የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace) @lovedbychrist Channel on Telegram

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

@lovedbychrist


“ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤”
— ቲቶ 2፥11

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace) (Amharic)

በዚህ ገጽ የቴምር ኢንፈረምንት 'የእግዚአብሔር ፀጋ' ተገኝተናል፡፡ የዚህ እሱማ መሰረት ምንድን ነው? ምንድን ነው? የእግዚአብሔር ፀጋ ቴምር ማንኛውንም መልካም ሰዎች በአቶ ቲቶ 2 ረከት ትምህርት ማህበራዊ መሆኑን አስተምረናል፡፡ በእንደገና የዚህ ቴምር አገልግሎት ከመሆን እንጂ በገንዘብው ላይ ሲያስወግድልን አገልግሎታችን በኢንሱስ ስልክ ወደ +1000197949377 ውስጥ ይላኩ፡፡

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

16 Feb, 06:37


ሃሌሉያ ♥️
ኢየሱስ ጌታ ነው
መልካም እሁድ
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

16 Feb, 05:02


ቃላችሁ ለእግዚአብሔር ይጣፍጠው እሱ ሁሌም ሊሰማችሁ ከእናንተ ጋር ነው

“ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል።”
— መዝሙር 104፥34

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

15 Feb, 22:15


እንደ እናት እንደ አባት
#ኢየሱስ

በዘመኔ አንድም ቀን ፊቱን አዙሮብኝ ጀርባውን ሰቶኝ አያቅም
ይጠብቃል
ይወዳል
ይመራል
ይንከባከባል

በዘመኔ ማይደበዝዝብኝ ፍቅር ማይለቀኝ እጅ ማይተወኝ አፍቃሪ
#ኢየሱስ ♥️🙌🏼

ለዚህ ጌታ ምንስ ቢኮንለት
ሆኖልኝ እንጂ ምን ሆንኩለት
ዛሬም አለ ድጋፍ ሊሆንልኝ

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

15 Feb, 19:59


“ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።”
  — 2ኛ ቆሮ 9፥8-9
ደህና እደሩ

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

15 Feb, 18:15


እግዚአብሔር ዛሬም ለሚሰማው ይናገራል
ዛሬ በጠዋት የመውጣት እቅድ ነበረኝ ነገር ግን አልወጣውም ነበር
በተለየ ሁኔታ እንቅልፍ እያዳፋኝ ጀመር
ከዚያ ቀን ላይ ተኛው
እና ጌታ በህልም ያወራኝ ጀመር ረዘም ያሉ ህልሞችን ማየት ጀመርኩ

ካየዋቸው ሕልም ውስጥ ሰዎች ለራሳቸው ለቤተሰባቸው መፀለይ እንዳለባቸው ነበር
ስለዚህ ጌታ አስቀድመን እንድንነቃ በህልም አውርቶኛል ለቤተሰቦቻችሁ በብርቱ ፀልዩ
ንቁ ፀልዩ
ቤተሰቦቻቹን ከጠላት ሃሳብ በፀሎት አስመልጧቸው

ተባረኩ

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

15 Feb, 12:57


ታሪኬ የጀመረው 😭
በመስቀሉ ስር ነው

Tibebu Workiye
Amazing Worship
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

15 Feb, 12:06


“ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!
— ኢዮብ 26፥2

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

14 Feb, 19:49


መች አመስግኜ ጨርሼ አጉረመርማለው
ዛሬም ጌታ ይመሰገናል
ብሩካን ናችሁ
መልካም ምሽት

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

14 Feb, 16:31


ምሳሌ 31
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰
#ልባም_ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? #ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ #እጅግ_ይበልጣል
¹¹
#የባልዋ_ልብ_ይታመንባታል#ምርኮም_አይጐድልበትም
¹²
#ዕድሜዋን_ሙሉ_መልካም #ታደርግለታለች#ክፉም_አታደርግም

#አሜን 🙌🏼
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

14 Feb, 13:45


“ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፦ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና አለው።”
— ሐዋርያት 18፥9-10

