ቅድስት ሆይ ለምኝልን @dnglemaryamenate Channel on Telegram

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

@dnglemaryamenate


@እንደ ኤፍሬም ባይሆን
በአቅሜ በምችለው
ማርያምን ማርያም
በጣም እወድሻለው

@dnglemaryamenate

ቅድስት ሆይ ለምኝልን (Amharic)

የቅድስት ሆይ ለምኝልን ቴሌግራም አካባቢ ነው የሚለዋወጡት። ይህ ቴሌግራም አካባቢ ማህበረሰብ ወደ አገልግሎት መጠን፣ የአውቶማወው ብርሃን መልዕክት፣ በጭስ መናገርና በምክትል የጀመረው ከእንግሊዝም የምንሆን አስተሳሰብ ነው። የመገበያ አቅም በቅድስት ገፍቶ ሆና ባይኖርት ባይኖርህ፣ በጣም እወድሻለው።nnይህ ቴሌግራም አካባቢ የኤፍሬም ባይሆን ማርያምን ማርያም እንደሆነ መሆንን እንዲችል ለምኝልን መረጃ እንዲሰጥ የሚረዳውን የአገልግሎት ቅድስት ሆይ ለምኝልን ቴሌግራም አካባቢን እንኳው እንደ ሆነ በመጠቀም እንዲሰማል። ከማንኛውም ሰው ካልሆነ፣ ወደ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ቴሌግራም አካባቢ እንዴት ሊመረጥ ይቻላል።nnመሰረታዊያን ለምኝልን እያንዳንዱ ለማወጣት እና እንዲቻለ ነገር ከምኝልን ሆይ ለምኝልን ቴሌግራም አካባቢ መረጃ እንጠቀማለን።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

13 Jan, 18:05


ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡

እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ?ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ የሚያስቁ ናቸው

አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡ ከ150 አመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወስ ይሆናል ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡
እናም በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፡፡ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም ብሏልና የማያልፈውን አምላክ ተከተል፡

ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡

ለምትወዱት ሼር ሼር አርጉላቸው፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

08 Jan, 17:51


"ይህቺ ጥፊ የኔ ናት"

መነኮስ አባ አርሳንዮስ በገባበት ገዳም ዉስጥ፣ እግዚአብሔርን
እያገለገለ ሲኖር አንድ ቀን ከገዳሙ ሕግ ዉጭ የሆነ ነገር
ይፈጽማል፡፡ ጥፋቱ ከገዳሙ አበምኔት ይደርስና አበምኔቱ አስበዉ
ብገስጸዉ ያፍራል፣ ዝም ብል ጥፋቱ ጥፋት ሳይመስለዉ ሊቀር ነዉ
አሉና፡፡ የሱን ረድዕ ጠርተዉ እንዲህ አሉት፡፡ "አርሳንዮስ ያጠፋዉን
ጥፋት እኔ እያየሁህ በእርሱ ፊት አንተ አጥፋ ከዛ በጥፊ
እመታሃለሁ፡፡ ያኔ እርሱ በአንተ ጥፊ ይማራል አሉት፡፡"
እንደተመካከሩት በአርሳንዮስ ፊት ረድኡ የእርሱን ጥፋት አጠፋ
አበምኔቱም ተቆጥተዉ በጥፊ መቱት በዚህ ጊዜ ነገሩን የተከታተለዉ
አርሳንዮስም "ይህች ጥፊ የኔ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
እግዚአብሔር እኛን ባጠፋነዉ ቅጣት የግድ እስከሚቀጣን ቁጭ
ብለን መጠበቅ የለብንም ፣ከሌላዉ ጥፋት፣ ከሌላዉ ቅጣት መማር
አለብን፡፡ ከሌላዉ ጥፋት መማር ትልቅ ዕዉቀት፣ ታላቅ ማስተዋል
ነዉ፡፡ አርሳንዮስ ጓደኛዉ በጥፊ ሲመታ፣ ይች ጥፊ የኔ ናት አለ እንጂ
ባጠፋዉ ጥፋት ነዉ የተቀጣዉ ብሎ አልፈረደበትም፡፡ እኛም ቁጣ፣
መቅሰፍት፣ እኛ ጋር እስኪመጣ መጠበቅ የለብንም ከጓደኞቻችን
ከጎረቤቶቻችን በሌላም ሀገር ከምናየዉ ከምንሰማዉ ተምረን ንስሓ
መግባት አለብን ጾም ማለትም ይህ ነዉ፡፡ ንስሐ የምንገባዉም
ኃጢአታችንን ስናስተዉል ነዉ፡፡ ማስተዋል ከሌለን ኃጢአቱን እንደ
ጽድቅ ቆጥረን ለንስሐ አንበቃም፡፡
ማስተዋልን ገንዘብ ያደረገ ምዕመን በሌላ ላይ የተደረገ ቅጣት
በርሱ ላይ እንደመጣ ይጠነቀቃል፡፡ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ
ብልህ በመሆን የነገሮችን ሁኔታ በማስተዋል ይከታተላል፡፡ ከሰብአ
ትካት ከሰዶም ይማራል ሎጥ የዳነበትን መንገድ ይከተላል ቃሉን
በመስማት በኖህ መርከብ በተመሰለች ቅድስት ቤተክርስቲያን
ይገኛል እራሱን በንስሐ በሥጋ ወደሙ በጸሎት በእግዚአብሔር
ቸርነት ከሚመጣዉ መቅሰፍት ያድናል፡፡
የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

05 Jan, 04:08


ጽድቅን የተጠማች ኃጢአተኛ ነፍሴ
ጽድቅን የተጠማች ኃጢአተኛ ነፍሴ
ጎስቁላ ደርቃለች ክብሯንም ጥላለች
ለአለማዊ ነገር ራሷን ሸጣለች
መዋብ መኳኳሉን ፋሽን መከተሉን
ገንዘብ አድርጋለች መጠጣት መዝፈኑን
የምሕረትህ ብዛት ቢያቆያትም ዛሬ
እሷ ግን አልገባት ጭራሽ አልተረዳች
ከመለወጥ ይልቅ መሸሽን መርጣለች
ዝሙቱ ሐሜቱ መስረቁ ውሸቱ
መናቅ መታበዩ ማስመሰል መክፋቱ
ነፍሴን ተስማምቷታል
የሰከንዳት ደስታ እውነተኛ ያልሆነ ሰላምን ሰጥቷል

እናማ አምላኬ ሆይ

ለታወረች ነፍሴ ኃጢአት ለጋረዳት ብርሐህን ላክላት አንተን የምታይበት
እውነተኛው ሰላም እውነተኛው ደስታ
እራስህ ነህና
አቅርባት ወደ አንት ጌታ መድኃኔዓለም
በቃሽ በላትና

እንኳን ለመድኃኔዓለም ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

04 Jan, 19:09


ቆይ እኔ የቱ ነኝ

ቤተ ክርስትያን ስሄድ
ምጾም ምጸልየው
ዝቅ ጎንበስ ብዬ
የማገለግለው
ከመልካም ቃል በቀር
ከአፌ የማይወጣው
በእልልታ ሆኜ
መዝሙር ምዘምረው
እኔ ያላረኩትን
ሰዎች የምመክረው


ወይስ.....................

ሰፈሬ ስመለስ
ጌታን የረሳሁት
ከጓደኞቼ ጋር
በሀሜት ያለሁት
ብር ለመሰብሰብ
ቁማር የተጮትኩት
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ
ሴቶች የለፍኩት
እናትና አባቴን
ጭራሽ ያልታዘዝኩት
ስልክ ላይ አፍጥጬ
የተጀናጀንኩት

ወይስ.....................

ማታ ልተኛ ስል
ጸጸት የሚገርፈኝ
ሕሊናዬ አቃጥሎ
ሲዖል የሆነብኝ
የማደርገው ነገር
ግራ የሚያጋባኝ
የህይወት መንገዱ
ጎዳናው የጠፋብኝ
ጥርሴ እየሳቀ
ልቤ ያለቀሰብኝ
እድሜዬ በከንቱ
ቶሎ ያለቀብኝ


ቆይ እኔ የቱ ነኝ
እውነት ግራ ገባኝ
ቸሩ መድኃኔዓለም
ከዚህ ሁሉ አውጣኝ

በኃይለ ማርያም 01/06/16 አርብ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

03 Jan, 07:49


ጌታችን የሞተውን አልዓዛርን "አልዓዛር ሆይ" ብሎ ጠራው።
የሞተን ሰው ማን በስሙ ይጠራዋል? "ሬሳው ወጣ" እንላለን እንጂ መች "እገሌ" እንለዋለን። የምንወደውን ሰው ሲሞት እንፈራው የለ? እንደማርታ ይሸታል እንል የለ? ጌታ ግን አክብሮ አልዓዛር ሆይ ብሎ በስሙ ጠራው።
እኛን የሚያጽናናን ይኼ ነው። ምንም በኃጢአት ሞተን ብንከፋም ፣ ስም አጠራራችን ቢጠፋም ፣ ሰዎች ስማችንን ሊጠሩ እስኪጠየፉ
ብንበላሽም እግዚአብሔር ግን በክብር ስማችን ይጠራናል። ሰዎች ስማችንን
ትተው ኃጢአትን ስማችን : አድርገው : አመንዝራዋ” ብለው ይጠሩን ይሆናል። መድኃኔዓለም ግን የሚጠራን "ይሸትሃል" የሚሉትን ሰዎች ሳይሰማ ወደተቀበርንበት የኃጢአት መቃብር እያለቀሰ ይመጣል። የተጫነንን የበደል ድንጋይ ያስማልናል። ለአልዓዛር "ፍቱት" ብሎ ደቀመዛሙርቱን እንደላከ ለእኛም ካህናቱን ልኮ ከተተበተብንበት የኃጢአት ማሠሪያ ይፈታናል። ሰዎች ከሞት ተነሥተንም እንኳን መነሣታችን አያምኑም ፣ ለአልዓዛር እንዳደረጉት ሊደግፉን
ይሞክሩ ይሆናል። ጌታችን ግድ "ተዉት ይሒድ" ብሎ ያቆመናል። ከአልዓዛር የበለጠ ከኃጢአት መቃብር ውስጥ ብንቆይም ዳግም በሕይወት ያኖረናል።
"አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል"
ኤፌ 5:14
ሚያዝያ 15 2009 ዓ ም

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

02 Jan, 18:25



_ ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን? አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ ይሆን? የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ የማይሰማው ይመስላችኋል? እንዴት አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ ለእኛ እኮ ያፈሰሰው
ደሙን ነው!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

01 Jan, 17:25


"እመቤታችን እናቴ እንደሆነች እንደማስብበት ሰዓት ያለ ልቤን የሚጠግነው ነገር የለም።ይሄን እናትነት ምን እንደሆነ ልብ ያለው ያውቀዋል።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

31 Dec, 11:29


በኃጢአት የጎሰቆለው አዳም የሚታደስበትን ዜና ሊያበስር መልአኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፤

ንጹሕ ለሆነው ሙሽራ የተገባች አዳራሽ ትሆነው ዘንድ መመረጧን ሊያበሥራት መልአኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፤

ከኃጢአት ንጹሕ የሆነው መልአክ በደል ወዳልተገኘባት ንጽሕት ድንግል ተላከ፤

የፀሐየ ጽድቅን መምጣት ያበሥር ዘንድ ብርሃናዊው መልአክ ተላከ፤

በአባቱ እቅፍ ያለው አንድያ ልጅ በእናቱም እቅፍ እንደሚሆን ያበሥር ዘንድ መልአኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፤

እንኳን ለበዓለ ብሥራት በሰላም አደረሰን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

30 Dec, 04:34


ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ3ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ አንድ የሚያስገርመኝ ዜኖ የሚባል ፈላስፋ ነበር። ይህም ሰው ከዕለታት በአንዱ ቀን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመለስ ድንገት ወደቀና ጣቱ ክፉኛ ተጎዳ። ከዚያም ከወደቀበት ሳይነሣ በእጆቹ መሬቱን እየመታ “እየመጣሁ ነውና እኔን ለመጥራት መድከምህ ከንቱ ነው” ሲል የአንድ ባለ ቅኔን ንግግር ተናግሮ እዚያው ራሱን አፍኖ ገደለ።

አትላንቲክ ውቅያኖስ አካባቢ የሚኖሩ Celts የሚባሉ ወገኖችም ነበሩ። እነዚህ ሰዎች ሞትን መፍራትን እንደ ትልቅ ውርደት አድርገው ስለሚያስቡ ትልልቅ ጥፋት የሚያመጡ ነገሮችን ሳይቀር ፊት ለፊት ይጋፈጡ ነበር። ለምሳሌ ቤቱ ሊያፈርስ ቢያዘምባቸው ወይም ግድግዳው ሊናድ ቢንደረደርባቸው ሮጠው ከዚህ አደጋ ለማምለጥ አይሞክሩም። በውቅያኖስም ውስጥ ሆነው ማዕበል ቢቀሰቀስ ወደ ኋላ አያፈገፍጉም። እንዲያውም ወጀቡ እስኪያልፍ ባሉበት ሳይንቀሳቀሱ ይቆማሉ። ሞትን ፈርተው ሸሹ እንዳይባሉ እነዚህን አስፈሪ ነገሮች ያደርጋሉ።

“ሕይወት” እግዚአብሔር የሰጠን ትልቁ ስጦታ ነው። እርሱ በቀጠረው ጊዜ እስኪጠራን ድረስ አለመታገስ የዚህን ስጦታ ዋጋ አለመረዳት ነው። እውነተኛ ጀብድ በዚህ አስቸጋሪ ዓለም ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ፈተናዎች ሁሉ ታግሎ ለማሸነፍ እስከ መጨረሻዋ ሕቅታ ድረስ መፋለም እንጂ ቀድሞ ሩጫ ማቋረጥ አይደለም። አንድ ክርስቲያን ሞትን እንደማይፈራ ማሳየት ያለበት “ሕያው የሚያደርገውን” የክርስቶስን ሥጋ እና ደም በመቀበል እንጂ ራሱን ለሞት በማጋለጥ መሆን የለበትም።

“ማምሻም ዕድሜ ነው” እንደሚባለው አይደለም በወጣትነት በሽምግልና ዘመን የቀረች ጥቂት ቀን እንኳ ታሳሳለች። ምክንያቱም ከመሰንበት ንስሐ መግባት፣ መጸጸት፣ መመለስ፣ የኋላውን ትቶ የፊትን ለመያዝ መዘርጋት አለና።


ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

26 Dec, 12:54


ምጽዋት

የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ፡፡ የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ፡፡

አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው፡፡ የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፡፡ ታድያ ወንድምህስ? የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነው? መሆን የለበትም፡፡ ማስቀመጫ እንዳጣ መጣያ አታርገው ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው፡፡ ከምትለብሳቸው ሁለት ልብሶች አንዱን ስጠው፡፡ የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው፡፡ ለአንተ የምትመኘውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ፡፡

“ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው” ያለውን የእግዚአብሔር ቃል መለስ ብለህ አስብና፣ የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ፡፡ ከዚሁ ጋር አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋዕት እንዴት እንደነበረ አስብ፡፡ “አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፡፡” (ዘፍ 4፥4) ለምን መረጠለት? ብትል ፣ ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ስላቀረበ ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ 4፥34-35 ላይ ሠፍሮ የሚገኘውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ፡፡ ክብርን ለመፈለግ አትስጥ በአንደበትህም ይሁን በልብህ፣ በስሜትህም ይሁን በሃሳብህ የራስህ ነገር ኖሮህ እንደሰጠህ አስበህ አትኩራራ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን እንደ ትልቅ ማስረጃ ተጠቀም፡፡ “አንተ እድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልክ ከሆነ ግን እንዳልተቀበልክ የምትመካ ስለምንድር ነው?” (1 ቆሮ 4፥7) ስለዚህ ስጦታ ሁሉ ከእግዚአብሔር ተቀብለን የምንሠጠው እንጂ የራሳችን እንደሆነ በከንቱ የምንመካበት አይደለም፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

26 Dec, 05:54


ሊቁ ይስሐቅ ሶርያዊ እንዲህ ብሎ ይገስጸናል “እግዚአብሔር ልመናችንን ከመመለስ ከዘገየ፥ ጠይቀንም ወዲያው ባይሰጠን እንከፋ እንናደድ ዘንድ አይገባም! እኛ ከእግዚአብሔር በላይ አዋቂ አይደለንምና።”

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

23 Dec, 18:46


ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰው ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን!
አልዓዛርስ ከመቃብሩ ውጣ ቢባል ይወጣል፤ ካለንበት የኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ ይሆን!
ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰውን ጌታ ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው !

ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

20 Dec, 19:22


ተመላለሽ ድንግል በትንሽ ድንኳኔ
የጎደለብኝን ምን አውቃለሁ እኔ
ይውጣ መናኛዬ አሮጌው ይሻር
በክርስቶስ ፍቅር በአዲስ እንድኖር
በአባቴ ፍቅር በአዲስ እንድኖር


#እመቤቴ_የኔ_ሕይወት_ተስፋ❤️‍🩹

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

19 Dec, 04:27


ምጽዋት ሥርየተ ኃጢአትን ትሰጣለች፡፡ ሞትንም ቢኾን ታርቃለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልጽ አደርግልሃለሁ፡፡

“መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውን ከተደረገ ታሪክ ተነሥቼ እነግርሃለሁና የምነግርህን ነገር አትጠራጠር፡፡

ጣቢታ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፡፡ መልካም ሥራን የሞላባትና ምጽዋትን የምትወድ በዚህም ለራሷ መዝገብ የምታከማች ነበረች፡፡ ለመበለቶች ልብስንና የሚያስፈልጋቸውን ኹሉ ትሰጣቸው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ሞተች፡፡

አሁን ደግሞ እነዚያ እርሷ ስትረዳቸው የነበሩ መበለቶች በየትኛው ሰዓት ብድራታቸውን እንደሚከፍሉ ተመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን መበለቶቹ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ኼዱ፡፡ ጣቢታ የሰጠቻቸውን ልብስንና ሌላውን ኹሉ አሳዩት፡፡ ከእነርሱ ጋር በሕይወተ ሥጋ ሳለች ምን ምን ታደርግላቸው እንደ ነበረች ነገሩት፡፡ እንደ እናት የምትኾንላቸውን እንደ አጡ አልቅሰው ነገሩት፡፡ ስለ እነርሱ እጅግ እንዲያዝንም አደረጉት፡፡ 

የተወደደ ጴጥሮስስ ምን አደረገ? “ኹሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ፡፡ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ ‘ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ’ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች፡፡ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች፡፡ እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፡፡ ምእመናንንና መበለቶችንም ጠራ፡፡ ሕያውም ኾና በፊታቸው አቆማት”  (ሐዋ.9፥40-41)፡፡

የሐዋርያውን ኃይል ወይም በሐዋርያው አድሮ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ አስተዋልህን? በወዲያኛው ዓለምስ ተወውና በዚህ ዓለምም ሳይቀር ጣቢታ ስለ መልካም ሥራዋ ምን እንደ ተቀበለች ተገነዘብን? እርሷ ለመበለቶች የሰጠችውንና መበለቶቹም ለእርሷ የሰጡትን አየህን? እርሷ ምግብና ልብስ ሰጠቻቸው፤ እነርሱ ግን ከሞት ወደ ሕይወት እንድትመጣ አደረጓት፡፡ ለመበለቶቹ ባሳየችው ቸርነት ቸሩ እግዚአብሔር ብድራቷን ከፈላት፡፡ 

እንግዲህ የምጽዋት የመድኃኒትነቷን ኃይል ተመለከትህን? እንግዲያውስ እኛም ይህን መድኃኒት ለራሳችን እናዘጋጅ፡፡ መድኃኒቱ ይህን ያህል ጽኑ መድኃኒት ቢኾንም ቅሉ እጅግ ርካሽ እንጂ ውድ አይደለምና ለራሳችን እንግዛ፡፡ ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ አይጠይቅምና እንግዛ፡፡ መልካም ሥራ መልካም የሚባለው በሚሰጡት ገንዘብ መጠን ሳይኾን በሚሰጡት የእደ ልብ ስፋት መጠን ነውና እንግዛ፡፡ አንድ ሰው አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ሰጥቶ እጅግ እንደ ሰጠ የሚቈጠርለትም እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን የሚሻው ወደንና ፈቅደን የምንሰጠው በጎ ፈቃዳችንን መኾኑን የሚያሳይ ነውና ይህን እንግዛ፡፡ መበለቶች፥ እንደ ጣቢታ ከሞተ ነፍስ ይታደጉን ዘንድ ይህን መድኃኒት ከእነርሱ እንግዛ፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

18 Dec, 09:11


+++ የማያሳፍር ተስፋ +++

ክርስቲያኖች በራሳቸው ማስተዋል ወይም በሀብታቸው አይደገፉም። እንደ እነርሱ ተሰባሪ በሆነ ሰው ላይም ተስፋቸውን አያደርጉም። የክርስቲያን ተስፋው “የተስፋ አምላክ” ክርስቶስ ነው።(ሮሜ 15፥13) ክርስቶስን ለምን ተስፋ እናደርጋለን? “ሁሉ በእርሱ ስለሆነ፤ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ” ስለሌለ፣ ኃይልና ችሎታ በእጁ ስለሆነ፣ ያጎበጠንን ሸክም አራግፎ ሊያሳርፈን “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ብሎ ስለ ጠራን፣ ወደ ጠራን አምላክ ቀና እንላለን።(ዮሐ 1፥3፣ 2ኛ ዜና 20፥6፣ ማቴ 11፥28) እርሱን ተስፋ ብናደርግ እንደ ሰው አይለወጥብንም። እስከ ሽበት እንኳን ተሸክሞን አይሰለቸንም።(ኢሳ 46፥4) ነፍሱን እስኪሰጥ ስለወደደን፣ በብዙ ሕማም በእጁ መዳፍ ላይ ስለቀረጸን ፍቅሩ ቀዝቅዞ ጨርሶ ሊረሳን አይችልም።(ኢሳ 49፥16)

"ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመ ቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ"

"ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ አባቶቻችን አልነገሩንም። እኛም አልሰማንም፤ አላየንምም!"

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

17 Dec, 09:25


አይዞህ አነካህም
ይህ የብዙዎቻችን የልጅነት ታሪክ ነው::
ጥፋት አጥፍተሃል:: ወላጆችህን በጣም የሚያስቆጣ ጥፋት ነው:: ወይ ውድ ዕቃ ሰብረሃል:: ወይ አንዳች በጣም የሚጠሉትን ነገር ሠርተሃል:: አለዚያም አድርግ
ብለህ ሳታደርገው የቀረኸው ነገር አለ::
ወላጆችህ ያጠፋኸውን ቢያውቁ ምን ሊያደርጉህ እንደሚችሉ እያሰብህ ተጨንቀሃል::
"አባዬ ዛሬ ገደለኝ"
እማዬ በጥርስዋ ነው የምትዘለዝለኝ''
ዛሬ መሞቴ ነው' እያልህ በፍርሃት ውስጥ ነህ::ስለዚህ ተደብቀሃል::
መደበቅህን ሲያውቁ ወላጆችህ የሆነ ነገር ጠረጠሩ::
"ምን ሆነህ ነው አንተ?''
"ምንም"
"ታዲያ ምን ያርበተብትሃል"
"ምንም"
"ተናገር እንጂ"
ራስህን ወዘወዝህ እንጂ አልተናገርክም::
አባት ቀረብ ይልና
"አይዞህ የኔ ልጅ ምንም አልልህም አልገርፍህም ንገረኝ" እያለ ማባበል
ይጀምራል:: ይሄን ጊዜ ለመናገር እያመነታህ ትቁለጨለጫለህ::
አባትም ነገሩ ይገባውና :-
"እኔ እኮ እውነት እንድትነግረኝ ብቻ ነው የምፈልገው:: ሐቁን ከነገርከኝ
አልነካህም:: እኔ የማልወደው ውሸት ብቻ ነው'' ይልሃል::
ይሄን ጊዜ እየተቅለሰለስክ በሹክሹክታ ጥፋትህን ትናዘዛለህ::
"አያትህ የሠጡህን የሸክላ ጌጥ እኮ ሰበርኩት"
ለትምህርት ቤት ክፈል ብለህ የሠጠኸኝን ብር ጣልኩት" ወዘተ ትዘረግፈዋለህ::
ተናግረህ ስትጨርስና ፊትህ ላይ የመብረቅ ድምፅ ስትሰማ እኩል ይሆናል::
የአባትህ ጥፊ ነው::
"ሥራህን አውቀህ ነዋ የተደበቅከው!? ኸከከከከ"
ሌላ ቀን ከተገረፍከው የላቀ ግርፊያ ይወርድብሃል:: "አይዞህ ያጠፋኸውን
ንገረኝ አልነካህም" የሚል ቃል ዋጋ እንደሌለው ትረዳለህ::
ያጠፋኸውን ንገረኝ ብሎ ስትናዘዝ የሚምርህ አባት እግዚአብሔር ብቻ ነው:: "በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው" 1 ዮሐ. 1:9

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

11 Dec, 21:29


ባዘንኩም በተቆረቆርሁ ጊዜ የኃዘኔ መፅናኛ ነሽ።
ባለቀስኩም ጊዜ የለቅሶዬ መተዊያ ነሽ።
በዘመርሁ ጊዜ ለእጄ እንደመሰንቆ ለጣቶቼም እንደበገና ነሽ።
በተራብሁ ጊዜ ለሆዴ ትመግቢኛለሽ።
በተጠማሁ ጊዜ እኔን ለማርካት የሕይወት ውሃን የተመላሽ ነሽ። በተጨነቅሁ ጊዜ ጭንቀቴን ታርቂያለሽ።
በቆሰልኩም ጊዜ ቁስሌን ታጠጊያለሽ።
በበደልኩም ጊዜ ኃጢያቴን ታቀልያለሽ።
በርኩሰቴም ጊዜ ንጹሕ ታደርጊኛለሽ።
በደኸየሁም ጊዜ ለድህነቴ ባለጸግነት ሀብቴ ነሽ።
             አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

11 Dec, 13:16


አባ መቃሪ በአንድ ወቅት ስለ ትሕትና ሲያስተምር ‹አንድ ባለጠጋ የነበረ ንጉሥ ያለውን ሀብት በአደራ መልክ ከአንድ ደሃ ዘንድ ቢያኖር ፤ ያ ደሃ በእነዚያ ብሮች እና ወርቆች ሊመካ ይችላልን? እንደ ራሱ ንብረትስ በመቁጠር የባለቤትነት ስሜት ሊሰማው ይገባል?› ሲል ይጠይቃል፡፡ በዚህ ቅዱስ አባት ምሳሌ መሠረት ያ ባለጠጋ ንጉሥ እግዚአብሔር ነው፡፡ አደራ ተቀባዩ ነዳይ ደግሞ እኛ ነን፡፡ አደራውም በእጃችን ያሉ በጎ ነገሮች ሁሉ ናቸው፡፡ ያሉንን መልካም ነገሮች እንደ ራስ ንብረት መቁጠርና በሌላው ላይ መኩራራት አደራ ተቀባይነትን እንደ መርሳት ነው፡፡ ሰው ባልፈጠረው በጎነት እንዴት ይኩራራል?


ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

09 Dec, 11:29


#ኑ_የበአታ_ለማርያም_በዓልን_አብረን_እናክብር!
ታኅሣሥ 03 ቀን 2017 ዓ.ም. ዓመታዊ የንግሥ በዓል

ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ኪዳነ ማርያም ደለለኝ - የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ

ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም
ዐዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
4 ኪሎ ቤተ መንግሥት አጠገብ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

09 Dec, 11:29


እንኳን ለበአታ ለማርያም ዓመታዊ በዓል (ታኅሣሥ 03) አደረሰን!
ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም
ዐዲስ አበባ
4 ኪሎ ቤተ መንግሥት አጠገብ
+++
ኹላችንም ተጋብዘናል!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

09 Dec, 11:29


#ዓመታዊ_የበአታ_ለማርያም_ክብረ_በዓል_ጥሪ!
ኹላችንም ተጋብዘናል!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

07 Dec, 04:44


በውጭው ካሉት ይልቅ በአንተ ውስጥ የሚገኙት ፍትወታት ጠንካራ ጠላቶችህ ናቸው። ልክ ያልተሠራለት ምኞት ከባቢሎን እሳት ይልቅ ያቃጥላል። አልጠግብ ባይነትም ከጥፉት ውኃ ይልቅ ያሰጥማል። ያልተገራ ፍላጎት ማንነትን አስጥሎ የሰይጣን ባሪያ ያደርጋል። ራስን መግዛት የሰው ልጆች ጌጥ ነው። ዮሴፍ ግብጽን ከፈርዖን ሁለተኛ ሆኖ ከገዛበት ታላቅ ሥልጣን ይልቅ፣ በጌታው ሚስት ፊት ያሳየው ራስን መግዛት ይበልጥ ይደነቃል። ጠቢቡ "በመንፈሱ ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ (ከሚገዙ) ይበልጣል" እንዳለ።(ምሳ 16፥32)

ራስህን ነጻ ማውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከውስጥህ ጀምር። ሁል ጊዜ ካልበላሁ የሚለው ሆድህ ስስት አስለምዶ በወንድምህ ላይ ጨካኝ እንዳያደርግህ ለሰውነትህ ጾም አስተምረው። "ነገ እሞታለሁና ልብላ ልጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍናህን (Pig philosophy) ተውና አንተ በፈቃድህ እየተራብህ (እየጾምህ) ያለ ፈቃዱ የተራበው ወንድምህን በምጽዋት አጥግበው።

ጌታ ወደ ገሊላ የተመለሰው ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ነበር።(ማቴ 2፥20) አንተ ውስጥ ያለውን ሄሮድስ የተባለ ክፉ ምኞት እንዲሞት ካላደረግኸው በቀር የተሰደደው ክርስቶስ ወደ አንተ ሊመለስ አይችልም። ይህ ክርስቶስን ከልብህ የሚያሳድድብህን ሄሮድስ እንዴት ልትገድለው ትችላለህ? እርሱንስ ወግተህ የምትጥልበት የብረት ካስማ ምን ይሆን? ለዚህስ ከጾም እና ከጸሎት የሚበረታ ምንም ዓይነት የጦር ዕቃ አታገኝም። በል እነዚህን ይዘህ ዝመትበት።

መልካም የነቢያት ጾም ይሁንልን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

06 Dec, 15:25


"የአንድ ፈረስ ፈረስነቱ ምኑ ላይ ነው? በወርቅ ልጓም ማሸብረቁ፣ እጅግ ቅንጡ በኾነ ኮርቻው፣ ከሐር በተሠሩና በባለ ብዙ ኅብረ ቀለማት ባጌጠ ልብሱ፣ እጅግ በጣም በተጋጌጠ ቆቡ እንዲሁም በወርቅ ገመድ በተገመዱ ፀጉሮቹ ላይ ነውን? ወይስ እጅግ ፈጣንና ብርቱ በኾኑት እግሮቹ፣ ለመሮጥ በሚያመቸው በሰኮናው፣ ረጅም ጉዞና ውጊያም ለማድረግ ባለው ተነሣሽነቱ፣ በጦር ሜዳ ላይ በማይደነብር ባሕርይው፣ ሸሽቶ ማምለጥ ካለበትም ጋላቢውን ለማሸሽና ለማዳን ባለው ጉብዝናው ላይ ነው? አንድን ፈረስ መልካም ፈረስ የሚያስብሉት መጀመሪያ ላይ የጠቀስናቸው ነገሮች ሳይኾኑ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጥናቸው ነገሮች አይደሉምን? አህያና በቅሎስ አህያና በቅሎ የሚያስብላቸው ምናቸው ነው? ደስ እያላቸው ሽክምን የመሸከም ኃይላቸው፣ ይህን ተሸክመው በቀላሉ ጉዞዎችን ማድረጋቸው፣ ለዚህም እንደ ዓለት የጠነከረ ሰኮና ስላላቸው አይደለምን? እነዚህ እንስሳት ይህን ተግባር ለማከናወን ከአፍአ የሚያደርጉት ጌጣጌጥ አስተዋጽኦ ያደርጋልን? በጭራሽ!

የምናደንቀው ወይንስ የትኛዉን ወይን ነው? ብዙ ቅጠልና ቅርንጫፍ ያለውን ወይስ ፍሬ አፍርቶ ጎንበስ ያለውን? ከአንድ የወይራ ዛፍ የምንጠብቀውስ ምንድን ነው? ትልልቅ ቅርንጫፎችና ለማየት ደስ የሚያስኝ ቅጠል እንዲኖረው ነው ወይስ በቅርንጫፉ ኹሉ ላይ ፍሬ እንዲያፈራ?

