3 - ቅዳሜ

አመሻሽ 12:00

🏟️ ስታምፎርድ ብሪጅ

መልካም ዕድል ለታላቁ ክለባችን ቼልሲ! 💙

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Jan, 12:25


ዌስሊ ፎፋና

"የተባለው ነገር እውነት አይደለም ከቀሪው የውድድር ዘመን ውጪ አይደለውም ለምን ማሬስካ ይህን እንደተናገረ አላውቅም. ከ4-6 ሳምንታት ውስጥ እመለሳለሁ. "

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

26 Dec, 06:42


የጨዋታ ቀን | Match Day

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ተኛ ሳምንት ተጠባቂ የምዕራብ ለንደን ደርቢ ጨዋታ

   🔵  ቼልሲ ከ ፉልሃም ⚪️

🗓 ዛሬ አመሻሽ 12:00

🏟️ ስታምፎርድ ብሪጅ

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

26 Dec, 06:21


ቼልሲዎች በሳምንት £200k የሚከፈለውን ተጨዋች ለመልቀቅ እየታገሉ ነው

ለ28 አመቱ የቼልሲ የመስመር ተከላካይ ምንም አይነት ጥያቄዎች እንዳልቀረቡ ከተገለጸ በኋላ ለቤን ቺልዌል የጥር የዝውውር መስኮት ተስፋ አስቆራጭ ሊሆን ይችላል እስካሁን በ2024/25 የውድድር ዘመን ኤንዞ ማሬስካ ለቼልሲው የመስመር ተከላካይ 45 ደቂቃ ብቻ የሰጠው ሲሆን እሱም በካራባኦ ካፕ ጨዋታ ላይ ነበር

በሳምንት £200k ተከፋዩ ቺልዌል የጣሊያኑ አሰልጣኝ እቅድ አካል እንዳልሆነ ግልፅ ነው እናም ሰማያዊዎቹ በዚህ የውድድር አመት ምን ያህል ጥሩ ነገር እያሳዩ እንደሆነ ለተመለከተ ማሬስካ በቺልዌል ላይ ባረገው ነገር ለመከራከር ከባድ ነው

እስካሁን ቤን ቺልዌልን የሚፈልግ ክለብ የለም አሰልጣኙ በቅርቡ በሰጡት አስተያየት ቺልዌል እና ሌላ የሰማያዊዎቹ ተጨዋች በጥር ሊለቁ እንደሚችሉ አምነዋል የቀድሞውን የሌስተር ሰው ማንም አይፈልገውም ሲል ዘ ሰን ዘግቧል

ሌላው የሰማያዊዎቹ ችግር ሊሆን የሚችለው የ28 አመቱ ተጫዋች ከክለቡ ጋር እስከ ሰኔ 2027 የሚያቆየው ኮንትራት ያለው መሆኑ ነው ኮንትራቱን ካቋረጡበት ብዙ ዋጋ ይከፍሉበታል ፈላጊ ክለብ ካጡም እስከ ሰኔ በወር እስከ £800k እየከፈሉት ይቆያሉ ለዚህም ነው የምዕራብ ለንደኑ ቡድን ተጨዋቹን በአስቸኳይ ለመልቀቅ እየሰሩ ያሉት

ምናልባት ተጫዋቹ ራሱ አማራጮቹን እየፈለገ ነው ተብሎ ይገመታል ቺልዌል ከስታምፎርድ ብሪጅ ለመውጣት ከፈለገ ወደ ትልቅ ክለብ መሄድ እንዳለበት ያስባል በአሁኑ ጊዜ ምንም እንኳን ውሳኔ ለማድረግ ባይፈልግም የግዴታ በጥር ከብሪጅ መልቀቅ እንዳለበት ያምናል.

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Dec, 12:39


ገብተህ ማትወጣበት ቻናል ላሳይህ ናና ከስር ያለውን ንካው/ንኪው

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

06 Dec, 12:37


የየትኛው ክለብ  ደጋፊ ናችሁ  የክለባችሁን ቻናል በመምረጥ ተቀላቀሉ ❗️❗️

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

04 Dec, 21:41


በ14ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋት ወደ ሀምፕሻየር አቅንቶ ከሜዳው ውጭ ሳውዝሀምፕትንን የገጠመው ቼልሲ 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል::

የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ዲሳሲ,ንኩንኩ, ማዱዌኬ ,ኮል ፓልመር እና ጃደን ሳንቾ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ቼልሲ በደረጃ ሰንጠረዡ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል::

ቼልሲ በቀጣይ ጨዋታ እሁድ በፕሪሚየር ሊጉ በለንደን ደርቢ ከሜዳው ውጭ ከቶተንሀም ጋር ጨዋታውን ያከናውናል::

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

03 Dec, 18:21


በዚህ የውድድር አመት በፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ኳስ የማዳን ስኬት ያላቸው ግብ ጠባቂዎች ሮበርት ሳንቼዝ በቀዳሚነት ተቀምጧል።

81% - ሮበርት ሳንቼዝ 💙
77% - ኒክ ፖፕ
76% - ኬልሄር
75% - አንድሬ ኦናና
75% - ማትዝ ሴልስ

@ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

03 Dec, 04:44


ኮል ፓልመር የ2024 የ FSA ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

01 Dec, 15:42


ጣፋጭ ድል ወሳኝ ሶስት ነጥብ

@ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

01 Dec, 15:36


🇬🇧 #የእንግሊዝ_ፕሪሚየር_ሊግ  13ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች    

FT :- ቼልሲ 3-0 አስቶንቪላ


የቼልሲ ጎል በፓልመር ፣ ጃክሰን እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ ግቦች አስቶንቪላን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ኮል ፓልመር በዚህ የውድድር አመት ባደረጋቸው አስራ ሶስት ጨዋታዎች ስምንት ግብ አስቆጥሮ ስድስት አመቻችቶ አቀብሏል።

