EED (ህዳር 27/2017 ዓ.ም)
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ከዩኒዶ ግሎባል ማርኬት አክሰስ ፕሮግራም ከመጡ ልዑካን ጋር በማር ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ድጋፍ በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተሩ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት የአምራች ዘርፉን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው በተለይም የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኤንሼቲቭ አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ወደ ዘርፋ በስፋት ለማስገባትና ዘርፉን ለማሳደግ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ በሙያ ስልጠና፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በምርት ጥራት ሰርተፍኬት እንዲሁም በገበያ ትስስር ዙርያ ከአጋዥ ተቋማት ጋር በቅርበት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ለልዑካን ቡድኑ በሀገራችን ሰፊ የማር ምርት መኖሩን በመጥቀስ ያለውን ሃብት ግን ከአመራረት ጀምሮ እስከማቀነባበር ድረስ በሚስተዋሉ ችግሮች በተገቢው ሁኔታ ጥቅም ላይ አለመዋሉን ገለፃ ተደርጓል፡፡
የዩኒዶ - ግሎባል ማርኬት አክሰስ ፕሮግራም በማር ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን በአቅም ግንባታ ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ፣ በገበያ ትስስር በፓኬጅንግ መሰል ድጋፎችን ተደራሽ በማድረግ ከተቋሙ ጋር በጋራ እንደሚሰራ የልዑካን ቡድኑ መሪ ሚስተር ቾንግ ዉ ገልጸዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት