Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS @epsaethiopia2012 Channel on Telegram

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

@epsaethiopia2012


Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service , EPSS, is legal entity established under the law of Federal Democratic Republic of Ethiopia Government to overcome the problems and assure uninterrupted supply of pharmaceuticals to the public.

Promotional Article for Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS (English)

Welcome to the Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS! Are you looking for a reliable and reputable source for all your pharmaceutical needs in Ethiopia? Look no further than EPSA, the Ethiopian Pharmaceuticals Supply Agency. Established as a legal entity under the law of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Government, EPSA is dedicated to overcoming the challenges in the pharmaceutical supply chain and ensuring the uninterrupted supply of essential medications to the public. Who is EPSA? EPSA is a leading provider of pharmaceutical products in Ethiopia, working closely with local and international suppliers to bring a wide range of high-quality medications to the market. With a team of experienced professionals and a strong commitment to excellence, EPSA is your trusted partner in healthcare. What is EPSA? EPSA is more than just a pharmaceutical supplier - it is a lifeline for those in need of essential medications. By ensuring a steady and reliable supply of pharmaceuticals, EPSA plays a crucial role in improving public health and well-being in Ethiopia. From prescription drugs to over-the-counter medications, EPSA offers a comprehensive range of products to meet the diverse needs of customers across the country. Whether you are a healthcare provider looking for a dependable source of medications or an individual in need of essential drugs, EPSA is here to serve you. With a focus on quality, affordability, and accessibility, EPSA strives to make pharmaceuticals more accessible to all Ethiopians, regardless of their location or economic status. Join us on Telegram at @epsaethiopia2012 to stay updated on the latest news, promotions, and product offerings from EPSA. Don't miss out on this opportunity to connect with a trusted pharmaceutical supplier and improve the health and well-being of yourself and your loved ones. Together, we can work towards a healthier and happier Ethiopia with EPSA by our side. Visit us today and experience the difference that quality pharmaceuticals can make in your life.

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

15 Feb, 19:37


የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ አገልግሎቱን ጎበኙ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር በአጋርነት ከሚሰሩ በርካታ አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች መካከል በዋነኝነት ግሎባል ፈንድ ይጠቀሳል ፤ ግሎባል ፈንድ የጤናውን ዘርፍ በመደገፍ ቁልፍ አጋር ሲሆን የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ በአገልግሎቱ የካቲት 8/2017 ዓ.ም ጎብኝተዋል ፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ አገልግሎቱ ያለውን ተቋማዊ መዋቅር ፣ የህክምና ግብዓቶች የክምችት መጠን ፣ የፋይናንስ አሰራር ፣ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ፣ የግሎባል ፈንድ መዋዕለ ንዋይ በአገልግሎቱ ምን እንደሚመስል ፣ ከአጋር አካላት ጋር ያለው የግንኙነት ሁኔታ ፣ የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ የትግበራ ሂደት ፣ የቀጥታ ስርጭት አቅርቦት መሻሻል ፣ የፀደቀው አዋጅ የሚያመጣቸውን ለውጦች ፣ ወረቀት አልባ የቢሮ አገልግሎት የመስጠት ሂደት በዝርዝር አቅርበው ከጎብኚዎች የተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡

በኢትዮጵያ በተለይም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ያደረጉት ጉብኝት ውጤታማ መሆኑን የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ ተናግረው ፤ እ.ኤ.አ በ2019 አገልግሎቱን መጎብኘታቸውን አስታውሰው ከፍተኛ ለውጥ መመልከታቸውን በተለይም የቆጠራ ትክክለኝነት ፣ የተቀናጀ የመረጃ አሰራር ስርዓት የትግበራ ሂደት(ERP Implementation) ፣ የቀጥታ ስርጭት አቅርቦት መሻሻል ፣ የፀደቀው አዋጅ የሚያመጣቸውን ለውጦች ፣ አጠቃላይ የአገልግሎቱ የአፈፃፀም መሻሻሉን ጠቅሰዋል ፡፡

ከኢትዮጵያ ብሎም ከጤና ሚኒስቴር ጋር የቆየና ጠንካራ አጋርነት እንዳላቸው ፒተር ሳንድስ አስታውሰው በቀጣይ በርካታ ስራዎችን መስራት እንቀጥላለን ብለዋል ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ በበኩላቸው፤ ግሎባል ፈንድ ባደረገው የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ የመድሃኒት አገልግሎትን የሚያዘምን ዲጅታል ስርዓት መዘርጋቱን አንስተዋል።

ማገልገል ክብር ነው !
ማኅሌት አበራ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

12 Feb, 19:26


አገልግሎቱ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ለሚሰሩ ባለሞያዎች ስልጠና ለመስጠት ከEmpower School of Health ጋር ስምምነት ተፈራረመ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እ.ኤ.አ በ2030 በአፍሪካ ፈጣን ምላሽ ሰጪ እና ቀልጣፋ የመድኃኒቶች አቅርቦት ሰንሰለት ያለው ድርጅት ለመሆን የያዘዉን ራዕይ ለማሳካት ከሚያስፈልጉት በርካታ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሰለጠነ የሰው ሀይል መገንባት መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ አስታውሰው ፤ ይህንንም ለማድረግ Empower School of Health በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱ መልካም ጅማሮ መሆኑን ተናግረዋል ::

ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር ለበርካታ አመታት መስራታቸውን የEmpower School of Health መስራችና አስተዳዳሪ ፕሮፌሰር ፖል ላልቫኒ ተናግረው ፤ በአሁኑ ወቅት ከፀደቀው አዋጅ እና እየተገበረ ከሚገኘው የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት አንፃር በዋና መስሪያ ቤትና በቅርንጫፍ ለሚገኙ እስከ 400 ለሚደርሱ ባለሙያዎች የተለያዩ አይነት ስልጠናዎችን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ጭምር እንደሚሰጡ ገልፀዋል ::

ስልጠናዎቹ ከሚሰጥባችው ኮርሶች መካከል የመሪነት ፣ የትንበያ እቅድ ፣ የአቅርቦት ሰንሰለት ፣ የቆጠራ ፣ የስርጭት አስተዳደርና መሰል ኮርሶችን በአለም አቀፍ ደረጃ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የሚሰሩ ተቋማት በሚጠይቁት አግባብ መሰረት ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ፕሮፌሰር ፖል አስረድተዋል ፡፡

አገልግሎቱ የያዘውን የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ለማሳካት ከባለሙያዎች አንፃር አሁን ላይ ያለው ክፍተት ምንድነው የሚለውን በማየት ስልጠና ሊያገኙ የሚገባቸውን በመለየት ስልጠናው እንደሚሰጥ የEmpower School of Health በኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ሩት ይድረስልኝ ተናግረው ፤ ስልጠናዉ በበይነ መረብ ፣ በስራ ላይ መጋዘን ውስጥ ፣ በመማሪያ ክፍል ውስጥ አንደሚሰጥ እና በቀጣይ የራሱ የሆነ የማስተማሪያ አስተዳደር ስርዓት እንደሚኖረው አስረድተዋል ፡፡

ማገልገል ክብር ነው !
ማኅሌት አበራ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

07 Feb, 18:39


https://youtu.be/TBERNip7BNQ?si=v893Oz2n95cYjh-J

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

06 Feb, 18:22


አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ቀጥታ ስርጭት አድማሱን 75% ማድረሱን አስታወቀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ደቡብ ምዕራብ ፣ ኦሮሚያ ሸዋ ዞን ፣ ሸገር ከተማ አስተዳደር ፣ ጉራጌ ዞኖች እና አዲስ አበባ ዙሪያ ዉስጥ ለሚገኙ 330 ጤና ተቋማት የህክምና ግብአቶችን ያቀርባል፡፡

ቅርንጫፉ የጤና ፕሮግራም እና የክትባት ግብአቶችን 188 ጤና ተቋማት ላይ ብቻ በቀጥታ ይደርስ የነበረዉን በተያዘዉ በጀት አመት በ6ወራት ዉስጥ አገልግሎቱ በሰፊዉ ትኩረት አድርጎ በመስራት እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር እና FIT(Frieght in Time) ድጋፍ 250 ተቋማትን በቀጥታ በማድረስ ከ57% ወደ 75% ማሳደግ እንደተቻለ የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ሞገስ ተናግረዉ ፤ በቀጣይ ግማሽ አመት ተጨማሪ 30 ጤና ተቋማትን ለመድረስ እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

