ኦሪት እምነት እና ሥርዓት ናት።ወንጌል ደግሞ እምነትም ሕይወትም ናት።
ኦሪት በሥጋ ግዝረት ታትማለች።ወንጌል ግን በቅዱስ ጥምቀት በመንፈስ ግዝረት ታከብራለች።
ኦሪት በአብርሃም ቤተሰብ ትገለጻለች።ወንጌል ግን በመስቀል ሕየወት በክርስቶስ ራስነት ትገለጻለች።
ኦሪት በተስፋ በትንቢት ትነባለች ወንጌል ደግሞ በአካለ ክርስቶስ በዘለዓለም ሕይወት ትነበባለች።
ነቢዩ ኤርምያስ ከኦሪታዊ ሥጋ ግዝረት ባሻገር የወንጌል የልቡና ግዝረትም እንደሚያስፈልግ እንዲህ ይለናል፦"እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ። "ኤር.4፥4