መልካም! በሰው ልጆች ዘንድም እንዲህ እያደረግን እንመልከተው፡- አንድን ሰው ሰው የሚያስበለው ምን እንደ ኾነና ይህንንም ምን እንደሚጎዳውና እንደሚያጠፋው እንየው፡፡ እናስ ሰውን ሰው የሚያስብለው ምኑ ነው? ድኽነት የሚያስፈራው ሀብቱ አይደለም፤ በሽታ የሚጎዳው ጤንነቱ አይደለም፤ ተቃውሞ ሊነሣበት የሚችለው የሕዝብ ውዳሴ አይደለም፤ ከፊት ለፊቱ ሞት በሚጠብቀው ሕይወተ ሥጋው አይደለም፤ ባርነትን ሊያስቀሩበት በማይቻለው ነጻነቱም አይደለም፤ እውነተኛ ዶክትሪንና የቅድስና ሕይወትን በጥንቃቄ ይዞ መገኘቱ ነው እንጂ።

ተመልከቱ! አንድ ሰው ራሱ እውነተኛ ዶክትሪንና የቅድስና ሕይወትን አስፈላጊ በኾነ ጥንቃቄ እስከያዘው ድረስ (ሌላ ሰውስ ይቅርና) ዲያብሎስም ቢኾን ሊወስድበት አይችልም። እጅግ ተንኰሎኛውና ጨካኝ የኾነው ጋኔንም ይህን ጠንቅቆ ያውቃል። የኢዮብን ሀብትና ንብረቱን ያጠፋበት ስለዚሁ ዋና ዓላማ ነበር።

ዲያብሎስ ይህን ያደረገው ኢዮብን ድኻ ለማድረግ አስቦ አልነበረም፤ ኢዮብ በእዚአብሔር ላይ ነቀፋን እንዲናገር እንጂ። ሰውነቱን በቁስል የመታው ሥጋው እንዲደክም ፈልጎ አልነበረም፤ የነፍሱን በጎነት ሊያሳጣው ወድዶ እንጂ፡፡ ኾኖም በአንድ ቅጽበት ያለውን ኹሉ ቢያሳጣውም፣ በእኛ እይታ እጅግ ክፉ መስሎ የሚታየን ከባለጸግነቱ አውርዶ እጅግ ድኻ ቢያደርገውም፣ በብዙ ልጆች ተከብቦ ይኖር የነበረውን ልጅ አልባ ቢያደርገውም፣ በአደባባይ ላይ ሰውን ከሚገርፉ ጨካኞች በላይ ከፍቶ መላ ሰውነቱን ቢገርፈውም (ምክንያቱም የቆስለ ሰውነትን በትላትል መበላት የሚገርፉትን ሰው በጥፍር ከመቧጠጥ በላይ ይፀናልና)፣ እጅግ ክፉ ተግሣጽን በገዛ ጓደኞቹ ቢያመጣበትም (ምክንያቱም ኢዮብን ለመጠየቅ መጥተው ከነበሩ ጓደኞቹ አንዱ፡- “እንደ ኃጢአቶችህ መጠን አልተቀጣህም" የሚሉና ሌሎች የነቀፋ ቃላትን ተናግሮታልና)፣ ከከተማውና ከገዛ ቤቱ አውጥቶ ወደ ሌላ ከተማ እንዲወጣ ብቻ ሳይኾን እዚያ ከሔደ በኋላም እጅግ በቆሸሽ ስፍራ እንዲኖር ቢያደርገውም ግን ከዚህ ኹሉ በኋላ እርሱ (ዲያብሎስ) ራሱ ባዘጋጀው መንገድ የበዛ ክብርን አመጣለት እንጂ ምንም ጉዳትን አላደረሰበትም። እጅግ ብዙ ነገሮችን ቢወስድበትም የምግባር ሀብቱን ይበልጥ ጨመረለት እንጂ ካለው ነገር አንዳችስ እንኳን አልወሰደበትም፡ ምክንያቱም ከእነዚህ ነገሮች በኋላ አስቀድሞ ከነበረው ነገር በላይ አግኝቷል፡፡

እንግዲህ ኢዮብ እነዚህን የሚያኽሉ መከራዎችን ከሰው ሳይኾን ከሰዎች ኹሉ እጅግ ከሚከፋው ከዲያብሎስ እንኳን ምንም ጉዳት ካልደረሰበት፣ እነ እገሌ ይህንና ያንን የመሰለ ጉዳት አደረሱብኝ የሚሉት ሰዎች ምን ዓይነት ምክንያትን ነው የሚያቀርቡት? እጅግ ታላላቅ ተንኰሎችን የተሞላ ዲያብሎስ አለ የሚለውን መንገድ በመጠቀም ከተንቀሳቀሰና ጦሩን ኹሉ ካራገፈ፣ ለዚህ አንድ ሰው ብቻ ይህን ኹሉ ክፉ ነገር በላዩ ላይ ከጨመረበት፣ hዚህ በላይ እጅግ ከፍቶም የዚህን ጻድቅ ሰው ቤተሰብ ኹሉ ቢገድልበትም አንዲት ጉዳትስ እንኳን ማድረስ ካልተቻለው፣ ይልቁንም አስቀድሜ እንደተናገርኩት ከጠቀመው፣ ሰዎች'ማ እነርሱ ራሳቸው ራሳቸውን ካልጎዱ በስተቀር እነ እገሌ እንዲህና እንዲህ አድርገው ጎዱን ብለው እንዴት ወቀሳን ማቅረብ ይቻላቸዋል?"

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

30 Nov, 08:04


ድንግል ማርያም ሆይ

ልጅሽን ቅዱሳን መላእክት ሊቀርቡት ይፈሩታል፤ አንቺ ግን ጸንሰሽ ወለድሽው።

ልጅሽን  ፍጥረታት ሁሉ "ፈጣሪያችን" ይሉታል፤ አንቺ ግን ልጄ ትይዋለሽ።

መልክና ባህሪሽ ልጅሽ ፈጣሪን  ይመስላል።

የተባረኩት ሴቶች ቅዱሳንን ይወልዳሉ፤ አንቺ ግን ፈጣሪሽን ወለድሽ።

ምስጢሩ ከሰው አእምሮ በላይ ስለሆነ እጹብ ድንቅ ተብሎ ማለፍ ነው እንጂ።

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሀገራችን ሰላምን ለህዝባችን ፍቅርን ለታመሙት ፈውስን ለተራቡት ምግብን ታድልልን አሜን!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

30 Nov, 06:36


+++ ማሰብና ማድረግ እኩል ናቸው? +++

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመን የኖሩ እጅግ ለእምነታቸው የሚቀኑ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ነበሩ። ታዲያ በአንድ ወቅት ኃጢአትን በማሰብ እና በማድረግ መካከል ስላለው ልዩነት አንሥተው ይከራከሩ ጀመር። ብዙዎቹም "ማሰብና ማድረግ ምንም ልዩነት የላቸውም" የሚል የሚል አቋም ነበራቸው። በስተመጨረሻም ይህን ጥያቄ እንዲመልስላቸው ወደ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይዘው ቀረቡ። ቅዱሱ በምሳሌ ሊያስተምራቸው ስለ ፈለገ አንድ ቀን ሙሉ ምንም ምግብ ሳይቀምሱ ቆይተው ማታ ለእራት እርሱ ዘንድ እንዲመጡ ጠራቸው። በቤቱም ለዓይን ያማረ ለመብላት ደስ የሚያሰኝ ፈታኝ ማዕድ እንዲያዘጋጁ ለአርድእቱ ተናገረ። እነርሱም እንዳላቸው አዘጋጁ።

እንግዶቹም በመጡ ጊዜ በየቦታቸው ተቀመጡ። የተዘጋጀውም መዓድ ከፊት ቀረበ። የምግቡ መዓዛ የምግብ ፍላጎት የሚከፍት ብቻ ሳይሆን የሰዎቹን ረሃብ የሚያባብስም ጭምር ነበር። ከዚያም ቅዱስ ዮሐንስ በቤቱ የሚያገለግለውን ዲያቆን ከመዝሙራት እያወጣ እንዲያነብ አዘዘው። ዲያቆኑም ረዘም ላሉ ሰዓታት ማንበቡን ቀጠለ። እንግዶቹ ግን ከመጎምዠት ብዛት በአፎቻቸው ምራቅ ሞላ። ጸሎቱ አልቆ እስኪመገቡ መቆየት ጣር ሆነባቸው።

አሁን ጸሎቱ ተጠናቋል። ይሁን እንጂ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን እንግዶቹን ለመዓዱ እንዲቀመጡ በመጋበዝ ፈንታ "በቃ ወደየቤታችሁ በሰላም ግቡ" ብሎ አሰናበታቸው። ወደ ቤቱ ተጠርተው የመጡት እንግዶችም ደነገጡ። ይህን ያየው ቅዱሱ "ምነው ግራ የገባችሁ ትመስላላችሁ? ምግቡን በደንብ አላያችሁትም? ልትበሉስ እጅግ ተመኝታችሁ አልነበረም?" ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም "አዎን" አሉት። አፈወርቅም "ጥሩ፤ እንግዲያውስ እንደ በላችሁ ይቆጠራላ" ቢላቸው ሁሉም ፈገግ አሉ። በዚህ ጨዋታ መካከል የእነዚያ ክርስቲያኖች ጥያቄ በሚገባ ተመለሰላቸው።

ክፉን ነገር በማሰብና በማድረግ መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ በዚህ ታሪክ ውስጥ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ክርስትና ሐሳብ እና ሥራን መቀደስ ነው። ነገር ግን የሐሳብ ንጽሕና ባይኖርህ "ማሰብ ከማድረግ ጋር እኩል አይደል!" ብለህ በኅሊናህ የቋጠርከውን ክፋት ለማድረግ ራስህን አታደፋፍር። ያሰብከውን እስካልፈጸምህ ድረስ አሁንም ከኃጢአት ወጥመድ የማምለጥ እድሉ በእጅህ ነው።

"ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት" ዘፍ 4፥7

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

29 Nov, 11:15


ከሰው ወገን ማንም እንደ እኔ ኀጢአት የሠራ በደለኛ የለም፤

እንደ አንተም ያለ መሐሪ ይቅር ባይ አምላክ አይኖርም፤


ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፣
ዓለማትን ኹሉ የፈጠርህ ፈጣሪ እንደ መኾንህ መጠን፥

በኋለኛው ዘመን በዓለም ላይ ለመፍረድ በምትመጣበት ጊዜ፥

ከጎንህ በፈሰሰው ደም
ኀጢአቴን እጠብልኝ!



መልክአ መድኀኔዓለም

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

28 Nov, 08:13


፨ግልጽ ነው ሚዛኑ፨


እንኳን ለመላዐኩ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

28 Nov, 08:11


#እሳት_ውሀ_ሲሆን

እሳት ቢንቀለቀል ነበልባል ቢያበራ
ዲኑ ውሀ ሆኖል በመላኩ ስራ
ብንገባ ከሳቱ ወጥተናል በግርማ
የሚያድነን መላክ መጥቶልን ከራማ
ዛሬም እሳት ቢነድ ገብርኤል ብለናል
እሳት ውሀ ሲሆን ዱራ ሜዳ አይተናል

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

24 Nov, 05:28


በመንፈሳዊ ሕይወት ለመለወጥ

#1ኛ የፀሎትን ህይወት ተለማመድ ተጠቀምበትም፣
#2ኛ ከመንፈሳዊ አባቶችና ሊቃውንት መ/ራን ምክርና ትምህርት አትራቅ
#3ኛ ከቅዱሳት መፃህፍት ጋር ያለህን ግንኙነት አዘውትር፣
#4ኛ የምትውልባቸውን ቦታዎች ፥የምታነባቸውን መፃህፍት፥ የምትመርጣቸውን ባልጀሮችህን ምረጥ፤ለመንፈሳዊ ህይወትህና ለሌሎች ወንድሞችህና እህቶችህ የሚያሰናክሉ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ፣
#5ኛ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ መሆንህን ዘወትር አትዘንጋ፣
#6ኛ ሃፍረትንና ፍርሃትን አስወግድ፥በራስህ ማስተዋልም አትደገፍ፣
#7ኛ አላዋቂነትህን ተቀበል 'እኔ ብቻ'፦ አትበል ውዳሴ ከንቱንም አትፈልግ፣
#8ኛ ለሰራሃው ሃጢአት ሳትዘገይ ንስሃ ግባ፣
#9ኛ ልበ ደንዳናነትንና አመፀኛነትን ከአንተ አርቃቸው፣
#10ኛ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ለመኖርና የቃሉ ሙላት በውስጥህ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር መኖርን ተለማመድ በቃሉም ፀንተህ ተገኝ፣
#11ኛ የቅዱሳንን ተጋድሎና ፍቅር በመመልከት እነርሱን ለመምሰል ትጋ፣
#12ኛ ከዚህ በፊት የነበርክበትን የሃጢአት ህይወት ኮንነው
#13ኛ ሰዎችን/ባልንጀራህን አፍቅር ከጥላቻም ራቅ፣
#14ኛ ነገርን ሁሉ ለበጎነው ብለህ ተቀበል። ጌታ ሆይ ይህን እንድናደርግ እርዳን አሜን ይቆየን።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

23 Nov, 05:04


አስተማሪ ታሪክ የመጨረሻው ክፍል

" ምነው አባ አልኳቸው ቀና ብዬ " ልጄ ምን እያልክ እንደሆነ እያወቅክ ስላልሆነ ነው ያስቆምኩህ በደላችንን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል ማለት እኮ እግዚአብሔርን እኔ የበደልኳቸውን ይቅር ካላልኩ አንተም እኔን ይቅር አትበለኝ እያልክ ነው አስተውል እኛ የይቅርታ ልብ ካለን እግዚአብሔር እኛን ይቅር ሊል ሁሌም ዝግጁ ነው ልብህን አታደንድነው አሉኝ ። "

" እሺ አልኩኝ አቀርቅሬ "

" እስኪ በድጋሜ አብረን እንጸልይ አሉኝ "

ድጋሜም ጀመርን ልክ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል ስል

" በድጋሜ አስቆሙኝና ከልብህ ይቅር ብለኸዋል አይደል ብለው ጠየቁኝ "

" አው ይቅር ብዬዋለው እንግዲያውስ ከልብህ መሆኑ እንዲረጋገጥ ሂድና አብረኸው ዘምር ትደርስበታለህ አሉኝ "

እሺ ብዬም በራቸውን ከፍቼ ስወጣ መዝሙር አስጠኚዬ በሩ ስር ቁጭ ብሏል ። ከዛም ዩኒፎርሙን አውልቆ ለእኔ ሰጠኝ ለራሱም ነጠላ ለበሰ አብረንም ዘመርን እኒዚያንም አባት ተመልሼ አገኘኋቸውና አመስግኜ የንስሐ አባቴ አደረኳቸው ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን

ተፈጸመ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

22 Nov, 17:15


አስተማሪ ታሪክ ክፍል ሁለት

በዚህ መሀል አንዱ ተናዶ በፑል እንጨት ወገቡን ሲለው ያኛውም ተናዶ የፑል ኳስ ወርውሮ ጉልበትን ሲለው ተያይዘው መጣላት ጀመሩ ። በዚህም መካከል አንድ በእድሜ ከ45 እስከ 50 የሚጠጋ ሰውዬ ለማገላገል ሲገባ የፑል እንጨት የያዘው ልጅ እግሩን መታውና ከጣለው በኋላ የሰውዬውን ፊት መርገጥ ጀመረ ሰውየው ደምበደም ሆነ ።

እኔ ግን በዚህ መሐል እንደ ሀውልት ደርቄ ቀረው የማወራውም ጠፋኝ ሹልክ ብዬም ከፑል ቤቱ ወጣሁ ወደ ቤቴ ሄጄም አረፍ ብዬ ማሰላሰል ጀመርኩ ። ይሄ የተረገመ መዝሙር አስጠኚ በእሱ ምክንያት ነው ይሄን ሁሉ የሆንኩት ደግሞ እሱን ብሎ ዘማሪ አውቀው የለ እንዴ ማን እንደሆነ እያልኩ አማርር ጀመር ። የሰውዬን መድማት ሳስብ ግን ልቤ ተነካ ከዛም እንደ ልማዴ ያስጫንኩትን ፊልም ካየሁ በኋላ ለጥ አልኩኝ ። ቀን ላይም በወንድሜ ስልክ ቤት ስሰራ ውዬ እቤት ገብቼ አረፍ ስል ሄኖክ እቤት መጣና

" ና እንሂድ አለኝ "

" እንሂድ ትላለህ እንዴ ትላንት የሆንኩትን እረሳህ ድጋሜ ድርሽ አልልም ዛሬ እንደውም ፑል ቤት ነው የማመሸው ስለው "

ምንም ሳይለኝ ወጣና ሄደ ከዛም እጄ ላይ የነበረውን ብር ይዤ ፑል ቤት ገሰገስኩኝ እዛም እየተጫወትኩ ሳለ መዝሙር አስጠኚዬ እስከነ የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርሙ መጣና

" ዳኛ አለ እሺ አለ። " ፑል ቤት ያሉት በሙሉ ደንግጠው ያፈጣሉ እኔም ግራ ገብቶኝ አፌን ያዝኩኝ ። ከዛም ሼም እየያዘኝ

" እዚህ ምን ትሰራለህ ይሄ ቦታ እኮ ላንተ አይሆንም አልኩት አቀርቅሬ ። "