አያይዘዉ በ6ወር ዉስጥ ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም የህክምና ግብአቶችን ለጤና ተቋማት መሰራጨቱን ገልፀዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነው
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

05 Feb, 12:32


https://youtu.be/ksLxDYWlaHo?si=qgqMoQhcRzEwjOVC

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

05 Feb, 05:43


አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ የኢ. አር.ፒ 2ተኛ የትግበራ ምዕራፍ (Tranch 2) አስጀመረ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ የኢ.አር.ፒ አሰራር ሁለተኛውን ምዕራፍ (Tranch 2) የፕሮጀክት ቢሮ ባለሙያዎች እና የዲሎይት አማካሪዎች በተገኙበት ጥር 26/2017 በይፋ አስጀምሯል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ 7 ሞጅሎች ወደ ትግበራ ገብተው ሲሰሩበት መቆየታቸውን የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ሞገስ አስታውሰው ፤ በሁለተኛው ምዕራፍ የአሰራር ስርአታችንን በእጅጉ የሚያሻሽሉ EWM ፣ HR እና CRM ውስጥ የሚገኙ ሞጅሎች በተሳካ ሁኔታ ወደ ትግበራ መግባቱን ተናግረዋል።

አክለውም ለትግበራው መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለቅርንጫፉ እና ፕሮጀክት ቢሮ ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።

#ማገልገል ክብር ነው
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

30 Jan, 18:57


የአገልግሎቱ ነጌሌ ቦረና ቅርንጫፍ የቀጥታ ስርጭት አድማሱን ለማስፋት ከFrieght in Time (FIT) ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ነጌሌ ቦረና ቅርንጫፍ የክትባት እና የጤና ፕሮግራም መድኃኒቶችን በተቀናጀ መልኩ በቀጥታ ጤና ተቋማት ላይ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ከFrieght in Time (FIT) ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ (MoU) የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸው፣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ተወካይ አቶ ጌትነት አርጋው ፣ የ FIT Managing Director ወ/ሮ ዮዲት አድማሱ ፣ የክልል ጤና ቢሮ ተወካዮች ፣የዞን ጤና መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የወረዳ ጤ/ፅ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ነገሌ ቅርንጫፍ ስለሚኖረው የቀጥታ ስርጭት (Last Mile Delivery) ኢኒሼቲቭ አተገባበር ሁኔታ ፤ ባለድርሻ አካላት ስለሚኖራቸው ኃላፊነት እና የትግበራ እቅድ በቅርጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንደሰን ማዘንጊያ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት የተደርገ ሲሆን ፤ ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የቀጥታ ስርጭት ኢኒሼቲቭ በሀዋሳ ቅርንጫፍ እና በሌሎች የአገልግሎቱ ቅርንጫፎች ተግባራዊ በማድረግ ክትባቶች እና የጤና ፕሮግራም መድኃኒቶች በቀጥታ ጤና ተቋማት ከማድረስ ባሻገር በወቅቱ ጤና ተቋማት እንዲደርስ መቻሉንና አቅርቦቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሻሻል ያደረገ በመሆኑ፤ ይህንኑ ተሞክሮ በአገልግሎቱ ነጌሌ ቦረና ቅርንጫፍ በመተግበር የአቅርቦት ሠንሠለቱ ላይ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት እንደሚችል እምነት አለን ሲሉ የአገልግሎቱ ሀዋሳ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ክላስትር አስተባባሪ አቶ ዘመን ለገሰ ተናግረዋል፡፡

የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ እንዳሉት የቀጥታ ስርጭት (Last Mile Delivery) ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላችውን ኃላፊነት እንዲወጡና አስፈላጊውን የስራ ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡

#ማገልገል ክብር ነዉ!

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

28 Jan, 12:50


የአገልግሎቱ መሰረተ ልማት ዝርጋታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዳስደነቃቸው የአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና የልማት አጋር ድርጅቶች ጥምረት ግሎባል ሄልዝ ኢኒሽዬቲቭ ተወካዮ አገልግሎቱን ጥር 19 2017ዓ.ም የጎበኙ ሲሆን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተቋሙ ያለበትን አሁናዊ ሁናቴ አስረድተዋል፡፡

የክትባት መድኃኒቶችን እስከተጠቃሚዉ ለማድረስ (Last mile Delivery) እየተሰራ መሆኑን ፤ የአገልግሎት ጥራትን ማስጠበቅ ፤ ዘላቂ የሆነ የህክምና ግብአቶች ተደራሽነትን ማስፈን እንዲሁም ተአማኒነትን ለማረጋገጥ የተጀመረዉን ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ (Digitalization) እዉን ማድረግ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ አገልግሎቱን ለጎበኙ አለም አቀፍ ለጋሾች ገልፀዋል፡፡

የጋቪ ተወካይ የሆኑት ታባኒ ማፎሳ እንዳሉት አገልግሎቱ እየዘረጋ ያለው መሰረተ ልማት እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሊደነቅ የሚገባው ጠቁመው የክትባት መድሃኒቶች በተሻለ መልኩ ተደራሽ እንዲሆኑ በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት ተቋሙ እ.ኤ.አ በ2030 በአፍሪካ ፈጣን ምላሽ ሰጪ እና ቀልጣፋ የመድሃኒቶች አቅርቦት ሰንሰለት ያለው ድርጅት መሆን የሚል ራዕይን ሰንቆ እየተጋ ሲሆን፤ የመረጃ ግልፀኝነት በመፍጠር ዘመናዊ አሰራርን በመጠቀም የመድኃኒት ተደራሽነትን ማሻሻል እንደተቻለ ፤ በዘንድሮ የግማሽ አመት የግብዓት ቆጠራ ወደ 3 ቀን መምጣቱን ፤ የመድኃኒት ፈንድ አዋጅ ቁጥር 1354/17 መፅደቁ አቅም እንደሚሆን እንዲሁም የግብአት ስርጭቱን የሚያሳልጥ የባርኮዲንግ አሰራር እንደሚጀመር ጠቁመዋል።

ለጋሽ ተቋማትም ቀልጣፋ የግብአት አቅርቦት ሰንሰለት እንዲረጋገጥ አገልግሎቱ ሊገነባ ያሰበዉን ዘመናዊ መጋዘን (mega warehouse) እና የBarcoding አሰራር ዉጤታማ እንዲሆን ድጋፍ እንዲያረጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የለጋሽ ተቋማቱ ከፍተኛ ሀላፊዎችና ተወካዬችም አገልግሎቱ ያለበትን ቁመና አድንቀዉ ፤ ግጭቶች ባሉባቸዉ የሀገሪቱ ክፍሎች የህክምና ግብአቶችን በሀላፊነት መንፈስ ተደራሽ መሆናቸዉ ፤ አዋጁ መፅደቁና የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአት መጀመሩ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን መሆኑን ተናግረዋል።

#ማገልገል ክብር ነዉ
ዘጋቢ አማኑኤል ወርቃየሁ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

24 Jan, 19:24


አገልግሎቱ የግማሽ አመት የህክምና ግብአቶች ቆጠራ አከናወነ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወራት የህክምና ግብአቶች ቆጠራ በ14 ማዕከላዊ መጋዘኖች (Central Warehouse) በ5 ቀናት ዉስጥ በጥራት አከናዉኖ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በቅድመ ቆጠራ ጊዜ ሲስተሙን ዝግጁ የማድረግ ስራ ፣ ግብአቶችን በየፈርጁ ማስተካከል ፣ የመብራት እና ፎርክ ሊፍት የማደራጀት ስራ ተከናዉኖ ወደ ቆጠራ መግባታቸዉን የክምችት እና ስርጭት አማካሪ አቶ ጋሻዉ በለጠ ተናግረዋል፡፡

ቆጠራዉ በሲስተም እና በመጋዘን ላይ ያለዉን ክምችት ተመሳሳይ መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም በአይነት እና በዋጋ ምን ያህል ክምችት እንዳለን ለማወቅ አስችሎናል ሲሉ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡

በፊት የነበረዉ የቆጠራ ስርአት ረጅም ጊዜ ይወስድ እንደነበር የህክምና መሳሪያዎች አያያዝና ስርጭት ባለሙያ አቶ የቻለ ሽፈራው አስታዉሰዉ ፤ አሁን ላይ ዘመናዊ የአሰራር ስርአት በመከተል በጥቂት ቀናት ዉስጥ በመጨረስ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት እንደቻሉ እና የቆጠራ ትክክለኝነት (Inventory Accuracy) 99% መድረሱን ተናግረዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

