Ministry of Labor and Skills - Ethiopia @fdre_mols Channel on Telegram

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

@fdre_mols


FDRE, Ministry of Labor and Skills

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia (English)

Welcome to the official Telegram channel of the Ministry of Labor and Skills in Ethiopia! With the username @fdre_mols, we are dedicated to providing you with the latest updates, information, and resources related to labor and skills development in Ethiopia. Our channel serves as a platform for communication, collaboration, and knowledge sharing among stakeholders in the labor and skills sector. Who are we? The Ministry of Labor and Skills is the government body responsible for overseeing labor policies, regulations, and programs to promote decent work and enhance skills development in Ethiopia. We work towards creating a conducive environment for sustainable employment, skills training, and vocational education to support economic growth and social development in the country. What do we do? Through our Telegram channel, we keep our subscribers informed about upcoming events, job opportunities, training programs, and policy announcements related to labor and skills development. We also share relevant research findings, best practices, and success stories to inspire and empower individuals to pursue rewarding careers and contribute to the growth of the labor market in Ethiopia. Why should you join us? By joining our Telegram channel, you will have access to valuable insights, resources, and networking opportunities that can help you stay ahead in the labor market and enhance your skills for future employment opportunities. Whether you are a job seeker, employer, educator, or policy maker, our channel offers something for everyone interested in the field of labor and skills development. Get connected with us today on @fdre_mols and be a part of our growing community of professionals, experts, and enthusiasts dedicated to shaping the future of work and skills in Ethiopia. Together, we can build a more inclusive, sustainable, and resilient labor market that benefits all stakeholders. Join us now and let's work towards a brighter future for labor and skills in Ethiopia!

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

14 Nov, 08:22


ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር አካባቢን በደንብ ማየትን፣ በጆሮ ብቻ ሳይሆን በልብ ማዳመጥን እና በጋራ መስራትን ይጠይቃል።

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

‹‹ክህሎት ኢትዮጵያ ›› 2ኛው  ሀገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል።

መርሃ ግብሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌድሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና  ኢኒስቲትዩት እና ከኢንተርፕሪነርሺፕ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

ችግር ፈቺና መፍትሔ አመንጪ የፈጠራ ውጤቶችን  የማምረት  ዓላማ ባለው በዚህ መድረክ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎ፣ የዘርፉ ባለድርሻና አጋር አካላት ተገኝተዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት  ‹‹ክህሎት ኢትዮጵያ›› የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ የዓለም ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ የሆነችውን ኢትዮጵያ ክብር  የሚመልሱ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች የሚፈሩበት መርሃ ግብር ነው፡፡


ኢትዮጵያ ስልጣኔን ለዓለም ያሳየች ሀገር ነች ያሉት ክብርት ሚኒስትር ይህንን ገናናነት መመለስ የሚችሉ ወጣቶች አሉን።

ይህም ብሔራዊ ቁጭት፣ ያለን የልማት ፀጋ እና የመለወጥ ፍላጎት ለመርሃ ግብሩ መጀመር ገፊ ምክንያት እንደሆነም ጠቁመዋል።

እንደ ሀገር ያሉ ችግሮች ለሥራና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዕድሎች ናቸው። ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር አካባቢን በደንብ ማየትን፣ በጆሮ ብቻ ሣይሆን በልብ ማዳመጥን እና በጋራ መስራትን እንደሚጠይቅም አመላክተዋል።

ይህም ብርታትን፣ ጽናትን፣ ሥራ ወዳድነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣ የዜጎች ህይወት የመቀየር ፍላጎትን እና መሰጠትን ይልጋል ብለዋል።

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ህዳር 5፤ 2017

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

13 Nov, 08:17


ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ መርሃ ግብር ዛሬ ይጀምራል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና የአንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ ይጀመራል፡፡

መርሃ ግብሩ "ክህሎት ኢትዮጵያ" በሚል ስያሜ የሚካሄድ ነው፡፡

መርሃ ግብሩ ከመላ ሀገሪቱ የተወጣጡ ተሰጥኦና ፍላጎቱ ያላቸው ወጣቶች በአንድ ማዕከል ተሰባስበው የቴክኖሎጂ ፈጠራ አቅማቸውን የሚያሳድጉበት እና ከውጪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን የሚተኩ፣ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሰሩ የሚደገፉበት ነው፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ህዳር 04፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

12 Nov, 06:57


የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያው ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

ይህ የተገለፀው በ5ኛው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሥራ ኤክስፖ አፈፃፀምና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት በተደረገበት መድረክ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ ቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱን ሥራ አጠናክሮ ከማስቀጠል ባሻገር የሥራ ፈጠራ ስነ-ምህዳሩን ማስፋት የሚያስችሉ ጉዳዮችን በዝርዝር ተነስተዋል፡፡

በዚህም ቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ የርቀት የሥራ መስክን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያሉ እድሎችን አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

በዚህም የግሉ ዘርፍ ሚናውን እንዲወጣ የማስቻል፣ ማነቆዎችን በመፍታት እና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዜጎችን ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የደረጃ ዶት ኮም እና የኢትዮ ጆብስ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ህዳር 03፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

10 Nov, 08:27


በሀገራችን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በፍጥነት እያደገ የሚገኝ በመሆኑ የብየዳ ሙያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተፈላጊ ነው፡፡

ዶ/ር ብሩክ ከድር
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዋና ዳይሬክተር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም በሆነው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ስር በሚገኘው የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የብየዳ ስልጠኞች ተመረቁ፡፡

በምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በሀገራችን በፍጥነት እያደገ የሚገኝ በመሆኑ የብየዳ ሙያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተፈላጊ መሆኑን ጠቁመው የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ጉልህ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
https://www.facebook.com/share/p/1ASmNUo4uz/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

08 Nov, 10:54


ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሥራ ፈላጊ  አልምቶ ለሥራ ገበያው ለማብቃት  የመንግስትና የግል ዘርፍ ጥምረት ወሳኝ ነው።

