Geez Law & Business www.geezlaw.com️ @geezlaws Channel on Telegram

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

@geezlaws

www.geezlaw.com |0948449999
[email protected] #Free_Services
#Corporate_Lawyer #Business_Lawyer
Law & Business Integrated Services

Geez Law (English)

Geez Law is a Telegram channel dedicated to providing free services related to corporate and business law. With a focus on Law & Business Integrated Services, Geez Law aims to be a valuable resource for individuals and businesses looking for legal advice and support. The channel is run by experienced corporate lawyers who are passionate about helping others navigate the complexities of the legal system. Whether you're a startup entrepreneur, a small business owner, or a large corporation, Geez Law offers valuable insights and guidance to help you succeed in the business world. From contract negotiations to intellectual property rights, Geez Law covers a wide range of topics to ensure that you have all the information you need to make informed decisions. With a commitment to providing top-notch legal advice at no cost, Geez Law is a must-follow for anyone looking to stay ahead in the competitive business landscape. Join the Geez Law Telegram channel today and start benefiting from their expertise and knowledge in corporate and business law.

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

02 Feb, 20:51

Ethiopia’s Forex Rules Set To Change Under IMF Deal
https://www.thereporterethiopia.com/43608/

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

02 Feb, 19:45

በስር ፍርድ ቤቶች እንደተገለፀው ውል እንዲፈርስ በአመልካች ክሱ የቀረበው በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች መካከል ውል ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በህጉ ተመለከተው ጊዜ ካለፈ በኋላ ቢሆንም አመልካች ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ክስ ባለማቅረባቸው የይርጋው ጊዜ ማለፉን በመጥቀስ ወይም ውሉን በመቃወም ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበት ሌላ ሁኔታ የነበረ ስለመሆኑ በማረጋገጥ ውሳኔ አልተሰጠም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግስት መመሪያ ከሃገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩ ኤርትራዊያንን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ከወጡ ጀምሮ ተፈቅዶላቸው እስከተመለሱ ድረስ ያለው ጊዜ
በይርጋው ውስጥ ሊታሰብ የሚችልበት የህግ አግባብ እንደማይኖር ይህ ሰበር ችሎት የፍ/ብ/ህ/ቁ.1845 እና 1846 ድንጋጌዎችን በመተርጎም በሰበር መዝገብ ቁጥር 92408፣ 98177፣ 158255 እና በሌሎችም መዛግብት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን ይኸው ትርጉም በህጉ አግባብ እስካልተለወጠ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 መሰረት በተያዘውም ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው ነው፡፡ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ይህን ወደጎን በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢነት የለውም ብለናል፡:
ሰ.መ.ቁ፡ 247259 ጥቅ.04/2017ዓ/ም
#AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

02 Feb, 19:42

የፍ/ሕ/ቁጥር 2782/1 የገንዘብ አደራን በተመለከተ ሊቀርብ የሚገባውን የማስረጃ አይነት የፍ/ሕ/ቁጥር 2472 ን በማጣቀስ የብድር ውልን ለማስረዳት መቅረብ ያለበት የማስረጃ አይነት የአደራ ገንዘብንም ለማስረዳት መቅረብ እንዳለበት ያመለክታል፡፡ አደራ ሰጪው ለአደራ ተቀባዩ በሰጠው ገንዘብ እንዲገለገልበት በግልጽ መፍቀድ የሚችል ሲሆን ግልጽ ስምምነት ባይኖር እንኳን ገንዘቡ ለአደራ ተቀባዩ የተሰጠው ሳይታሸግ እና ሳይዘጋበት ከሆነ ተቀባዩ እንዲገለገልበት እንደተሰጠው የሚቆጠር መሆኑን የፍ/ሕ/ቁጥር 2782/2 ድንጋጌ ያመለክታል፡፡ በዚህ ጊዜ የአላቂ ነገር ብድርን የሚመለከቱ ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ የፍ/ሕ/ቁጥር 2472/1 በብድር የተሰጠ ገንዘብ ከብር 500 በላይ ሲሆን የብድሩን ውል በጽሁፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሃላ ካልሆነ በቀር ማስረዳት እንደማይቻል እና ለብድር ውል ሌላ ማናቸውም አይነት ማስረጃ ማቅረብ የማይቻል መሆኑን በፍ/ሕ/ቁጥር 2472/1 ተደንግጓል፡፡ በእርግጥ በፍ/ሕ/ቁጥር 2800 እንደተመለከተው የአደራው አይነት አስፈላጊ አደራ ከሆነ የቱንም ያክል የገንዘብ መጠን ቢሆን በሰው ምስክሮች ማስረዳት እንደሚቻል በፍ/ሕ/ቁጥር 2802/2 ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህም ማለት አደራ ሰጪው የጽሁፍ ውል ማድረግ በማይችልበት ሁኔታ ላይ እና ገንዘቡን በአደራ ባይሰጥ ሊዘረፍ ወይም ገንዘቡን ለመዝረፍ ሲባል በአደራ ሰጪው ላይ አደጋ ሊደርስ የሚችልበት ሁኔታ ላይ የነበረ በመሆኑ ገንዘቡን የጽሁፍ ውል ሳይኖር አደራ ከሰጠ የአደራው አይነት አስፈላጊ አደራ ይሆናል፡፡ ለእንደዚህ አይነት አስፈላጊ አደራ በልዩ ሁኔታ የፍ/ሕ/ቁጥር 2782 እና 2472 ተፈጻሚነት የላቸውም፡፡ በመሆኑም አስፈላጊ አደራ ካልሆነ በስተቀር የገንዘብ የአደራ ውል መኖሩን ለማስረዳት እንደ ሰው ማስረጃ ወይም በአደራ የተሰጠ ገንዘብ መሆኑን የማይገልጽ ሌላ ማንኛውም አይነት የሰነድ ማስረጃዎችን ማቅረብ አይቻልም፡
ስለሆነም የባንክ ሐዋላ ወረቀት የብድር ውል መኖሩን የሚያስረዳ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 31737 ላይ የህግ ትርጉም መሰጠቱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በመዝገብ ቁጥር 150290 በሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም እና በሌሎች በርካታ መዝገቦች በተሰጠ ውሳኔ የባንክ የገንዘብ መላኪያ ሰነድ ገንዘብ መላኩን ከማስረዳት ውጪ በምን ምክንያት ገንዘቡ መላኩን ወይም ገንዘቡ በብድር የተሰጠ መሆኑን ሊያስረዳ እንደማይችል የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡ በመሆኑም በሰበር መዝገብ ቁጥር 31737 የተሰጠው የህግ ትርጉም በመዝገብ ቁጥር 150290 እና ሌሎች በርካታ መዝገቦች ላይ በተሰጠ ውሳኔ የተቀየረ በመሆኑ አመልካች የባንክ ገንዘብ መላኪያ ደረሰኝ ገንዘቡን በአደራ የሰጠሁ ለመሆኑ ያስረዳልኛል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም፡፡

የሰ.መ.ቁ.221476 ጥቅ.28ቀን2015ዓ/ም

በስር ፍርድ ቤቶች እንደተገለፀው ውል እንዲፈርስ በአመልካች ክሱ የቀረበው በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች መካከል ውል ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በህጉ ተመለከተው ጊዜ ካለፈ በኋላ ቢሆንም አመልካች ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ክስ ባለማቅረባቸው የይርጋው ጊዜ ማለፉን በመጥቀስ ወይም ውሉን በመቃወም ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበት ሌላ ሁኔታ የነበረ ስለመሆኑ በማረጋገጥ ውሳኔ አልተሰጠም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግስት መመሪያ ከሃገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩ ኤርትራዊያንን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ከወጡ ጀምሮ ተፈቅዶላቸው እስከተመለሱ ድረስ ያለው ጊዜ
በይርጋው ውስጥ ሊታሰብ የሚችልበት የህግ አግባብ እንደማይኖር ይህ ሰበር ችሎት የፍ/ብ/ህ/ቁ.1845 እና 1846 ድንጋጌዎችን በመተርጎም በሰበር መዝገብ ቁጥር 92408፣ 98177፣ 158255 እና በሌሎችም መዛግብት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን ይኸው ትርጉም በህጉ አግባብ
እስካልተለወጠ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 መሰረት በተያዘውም ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው ነው፡፡ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ይህን ወደጎን በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢነት የለውም ብለናል፡:
የሰበር መ/ቁ 247259
ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰጠው ውሳኔ የተወሰደ።
#AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

02 Feb, 13:14

ባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ጣሪያ መስከረም ላይ ይነሳል:: ካለፈው ነሀሴ 2015 ዓ.ም. አንስቶ ተጥሎ የነበረው ባንኮች መስጠት የሚችሉት አዲስ ብድር ገደብ ሙሉ ለሙሉ ሊነሳ መሆኑን ተሰምቷል። የአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅትን (IMF) መረጃ እንደሚጠቁመው ባንኮች የሚችሉት የብድር መጠን ላይ ተጥሎ የቆየው ጣሪያ በቀጣይ መስከረም ይነሳል። በነሀሴ 2015ዓም ወደ ስራ የገባው የብድር ጣሪያ ባንኮች አመታዊ የብድር እድገታቸው ከቀደመው የብድር ክምችት መጠን በ14 በመቶ ብቻ እንዲያድግ የሚያደርግ ነው። ባለፈው ወር መጨረሻ እድገቱ ወደ 18 በመቶ እንዲሆን በብሄራዊ ባንክ ተወስኖ ነበር። ሆኖም ውሳኔው በባንኮች በአወንታዊ የታየ አልነበረም። @Addis_News #AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