" ተው እንጂ ለአንተስ ይሆናል ማን ነው ያለው አንተ ካለህ እኔም አለው አብረኸኝ ከሄድክ እሄዳለው አለኝ "

" ሁለተኛ እዛ ሰንበት ላልደርስ ምያለው አልኩት ። "

" አውቃለው ትላንት እንዳስቀየምኩህ ግን እንደዚህ ትሆናለህ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር ። ያንን ነገር በማድረጌ ግን ደስተኛ ነኝ ሁሉም ካንተ ስህተት ተምሮ መዝሙር ሲያጠና silent አድርጎ ነበር ። ዛሬም ዩኒፎርም ስንለብስ አንተን ፈልጌ አጣውህ ከዛም ሄኖክን አናግሬው ወደዚህ መጣው ። የመጣሁት ፑል ለመጮት እንዳልሆነ ታውቃለህ ። ይቅርታ ልጠይቅህ እንጂ ! አንተን አስቀይሜ በእግዚአብሔር ፊት ብዘምር ትዕቢት ይሆንብኛልና አሁን ተነስና እንሂድ የእኔም የአንተም ቦታ እዚህ አይደለም አሁን ሳይረፍድብን ቶሎ እንሂድ አለኝ ።"

" እሺ እሄዳለው ግን መዘመር አልፈልግም አልኩት እየተነጫነጭኩ ። "

ከዛም ሰንበት ትምህርት ቤት እስክንደርስ ድረስ በዝምታ ተጓዝን የመዝሙር አስጠኚዬም ሌሎቹን ተማሪዎች

" እናንተ መዘመር ጀምሩ እኔ እደርስባችኋለው ብሎ ና እንሂድ አለኝ "

ተከትዬው ሄድኩኝ ከዛም አንድ አባት ቤት ደረስንና ገባን ። መስቀል ከተሳለምን በኋላም

" አባቴ ይሄንን ወንድሜን አስቀይሜዋለው ። ይቅርታም ጠይቄዋለው ግን እርሱ ከልቡ ይቅር አላለኝም እንዲያስታርቁኝ እፈልጋለው አላቸው ።"

" አባም ምንድን ነው የለበስከው ብለው ጠየቁት "

" ዛሬ ኪዳነምህረት ናት እንዘምራለን አሁን እንደውም መዘመር ሊጀምሩ ነው አላቸው። "

" ሂድና ዘምረህ ስትጨርስ ተመለስ ከእሱ ጋር እስከዛ እኔ ላውራ አሉት ። "

ከዛም የሆነውን ነገር ጠየቁኝና ከመለስኩላቸው በኋላ

" ልጄ ተነስና አብረን ጸሎት እንጸልይ አሉኝ " እኔም እሺ አልኩኝና አባታችን ሆይ ብለን መጸለይ ጀመርን ። ልክ በደላችንን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል ስል እዚህ ጋር አቁም አሉኝ ምነው አባ አልኳቸው.....

ይቀጥላል

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

22 Nov, 05:24


አስተማሪ ታሪክ ክፍል አንድ

የሰንበት ተማሪ ነኝ ሄኖክ እባላለው ። መስከረም 15/2015 ከምሽቱ 12 ሰአት ነበር ። ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት ከጓደኛዬ ጋር ለማጥናት እየሄድን ነው ። በመሀልም እኔ ስለ ሰንበት ትምህርት ቤታችን እንደዚህ ብዬ ማውራት ጀመርኩ

" አሁን ያሉት ሥራ አመራሮች ቢነሱ ሰንበት ትምህርት ቤታችን እንደሚያድግ አልጠራጠርም ። እነርሱ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ሸክም ሆነውብናል ። ብዙ ተማሪም ከሰንበት ትምህርት ቤታችን እየወጣ ያለው በእነሱ ምክንያት ነው እላለው ። አንድ ደህና ሰው እኮ የለም ጠፍተህ ብቀር እንኳን ማንም አያስታውስህም ። "

ከዚህ በተጨማሪም ብዬ ልቀጥል ስል ሄኖክ አስቆመኝና

" ይሄን ነገር ነግሬሀለው ስለ እንደዚህ አይነት ጉዳይ ማውራት አልወድም ። እኔ እነርሱን ለማገልገል አልመጣሁም እግዚአብሔርን እንጂ ። ከቻልክ የእነርሱን ድክመት ማውራት ትተህ አቅምህ በቻለው ሁሉ የተሰጠህን ሥራ ስራ ። እግዚአብሔር ለፍርድ ሲመጣ የሚጠይቅህ እነርሱ ምን አድርገዋል ብሎ ሳይሆን አንተ ምን አድርገሀል ብሎ ነው ። ምሳሌም ከፈለክ በአቢይ ጾም በገብርሔር ሳምንት የምንማረውን ታሪክ ማወቅ በቂ ነው ። ጌታችን ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት ለአንዱ አንድ መክሊት ሰጥቷቸው ሄዶ ሲመለስ የጠየቃቸው ስለየራሳቸው መክሊት እንጂ ስለ ሌላው አይደለም ። መክሊቱን ቀብሮ የተገኘው ተቀጣ በመክሊቱ አትርፎ የተገኘው ደግሞ በብዙ ተሾመ ። እኔም አንተም መክሊት ተሰጥቶናል ትኩረት ማድረግ ያለብን የራሳችን መክሊት ላይ ነው ። ስለሌች ስናወራ የእኛን መክሊት ሳንጠቀምበት እንቀራለንና እና ስለሌሎች ድክመት ማውራት አቁመን እራሳችን ላይ እንስራ እያለ ምክሩን ቀጠለ ። "

እኔም ለጊዜው በሐሳቡ ተስማምቼ ዛሬ ስለምናጠናው መዝሙር ማውራት ጀመርን ።

ጓደኛዬ በጭራሽ ስለ ሌላ ሰው ማውራትም ሆነ መስማት አይፈልግም ። በዚህ ምክንያት ብዙ ሰንበት ተማሪዎች ጓደኛቸው ሊያረጉት ይፈልጋሉ ። እሱ ግን ብዙም መቀራረብ አይፈልግም በሰንበት ትምህርት ቤትም የሚሄደው ለሁለት ምክንያት ነው አንደኛው የተሰጠውን ስራ ለመስራት እና ለመዝሙር ጥናት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለማንበብ ነው ከዛ ውጪ እግሩን አያነሳም ።

እኔ ግን እዚህም እዛም ጓደኞች አሉኝ ከሁሉም ጋር እየተመሳሰልኩ አብሬያቸው እሆናለው ።
ከእነዚህ ጋር ስሆን እነዛን አማለው ። ከእነዛ ጋር ስሆን እነዚህን ማማት እጀምራለው ። ሀሜት ለእኔ እንደ HIV መድኃኒት ያልተገኘለት በሽታዬ ሆኗል ። ግን ሰዎችን አምቼ ከጨረስኩ በኋላ ህሊናዬ በጣም ይወቅሰኛል ። የሕሊናዬም ጩኸት ችላ ብዬ በነጋታው ህሐሜቴን እቀጥላለው ። ትንሽም ቢሆን ማማት የማቆመው ከሄኖክ ጋር ስሆን ነው ።

ሰንበት ትምህርት ቤት እንደደረስን ወደ ጥናት ገባን ጥናት ጀምረንም 20 ደቂቃ ካለፈ በኋላ ስልኬ መጮህ ጀመረ ። በዚህ ጊዜ መዝሙር የሚያስጠናን መምህር በአይኑ ገላመጠኝ ። በዚህም ምክንያት ተናድጄ ጥናቱን አቋርጬ ወጣው ። በልቤም ሁለተኛ ሰንበት ድርሽ አልልም እያልኩ መዛት ጀመርኩ ።

ሰፈር ስደርስም የሰፈሬ ልጅ ከፑል ቤት ሆኖ እያፏጨ መጣራት ጀመረ ።

ከዛም ወደ ፑል ቤት ሄጄ ቁማር መጫወት ጀመርኩ በዚህ መሀል ግን ክርክር ተነሳ ። የክርክሩ ዋና ምክንያት እኔ ፑል መጫወት ስለማልችል የእኔን ብር ለመብላት ሁለት ልጆች ከእኔ ጋር ነው የሚጫወተው አይ ከእኔ ጋር ነው የሚጫወተው እየተባባሉ ይጨቃጨቃሉ ። በዚህ መሀል አንዱ ተናዶ.......

ይቀጥላል

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

21 Nov, 05:06


እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

19 Nov, 04:21


+++የሚጠብቅ ሕግ+++

እንደ ጎርጎርዮሳውያኑ አቆጣጠር በ1847 ዓ.ም. በኦስትሪያ ቬና ውስጥ በሚገኝ በአንድ ሆስፒታል ዕውቁ የማኅፀን ሐኪም የነበረው ኢግናዝ ሴሞቫይስ (Ignaz Semmelweis) በዳይሬክተርነት ይሠራ ነበር፡፡ እርሱም በሚመራው የሕክምና ክፍል (ward) ብዙ በእርግዝና ያሉ ሴቶች እየመጡ የጤና ክትትል ያደርጋሉ፡፡ በአጠቃላይ ከሚመጡት እርጉዝ ሴቶች መካከል ከስድስቱ አንዷ በዚያ ክፍል ምርመራ የተደረገላት ሴት በኃይለኛ ንዳድ ተይዛ ትሞት ነበር፡፡ የእነዚህም ሟች ሴቶች አስከሬን ሲመረመር ከቆዳቸው በታች ባለው የሰውነት ክፍላቸው፣ ደረታቸው አካባቢ ባለው ክፍት ቦታ እና የዓይኖቻቸው ኳሶች በተቀመጡባቸው ሰርጓዳ ክፍሎች ውስጥ መግል ይታይ ነበር፡፡ ሴሞቫይስም እርሱ በሚመራው የሆስፒታሉ ዋርድ ሆነ በአጠቃላይ በአውሮፓ ውስጥ በሚገኙት ሆስፒታሎች ውስጥ እየታየ ባለው የእናቶች ሞት እጅግ ተጨነቀ፡፡

አንዲት ያረገዘች ሴት ለዚህ ሥራ ብቻ በተመደበች አዋላጅ አማክኝነት ስትወልድ የሞቱ መጠን ወደ 3% የሚቀንስ ሲሆን፣ የዚያች እርጉዝ ሴት ምርጫ የተሻለ ልምድና ዕውቀት ባላቸው እና በቀን ብዙ ታካሚ በሚጎበኙ ሐኪሞች እጅ መውለድ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ የሞቱ መጠን ወደ 18% ያሻቅብ ነበር፡፡

ዶ/ር ሴሞቫይስ ይህ ባረገዙ ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን እልቂት ለመግታት ብዙ ጥረት ቢያደርግም የሞታቸውን ቁጥር ግን ሊቀንስ አልቻለም፡፡ እንደውም ቢጨንቀው በአካባቢው ሌሊት ወደ መቅደሱ ሲገባ ካህኑ የሚደውለው የቤተ ክርስቲያን ደወል እያስደነገጣቸው ይሆናል የሚታመሙት ብሎ በማሰብ ካህኑን በጸጥታ ወደ መቅደስ እንዲገባ አድርጎም እንደ ነበር ተጽፏል፡፡ ይሁን እንጂ ነገሩ አንድም መፍትሔ ጠብ አላደረገም፡፡

ታዲያ ዶክተሩ በዚህ አጣብቂኝ መካከል ሆኖ ሲያሰላስል ሳለ አንድ ነገር ተመለከተ፡፡ ይኸውም በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ ወጣት የሕክምና ተማሪዎች የተለመደውን የእለት ክንውናቸውን፣ ማለትም የሞቱትን እናቶች አስከሬን መመርመር፣ ቀጥለውም በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ባለ በደም በደፈረሰ ውኃ እጆቻቸውን በመለቅለቅ የጋራ በሆነ ፎጣ አድርቀው በቀጥታ ለሕክምና የመጣችን ሴት የአካል ምርመራ ሲያደርጉ አየ። በርግጥ ይህን የመሰለው ተግባር pathologyን ለተረዳ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለሚገኝ ሰው በጣም እንግዳ ሊሆንበት እና “እንዴት?!” ሊያስብል ይችላል፡፡ ‹በጤነኛ አእምሮው ያለ አንድ ሐኪም የሞተን አካል በነካ እጁ ምንም ዓይነት የንጽሕና መጠበቂያ ጥንቃቄ ሳያደርግ እንዴት በሕይወት ያለችን ሴት ሰውነት መልሶ ይመረምራል?› ብሎ መጠየቁም አይቀርም፡፡ ነገር ግን በአውሮፓው ዓለም በአሥራ ዘጠነኛው ምእት ዓመት አጋማሽ "ጀርም" የሚባለው በሽታ አምጪ ስውር ሕዋስ የማይታወቅ እንግዳ ሐሳብ ነበር፡፡ በማጉያ መሳሪያም አይተውት አያውቁም፡፡ ከፍተኛ ጥፋት የማምጣት ኃይሉንም ገና በሚገባ አልተገነዘቡም ነበር፡፡

ዶ/ር ሴሞቫይስም እርሱ ባለበት ዋርድ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ሁሉ ማናቸውንም አካላዊ ምርመራ ከማድረጋቸው በፊትም ሆነ ካደረጉ በኋላ እጃቸውን በክሎሪን ውሕድ እንዲታጠቡ ጥብቅ ትእዛዝ አወጣ፡፡ ይህ በሆነ በሦስት ወራት ውስጥም የእናቶች ሞት መጠን ከ18% ወደ 1% ወረደ፡፡ ሐኪሙ ሴሞቫይስ የAntiseptic ጉዳይ ወደ ሕክምናው ትግበራ እንዲገባ በማድረግ የብዙ እናቶችን ሕይወት በመታደጉ በዚህ አስደናቂ ግኝቱ እስከ ዛሬ ድረስ በታሪክ ሲመሰገን ይኖራል፡፡

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን ለሚያነብ ሰው ግን ይህ ነገር በዶክተር ሴሞቫይስ የተገኘ ሳይሆን፣ ከ3300 ዓመታት በፊት እግዚአብሔር በሙሴ በኩል የሰጠው ትእዛዝ እንደ ሆነ ይረዳል፡፡ ትእዛዙም ‹‹የሞተውን ሰው በድን የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፡፡ በዚህም ውኃ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያጠራል፡፡ ንጹሕም ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያጠራ ንጹሕ አይሆንም›› የሚል ነበር። (ዘኁል. 19፤11-12) ዓለም ፈጽማ ስለ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን ዕውቀቱ ባልነበራት ጊዜ እግዚአብሔር ሕዝቡን በቃሉ ይጠብቅ ነበር። አሁንም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንመለስ፣ እንመርምረው፣ የጥበቦች መጀመሪያ ሆኖ እናገኘዋለን። እርሱም በነፍስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሲመራን፣ በሥጋ ደግሞ የሚጠቅመንንም ምክር አያስቀርብንም። ሕጉ የተሰጠን እንድንጠብቀው ብቻ ሳይሆን ሊጠብቀንም ጭምር ነው።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

18 Nov, 13:24


ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች

አሐቲ ድንግል የሚለውን የአባ ገብረ ኪዳንን መጽሐፍ አዲስ አበባ ያላችሁ ወንድም እህቶቻችን
ኃይለ ማርያም ነው የላከን በማለት በ 900 ብር እንዲሁም ሌሎች መጽሐፍትን በ 30% ቅናሽ በሰርዲኖን መጽሐፍ ቤት ማግኘት ትችላላችሁ ።

አድራሻ፦ አምስት ኪሎ ምስራች ማእከል አጠገብ በሚገኘው የገበያ ማእከል ውስጥ፥ ለበለጠ መረጃ

0910934578 ( ራሔል )
0973180001 ( ኃይለ ማርያም )

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

17 Nov, 17:28


."... እመ አምላክ እኛንም እንዲመልሰን ለምኝልን"
እመቤታችን የሕይወታችን የማዕዘን ራስ የተቀመጠባት ጽዮን።መለኮትን የመሸከም ኃይለ ድንግልና ያላት ተማምነው የሚጠጉባት ሀገረ ምስካይ!ፊትን ወደ እርስዋ ባዞሩ ጊዜ የድኅነት ብርሃን የሚወጣባት እመ ብርሃን።የተዳደፉትየሚነጹበት የደስታ ፏፏቴ የሚፈልቅባት የታተመች የውኃ ጉድጓድ።ዓለምን የሚያጠግብ ፍሬን የተመላች የታጠረች ገነት።የደስታውን ዘለላ ያፈራችው የወይን ሐረግ።ከጉድጓድ ወጥተን እስከ ሰማይ የምናርግባት ረጅሚቱ የወርቅ መሰላል።ማዕዷ የማይታጠፍ ሲሳየ ዓለምን በውስጧ የያዘች መሶበ ወርቅ።ንጉሥ ክርስቶስ ተገልጦ የነገሠባት የፍትሕ አደባባይ።በእሳተ ገሃነም ለነደዱ የምሕረት ዝናም ይዛ የደረሰች ፈጣን ደመና።እርሱዋ እናቴ ልጅዋ አምላኬ ከሆነችልኝ የምሻው ይህንን ነው።
እርስዋ እናቴ መሆኗን የማስብበትን ያህል የሚያበረታኝ ምንም የለም።

እመቤቴ ሆይ ከስደት እንደተመለስሽ ከቤታቸው፣ ከሀገራቸው የተሰደዱትን እንዲመልስ ከልጅሽ አማልጅን።ከእውነት በሐሰት፣ ከእምነት በክሕደት የተሰደዱትን መልሻቸው።ከትሩፋት በሐኬት የወጣነውንም መልሽን።ከሥደት ስትመለሺ በቃል ኪዳን የተቀበልሻት ኢትዮጵያን መከራዋ አብቅቷል የሚሉ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንና ሚካኤልን እንዲልክልን ልጅሽን ለምኝልን።

አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ኅዳር ፮-፫-፳፻፲፯ ዓም.
ሜልበርን አውስትራሊያ.

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

16 Nov, 17:34


ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ብልም ዝገትም በማያጠፋው ሌቦችም ቆፍረው በማይሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ ። " ( ማቴ 6፥20 ) ሲል ለነዳያን መጽውቱ ማለቱ ነው ። ከርሠ ነዳያን በሰማይ ያለ መዝገብ ተብሏል ። ይህ መዝገብ ዝገት ወይም ብል አያጠፋውም ። ሌቦችም ሊሰርቁት አይችሉም ። እኛ የነዳያንን ሆድ ስንሞላ ልባችን በጸጋ መንፈስ ቅዱስ ይሞላል ።

ቃላተ ወንጌል ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ ገጽ 43

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

15 Nov, 18:50


ክርስቶስን ይዤ በድንግል ታግዤ
መስቀሉን አንግቤ አኑሬው ከልቤ
ይሁንልኝ ሞቴ ፀንቼ በእምነቴ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

15 Nov, 16:48


ለክብርሽ ተደርሶ፥ ለፍቅር የተቆመ፤
ሥሙር ማኅሌትሽ፥ በቸር ተፈጸመ፤
ድንግል እመቤቴ፦
የኛ መከራ ግን፥ አለቅጥ ረዘመ!

እንኳን አደረሰን!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

14 Nov, 07:59


#መጽሐፍ_ቅዱስ

በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱን ማንበብ ጀመረ፡፡

አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡

ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመለስ ብለው” ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ! እዲሁ ነው የምደክመው እንጅ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡

ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡

ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እደሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     https://t.me/dnglemaryamenate

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

12 Nov, 17:46


+ ለእንቅልፋሞች መልካም ዜና +

እንቅልፍ ሲበዛ የስንፍና ምልክት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው:: "ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፤ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ” ፤ “የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳል" የሚሉት ጥቅሶች ለዚህ ምስክር ናቸው:: (ምሳሌ 20:13 ፣ 23:21)

ሆኖም በእንቅልፋቸው የተጠቀሙ ብዙ ሰዎችም አሉ:: አንቀላፍቶ ሚስቱን ያገኘው አዳም እንዴት ይረሳል? ከኤሳው ጋር ሲታገል የኖረው ያዕቆብ ሲባረክ ያደረውስ በእንቅልፉ አልነበር? ያዕቆብማ ምነው ባልነቃ ያሰኛል:: ሰማይ ድረስ መሰላል ወጥቶ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ያየው በእንቅልፉ ምክንያት ነበር:: በባቢሎን ምርኮ ዘመን የነበረው አቤሜሌክ ደግሞ የእንቅልፋሞች ንጉሥ ቢባል አያንስበትም:: የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየኝ ብሎ ሲጸልይ የነበረው ይህ ሰው በፈጣሪ ፈቃድ ለስድሳ ስድስት ዓመታት ያህል ተኝቶ ነበር:: ከእንቅልፉ ሲነሣም እንቅልፍ ሳይጠግብ እየተበሳጨ ነበር:: ማንቀላፋቱ ግን ብዙ ጉድ ከማየት አዳነው:: (ተረፈ ኤርምያስን ይመልከቱ)

ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የአቤሜሌክን የእንቅልፍ ክብረ ወሰን የሰበሩ ሰባቱ እንቅልፋሞች (The Seven Sleepers) የተሰኙ ቅዱሳንን እንተዋወቅ:: ወቅቱ የሮም ነገሥታት አላውያን የነበሩበት ክርስቲያኖች በግፍ እየተገደሉ የነበረበት ዘመነ ሰማዕታት ነው:: ክርስቲያን መሆን ወንጀል በነበረበት በዚያ ወቅት ክርስቲያኖች ከአንበሳ ጋር እየታገሉ በመስቀል እየተሰቀሉ በሰይፍ እየተቀሉ እየሞቱ የነበረበት ዘመን ነው::

በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት (249-251) ታዲያ በንጉሣዊ ምክር ቤቱ ውስጥ አባል የነበሩ ሰባት ወጣት ልዑላን ድንገት ክርስትናን ተቀብለው "ለጣዖት መሥዋዕት አንሠዋም" ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ ወጣቶቹ ይህን በማድረጋቸው የሚከተለውን ጽኑ ቅጣት ያውቁ ነበረና ፈርተውም በቅርብ ወዳለ አንድ ተራራ ሸሽተው በዋሻ ውስጥ ተደበቁ።


በዚያ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው እያሉ ታዲያ ሰባቱንም እንቅልፍ ይጥላቸዋል፡፡ ንጉሥ ዳክዮስ አሳድዶአቸው ሲመጣ ተኝተው እንዳሉ ያያል:: አውሬው ንጉሥ ሁኔታውን ሲያውቅ እዚያው ዋሻ ውስጥ ይሙቱ ብሎ የዋሻውን መግቢያ በር በግንብ አስደፍኖት ሔደ፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ወጣቶቹ እንቅልፍ ላይ ናቸው::

ከመቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ዓመታት ገደማ ከሆነ በኋላ እነዚህ ወጣቶች ከእንቅልፋቸው ይነቁና የረሃብ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ከእነርሱ አንዱን ወደ ከተማ ሔዶ ምግብ እንዲገዛላቸው ይልኩታል፡፡

ዋሻው የተዘጋበት በር ከዘመን ብዛት ፈርሶ ነበርና የተላከው ወጣት ከዋሻው በቀላሉ ወጥቶ ወደ ከተማ አቀና፡፡ ወደ ከተማ ገብቶ ለሰባቱም የሚበቃቸውን ምግብ አገኘና ሂሳብ ሊከፍል ከኮሮጆው ሳንቲም አወጣ፡፡ ያወጣው ገንዘብ ግን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት መገበያያ የነበረውን 'የጣዖት አምላኪዎቹን' ነገሥታት የወርቅ ሳንቲም ነበር። ሰባቱ ያንቀላፉ ቅዱሳን ከእንቅልፍ የነቁበት ያ ዘመን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ የኤፌሶን ከተማ ሙሉ በሙሉ ክርስቲያናዊት ከተማ በሆነችበት ደግ ዘመን ነበር፡፡


የሰባቱ ወጣቶች ዝና ወዲያው በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያን ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ደረሰ፡፡ ወጣቱ ወደ ዋሻው ከተመለሰ በኋላ ግን ሰባቱም ቅዱሳን ድጋሚ እንቅልፍ ጣላቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሲተኙ ግን እስከወዲያኛው በክብር አሸለቡ፡፡ ለእነዚህ ሰባት ሰማዕታት በሥፍራው ትልቅ ቤተ መቅደስ ተሠርቶላቸዋል፡፡

"እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ" መዝ.3:5

“የኤፌሶን ወንዝ” ገፅ 64 የግርጌ ማስታወሻ ላይ የተወሰደ

ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እድሳት የሚውለው የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ የመጀመሪያ እትም እያለቀ ነው:: እርስዎ እጅ ገብቶ ይሆን?

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

11 Nov, 18:21


#ዋናው_እኔ_ነኝ

ብዙ የበደሉህ ዋኖች ይኖራሉ እንደ እኔ ግን አልበደለሁም፣ አንተን ያስከፉህ ቢሰለፉ ከፊት የምገኘው እኔ ነኝ፣ በኃጢአት ባህር መዋኘት ድሎት የሆናቸው ብዙ አሉ ዋናው ግን እኔ ነኝ፣ ልክ ባልሆነው ጎዳና የሚራመዱ አሉ መሪያቸው ግን እኔ ነኝ፣ አንተን በመቅረብ ፈንታ ጀርባ የሰጡህ አሉ እኔ ግን እብሳለሁ፣ ጌታዬ መድሃኒቴ ኢየሱስ አንተን የምትል ነፍሴ በስጋ ድካም ውስጥ ሳለ አለሁሽ ያልካት አንተ ነህ።

እኔ መማርህ እንዴት ያለ ምህረት ነው። የምህረትህ ድልድልነት ለእያንዳንዱ መንገዴ መሸጋገሪያ ሆኖኛል። እኔን ለማዳን ወደዚች አለም የመጣ አስታዋሼ አንተ ነህ። ከነ ኃጢያቴ እንዳልጠፋ እኔ ባለሁበት ተገኝተህ ያገኘኸን ፈላጊዬ ነህ፣ በሞት ጥላ ውስጥ ያለሁትን በደምህ ድምጽ የጠራኸኝ ባለውለታዬ አንተ ነህ፣ በምድረበዳው ብቻዬን ስባዝን ና ወደ እኔ ያልከኝ አስጠጊዬ አንተ ነህ።

እኔ ብቻ እንኳን በኃጢያት የጠፋው ብሆን የራስህ ጉዳይ ብለህ ከነበደሌ የማትተወኝ ለእኔ ብቻ እንኳን ብለህ ልትሞትልኝ የምትመጣ አፍቃሪዬ ነህ። ለእኔ ስትል ሰው የሆንክ አምላኬ ክርስቶስ ሆይ ክበር ተመስገን። እኔን ዋናውን ለማዳን ስትል ከሰው ተርታ ተገኝተህ በሰው ልክ የተመላለስክ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ተመስገን።

ወደ ክብሬ ልትመልሰኝ ክብርህን እንደመቀመት ሳትቆጥር ከላይ ከሰማያት የመጣህልኝ አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ። እኔን ከማርከኝማ እኔን ይቅር ካልከኝማ ማንም ትምራለህ። እኔን ዋናውን ከተቀበልክማ መዳፍህ ሰፊ ነው ሁሉን ይቀበላል።

ለእኔ ስለሆነው በጎነትህ ክብር ይሁንልህ። አሜን

“ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤”  1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥15

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

11 Nov, 05:27


ኀበ ሀለወት ብዝኅት ኃጢአት በህየ ትበዝህ ጸጋ እግዚአብሔር። ሰአሊ ለነ ቅድስት

ብዙ ኃጢአት ባለችበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች።ቅድስት ሆይ ለምኝልን

የሰኞ ውዳሴ ማርያም

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

09 Nov, 11:10


+++ ቅዱስ ሉቃስ እና ቅዱስ ኤፍሬም በቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ +++

X. P. ሲል ስሙን በምሕጻር ያስቀመጠ አንድ የ46 ዓመት ጎልማሳ በቅዱሳኑ የተደረገለትን ተአምር እንዲህ ያወጋናል።
"ስሜ X. P. ይባላል። እድሜዬ አርባ ስድስት ዓመት ሲሆን በሰሜናዊው የግሪክ ክፍል ነዋሪ ነኝ። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2004 ዓ.ም ናላዬ ላይ በተፈጠረ እጢ (Brain tumor) አማካኝነት የቀዶ ሕክምና አድርጌ ነበር። ነገር ግን ይህ ከሆነ ከሦስት ዓመት ከስድስት ወር በኋላ እንደገና እጢው በናላዬ ላይ ታየ። በዚህም ምክንያት ብዙ ዶክተሮች ጋር የሄድኩ ቢሆንም አንዳቸውም ግን ቀዶ ጥገና ሊያደርጉልኝ ፈቃደኛ አልነበሩም። በዚህም ተበሳጭቼ እና ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብቼ ነበር።

በመጨረሻም ይህን አስቸጋሪ ቀዶ ጥገና ለማድረግ የተስማማ አንድ ሐኪም አገኘሁ። አንዳንድ የቅርብ ዘመዶቼም የታመሙትን የሚረዳ ባለመድኃኒት የሆነውን ቅዱስ ሉቃስን እንዳከብረው እና ሌሎች ሕሙማንን እንደረዳ እኔንም ይረዳኝ ዘንድ እንድማጸነው ነገሩኝ። እኔም በሁኔታው ተሰማምቼ ቅዱሱን ለማክበርና ለመማጸን ሕንጻ መቅደሱ ወዳለበት የግሪክ ከተማ ተጓዝኩኝ። በዚያም እጅግ የዋህና ትሁት የሆነ አንድ ካህን አገኘሁ (የእርሱንም ስም በምሕጻር Fr. K ይለዋል)።

እርሱ ጥንካሬና ብርታትን ሰጠኝ ፣ ጸሎትም አደረገልኝ። እኔም ኃጢአቴን ተናዝዤ ሥጋ ወደሙን ተቀብዬ ፤ የቀዶ ጥገናው ቀን በመቃረቡ ወደ መጣሁበት ተመለስኩ። ከእለታት በአንደኛው ምሽት በሕልሜ ቅዱስ ኤፍሬምን አየሁት። እርሱም እንዳልረበሽና ነገሮችም በጥሩ ሁኔታ እንደሚሄዱ ነገረኝ።

በመጋቢት 13 ፣ 2007 ዓ.ም ቀዶ ጥገና ወደሚደረግበት ክፍል ገባሁ። ምንም በመድኃኒት የደነዘዝኩ ብሆንም እንኳን ፤ ከቅዱስ ሉቃስና ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር ሆነው ቀዶ ጥገናውን የሚያደርጉትን ፤ ትንንሽ ክብ መነጽር ያደረጉና ስለቶች በእጃቸው የያዙ ሐኪሞችን ማየት እችል ነበር። ቅዱስ ኤፍሬም እንዳልፈራ እየነገረኝ እጄን ይዞታል ፤ በግራ እጁ ደግሞ ራሴ አካባቢ የሚያበራ መብራት ይዞ ነበር።

ቀዶ ጥገናው እንደተጠናቀቀም ወደ ከፍተኛ ክትትል ክፍል ወሰዱኝ። በዚያም ድጋሚ ቅዱስ ሉቃስ መጥቶ "በቀዶ ጥገናው ክፍል ውስጥ አብሬህ ነበርኩ" አለኝ። እኔም "አውቃለሁ" ብዬ መለስኩለት። አስቀድሞ ከቀዶ ጥገናው ክፍል ስወጣ ሐኪሙ "እንዲህ ዓይነት ሕመም ሆኖ ነገር ግን ቀላል ቀዶ ጥገና ሳደርግ የመጀመሪያዬ ነው።" እያለ ሲነግረኝ ሰምቼዋለሁ።

ከዚህ በፊት ስለ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም። አሁን ግን በዙሪያዬ የሚከቡኝ ጠባቂዎቼ ሆነዋል።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

08 Nov, 12:36


“በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥
የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።”
መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።”
መዝ 37፥4-5

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

06 Nov, 08:34


ከሰው ወገን ማንም እንደ እኔ ኀጢአት የሠራ በደለኛ የለም፤

እንደ አንተም ያለ መሐሪ ይቅር ባይ አምላክ አይኖርም፤


ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፣
ዓለማትን ኹሉ የፈጠርህ ፈጣሪ እንደ መኾንህ መጠን፥

በኋለኛው ዘመን በዓለም ላይ ለመፍረድ በምትመጣበት ጊዜ፥

ከጎንህ በፈሰሰው ደም
ኀጢአቴን እጠብልኝ!