የቼልሲ የአጥቂ መሰመር ተጫዋቾች በዚህ ሲዝን በፕሪሚየር ሊጉ

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 ኮል ፓልመር : 8 goals, 6 assists
🇦🇷 ኢንዞ ፈርናንዴዝ : 2 goals, 6 assists
🇸🇳 ኒኮ ጃክሰን : 8 goals, 3 assists

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3️⃣ ቼልሲ :- 25 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

እሮብ ሳውዝሀምፕተን ከ ቼልሲ

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

01 Dec, 10:12


◊...ዛሬ ከሞይሰስ ካይሴዶ ጋር ማን ይጣመር ይሁን..!

#Enzo_Fernandez_ቡድኑ በተለያዩ አቅጣጫ የጎሎ ዕድሎችን ይፈጥር ዘንድ የእሱ ሚና ቀላል አይደለም!!...እሱ ሜዳ ውስጥ ካለ ከፊት ያሉ አጥቂዎች ኳስ በምቾት ይጫወታሉ!

#Romio_Lavia--እሱ ሜዳ ውስጥ ካለ ቡድን በመከላከሉ በጣም ስል ነው!..የተቃራኒ Play-Makers)የምንላቸው ተጨዋቾች እንደፈለጉ መፈንጫት አይችሉም!+ቡድኑ በፈጠራ ላይ የተወሰነ ደከም ቢልም ሚዛናዊነት ላይ👌

ዛሬስ ማን በመጀመሪያ አሰላለፍ ይጀምር ይሁን🥶ብቻ አጓጊ ነው🙏

✍️በመጨረሻም ማንም ይሰለፍ ማንም.. ክለባችን ማሸነፍ ነው ዋናው ነገር 💙

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

30 Nov, 11:57


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

30 Nov, 11:55


👌ለዩንቨርሲቲ ና  ለ ሃይስኩል  ተማሪዎች   ብቻ የተከፈተ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው ቻናሎች ❤️❤️

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

29 Nov, 15:18


በዚህ ሲዝን በሊጉ 25+ ኳስ ወደ ጎል ሞክረው የሞከሩትን ኳስ ወደ ጎልነት የመቀየር ምርጥ ፐርሰንት ያላቸው ተጫዋቾች :

- #ኒኮላስ_ጃክሰን 25%

- ሞሀመድ ሳላህ 25%

- ማቲያስ ኩንሀ 20%

@ETH_CHELSEA @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

29 Nov, 14:56


🗣️ኤንዞ ማሬስካ በአስቶን ቪላ:

"ቪላ ከፍተኛ አሰልጣኝ አለው፣ ድንቅ እየሰሩ ነው። ኤመሪን ከሲቪያ አውቀዋለሁ እና ምን ያህል ሀይለኛ እንደሆኑ አውቃለሁ። በጣም ጥሩ በሆኑ ተጫዋቾች ድንቅ ነገሮችን እያሳዩ ነው። ከባድ ጨዋታ ነው።"
@ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

29 Nov, 14:55


🗣️ኢንዞ ማሬስካ በ'ርዕስ ውድድር' ላይ

"ቡድኑ ሲሻሻል ማየት ጥሩ ነው፣ ያ አስፈላጊ ነው፤ ጥሩ ነው ጥሩ ስሜት።"

"በተመሳሳይ ጊዜ ተጨባጭ መሆን አለቦት እና በእኛ እና በሌሎቹ መካከል ያለውን ልዩነት በአሁኑ ጊዜ ማየት ይችላሉ. ይህ ማለት ጨዋታዎችን አናሸንፍም እና እስከመጨረሻው አንወዳደርም ማለት አይደለም, ነገር ግን ዋናው ትኩረቱ ነው. ከጨዋታ በኋላ የምናሻሽልበት ስሜት ለመሆን።

"ሲቲ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ቢሸነፍም አሁንም ሁለተኛ ነው:: አርሰናል እዚያው ነው [በ22 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ያለው] ሊቨርፑልም ድንቅ እየሰራ ነው።ለኔ እነሱ የሚቀድሙን ነጥብ እና የደረጃ ሰንጠረዥ አይደለም። ሂደቱ ነው"

"አርሰናል አምስት አመታትን አሳልፏል፣ ማን ሲቲ በጋራ ከስምንት አመታት በላይ ነው፣ ሊቨርፑል ትንሽ ለየት ያለ ነው ነገርግን ካለፉት ጊዜያት ብዙ ለውጦችን አላደረጉም። ምክንያቱ ይህ ነው። ጉዳዩ በነጥብ ወይም በሠንጠረዥ ልዩነት ላይ አይደለም፣ እሱ ብቻ ነው። አብሮ ጊዜ."

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

29 Nov, 14:53


🗣️ኢንዞ ማሬስካ ተጠየቀ ከባድ ፉክክር ተጫዋቾችን መጫወት እንዲራቡ ያደርጋል?

"በትክክል."

"ይህ ከዒላማዎች አንዱ ነው, እነሱ በትክክለኛው መንገድ እርስ በርስ መወዳደር ይችላሉ. በሌላ ቀን, ሮሚዮ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ነበር ነገር ግን ይህ ማለት በሚቀጥለው ጨዋታ ላይ አግዳሚ ወንበር ላይ ይሆናል ማለት አይደለም. ለ ተመሳሳይ ነው. ውጭ የነበሩት ማሎ ጉስቶ ወይም ፔድሮ ኔቶ ጥሩው ነገር ደቂቃዎች ስንሰጣቸው ዕድሉን ለማግኘት መዘጋጀታቸው ነው።

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

29 Nov, 14:52


🗣️ኤንዞ ማሬስካ:

ብዙ ማሻሻል እንችላለን።በሌላኛው ቀን ከሌስተር ጋር በእግር ኳሱ ውስጥ በአንድ መንገድ ያለው ነገር በሰከንድ ሊለወጥ እንደሚችል መማር እንችላለን።

"የመጀመሪያው አጋማሽ ጎል አስቆጥረን ጎል ተከልክሎ ሶስት እና አራት ተጨማሪ እድሎችን አግኝተናል።በዚህ ነጥብ ላይ ክሊኒካዊ ሆነን 0-2 ወይም 0-3 ማድረግ አለብን ጨዋታው መጠናቀቁን ግን አረጋግጠናል። የሆነ ነገር እና ጨዋታው በህይወት ስለነበረ ከዚያ ጨዋታ በኋላ እንኳን ነገሮችን ማሻሻል እንችላለን እና እንሞክራለን።

"ተጫዋቾችን መተው ሲኖርብዎት ይህ ለሁሉም አስተዳዳሪዎች መጥፎው ክፍል ነው ፣ ግን ጥሩው ነገር በፕሪምየር ሊግ ውስጥ እያንዳንዱን ጨዋታ ተመሳሳይ XI አለመሆኑን በግልፅ ማየት ይችላሉ ። በመጨረሻው ጨዋታ ከሌስተር ጋር ቤኖይት ባዲያሺሌ አስደናቂ ነገር አድርጓል። በፕሪምየር ሊግ ብዙ አልተጫወተም ነበር ፣ ኤንዞ ድንቅ ነበር ፣ እና ጆአዎ ፊሊክስ በጣም ጥሩ ነበር ፣ ይህ እኛ ሁሉንም ስለምንፈልግ መስራት እንደምንፈልግ ያሳያል ።

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

29 Nov, 04:00


🚨 አዲስ፡ ጄሚ ካራገር ቼልሲን በአዲሱ ምርጥ 4 ትንበያዎች ውስጥ አስቀምጧል።

🔗 ስካይ ስፖርት

@ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

28 Nov, 19:56


የ ጨዋታዉ ስታተስ

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

28 Nov, 19:48


የ ተጨዋቾች ሬቲንግ

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

28 Nov, 19:45


የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ 4ኛ ዙር የምድብ ጨዋታ

              ተጠናቀቀ

      ሄደንሀም 0-2 ቼልሲ
                     ንኩንኩ 51'⚽️
ሙድሪክ 86'⚽️
ሰማያዊዎቹ ድል አድርገዋል !

በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ አራተኛ ዙር ጨዋታ ቼልሲ ከሄደንሄም ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሰማያዊዎቹን የድል ግቦች ክርስቶፈር ንኩንኩ እና ማይካሎ ሙድሪክ ከመረብ አሳርፈዋል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቶፈር ንኩንኩ  በውድድር አመቱ ባደረጋቸው አራት የኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ክርስቶፈር ንኩንኩ የዛሬው ግቡም በውድድሩ ሰባተኛ ጎሉ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመሩት ቼልሲዎች በውድድሩ ያደረጓቸውን አራት ጨዋታዎች በድል መወጣት ችለዋል።

ሰማያዊዎቹ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ 1⃣2⃣ ነጥቦችን በመሰብሰብ ደረጃ ሰንጠረዡን በበላይነት እየመሩ ይገኛሉ።

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

- አስታና ከ ቼልሲ

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

28 Nov, 17:41


ሚሻ ዝግጁ ነው
እስኪ አንዴ ለሚሻ 🔥

share @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

28 Nov, 14:17


🔥ሬሲ ጀምስ 2024 ቡሀላ ነው የሚመለሰው🔥
====================================
ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ቴሌግራፍ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ሬሲ ጀምስ በ2024 ቡሀላ ነው የሚመለስው በተደጋጋሚ የጡንቻ መሸማዘዘ (ሀምስትሪግ) እየተቸገረ ያለው ጀምስ ቀዶ ጥገና ቢያረግም በድጋሜ ተጎድቷል ይህም በዚህ የካላንደር አመት አይመለስም ሬሲ ጀምስ ወደ ሜዳ የሚመለሰው በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2025 ይሆናል ማለት ነው!!!

ቼልሲ ባወጣው መግለጫ ሁሌም ከጀምስ ጋር እንደሚሆን ተናግረዋል እንደሚደግፉት ጭምር አመላክተዋል!!!

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

28 Nov, 13:28


🚨🆕️ የሪሴ ጀምስ ጉዳት አዲስ የጅማት ጡንቻ ነው።

🔗 ቤን ጃኮብስ - talkSPORT

@ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

27 Nov, 14:19


DD በዚህ ሳምንት ከስድስት አመት በፊት ነበር ጫማውን የሰቀለው። ለቼልሲ ዋንጫ ፍፃሜ ኤሊት ነበር 🏆🔵🇨🇮

⚽️ 2005 የሊግ ዋንጫ ፍፃሜ
⚽️⚽️ 2005 የኮሚኒቲ ሺልድ
⚽️⚽️ 2007 የሊግ ዋንጫ ፍፃሜ
⚽️ 2007 የኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ
⚽️ 2008 የሊግ ዋንጫ ፍፃሜ
⚽️ 2009 የኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ
⚽️ 2010 ኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ
⚽️ የ2012 ኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ
⚽️ የ2012 ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ

14 የፍፃሜ ጨዋታዎች 11 ጎሎች 10 ዋንጫዎች 👑
DD የፍፃሜው ንጉስ💪🏿

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

26 Nov, 10:41


የተረጋገጠ፡ ስቱዋርት አትዌል የቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን ከአስቶን ቪላ ጋር ይመራል።

VAR: ሚካኤል ሳሊስበሪ


@ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

26 Nov, 09:56


ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ከወደ ፖርቹጋል እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት ቼልሲ ሲዊዲናዊ አጥቂ ዩኬሬሽን ለማስፈረም የሚደረገውን ጥረት እየመሩ ሲሆን በጥር የዝውውር መስኮት ቼልሲ 90 ሚሊዮን በመክፈል ፍቃደኛ መሆናቸው ተነግሯል ጥር ላይ አስፈርመው በውሰት በመስጠት ክረምት ወደ ቼልሲ ለማምጣት በዝግጅት ላይ ናቸው!!!

ጥር ላይ አስፈርመው በውሰት መልሰው ለስፖርቲግ ሊዝበን ይሰጡታል በአመቱ መጨረሻ ወደ ብሪጅ ይመጣል ተብሏል!!!

🥇 የፖርቹጋል ተነባቢ ጋዜጣ ሪከርድ ዘግቧል!!!

SHARE'' @ETH_CHELSEA

ETHIO CHELSEA 🇪🇹

26 Nov, 07:26


🗣️ ጄሚ ኦሃራ፡

❝ኒኮላስ ጃክሰን በእሳት ላይ ነው፡፡ሰዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን እያረጋገጠ ነው።በየሳምንቱ ጎሎችን ማስቆጠር ይችላል።❞

❝በእውነት ወደ ፕሮፌሽናል አጥቂነት እየተቀየረ ነው፡፡❞

🔗ሲሞን ጆንሰን ፣ ዲ አትሌቲክስ

❝ድሮግባ ለቼልሲ ባደረጋቸው የመጀመሪያ 57 ጨዋታዎች 23 ጎሎችን ማስቆጠር መቻሉ ብዙዎችን ሊያስገርም ይችላል።❞

❝ጃክሰን በመጀመሪያዎቹ 57 ጨዋታዎች ያስቆጠራቸው ግቦች 24 ናቸው።❞

SHARE'' @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 18:00


ምስጋና ማይበቃለት ጀግና🥹💪

💙TS6💙

Share
@ETH_CHELSEA
@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 13:59


በአድሱ የፈረንጆቹ አመት ነባሮቹ ባነሮች ተነስተው እነዚህ በሁለቱ ልተኩ ነው።

@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 13:40


በአንጻራዊነት ካሉት 20 ክለቦች ውስጥ ለሚቀጥሉት 10 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ቀላል ተጋጣሚዎችን በፐርሰንት(87) በማግኘት ቼልሲ 20ኛ ላይ መቀመጥ ችሏል💙💙🤗

@ETH_CHELSEA
@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 13:36


ቼልሲ ሳንቼዝ ላይ ትልቅ እምነት አላቸው እንድሁም የ22 አመቱ ፍልፕ ዮርገንሰንና የ19 አመቱ ማይክ ፔንደርስ ላይ ወደ ፊት ትልቅ ተስፋ ያደርጋሉ።

ቼልሲ ግብ ጠባቂ ያስፈርማል የምሉ መረጃዎች ከእውነት የራቁ ናቸው።

Share
@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 12:35


ክሌባችን ገና ከአሁኑ ከበርካታ ተጫዋቾች ጋር ስሙ እየተነሳ ይገኛል አብዛኛዎቹ ደግሞ የአጥቅ መስመርና የመሀል (አማካይ) ተጫዋቾች ናቸው።

እንደነ የግል አመለካከት ከሆነ ግን አጥቂና መሀል ሜዳ ላይ ብዙም ክፍተት አይታየኝም እንደውም አሁን ካሉት የፕርመሊግ ቡድኖች እንደ ቼልሲ አጥቂና አማካይ ያለው ቡድን የለም ለማለት የምያስደፍሩ ተጫዋቾች አሉን።

ነገር ግን አንድ ደህና የመሀል ተከላካይ ብናስፈርም የተከላካይ መስመሩ እጅግ ይጠናከራል ይሄ የግል ሀሳብ ነው።

እናንተ ምን ትላላችሁ 👇

Share @ETH_CHELSEA

✍️ @PETER_JADON2

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 10:08


🚨 የተረጋገጠ ቅዳሜ ከሌስተር ጋር የሚናደርገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የሚመሩት አንዲ ማድሊ መሆኑ ተረጋግጧል።

VAR: Paul Terney

Share @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 08:19


🚨 NEXT MATCH

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ 12ኛ ሳምንት

ሌስተር vs ቼልሲ

📆 ቅዳሜ ህዳር 14

⏱️ 9:30

🏟️ ኪንግ ፓወር

ድል ለቼልሲ 💙 💙 💙


Share

@ETH_CHELSEA
@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

19 Nov, 04:54


ከነዚህ ጨዋታዎች ስንቱን በድል ምንወጣው ይመስላቿል?