02 Feb, 12:17

ተከሳሽ የመከላከያ መልሱን አቅርቦ ክሱ ሊሰማ በተቀጠረበት ዕለት ባለመቅረቡ በፍ/ሥ/ሕ/ቁ 70(ሀ) መሰረት ክርክሩ በሌለበት እንዲታይ ብይን ከተሰጠ የመከላከያ ክርክር የማቅረብ መብቱን ከማሳጣት አልፎ በቀሪዎቹ የክርክር ሂደቶች ከመሳተፍ አያግደውም።
=========|•|========= #AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

02 Feb, 12:14

በስር ፍርድ ቤቶች እንደተገለፀው ውል እንዲፈርስ በአመልካች ክሱ የቀረበው በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች መካከል ውል ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በህጉ ተመለከተው ጊዜ ካለፈ በኋላ ቢሆንም አመልካች ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ክስ ባለማቅረባቸው የይርጋው ጊዜ ማለፉን በመጥቀስ ወይም ውሉን በመቃወም ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበት ሌላ ሁኔታ የነበረ ስለመሆኑ በማረጋገጥ ውሳኔ አልተሰጠም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግስት መመሪያ ከሃገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩ ኤርትራዊያንን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ከወጡ ጀምሮ ተፈቅዶላቸው እስከተመለሱ ድረስ ያለው ጊዜ
በይርጋው ውስጥ ሊታሰብ የሚችልበት የህግ አግባብ እንደማይኖር ይህ ሰበር ችሎት የፍ/ብ/ህ/ቁ.1845 እና 1846 ድንጋጌዎችን በመተርጎም በሰበር መዝገብ ቁጥር 92408፣ 98177፣ 158255 እና በሌሎችም መዛግብት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን ይኸው ትርጉም በህጉ አግባብ
እስካልተለወጠ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 መሰረት በተያዘውም ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው ነው፡፡ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ይህን ወደጎን በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢነት የለውም ብለናል፡:
የሰበር መ/ቁ 247259
ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰጠው ውሳኔ የተወሰደ

#AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

01 Feb, 13:44

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 212110 ታህሳስ 25 ቀን 2016 #በ7_ዳኞች_የተሰጠ_የህግ_ትርጉም።
===================
ከሶስተኛ ወገን የመድን ሽፋን ጋር በተያያዘ የተቋረጠ ጥቅምን (consequential loss) በተመለከተ በዉል ወይም በህግ በግልፅ ካልተመለከተ በስተቀር መድን ሰጪው የመክፈል የውልም ሆነ የህግ ግዴታ የለበትም፣ ሲል ከአሁን በፊት በሰ/መ/ቁጥር  197530፣ 196878፣ 204682 እና በተመሳሳይ ሌሎች መዝገቦች የተሰጠውን የህግ ትርጉም የለወጠ በ7 ዳኞች የተሰጠ የህግ ትርጉም።
==================== #AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

31 Jan, 18:43

፨ ሰ.መ.ቁ. 243973
[ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም]

"አንድ ሰው የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ቢሆንም ንብረቱን ይዞ እስካልተጠቀመ ድረስ የውርስ ንብረቱን በያዘው ሰው ላይ የሚያቀርበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000/1/ መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ ቀሪ ነው" በማለት በሰ/መ/ቁ 243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በ7 ዳኞች በሁሉም ፍ/ቤት አስገዳጅ የሆነ አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል።
#AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

31 Jan, 05:13

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 222041 ጥቅምት 04 ቀን 2015 የተሰጠ የህግ ትርጉም።
===================[=
ተከሳሽ በፅሁፍ መልስ ሲሰጥ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በሚል ርእስ ባይጠቅሰውም /ባይገለፅም በፍሬ ነገር መልስ ላይ መቃዎሚያወችን ከገለፀ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቆጥሮ በቅድሚያ እልባት ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ እና  በዚህ ጉዳይ ላይ / በመጀመሪያ መቃወሚያ ላይ እልባት ሳይሰጥ በዋናው ጉዳይ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጥቅምት 04 ቀን 2015 የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም።
#AA 0948449999 #Business& #CorporateLaws
Join our 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑪𝒉𝒂𝒏𝒏𝒆𝒍👇
https://t.me/GeezLaws

Geez Law & Business www.geezlaw.com️

31 Jan, 05:12