ትናንት ምሽት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌ አከባቢ በሚከሰት ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን፤ 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ ተናግረዋል።
አስተዳደሩ አክለውም ይህ ክስተት በሚድያ እንደሚባለዉ በቀን ሦስቴ እና ሁለቴ የሚከሰት ሳይሆን ከዚያም በላይ አስጊ እየሆነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በአካባቢዉ ያለዉ ተፈናቃይ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን ያነሱት አቶ አደም፤ መጠለያ፣ ምግብ እና መሰረታዊ ግብአቶች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል። የክልሉ የአደጋ ስጋት ድጋፍ እንዲያደርግም እንደጠየቁ ገልጸዋል።