@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

18 Nov, 18:24


ስለ ቅዳሜው ጨዋታ አንድ አሳዛኝ መረጃ ልጠቁማችሁ እንደምታወቀው ላቪያ ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም በጉዳት ምክንያት ለቅዳሜው ጨዋታ ላይደርስ ይችላል።እናም ነበር ግን ሁላችንም እያሰብን ያለነው ነገር አለ እሱም ላቪያ ባይኖርም ኤንዞና ካይሴዶ ይገባሉ የምል።

ነገር ግን ሁላችንም ያላሰብነውና ያልገመትነው ነገር ልፈጠር ይችላል።

(Mail sport) የተሰኘ ገፅ እንዳስታወቀው ከሆነ ኤንዞና ካይሴዶ ከሀገራት ጨዋታ መልስ በ48 ሰዓታት ውስጥ ወደ London (Cobham) ምደርሱበት (ምበሩበት) ዕድል ጠባብ ነው መምጣት እንኳን ብችሉ ጨዋታውና በረራው አንድ ላይ ተደራርቦባቸው ድካም ስለምኖር ላይሰለፉ ይችላሉ።
ይህንንም ተከትሎ ቼልሲ ቅድምያ ለተጫዋቾቹ ጠንነትና ደህንነት ቅድምያ ስለ ምሰጥ ጨዋታው ላይ የመሳተ ዕድላቸው ጠባብ ነው ።

እናንተስ ምን ታስባላችሁ ኤንዞና ካይሴዶ ለቅዳሜው ጨዋታ ይደርሳሉ ብላችሁ ታስባላችሁ?

@ETH_CHELSEA

✍️ @PETER_JADON2

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

18 Nov, 15:57


ቶሲን በግሉ አሰልጣኝ ቀጥሮ በትርፍ ሰዓትም ልምምድ እየሰራ ይገኛል።🔥💪


@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

18 Nov, 15:20


🚨 ሳንቾ ቅዳሜ ከሌስተር ጋር በሚናደርገው ጨዋታ የምመለስ ይሆናል🤩🥰💥💫💪

ይሄ ቅመም የሆነ ልጅ 💙

@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

18 Nov, 15:18


ክሌባችን በሜዳው ስጫወት ማየት የናፈቀው የለም?🥹

@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

18 Nov, 10:12


ለምቀጥሉት 10 ሳምንታት የሀገራት ጨዋታ አይኖርም።🤝

@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

18 Nov, 09:36


የክሌባችን ግብ ጠባቂ የሆነው ሮበርቶ ሳንቼዝ 27ኛ አመቱ ይዟል።🎉🎉

HBD ሮብ🤩💫

@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

18 Nov, 04:56


🚨የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደገለፁት ከሆነ ላቪያ የሀምስትሪንግ ጉዳት እንደደረሰበት ነው ያስታወቁት።💔

@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

17 Nov, 19:08


ንኩንኩ ለፈረንሳይ ቋም ሆኖ ይጀምራል 🔥🤩

መልካም ዕድል ንኩንኩ💙

Share
@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

05 Nov, 20:43


☄️🌐ከለሊቱ 6 ሰአት ተለቀቀ

የመጀመሪያው አስፈሪ ፊልም በኢትዮጵያ

ለአመታት ሲጠበቀው የነበረው ፊልም በስተመጨረሻም ተለቋል 🔥🔥🔥

ለመመልከት👇

https://t.me/+DC0ueZUTqzdhMGM0

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

05 Nov, 20:31


🔶ጥያቄ ቁጥር 1

ብሩህ አዕምሮ ያላችሁ ፈጠን ብላችሁ መልሷት
1=5
2=10
3=15
4=20
5= ?

ቀድሞ ለመለሱ 5 ሰዎች የ ካርድ ሽልማት አለ Request to Join ያድርጉ

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

05 Nov, 20:26


🎧🎵የማንን ሙዚቃ ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇

👤 Mikaya Behailu

👤 Minyeshu Kifle

👤 Muluken Melesse

👤 Neway Debebe

👤 Nati Haile

👤 Nhatty Man

👤 Sami Dan

👤 Sayat Demissie

👤 Seleshe Demissie

👤 Shewandagne Hailu

👤 Tamrat Desta

👤 Teddy Afro

👤Aster Awoke

👤Abnet Agonafr

👤Geremew Asefa

🌐 All Ethiopian Music🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

03 Nov, 04:36


ቀጣይ ጨዋታ | Next Match

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር

    🔴 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ 🔵

🗓 ጥቅምት - 24 - እሁድ

ምሽት 01:30

🏟️ ኦልድትራፎርድ

መልካም ዕድል ለታላቁ ክለባችን ቼልሲ! 💙

@ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

03 Nov, 04:28


🗣 የአርሰናሉ ሌጀንድ ማርቲን ኪውን :-

"ኒኮላስ ጃክሰን በፕሪምየር ሊጉ በጣም ከሚፈሩ አጥቂዎች መካከል አንዱ እየሆነ ነው።"

SHARE -: @ETH_CHELSEA
SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

02 Nov, 03:53


ካሊዱ ኩሊባሊ ስለ ኒኮላስ ጃክሰን

"ስለባላንዶር ማሰብ አለበት ምናልባትም ሊያሳካው ይችል ይሆናል እናም ይህንን በአዕምሮው ውስጥ ማሰብ አለበት።"

SHARE -: @ETH_CHELSEA
SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

02 Nov, 03:22


አድሪያን ክላርክ :

" ካይሴዶ ከፕሪምየር ሊጉ ምርጥ የተከላካይ አማካዮች አንዱ በመሆን የጠፋውን ስሙን መልሷል። "

SHARE -: @ETH_CHELSEA
SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

27 Oct, 16:58


ቼልሲ አሸንፏል !

በዘጠነኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ኒውካስልን 2ለ1 አሸንፏል ።

የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ኒኮላስ ጃክሰን እና ኮል ፓልመር ሲያስቆጥሩ ለኒውካስል አሌክሳንደር አይሳክ ከመረብ አሳርፏል።

ኮል ፓልመር በውድድር ዘመኑ በሊጉ ባደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች በአስራ ሁለት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

4️⃣ ቼልሲ :- 17 ነጥብ
1️⃣2️⃣ ኒውካስል :- 12 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

እሁድ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

22 Oct, 07:43


የጥቁሮች መድመቂያ ።፤የጥቁሮች መፍለቂያ ።፤የጥቁሮች ክብር የሚሰጠው ታላቁ ክለብ ቸልሲ ።።

ከብሪጅ ሰማይ ሰማይ በጥቁር የቆዳ ቀለም ተሸፍኖ ይታያል ሊጉ ላይ ከሚገኙ ምርጥ የተከላካይ አማካኞች መካከል አንዱ ነው ብለህ ብታወራ የሚጠራጠር የለም እንደሌሎች ተጭዋቾች ልታይ ልታይ የማይል ነገር ሜዳ ላይ ሁሌ ጠንክሮ የሚሰራ ታታሪ አማካኝ ነው ሜዳ ላይ ብዙ ሳሮችን የሚረግጥ ፤የአማካኝ ክፍሉን የሚቆጣጠር፤የቡድኑን ሚዛን የሚጠብቅ ፤የተከላካዮች ሽፋን የሚሰጥ ፤አማካኞች ወደ ፊት ሂደው የማጥቃቱን ሰራ እንዲሰሩ የሚያደርግ ፣ለክለቡ የሚዋደቅ ፤የሚታትር ፤የሚለፋ አሰገራሚ አማካኝ ነው ።ደቡብ አሜሪካዊው የቀድሞው የአሜክሱ የአሁኑ የብሪጁ የምሀል ሜዳ ተዋናይ ሞሰስ #ካሴዶ ኢኳዶራዊው 6ቁጥር አማካኝ ።።።

ኢኳዶራዊው የተከላካይ አማካኝ የሊቨርፑልን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው የጥቁሮች መድመቂያ የሆነውን እና እነ ዲደር ድሮግባ ፤ጆኖቪ ሚኬል ፤ራሜረስ ፤#ማይክል ኢሴን የደመቁበትን የጥቁሮች ክብር የሚሰጠውን የምእራብ ለንደኑን ክለብ ቸልሲን መቀላቀሉ አይዘነጋም ።።።።።።ታታሪው አማካኝ በቸልሲ ቤት ጥሩ ብቃቱን እያሳ ይገኛል ።።።።።።

ጉልበት አቅም ያለው ኳስ የሚችል፤የተረጋጋ ፤አሰተዋይ ፤ለውሳኔ የማይቸኩል ፤ ለካርድ ሰለቫ የማይህን ድንቅ አማካኝ ነው ።ለአዲሱ የኢንዞ ማውሬስካ የቡድን ግንባታ ተመረጭ እና ቀዳሚ ተጭዋች ነው ።።።።።

ጉዳት ካላጋጠመው በዚህ የውድድር አመት የተሻለውን ቸልሲን እና ካሴዶን ትመለከቱታላችሁ ቸልሲ ከኒጎሎ ካንቴ በኋላ ያገኙት ሌላኛው ንጎሎ ካንቴ 👏👏👏👏👏ነጭ ቢሆን እና እንግሊዛዊ ቢሆን ከዚህ የበለ ይወራለት ነበር

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

21 Oct, 19:17


ሌላኛው የፔፕ ጋርዲዎላው ቅጥቅጥ፤ሌላኛው የፔፕ ጋርዲዎላው ተማሪ ጣሊያናዊው አለቃ ኢንዞ ማውሬስካ ።።

የቀድሞው የውሃ ሰማያዎቹ ረዳት አሰልጣኝ ፤የቀድሞው የቀበሮዎቹ የአሁኑ አዲሱ የሰማያዎቹ አለቃ ኢንዞ ማውሬስካ ጣሊያናዊው የመልካም እግር ኳስ አቀንቃኙ አሰልጣኝ በኪንግ ፓዎር አሰገራሚ ቲም ሰርቷል ሌስተር ሲቲን በአጭር ግዜ አፍርሶ በመርሳት ጥሩ እግር ኳስ በመጫወት ከሻምፒዎን ሽፑ ወደ ታላቁ የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ማሳደግ ችሏል ።።።።

አዲሱ የብሪጁ እንግዳ ኢንዞ ማውሬሰካ በብሪጅ አየር ንብረት ገና አልተላመደም ፤ለሊጉም አዲስ ነው ።።አንድን አሰልጣኝ በትትንሽ የጭዋታ መርሃ ግብሮች ማድነቅ እና መተቸት አይቻልም ነገር ግን የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል እንደሚባለው ሁሉ ማውሬስካም እጀግ ትልቅ ተሰፋ የሚጣልበት አሰልጣኝ እንደሆነ አሳይቷል በአጭር ግዜ ቸልሲን ወደ ጥሩ መንገድ እየወሰደው ይገኛል ኳሰ መስርቶ የሚጫወት ፤ተሎተሎ ወደ ጎል የሚደርስ ፤ተጭኖ የሚጫወት ፤ሜዳላይ ጥሩ እግር ኳስ የሚጫወት ጥሩ ቡድን እየሰራ ይገኛል።።።