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከደረጃ ዶትኮምና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው  5ኛው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሥራ ኤክስፖ ተጠናቋል።

በማጠቃለያ መድረከኩ ላይ  የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር እንደመሆኗ  ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሥራ ፈላጊ  አልምቶ ለሥራ ገበያው ለማብቃት የመንግስትና የግል ዘርፍ ጥምረት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ሀገራችን የምትፈልገውን በክህሎት የበቃ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጠውን ሥልጠና ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ስልጠና አጠናቃቂዎች በሥራ ገበያው ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነት በማጎልበት ብቁ እንዲሆኑ ከማስቻል አኳያ ኢንዱስትሪዎች የራሳቸውን ሚና መጫወት እንደሚኖርባቸውም ገልፀዋል፡፡

በልምድ የሙያ ባለቤት የሆኑ ዜጎችን በምዘና ብቃታቸውን በማረጋገጥ ዕውቅና የመስጠት አሠራር ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። 

ይህም በዜጎች የራስ መተማመንና ውጤታማነት ላይ ጉልህ ለውጥ የሚያመጣ በመሆኑ ኢንዱስትሪዎች የሰው ኃይላቸውን በማስመዘን ምርታማነታቸውን በማሳደግ የጋራ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያልቁ ጥሪ አቅርበዋል። https://www.facebook.com/share/p/15PgN2x33v/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

08 Nov, 07:35


ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ጅምር ሥራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራ ፣ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) የጋራ ትብብር የተዘጋጀው ውጤታማ የሥራ ላይ ልምምድ እና ትግበራ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄዷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሥራ ፈላጊዎች በኢንዱስትሪው ውስጥ ተግባራዊ ክህሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ የአሰራር ሥርዓትን ለመዘርጋት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ቀደም ብሎ የሥራ ላይ ልምምድ መመሪያ ማፅደቁን የገለፁት ክቡር አቶ ሰለሞን ይህ መመሪያ በዓለም የሥራ ድርጅት የሥራ ላይ ልምምድ ጥራትን አስመልክቶ ካስቀመጠው ምክረ ሃሳብ ጋር ተናባቢ መሆን እንደሚኖርበት ጠቁመዋል፡፡

ይህ ተናባቢነት የሥራ ልምምዱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ለተለማማጅ ሰልጣኞች እሴት አካይ የሆነ ልምድ እንዲያገኙ ዕድል የሚሰጥ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በመድረኩ የዓለም የሥራ ድርጅት ከአሠሪዎች ፌዴሬሽንና ከመንግስት ጋር በመተባበር ‹‹ፕሮ አግሮ›› በተሰኘው ፕሮጀክቱ በዶሮ እርባታ ዘርፍ 200 የሚሆኑ ወጣቶች እንዲሁም ‹‹ፕሮስፔክት›› በተሰኘው ፕሮግራሙ በብየዳና በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዘርፍ 300 የሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የሥራ ገበያው በሚፈልገው ደረጃ ሰልጣኞችን ለማብቃት የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን መደገፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሂደት መሆኑን የጠቀሱት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ሚኒስትር መ/ቤቱ በዚህ ዙሪያ የተሠማሩ አካላትን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

በመድረኩ የዓለም የሥራ ድርጅት፣ የኢኖቬሽንነና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአይ ሲ ቲ ፓርክ፣ የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽንን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ እና አጋር አካላት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 29፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

04 Nov, 08:28


በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የዲጂታል አቅምዎን ያሳድጉ! ተጠቃሚነትዎን ያስፉ!

5 #ሚሊዮን_የኢትዮጵያ_ኮደርስ_ለምን?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ዓለም ዜጎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘመን ክህሎቶችን ለማስታጠቅ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋ የተደረገ መርሃ ግብር ነው?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በዲጂታሉ ዓለም ጊዜውን የዋጀ እውቀትና ክህሎት በመታጠቅ ራሳቸውንና ሀገራቸውን መቀየር የሚፈልግ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስልጠናውን በነፃ መከታተልና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡

#እንዴት_መመዝገብ_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የሚሰጠውን ሥልጠና ለመከታተል ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ተመዝግበው አሁኑኑ ስልጠናዎን መጀመር ይችላሉ፡፡ www.ethiocoders.et

#የዲጂታል_ሥራዎች_እንዴት_ማግኘት_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ በዲጂታል ክህሎት መሰረታዊ እውቀትና ክህሎት ኖሯቸው በኦን ላይን የሚመጡ የሥራ ዕድሎችን ለመጠቀም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et)ላይ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡

እስካሁን በስርዓቱ ከመጡ ከ85 ሺህ በላይ የኦን ላየን ሥራ (Remote Job) ዕድሎች ከ26 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 25፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

02 Nov, 11:27


የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይኖርብናል፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች የዘርፊን አፈፃፀም ለማላቅ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የምክክር መድረኩን አጠናቋል፡፡

የማጠቃለያ መድረኩ ላይ "Perspective" በሚል ርዕሰ በዘርፉ ትልቅ ልምድና ተሞክሮ ባለው ዶ/ር ለማ ደገፋ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ ዘርፉ ሀገር ብዙ የምትጠብቅበት በመሆኑ ሥራ አጥነትን ጨምሮ የዘርፉ አንገብጋቢ ችግሮችን ለመቅረፍ አዲስ ዕይታና ልዩ ተነሳሽነት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በየዓመቱ በርካታ ዜጎች ሥራ ፈላጊ ሆነው እየመጡ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር አቶ ሰለሞን በሥራ ፈላጊው ልክ ረጅም ርቀት መሄድና አንገብጋቢነቱን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

የዘርፉን አፈፃፀም ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የተቀናጀ ሥራና አዲስ ዕይታ መከተል ይገባል።

በቀጣይ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ግብዓትና ግብይት ላይ እንዲሁም የቤተሰብ ቢዝነስና የማህበረሰብ አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

