#እኔ በሁለቱም በኩል ያለውን ለማስቆም እየሞከርኩ ነው።
እኛ የምንፈልግ የጎንደር በጌምድር ፋኖ እንደ ጎንደር በጌምድር አንድ ሁነው ከሌላው አማራ ጋር ውህደት እንዲፈጥሩ እንጅ አንድ ሳምንት ከእስክንድር ጋር አንድ ሳምንት ከዘመነ ጋር እና የጎንደር በጌምድር ህዝብ መሪ እንደለለው አድርጎ ከሌላ ጋር መለጠፍ ለጎንደር በጌምድርን ህዝብ አይመጥንም።
ሌላው ነገር በጎንደር በጌምድር አማራ ዲያስፖራ እየከፋፈሉ ያሉ የዘመነ ደጋፊ ናቸው በተለይ የነ ሀብቴ አደረጃጀት ከእስክንድ ወጥተው በዘመነ ስር እንዲሆኑ አድርገናቸዋል የእኛ ተለጣፊ ናችሁ በማለት አስነዋሪ ንግግር ይናገራሉ።
ለማንኛውም እኔ እና እኔን መሳይ የጎንደር በጌምድር ተወላጅ በትግሉ ላይ የቆየነውን ብዙ አስተዋፆ ያደረግነው ለህዝባችን መስራት እየፈለግን ፋኖዎች ከፋኖ አደረጃጀት እንድንወጣ አድርገውናል ምክናቱም እነሱ እየሰሩ ያለው ከአረብ ሀገር እስከ አውሮፓ አሜሪካ ምንም የፖለቲካ ንቃተ ህሊና የለላቸው ዘመድ አዝማድ እና የቀበሌ ስብስብ ሰብስበው ነው እየታገሉ ያሉ እንደዚህ አይነት ትግል ለጎንደር በጌምድር አማራ ትግል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ እያየነው ነው።
አንተ ምን ትላለህ ካላችሁኝ እኔ የምለው ለጎንደር በጌምድር አማራ ህዝብ የሚጠቅመውም ለውጥም የምናመጣም መጀመሪያ ከሌላ ጋር ከመለጠፍ ከቅርብ ካሉት ወንድሞቻቸው ጋር አንድ ሁነው የጎንደር በጌምድርን ህዝብ በሚመጥን የተማረ መሪ መርጠው ከሌላው አማራ ጋር አንድ ሁነው የሚሰሩበት መንገድ ቢፈጠር ባይ ነኝ ።
ከዛ በተረፈ የዘመነ ደጋፊ በጎንደር ትግል ገብታችሁ እርስ በእርስ የምታባሉነን እንድታቆሙልን እጠይቃለው ትናንት እስክንድርን ደገፉ የጎንደር ፋኖ ብላችሁ የሻለቃ ሀብቴን እና የአርበኛ መሳፍንትን ፎቶ ዘቅዝቃችሁ ስትሳደባ የነበሩ ዛሬ ከዘመ ጋር ሁነዋል በማለት የእነ ሀብቴ ደጋፊ በመምሰል የጎንደርን ህዝብም ፋኖንም እየከፋፈላችሁ ነው እና የአማራን ነፃነት የምትፈልጉ ከሆነ በአማራ ስም እንለምናችሁ ጎንደር ላይ ያለውን አንድ እስክናደርግ አይመለከታችሁም አርፋችሁ ቤታችሁ ላይ ያለውን ስራ ስሩ! ከዛ በተረፈ ሁለቱ አደረጃጀት አንድ እስኪሆኑ በአንተ አይታ እና የጎንደር በጌምድርን ህዝብ ክብር ይመጥናናል ያልከው የትኛውን ትደግፋከህ ካላችሁኝ የነ #ሰለሞን አጠና የነ #ደረጀ በላይ የነ ረዳት #ፕሮፌሰር እያሱ እና ረዳት #ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ እና ሌሎችም ያሉበት የጎንደር በጌምድር አማራ ፋኖ ደውየ ሀሳባቸውን ፍላጎታቸውን ስለሰማው እኔ እንደ ሰለሞን እነዚህን እደግፋለው።
ሰለሞን ቦጋለ