23 Jan, 18:22


አገልግሎቱ የመረጃ ሽግግር (Data Migration) ቅድመ ዝግጅት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አገልግሎቱ ህብረተሰቡን በተሻለ መልኩ ለማገልገልና ፈጣንና ዘመናዊ አሰራርን ለማምጣት የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአት መዘርጋቱን ተከትሎ የተቋሙ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሞያዎች ከዘርጋዉ ክላዉድ ጋር በመቀናጀት የመረጃ ሽግግሩን ስራ ሲሰሩ ክፍተቶች እንዳይኖሩ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናዉ ካዉዛ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የኢትዮ ቴሌኮም ሰርቨር ላይ ያሉትን መረጃዎቹን ወደ ራሱ ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል (Data Center) የመረጃ ሽግግር ቅድመ ዝግጅት ስራ ጥር 14/2017ዓ.ም መጀመሩን የአገልግሎቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አወል ገልፀዋል።

ዳይሬክተሩ እንዳሉት አገልግሎቱ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአት (ERP) መጀመሩን አስመልክቶ ነባሩን የመረጃ ማዕከል ማዘመን አስፈላጊ በመሆኑና በሽግግር ሂደቱ ለኢትዮ ቴሌኮም ሰርቨር ኪራይ የሚወጣዉን ወጪ ለማዳን ከ22-24/5/17ዓ.ም ባሉት ቀናት የመረጃ ሽግግር (Data Migration) ስራ የሚያከናዉን ሲሆን ፤ የሙከራ (Testing) ስራዎች በማድረግ አገልግሎቱ በራሱ ሰርቨር ስራ እንደሚያከናዉን አስረድተዉ ለጥቂት ቀናት የERP ሲስተም ስለሚቋረጥ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በተቋሙ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የበለፀጉ ሶፍትዌሮችን ፣ የደህንነት ካሜራ ምስሎችን እንዲሁም ተቋማዊ መረጃዎችን ዉስን በሆነ መልኩ በቀድሞው ሰርቨር ላይ ይቀመጥ እንደነበረ ያስታወሱት የተቋሙ የኔትዎርክ እና ደህንነት መሰረተ ልማት ቡድን መሪ አቶ ማንያዝሃል አዲሴ አሁን ግን በጥቂት ቀናት ዉስጥ በሚጠናቀቀው የመረጃ ሽግግር ስራ የመረጃ ትንታኔን መስጠት የሚያስችልና ሁሉንም ቅርንጫፎች ተደራሽ የሚያደርግ የመረጃ ግልፀኝነትን የሚፈጥር ደህንነቱ የተረጋገጠ ሰርቨር እየተገነባ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ዘጋቢ አማኑኤል ወርቃየሁ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

22 Jan, 11:49


https://youtu.be/ikZ0gk76pwI

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

22 Jan, 08:27


https://youtu.be/dy0gfmGR7WQ?si=XUhFgUt6INhdBY7_

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

22 Jan, 06:58


ለጭንቅላት ፣ ነርቭ እና ህብረ ሰረሰር ህክምና የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Reach Another Foundation የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለጭንቅላት ፣ ነርቭ እና ህብረ ሰረሰር ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች ህክምና የሚዉሉ ከ137 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ 4 ኒዉሮሰርጂካል ማይክሮስኮፕ መሳሪያዎች የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ እና የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በተገኙበት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

መሣሪያዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ለ4 የማስተማሪያ ሆስፒታሎች እንደሚሰራጩ ወ/ሮ ፍሬህይወት አንስተዉ ፤ ይህም በዘርፉ የሚሰጠዉ የአገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት እንዲሁም የህክምና ስልጠናዉን በእጅጉ እንደሚያሻሽል ይጠበቃል ብለዋል፡፡

አገልግሎቱ ትላልቅ የህክምና መሣሪያዎችን በታማኝነት ለታለመለት አላማ እንዲዉል የማድረስ ስራዉን እያከናወነ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ገልጸዉ ፤ የተደረገዉ ድጋፍ የማህበረሰቡን የጤና ችግር በብዙ የሚቀርፍ በመሆኑ ለለጋሽ ድርጅቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የReach Another Foundation ዳይሬክተር ዶ/ር ያዕቆብ አህመድ እንዳሉት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማስፋት በቀጣይ ተጨማሪ 5 መሣሪያዎችን ድጋፍ እንደሚያደርጉ እና በ2 አመታት ዉስጥ በመንግስት ሆስፒታሎች የተደራጀ የህክምና አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

10 Jan, 18:47


አገልግሎቱ ወረቀት አልባ የመረጃ ልዉዉጥ አሰራር (EDMS) ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመረጃ አያያዙን ለማዘመን ወረቀት አልባ የመረጃ ልዉዉጥ አሰራር(Electronic Document Management System) ተግባራዊ ለማድረግ ባለፈዉ በጀት አመት ከዋሊያ ቴክኖሎጂ ጋር መፈራረሙ አይዘነጋም ፤ በዚህም አሁን ላይ በዋናዉ መ/ቤት ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የዉስጥ ደብዳቤዎች (Internal Memo) እና ሌሎች ሰነዶችን ወረቀት አልባ የመረጃ ልዉዉጥ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ መጀመራቸዉን የአገልግሎቱ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አወል ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ ጊዜን ለመቆጠብ ፣ ቀልጣፋ የስራ ፍሰት እንዲኖር ፣ የወረቀት ግዥ ወጭን ለመቀነስ እንዲሁም ሰራተኞች የሚፈልጉትን መረጃ በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ አስተዋፆ እንደሚያበረክት አቶ መሀመድ አንስተዋል፡፡

በዋሊያ ቴክኖሎጂ የEDMS ፕሮጀክቱ ማናጀር ወ/ሮ እሌኒ እሸቱ እንዳሉት ሲስተሙ አገልግሎቱ ከሚያከናዉነዉ የስራ ሂደት አኳያ የተቃኘ እና የተቀናጀ በመሆኑ በቀላሉ መጠቀም ያስችላል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ሲስተሙን ለቅርንጫፎች ለማዉረድ የክፍተት ትንተና (Gap Analysis)ተሰርቶ ተግባራዊ እንደሚደረግ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

09 Jan, 19:30


ቅርንጫፉ ለ117 ጤና ተቋማት የክትባት እና የመደበኛ መድኃኒቶችን ቀጣይነት ባለው መልኩ እያቀረበ መሆኑን ገለጸ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርጫፍ ለ117 ጤና ተቋማት የክትባት እና የመደበኛ መድኃኒቶችን ቀጣይነት ባለው መልኩ እያቀረበ እንደሚገኝ የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ ማህሙድ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርጫፍ በሱማሌ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ ለ 4 ዞኖች ከ 3ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የሀገራችን ህዝቦች የክትባት መድኃኒቶችን ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የመደበኛ መድኃኒቶችን ለጤና ተቋማት የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት በወር እና በየሁለት ወሩ ስርጭት እየተደረገ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

የህክምና ግብአቶች ዞን እና ወረዳዎች ላይ ሳይቆዩ በቀጥታ ጤና ተቋማት ላይ ማድረስ የ"ላስት ማይል ደሪቨሪ" አሰራርን አፈጻጸማቸው በመደበኛ ግብአቶች 54 ከመቶ መድረሱን የተናገሩ ሲሆን ፤ የክትባት መድኃኒቶች በቀጥታ የማድረስ አፈጻጸማችን 75 ከመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል፡፡

