AACRA @addisroads Channel on Telegram

AACRA

@addisroads


Addis Ababa City Roads Authority (AACRA) is a government organization under the Addis Ababa City Adminstration. It was established on March 1998 with the aim of realizing sustainable road infrastructure and creating interchangeable road transport to A.A.

AACRA Promotion (English)

Welcome to AACRA - Addis Ababa City Roads Authority! AACRA is a government organization under the Addis Ababa City Administration, dedicated to improving the road infrastructure of the city. Established in March 1998, AACRA's main goal is to create sustainable road infrastructure and promote efficient road transport within Addis Ababa. If you are looking for updates on road projects, infrastructure developments, or road transport initiatives in Addis Ababa, then this is the perfect channel for you. Stay informed about the latest news, events, and projects undertaken by AACRA to enhance the city's road network and improve transportation for its residents. Join us on our journey towards creating a more connected and accessible Addis Ababa. Follow AACRA on Telegram for regular updates and valuable insights into the organization's efforts to make the city's roads safer and more efficient for all. Be a part of the progress and stay informed about the future of road infrastructure in Addis Ababa with AACRA. Let's work together towards a better and more sustainable transportation system for Addis Ababa!

AACRA

08 Jan, 20:37


የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር ተካሄደ


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ገላን ጉራ በሚገኘው ቁጥር 22 ተስፋ የምገባ ማዕከል፤ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አካሂዷል።


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተቋም ለውጥ እና ድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል ዶሌቦ፤ በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ ከተሰጠው መደበኛ ተልዕኮው በተጨማሪ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስኮች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።


ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ቀደም ሲልም፤ በገላን ጉራ አካባቢ ለልማት ተነሺዎች በተዘጋጀው መንደር የመቃረቢያ መንገድ እና የአውቶብስ ተርሚናል ገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን የጠቁሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ በማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብሮች ላይ በተለያዩ ጊዜያት የመሳተፍ እድል በማግኘታችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል።


አቶ ጀማል አያይዘውም፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የዘንድሮውን የገና በዓል ምክንያት በማደርግ ያዘጋጀው የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር በየጊዜው የሚያካሂደው ሰናይ ተግባር አካል በመሆኑን ጠቁመው፣ ወደፊትም የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡


የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው፤ የከተማ አስተዳደሩ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ለካዛችስ የልማት ተነሽዎች በተመሰረተው መንደርም 22ኛውን ተስፋ የምገባ ማዕከል በማቋቋም ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት መርሀሃ-ግብር እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።


አቶ አለማየሁ አክለውም፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግ እየሰራ ከሚገኘው ተግባር ባሻገር፤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ማዕድ በማጋራቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለአደረገው የበጎ ፍቃድ ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ሌሎች ተቋማትም በመሰል የበጎ ፈቃድ ተግባራት በመሳተፍ የበኩላቸውን ድርሻእንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

06 Jan, 20:49


https://youtu.be/Kpqu48eKrTU

AACRA

05 Jan, 10:41


Invitation for bid

AACRA

03 Jan, 12:04


The new face of Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹

AACRA

03 Jan, 11:45


በደቡብ አዲስ አበባ በመንገድ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራትና አማካሪ ድርጅቱ ላሳዩት መልካም አፈፃፀም እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም፡- በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በተከናወኑ የመዳረሻ መንገድ እና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ግንባታ ስራዎች ላይ የተሳተፉ መልካም አፈፃፀም ላስመዘገቡ የመንገድ ዘርፍ ሥራ ማህበራትና ለአማካሪ ድርጅቱ የእውቅና እና የምስጋና መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የእውቅና እና የምስጋና መርሃ-ግብሩ የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር ነው፡፡


በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አወል፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማዋ በስፋት እያከናወናቸው ከሚገኙ የአስፋልት መንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች በተጨማሪ፣ የመንገድ መሠረተ-ልማት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ለህብረተሰቡ የመውጫና መግቢያ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ፤ የጠጠር መንገዶችን ከመገንባት ጎን ለጎን የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል የድሬኔጅ መስመር ግንባታ እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።


በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የተከናወኑት የአክሰስ መንገድ እና የድሬኔጅ መስመሮች ግንባታ ይህን ተግባር ከሚያመላክቱ ማሳያዎች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን የጠቆሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ በሥራው ላይ የተሳተፉ ማህበራት እና ጎንድዋና አማካሪ ኢንጅነሪግ፣ በግንባታ ሥራው ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በመቋቋም ላስመዘገቡት የተሻለ አፈፃፀም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


የደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር ኢንጅነር ህይወት ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በ2016 በጀት ዓመት በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች 30 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የአክሰስ መንገድ እና 2 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመር ግንባታ ስራ ማከናወን መቻሉን ገልፀው፤ በዚህም 70 ሺ የሚሆኑ ነዋሪዎችን በመንገድ መሰረተ ልማት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ።


በሁለቱም ክፍለ ከተሞች በተከናወኑ የመቃረቢያ መንገድና የድሬኔጅ መስመሮች ግንባታ ሥራ ላይ 29 ማህበራትና አንድ አማካሪ ድርጅት መሳተፋቸውን የገለፁት ኢንጅነር ህይወት፤ በሥራው የተካፈሉ አካላት በትጋት በመስራት ላስመዘገቡት ውጤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


በመርሃ-ግብሩ ላይ እውቅና የተሰጣቸው ማህበራትና አማካሪ ድርጅቶች በበኩላቸው፤ የተሰጣቸው እውቅና ለወደፊቱ በተሻለ የሥራ ተነሳሺነት የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ጠንክረው እንዲሰሩ የሚያተጋ መሆኑን ገልፀው፤ ለዝግጅቱ አስተባባሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

21 Nov, 14:01


የቦሌ-መገናኛ መንገድ አዲስ ገጽታ

AACRA

20 Nov, 09:59


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፤ ከአዲስ ልሳን ጋር በመተባበር በምናዘጋጀው አምድ የባለስልጣኑን የሰው ሃብት አቅም ግንባታ ስራ ዳሰሳ አቅርበናል

AACRA

20 Nov, 09:37


ውድ የዜና መጽሄታችን ተከታታዮች። የህዳር ወር ዜና መንገድ ያን እንድታነቡ እንጋብዛለን

AACRA

18 Nov, 21:04


የኤልክትሪክ ዕቃዎቸች ግዢ ጨረታ

AACRA

18 Nov, 19:45


የክሬን ግዢ ጨረታ ፡-

AACRA

18 Nov, 19:39


የመጸዳጃ ቤት እና የቧንቧ እቃዎች ግዚ ጨረታ

AACRA

18 Nov, 19:34


የአሸዋ ምርት ግዢ ጨረታ

AACRA

18 Nov, 18:17


https://youtu.be/K40AP3ihCHM?si=X77Tn9WFrh6Fa3wp

AACRA

16 Nov, 11:57


ከንቲባ አዳነችን አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሃላፊዎች ቦሌ ካርጎ ቡልቡላ እስከ አቃቂ ድልድይ ያለውን የአረንጏዴ ልማት ስራ ጎብኝተዋል::

ዛሬ የተጎበኘው የአረንጏዴ ልማት በክፍለከተማው የተገነባ ሲሆን በውስጡም:-

- 13 ኪ/ሜ የሚሸፍን የአረንጏዴ ልማት ስራን
- አራት ዘመናዊ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች
- ሁለት የህጻናት መጫዎቻ ሜዳዎች
- አንድ የስፖርት ሜዳ
- አምስት ዘመናዊ የህዝብ መገልገያ የጋራ መጸዳጃ ቤቶች
- ደረጃውን የጠበቀ ሰፊ የእግረኞች መንገድ
- በከተማው ስታንዳርድ መሰረት የተሰራ የህንጻዎች እድሳት
- ፋውንቴኖች
- የመዝናኛ ፓርኮች
- የህዝብ መናፈሻ ቦታዎችን ያካተተ ስራ ነው::

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

15 Nov, 14:21


በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እና በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን መካከል ይፋዊ የስራ ርክክብ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም፡- አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አዲስ ከተቋቋመው አዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ጋር ይፋዊ የስራ ርክክብ ስነ ስርዓት አከናወነ፡፡

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የከተማዋን የመንገድ ዳር መብራት ተደራሽ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በርካታ ስራዎች ሲከናወን መቆየቱን ገልፀዋል፡፡


የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎትን ማሻሻል የአንድ ከተማ የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን የጠቆሙት የከተማዋ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የከተማዋ ነዋሪዎች በቀንም ሆነ በማታ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ምቹ እና ከአደጋ የፀዳ ለማድረግ በአዲስ የተደራጀው ተቋም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተቃኘ የመንገድ ዳር መብራት ከመዝርጋት ጀምሮ ነባር የመንገድ መብራቶችን ደረጃ የማሻሻል ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅበት ኢንጂነር ወንድሙ ተናግረዋል፡፡