ተቋማዊ ግባችንን ለማሳካት ሁሉንም አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ የጠቆሙት ክቡር አቶ ሰለሞን በየደረጃው በቅንጅት እንዲሠራ አሳስበዋል።

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 23፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

31 Oct, 16:30


በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ጥሩማር አባቴ የተመራ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት የሪፎርም ትግበራ ሂደት የልምድ ልውውጥ አካሂደ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ጥሩማር አባቴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሪፎርም ትግበራው አኳያ የሄደበት እርቀት እጅግ የሚደነቅና ጥሩ ግብዓት ያገኘንበት ነው ብለዋል፡፡

በተለይ መደበኛ ሥራውንና የሪፎርም ሥራውን ጎን ለጎን በተቀናጀ መንገድ የተመራበት መንገድ እጅግ አስተማሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሪፎርም ትግበራ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው፤ ሚኒሰቴሩ በቅርቡ ተደራጅቶ ወደ ሥራ የገባ በመሆኑ አዲሱን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያከናወነ የሚገኘው አዲሱ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ትግበራ ሂደትን ከመጀመሪያው ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ ድረስ የተከናወኑ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች ላይ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በሪፎርም ሥራው የተከናወኑ እና የተጠናቀቁ ሥራዎችም የኮሚቴ አባላቱ ተዘዋውረው ተጎብኝተዋል፡፡

ጥቅምት 21፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

31 Oct, 09:22


የማንሰራራት ዓመት

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

31 Oct, 08:21


የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ 100 ቢሊዮን እንዲደርስ ማቀድ አለብን”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ በሚቀጥሉት ዓመታት 50 እና 100 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ አለብን ሲሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ማኒስትሩ በማብራሪያቸው ባለፉት ሶስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ ያገኘነውን የወጪ ንግድ ገቢ ማስቀጠል ከቻልን በዓመት ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ልናስገኝ እንችላለን

የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ በሚቀጥሉት ዓመታት 50 እና 100 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ አለብን፡፡

ኢትዮጵያ ከነበረችበት የወጪ ንግድ ገቢ የተሻሻለች ቢሆንም መድረስ ካለባት ግብ አልደረሰችም ብለዋል፡፡
ጥቅምት 21፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

31 Oct, 08:06


በተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ የሚገኙት ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር ተጨባጭ እመርታ እያሳየ እንደሚገኝ የሚያመለክቱ የሚከተሉትን ተጨባጭ ማሳያዎች አንስተዋል፡-
• 3.4 ቢሊዮን ዶላር ዶላር በእርዳታና በብድር ተገኝቷል፤
• የፋይናነስ ሴክተር አጠቃላይ ሀብት 3.5 ተሪሊዮን ብር ደርሷል፤
• 50 ሚሊዮን ሰዎች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ሆነዋል፤
• 13ሺ የባንክ ቅርንጫፎች ተከፍተዋል፤
• 50 ቢሊዮን ብር ብድር ለዜጎች ተደራሽ ተደርጓል፤ ከዚህ የገንዘብ መጠን ውስጥ 15 በመቶ ለአነስተኛና መካከለኛ ቢዝነሶች የቀረበ ነው፡፡
ጥቅምት 21፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

30 Oct, 20:41


በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የዲጂታል አቅምዎን ያሳድጉ! ተጠቃሚነትዎን ያስፉ!

5 #ሚሊዮን_የኢትዮጵያ_ኮደርስ_ለምን?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ዓለም ዜጎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘመን ክህሎቶችን ለማስታጠቅ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋ የተደረገ መርሃ ግብር ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ዜጎች በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በአንድሮይድ ልማት መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ በማድረግ ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ጊዜ እንዲዘጋጁ የሚያደርጋቸውን ስልጠና በነፃ ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

በ5 #ሚሊዮን_የኢትዮጵያ_ኮደርስ_ማን_መመዝገብ_ይችላል?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በዲጂታሉ ዓለም ጊዜውን የዋጀ እውቀትና ክህሎት በመታጠቅ ራሳቸውንና ሀገራቸውን መቀየር የሚፈልግ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስልጠናውን በነፃ መከታተልና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡  

#እንዴት_መመዝገብ_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የሚሰጠውን ሥልጠና ለመከታተል ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ተመዝግበው አሁኑኑ ስልጠናዎን መጀመር ይችላሉ፡፡ www.ethiocoders.et

#የዲጂታል_ሥራዎች_እንዴት_ማግኘት_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ በዲጂታል ክህሎት መሰረታዊ እውቀትና ክህሎት ኖሯቸው በኦን ላይን የሚመጡ የሥራ ዕድሎችን ለመጠቀም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et)ላይ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

29 Oct, 11:09


#የገጠር_ኮሪደር

ጽዱ አካባቢ፣ ጤናማ ሕይወትና አምራች ዜጋ ለሀገራዊ ልዕልና!

የገጠር ኮሪደር ማለት የእያንዳንዱን አርሶ አደር ቤት እና የአኗኗር ዘዬ መቀየር ነው። አላማውም በቤተሰብ ደረጃ የአርሶ አደሩን ሕይወት በመቀየር እንደ ሀገር የምናስበውን ብልጽግና ማረጋገጥ ነው።

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

28 Oct, 20:12


352ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት የበላይ አካል (Governing Body) ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ትልቅ መድረክ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

በጄኔቫና ኦስትሪያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው እና ሌሎች የቴክኒክ ባለሙያዎችም ሃገራችን በመወከል በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና አሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አኳያ ተቀርፀው ተግባራዊ በተደረጉ የሪፎርም ሀሳቦች ማህበራዊ ፍትህን በማንገስ ዘላቂ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅትን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ተቀራርባ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡

ባሳለፈው ዓመት በጄኔቭ በተካሄደው 112ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሥራ ድረጅት ምክትል የበላይ አካል (ILO governing body) ሆና መመረጧ ይታወሳል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 18፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

