የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመቐለ ዲስትሪክት የሚያቀርበውን የብድር አገልግሎት በማሳደግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል።
ቋሚ ኮሚቴው በመቐለ ዲስትሪት በመገኘት በባንኩ ፋይናንስ የተደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡
በዚህም ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝ ፋይናንሲንግ ሥልጠና በመስጠትና ወደ ሥራ በመመለስ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የቡድኑ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አዲስ ዓለማየሁ ተጠቁመዋል።
በጥናትና በዕቅድ ላይ የተመሰረተ የብድር አሰባሰብ ላይ ትኩረት በማድረግ ኃብትን በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የቡድኑ ሰብሳቢ በዚሁ ወቅት አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በመወከል ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ተገኝተው የመስክ ምልከታው ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው አበራ በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው በየጊዜው ባንኩ ፋይናንስ ያደረጋቸውን ፕሮጀክቶች በአካል ተገኝቶ የመስክ ምልከታ በማድረግ የሚሰጠው ግብረ መልስ ለባንኩ ስራ አጋዥ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
https://web.facebook.com/photo?fbid=1113959777185867&set=pcb.1113960007185844