አሰልጣኙ ሜዳላይ በልምምድ ወቅት እንደተጭዋቾች ይሮጣል፤ይናገራል ፤ይጮኸል በተለይ ቸልሲ ትናንት ምሽት ወደ አንፊልድ አምርቶ በሊቨርፑል 2_1"ቢሸነፍም በጭዋታው ያሳየው አሰገራሚ ፉክክር እና በጭሆታማው የአንፊልድ ሰማይ ሰር ሙሉ የጭዋታ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል በአጠቃላይ ጣሊያናዊው አለቃ ሜዳላይ እጅግ ውብ የሆነ እግር ኳስ የሚጫወት ትልቅ ተሰፋ የሚጣልበት ድንቅ ቲም እየሰራ ይገኛል ።ይህ ገና ኤክስፐርመንት እንጂ ገና ተሰርቶ አላለቀም።።

ቸልሲ ወደ ፊት ወደ ገናናነቱ ይመለሳል ኢንዞ ጥሩ አሰልጣኝ ነው

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

21 Oct, 17:28


🚨🤯 የአመታት ሪኮርድ ተሰበረ!

የቼልሲ ንብረት የሆነው ድንቁ ታዳጊ ዊሊያን ኤስቴቫዮ በ2024 ብራሴሌሬዮ 17 ጎሎች ላይ ግብ በማስቆጠርና አሲስት በማድረግ የኔይማር ጁኒየርን ታሪካዊ ሪከርድ መስበር ችሏል።

ኔይማር ጁኒየር በ2009 ብራሲሌሬዮ 16 ጎሎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ሪከርድ አስመዝግቦ ነበር።

ኤስቴቫዮ ከ17 አመት በታች ሆነው ብዙ ግብ ላይ የተሳተፈው ብቸኛው ታዳጊ ተጫዋች መሆን ችሏል💫

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

15 Oct, 11:24


የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ( ፒኤፍኤ ) የፕርሚየር ሊጉ የወርሀ መስከረም የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር የፕርሚየር ሊጉ የወርሀ መስከረም የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመስከረም ወር ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ አይዘነጋም።

ኮል ፓልመር በወሩ ባደረጋቸው አራት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

14 Oct, 17:59


ሬስ ጄምስ ካጋጠመው ጉዳት በማገገም ወደ ቡድን ልምምድ መመለሱ ተገልጿል። ሬስ ጄምስ በጉዳት ምክንያት ባለፉት ስድስት ወራት ለክለቡ ግልጋሎት እንዳልሰጠ ይታወሳል።

የ 24ዓመቱ ተጨዋች ሬስ ጄምስ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራት ችሏል።

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

14 Oct, 17:57


መጪዎቹ ሳምንታት ለቼልሲ ፈታኝ ይሆኑ ይሆን?

በዚህ ሳምንት መጨረሻ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሀገራት ጨዋታ መልስ ተጠባቂ መርሀግብሮችን ይዞ ይመለሳል።

ሊጉ ተቋርጦ ሲመለስ ለአራት ሳምንታት በተከታታይ ይደረግና በድጋሚ ለሀገራት ጨዋታ ይቋረጣል።

በእነዚህ አራት ሳምንታት በኢንዞ ማሬስካ የሚመሩት ቼልሲዎች በተከታታይ ከሊጉ ታላላቅ ክለቦች ጋር ይፋለማሉ።

ከሊቨርፑል በአንፊልድሮድ ፣ ከኒውካስትል በስታንፎርድብሪጅ ፣ ከማንችስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ እና ከአርሰናል በስታንፎርድ ብሪጅ ይጫወታሉ።

ከነዚህም የሊግ ጨዋታዎች በተጨማሪ በካራባኦ ካፕ ከኒውካስትል በሴንጀምስ ፓርክ እና በኮንፍረንስ ሊግ ከፓናቲያኮስ እና ከኤፍሲ ኖአህ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በሊጉ በአሁን ወቅት በ14 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ቼልሲዎች በኢንዞ ማሬስካ እየተመሩ በተከታታይ 7 ጨዋታዎች ሽንፈት ምን እንደሆነ አያውቁም።

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

11 Oct, 10:37


ኮል ፓልመር በመስከረም ወር ያለው ስታትስቲክስ

5 ጎል
አንድ አሲስት

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

05 Oct, 17:28


ኤንዞ ማሬስካ የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ተመርጧል 💙🔥

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

05 Oct, 08:03


Jamie o'hara on "whether saka is world class"
"ሳካ የአለማችን ትልቅ ተጫዋች አይደለም, ጥሩ ተጫዋች ነው ግን palmer and lamin are worldclass player "💙💙💙

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

04 Oct, 04:23


ባለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች በሁሉም መድረክ ተጫውተን አምስቱንም አሸንፈን 17 ጎሎች አግብተን 4 ጎሎች ብቻ ናቸው የተቆጠሩብን አምስቱንም አሸንፈናል!!!

ፔድሮ ኔቶ እና ጃዶን ሳንቾ ለቼልሲ 6  ግብ + አሲስቶችን ማድረግ ችለዋል።

ክሪስቶፈር ንኩንኩ በቼልሲ ቤት ያለው ቁጥራዊ መረጃዎች፡-

960 -  ደቂቃዎች ተጫወተ
10  - ግቦች አስቆጠረ

በየ96 ደቂቃው ግብ ያስቆጥራል !

👏👏 ለኢንዞ ማሬስካ👏👏

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

04 Oct, 04:14


🇪🇺 የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ 1ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ !

               ተጠናቀቀ :- ቼልሲ 4-2 ጌንት

🏟️ ስታምፎርድ ብሪጅ

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

03 Oct, 10:28


የጨዋታ ቀን

ቼልሲ ምሽት 4:00 ጀምሮ የቤልጀሙን ጀንት በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል

በትናትናው ጋዜጣዊ መግለጫ ማሬስካ ከሪስ ጀምስ ውጭ ሁሉም ተጫዋቾች ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆነ ገልፃል ነገር ግን ብል ፓልመር ሮሚዬ ላቪያና ሊቬ ኮልዊል እንዲሁም ቤን ችልዌል ከዬሮፓ ኮንፈርስ ሊግ ምድብ ጨዋታ ውጭ ናቸው።

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

02 Oct, 05:53


OFFICIAL

ኒውካስል ዩናይትድ ትላንት ምሽት ዌልብደንን ማሸነፉኖ ተከትሎ በካራባዎ ካፕ አራተኛው ዙር ቼልሲን ያስተናግዳል !!

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

01 Oct, 14:54


#ቼልሲን_ማሬስካ_አሻሽሎታል!!

➫ግብ ጠባቂ በቀላሉ የሚሰራቸውን ስተቶች ማሻሻል አለበት!
➫ተከላካዮች ከመጀመሪያው ጨዋታ ጀምሮ በየጨዋታው እየተሻሻሉ ይገኛሉ..ይሁንና በስድስት ጨዋታ ላይ 7 ግብ ተቆጥሮባቸዋል አሁንም ልሻሻሉ ይገባል።
➫የኤንዞ ና ካይሴዶ ጥምረት ወደ ውጤታማነት መጥቷል።
➫የፊት አጥቂዎቻችን እጅግ አስፈሪ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ!!

በቅርቡ የትኛውም ክለብ መግጠም ማይፈልገውን ቼልሲ የምንመለከተው ይመስለኛል!!

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

30 Sep, 10:36


"ፓልመር ነገሮችን ቀላል ያደርግልሀል" ጄደን ሳንቾ

እንግሊዛዊው ተጫዋች የቡድን አጋሩ በቼልሲ ቤት ካለ ሁሉም ነገር ለቡድኑ ቀላል እና የሚቻል መሆኑን አስታውቋል።

ፓልመር ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰማያዊዊዮቹ በሜዳቸው ስታምፎርድ ብሪጅ ብራይተን ሆቭ አልቢየንን አስተናግደው አራት ለሁለት በረቱበት ግጥሚያ አራቱንም የድል ጎሎች በመጀመሪያው አጋማሽ በማስቆጠር አዲስ ታሪክ መጻፍ መቻሉ ይታወሳል።

"እንደ ፓልመር አይነት ተጫዋች በቡድን ውስጥ ሲኖር ምንም ነገር ማድረግ ትችላለህ።ኮልን ለረጅም ጊዜ አውቀዋለው።

በማንቺስተር ሲቲ ቤት የነበረን አብሮነት ጊዜ ጀምሮ ማለት ነው።በወቅቱ ስመለከተው ትልቅ ተጫዋች እንደሚሆን እምነቱ ነበረኝ።

አሁን ላይ እሱን እያስመለከተ ነው" ሲል ሳንቾ ለቡድን አጋሩ አድናቆቱን ገልጿል።

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

27 Sep, 09:00


ማን ያሸነፈ ይመስላችኋል?

Palmer❤️
Sancho👌

SHARE -: @ETH_CHELSEA
SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

25 Sep, 03:52


ጨዋታው ተጠናቀቀ
                
                   FULL_TIME

         ቼልሲ 5 - 0 ቦሮው
      #ንኩንኩ3
      #ኔቶ
#በራስላይ

SHARE -: @ETH_CHELSEA
SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

23 Sep, 19:54


ኢንዞ ማሬስካ በሰጡት መግለጫ ነገ በካራባኦ ዋንጫ በሜዳችን በምናረገው ጨዋታ ላይ ማሎ ጉስቶ ከጉዳት አገግሞ ለጨዋታ ዝግጁ ሁኗል ሮሚዩ ላቪያ ለነገ አይደርስም ለቅዳሜ ለብራይተን ጨዋታ ግን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል!!!

በነገው ጨዋታ ላይ ቤንችልዌል,ባዲያሽሊ እና ሌሎች መሰለፍ ያልቻሉ ተጨዋቾች በነገው ጨዋታ የጨዋታ እድል ያገኛሉ ሲሉ ኢንዞ ማሬስካ ተናግረዋል!!

ነገ በስታንፎርድ ብሪጅ ማታ 3:45 ላይ ባሮ ከሚባል የታችኛው ሊግ የሚጫወት ክለብ ጋር እንጫወታለን !!!

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

23 Sep, 13:50


ከርእስ ዉጪ: ከዚህ ይጠብቀን😂😂😂

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

22 Sep, 13:35


🔥ሳንቾ 🤝 ቼልሲ🔥

በዚህ ሲዝን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አንድም የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ከአንድ በላይ አሲስት ማድረግ የቻለ ተጫዋች የለም!

ከዩናይትድ ተገፍቶ ወደ ቼልሲ ያመራው ጄዳን ሳንቾ ግን በፕሪምየር ሊጉ በቼልሲ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ሁለት አሲስትቶችን ማድረግ ችሏል።

ሳንቾ በፕሪምየር ሊጉ በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች አሲስት ማድረግ የቻለው በቼልሲ ማሊያ ብቻ ነው። 👏

ቼልሲም በትናንቱ የዌስትሀም የ 3ለ0 ድል ጨምሮ በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ጉዞውን አሳምሯል።

SHARE -: @ETH_CHELSEA

🇪🇹 ETHIO CHELSEA

10 Jun, 16:47


Channel created

17,725

subscribers

18

photos

1

videos