28 Oct, 07:51


#አሁን
#HappeningNow

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡ ፡

በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በማክሮ ኢኮኖሚው ሪፎርም ስኬቶችና አዝማሚያዎች ላይ ለውይይት መነሻ ሰነድ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው፣ በማክሮ ኢኮኖሚው ረፎርሙ ስኬቶች እና አዝማሚያዎች ላይ ሁሉም ተቀራራቢ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ የመድረኩ ዓላማ እንደሆነ የጠቀሱት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይ ለማክሮ ኢኮኖሚው ሪፎርም ስኬት አመራርና ሠራተኛው ከተቋማሙ ተልዕኮ አኳያ የበኩሉን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 18፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

28 Oct, 03:16


በክልሉ ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ እየተሠራ ነው።

ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር

የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አስታወቁ፡፡

የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት በክልሉ ዘላቂ፣ አስተማማኝና ፍትሐዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑ ተናግረዋል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራ በቅንጅት የሚሠራ እንጂ በአንድ አካል ብቻ የሚከናወን አለመሆኑን በመገንዘብ በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮች እና የዘርፉ ኃላፊዎች ለዘርፉ ስኬት ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር እና የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ገብረ መስቀል ጫላ በመድረኩ ላይ በበኩላቸው ÷ የሥራ ዕድል ፈጠራ የኢኮኖሚ ሥርዓት ጤነኝነት ማስጠበቂያ ነው፡፡

ሁሉም ሥራ የሚፈልጉ ዜጎች ስልጠና እንዲያገኙ የማድረግ ክኅሎት መር ተግባር እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጴጥሮስ ወልደ ማሪያም ÷ በዞኑ ባለፉት ሦስት ወራት ከ105 ሺህ 559 በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ተለይተዋል ብለዋል፡፡

በዚህም 1 ሺህ 763 ሔክታር መሬት በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ወጣቶች መሰጠቱን እና ለ8 ሺህ 427 ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የፋና ዘገባ ያመለክታል።

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 18፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

27 Oct, 08:09


#አሁን
#HappeningNow

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላው ውይይት እያደረገ ነው፡፡

በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀም ከሁሉም ክልሎች ጋር በተናጠል ባለፈው ሳምንት መገምገሙ ይታወሳል፡፡ ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው መድረክ የዘርፎችን እና የተጠሪ ተቋማቱን ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 17፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

27 Oct, 07:25


የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች ነፃ የስልክ መሥመር ይጠቀሙ!

ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ  በውጭ ሀገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ላይ እንዲሰማሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዲስ ሥርዓት ዘርግቶ እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተ ያለዎትን ማንኛውንም ጥያቄ ወደ ☎️9138 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን!

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 17፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

27 Oct, 06:30


"ይህንን ሥራ የምሰራው ሴቶች እንደሚችሉ ለማሳየት ነው"

ወለላ ሰይድ
አሰልጣኝና ዓለም አቀፍ ዌልደር

ወለላ ሰይድ ትባላለች፡፡ የሐዋሳ ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ የብየዳ ልህቀት ማዕከል አሰልጣኝ ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ በብየዳ ክህሎት ዓለም አቀፍ ሰልጥና ወስደው እውቅና ካገኙ በጣት ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ ናት፡፡

ወለላ በተለያዩ ሀገራት ያገኘችውን ክህሎት ለወገኖቿ ለማካፋል በአሁን ወቀት በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ በሆነው በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የምህንድስና ልህቀት ማዕከል በማሰልጠን ላይ ትገኛለች፡፡

የብየዳ ሥራ እጅግ አድካሚ እና ጉልበት የሚፈልግ ሥራ ቢሆንም ሴቶች ይህንን በብቃት መወጣት አንደሚችሉ ለማሳየትም ሥራውን በፍቅር እየሰራሁ እገኛለሁ ትላለች ወለላ፡፡

በብየዳ ዘርፍ በሀገራችን ሰፊ የሆነ ክፍተት መኖሩን የምትናገረው አሰልጣኝ ወለላ ይህ በብየዳ ልህቀት ማዕከል እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ይህንን ክፍተት የሚሞላ ነው ባይ ነች፡፡

ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተውጣጡት ሰልጣኞች ስልጠናውን ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተከታትለውና ተመዝነው የክህሎት ባለቤት ይሆናሉ፡፡

ሥልጠናው ብረት ነክ በሆኑ የብየዳ ሥራዎች ላይ የሚያጋጥሙ የጥራት ጉድለቶችን የሚቀርፍ እና በየክልሉ በዘርፉ የሠልጣኞችን አቅም ለማጎልበት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑንም ወለላ ትናገራች፡፡

በተጨማሪም እነዚህ ሰልጣኞች በዚህ ስልጠና ከሶስት እስከ አስር ሴንቲሜትር የሚደርስ ውፍረት ያላቸው ብረቶች በጥራት መበየድ የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው በመሆኑ በየትኛውም የዓለም ክፍል ተቀጥረው የመስራትም ይሁን የማሰልጠን ብቃት ይኖራቸዋል ትላለች፡፡

ወላለ እና ሌሎችም በዘርፍ ዓለም አቀፍ እዉቅና ያላቸው አሰልጣኞች በአሰልጣኝነት እየተሳተፉበት በሚገኘው በዚህ ስልጠና 36 የሚሆኑ ሴት እና ወንድ ሰልጣኞች በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 17፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

26 Oct, 16:41


የሥራ ዕድል ፈጠራ በዜጎች ሁለንተናዊ ህይወት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንዲችል በትኩረት መስራት ይገባል

ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በንቅናቄ መድረኩ ባስተላለፉት መልዕት፣ የሥራ እድል ፈጠራ በዜጎች ሁለንተናዊ ህይወት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንዲችል በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ገቢ ሲጨምር ኢኮኖሚው ያድጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የሥራ ዕድል ፈጠራ በሚፈለገው ልክ ውጤት ለማስመዝገቡ በልዩ ልዩ አደረጃጀቶች በመታገዝ መስራት እንደሚገባም አመላከሰተዋል።

በቋሚነት እና በጊዜያዊነት ሥራ የሚፈጠርላቸው ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግም ጨምረው ገልፀዋል።

በስራ እድል ፈጠራ ላይ የሚሰጡ ድጋፎችን መለየት፣ማደራጀት፣ማሰልጠን የስራ ስምሪት መስጠት፣እንዲሁም የመስሪያ እና የመሸጫ ማዕከል ማመቻቸት ለዘርፉ እድገት ወሳኝ መሆኑን እንደጠቆሙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል።

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 16፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

26 Oct, 10:16


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚሰጠው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዝርዝር።

ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ!

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 16፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

26 Oct, 08:11


መድረኩ የተቀመጠውን ግብ ያሳካና ውጤታማ እንደነበር ተጠቆመ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ላለፉት አምት ተከታታይ ቀናት የሁሉንም ክልሎች የሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡

ከክልሎች ጋር በተናጥል ሲያካሂድ በነበረው የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የየክልሉና የሁለቱም ከተማ መስተዳድሮች ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዘርፉ አጣዳፊ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ በመግባቱ የዝግጅት ምዕራፍ በሚል ይባክን የነበረውን ጊዜ ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም አስችሏል፡፡

በዚህም በዘርፉ አዲስ የሥራ ባህል ከመፍጠሩም በሻገር ተጨማሪ ስኬቶችን ለማስመዝገብ አግዟል ብለዋል፡፡

ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በዚህ ዓመት ከፍተኛ ግብ እንደተቀመጠና በሩብ ዓመቱ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከ619 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉም አመላክተዋል፡፡

የተፈጠረው የሥራ ዕድል ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በውጭ ሀገር የ36 በመቶ እንዲሁም በሀገር ውስጥ የ8 በመቶ እድገት እንዳለው ገልፀዋል፡፡

በክህሎት ልማት ዘርፉ የሥልጠና ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ ምርታማ እንዲሆኑ የተጀመረው ጥረትና የተገኙ ውጤቶች፣ ከ20ሺህ በላይ ለሚሆኑ አሰልጣኖች የተሰጠው ስልጠና የፈጠረው አቅምና መነቃቃት እንዲሁም በአዲሱ እሳቤ መሰረት የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች እንደነበሩም አንስተዋል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛው ዘርፍ ከክርክር ይልቅ ምክክርን በማስቀደም ሰላማዊ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት በመፍጠር ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራዎች ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የአሠሪና ሠራተኛውን የመደራጀት ምጣኔ ለማሳደግ የተጀመረው ጥረትም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በተቋም ግንባታ የትኩረት መስኩም ተስፋ ሰጪ እና መስፋት የሚገባቸው ሥራዎች መኖራቸው የገለጹት ክብርት ሚኒስትር መድረኩ የተቀመጠውን ግብ ያሳካና ውጤታማ ነበር ብለዋል፡፡

ነገር ግን በበጀት ዓመቱ በክህሎት ልማት ሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፉ የተቀመጠው ግብ ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይ ተጨማሪ ጥረትና ርብርብ የሚፈልጉ ጉዳዮች እንዳሉ በመድረኩ ላይ መግባባት እንደተፈጠረባቸው ጠቁመዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 16፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

25 Oct, 13:46


በልምድ የተገኘ ብቃትን በምዘና ማረጋገጥና እውቅና መስጠት አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን እውን ለማድረግ ያስችላል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሲካሂድ የነበረው የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ የሀረሪ፣ የጋምቤላ እና የአፋር ክልልን አፈፃፀም በመገምገም ተጠናቋል፡፡

በአፈፃፀም ግምገማው ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የክልሎቹ ሁሉም ከፍተኛና መካከለኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በማጠቃለያ ውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዓመታዊ ግቦቻችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ የተለጠጡና ቀን ተሌት ርብርብ የሚፈልጉ ናቸው፡፡

እስካሁን ተግባራዊ የተደረጉ የሪፎርም ሥራዎች ለዚህ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ ዓመታዊ ግቡን ለማሳካት በሩብ ዓመቱ በጥንካሬና በክፍተት የተለዩትን ሥራዎች በአግባቡ ለይቶ ጥንካሬዎቹን ለማላቅ ድክመቶችን ደግሞ ለማረም የሚያስችል ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ሥራዓት ተዘርግቷል፡፡ ይህም በየደረጃው ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በልዩ ትኩረት ከሚተገበሩ ሥራዎች መካከል አንዱና ዋነኛው በልምድ የተገኘ ብቃትን በምዘና ማረጋገጥና እውቅና መስጠት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

በልምድ የተገኘ ብቃትን በምዘና ማረጋገጥና እውቅና መስጠት አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን እውን ለማድረግ ያስችላል ያሉት ክብርት ሚኒስትር የክህሎት ልማቱ ዘርፉ በየደረጃው ለሥራው ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራበት አሳስበዋል፡፡


ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 15፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

25 Oct, 04:03


አንድ አካባቢ የራሱን መለያ አንድ ምርት ይዞ በመውጣት ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር ርብርብ ማድረግ ይገባል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

አንድ አካባቢ የራሱን መለያ አንድ ምርት ይዞ በመውጣት ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡

ክብርት ሚኒስትር ይህን የገለጹት ሚኒስቴሩ የአዲስ አበባን የዘርፉን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም በገመገመበት መድረክ ላይ ነው፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በመድረኩ የሦስት ወራቱን ዕቅድ አፈፃፀም አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በዚህም የተጀመረው የተቋም ግንባታ ሥራ እስከ ታችኛው እርከን መውረዱ እና የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች በተጨባጭ መሬት መታየት መጀመራቸው የሚያበረታታ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕት፣ በከተማው ዘርፉ የተሰጠው ትኩረትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘርፎችን አዋህዶ ውጤት ለማምጣት የተደረገው ጥረት የሚያበረታታና ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆን ነው፡፡