ኢንጂነር ወንድሙ አክለውም በከተማዋ የሚገነቡ የመንገድ ዳር መብራቶችን ከጉዳት መጠበቅና መንከባከብ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የከተማዋን የመንገድ ዳር መብራት በተደራጀ መልኩ ለመገንባትና ለማስተዳደር ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 166/2016 ሊቋቋም መቻሉን ገልፀው፤ተቋሙ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት በትጋት ለመወጣት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ በበኩላቸው፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ቀደም ሲል ባለፈባቸው አደረጃጀቶች ውስጥ ሆኖ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታና ጥገና በማከናወን የመንገድ ዳር መብራት ተደራሽነትን ለማሳደግ ሰፊ ስራ ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል።

ኢንጅነር ሙህዲን አያይዘውም፤ ከተማዋ ከሚያስፈልጋት የመንገድ መሠረተ-ልማት ማስፋፋትና ማዘመን ፍላጎት አንፃር፤ የከተማዋን የመንገድ መብራት ራሱን አስችሎ ማስተዳደር በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ሊመሰረት መቻሉን ገልፀው፤ በቀጣይም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት የሚያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በሁለቱ ተቋማት መካከል የተሸከርካሪዎች፣ የሰንድ ርክክብ እና የፊርማ ሥነ - ሥርዓት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

14 Nov, 14:17


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከጀሞ 2 አደባባይ ወደ ጀሞ ሚካኤል በሚወስደው ጎዳና ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል፤ ለፈጣን አውቶብሶች መተላለፊያ በተገነባው መስመር ላይ ተሸከርካሪዎች በፈረቃ የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ አመቻችቷል፡፡

AACRA

12 Nov, 20:39


ሰላም የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች በጉጉት የምትጠብቋት ዜና መፅሄታችን እነሆ ተጋበዙልን

AACRA

11 Nov, 20:08


የጨረታ ማስታወቂያ

AACRA

11 Nov, 15:58


የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርን ቀድሞ ለመከላከል የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ


አዲስ አበባ፣ ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ፡- በየዓመቱ በጥቅምት ወር የሚካሄደውን የዓለም የጡት እና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መካከል የግንዛቤ ወርን ምክንያት በማድረግ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሴት ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡


የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወ/ት ፀደንያ አበበ፤ ስልጠናው በጡት እና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምንነት፣ የመከላከያ መንገዶች፣ ቅድመ ካንሰር ምርመራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ስልጠናውን ከሰጡት ባለሙያዎች መካከል ሲስተር በእምነት ነጋ እና ወ/ት ብሩክታዊት አበበ፤ በቀላል ህክምና ሊድን የሚችልን ህመም ወደ ካንሰርነት ከተቀየረ ሴቶችን ለጤና፣ ለኢኮኖሚና ለማህበራዊ ቀውስ ከመዳረጉም በላይ እስከ ሞት ስለሚያደርስ ቅድመ ምርመራዎች ማድረግ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ገልፀዋል።


አሰልጣኞቹ አያይዘውም የማህፀን በር ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች በገዳይነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህን መሰል የምርመራ እድሎች መመቻቸታቸው የማህጸን ካንሰር ተጋላጭነትን ስለሚቀንስ የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ሥልጠና ላይ 200 የሚሆኑ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሴት ሠራተኞች ተካፍይ ሆነዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

10 Nov, 10:13


በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ495 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓቶች ተመርተወዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለመንገድ ግንባታ ግብዓት የሚሆኑና ከ495 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ምርቶችን በማምረት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም ከ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀርም የ394 ሚሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡

ባለፉት 3 ወራት ተመርተው ጥቅም ላይ ከዋሉት የግንባታ ግብዓቶች መካከል፤፧ ልዩ ልዩ የካባ ምርቶች፣ የተለያየ ቅርፅና መጠን ያላቸው የሲሚንቶ እና የአስፋልት ኮንክሪት ውጤቶች ይገኙበታል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የግንባታ ግብዓቶችን በራስ አቅም መመረት በመቻሉ፤ ከምርት አቅርቦትና ከዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመሻገር የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎችን ለማከናወን አስችሎታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

09 Nov, 13:00


በቦሌ አራብሳ 5 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ የመንገድ የኮብል ንጣፍ ሥራ መከናወን ተጀመረ


አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ቦሌ አራብሳ 5 ሎት 1 እና 2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ ማከናወን ጀምሯል፡፡ 


የቦሌ አራብሳ 5 እና 6 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የስራ ተቋራጭነት ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡


ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ በፍጥነት ባለመፈፀሙ፤ አሁን ላይ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክቶቹን ከስራ ተቋራጩ በመረከብ በራስ ኃይል እየገነባ ይገኛል፡፡


በሁለት ሎት ተከፍሎ የግንባታ ስራው በመከናወን ላይ የሚገኘው የቦሌ አራብሳ 5 የመንገድ ፕሮጀክት 10.9 ኪሎ ሜትር የአስፋልት እና 10.1 ኪሎ ሜትር የኮብል፣ በአጠቃላይ 21 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፤ አሁን ላይ 2 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር በሚሆነው የመንገዱ ክፍል የኮብል ንጣፍ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡


በተመሳሳይም በቦሌ አራብሳ 6 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ፕሮጀክት 3.8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የመንገዱን ክፍል ለኮብል ንጣፍ የማዘጋጀት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በቀጣይ ቀናት የኮብል ንጣፍ ስራው የሚከናወን ይሆናል፡፡ 


የቦሌ አራብሳ 6 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ፕሮጀክት በአስፋልትና በኮብል ደረጃ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን በአጠቃላይ 8 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ነው፡፡


ይሁን እንጂ በፕሮጀክቱ  የግንባታ ስፍራ አሁንም ያልተጠናቀቀ የወሰን ማስከበር ስራ በመኖሩ ምክንያት የግንባታ ሥራውን በፍጥነት ለማከናወን አስቸጋሪ አድርጎታል።


በመሆኑም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመንገዱ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በማጠናቀቅ ለግንባታ ሥራው መፋጠን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

AACRA

04 Nov, 11:33


የጨረታ ማስታወቂያ

AACRA

04 Nov, 09:27


የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ማራዘሚያ ማስታወቂያ

AACRA

02 Nov, 08:00


ቋሚ ኮሚቴው የባለሥልጣኑን የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀመረ


አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ፡- የአዲስ  አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱን 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል፡፡


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን ስራዎች የሚያሳይ ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድ በጀት እና ስትራቴጅክ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አብነት ኤርገንዶ፤ ተቋሙ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 497 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች በማከናወን ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል፡፡


የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ግዛቸው አይካ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ  በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ የግንባታና የጥገና ስራዎች አፈፃፀምና የተመሩበት አግባብ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።


ዶክተር ግዛቸው አክለውም ከተማዋ አሁንም ከሚያስፈልጋት የመንገድ ልማት ፍላጎት አንፃር ሰፊ ስራዎችን መስራት የሚጠይቅ በመሆኑ በባለስልጣኑ  ያለውን ውጤታማ  የስራ አፈፃፀም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረው፣ ቋሚ ኮሚቴው የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡


በቋሚ ኮሚቴው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ  የሰጡት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ፤ ለመንገድ መሰረተ ልማት ማነቆ የሆኑ የወሰን ማስከበር እና ሌሎች እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች በመፍታት በኩል የቋሚ ኮሚቴው እገዛ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይም ልዩ ድጋፍ በሚፈልጉ ፕሮጀክቶች ላይ የድጋፍና ክትትል ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡


ቋሚ ኮሚቴው በቀጣዮቹ ቀናትም የአውቶቢስ ተራ - 18 ማዞሪያ፣ የአየር ጤና - ወለቴ እና የአቃቂ ቃሊቲ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በመስክ ተዘዋውሮ በመመልከት የማጠቃለያ ግብረ-መልስ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

02 Nov, 07:54


የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ

AMN - ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል በዚህም መሰረት

መገናኛ ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ከመገናኛ - ቃሊቲ ፣ ከመገናኛ - ሳሪስ ፣ ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች ወደ መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በጊዜያዊነት ተዛውሯል፡፡

ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበሩት መስመሮች ደግሞ አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ) ወዳለው ቦታ ተዛውሯል፡፡

ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች ከመገናኛ - ገርጂ ፣ ከመገናኛ-ጎሮ ፣ ከመገናኛ - አያት እና ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው በመረጃው አስታውቋል።

AACRA

31 Oct, 12:39


በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል


አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም፡- በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት 3 ወራት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪዎች ግጭት ምክንያት ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡


በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አጠቃላይ 85 የግጭት አደጋዎች የደረሱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 27 የሚሆኑት በቀለበት መንገድ ላይ ሲከሰቱ 58 የግጭት አደጋዎች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ ያጋጠሙ ናቸው፡


በግጭት አደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው የመንገድ መሰረተ ልማቶች መካከል በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ተገዝተው በምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ በተተከሉ የመንገድ መብራት ምሶሶዎች ፣ የትራፊክ ምልክቶች ፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች ፣የእግረኛ መከላከያ አጥሮች ፣ የመንገድ ማካፈያ ግንቦች እና የማንሆል ክዳኖች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡


ከዚህ በተጨማሪ በእግረኛ መንገዶች ላይ የግንባታ ተረፈ ምርቶች ማከማቸት ፣ህገወጥ የመንገድ ላይ ንግድ እንዲሁም አሽከርካሪዎች ከግንባታ ሳይቶች ሲወጡ ጎማቸውን በአግባቡ ሳያፀዱ ወደ መንገድ በመውጣታቸው የአስፋልት መንገዱን በጭቃ እና በግንባታ ተረፈ ምርት በከፍተኛ ደረጃ በማበላሸት የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡


ባለስልጣኑ በተሸከርካሪዎች ግጭት ምክንያት የመንገድ ሀብቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት በመጠገን ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እንዲያስችለው ከግጭት አድራሾችና ከሌሎች የአገልግሎቶች ክፍያዎች ተመጣጣኝ የጉዳት ካሳ ለመሰብሰብ ችሏል፡፡

በመሆኑን መንገድ የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀብት በመሆኑ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት የሁሉም ህብረተሰብ ጉዳት መሆኑን በመረዳ በእኔነት ስሜት የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል የመንገድ መሰረተ ልማቶች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ የበኩላችንን ሀላፊነት እንወጣ ሲል ባለስልጣኑ የዘወትር መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

31 Oct, 09:17


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ - ክፍል አንድ

ሀገራዊ ሪፎርምን በተመለከተ

በተለያዩ ዘርፎች ሲከናወኑ የነበሩ ሪፎርሞችን አጠናቀን ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዘመን የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ተገኝተናል፡፡ በመሆኑም በ2017 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ የምናስመዘግብ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ከትናንት እሳቤ ወጥተን በጋራ ወደ ነገ መሻገር አለብን፡፡

ኢኮኖሚያዊ እድገትን በተመለከተ

በ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ስኬት ነው፡፡ በዘንድሮው በጀት ዓመትም 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም ውስጥ ግብርና 6 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚያደግ የሚጠበቅ ሲሆን፤ 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል፡፡

የሌማት ትሩፋትን በተመለከተ

የሌማት ትሩፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ እድገት የተመዘገበበት ዘርፍ ሆኗል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት ምርቶች የ5 ነጥብ 4 በመቶ እድገት የሚያስመዘግቡ ሲሆን፡፡ ለአብነትም በወተት ብቻ በዓመቱ 12 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት ይጠበቃል፡፡ በዓመቱ 8 ቢሊዮን የዶሮ እንቁላል እንዲሁም 218 ሺህ ቶን ስጋ እና 297 ሺህ ቶን ማር ምርት ለማምረት የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል፡፡

የቡና ምርትን በተመለከተ

በቡና ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጻር 1 ሚሊዮን ኩንታል የምርት እድገት ተመዝግቧል፡፡ አሁን ላይ ኢትዮጵያን በዓለም ላይ 2ኛ ቡና አምራች ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት ከፍተኛ ስራ ተከናውኗል፡፡ በተለይ ከኃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የተሻል ስራ የተከናወነ ሲሆን፤ አሁን ላይ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 67 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡ የኢንዱስትሪ ዘርፉም በተያዘው በጀት ዓመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በተመለከተ

በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ ይህ አዲስ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያም በዓመት ከ100 አስከ 130 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተነናግዳል፡፡ አሁን ላይ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለማግዛት አዘናል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ባለቤት ብቻ ሳይሆን ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ተቋም ያደርገዋል፡፡ ይህ ለውጥ በተለይ በአገልግሎት ዘርፍ ለማስመዝገብ የተያዘውን ውስጥ ለማሳካት ሚናው የጎላ ነው፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም የአገልግሎት ዘርፉ 7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ

የኢኮኖሚ ስርዓታችን እጅግ የተዘጋ ነበር፡፡ ይህም በወጪ ንግድ፡ በተኪ ምርቶች፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመት ላይ ኢትዮጵያ መጠቀም ያለባትን ያህል እንዳትጠቀም አድርጓት ቆይቷል፡፡ ከዚህ አኳያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን መሰረት የሚጥል ነው፡፡

የመንግስት ገቢን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመንግስት ገቢ በእጅጉን ጨምሯል፡፡ ባላፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የተሻለ እድገት የተመዘገበበት ነው፡፡ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ 109 ቢሊዮን ብር ብቻ ነበር፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት አንጻር አሁንም ዝቅተኛ ገቢ የምትሰበስብ ሀገር ናት፡፡ ይህ በቀጣይ መሻሻል አለበት፡፡

የወጪ ንግድን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ባላፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡በዚህ አፈጻጸም ከቀጠልን በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል፡፡ ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ1 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አለው፡፡ በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ይህም የወርቅ ምርት ምን ያህል ለህገ ወጥ ንግድ ተጋልጦ እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡ በቡና ምርትም በበጀት ዓመቱ 2 በሊሊዮን ዶላር ገቢ ይጠበቃል፡፡

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ6 ነጥብ 4 በመቶ አድጓል፡፡በተለይ ለኢንቨስትመንት ምቹ ከባቢ በመፍጠር ረገድ የተከናወኑ ስራዎችም ኢንቨስትመንት ለመሳብ ትልቅ አቅም እየፈጠሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያላት መሬትና ታዳሽ ኃይል፣ እንዲሁም የሰው ሃይል ለኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውም ይህን የኢንቨስትመንት አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል መንገድ ከፍቷል፡፡

የውጭ ሃብት ፍሰትን በተመለከተ

ባላፉት ሶስት ወራት በተለያየ መንገድ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር መጥቷል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ተመዝግቦበታል፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ሃብት 400 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡ በአጠቃላይ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው 27 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ይጠበቃል፡፡

የእዳ ጫናን በተመለከተ

ባላፉት ስድስት ዓመታት መንግስት ምንም አይነት የንግድ ብድር አልወሰደም፡፡ የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ጥቅል ምርት አንጻር ከነበረበት ከ30 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ በሚቀጥሉት ዓመታትም ይህን አሃዝ ከ10 በመቶ በታች ዝቅ ለማድረግ ይሰራል፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት አየር መንገድና ቴሌን ሳይጨምር 13 ቢሊዮን ዶላር እዳ ተከፍሏል፡፡ ይህም እዳን ሳይሆን ለትውልዱ ምንዳን ለማውረስ የምናደርገውን ስራ የሚያግዝ ነው፡፡

ባንኮችን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከመፍረስ የታደገ ነው፡፡ ፡፡ በሪፎርሙ ባንኩ 900 ቢሊዮን በር የተራዘመ ቦንድ አግኝቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስኬታማ መሆን ደግሞ ሁሉንም የሀገር ውስጥ ባንኮች የሚያነቃቃ ነው፡፡አሁን ላይ የባንኮች ተቀማጭ ሃብት 3 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፡፡ የባንኮች ቁጥርም 32 የደረሰ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን ደንበኞች የሞባይል ባንክ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ

የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት መቅረፍ የምንችለው ምርታማነትን በመጨመር ነው፡፡ የንግድ ስርዓቱን ማዘምንም ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡ የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት ከ300 እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መድቧል፡፡ ማዕድ ማጋራት፣ ትምህርት ቤት ምገባ እና እሁድ ገበያ መንግስት አቅመ ደካሞችን ለማገዝ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም 249 ሺህ አቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ይህ መንግስት ባለሃብቶችን በማስተባበር ያከናወነው ስራ ነው፡፡ የዋጋ ንረቱ አሁን ላይ ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፤ ይህን ወደ ነጠላ አሃዝ ማውረድ የመንግስት ቀዳሚ ትኩረት ነው፡፡

የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ

AACRA

31 Oct, 09:17


በተያዘው በጀት ዓመት ለ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ተይዟል፡፡ከዚህም ውስጥ 700 ሺህ ለሚሆኑት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለመፍጠር እቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ባለፉት ሶስት ወራት ለሰለጠኑ ለ100 ሺህ ዜጎች በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ተፈጥሯል፡፡ ኮዲንግ እና የመረጃ ትንተናን ጨምሮ በርቀት ስራዎች ደግሞ ለ26 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡


#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia

AACRA

30 Oct, 13:32


በመገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ ተጀመረ፡፡

AACRA

30 Oct, 06:31


ባለፉት 3 ወራት ውስጥ ከ268 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት ተከናውኗል

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሃብት ደህንነት ለማረጋገጥና የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከ268 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳትና የእድሳት ስራዎች አከናውኗል፡፡

ባለሥልጣኑ በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ 3 ወራት ውስጥ 211.1 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመሮችን የፅዳት ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ 268.3 ኪሎ ሜትር በማከናወን ከዕቅዱ በላይ ለማሳካት ችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

29 Oct, 11:58


በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ497 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል

• አፈፃፀሙ ከ2016 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ61 በመቶ ብልጫ አለው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 262 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች ለመስራት አቅዶ 497 ኪሎ ሜትር በማከናወን ከዕቅዱ በላይ ማሳካት ችሏል፡፡

በሩብ ዓመቱ ከ52 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተገነቡ መንገዶችን ጨምሮ፣ 8.7 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 2.76 ኪሎ ሜትር የጠጠር እና 27.45 ኪሎ ሜትር የኮብል ንጣፍ መንገድ ስራዎች ይገኙበታል፡፡

በሌላም በኩል፤ ነባር የእግረኛ መንገዶችን ለማዘመን 12.1 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ የመልሶ ግንባታ ስራ ከመከናወኑም በተጨማሪ፣ 1.57 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የዝናብ ውሀ መፋሰሻ መስመር ግንባታ፣ 0.35 ኪሎ ሜትር የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኮብል ስቶን መንገዶች የሰብ ቤዝ ዝግጅት ስራ ተካሂዷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 22.16 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 2.27 ከ.ሜ የጠጠር፣ 0.42 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ መከለያ አጥር ስራ፣ ከ268 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት፣ 1.28 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ዕድሳትና ጥገና፣ 3.38 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ባለስልጣኑ 145.38 ኪሎ ሜትር የሚሆን በአዲስና ነባር የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የእግረኛ መከላከያ አጥር የቀለም ቅብ ስራ እና 1.51 ኪሎ ሜትር ለሌሎች የመሰረተ ልማት የማሻሽያ ስራዎች ሲባል የተቆረጡ መንገዶች መልሶ በመጠገን፤ በድምሩም 444.75 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራዎችን በሩብ ዓመቱ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
በሌላም በኩል፤ 2 ሺህ 928 የመንገድ መብራት ፖል እና አምፖል ጥገና ስራዎች በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ የሚካተቱ የመንገድ ጥገና ተግባራት ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

29 Oct, 06:41


ለአንድ ወር በቆየው ልዩ የመንገድ ጥገና የዘመቻ ስራ እና በሌሎች የመንገድ መሠረተ-ልማት መስኮች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የሥራ መሪዎችና ሰራተኞች የእውቅና አሰጣጥ መርሃ-ግብር በምስል

AACRA

25 Oct, 07:19


የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሚኒባስ መኪና እና ባለአራት ተካፋች ፒክአፕ ኪራይ ጨረታ

AACRA

25 Oct, 07:19


የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሚዲባስ ተሽከርካሪ ኪራይ ጨረታ

AACRA

24 Oct, 06:52


የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች አዲስ ልሳን ጋዜጣ፤ በጥቅምት 9 2017 ዓ.ም እትሟ የመንገድ ተደራሽነት ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ላይ ትኩረት አድርጋለች፤ እንድታነቡ እንጋብዛለን፡፡

AACRA

22 Oct, 13:19


የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች አዲስ ልሳን ጋዜጣ፤ መስከረም 25 2017 ዓ.ም እትሟ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ደረጃ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትን ቃኝታለች ፤ እንድታነቡ እንጋብዛለን፡፡

AACRA

22 Oct, 11:17


የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ማራዘሚያ ማስታወቂያ

AACRA

20 Oct, 10:42


የቦሌ ሆምስ - ጎሮ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 85 በመቶ ተከናውኗል

   
የአዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ ከቦሌ ብራስ የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ጀምሮ በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ጎሮ አይ.ሲ.ቲ ፓርክ እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክት  85 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡


ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 4.9 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ   የውል ዋጋ እየተገነባ ይገኛል፡፡


ቀደም ሲል ከቦሌ ብራስ የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ጀምሮ 1.3 ኪ.ሜ የሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ንጣፍ ስራ ተከናውኖ በከፊል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም ይታወቃል፡፡


አሁን ላይ ከቦሌ ጉምሩክ ጀምሮ እስከ ጎሮ ባለው ቀሪ የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል በመከናወን ላይ የሚገኘው የሰብ ቤዝ፣ ከርቭ ስቶን፣ የድልድይ፣ የከልቨርት ቦክስና የድጋፍ ግንብ ስራ ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም ከቦሌ ኤርፖርት ካርጎ ተርሚናል ፊት ለፊት ወደ ገርጂ ሮባ ዳቦ በሚያስወጣው እና 600 ሜትር ርዝመት ባለው የመንገድ ፕሮጀክቱ ሌላው ክፍል፣ የከርቭ ስቶን እና የሰብ ቤዝ ስራ በከፊል ተጠናቆ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ተደርጓል፡፡


በቅርቡም ቀሪ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን የአስፋልት፣ የእግረኛና ቀሪ የስትራክቸር ስራዎች ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡


የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከቱሉ ዲምቱ የክፍያ መንገድ አቅጣጫ በጎሮ በኩል ወደ መሃል አዲስ አበባ ለሚገቡ ተሽከርካሪዎች፣ እንዲሁም ከአይ.ሲ.ቲ ፓርክ ወደ አራብሳ እየተገነባ ከሚገኘው ሌላኛው የመንገድ ፕሮጀክት ጋር ተሳስሮ አቋራጭና አማራጭ መንገድ ሆኖ የሚያገለገል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

19 Oct, 14:20


ከሾላ ገበያ ወደ ሃያ ሁለት የሚወስድ አቋራጭ መንገድ ግንባታ በመከናወን ላይ ነው


አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አጫጭር እና አቋራጭ መንገዶችን በራስ ኃይል በመገንባትና በየአካባቢው የሚገኘውን የመንገድ መረብ ይበልጥ በማስተሳሰር የተሻለ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል እየሰራ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች እያከናወናቸው ከሚገኙ የዋና ዋና መንገዶች ግንባታ በተጨማሪ፤ አቋራጭ መንገድ እየገነባ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ውስጥ በመገንባት ላይ የሚገኘው መንገድ ይጠቀሳል፡፡

ከአድዋ አደባባይ ወደ መገናኛ የሚወስደውን ዋና መንገድ - በሃያ ሁለት አካባቢ ካለው የመንገድ ኔትወርክ ጋር በአጭር ርቀት ለማስተሳሰር፣ ሃያ ሁለት አካባቢ ከሚገኘው ኬብሮም ፋርማሲ ወደ ዮናስ ሆቴል የሚወስደው መንገድ የእግረኛ መንገድን አካቶ እየገነባ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በራስ አቅም የሚገነባው ይህ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የእግረኛና የአስፋልት መንገዱን ጨምሮ በአጠቃላይ 530 ሜትር ርዝመት እና 15 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡

አሁን ላይ የገረጋኒቲ ሙሌት፣ የማንሆል፣ ሰቤዝ እና ተያያዥ ስራዎች በመከናነወን ላይ ሲሆን፣ በቀጣይ የአስፋለት ማንጠፍ ስራው የሚከናወን ይሆናል፡፡

የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ነዋሪዎች የመውጫ እና የመግቢያ የመንገድ ችግር ከመቅረፉ በተጨማሪም፣ ከሃያ ሁለት ወደ ሾላ ገበያና ተቃራኒ አቅጣጫ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች አማራጭ መጋቢ መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

AACRA

18 Oct, 06:46


ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 ቀን 2017ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር ከነሃሴ13 እስከ ጥቅምት 7 ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ፤ ባለሥልጣኑ ለሚያከናውናቸው መጠነ ሰፊ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች የመፈፀም አቅም ለማሻሻል ከኢንስትቲዩቱ ጋር በመተባበር በተለያዩ ጊዚያት የሰራተኞች የስራ ክህሎት የሚያዳብሩ በርካታ ስልጠናዎች እንደተሰጡ አስታውሰዋል፡፡


ኢንጅነር ሙህዲን አያይዘውም በተያዘው በጀት ዓመት ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመት ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር ለ48 ቀናት፣ በ16 የስልጠና ርዕሶች 770 ለሚሆኑ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠቱ ምስጋናቸው አቅርበዋል፡፡


በቀጣይም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ አቅምና ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር የሠራተኞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ተከታታይ ሥልጠናዎችን መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በስልጠና የሚያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር እንዲለውጡ ዋና ዳይሬክተሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመት ኢንስቲቲዩት የግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ዳዊት መሀሪ በበኩላቸው ኢንስቲቲዩቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና በምህድስና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያተኞች ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ለማጣጣም የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡


ኢንጅነር ዳዊት አክለውም በቀጣይ ኢንስቲቲዩት ከባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር በተለያዩ የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ የአሰልጣኞችንና የስልጠና ማቴሪያል ወጪ በመሸፈን ስልጠናውን ሲሰጥ ለቆየው ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመት ኢንስቲቲዩትና ለአዚማን ሆቴል የምስጋና የምስክር ወረቅት በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ተበርክቶላቸዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

10,006

subscribers

3,407

photos

49

videos