መግለጫ ለማየት join በሉ
@yeaelafat_zmare
አንድሮሜዳ አስትሮኖሚ (Sirnhatty) በአስትሮኖሚና ፍልስፍና አፍቃሪያን መካከል ላይ የተዘጋጀው ቻናል ነኝ። በቴሌግራም በተጨማሪ ዩቲዩብ እና ቲክቶክ የሚለቀቁትን ቪዲዮወችን ለመመልከት እና ግንባታውን ለመጠቀም እንዴት እንደፈለግን እንዲህ ይላል፡nnአስትሮኖሚ እና ፍልስፍና አፍቃሪያን ካሉት ፕሮፌሰንን፣ አንዶ ባተን ተኮርን ፕሮፌሰን እና የተላቀቁትን መረጃዎች ላይ ነው። ይህን ማስታወቂያዎችን ለመረጃን እዚህን ቦታውን በቴሌግራም በተጨማሪ ላይ ገልጿል። በዚህ ቦታ ለማግኘት የቴሌግራም እርዳታዎችን ማያያዝ እና የተተካራከበትን አካባቢ ለመረጋገጥ አልቅድ ያሉን ቪዲዮወች ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ።nnበአንድሮሜዳ አስትሮኖሚ ቻናሎችን ለመመልከት ለማንበብ ሊንኩ @Sirnhatty ይጫኑ።
06 Dec, 14:20
01 Dec, 09:17
30 Nov, 14:49
What is life¿ ሕይወት ምንድን ነው?]
Dostoyevsky፦ ሲኦል ነው።
SOCRATES፦ ወረራ ነው።
Aristotle፡- አእምሮ ነው።
Nietzsche፦ ጥንካሬ ነው።
Freud፦ ሞት ነው።
Marx፦ ሀሳብ ነው።
Picasso፦ ጥበብ ነው።
Gandhi፡- ፍቅር ነው።
Schopenhauer፦ መከራ ነው።
Russell፦ ውድድር ነው።
Steve Jobs፦ እምነት ነው።
Einstein፡- እውቀት ነው።
Stephen Hopkins፦ ተስፋ ነው።
Kafka፦ መጨረሻው ነው።
ለኔ ደግሞ Surprise (የማይገመት) ነዉ
..እና ፣ ህይወት ለእናንተ ምንድን ነው?
29 Nov, 18:53
28 Nov, 17:04
27 Nov, 20:45
!!
!!
27 Nov, 16:11
27 Nov, 12:05
26 Nov, 19:34
ኬቨን ካርተር የሚባል ፎቶግራፈር። ትንሿ ልጅ በረሃብ ምክንያት ልትሞት አጎንብሳ ባለበት። በዛው ትይዩ ልጅቷ እስከምትሞት ድረስ ትዕግስት አጥቶ ሲጠብቅ የሚያሳይ አንድ አሞራ በአጋጣሚ አግኝቶ ፎቶ አንስቶ ነበር። በኋላም በዚህ ሥዕል የፑሊትዘር ሽልማት በ1984 ዓ.ም አሸነፈ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ጥቂት ወራት ብቻ ነው የኖረው። ምክንያቱም ለሞት የሚያበቃ ከባድ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ ሊወድቅ ችሏል።
ከመጽሔት እስከ መጽሔት፣ ከቴሌቭዥን እስከ ቴሌቪዥን፣ በዓለም ዙሪያ ባከናወነው ስኬት ተደስቷል። የመንፈስ ጭንቀት የጀመረው በአንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ከአንድ ተመልካች ጋር የስልክ ቃለ ምልልስ ካደረገ በኋላ ነው። ሰውዬው በስልክ ደውሎ “ከፎቶው በኋላ ትንሿ ልጅ ምን ሆና ይሆን?” ሲል ጠየቀው።
እሱም መለሰ፡- ወደሃገሬ ለመመስ በረራ ስለነበረብኝ ቀጥሎ የሚሆነውን ለማወቅ አልጠበቅኩም።
ደዋዩ፡- “እነግርሃለሁ በዚያ ቀን ሁለት አሞራዎች ነበሩ። አንደኛው ካሜራውን ያነሳው ሰው ነበር!”
የዚህ እንግዳ ቃል በአእምሮው ውስጥ ደጋግሞ አቃጨለበት፤ ወደ ከፍተኛ ድብርት መራው እና.. በመጨረሻም እራሱን አጠፋ!።
25 Nov, 15:31
24 Nov, 19:21
22 Nov, 08:26
21 Nov, 17:53
የዚህ አለም ችግር መሰረታዊ ምንጩ ቢጠና EGO ነው። ትእቢት ልንለው እንችላለን። የሰው ልጅ ከንቱ ስነልቦና የመከራችን ዋርካ ስር፣ የስቃያችን ፏፏቴ ምንጭ ነው። የሰውን ሁለንተናዊ ህይወት ብትመለከቱ የሚያጠነጥነው በዚሁ ዙሪያ ነው፦ የኔ ዘር ካንተ ዘር ይበልጣል፤ የኔ እግዚአብሔር ካንተ እግዚአብሔር የበለጠ ያድናል፤ የኔ ሚስት ካንተ ሚስት በላይ ታማልላለች ወዘተ።
ታላቁ እስክንድርን ውሰዱ። ከትንሿ ሜቄዶኒያ ተነስቶ መላውን አለም በመዳፉ ስር አውሏል። የእስክንድርን "ታላቅ" የመሆን ፍላጎት የሚሾፍረው ኢጎው ነበር። ሁላችንም ውስጥ ታላቅ የመሆን ወላፈን ይንቀለቀላል። ነገር ግን ይህንን ወላፈን በጥበብ ካልያዝነው መላ ሁለንተናችንን ያጠፋናል። እስክንድርም የገጠመው ይኼው ነው። እስክንድር የሞተው ገና በ32 አመቱ ነበር። የሞተውም በገዛ ወታደሮቹ እጅ ነው። ምክንያታቸውም "በቃህ!" ነው። ዛሬ ኢጓችንን በቃህ ልንለው ይገባል። እስክንድር ለራሱ ዝናና ክብር ሲል ወታደሮቹን ከመንደር መንደር፣ ከሃገር ሃገር፣ ከአህጉር አህጉር ሲያንከራትት ወጣትነቱን ፈጀ። በ32 አመቱም ሞተ። እስክንድር መላውን አለም ቢቆጣጠርም ኢጎውን አላሸነፈም ነበር።
ሌላ ምሳሌ። ፈረንሳዊው ናፖሌዮን ቦናፓርት አውሮጳን አንድ አድርጎ ለመግዛት ያልም ነበር። ናፖሊዮን ታላቅ የጦር አዋቂ ነበር፤ ህልሙም እንደዚሁ። ከዛ ሁሉ ጦርነት፣ ከዛ ሁሉ ዘመቻ፣ ከዛ ሁሉ ግዳይ በኋላ ግን ናፖሊዮን በአንድ ደሴት ተሰቃይቶ ሞተ። አውሮጳም ከናፖሊዮን በፊት ወደ ነበረችው ቅርፅ ተመለሰች። ናፖሊዮን ምን ከወነ? ምን አተረፈ? ምንም!
የኢጎ ነገር እንዲሁ ነው። ኢጎ ከንቱነት ነው። ኢጎ ስግብግብነት ነው። ኢጎ ያልተገራ ፈረስ ነው። ያልተገራ ፈረስ የእውር ድንብሩን እዬጋለበ ከገደል ይከታል። መጨረሻውም መከራ፣ ሰቀቀን፣ ሞት ነው።
ጠላታችን ኢጎ ነው ስንል የገዛ ጠላታችን እራሳችን ነን እያልን ነው። ምክንያቱም ኢጎ ሌላ ምንም ሳይሆን የገዛ ራሳችን PSYCHE ፍንካች ነው። ኢጎ ደመኛ ጠላታችን ነው። ደመኛ ጠላታችንን ለማሸነፍ ማጥፋት፣ መደምሰስ፣ ማኮላሸት አለብን። ኢጓችንን መግደል አለብን። በዚህ ህይወት ሁላችንም ነፍሰገዳይ መሆን አለብን። የምንገድለውም የገዛ ራሳችንን ነው፤ ከማንነታችን ከፊሉን ነው። አስፈሪ ሃሳብ ነው። ግን የሕይወት ግብም ይኼው ነው። ኢጓችን እኛን ከመግደሉ በፊት እኛ ኢጓችንን መግደል አለብን። Here's the tricky part! How do we kill our ego?
መልሱ ቀላል መሳይ ነው። መልሱ በጥልቅ ማሰላሰል ነው። የሰው ልጅ አብርሆት ላይ ሲደርስ ኢጎ ይሞታል። ከኢጎ ጋር አብሮ ከንቱነት ፣ ስግብግብነት፣ እኔነት ይሞታል። እኛነት ይወለዳል። ኢጓችንን በጋንግሪን እንደተመረዘ የሰውነታችን አካል ቁጠሩት። ይህ ጋንግሪን የቀረውን አካላችንንም ከመመረዙ በፊት በጥበብ ተቆርጦ መጣል አለበት። በተመስጦ ማሰላሰል ኢጓችንን ቀርፎ የመጣል ጥበብ ነው።
የሃገራችንን ነባራዊ እውነታ ብንመለከት እንኳ መሰረታዊ ችግሩ collective ego ነው። የኛ ዘር ከእናንተ ዘር ይበልጣል፤ የእኛ ሕዝብ ከእናንተ ሕዝብ የበለጠ ጀግና ነው ወዘተ። አያችሁ ኢጎ ጉልበተኛ ነው ቢሆንም ኢጎ እውር ነው። ኢጎ በሁላችንም ነፍስ ውስጥ ያለ ግዙፍ አውሬ ነው። ቢቻል በጥበብ ማላመድ አሊያም ነጥሎ መግደል ይገባል። ኢጓችሁን ማንም መጥቶ ሊገድልላችሁ አይችልም፤ ወንዙን ሌላ ሰው መጥቶ ሊያቋርጥላችሁ አይችልም፤ ተራራውን ማንም ሊወጣላችሁ አይችልም። You've to kill your own self yourself. [ ቴዎድሮስ ]
20 Nov, 21:13
15 Nov, 19:33
15 Nov, 10:48
15 Nov, 06:01
13 Nov, 18:31
“
Should I kill myself, or have a cup of coffee? But in the end one needs more courage to live than to kill himself.”
የሚሰኘውን መፅሐፍ ሳነብ
(“
Should I kill myself. or have a cup of coffee/ራሴን ላጥፋ ወይንስ ቡና ልጠጣ?)” የሚል ሀረግ ገንጥዬ አወጣው፤ ይህ ንግግር ለአልበርት ካሙስ ጥያቄ የሆነ ሀረግ ለእኔም እንደዛው ጥቂት ጥያቄ ጫረብኝና
..ነገር ግን እኔ ካልበርት ካሙስ በተለየ መልኩ፤ ይህንን ሀሳብ ቡና እየጠጣው ነበር ያሰብኩት።
😊ለማንም ማስረዳት አልፈልግም ነበር፤ ስለዚህ ዝም ብዬ ሲጋራ አጨስኩና ባሕሩን ተመለከትኩ
. .። ``12 Nov, 15:36
08 Nov, 16:41
29 Oct, 21:16
28 Oct, 12:59
18 Oct, 19:31
18 Oct, 19:21
18 Oct, 19:21
10 Oct, 10:18
07 Oct, 07:49
01 Oct, 14:52
18 Sep, 13:18
05 Sep, 20:07
15 Jun, 03:52
15 Jun, 03:42