ዋና ችግር የነበረብን አሉ አቶ መሀመድ ከ2008 ዓም ጀምሮ በኪራይ መጋዘን ውስጥ የፕሮግራም እና የ መደበኛ ግብአቶች ለየብቻ በተለያዩ ቦታዎች የሚከማቹ በመሆናቸው ለማኔጅመንት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ጠቁመው ፤ ይህንን ችግር ለዘለቄታው የሚቀርፍ ከሱማሌ ክልላዊ መንግስት በተገኝ 15 ሺ ካሬ ሜትር መሬት ርክክብ ተደርጎ የመጋዘን የግንባታው የጨረታው ሂደት በዋናው መ/ቤት በአሁኑ ወቅት በሂደት ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የህክምና ግብአቶች ጤና ተቋም ላይ በትክክል ስለመድረሳቸው ማረጋገጫ ሞዴል 19 የማሰባሰብ ስራ 100 % ነው ያሉት ኃላፊው የተቀናጀ የመረጃ ስርኣት /ERP -SAP/ በቅርጫፉ ስራ ላይ በማዋል በቀን እስከ 20 ደንበኞች በዲጅታል ቴክኖሎጂ ማስተናገድ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ጥቅም ላይ የማይውሉ የህክምና ግብአቶች ማስወገጃ ማእከሉን "ኢንስሌሬተር" ስራ በማስጀመር ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከአገልግሎቱ ያሉ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የህክምና ግብአቶችን በጥንቃቄ አየተወገዱ መሆኑን አቶ መሀመድ አክለው ገልጸዋል።

#ማገልገል ክብር ነው

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

08 Jan, 15:46


ለማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚውል የክትባት መድኃኒቶች በአገልግሎቱ 19 ቅርንጫፎች አማካኝነት መሰራጨቱ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከ4.5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የማህፀን ጫፍ ካንሰር ክትባት መድኃኒቶች በ19 ቅርንጫፎች አማካኝነት ማሠራጨቱን የክትባት መድኃኒቶች ተወካይ ባለሙያ ወ/ት ሰሚራ ጀማል አስታውቀው ፤ የክትባት መድኃኒቶቹ ጋቪ ከተሠኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት የተገኙ ሲሆን ሕብረተሰቡ ክትባቱን እንዲያገኝ የዘመቻ ስራ እየተከናወነም እንደሆነ አክለዋል።

በአሁኑ ሠዓት አገልግሎቱ ከ830 ሺ 480 በላይ የሚገመቱ የማህፀን በር ጫፍ ካንሠር የክትባት መድኃኒቶች በማከማቻ መጋዘኖቹ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ማገልገል ክብር ነው !
ዘጋቢ ማኅሌት አበራ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

08 Jan, 14:14


https://youtu.be/Tus4ZzJv6Fk?si=X3AEJjtJP9XO0FKC

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

08 Jan, 11:49


https://youtu.be/HJCk7zR9e7Q?si=QHakpAfoF1kvWLRi

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

06 Jan, 21:10


መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም ፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

#ማገልገል ክብር ነው!

Proud to serve

መልካም በዓል!

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

01 Jan, 06:05


Dear our stakeholders, partners & Donners marry Christmas & Happy new year 2025.

Wishing you warmth, healthier, prosperous & joy this Holiday.

we look forward to serving you in 2025.

አዲስ ዓመትን በግሪጎርያን ካላንደር ለምታከብሩ መልካም አዲስ ዓመት

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

30 Dec, 17:44


አገልሎቱ የተጠናከረ እና ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ አቅምን ለማጎልበት እየተሠራ መሆኑ ተጠቆመ
----------------------------------------

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የፋይናንስ አቅሙን ለማጎልበት የወጪ ቋቶቹን አላስፈላጊ ወጪ፣ መቀነስ የሚገባቸው ወጪዎች እና ወደ ሶስተኛ ወገን የሚተላለፉ በማለት የለየ ሲሆን ሠሞኑን በአዳማ ከተማ የ3 ቀን ሠርቶ ማሣያ ምክክር ከዋናው መ/ቤትና ከቅርንጫፍ ባለሙያዎች ጋር አከናውኗል፡፡

ተቋሙ ከመንግስት በጀት ተመድቦለት የማይሠራ እንደመሆኑ መጠን ልናርማቸው የሚገቡ ተግባራትን በማስተካከል፣ ሌሎች የገቢ ምንጮችን በመፍጠርና በማጎልበት የተቋሙን ገቢ የተጠናከረ እንዲሆን ተግተን ልንሠራ ይገባል ሲሉ የፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ አሣስበዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የመድኃኒት ፈንድ እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 1354/2017 አዋጅ ተቋሙን በፋይናንስ ለማጎልበትና የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ጥሩ አጋጣሚዎችን እንደሚፈጥር፤ በተጨማሪም አዲስ የተገበርነው ሲስተም ERP/SAP የምናሠራጫቸው መድኃኒቶችን በመቆጣጠር የተቋሙን አላስፈላጊ ወጪ ለመከላከል እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

የተጠናከረና ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ አቅምን ለማጎልበት አገልግሎቱ ከ"UNFPA" ጋር የተቋሙን የ10 ዓመት ሂሣብ በመመርመር ጥናት ያስጠና ሲሆን ወጪን ከመቀነስ ባሻገር በቀጣይ ለተቋሙ የገቢ ምንጭ የሚሆኑ ምክረ ሃሣቦችንም ለይቷል፡፡

አገልግሎቱ እንደ ሃገር ለማህበረሠቡ መድኃኒት ገዝቶ ማቅረብ የሚያስችልበት ስትራቴጂ እየተሠራ እንደሆነና አላስፈላጊ ወጪዎችን እንዲሁም ተጨማሪ ገቢ የምናገኝባቸውን ነገሮችን በመለየት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉ የአገልግሎቱ የኘሮግራም ኘሮጀክት ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

በፀሎት የማነ

# ማገልገል ክብር ነው

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

28 Dec, 04:35


የጤና ተቋማት ፍላጎት ያገናዘበ የካንሰር መድኃኒት አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የጤና ተቋማትን ፍላጎት መነሻ በማድረግ 54 አይነት የካንሰር መድኃኒት በማቅረብ የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ ይገኛል።

የአቅርቦት መቆራረጥ እንዳይከሰት ጤና ሚኒስቴር ፣ አገልግሎቱ እና ጤና ተቋማት በጋራ የሶስትዮሽ ስምምነት በመዋዋል ጤና ሚኒስቴር የመድኃኒቱን ዋጋ 50% ከመቶ በመሸፈን ለተገልጋዮች ድጎማ ለማድረግ አቅደን እየሰራን ነው ሲሉ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ተናግረዋል።

አገልግሎቱ በስምምነቱ መሰረት ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ዋና ዋና የካንሰር መድኃኒቶች ግዥ ተፈፅሞ ወደ መጋዘን እየገቡ እንደሆነ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አንስተው ፤ በ1ወር ውስጥ የሁሉንም የመንግስት ጤና ተቋማት ፍላጎት ያገናዘበ የካንሰር መድኃኒት አቅርቦት እንደሚኖር ገልፀዋል።

አክለውም የሶስትዮሽ ውሉ ማህበረሰቡ መድኃኒቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ አስተዋፆ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

#ማገልገል ክብር ነው!
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

26 Dec, 18:17


ነገሌ ቦረና ጠቅላላ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት
*****

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ለነገሌ ቦረና ጠቅላላ ሆስፒታል 20 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የተገኘው በኢጋድ ዋና ፀሐፊ በወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አማካኝነት ሂውማን ብሪጅ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት እንደሆነም ተመልክቷል።

በድጋፍ መርሐ-ግብሩ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ባለስልጣን የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ አበባው ቢሆነኝ፣ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱርቃድር ገልገሎ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቦኮና ጉታ እንዲሁም የምስራቅ ቦረና ዞን የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የተደረገው ድጋፍ የሆስፒታል አልጋዎች፣ የአካል መደገፊያ መሳሪያዎች፣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ድጋፉ የሆስፒታሉን አገልግሎት የሚያሳድግ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ሆስፒታሉ በምሥራቅ ቦረና እና አካባቢው ለሚገኙ 100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ EBC

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

23 Dec, 15:10


የኢፌዴሪ ጤና ሚንስቴር ከደቡብ ኢትዮጵያ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን የወባ በሽታ ስርጭት መከላከል ላይ የተደረገ ድጋፋዊ ክትትል የግብረ መልስ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይርክተር ዶ/ር አብዱቃድር ገልገሎ የተመራው ቡድን የወባ በሽታን ስርጭት ለመቀነስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲያደርግ የነበረውን ድጋፋዊ ክትትል የግብረ መልስ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

ዋና ዳይርክተሩ የወባ በሽታ ከወትሮው እንደ ሀገር እየጨመረ መምጣቱን ገልፀው በከፍተኛ ደረጃ የበሽታው ስርጭት የሚታይባቸው 222 ወረዳዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዴተለዩ ተናግረዋል።

ከእነዚህ ውስጥ 22ቱ ወረዳዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንደሚገኙ ዶ/ር አብዱል ቃድር ጠቅሰው ህብረተሰቡ ለከፋ ጉዳት ሳይዳርግ ለመከላከል ታስቦ ድጋፋዊ ክትትሉ መደረጉን ገልፀዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ መና መኩሪያ በበኩላቸው የወባ በሽታ እያስከተለ ያለውን ጉዳት በመገንዘብ በሽታውን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ከሀገራችንም ሆነ ከክልላችን ጨርሶ ለማስወገድ ከፍተኛ ቁርጠኝነት በማሳየት የጤና አጋሮችን እና ህብረተሰቡን ያሳተፈ ርብርብ መደረጉ ውጤታማ በመሆኑ ስርጭቱ እየቀነሰ እንደሚገኝ አብራርተዋል ።

ጤና ሚንስቴር ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አመራርና አባላት ጋር በጋራ በመሆን የወባ ስርጭት እየተባባሰ በሚገኝባቸው አካባቢዎች በተደረገ ድጋፋዊ ክትትል ወቅት በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግብረ መልስ እየቀረበ ይገኛል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ማኔጅመንት አባላት፣ የዞን ጤና መምሪያ ኃላፊዎች፣ የተመረጡ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት፣ የሆስፒታልና ጤና ጢቢያ ኃላፊዎችና ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል።

#ማገልገል ክብር ነው!

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

23 Nov, 07:32


https://youtu.be/UyN6qXxIdvo?si=xkZG5jcFsfRGLgv8

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

20 Nov, 19:25


የህክምና ግብአቶች ግዢ የተሳለጠ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደሆኑ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ከፍተኛ ሃላፊዎች ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአገልግሎቱ ዋና መስሪያቤት ህዳር 10 ቀን 2017ዓ.ም በህክምና ግብአት ግዢ ሂደት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ዉይይት አድርገዋል።

በዉይይቱም ባጠረ ጊዜ ግብአቶች መገዛት እንዳለባቸዉና አስቀድሞ ተቋማቶቹ በእቅድ የሚመራ የተቀናጀ አሰራራቸዉ መጎልበት እንደሚያስፈልገዉ የተነሳ ሲሆን ፤ የደንበኞችን አስተያየት በመቀበል ለለዉጥ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ገልፀዋል።

በሎጅስቲክ ስርአት አገልግሎቱ ለዉጥ እያመጣ ያለዉ ባለድርሻ አካላትን አሳትፈን እና ተቀራርበን በመስራታችን ነው በማለት የግዢ አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ገልጸዋል ።

አገልግሎቱ ግብአቶቹን ወደ ሀገር ዉስጥ ሲያስገባ በቀጥታ እንደሚከታተሉ የገለፁት በአገልግሎቱ የኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ናሆም ገመቹ ሲሆኑ የክፍያ ስርአቱ በብር እንዲሆን እንዲሁም ለተሳለጠ እና ፈጣን አሰራር በኮፒ ሰነድ መስተናገድ የሚቻልበትን ጥያቄ ለኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖር ሎጀስቲክስ መቅረቡን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሃላፊዎችም በውይይት የተነሡ ሀሳቦችን የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ለደንበኞች ምላሽ እንደሚሰጡ ገልፀው አገልግሎቱ ለረጅም አመታት ታማኝ አጋር በመሆንና ከፍተኛ መጠን ያለዉ ጭነት በማጓጓዝ ምስጉን ደንበኛ መሆኑን የሚገልፅ የምስክር ሰርተፍኬት በዋና ስራ አስፈፃሚያቸዉ ዶ/ር በሪሶ አመሎ በኩል የተላከ ለአገልግሎቱ የተበረከተ ሲሆን ተቀራርቦ በመወያየት ከዚህ የላቀ ዉጤት በጋራ በማስመዝገብ ቀልጣፋ አገልግሎት ማምጣት እንደሚቻል ገልፀዋል።

ዘጋቢ አማኑኤል ወርቃየሁ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

18 Nov, 17:57


የአቅርቦት ሰንሰለቱን ማነቆዎች ለመለየት የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል እና ምልከታ በሁሉም ክልሎች እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የሀገሪቱን የአቅርቦት ሰንሰለት ማነቆዎችን ለመለየት ጤና ሚንስቴር እና አገልግሎቱ ባካሄዱት አመታዊ ግምገማ ላይ ሲነሱ የነበሩ የህክምና ግብአቶች አቅርቦት ችግሮች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባለመ መልኩ በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የአገልግሎቱ የእቅድ ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ አበበ ተናግረዋል፡፡

በምልከታዉ ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከአገልግሎቱ ፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከአጋር አካላት የተወጣጡ የሚመለከታቸዉ ባለሙያዎች ሁሉም ክልሎች ላይ ያሉ የተመረጡ 150 ጤና ጣቢያዎች ፣ ሆስፒታሎች ፣ ዞኖች ፣ ወረዳዎች እንዲሁም 14 የአገልግሎቱ ቅርንጫፎች ላይ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ምን እንደሚመስል ፤ የተሰራጨዉ ግብአት እና ማህብረተሰቡ ጋር የደረሰዉ ግብአት መመጣጠኑን እንዲሁም በቅርንጫፎች ያለዉን የኢ.አር.ፒ ትግበራ ሁኔታ በማየት ጉድለቶች ካሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚሰጥበት ምልከታ እንደሚሆን በጤና ሚኒስቴር የመድኃኒት እና ህክምና ግብአቶች አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አማካሪ አቶ ፈይሳ ሳፋዎ ገልፀዋል፡፡

በድጋፍ እና ክትትሉ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች የመከታተያ ቼክሊስት ተዘጋጅቶ በምን አይነት መልኩ መስራት እንዳለባቸዉ በከፍተኛ አመራሩም ጭምር ገለፃ እና ስልጠና እንደተሰጣቸዉ አቶ ፈይሳ አንስተዉ ፤ ምልከታዉ ከህዳር 8 ጀምሮ በ3 ሳምንታት ዉስጥ እንደሚጠናቀቅ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡

ምልከታዉ ሲጠናቀቅ በተለይም አገልግሎቱ እስካሁን እየሰራ ያለዉን ስራ በብቁ ሁኔታ እየተወጣ መሆኑን እና ጉድለቶችን በማወቅ የአጭር ጊዜ እቅድ በማዉጣት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሚያግዘዉ አቶ ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

16 Nov, 12:05


አገልግሎቱ "የፋርማሲዩቲካል አቅርቦት ሰንሰለት ቀጣይነት ሂደት የማሻሻያ ጉዞ" ከቀረቡ 31 ጉዳዮች በምርጥ ኬዝ አቅራቢነት ተሸላሚ ሆነ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒ አቅራቢ አገልግሎት በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት በ2024 ዓለም አቀፍ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ስብሰባ "ምርጥ ኬዝ አቅራቢነት" ሽልማት ሌጎስ ናይጄሪያ ለውድድር ከቀረቡ 31 ጉዳዮች መካከል ተወዳድሮ አሸናፊ ሆኗል።

በአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ካቀረብናቸው 4 ኬዞች በምርጥ ኬዝ አቅራቢነት ማሸነፍችን አገልግሎቱ በ2030 ፈጣን ምላሽ ሰጭ ተቋም ለመሆን የያዘውን ራዕይ ለማሳካት ማሳያ ነው ሲሉየአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ ተናግረዋል።

የማሻሻያ ፕሮጄክቶቹ አፈፃፀም ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ላደረጉልን የአገልግሎቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ለካይዘን ፈጻሚ ቅርንጫፎች፣ ለካይዘን ትግበራ ቢሮ እና ለግሎባል ካይዘን ኢንስቲትዩቶች የጥራት ቁጥጥር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ አወል ጀማል አመስግነዋል።

#ማገልገል ክብር ነው።

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

15 Nov, 13:53


አገልግሎቱ ከኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር እውቅና አገኘ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
“ለስኳር ህመም ህክምና እና ክብካቤ ተገቢውን ተደራሽነት ካገኙ ሁሉም የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች በተሟላ ጤንነት የመኖር እድል አላቸው” በሚል መሪ ቃል ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም 14ኛው የአለም የስኳር ህመም ቀን በአዲስ አበባ በካፒታል ሆቴል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

በእለቱ በስኳር ህመም ጥናትና ምርምር ያደረጉ ምሁራን፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና አጋር ድርጅቶች የተገኙ ሲሆን በስኳር ህመምና ምሉዕ ደህንነት፣ በጤናማ የኑሮ ዘይቤ፣ የዓካል ብቃት እንቅስቃሴና ጤና፣ የአመጋገብ ስርዓትና የስኳር ህመም መከላከል ዙሪያ የጥናታዊ ጽሁፍና የፓናል ውይይቶች ተደርገዋል።

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በቆየው በዚህ መርኃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ያለው ጉልህ ሚና የተገለጸ ሲሆን አገልግሎቱ ከስኳር ህመም ማህበር ጋር በቅንጅትና መቀራረብ በመስራት ለስኳር ህመም ህክምና የሚውሉ ኢንሱሊኖችና እንክብሎች ያለማቋረጥ እያቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ይሁንና በበቂ ክምችት ያለውን ይህንን ግብዓት ተደራሽነትና በቀጣይነት ባለው መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ንጉሴ ከኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር የእውቅና ሰርተፊኬት ተቀብለዋል።

ማህበሩም የስኳር ህመምን ለመከላከል፣ ለህሙማን ለተደረገው በተመጣጣኝ ዋጋ መድኃኒት አቅርቦት እንዲሁም አገልግሎቱ ለሚያደርገው ትርጉም ላለው አጋርነት በህሙማንና በማህበሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለስኳር ህመም የሚያገለግሉ ኢንሱሊን እና እንክብሎች እጥረት አለ ተብሎ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ ለቀረቡ ሚዛናቸውን ያልጠበቁ የተሳሳቱ ዘገባዎች በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ጤና ተቋማት በኩል በተለያየ ወቅት ስርጭት የተደረገ ሲሆን በአገልግሎቱ ቅርጫፎችና በማአከል የህክምና ግብቶች ማከማቻ በጋዘኖች የቅዝቃዜ ሰንሰለቱን በጠበቀ ሁኔታ በቂ የኢንሱሉን ክምችት መኖሩን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በቅርቡ ማሳወቁ ይታወሳል።

#ማገልገል ክብር ነው!

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

15 Nov, 07:42


አገልግሎቱ ላለፉት ሶስት አመታት ከግሎባል ፈንድ ያገኘውን በጀት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዬጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከተለያዩ አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል ፤ ከእነዚህም መካከል ግሎባል ፈንድ አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይጠቀሳል ፤ ግሎባል ፈንድ በአለም አቀፍ ደረጃ የጤና ዘርፍ ስርዓት የተጠናከረ እንዲሆን በተለይም የኤች አይ ቪ ፣ የሳንባ ፣ የወባ ፣ የጉበት ቫይረስ በሽታዎችን ከሀገራችን ብሎም ከአለማችን ለማጥፋት የሚሰራ ለጋሽ ድርጅት ነው ፡፡

ግሎባል ፈንድ የኤች አይ ቪ ፣ የሳንባ ፣ የወባ ፣ የጉበት ቫይረስ ፣ የተጓዳኝ በሽታ ማከሚያ መድኃኒቶችን ፣ ኬሚካሎችና ፣ የህክምና መመርመሪያ መሳሪያዎችን ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን በአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ቢሮ የግሎባል ፈንድ ፕሮግራም ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ደገፉ ኡማ ገልፀው ፤ በተጨማሪም አገልግሎቱ የተጠናከረ የአቅርቦት ሰንሰለት እንዲኖረው የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት(ERP) ትግበራ እና የሰው ሀይል አቅም ግንባታ ላይ በርካታ እግዛዎችን እንዳደረጉ ተናግረዋል ፡፡

የዚህ ድጋፍ ዋነኛ አላማ የኤች አይ ቪ ፣ የሳንባ ፣ የወባ ፣ የጉበት ቫይረስ በሽታዎችን ከኢትዮጵያ በማጥፋት ጤናማና ፍሬያማ ማህበረሰብ ማፍራት መሆኑን ዶ/ር ደገፉ አስታውሰው ፤ ይህንንም በቀጣይነት ለማረጋገጥ የቀጣይ ሶስት አመታት ድጋፉ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ፡፡

አገልግሎቱ በጤና ሚኒስቴር በኩል ከሚተላለፍለት ድጋፎች መካከል ከፍተኛው የግሎባል ፈንድ መሆኑን የፕሮጀክት ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ጌታቸው ጠቅሰው ፤ በዚህም ባለፉት ሶስት አመታት ከአጠቃላይ በጀት 80 % የሚሆነው ለህክምና ግብዓት ግዢ መሆኑን እና ቀሪው የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት (ERP) ትግበራ እና የሰው ሀይል አቅም ግንባታ ላይ እንደዋለ አክለው ገልፀዋል ፡፡

አገልግሎቱ በባለፉት ሶስት አመታት መጠቀም ከሚገባው በጀት 99.9 % በአግባቡ በመጠቀሙ የተሻለ የበጀት አፈፃፀም በማስመዝገብ ተጨማሪ 180 ሚሊዮን ዶላር ግሎባል ፈንድ በማበርከቱ ለህክምና ግብዓት ስርጭት የሚያገለግሉ 33 ተሽከርካሪዎች ግዢ መፈፀሙን አቶ ወንድማገኝ አስታውሰዋል ፡፡

ማገልገል ክብር ነው !
ዘጋቢ ማኅሌት አበራ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

12 Nov, 07:57


https://youtu.be/wSf2knIG82U?si=zX6IDW7MktgMhiEb

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

12 Nov, 07:30


https://youtu.be/qTka5iEI8bg?si=IVA_wcuW8IrmJERy

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

09 Nov, 10:40


የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሐዋሳ ቅርንጫፍ   በሲዳማ  ብሄራዊ ክልላዊ  መንግስት   በጤናው ዘርፍ ለተመዘገበው  ውጤት ላበረከተው አስተዋጽኦ  ከክልሉ ፕሬዝዳንት  ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ  እጅ የዕውቅና  ሽልማት ተቀብሏል።

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

09 Nov, 09:26


የአገልግሎቱ ጥቅም ላይ የማይዉሉ ግብአቶች ማስወገጃ 7 ማዕከሎች በሙሉ አቅማቸዉ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጥቅም ላይ የማይዉሉ ግብአቶች ማስወገጃ 8 የማቃጠያ ማዕከሎች ያሉት ሲሆን ፤ አዳማ ፣ ሀዋሳ ፣ ጅማ ፣ ነቀምት ፣ መቀሌ ፣ ደሴ እና ጅግጅጋ ማቃጠያ ማዕከሎች በሙሉ አቀማቸዉ አገልግሎት እየሰጡ ንደሚገኙ እንዲሁም ባህርዳር ማዕከል ወደ ስራ ለማስገባት የሙከራ ስረዎችን እያከናወኑ መሆኑን እና በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የአገልግሎቱ ጥቅም ላይ የማይዉሉ መድኃኒቶች አወጋገድ ስርአት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽፈራዉ በቀለ ተናግረዋል፡፡

በተለይም የአዳማ ማዕከል 1000 ኪሎ ግራም በሰአት እንዲሁም ሌሎች ማዕከሎች 500ኪሎ ግራም በሰአት የማስወገድ አቅም አንዳላቸዉ አቶ ሽፈራዉ አንስተዉ ፤ ማቃጠያ ማሽኖች ዘመናዊ በመሆናቸዉ የአካባቢዉን አየር ንብረት በማይጎዳ መልኩ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡

ማዕከሎቹ ሀገሪቱ ላይ ያሉ ጤና ተቋማትም እንዲገለገሉበት ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ በመሆኑ በአገልግሎቱ መመሪያ መሰረት ተደርጎ በተተመነዉ ዋጋ እንዲጠቀሙ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዉ ፤ በዚህም ጤና ተቋማት ጥቅም ላይ የማይዉሉ ግብአቶችን ለማስወገድ አገልግሎቱ ባሉት 8 ማዕከሎች እንዲጠቀሙ ዳይሬክተሩ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

08 Nov, 12:01


https://youtu.be/wvTb44zOxJY?si=3neCb8nwpIdZHvpP

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

08 Nov, 11:05


የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የመሠረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት 77 ከመቶ መሆኑ ጤና ተቋማት ከ ቅርጫፎች ተቀራርበው ለመስራታቸው ማሳያ መሆኑ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በ26ተኛው የጤና አመታዊ ጉባኤ በመስክ ምልከታ ከታዩት የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የመሠረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት 77 ከመቶ መሆኑ ጤና ተቋማት ከ ቅርጫፎች ተቀራርበው ለመስራታቸው ማሳያ መሆኑን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲልቃድር ገልገሎ ገለፁ ።

የጤና ተቋማት ተገቢውን በጀት ይዘው ካልሆነም የዱቤ ክፍያቸውን በወቅቱ አጠናቀው ከቅርጫፎቻችን ጋር ባላቸው ኮሙኒኬሽን የመሠረታዊ መድሀኒቶችን የመገኘት ምጣኔ ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

መንግስት ለህዝቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መድኃኒት በድጎማ እንደሚያቀርብ ጠቁመው ለዚህም አድሡ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መሬት ላይ እየተተገበረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

በአርባ ምንጭ የተከፈቱት የኮሙኒቲ ፋርማሲና ላቦራቶሪ አገልግሎቾች መልካም ተሞክሮዎች ናቸው ብለዋል።

በአመት እስከ 45 ሚሊዮን ብር የመድኃኒት መግዥያ በጀት ለአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ይመደባል ያሉት የሆስፒታሉ የመድኃኒት ክፍል አስተባባሪ የሆኑት አቶ መሳይ ሽብሩ ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አርባምንጭ ቅርጫፍ ጋር መልካም የስራ ግንኙነት ስላለን በዚህ አመት ተሸላሚ ሆነናል ብለዋል።

ሆስፒታሉ ለ1.7 ሚሊዮን ታካሚዎች በአመት ግልጋሎት እንደሚሰጥ ተናግረው በርካሽ ዋጋ ስለምታቀርቡልን EPSS ባይኖር እኛም ሆነ ህብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ጫና አሳስበው ይከብደኛል ብለዋል።

#ማገልገል ክብር ነው

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

07 Nov, 16:28


አርባምንጭ ቅርንጫፍ የጀመረዉን የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባዉ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍን የጎበኙና ሰራተኞችን ያወያዩ ሲሆን ቅርንጫፉ የጀመረዉን የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባዉ ገልፀዋል።

የቅርንጫፉ ስራአስኪያጅ አቶ አንድነት አሰፋ እንዳሉት 216 ጤና ተቋማትን በቀጥታ ስርጭት የግብአት ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ ጠቁመዉ ፤ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአትን ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ የክምችት አቅም መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።

የመልካም አስተዳደርና ስራን ማዕከል ያደረጉ ሃሳቦ በዉይይት ወቅት የተነሱ ሲሆን ለአብነትም የሰዉሃይል አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ ፤ ተቋሙ የተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ አዋጁን ማፀደቅና ወደተሻለ አገልግሎት ሰጪነት መድረስ እንደሚያስፈልግ በተጨማሪም የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአቱ ያመጣዉን መልካም የለዉጥ ጅማሮ በባለቤትነት ማስተዳደር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በቀጣይ አገልግሎቱ ፈጣን የግዢ መመሪያ እንደሚኖረዉ ፤ ሰራተኞች በሰሩት ልክ እንደሚያገኙ እንዲሁም የዉስጥ ገቢን ማጠናከር እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

ዘጋቢ አማኑኤል ወርቃየሁ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

05 Nov, 13:10


https://youtu.be/aDyO4oeIhDA?si=W5FnBL7RSA1LXe_h

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

05 Nov, 13:08


https://youtu.be/qEWZOHbs_KM?si=PW0-nD-gtSABMwHp

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

05 Nov, 13:07


https://youtu.be/nN9adL-zhi8?si=nvkaYwFj8iC5UIws

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

05 Nov, 13:06


https://youtu.be/jYvE8ag60Zw?si=SYfUdvOt7oUTwILL

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

04 Nov, 06:18


የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አፈፃፀሞቹን በጤና ሚንስትር አመታዊ ጉባኤ ላይ ኤግዝቢሽን አሳየ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

26ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማ “የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ እመርታ ለተፋጠነ የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ ቃል ተካሄዷል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣የጤና ሚኒስትር ደኤታዎች ና የተጠሪ ተቋማት ሀላፊዎች እንድሁም የጉባኤው ተሳታፊ እንግዶች በተገኙበት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አፈፃፀሞቹን በአመታዊ ጉባኤ ላይ ኤግዝቢሽን አሳይቷል።

በ2016 በጀት አመት በመደበኛ መድኃኒቶች፣የህክምና መገልገያዎች እና መሳሪያወች እንዲሁም በላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች ፣ የጤና ፕሮግራም ግብአቶች ከፍተኛ መጠን ያላቸው ሲሆኑ በጥቅሉ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ የነበራቸው የህክምና ግብአቶች በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ስርጭት መደረጉ ተገልጿል።

፣በመደበኛ ሙቀት ና ቅዝቃዜ ከ81 በሽህ 134 ሜትር ካሬ የክምችት መጠን መድረሱን፣ በቅዝቃዜ ሰንሠለት ደግሞ 5137 ሜትር ኩዮቢክ የማከማቸት አገራዊ አቅም ማደጉ፣የሀገር ውስጥ አምራቾች አፈፃፀም፣አገልግሎቱ በቴክኖሎጅ እራሱን በማዘመን ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የተነተኑት የግዥና የስርጭት መረጃዎችን ጨምሮ ዋና ዋና አፈፃፀሞች በግራፍ፣በፎቶ፣ በቪድዮ እና በህትመት ውጤቶች ቀርበዋል።

ኤግዝቢሽኑን ያቀረቡት የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አወል ሀሠን ፣የህዝብ ግንኙት እና ኮሙኒኬሽን አማካሪው አቶ ብሩክ አለማየሁ እንዲሁም ከአገልግሎቱ አርባምንጭ ቅርጫፍ ሙያተኞች ጋር በመተባበር ነው።

#ማገልገል ክብር ነው።

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

02 Nov, 11:05


አገልግሎቱ መጋዘኖችን የጥገና ስራ ለማከናወን ከአቢታ ኮንስትራክሽን ጋር ተፈራረመ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከ UNICEF ባገኘዉ 1.3 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ መጋዘኖችን የጥገና ስራ ለማሰራት ከአቢታ ኮንስትራክሽን ጋር የአገለግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸዉ በተገኙበት ተፈራርመዋል፡፡

በተለይም የጥገና ስራዉ የሚከናወነዉ አገልግሎቱ ካሉት 19 ቅርንጫፎች መካከል አስቸኳይ ጥገና የሚፈልጉ ዋናዉ መስሪያ ቤትን ጨምሮ ድሬዳዋ ፣ ደሴ ፣ ጅማ እና ሰመራ ቅርንጫፍ መጋዘኖች ላይ የካኖፒ ፣ የወለል እና የኤሌክትሪክ ጥገና እንደሚከናወን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

አክለዉም UNICEF ላደረገዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዉ ፤ አቢታ ኮንስትራክሽን ስራዉን በተያዘለት ቀን አጠናቆ እንዲያስረክብ አደራ ብለዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

01 Nov, 09:06


የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርንጫፍ የስራ ባልደረባ የሆኑት ወ/ሮ አሰለፈች ስዩም ከዚህ አለም በሞት ስለተለዩ የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንድሁም ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን።

# ማገልገል ክብር ነው

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

30 Oct, 15:14


Channel name was changed to «Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS»

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

30 Oct, 12:51


በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አማካኝነት ተገዝቶ የተተከለው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ባለ 64 ስላይስ ሲቲ እስካን ማሽን ርክክብ ተደረገ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት አማካኝነት ተገዝቶ የተተከለው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ባለ 64 ስላይስ ሲቲ እስካን ማሽን ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአክሱም ከተማ በተደካሄ የ ርክክብ ስነስርዓት ላይ ተገልጿል ።

በኘሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸው የተገኙ ሲሆን አገልግሎቱ ጥራታቸውን የጠበቁ የህክምና ግብዓቶችን ከ5000 በላይ ለሚሆኑ ጤና ተቋማት የሚያቀርብ መሆኑን ገልፀው በተለይ እንደነዚህ አይነት የህክምና መሣሪያዎች ጤና ተቋማቱ ከአገልግሎቱ ጋር ውል በመግባት የሚፈፀም መሆኑን ገልፀው በእኛ በኩል የህክምና ግብአቶችን የገባናቸውን የውል ግዴታዎች ለመወጣት በርካታ ማሻሻያዎችን እያደረገን ነው ተብለዋል። የአክሱም ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ሲቲ እስካንም የዚህ የአሰራር ስርዓት የቀረበ መሆኑ ተገልፀዋል።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብረየሱስ ብረሀነ ፣ ምክትል ኘሬዘዳንት ዶ/ር መኮነን ወልደአረጋይ ፣ የሆስፒታሉ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገብረህይወት ተ/ሀይማኖት እንዲሁም ከትግራይ ጤና ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ፀገየ በሪሁ በርክክቡ ላይ የተገኙ ሲሆን የህክምና መሳሪያው ተተክሎ ስራ መጀመሩ በህክምና አገልግሎት አሰጣጡና በመማር ማስተማር ጥረቱ ለይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተምኖበታል። ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና በማቀረብ እና እውቅና በመስጠት ርክክብ ተደርጓል ።

#ማገልገል ክብር ነው

Ethiopian Pharmaceutical Supply Service - EPSS

30 Oct, 12:50


አገልግሎቱ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የ100 ቀን አፈፃፀም ገመገመ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የ100 ቀን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀም እና የአገልግሎቱ የሩብ አመት አፈፃፀም ከፍተኛ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተገምግሞ ውይይት ተካሂዷል ።

በግምገማዉ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፤ በሩብ አመቱ የኢ.አር.ፒ አሰራር ዉጤታማ መሆን ፤ የመቋቋሚያ አዋጁ ጫፍ መድረስ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መሻሻል ለአገልግሎቱ እንደ እድል የሚታዩ ጉዳዮች መሆኑን አንስተዉ ፤ በግምገማዉ አጠቃላይ ከአቅርቦቱ ጋር ተያይዞ የተገኙ አፈፃፀሞችን የምናይበት ነዉ ብለዋል፡፡

የሩብ አመቱን ዝርዝር ሪፖርት የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ያቀረቡ ሲሆን ፤ በመጀመሪያዉ ሩብ አመት ከ 8.1 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸዉ የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም የህክምና ግብአቶች መሰራጨቱን እና ከ22.3 ቢሊየን ብር በላይ በሁሉም ቅርንጫፎች በክምችት እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

በተለይም በሀገሪቱ የነበረው የፀጥታ ችግር እና ወረርሽኝ በተከሰተባቸዉ አካባቢዎች የሚያስፈልጉ ግብዐቶችን አቅም በፈቀደ መልኩ ለማቅረብ ከፍተኛ ርብርብ መደረጉ ፣ የአገልግሎቱ የግዥ መመሪያ በልዩ ሁኔታ ተቃኝቶ ለውሳኔ እንዲቀርብ መደረጉ ፣ ለጤና ተቋማት የቀጥታ ስርጭት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች ማቅረብ መቻሉ እና የኢ.አር.ፒ አሰራር ስርአት ትግበራ ዉጤታማ መሆን በሩብ አመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖች መሆናቸዉን ም/ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡

በሩብ አመት የታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የአመራር ሰጭነትና አስተዳደር ጉዳዮችን እንዲሁም የኦፕሬሽን ዉጤታማነት ማሳደግ ፤ የቴክኖሎጂና የመረጃ ስርአት ማጠናከር እንዲሁም መሰረተ ልማት እና የክትትልና ግምገማ ስርአትን ማሻሻል የቀጣይ 100 ቀናት የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸዉን አቶ ሰለሞን አክለዉ ገልፀዋል፡፡

ከቀረበዉ ሪፖረት በመነሳት የዉይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄወች የተነሱ ሲሆን ፤ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እና አቶ ሰለሞን ንጉሴ ሰፋ ያለ ምላሽ በመስጠት ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

29 Oct, 10:27


የመድኃኒት ስርጭትን የማዘመን ሥራ
https://youtube.com/watch?v=-z4syJBahCY&si=jgLaercJN4hRwOHu

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

28 Oct, 10:36


አገልግሎቱ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዬጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸው ከቤንሻንጉል ጉምዝ ጤና ቢሮ አመራሮች ጋር ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የህክምና ግብአቶችን በምን መልኩ እናድርስ በሚሉ ጉዳዬች ዙሪያ በአሶሳ ከተማ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት አጋር የሆነው FIT(fright in time) የተሰኘው ድርጀት ድጋፍ እንደሚያደርግ አጋርነቱን ገልጿል።

#ማገልገል ክብር ነው

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

17 Oct, 18:06


የጤናዉን ዘርፍ ለማጠናከር አመራሮችን ማብቃት እንደሚገባ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨

የ6ኛዉ ዙር የጤና አመራር ሰልጣኞች (LIP-H) ለ6 ወራት የወሰዱትን ስልጠና ጨርሰዉ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች ፣ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎን ጨምሮ ሌሎች የተጠሪ ተቋማትና ኤጀንሲ ሃላፊዎች በተገኙበት መድረክ ተመራቂዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በስካይላይት ሆቴል የተቀበሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትም ሰልጣኞቹን አስመርቋል።

የተሰጠንን እድል ቸል ሳንል ህብረተሰባችንን በማገልገል ፤ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ለለዉጥ ዝግጁ በመሆን ዉጤት ማምጣት ይኖርብናል ያሉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሯ እካሁን 161 ሰልጣኞች በLeadership Incubation Program for Health ተሳታፊ እንደሆኑና ሰልጣኞች ያወቁትን በተግባር በማዋልና ሌሎችንም በማብቃት የጤናዉን ሴክተር መደገፍ እንዳለባቸዉ ተናግረዋል።

የሃዋሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሰ ከተመራቂዎቹ መካከል አንዱ ሲሆኑ አገልግሎቱ የጀመረዉን የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርኣት እዉን በማድረግ ቀልጣፋ የህክምና ግብአት ተደራሽነት እንዲፈጠር አመራሮችን በክህሎትና ስነምግባር ብቁ የሚያደርግ ስልጠና መሰጠቱ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዉ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበትን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተቋሙን ራዕይ ማሳካት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በጤና ሚኒስቴር Bill & Melinda Gates Foundation , international institute for primary health care (IPHCE) , American International Health Alliance (A.I.H.A) አዘጋጅነት ስልጠናዉ ቀጣይነት ያለዉ ሲሆን የህክምና ግብአት ተደራሽነቱን ለማሳደግ አገልግሎቱ እያሰለጠናቸዉ ያሉ ባለሞያዎችም ተጨማሪ አቅም እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

ዘጋቢ አማኑኤል ወርቃየሁ

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

14 Oct, 19:18


አገልግሎቱ 17ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበረ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 17ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ‹‹ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፤ ለሉአላዊነታችንና ለኢትዮጵያ  ከፍታ!›› በሚል መሪ ቃል የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ አከበረ ፡፡

ሀገራችን ለዘመናት ነፃነቷን ጠብቃ የኖረች ስትሆን ይህም በአባቶቻችን ደምና አጥንት አስከብረው ያቆዩልን ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ አርአያ የምንሆን ህዝቦች መሆናችንንና ሰንደቅ ዓላማችን የምናስብበት ምክንያት ነፃነታችንና ሉዓላዊነታችንን በማስጠበቅ፣ የሰላምና የፀጥታ ችግሮቻችንን በመፍታት አንድነታችንን የምናስቀጥልበት መሆን እንዳለበት የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናው ካውዛ  ገልፀው፤  በቀጣይ የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የምንረባረብበት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ማገልገል ክብር ነው !
ዘጋቢ ማኅሌት አበራ

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

12 Oct, 18:57


https://youtu.be/Zwgeo08VJNM?si=Z46aEwe6sWbvFmEE

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

12 Oct, 18:56


https://youtu.be/10LIeynLdDE?si=njo9WhFmMebgaUXA

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

12 Oct, 18:56


https://youtu.be/BquYnmdutjg?si=LlftUfgIs2UPcZ5C

Ethiopian Pharmaceutical Supply service - EPSS

12 Oct, 18:55


https://youtu.be/XhO8VRDs6Jk?si=yqRFc0cGv_hvDEkD