ይህን ግለቱን አስጠብቆ ለመሄድ የዘርፉን የርብርብ ማዕከላት በአግባቡ መለየትና የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለላቀ ውጤት በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በተለይ በሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ንግድ ላይ በመሥራት ብዙዎችን መድረስ እንደሚቻልም ጠቁመዋል፡፡

የክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ ጥራትና ቀጣይነት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር ዓላማው እንደሆነ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ለግቡ ስኬት የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ንግድን ለማስፋት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህ ማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን እንደ ዋነኛ መሳሪያ መጠቀም ተገቢ እንደሆነም ነው ክብርት ሚኒስትር የገለጹት፡፡

ከቤተሰብ ጀምሮ በየደረጃው ባለው መዋቅር የሚደረገው የማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይት የየአካባቢውን ፀጋ መሰረት በማድረግ አንድ አካባቢ የራሱን መለያ አንድ ምርት ይዞ እንዲወጣ ያስችላል፡፡ ይህም ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያግዝ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

ጥራት ያለው የሥራ ዕድል በመፍጠር እንደ ሀገር ያሰብነውን ብልጽግና ለማሳካት አዲስ ከሚፈጠሩ ቢዝነሶች ባሻገር ነባር ቢዝነሶችን ማጠናከር እና ኢመደበኛ ቢዝነሶችን ወደ መደበኛ ማምጣት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 15፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

23 Oct, 17:26


የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ጋር ተወያዩ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ውይይቱ በትምህርትና ሥልጠናው ዘርፍ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂያዊ ግንኙነትን ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና በትምህርትና ስጠናው ዘርፍ የረዥም ጊዜ ትብብር እንዳላቸው የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር አሁን ላይ በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴክኒክና ሙያ ልህቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገ ያለው የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በቻይና መንግስት ድጋፍ የተሰራ መሆኑን አውስተዋል፡፡

የተጀመረው ውይይት ስትራቴጂያዊ አጋርነትን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡

የቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ሪፎርም አድንቀው በሁለቱ ሀገራት መካከል በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የነበረውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡

በቀጣዮቹ ዓመታት ዘርፉን በቴክኖሎጂና በሰው ሃይል ማጠናከርና ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዘርፉን ሪፎርም መደገፍ የሚያስችሉ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር መስኮች ተለይተው ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ከውይይቱ በኋላ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የሚገኘውን የሉባን ወርክሾፕ ጎብኝተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ከቲያንጅን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዣንግ ጂንጋንግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 13፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
ኤክስ ፡- https://x.com/Jobs_FDRE

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

23 Oct, 17:25


ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ተባለ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የክልሎች አፈፃፀም ግምገማን ቀጥሎ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የሱማሌ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኮቹ ላይ ባስተላለፉት መልዕት፣ እንደ ዘርፍ በጀት ዓመቱ በስፋትም ሆነ በይዘቱ የተለየ ሥራ የምንሰራበት እንደሆነ ተግባብተን ወደ ተግባር ገብተናል፡፡

በዚህ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ከተለመደው አሰራር የተላቀቀ አካሄድ እንዲሁም የተለየ የድጋፍና የክትትል ሥራ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በሦስቱም ዘርፎች የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የተጀመሩ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየደረጃው በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 13፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

22 Oct, 13:11


የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን የሚፈልግ መሆኑ ተጠቆ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ ቀጥሎ የሲዳማ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በዚህ ዓመት የሚደረገው የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን ይፈልጋል ብለዋል፡፡

ዜጎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከመደበኛ እና አጫጭር ስልጠናው በተጨማሪ በልምድ የተገኘ ሙያ ላይ ግብ አስቀምጦ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 12፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
ኤክስ ፡- https://x.com/Jobs_FDRE

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

22 Oct, 10:13


ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ

ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡

ክብርት ሚኒስትር ይህን የገለፁት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዘርፉን የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በተገመገመበት መድረክ ላይ ነው፡፡

ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በበጀት ዓመቱ እንደ ዘርፍ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የተቀናጀና የተናበበ ርብርብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡

በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ መሰረት ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራ ግብዓትና ግብይት መስኩ ላይ ለበርካቶች ሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚቻል የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በየደረጃው ያለውን ፀጋ መሰረት ያደረገ እና ያለውን ፍላጎት ያማከለ ሥራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 12፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
ኤክስ ፡- https://x.com/Jobs_FDRE

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

21 Oct, 17:40


የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የክልሎችን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀምን ግምገማን ቀጥሎ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የአማራ ክልል የዘርፉ እቅድ አፈፃፀምን ተመልክቷል፡፡

በመድረኩ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የማህበራዊ ጉዳይ እና የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ የሦስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ በዘርፉ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የተደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ ያለው የክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት የመፍጠር ሥራ የተለየ አካሄድን፣ የክትትልና ድጋፍ ሥራን የሚጠይቅ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

የተጀመሩ ስራዎችን ለማላቅ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ለክህሎት ልማት፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ድጋፎችን ለማመቻቸት የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሚደረገው ምዝገባ እንደ ሀገር ፋይዳው ሰፊ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 11፤ 2017

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

21 Oct, 12:31


የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ደ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጻ ሰጥተዋል፡፡

ዶ/ር ተሻለ በመግለጫቸው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ እንደሚዘጋጅ ገልጸው በዚህ ዓመትም የ12 ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 526,683 የሚሆኑት ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ ስልጠና ለመሰልጠን ተቋማቱን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

ገበያ ተኮር በሆኑ በአጫጭር ስልጠናዎች ደግሞ ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተቋማቱ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞች በተቋማቱ በቂ ክህሎት ታጥቀው እንዲወጡ በክረምቱ የአሰልጣኞች የአቅም ግንበናታ ስልጠና፣ የማሽነሪዎች ጥገና እና አስፈላጊ የማሰልጠኛ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ይህንን የመቁረጫ ነጥብ መነሻ አድርገው ሰልጣኞችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል፡፡