መልክአ መድኀኔዓለም

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

05 Nov, 17:26


ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይፀልያሉ አንደኛው ፀሎቱ ተመለሰለት አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ፀሎቱ ያልተመለሰለት ሰው "ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ፀልየን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ ከለከልኝ ለምንድ ነው?" አለው። እግዚዘብሔርም "ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ደግሞ ትጠፋለህ" አለው ይባላል።

እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሳቱም ሁለቱም በፍቅር ነውና በልመናችን በፀሎታችን የአንተ ፈቃድ ይሁንልን ማለት ተገቢ ነው። ስለሁሉም የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን። አሜን!!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

05 Nov, 10:54


🌿 ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡

ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡

አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡

የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቅፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡

እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡

በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳  እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡

ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡

የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡

ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’
ብዬ ላመስግነው፡፡

ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡

የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ”

•• ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

[ የብርሃን_እናት - ገፅ 305-308]

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

31 Oct, 18:41


“ጌታ ሆይ እኛ ከራሳችን ስላንተ መናገር የምንችል አይደለንም"
💠የመዝሙረ ዳዊት ጉባኤ ተዘክሮ 💠
ክፍል 1
Size:-13.7MB
Length:-59:54

🎤በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን👂

https://t.me/dnglemaryamenate

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

31 Oct, 18:37


አቡነ ዮሐንስ የተባሉ አባት በየሳምንቱ ሐሙስ ሐሙስ በአቅራቢያቸው ወዳለ አንድ መንደር ለማስተማር ይሔዱ ነበር።
በግብፅ እንደተለመደው ወደዚያች መንደር ለመሔድ ሲሳፈሩ ከአንድ ሌላ ሰው ጋር መዳበል ነበረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ አክራሪ ሙስሊም ሁልጊዜ በተመሳሳይ ሰዓት አብሯቸው ይሳፈር ነበር፡፡ ሊሳፈሩ ሲገቡ ታዲያ ፊቱን ዞር ያደርግና ይተፋ ነበር! ይህን አስነዋሪ ድርጊት ለዓመታት ይፈጽም ነበር፡፡ አንድ ቀን ጳጳሱ ሊሳፈሩ ሲመጡ ያ ሰው አልነበረም ፡፡

አቡነ ዮሐንስ ከልባቸው አዝነው እግዚአብሔርን መጠየቅ ጀመሩ ‹‹ጌታዬ ይህንን በረከት ለምን አስቀረህብኝ? ይህንን በረከት ከዚህ በላይ እቀበል ዘንድ እንደማልገባ የወሰንከው በኃጢአቶቼ መብዛት ይሆን?››

ሌላው የተቀደሰ ትውስታ ባለቤት ደግሞ የማይታክቱት የእግዚአብሔር ሠራተኛ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤል ነበሩ፡፡ እኚህ አባት እንደተለመደው ብዙ ጠላቶች ነበሯቸው 1 እጅግ አስጸያፊ መልእክቶችን እየጻፉ በደብዳቤ መልክ ይልኩላቸው ነበር፡፡ እሳቸውም እነዚህን አስጸያፊ ስድቦች በመሳቢያቸው ውስጥ ያስቀምጡአቸው ነበር፡፡ በሚከፋቸውና በሚተክዙ ጊዜ ማኅደራቸውን ከፍተው እነዚህን ደብዳቤዎች ያነብቡ ነበር ! ከዚህ በኋላ የመታደስ ስሜት ይሰማቸዋል ምክንያቱም ነቀፋዎቹን ሲያነብቡ በእያንዳንዱ ስድብ ውስጥ በረከት እንዳለ ስለሚያዩ ነበር፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የምናነብበውን በልባችን ውስጥ መትከል የምንለው እንግዲህ ይህንን ነው፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

30 Oct, 09:32


ከመሬት የተገኘች ሰማይ ከሰማይ የሰፋች አለም ። እግዚአብሔር ለእግዚአብሔርነቱ በራሱ ለራሱ ያበጃት መቅደስ። ኮሬብ ያልቻለችውን ሲና የተንቀጠቀጠችለትን ታቦር የራደችለትን ዮርዳኖስ የሸሸችለትን ግሩምና ታላቅ ኃይል በማህፀኗ የተሸከመች ደብር ነባቢት ቃል የማይገልጣት ንፁህ ለቅድሱ አምላክ ፍፁምና ቅዱስ ማደሪያ የሆነች ከሰው ተገኝታ ከመላዕክት የበለጠች ።
የፍቅር እናት ...የጌታ እናት... የቤተ ክርስትያን እናት ..የአለም እናት ...የእኛ እናት ....የፍጥረት ሁሉ ጌጥ ወላዲተ አምላክ ። የእናትነት ምልጃዋ አይለየን ። ቅድስት ድንግል ሆይ ለምኝልን🙏

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

29 Oct, 17:43


ጥያቄና መልሱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን የእስካሁኑ ውጤት ይሄን ይመስላል ።

ብዙዎች እንዲሳተፉ በማሰብ እስከ ነገ ምሽት የትላንቱን ጥያቄ እስከ ነገ ማታ 12 ሰአት ይቀጥላል ።

መልካም ምሽት

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

28 Oct, 18:31


እውነት ሀሰት

1 ስለዚህ፥ከዮሐንስ፡ጥምቀት፡ዠምሮ፡ከእኛ፡ዘንድ፡አስካረገበት፡ቀን፡ድረስ፥ጌታ፡ኢየሱስ፡ በእኛ መካከል፡በገባበትና፡በወጣበት፡ዘመን፡ዅሉ፥ከእኛ ጋራ፡ ዐብረው፡ከነበሩት፡ሰዎች፥ከነዚህ፡አንዱ፡ከእኛ፡ጋራ፡የትንሣኤው፡ምስክር፡ይኾን፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ል።

2 ደግሞ፡አርባ፡ቀን፡እየታያቸው፡ስለእግዚአብሔርም፡መንግሥት፡ ነገር እየነገራቸው፥በብዙ ማስረጃ፡ ከሕማማቱ፡በዃላ፡ሕያው፡ኾኖ፡ለእነርሱ፡ራሱን፡አሳያቸው፡፡

3 በትንቢት መጽሐፍ፡-መኖሪያው ምድረ፡በዳ፡ትኹን፥የሚኖርባትም፡አይኑር፤ደግሞም፡-ሹመቱን፡
ሌላ፡ይውሰዳት፡ተብሎ፡ተጽፏልና።

4 ይህም፡ሰው፡በልፋት ዋጋ፡መሬት፡ገዛ፥በግንባሩም፡ተደፍቶ፡ከመካከሉ፡ተሰነጠቀ፥አንዠቱም፡ዅሉ፡ተዘረገፈ።

5 በዚህም፡ወራት፡ ጳውሎስ፡መቶ፡ኻያ፡በሚያኽል፡ በሰዎች፡ ማኅበር፡ዐብረው፡በነበሩ በወንድሞቹ፡መካከል፡ተነሥቶ፡ኣለ፡-ይሁዳ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡አስቀድሞ፡በዳዊት፡አፍ፡የተናገረው፡የመጽሐፍ፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟፡ነበር፤

6 እነዚህ፡ዅሉ፡ ከሴቶችና፡ከኢየሱስ፡እናት፡ ከማርያም፡ከወንድሞቹም፡ጋራ፡ባንድ፡ልብ፡ኾነው፡ለጸሎት፡ይተጉ፡ነበር።

7 በዚያን፡ጊዜ፡ደብረ፡ታቦር፡ከሚባለው ተራራ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ ተመለሰ፥ርሱም፡ከኢየሩሳሌም፡የሰንበት፡መንገድ፡ያኽል፡የራቀ፡ነው።

8 ርሱም፡ሲኼድ፡ወደ፡ሰማይ፡ትኵር፡ብለው ሲመለከቱ፡ሳሉ፥እንሆ፥ነጭ፡ልብስ፡የለበሱ፡ኹለት፡ሰዎች፡በአጠገባቸው ቆሙ"፤ደግሞም፦ የገሊላ፡ሰዎች፡ሆይ፥ወደ፡ሰማይ፡እየተመለከታችኹ፡ስለ፡ምን፡ቆማችዃል፡ይህ፡ ከእናንተ፡ወደ፡ሰማይ፡የወጣው፡ኢየሱስ፡ወደ፡ሰማይ፡ሲኼድ፡እንዳያችኹት፥
እንዲሁ፡ይመጣል፡አሏቸው፡፡

9 ነገር፡ግን፥መንፈስ፡ቅዱስ፡በእናንተ፡ላይ፡በወረደ፡ጊዜ፡ኅይልን፡ትቀበላላችኹ፥በቤተልሔምም፡
ምስከሮቼ፡ትኾናላችኹ፡አለ፡፡

10 እነርሱም፡በተሰበሰቡ፡ጊዜ፦ጌታ፡ሆይ፥በዚህ፡ወራት፡ለእስራኤል፡መንግሥትን፡ትመልሳለኸን ብለው
ጠየቁት።

11 ይህንም፡ከተናገረ፡በዃላ፡እነርሱ፡እያዩት፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፤ደመናም፡ከዐይናቸው፡ሰውራ፡ተቀበለችው።

12 ዮሐንስ፡በውሃ፡አጥምቆ፡ነበርና፥እናንተ፡ግን፡ከጥቂት፡ቀን፡በዃላ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ትጠመቃላችኹ፡አለ፡፡

ዳሽ ሙላ

13 .........................፡ሆይ፥ኢየሱስ፡የመረጣቸውን፡ሐዋርያትን፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ካዘዛቸው በዃላ፡እስከዐረገበት፡ ቀን፡ድረስ፥ያደርገውና፡ያስተምረው፡ዘንድ፡ስለዠመረው፡ዅሉ፡መዠመሪያውን፡ነገር፡ጻፍኹ።

14 በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖሩ፡ዅሉ፡ታወቀ፤ስለዚህም፡ያ፡መሬት፡በቋንቋቸው፡.............. ፡ተብሎ፡ ተጠራ፥ርሱም፡የደም፡መሬት፡ማለት፡ነው፡፡

15 ኢዮስጦስም የሚሉትን፡..............፡የተባለውን፡ዮሴፍንና፡ማትያስን፡ ኹለቱን፡አቆሙ።

16.....................፡-የዅሉን፡ልብ፡የምታውቅ፡አንተ፡ጌታ፡ሆይ፥ይሁዳ፡ወደገዛ፡ራሱ፡ስፍራ፡ይኼድ፡ዘንድ፡ በተዋት፡ በዚች አገልግሎትና፡ሐዋርያነት ስፍራን፡እንዲቀበል፡የመረጥኸውን፡ከነዚህ፡ከኹለቱ፡
አንዱን፡ሹመው፡አሉ፡፡

17 ዕጣም፡ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም፡.....................፡ወደቀና፡ ከዐሥራ፡አንዱ፡ሐዋርያት፡ጋራ፡ተቈጠረ።

ደረቅ ጥያቄ

1 የሐዋርያት ስራ ስንት ምዕራፍ አለው

2 የሐዋርያት ስራ ምዕራፍ በአጭሩ በአራት አረፍተ ነገር ስለምን ያወራል ።

ጥያቄው የወጣው ከሐዋርያት ስራ ምዕራፍ አንድ ሲሆን መልሳችሁን ከታች ባለው username መላክ ትችላላችሁ

ውጤታችሁ ቻናል ላይ ይለቀቃል

አስተውላችሁ አንብቡ መልካም ምሽት

@weladiteamlakdengl

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

21 Oct, 10:05


ማርያም ማለት ምን ማለት ነው?

ማርያም ማለት፦
እግዝእት:- እመቤት ማለት ነው የዓለሙን ንጉስ በመውለዷ ከፈጣሪ በታች የፍጥረት ንግስት ሆናለችና፤

ጸጋ ዘተውኅበት ለኩሉ ዓለም፦ ለዓለሙ ሁሉ የተሰጠች ጸጋ ማለት ነው። ለአበው በተስፋ የሰጣቸው ሲሆን ለእኛ ደግሞ ከመስቀሉ ሥር እናት ትሁናችሁ ብሎ ሰጥቶናልና። (ዮሐ ፲፱፤፳፮) ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ንግሲቲቱ በቀኝህ ትቆማለች የሚለውን የዳዊት መዝሙር ሲተረጉም In becoming the mother of creator she become the Mistress of all creation (የፈጣሪ እናት በሆነች ጊዜ የፍጥረታት ሁሉ ንግስት እመቤት ሆናለችና በማለት ተርጉሞታል። (መዝ 44፤9)

ተስፋ ማለት ነው፦ ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ካለው ጀምሮ መድኃኒቴን የምትወልጅልኝ ልጄ እያለ ተስፋ አድርጓት በልቦናው መዝገብነት ይዟት የኖረ ስንቁ ናት። አበውም ድንግል ማርያምን መቼ ፀሐይ ክርስቶስን ወልዳልን ከቁረ መርገም ድነን አይተነው እያሉ ተስፋ አድርገዋት ነበር። ተስፋቸው ክርስቶስም ከእርስዋ ተወልዶ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ገብተዋል። ለዚህ ምስክር የሚሆነን አረጋዊ ስምዖን "ጌታ ሆይ አገልጋይህን ዛሬ ታሰናብተዋለህ፥ አቤቱ በሰላም እንዳዘዝክ አይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና በህዝብ ፊት ሁሉ ያዘጋጀኸውን ለአህዛብ ብርሃንን ትገልጽ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ክብርን" በማለት ተስፋውን አይቶ አርፏል። (ሉቃ 2፥29)

የባህር ከርቤ (Myrrh of the sea) ማለት ነው። ይህ ከርቤ እጅግ ውድ ዋጋ ያለው ከዘይት ጋር ተጨምሮ  በጠበብተ ኦሪት ተቀምሞ ለንዋያተ ቅድሳት ማክበሪያ የታዘዘ ሽቱ ነው። ሙሴ ደብተራ ኦሪቱን በኦሪት መቅደሱ ያሉትን ሁሉ በዚህ ሽቱ እንዲቀባ ታዟል። ሽቱ ያረፈባቸውን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮታል። ባህር የተባለ ይህ ዓለም ሲሆን እመቤታችንም ከእርስዋ ስጋን ነስቶ ክርስቶስ ተብሎ ስሙ እንደ ዘይት ተዋህዶን ክርስቲያን ተብለን እንድንጣፍጥ የድኅነት መሳሪያ የመዓዛ መንፈሳዊ ምንጭ ናትና የባህር ሽቱ ትባላለች።

ሽቱ ያረፈበትን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ በልጇ ስም አምነው ተጠምቀው በእምነት የሚቀርብ ሁሉ ይጣፍጣልና ይላሉ አበው!

የባህር ኮከብ (Star of the seas) ማለት ነው። ባህር የተባለ ይህ ዓለም ነው፥ በባህር የሚበላም የማይበላም ደግሞ ክፉም ፍጥረት እንዳለ በዚህ ዓለምም አማኒም ከሓዲም መናፍቅም ጻድቅም ኃጥእም ይኖራልና፥ ዳግመኛም ባህር ከሁከት አይርቅም ይች ዓለምም ከሁከት አትርቅምና፥ በባህር ላይ ሲጓዙ በመርከብ ላይ ሆነው የንጋት ኮከብን አብነት አድርገው ከተጓዙ ካሰቡት ይደረሳል። ሰብአ ሰገልን ኮከብ እየመራ ቤተልሔም እንዳደረሳቸው ማለት ነው። እንዲሁም ሁሉ እመቤታችን በዚህ ዓለም የክህደት የኃጢአት  ምገድ እንዳያጠፋን የተረፍንባት መርከባችን ናት።

ብርህት (Illuminated) ማለት ነው። ብርሃኗ ከፀሐይ ይበልጣል፤ መለወጥ የሌለባት የድህነት በር ናት ውበቷም በፍፁም ክብርና ሞገስ የተሸለመ ነው፤ እውነት በእውነት የመና መሶብ ነች። ጽድልት መባሏ ነውርና ነቀፋ የሌለበት የእግዚአብሔር እናት በመሆኗ ነው።

አሐቲ ፍቅርት፦ ብቻውን የምትወደድ (Beloved One) ማለት ነው። ንጉስ ውበትሽን ወዷልና ተብሎ የተዘመረላት እግዚአብሔር መዓዛ ድንግልናዋን ወዶ ከእርሷ ሰው እስኪሆን ድረስ፥ ፍጥረትን ሁሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብቅሎ የሚመግብ ጌታ ጡቶቿን ጠብቶ እስከማደግ ድረስ ደርሶ ብቻዋን በእግዚአብሔር የተወደደች ናትና።

የባህር ምንጭ (Drop of the sea) ማለት ነው። እመቤታችን በዚህ ዓለም በሦስት ዋና ዋና የድኅነት ምንጭ ሆናለችና። የጥምቀት፥ የቁርባን፥ የቅዳሴ ናቸው። ይህም ማለት ከጎኑ የፈሰሰው ውሃ፥ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ከእርሷ ባህሪ የተገኘ ነውና ጌታ የተጠመቀውም ከእርሷ በነሳው ስጋ ነው የምንበላው ቅዱስ ስጋው የምንጠጣው ክቡር ደሙ ከእርሷ የነሳው ነውና የቁርባን ምንጭ ትባላለች።
(አሐቲ ድንግል በአባ ገብረኪዳን ግርማ ከገፅ 257-260 ላይ የተቀነጨበ)

              

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

17 Oct, 18:44


እግዚአብሔር ተስፋ አድርግ

ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር #በዝምታ_ይሠራል ። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሠራ አድርገው ያስባሉ ። እነርሱ እግዚአብሔር አይሠራም ብለው በሚያስብበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ #በጥልቅ_እየሠራ ነው ። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ የእግዚአብሔርን ሥራና የሥራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይናቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል ። " እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ። " [መዝ 26*14 ] ።
እግዚአብሔርን እንዴት እንጠብቅ?

እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ ፤ በእምነት ፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል ። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል ። " እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ።" [ ሮሜ 8*28] ። " እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም " [ኢሳ 40*31] ። ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው ። " ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል " የሚል ቃል ተጽፋል [ መዝ 102*5] ። ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር #እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል ።
ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት ። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው ። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም ። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? /ሐዋ 1*7/ ። አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው ። ችግርህን እግዚአብሔር በጊዜው እንደሚያቃልለው መጠባበቅ የአንተ ሥራ አይደለም ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

15 Oct, 17:46


የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል ።

ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል ። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ ።

"ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው ።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር ! እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ ! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል ።

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

10 Oct, 19:44


ድንግል ማርያም ሆይ

ልጅሽን ቅዱሳን መላእክት ሊቀርቡት ይፈሩታል፤ አንቺ ግን ጸንሰሽ ወለድሽው።

ልጅሽን  ፍጥረታት ሁሉ "ፈጣሪያችን" ይሉታል፤ አንቺ ግን ልጄ ትይዋለሽ።

መልክና ባህሪሽ ልጅሽ ፈጣሪን  ይመስላል።

የተባረኩት ሴቶች ቅዱሳንን ይወልዳሉ፤ አንቺ ግን ፈጣሪሽን ወለድሽ።

ምስጢሩ ከሰው አእምሮ በላይ ስለሆነ እጹብ ድንቅ ተብሎ ማለፍ ነው እንጂ።

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሀገራችን ሰላምን ለህዝባችን ፍቅርን ለታመሙት ፈውስን ለተራቡት ምግብን ታድልልን አሜን!

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

09 Oct, 08:19


ታላቅ በሆነው እምነትሽ

ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ ለዓለም ተሰማ
#-አዝ።።።።።።።።
ስመጣ ባልጋ ነበረ
ተስፋዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ሥራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት
#-አዝ።።።።።።።።።
ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር ታጭተሽ
የእምነቴ አሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለሁ በህይወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል
#-አዝ።።።።።።።።።።።።
እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
ባንቺ አፍሮ የሄደው ማነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

08 Oct, 20:19


ጌታ ሆይ፥ ከአንተ የሆነውን ሰማያዊ ደስታ አትንፈገኝ።
ጌታ ሆይ፥ ከዘላለም ፍርድ አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ በአሳብም ሆነ በአእምሮ፥ በቃልም ሆነ በሥራ ብበድል ይቅር በለኝ።
ጌታ ሆይ፥ ከአላዋቂነት፥ ከዝንጉነት፥ ከፈሪነት፥ ከልብ ጥንካሬ አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ከማናቸውም ፈተና አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ ክፉ ምኞት ያጨለመውን ልቤን አብራልኝ።
ጌታ ሆይ፥ ሰው የሆንኩት እኔ በድያለሁ፥ ነገር ግን አንተ ባለጸጋው አምላክ፥ ምሕረት አድርግልኝ፤ የነፍሴን በሽታ ታውቃለህና።
ጌታ ሆይ፥ ቅዱሱ ስምህን አክብር ዘንድ ጸጋህ እንዲያግዘኝ ላክልኝ።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ እኔን ባሪያህን በሕይወት መጽሐፍ ጻፈኝ፤ መልካም ፍጻሜ ስጠኝ።
ጌታዬ አምላኬ፥ በፊትህ ምንም መልካም ሥራ ባይኖረኝም፥ ከጸጋህ የተነሣ መልካም ጅማሬ አድለኝ።
ጌታ ሆይ፥ የጸጋህን ጠል በልቤ ላይ እርጨው፤ የሰማይና የምድር ጌታ፥ እኔን ኃጢአተኛውን አገልጋይህን በመንግሥትህ አስበኝ። አሜን።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

08 Oct, 15:10


አዝላው ወረደች ወደግብፅ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

08 Oct, 10:14


እግዚአብሔር የሌለበትን ሕይወት መኖር እንዴት ኪሳራ እንደሆነ? እውነት ከእሱ እንድንርቅ ከሚያደርገን ደስታ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን ኀዘን ይሻለናል

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

01 Oct, 09:34


የሰው ልጅ የተፈጠረበት አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ምሳሌነታቸው እንደምንድን ነው ቢሉ፦

#እሳት️ ፡- በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ይመሰላል። ለምን ቢሉ እሳት ፈቃድ ፈጻሚ ነው አንድ ቦታ ላይ ብንጭረው ሃገርን ሊያወድም ይችላል እግዚአብሔርም ሁሉን ማድረግ የሚችል ምንም ማይሳነው አምላክ መሆኑን።

#ውሃ ፡- በእግዚአብሔር ርህራሄ ይመሰላል። ውሃ እድፍን እንደሚያጠራ በኃጥያታችን ተጸጽተን ንስሐ ብንገባ ይቅር ሊለን፣ ከኃጢአታችን ሊያነጻን የታመነ መሆኑን።

#ንፋስ፡- በእግዚአብሔር ፈራጅነት ይመሰላል። ንፋስ ገለባውን ከስንዴ እንደሚለይ እግዚአብሔርም በዳግም ምጽዓት ጊዜ ኃጥኡን ከጻድቁ በእውነተኛው ፍርዱ የሚለይ መሆኑን።

#መሬት (#አፈር):- በእግዚአብሔር ታጋሽነት ይመሰላል። መሬት ጥቁር፣ ቀይ፣ ወፍራም፣ ቀጭን ፣ ኃጥእ፣ ጻድቅ ሳትል ሁሉንም ችላ ትኖራለች ፈጣሪም እንዲሁ በማንነታችን ሳይለየን የሚታገሰን መሆኑን።

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

30 Sep, 18:52


ጸሎት እየጸለዩ በመሃል ጸሎት አቋርጦ ማውራት ትልቅ ስህተት ነው!


በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ወዳጆቻችን ከስህተት እንዲታረሙ ያድርጉ!

ተወዳጆች ሆይ ብዙዎቻችን ማለት በሚቻል ደረጃ ጸሎት እየጸለይን በጸሎቱ መሃል እያቋረጥን የማውራት ልምድ አለን፡፡ በእርግጥ በጸሎታችን መሃል ጸሎቱን አቋርጠን የምናወራበት ምክንያት ለእኛ አሳማኝ እና ልክ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር በመንፈስ መነጋገር መሆኑን ላወቀ ክርስትያን ጸሎቱን እየጸለየ በመሃል ጸሎቱን አቋርጦ ለጉዳዩ ቢያወራ፤ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ ንግግሩን አቋርጦ ከሰው ጋር እንደማውራት ነው የሚሆንበት፡፡

እጅጉን የሚገርመው ደግሞ የጸሎት ሰዎች የሆኑት አባቶቻችንን የዚህ አመል ተጠቂ መሆናቸው ነው፡፡ ምናልባት እኛም ከእነሱ ወርሰን ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ አባቶች ጸሎት እየጸለዩ ጸሎቱን አቋርጠው ከሰው ጋር መነጋገር ችግር ያለው አይመስላቸውም፡፡

ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ‹‹ሥርዓተ ቤተ ክርስትያን›› በሚለው ድንቅ መጽሐፋቸው ላይ ስለ ጸሎት አፈጻጸም በጻፉት ንዑስ ርዕስ ሥር ‹‹የሚጸልይ ሰው በጸሎት ላይ ሳለ ጸሎቱን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መነጋገር የለበትም፡፡ ጸሎቱን እስከሚጨርስ ድረስ ቃል መለዋወጥና ማንንም ወደ እርሱ መጥቀስ አይገባውም፡፡ ጸሎቱን የሚያቋርጥ ችግር ቢገጥመው ግን በአቡነ ዘበሰማያት/በአባታችን ሆይ/ ጸሎቱን አሥሮ ንግግሩን ሲፈጽም ከአቋርጠበት ጀምሮ ጸሎቱን ሊጸልይ ይገባል›› ብላዋል፡፡

ፍትሐ ነገሥት ስለ ጸሎት በሚያትተው አንቀጽ ላይ አንቀጽ 14 በቁ 561 በ ድስቅ 10 ‹‹የከበረ እንግዳ ባላገርም በመጣ ጊዜ ኤጲስቆጶስ ሆይ ጸሎትህን አታቋርጥ ወንድሞች ከእነርሱ ዘንድ ይቀበሉት እንጂ ዲያቆኑም ቦታውን ያዘጋጅለት እንጂ አገልግሎቱ እግዚአብሔርን ደስ የምታሰኝ ትሆን ዘንድ›› ይላል፡፡

ወዳጆቼ እዚህ ጋር ልብ ልትሉት የሚገባው እንኳን እኛ አገልግሎት የሚበዛበት፣ጸሎት ሥራው የሆነ ኤጲስ ቆጶስ እንግዳ እንኳን ቢመጣበት ጸሎቱን አቋርጦ መቀበል እንደሌለበት ያሳየናል፡፡ ይህም በጸሎቱ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር እንዲደሰትበት ነው፡፡ ታድያ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነው ኤጲስ ቆጶስ ጸሎቱን አቋርጦ ሰው እንዳያናግር ከተከለከለ እኛ ጸሎቱ ሥራችን ሳይሆን የግዳችን፣የችግራችን ጊዜ የሆነብንማ ጸሎታችንን ትተን ሰውን ማናገር አይገባንም፡፡ ግን እየሆነ ያለው ይሄ አይደለም፡፡ ከላይ እስከ ታች ያለነው ጸሎትን እንደ ሁለተኛ ጉዳይ እና ሥራ ስለምንቆጥረው ጸሎታችንን ትተን ከሰው እንነጋገራለን ወሬያችንን እንሰልቃለን፡፡

ወዳጆቼ ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት እየተነጋገርን ጸሎታችንን አቋርጠን ከሰው ብናወራ ይህ ጥሩ ያልሆነ ልምዳችን የራሱ የሆነ ጎጂ ጎን አለው፡፡ አንደኛ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የጸሎት ግንኙነት በራሳችን እናቋርጣለን፡፡ ሁለተኛ የጸሎት ተመስጦአችንን እናጣለን፡፡ ይህም ትኩረት እና ዓላማ የሌለው ጸሎት ይሆንብናል፡፡ ሦስተኛ ጸሎቱ ጸሎት ሳይሆን ወሬ ይሆናል፡፡ አራተኛ እኛም የጸሎትን ክብር እናጣለን የሚያናግሩንም ሰዎች ጸሎታችን ጸሎት ላይመስላቸው ይችላል፡፡ አምስተኛ ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር አይደርስም፡፡ ስድስተኛ በተመስጦ ሳይሆን በወሬ የታጀበ ጸሎት በአጋንንት ላይ ጉልበት አይኖረውም፡፡ ሰባተኛ በወሬ የሚባክን ጸሎት እንደ ባከነ ይቀራል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ታድያ በጸሎታችን መሃል እጅግ አንገብጋቢና አስፈላጊ ነገር ቢገጥመን ምን እናድርግ? ለሚለው ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል እንዳስቀመጡልን፣አባቶቻችንም እንደነገሩንና እንደሚጠቀሙት ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት/በአባታችን ሆይ አስረን ሰውን ማናገር፡፡ ጉዳያችንን ስንጨርስ ወደ ጸሎታችን መመለስ፡፡ ወዳጆቼ አንዳንዴ ጸሎታችንን አቋርጠን ሰው አውርተን ወደ ጸሎታችን ስንመለስ ጸሎታችንን የት ጋር እንዳቆምን አናውቅም፡፡

አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በጸሎት ላይ እያሉ እጅጉን የሚያስፈራና እንደ ወርቅ የሚያበራ ዘንዶ አፉን ከፍቶ፣ምላሱን እያውለበለበ ሊበላቸው ወደ እሳቸው በተጠጋቸው ጊዜ ለሰከንድ ሽርፍራፊ ጸሎታቸውን እንኳን ሊያቋርጡ ዞር ብለው አላዩትም፡፡ ይልቁንም ዘንዶው ወደ እሳቸው ተጠግቶ ሊውጣቸው ሲል በመስቀላቸው ቢያማትቡበት ለሁለት ተሰንጥቆ ሞቷል፡፡ የሚገርመው አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሊፈትናቸው የመጣው ዘንዶ ሳይሆን በሰንዶ ተመስሎ የመጣው ሰይጣን ነው፡፡ እንዲህ አይነት ጸሎት በአጋንንት ላይ ትልቅ የበላይነት ይኖረዋል፣ተአምርም ይሠራል፡፡

ለምሳሌ ውዳሴ ማርያም እያደረስን የእመቤታችንን ውዳሴ አቋርጠን ከሰው ጋር ብናወራ እመቤታችንን አትታዘበንም? ምስጋናዋን ከአፋችን ነጥቀን ከሰው ጋር ብናወራ ጸሎቱ ጸሎት ይሆናል? ስለዚህ በጸሎት መሃል ከሰው ጋር የማውራት ልምድ ያለን ልንተው፤የግድ የሚያስወራን ነገር ከሆነ በአባታችን ሆይ ጸሎቱን አሥረን ጉዳያችንን ከጨረስን በኃላ ወደ ጸሎታችን ልንመለስ ይገባል፡፡

አጋንንትም ጸሎታችንን ለማቋረጥ፣ተመስጦአችንን ለማጥፋት በሰው እያደረ በሆነው ባልሆነው እንዳይፈትነን፣ለጸሎታችንም እንቅፋት እንዳይሆንብን በጸሎት መሃል የማውራት ልምዳችንን ልንተው ይገባል፡፡ ጸሎት የራሱ የሆነ ሥርዓት ስላለው በሥርዓት እንጸልይ፡፡ በተረፈ በጸሎታችሁ የራሳችሁን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገራችንን፣የቅድስት ቤተ ክርስትያናችንንም ወቅታዊ ፈተና ለጌታችንና ለድንግል ማርያም እናሳስብ፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

29 Sep, 18:22


የእመቤታችን የስሟ ክብር!

በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም

በአንድ ወቅት ወደ ወሎ አካባቢ ሁለት የቆሎ ተማሪዎች ሲከራከሩ አንድ አባት የይሰማሉ፡፡ መከራከሪያ ነጥባቸው አንዱ የቆሎ ተማሪ ማርያምን ብሎ ሲምል ይሰማዋል፡፡ ይህን የሰማው ተሜም ‹‹ማርያምን ብለህ፣ በሙሉ አፍህ ጠርተህ መማል ቀርቶ ስሟን መጥራት አይገባህም›› ይለዋል፡፡ ምላሽ ሰጪ ተሜ ደግሞ ‹‹እናቴ ናት ስሟን ብጠራ፣ በስሟ ብምል ምን ገዶህ››ይለዋል፡፡ ተከራካሪ ተሜም ‹‹ትሰማለህ ውዳሴዋን ሳታደርስ፣ ፍቅሯን በልቦናህ ሳታሳድር ማርያም ስትል አታፍርም? አባቶች እመቤታችን ድንግል ማርያም ብለው ቢጠሯት ውዳሴዋን አድረሰውላት፣ በፍቅሯ ብዙ ሆነውላት ነው የከበረ ስሟን የሚጠሩት›› ይለዋል፡፡

ለመሸነፍ የዳዳ ተሜ የራሱን ባዶነት የእመቤታችንን የስሟን አክብሮት በመገንዘብ ‹‹ታዲያ በስሟ ካልጠራኋት ምን ብዬ ልጥራት›› ይለዋል፡፡ አዛኜ ብለህ ጥራት ይለዋ፡፡ የእነዚህን የፍቅር ክርክር የሰሙት አባት በመሃላቸው በመግባት ‹‹ትሰማለህ ተሜ አንተም ስሟን መጥራት ፈርተህ አዛኜ ብትላት የከበረ ስሟን አክብረህላት ነው፡፡ አንተም እመቤቴ ማርያም ብትላት የከበረ ስሟን ወደህላት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለታችሁም ልክ ናችሁ›› ብለው ሃሳባቸውን በማስታረቅ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡

ለብቻቸው እየሄዱ ‹‹አይ እመቤቴ እንኳን ለምስጋናሽ ለከበረው ስም አጠራርሽ የማልበቃ ኃጢአተኛ ነኝ›› ብለው የእመቤታችንን የሥም አጠራር ተረድተው በተማሪው ትህትና ተገርመዋል፡፡ የእመቤታችን ስም የክርስቶስን ፍርድ የሚያራራ ነው፡፡ ኃጥአን በምድር በሥጋ በሠሩት በደል፣ ጌታችን በሰማይ በነፍስ ብድራቸውን ሲከፍል፣ እነዛ በእሳት ዙፋን ፊት የቆሙ ምስኪን ነፍሳት ጌታችንን ‹‹እባክህን ስለ እናትህ ብለህ ማረን ይቅር በለን፡፡ ስለ ስሟ ተለመነን›› ይሉታል፡፡ ጌታችንም ስለ ስሟ ፍርዱን ያቀላል፡፡ በእሷ ጸጋ ያጸድቃል፡፡

ጌታችን እንኳን ለሙሉ ክብሯ፣ ለስም አጠራሯ ልዩ ቦታ አለው፡፡ የእመቤታችን ስሟ መድኃኒት ነው፡፡ አባቶቻችን እናቶቻችን ለፍቅሯ ለስም አጠራሯ ከመሳሳታቸው የተነሳ አዛኜ፣ ወለላይቱ፣ እማዋይሽ፣ ወይኒቱ ወዘተ… በማለት
ይጠሯታል፡፡

እመቤታችን እንኳን ያደረባት የመለኮት ጸጋ ቀርቶ፣ስሟ የአጋንንት መዶሻ፣ የሰይጣን ድል መንሻ፣ የዲያብሎስ ማሸሻ፣ ነው፡፡ ስሟ ሲጠራ አጋንንት ረአድ፣ በድንጋጤ መርበድበድ ስለሚይዛቸው ስም አጠራሯን ይፈሩታል፡፡

እናውቃለን ዛሬ በዘመናችን ድንቅ ሠሪ፣ አጋንንት አባራሪ የሆነችው ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ሲጠራ አጋንንት ይቃጠላሉ፣ መሄጃ መሮጫ ያጣሉ፣ በድንጋጤ ባህር ገደል ይገባሉ፡፡ እመቤታችን በወለደችው በክርስቶስ ስም መከራ እና በአንገቷ ካራ የተቀበለችው የቅድስት አርሴማ ስም ተዓምር ከሠራ የቅድስት አርሴማን አምላክ የወለደችው የእመቤታችን ስሟ ምን ይሠራ ይሆን?

እመቤታችን በሥጋ አርፋ ቅዱሳን ሐዋርያት ለቀብር ወደ ቤቴሴማኔኒ ይዘዋት በሄዱበት ሰዓት በትዕቢት የደነዘዘ፣ የአልጋዋን ሸንኮር ለመጣል እጁን የመዘዘ ታውፋንያ በቅዱስ ገብርኤል የእሳት ሰይፍ እጁ ተጎምዶ ነበር፡፡ የእመቤታችንን የስሟ ክብር ያወቀው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የታውፋንያን እጅ በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ በተአምራት ሊገጥምለት አላሰበም፡፡ ይልቁኑም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በድንግል ማርያም ስም በማለት ወደ ነበረበት ቦታ መልሶለታል፡፡ ቅዱስ ጴጥረስ በጌታችን ስም ሙት እያስነሳ፣ ድውያንን እየፈወሰ ድንቆችን የሚያደርግ ሊቀ ሐዋርያት ነው፡፡ ነገር ግን ከጌታው ስም በተጨማሪ የእናቱ ስም ተአምር እንደሚያደርግ ስላወቀ በተግባር አሳይቶናል፡፡

የበላዔ ሰብዕ የመዳን ምክንያት፣ የእመቤታችን የስሟ መጠራት ነው፡፡ በላዔ ሰብዕ በስሟ ተለመነ ጥሪኘ ውሃ ሠጠ፣ ከሰባ ስምንት ነፍስ ዕዳ አመለጠ፡፡ ጌታችን ለቅዱሳን ቃል ኪዳን ሲገባ የመጀመሪያው ‹‹ስማችሁን የጠራ፣ በስማችሁ የተማጸነ›› በማለት ነው፡፡ ለካ ስም መጥራት ያስገባል መንግስተ ሰማያት፡፡

በአገራችንም በውጭም ያሉ ቅዱሳኖች የተትረፈረፈ የጸና ቃል ኪዳን ከፈጣሪያቸው ተቀብለዋል፡፡ ከተቀበሉት ውስጥ አንዱ ‹‹ስማችሁን የጠራ፣ በስማችሁ የተማጸነ፣ ስሙን በስመማችሁ የሰየመ›› የሚል ነው፡፡ ጌታችንም እመቤታችንን ‹‹ስሙን /ስሟን/ በስምሽ የሰየሙ በመላእክት ፊት የከበሩ፣ በመንግስቴ ለዘላለም የሚኖሩ ናቸው›› ብሎ በስሟ ብቻ ቃል-ኪዳን ገቶላታል፡፡ ወገኔ አማላጅነቷ አይድነቀን ስሟ ብቻ መጽደቂያችን ነው፡፡ በእርግጥ ለመጽደቅ ሥራ ያስፈልጋታል፡፡ ግን ብዙዎች በስሟ ገነት ገብተዋል፡፡

ማርያም የሚለው ስሟ ብዙ ትርጓሜ ቢኖረውም እንደ አባቶቻችን አስተምህሮ ማርያም የሚለውን ስሟን በሁለት ከፍለው ትረጉሙን ይነግሩናል፡፡ ማር እና ያም!፡፡

ማር ፡- በምድር ካሉ ጣፋጭ ምግቦች አንዱ ነው፡፡ ማር በጣፋጭነቱ ብቻ ሳይሆን በመድሃኒትነቱም ይታወቃል፡፡

ያም፡- በሰማይ ያሉ ቅዱሳን የሚመገቡት እጅግ ጣፋጭ ምግብ ነው፡፡

ስለዚህ የእመቤታችን ስም በምድርም በሰማይም ላሉት ሁሉ እንደ ምግብ ጣፋጭ እና መድሃኒት ነው፡፡ ማርያም የሚለውን ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ከእመቤታችን በፊት እና በኋላ የተጠሩበት ሴቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-

1/ ማርያም፡- የሙሴ እህት - ዘፀ. 15-20

2/ ማርያም፡- የዮቶር ልጅ የእዝራ የልጅ ልጅ 1 ዜና.መ 4÷17

3/ ማርያም፡- የማርታና የአልዓዛር እህት - ዮሐ. 11÷1

4/ ማርያም መግደላዊት፡-ሰበት አጋንንት የወጣላት ሉቃ. 8÷2,፣ ማር. 15÷40-41

5/ ማርያም፡- የታናሹ የያዕቆብና የዮሳም እናት ማር.16÷1፣ ሉቃ. 24÷10

6/ ማርያም፡- የቀለዮጳ ሚስት- ዮሐ. 19÷25

7/ማርያም፡- የማርቆስ እናት - ሐዋ.ሥራ 12÷12

እነዚህ ከላይ ያሉት በማርያም የተጠሩ ቢሆንም የእመቤታችን የድንግል ማርያም ስም ግን ግብሯን ይጠቅሳል፡፡ ያ ማለት ቅድስናዋን ንጽህናዋን፣ መድኃኒትነቷን፣ በምድርም በሰማይም የከበረች መሆንዋን ስለሚገልጽ ልዩ ያደርጋታል፡፡

ውድ የእመቤታችን ልጆች እኛም ስሟን ልናከብር እንጂ በሆነውም ባልሆነውም ስሟን መጥራት አልያም በስሟ መማልና መገዘት የለብንም፡፡ ማርያም የሚለው ስም ለእኛ ለልጆቿ እንደ ማርዳ በአንገታችን የሚጠለቅ ጌጣችን፣ እንደ ቅቤ ከሰውነታችን የሚዋኃድ፣ ኋላም የሚያድን ከፍርድ ነው፡፡ ስለዚህ የከበረ ስሟን በአግባቡ ጠርተን አክብረን ለመክበር ያብቃን፡፡

‹‹በስምሽ ያመነውን ማን ያስፈራዋል፡፡ በልጅሽስ ያመነውን ማን የስፈራዋል፡፡ የአንበሳም ጩኸት እንደ ውሻ ጩኸት ይመስለዋል፡፡ የነብሮችም ኃይል እንደ ድመት ደካማ ነው›› አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ይቺን ቅድስት እናት እናክብር፣ እንውደዳት በፍቅር!
‹‹ስለ እመቤታችን ክብር፣ያላስተዋልነው ነገር›› ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

27 Sep, 06:23


+ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር +

☞ ተወዳጆች ሆይ ጊዜ ሳለልን ድኅነታችንን እንፈጽም፡፡ ጊዜ ሳለልን ለመብራታችን ዘይት የተባለ ምጽዋትን እንያዝ፡፡ ጊዜ ሳለልን መክሊታችንን ለማብዛት እንፍጨርጨር፡፡ በዚህ ዓለም ሳለን ይህን ለማከናወን ልል ዘሊል እና ሐኬተኞች ከኾንን በወዲያኛው ዓለም እልፍ ወትእልፊት ጊዜ ወዮ ብለን ብናለቅስ ብንጮህም እንኳን የሚረዳን የለምና፡፡ ያ ባለ አንድ መክሊት ሠራተኛ አንዲቷን መክሊት ሳይቀንስ ለጌታው ቢያስረክብም ከኩነኔ አላመለጠምና፡፡ አምስቱ ሰነፎች ደናግልም ጌታችንን ለምነውት ነበር፤ በሩን አንኳኩተው ነበር፡፡ ነገር ግን ልመናቸውም ማንኳኳታቸውም ከንቱ ነበር፥ ጥቅም አልባ ነበር፡፡

☞ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ዐውቀን በሀብታችንም፣ በትጋታችንም፣ ለወንድማችን በምናደርገው ማናቸውም ጠቃሚ ነገርም የዓቅማችንን ያህል እንጣር፡፡ መክሊት የተባለው የእያንዳንዱ ሰው በእጁ ያለውና ማድረግ የሚችለው ነገር ማለት ነውና፡፡ ለአንዱ ወንድሙን መጠበቅ ሊኾን ይችላል፥ ለአንዱ በገንዘቡ ደግ ነገር ማድረግ ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ማስተማር ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ደግሞ ይህን በመሰለ ሌላ ነገር ሊኾን ይችላልና ጊዜ ሳለልን በሞተ ሥጋም ሳንወሰድ መክሊታችንን እናብዛ፡፡ አንድ ሰውስ እንኳን መክሊቴ አንዲት ናት አይበል፡፡ የተሰጠችህ መክሊት አንዲት ብትኾንም አንተ ንቁ ከኾንህ ንዑድ ክቡር ከመባል አትከለከልምና፡፡ ምንም ያህል ድኻ ብትኾንም ከዚያች ኹለት ሳንቲም ከሰጠችው ሴት በላይ ድኻ ልትኾን አትችልምና የተሰጠቺኝ ትንሽ ናት አትበለኝ፡፡ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ዮሐንስ በላይ ያልተማርክ ልትኾን አትችልምና እኔኮ አልተማርኩም አትበለኝ፡፡ እነርሱ ምንም ያልተማሩ ቢኾኑም ባሳዩት ትጋት ርስት መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ተችሎዋቸዋልና እኔ አይቻለኝም አትበለኝ፡፡

☞ እግዚአብሔር አንደበትን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር እግርን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ብርታትን፣ አእምሮን፣ ማሰብን የለገሰን ለዚህ ነው፡፡ እነዚህን ኹሉ የሰጠን ለራሳችን እንድናተርፍባቸውና ለባልጀሮቻችንም እንድንጠቅምባቸው ነውና ኹለት ወይም አምስት መክሊት አልተሰጠኝም አትበለኝ፡፡'

ተርጓሚ፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

25 Sep, 17:55


አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝና አድምጠኝ።አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።

መዝሙር 27:7-9

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

21 Sep, 10:17


ለሕጻናት የሚሆን መንፈሳዊ ስጦታ

ዋጋ 1250 ብር

አድራሻ አራት ኪሎ

ስልክ 0973180001

መንፈ�ሳዊ ስጦታ ለወዳጆቻችሁ መስጠት የምትፈልጉ ይሄንን ግሩፕ ተቀላቀሉ 🙏🙏🙏

ከአራት መቶ ብር ጀምሮ መንፈሳዊ ስጦታ አለን

https://t.me/+17wih6srsiY0ZDBk

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

21 Sep, 10:17


ለአዋቂዎች የሚሆን መንፈሳዊ ስጦታ

ዋጋ 1250 ብር

አድራሻ አራት ኪሎ

ስልክ 0973180001

መንፈ�ሳዊ ስጦታ ለወዳጆቻችሁ መስጠት የምትፈልጉ ይሄንን ግሩፕ ተቀላቀሉ 🙏🙏🙏

ከአራት መቶ ብር ጀምሮ መንፈሳዊ ስጦታ አለን

https://t.me/+17wih6srsiY0ZDBk

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

21 Sep, 10:17


ለአዋቂዎች የሚሆን መንፈሳዊ ስጦታ

ዋጋ 1250 ብር

አድራሻ አራት ኪሎ

ስልክ 0973180001

መንፈ�ሳዊ ስጦታ ለወዳጆቻችሁ መስጠት የምትፈልጉ ይሄንን ግሩፕ ተቀላቀሉ 🙏🙏🙏

ከአራት መቶ ብር ጀምሮ መንፈሳዊ ስጦታ አለን

https://t.me/+17wih6srsiY0ZDBk

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

19 Sep, 17:17


ዳግመኛ ፍጠረኝ

በሀጥያት ተውጬ ቆሽሽለውና
ዳግመኛ ፍጠረኝ ልኑር በንፅህና
አሁን ባለሁበት በእድፉ ህይወቴ
መኖር ሰልችቶኛል ከነስህተቴ
ንሰሀ መግባቱን ቅኖና መውሰድን
መች ታደልኩኝና ባንተ መመረጡን

ዳግመኛ ፍጠረኝ ልኑር እንደገና
መሄድ አብዝቻለው በስህተት ጎዳና
አብረቅርቃ አታላኝ ይቺ ከንቱ አለም
ካንተ ትዕዛዛቶች አምልጫለው ዳግም
🤲
🤲
ዳግመኛ ፍጠረኝ
አፈራርሰህ ስራኝ
ወዳንተ መልሰኝ
ልጄ ነይልኝ በለኝ
በእቅፍህ አስገባኝ

ዳግመኛ ፍጠረኝ የሰማዩ ጌታ
መኖር ሰልችቶኛል በዓለም ሁካታ
ዳግም ካነሳኸኝ ከነስህተቴ
ሌላም አልፈልግም ነገ ይሁን ሞቴ

በንሰሀ አጥበኸኝ ዳግም ከሰራኸኝ
ድጋሚ ለመኖሮ ዕድል ካገኘሁኝ
ታዲያ ለምን ብዬ ለምን እፈራለው
በቅድሱ ስፍራ ካንተ ጋር እስካለው

✍️ሄለን ንጉሴ

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

18 Sep, 13:10


ቅድስት መሪና
ቅዱስ ፊልጶስ
ቅዱስ ናሆም ነቢይ
ቅዱስ ሙሴ ጸሊም
ቅዱስ አባ ሲኖዳ


ከላይ የተዘረዘሩት ስሞች ስንት ቁጥር ላይ እና የትኛው ፊደል ላይ ይገኛሉ መልሳችሁን ግሩፕ ላይ መልቀቅ ትችላላችሁ

እንዴት እንዳሚመለስ ካልገባችሁ ከታች ያለውም ምሳሌ ተመልከቱ


ምሳሌ አንድ

አባ ጊዮርጊስ የሚለው ስም

የሚገኝበት ፊደል ( ሀ )

የሚገኝበት ቁጥር ( 8 )

ምሳሌ ሁለት

ቅዱስ ዲዮናስዮስ

የሚገኝበት ፊደል ( ለ )

የሚገኝበት ቁጥር ( 6 )

ቀድሞ ለጨረሰ እና ትክክል ለሆነ የካርድ ሽልማት አለው

የጥያቄው ዋና አላማ ቢያንስ እንኳን የቅዱሳንን ታሪካቸውን ባናውቅ እንኳን ስማቸውን እንድናውቅ በሚል ነው 🙏🙏🙏

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

18 Sep, 12:57


የዚህ ቻናል የቲክቶክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን ከታች ባለው username ልታገ ኙት ትችላላችሁ

tiktok.com/@holyvirginmaryprayforus

3,847

subscribers

276

photos

84

videos