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

14 Feb, 12:41


ላመስግንህ አባ ላመስግንህ
መስከረም ጌቱ
የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

14 Feb, 10:21


“አቤቱ፥ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።”
— መዝሙር 94፥19

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

14 Feb, 05:29


የዘላለም አባት እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ ማለዳ ስምህ ቡሩክ ይሁን

አቤቱ ከቀኑ ክፋት ጠብቀን። መንገዳችን ሁሉ አንተ የቀደምክበት፣ በውሏችን ሁሉ አንተ የምትውልበት ቀን አድርገው። ተመስገን! አሜን

የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

13 Feb, 18:28


እግዚአብሔር -በድምፅ
-በህልም
- በራእይ
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይናገራችሁ
መልካም ምሽት

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

13 Feb, 18:02


የሕይወቴ መልህቅ ሰሪው ተረከብከኝ
ከመንገዳገዴ ከእንቅፋት ያከምከኝ
መንገዴን አልመርጥ ከእንግዲህ በኋላ
በወደድከው ምራኝ ሕይወቴን በሞላ

🙌🏼🙌🏼🙌🏼🙌🏼🙌🏼
Kaleab Mengistu
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

13 Feb, 09:05


ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ አሳልፉ
ቃሉን ብሉት ደግሞም ፀልዩ

Live አገልግሎት ቀኖች ተስተካክለዋል እንቀጥላለን እንፀልያለን ቃል እንማራለን
40 ቀን ፆም ፀሎት ሰኞ እንጀምራለን
ከእኛ ጋር ምትፀልዩ አናግሩኝ
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

13 Feb, 05:36


ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው!
ለድል ተጠርታቹዋል

በነገር ሁሉ ማሸነፍ ይሁንላችሁ

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

13 Feb, 05:29


ታማኝ ነህ እንደስምህ
ፍቅር ነህ እንደስምህ
ወዳጅ ነህ እንደስምህ
እደስምህ አሜን

ቤተልሄም ወልዴ
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

12 Feb, 18:57


ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ
ዛሬ ወደ ቤት እየተመለስኩ አንድ ነገር አጋጠመኝ እሱም የተሳፈርንበት ታክሲ ሹፌር መኪናውን እንዲህ ይነዳል እንዴ በሚያስብል ፍጥነት ይነዳዋል
በታክሲ ውስጥ ያሉ በሙሉ ተረጋግተህ ንዳ ብለው የጮሁበት ክስተት ነበር
በጣም ስለሚሽለኮሎክ ያስፈራል አደባባይ ሲዞር ሊገለበጥ ሚደርስ ይመስላል
እና በዚህ መሃል አንዲት ሴት ዕቃዋን ከላይ ጭናለች እና እቃዬን ብላ ነው ምትጮኸው
ስለራሷ ረስታዋለች
ከዚህ ሰው ሁሉ ጩኸት መሃል የሷ በተለየ መልኩ ወደ ጆሮዬ ገባ
በጣም ገረመኝ ተደነኩ ዞሬ አንድ ነገር አልኳት
አንቺ ስትቀጥዪ ነው እቃው ሚቀጥለው ዋናው አንቺ ነሽ እንጂ እቃው አይደለም ብዬ ዞርኩና ሹፌሩን በጨዋ መንገድ ቀስ ብለህ ንዳ እንደርሳለን አልኩት እሱም ተረጋግቶ ደረስን
ወደ ልቤ አንድ ነገር መጣ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌባው ሊያርድ ሊያጠፋ ነው ሚመጣው እኔ ግን ሕይወት እንዲበዛላችሁ መጣሁ አለን
ምን ላይ ትኩረት አርገን ነው ያለነው?
ዋና ያደረግነውስ ምንድነው?
ወዳጆቼ በዚህ ምድር የማያልፍ ነገር የለም ቅድምያ የሰጠነው የእግዚአብሔር መንግስት ከሆነ ግን ለዘላለም ነው ምንኖረው
አይናችሁን ዋና በሆነው ላይ አድርጉ
👉🏼“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥
#የእምነታችንንም #ራስና_ፈጻሚውን_ኢየሱስን_ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”
— ዕብራውያን 12፥1-2

ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል ወደ ቤታችን ይወስደናል በሚያልፈው ላይ ሃሳባችሁን አትሠሩ
ብሩካን ናችሁ

አገልጋይ አብዲ ነኝ


@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

12 Feb, 11:14


#ከእኔ_ጋር_ውለዋልና_ጦማቸውን #አላሰናብታቸውም

🎤ጦምህን ከነረሃብህ አትሰናበትም እመነኝ ጠግበህ ይተርፍሃል
🎤ጠዋትህን የሰጠኸው ጌታ ማታህን አያበላሸውም
🎤 ጥያቄው ከማን ጋር ውለሃል ከርመሃል ነው
ከኢየሱስ ጋር ውለህ አድረህ ባዶህን አትሰናበትም ።
ከሰአትህን ማታህን የጤና ረሃብተኛ, የኑሮ ረሃብተኛ, የሰው ረሃብተኛ,የምግብ ረሃብተኛ,አያደርገውም አጥግቦ ይሸኝሃል ።

“ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ፦ ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም አላቸው።”
— ማቴዎስ 15፥32

ወንድማችሁ አብዲ ማርቆስ ነኝ

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

07 Feb, 05:00


በፀሎታችሁ አስቡኝ
ፀልዩልኝ

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

07 Feb, 04:10


የፍቅር መጀመሪያ
ድንቅ አምልኮ
Nuhamin Teferi
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

06 Feb, 20:18


አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
— መዝሙረ ዳዊት 46:1

መልካም ምሽት ❤️

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

06 Feb, 13:57


ድፍረቴ አብሮነትህ ነው ኢየሱስ

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

06 Feb, 13:14


ጋብቻ ቁማር አይደለም!
ከማያምን ጋርም አትጠመዱ
ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው

መልዕክቱን ስሙት
ነብይ ዘኔ you are our blessing
Much love and respect ሁሌም

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

06 Feb, 10:24


ከባርነት ሀገር ያወጣኸኝ
ዕስራቴን ፈተህ የለቀከኝ
ምስጋናዬን እንካ የኔ ጌታ
እንዳንተ አላየሁም የሚረታ

እግዚአብሔር ብርሀኔና መድኃኒቴ ነው።

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

06 Feb, 06:44


ሰዎች በብዙ አቅጣጫ ይሄ ነገር ይደርስባቸዋል ከትልቅ እስከ ትንሽ ባለው
እና ይሄን ፅሁፍ አንብቡት ትማሩበታላችሁ
ምንም ይሁን ምንም ግን ሰው መውደዳቹን አትተዉ!!! የቱንም ያህል ቢከብዳችሁ just Give them Love!!!

እልፍ እልፍ በሉ

የሰው ልጅ አመል እጅግ አስቸጋሪ ነው። ፍቅር እንደ አባጨጓሬ የሚኮሰኩሰው ነው። ስታቅፉት አንገላታችሁኝ፣ ስትስሙት ነከሳችሁኝ፣ ስታስቡለት አሴራችሁብኝ ይላችኋል። እንደዚህ ያለን ሰው በሕይወታችን ውስጥ ይዘን መቀጠል ይከብደናል። ከሕይወታችን ገንጥለን ለማውጣት እንሞክርና አዝነን የእንደገና እድል ልንሰጣቸው እንሞክራለን። ከእናንተ ሳይሆን ከእነርሱ ጎድሎ ነውና ህመም ይፈጥሩባችኋል። ደግ በሰራሁ፣ ፍቅር በሰጠሁ፣ አለውልህ ብዬ ከጎኑ በቆምኩ ለምን ይህ ተመለሰልኝ ትላላችሁ። የምትችሉት መውደድ፣ ፍቅርን መስጠት፣ ደግ መሆን ነው እንጂ ያ ሰው እንዲወዳችሁ እንዲያፈቅራችሁ ማድረግ አትችሉም። ልቡ ላይ ደግነትና ፍቅርን መዝራት ትችላላችሁ ተንከባክቦ ማብቀል ግን የሰውዬው ድርሻ ነው።

ክርስቶስ ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ ፍቅርን ሰጣቸው፣ ምህረትን አደረገላቸው፣ መልካምነቱን በልባቸውም በቤታቸውም አደረገላቸው፣ ጉድለቶቻቸውን ቀረፈላቸው እነርሱ ግን አልተቀበሉትም። እልፍ ብሎ ወገኖቹ ወዳልሆኑት አህዛብ ሄደ። ወዳጆቼ አለመቀበል፣ አለመፈለግ ወዳጅ ጓደኛ ካረጋችሁት ይቅርና ወገኔና ቤተሰቤ ከምትሉትም ሊገጥማችሁ ይችላል።

ዮሴፍ ወንድሞቹ ሲሸጡት የማያውቁት ናቸው የገዙት፣ ከተወለደበት አገር ሲገፉት ያልተወለደበት አገር ላይ ነው የተሾመው፣ የስጋ ክፋዮቹ ጠሉት በስጋ ያልተዛመዱት ወደዱት። ስለዚህ የግድ ሲጠሏችሁ ለመወደድ አትጣሩ፣ ሲገፏችሁ ላለመውደቅ እንጂ ላለመለየት ግትር አትበሉ። እልፍ ማለትን ልመዱ! ሕይወት ከሰውም ከእግዚአብሔርም ጋር የምንጓዛት መስካችን ናት። ስለዚህ ከሰው ጋር ያለንን ግንኙነት በፍቅር እናድርገው። አንድነታችሁ ብቻ ሳይሆን ከሰው ጋር ስትለያዩም በሰላም አድርጉት።


@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

06 Feb, 06:15


እግዚአብሔር ቸር ነው
ዘወትር ሐሙስ ጌታ ድንቅ ጊዜን እየሰጠን ነው
የእግዚአብሔር ቃል በኃይል እየተካፈልን ነው
በሚደንቅ አምልኮ ጌታን እያመለክን ነው
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በኃይል እየፀለይን ነው
የጌታ እጅ ቅዱሳንን እየጎበኘ ነው
መጥታችሁ ፀጋን ተካፈሉ

ወንድማችሁ አብዲ ነኝ
ክለሜንሲ ኦፍ ጋድ ቤተክርስቲያን
አድራሻ 22 ሰገን ህንፃ ስር

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

06 Feb, 04:20


“ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።”
— ኤፌሶን 3፥18-19

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

05 Feb, 17:37


ሃሳባችሁን(ልባችሁን) ጠብቁ

መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል
👇🏼
“አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።”
— ምሳሌ 4፥23

አጥብቀህ ነው ሚለው ለዛም ልብ የሚጠበቅ ነው!
በልባችሁ ላይ ብዙ ነገር ሊፈራረቅበት ይችላል ነገር ግን አጥብቆ የጠበቀ ለሕይወት እንጂ ለሞት አይዳረግም
ምክንያቱም የተበላሸን ሃሳብ ማሰላሰል የሚገድልህን አውሬ እንደ ማሳደግ ነው::
ልብህን ጠብቅ ያለን እግዚአብሔር ልባችንን ሊኖርበት እና ሊታሰብበት ሚፈልገው ስፍራ ስለሆነ ነው

የሚበጃችሁን ያቅላቹዋል እና በራሳችሁ መንገድ ሮጣችሁ እራሳችሁን አትጡ

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልባችሁ ላይ ኢየሱስ ብቻውን ይንገስ.
ኢየሱስ ከመንገሱ የተነሳ በዘመናችሁ ሁሉ ሀሳባችሁ የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት ሃሳብ ይሁን
ልባችሁ ከመጠበቁ የተነሳ ሕይወታችሁ በሙሉ በደስታ የተሞላ ይሁን
በጊዜውም ያለ ጊዜውም ልባችሁ የበረታ ይሁን

መልካም ምሽት
የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

05 Feb, 16:40


የዕሮብ ምሽት መዝሙር ግብዣዬ

ዝም ብዬ ልዘምር
ይሁን አንተ እንዳልከው
አሜን አሜን አሜን
ያልከው ይሁን
እሺ እሺ እሺ በቃ
ነብሴ ትረፍልኝ ያልክላትን አውቃ

አስቴር አበበ
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

05 Feb, 10:35


ጎልያድን ማነው የገደለው?
ተብሎ ሲጠየቅ ዳዊት
የወረወርኳት ጠጠር ናት ብሎ አልመለሰም
ለካስ እንደ ዳዊት መነሻቸውን ሁሉን በሚችል አምላክ ላይ ያደረጉ ሰዎች
ወፍ እንኳን መግደል በማትችል ጠጠር ጎልያድን የሚያክል ችግር ይጥላሉ
ወዳጆቼ እግዚአብሔር ከሌለበት እልፍ የጦር ሰራዊት ይልቅ እግዚአብሔር ያለበት ትንሿ ጠጠር በህይወታችሁ ትልቅ ታሪክን ትሰራለች

መልካም ጊዜ
የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

05 Feb, 05:13


“ይህም ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ መንግሥት ኑሮው ተቃናለት።”
— ዳንኤል 6፥28

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

04 Feb, 20:34


"#እንደቆጠሩን" አይደለንም " #እንደቆጠረን" ነን!

1ኛ ሳሙ 1:11 " ሐናም በልብዋ ትናገር ነበር፤ ድምፅዋም ሳይሰማ ከንፈርዋን ታንቀሳቅስ ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከረች ቈጠራት"
የልጅ ጥያቄ የነበራት ሃና ፣ በብዙ ጭንቅ ውስጥ ሆና ጥያቄዋን ለአምላኳ ስታቀርብ ነው እንግዲህ ካህኑ ኤሊ እንኳ በተሳሳተ መረዳት ተገንዝቧት " እንደ ሰከረች" የቆጠራት።

ብዙ ጊዜ ሰዎች የምናልፍባትን መንገድ፣ ሰማይ ያለውን አጀንዳ ፣ የጌታን ፍቃድ እና ይህን የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ሳያጤኑም ሆነ ሳያስተውሉ ብሎም በትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንገድ ሳይከተሉ እንደነሱ መረዳት " ሊቆጥሩን" ይከጅላሉ።

አሃ! የሃና ጉዳይ መች ስካር ሆነና ?! የሳሙኤል ናፍቆት እንጂ! የስማይን አጀንዳ ማስፈጽም እንጂ!

እግዚአብሔር ዘግቶ እየሰራ ሆኖ እንጂ!
የዛሬ ምሽት መልዕክቴ ይህ ነው:- በትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንገድ እየሄድን ምንም ነገር ገጥሞን፣ ሰዎች ያሻቸውን መላምት ቢለማመዱብን ሆነ የግምታቸውን ናዳ ቢያወርዱብን ...... እኛ ግን እንደ "
#ቆጠሩን " #አይደለንም!
ደግነቱ ሰማይ ይረዳናል! በምን እያለፍን እንደሆነ ያውቅልናል! ምጣችንን ያውቀዋል! ዘግቶ ምን እያበጃጀ እንዳለ አሳምሮ ያውቃል!

ደግሞ ትንሽ ልጨምር ......... ቁጥር ብቻ ማማጥ ሳይቀል አይቀርም፤ ማንምም ምንም ላይል ይችላል። (እንደፍናና ሰባት ማግበስበስ ከመደበኛ አካሄድ ውጪ ብዙ ጣጣ ላይኖረው ይችላል)። የሰማይ ሃሳብ ያለበት አንድ የሳሙኤል ጉዳይ ግን ........ ያው ደግሞ ሲወለድ ሳሙኤል ነዋ!!!!!!!!!!!!!

እንደ "
#ቆጠሩን " አይደለንም ... ይልቁን እንደ " #ቆጠረን " ነን!!!!!!!!

1ኛ ጢሞ 1:12 ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤


@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

04 Feb, 19:03


ምስክርነት 🙌🏼
ጌታ ታማኝ ነው
ጌታ የቅርብ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለም
ዛሬም እግዚአብሔር ይፈውሳል
ከእናንተ ሁኔታ አልፎ የሚሰራ አምላክ ነው ጌታችሁ
ተባረኩ
አገልጋይ አብዲ ነኝ

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

04 Feb, 12:41


ባየው ባየው አይለወጥም ፍቅሩ
ባየው ባየው አይቀዘቅዝም መውደዱ
ባየው ባየው አይቀየር እንክብካቤው
እንደትናንቱ እንደልጅነቴ ሲወደኝ ያው ነው

ድንቅ አምልኮ
አስቴር አበበ
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

04 Feb, 06:39


ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
ሰቆቃው ኤርሚያስ 3:26 ❤️

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

04 Feb, 04:32


መጠበቅ🤔

ስምኦን የተነገረውን ትንቢት ጠንቅቆ ያውቃል፤ ተስፋውንም በትጋት ይጠባበቅ ነበር። ሉቃ 2፥25-35

- መጠበቅ የአንድ ቀን ክስተት አይደለም። የስምኦን ኑሮው ምልልሱ ነበር።

#ሲጠባበቅ የነበረው መንፈሳዊ ቁመና ይህን ይመስል ነበር።
--- ጻድቅ እና ትጉ ነበር፤
--- መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ነበር፤
--- ለሰማው ድምጽ ታዛዥ ነበር፤

+++ በትጋት የሚጠብቅ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የተግባባ ሰው ከተስፋ ቃሉ መቼም አይተላለፍም።
💐ስምኦን ታዞ ወደ ቤተ መቅደስ ሲወጣ
እነ ማርያም ሕጻኑን ይዘው ለመስዋት ሲመጡ  ተገጣጠሙ። ሕጻኑን አቀፈውና እግዚአብሔርን ባረከ።🙏🙏🙏

ስምኦን ለሰማው ድምጽ በመታዘዝ ሲኖር ከተስፋው ጋር ተገጣጠመ።
++ መጠበቅ እምነት ይጠይቃል። ነገር ሲዘገይ ደግሞ እምነትን ይፈታተናል።

እንዴት እንጠብቅ🤔

💐 ሳናቋርጥ በመጸለይ የተባረከውን ተስፋችንን በትጋት እንጠብቅ!💐

በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።❞ 
—ዕብራውያን 6: 11-12
💐+ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ያለንን ሕብረት እያስጠበቅን።
💐+ ድምጹን ብቻ እያስቀደምን፤ እየታዘዝን
💐ሁልጊዜ ከምንጩ አጠገብ በመሆን፤
የመጠበቅ አቅማችን እስከ መጨረሻው ይሁን።
ዛሬም
-+- በምድር ምልልሳችን እግዚአብሔር ሹክ ያለንን ማቀፍ ይሁንልን!!

የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል

@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

03 Feb, 19:35


መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ፤
የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረዉ፤
በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች፤
ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች


አዜብ ኃይሉ
የእግዚአብሔር ፀጋ ቴሌግራም ቻናል
@lovedbychrist
@lovedbychrist

የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)

03 Feb, 14:09


ሰውን ለማስደሰት አትኑሩ!
እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንጂ!
እግዚአብሔር ደስ ሚሰኘው በሚያምኑት ነው!
እንደውም እኮ መፅሐፍ ምን ይላል መሰላችሁ

👉🏼“ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።”
— ዕብራውያን 10፥38

@lovedbychrist
@lovedbychrist

4,993

subscribers

262

photos

28

videos