ለማህበራዊ ሳይንስ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ የተቀመጡ የመቁረጫ ነጥቦች ዝርዝር ከታች ይመልከቱ

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 11፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

21 Oct, 12:30


የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ደ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጻ ሰጥተዋል፡፡

ዶ/ር ተሻለ በመግለጫቸው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ እንደሚዘጋጅ ገልጸው በዚህ ዓመትም የ12 ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 526,683 የሚሆኑት ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ ስልጠና ለመሰልጠን ተቋማቱን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

ገበያ ተኮር በሆኑ በአጫጭር ስልጠናዎች ደግሞ ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተቋማቱ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞች በተቋማቱ በቂ ክህሎት ታጥቀው እንዲወጡ በክረምቱ የአሰልጣኞች የአቅም ግንበናታ ስልጠና፣ የማሽነሪዎች ጥገና እና አስፈላጊ የማሰልጠኛ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ይህንን የመቁረጫ ነጥብ መነሻ አድርገው ሰልጣኞችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል፡፡

ለማህበራዊ ሳይንስ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ የተቀመጡ የመቁረጫ ነጥቦች ዝርዝር ከታች ይመልከቱ

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 11፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

20 Oct, 07:35


የተቋምና የሲቪል ሰርቪስ ለውጥ ሥራዎች የእድገት ጥረታችንን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ - ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ስንተገብራቸው የቆዩት የተቋም እና የሲቪል ሰርቪስ ለውጥ ሥራዎች የእድገት ጥረታችንን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመቶ ቀን ግምገማችን ግምገማችን በተለያዩ ዘርፎች ላቅ ያሉ እድገቶች መመዝገባቸውን አሳይቶናል ብለዋል።

ይሁንና የእድገት አቅጣጫችን ከፊታችን የበለጠ ሥራ እንደሚቀረን ያመለክተናል ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሕዝብ አገልግሎቱ ዘርፍ አዲሱን የማብቃት ባሕል እንዲያሳድግ እና ሌሎችም ውጤታማ እንዲሆኑ እንዲደግፍ እጠይቃለሁ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የተቋም ግንባታ ሥራን እንደ አንድ የትኩረት መስክ በመውሰድ የተሰጠውን ተልዕኮ መሸከም የሚችል ተቋም ለመገንባት እና ተገልጋዩም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ ውጤታማ የሪፎርም ተግባራት ተከናውነዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይፋ የተደረገው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ በፓይለት ደረጃ እንዲተገበርባቸው ከተመረጡ ተቋማት መካከል አንዱ ነው፡፡

በዚህም ተቋሙ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ለማቀላጠፍ 23 ማይክሮ ሰርቪሶችን በአንድ ላይ ያቀፈውን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓትን ወደ ሥራ ማስገባትን ጨምሮ በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 10፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

20 Oct, 05:19


በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለ619 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል ተፈጥሯል

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

18 Oct, 15:26


በተወዳዳሪዎች የቀረቡት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን የሚያመላክቱ መሆኑ ተጠቆመ

የሴቶች ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡

ለአስር ተከታታይ ቀናት በተካሄደው በዚህ ውድድር 37 ሴት የፈጠራ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ አስር ተወዳዳሪዎችም እያንዳንዳቸው የአንድ መቶ ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ የሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት የህብረተሰቡ ግማሽ አካል ከሆኑት ሴቶች ተሳትፎ ውጭ የሚታሰብ አይደለም፡፡

በመሆኑም ሴቶችን በልዩነት ለመደገፍና ለማብቃት የሚስችሉ አሰራሮች በስፋት እየተተገበሩ ይገኛ፡፡በዚህም በዲጂታል ዓለም ላይ ያላቸውን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማጎልበትን መነሻ በማድረግ ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው፤ ተወዳዳሪዎች በኢኮሜርስ፣ በትምህርት፣ በጤና በተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ይዘው የቀረቧቸው ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ማሳያ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ እየተከተለች ያለችው ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ ዲጂታላይዜሽንን የሚያበረታታ መሆኑ በዘርፉ ለተሰማሩ ዜጎች መልካም አጋጣሚ ነው፡፡

ሴቶች የዘርፉን ተለዋዋጭ፣ ኢ-ተገማችና ድንበር የለሽ ባህሪ በመረዳት ራሳቸውን ብቁ አድርገው ለመገኘት መትጋት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ከተናጠል ይልቅ በጋራ አቅምን አስተባብሮ መስራት ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ቁልፍ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማሳደግ የሚያስችላቸውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያገኙ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡

ውድድሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት፣ ከኔስት ብሔራዊ ኢኒሼቲቭ፣ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅትና ሌሎችም አጋር አካላት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

ጥቅምት 8፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
ኤክስ ፡- https://x.com/Jobs_FDRE

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

18 Oct, 07:12


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

በሩብ ዓመቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት በሚገመገሙበት በዚህ መድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ እና የዘርፉ አመራርና ሰራተኞች እየተሳተፉ ይገኛል።

በመድረኩ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎች፣ የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር በመለየት የዘርፉን ዓመታዊ ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ የቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጥቅምት 8፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_officiald

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

18 Oct, 03:37


የተናበበ ትብብር-  የተጠናከረ አጋርነት

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን  የሥራ ኃላፊዎችና የፕሮግራም አስተባባሪዎች ጋር  በሥራ ፈጠራና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት  አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተከናወኑ አበይት ተግባራትና የተገኙ ውጤቶችን እንዲሁም የዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎችን የሚያመላክት ሰነድ በክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ቀርጓል፡፡

በዚህም በሦስት ዓመታት ውስጥ በሀገር ውስጥ ከ9 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር  በውስጥ አቅም ለምቶ ወደ ሥራ በገባው የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት  ከ517 ሺ በላይ ለሆኑ ዜጎች በውጭ ሀገራት  የሥራ ዕድል  መፈጠሩ  ጠቁመዋል፡፡

ዜጎች ከሀገራቸው ሳይወጡ በውጭ ሀገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበት የርቀት የሥራ ዕድል 83ሺ ለሚሆኑ ዜጎች መፈጠሩንና 26ሺ ያህሉ በተጨባጭ ወደ ሥራ መግባታቸውን አንስተዋል፡፡

አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን የዲጂታል አማራጮችን ጭምር በመጠቀም የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ፣  ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኢምፖሪየም ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

የኢንተርፕረነርሺፕ ልማትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ችግር የሚፈቱ ሚሊዮን ኢንተርፕሪነሮችን ለማፍራት የሚያስችል ሥርዓት በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተዘረጋ እንደሚገኝም ነው ክብርት ሚኒስትር የገለጹት፡፡

በክህሎት ልማት ረገድ  ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በሰጠው ልዩ ትኩረት 7.2 ሚሊዮን ዜጎችን በአጫጭር ስልጠና ማብቃት መቻሉንም ክብርት ሚኒስትር አስረድተዋል፡፡ 

በልምድ  የክህሎት ባለቤት የሆኑ ዜጎችን በማብቃትና  እውቅና ለመስጠት የሚያስችል  ፕሮግራም በይፋ መጀመሩን  የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ፕሮግራሙ   ‹‹አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ›› በሚል መሪ ቃል ዜጎችን ለማብቃት የተያዘውን ዕቅድ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

የተቋማዊ ግንባታ ሥራውን ጥራት ለማረጋገጥ እንዲቻልም በሚኒስትር መ/ቤቱ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራርን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝም በመድረኩ ተብራርቷል፡፡

በዚህ መልኩ የተገኙ ውጤቶችን ለማላቅ የአጋር አካላት ድጋፍ  ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር  በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እየተተገበሩ የሚገኙ ፕሮግራሞችን ከሚኒስትር መ/ቤቱ እሳቤ ጋር የተቀናጀ እንዲሆኑ ለማስቻል ብሎም በተጨማሪ  መስኮች ላይ ጠንካራ ትብብር ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 8፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

16 Oct, 14:11


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የአካል ጉዳተኞችንና የሌሎችም የጋላጭ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተያዙ  ዕቅዶችን ለማናበብ የሚያስችል የውይይት መድረክ  ከተጠሪና ከክልል የዘርፉ አስፈፃሚ ተቋማት  ጋር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት መነን መለሰ  ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማትና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፎች የሚስፈፅማቸው ተልዕኮዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከቱ እንደመሆናቸው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚታቀዱ ዕቅዶች  ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ማካተታቸውን የማረጋገጥ ሥራ በቋሚነት እንደሚከናወን ገልፀዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመደበኛ ዕቅዶቹ   ከሚያስፈፅማቸው ተልዕኮዎቹ ጎን ለጎን በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎቹ በሶማሌ ክልል የመማሪያ ክፍሎችንና ግንባታና የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤት የማደስ ሥራ ማከናወኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ በአዲስ አበባ ከተማ 54 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ባለ አራት ወለል ህንፃ የመኖሪያ ቤት አስገንብቶ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከቡንም ገልፀዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪና የክልል የዘርፉ አስፈፃሚ ተቋማት ከህብረተሰቡ ጋር በቀጥታ የሚገናኙ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ  የዘርፉን አካታችነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ጉዳዮችን በጥናት ከመለየት፣ በዕቅድ ከማካተትና ከማስተግበር አንፃር ያሉበትን ደረጃ ለመፈተሸና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡ 

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሃንስ በበኩላቸው ከጠቅላላው የሀገራችን የህዝብ ቁጥር ከግማሽ በላይ  ድርሻ   ያላቸውን ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን ያላካተተ ማንኛውም ሀገራዊ ዕቅድ የዜጎችን ሙሉ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ስለማይጠበቅ በየደረጃው ያሉ የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት ዕቅዳቸውንና አፈፃፀማቸውን በየጊዜው መፈተሽና  የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የላቀ ጥረት ማድረግ  እንደሚኖርባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 6፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

16 Oct, 13:59


#አሁን
#HappeningNow

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

ከከሰዓት በፊት በነበረ መድረክ የሥራ ዕድል ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን በአሁን ሰዓት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎች፣ የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተቀመጠውን የተለጠጠ ዓመታዊ ግብ ለማሳካት መከተል ስለሚገባው አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ውይይት በመደረግ ላይ ነው፡፡

በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ክህሎት የሁሉም ስራዎች መነሻና አስቻይ ሚና ያለው ዘርፍ ነው፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 6፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

16 Oct, 11:27


#አሁን
#HappeningNow

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ላይ ይገኛል።

በዘርፉ ደረጃ እየተደረገ በሚገኘው የግምገማ መድረክ የሥራና ከሀሎት ሚኒስትር ክብረት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የሥራና ከሀሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምረትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት 4.2 ለሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥ እንዲሁም 700 ሺህ ደግሞ በውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 6፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

15 Oct, 06:10


ስምምቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ራስን የመቻል ጉዞ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከቬክና ቴክኖሎጂ እና ከኦርቢት ሄልዝ ጋር በመተባበር ዲጂታላይዝ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ‹‹ብራት ቦክስ›› የተሰኘ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በማምረት በገጠር አካባቢዎች ዲጂታላይዝ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ አምራችነት የሚሸጋግር እና አዳዲስ ዕውቀትንና ክህሎትን ለመታጠቅ ያስችላል፡፡

ይህም በሂደቱ ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ራስን የመቻል ጉዞ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የሥምምነቱ ተግባራዊነት በጤና ቴክሎጂ ምርት፣ በሮቦቲክስና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ብቁ የሰው ኃይል ለማልማት የሚያስችል ዕድልን የሚፈጥር መሆኑም ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡

ጥቅምት 4/2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

14 Oct, 06:42


ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን!