ልብ ወለድ (fiction) english to amharic @familyethi Channel on Telegram

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

@familyethi


የኢትዮ by ahmric and english languageልብ ወለድ ጸሐፊዎች ከማዝናናት ወይም ከማስተማር በላይ ያደርጋሉ ፣ አንባቢዎች ስለራሳቸው እንዲማሩ ይረዳቸዋል። በውጭው ዓለም ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውስጠኛው ዓለምም እንዲሁ ቅርፅ የተሰጡት “ምን ቢሆን-ቢሆን” ልብ ወለዶች በሁሉም ዘመን ኖቶች ነበሩ ፡፡ ያ የውሸት እውነተኛ ዓላማ ነው.That is the true purpose of

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic (Amharic)

አሁን በዚህ ቦታ እንደገና ምስለኞቹን ገላጭ ላይ ሰለጠነችን መረጡ። በማዕከላላዊ መሆኑ አንድ ቀን ኢትዮጵያውያን ከአልመው የተነከረ እንድሉት እናመለከታለን። ልብ ወለድ ፊልሞች ከማዝናናት እንዲማሚን ያስከብራሉ። ይህ ተጨማሪ ነገር፣ ኢትዮጵያውያንን ምሳሌም በሚሰማበት ጊዜ እስኪምላታቸው ድረስ እንደነበረን ለማጥፋት ነው።

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

22 Oct, 15:00



Menu

Category » Inner Peace
11 Benefits of Peace of Mind and Tranquility
By Remez Sasson

Peace of mind is a state of tranquility and inner calm that brings numerous benefits to one’s overall well-being.
The benefits of peace of mind are numerous. It enhances mental health by reducing stress and anxiety levels. When the mind is at peace, it can focus better, think more clearly, and make decisions with greater clarity and confidence.
This heightened mental clarity also promotes creativity and problem-solving abilities, as worries or distractions do not cloud the mind.
A peaceful and tranquil mind is often associated with yogis, hermits, or monks sitting alone in a far-off place, in an ashram, cave, or monastery, praying or meditating all day.
The truth is that peace of mind can be attained and enjoyed here and now, even while leading an everyday, ordinary life with a job and family.
A peaceful mind means a mind that is calm and tranquil and stays poised in the various situations of daily life. A person with such a mind is more focused, stable, and efficient. This is a habit you can develop. It is a most helpful skill that can positively change one’s life.
Peace of mind sharpens the five senses, calms down the mind and the emotions, and enables you to focus more easily on mental and physical activities.
“The more tranquil a man becomes, the greater is his success, his influence, his power for good. Calmness of mind is one of the beautiful jewels of wisdom.”
– James Allen
11 Benefits of Peace of Mind
What are the benefits of peace of mind?
Peace of mind, which is inner peace, offers countless benefits:
Better concentration ability, meaning you can focus on anything despite distractions.
You become more efficient in handling your daily affairs of life. A tranquil mind makes better judgments and better decisions.
It contributes to a sense of inner strength and confidence.
It increases patience, tolerance, and tact.
A peaceful mind reduces and eliminates stress, anxieties, and worries.
There is a sense of inner happiness and bliss when there is calmness.
With a peaceful mind, there are no disturbing and uncontrolled thoughts, and this helps you fall asleep easily and sleep soundly.
When your mind is at peace, you are not affected by what people think or say about you.
A peaceful and tranquil mind is free from restless thinking and running from one unimportant thought to another.
With a peaceful mind, you stop being swayed and agitated by events, problems, or difficulties.
A tranquil mind helps you maintain a state of inner poise and clear judgment in all situations.
This is just a small list of the benefits of peace of mind, but I hope it is enough to let you consider gaining this skill.

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

09 Feb, 19:17


ሳናውቅ አንፍረድ...

በአንድ መንደር ውሰጥ ይኖር የነበረ አንድ ትልቅ አርቲስት ነበር ፤ ይኼም አርቲስት ስራዎቹን በመሸጥ የተሻለ ክፍያ ያገኛል። ታዲያ በአንድ ወቅት በአካባቢው የሚኖሩ ድሃዎች ተሰባስበው ወደ አንጋፋው አርቲስት ጋር በመሄድ እንዲህ አሉት፦
"አንተ ለምንድነው የአካባቢውን ሰዎች የማትረዳው? አንተ ከሁሉም የተሻለ ገቢ አለህ። ካንተ ያነሰ ገቢ ያላቸው ዳቦ ጋጋሪውና ባለ ልኳንዳው ስጋ ሻጩ ለአካባቢያችን ድሆች በነጻ ይሰጣሉ በማለት ጠየቁት?
    አርቲስቱም ፈገግ አለ በሁኔታው ሰዎቹ  ግራ ተጋብተውና  ተናደው ጥለውት ወጡ። ነግርግን ሌላ ቀን ወደ ውጭ ሲወጣ ጠብቀው ደበደቡት ፤ እድሜው የገፋ ነበረና በዚያው ታሞ አንድ ጠያቂ እንኳ ቤቱ ሳይመጣ በዚያው ሞተ።
    ሆኖም ከዚያም ቀን በኋላ ዳቦ ሻጩም ስጋ ሻጩም በነጻ መስጠት አቆሙ። የአካባቢው ሰዎች ግራ ቢገባቸው ምከንያቱን መጠየቅ ጀመሩ። ያገኙትም ምላሽ ያ አንጋፋው አርቲስት በየወሩ በነጻ እንድንሰጥ ብዙ ብሮችን ይሰጠን ነበር ፤ አሁን ግን ስለሞተ አገልግሎቱ መስጠት እንደማይችሉና  እንደተቋረጠ ተነገራቸው።
    ብዙዎቻችን በሰዎች ላይ በቂ መረዳት ሳይኖረን የተሳሳተ ግንዛቤ ሊኖረን ይችላል።
  አንዳንዴ ነገሮች እንደምናየቸው አይደሉም በሰዎች ላይ ለመፍረድ አንቸኩል።

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

08 Jan, 17:26


ለምን መጣህ?" እና "ለምን ነው የምትኖረው?" ይህ ደግሞ ስለ ሕይወት ትርጉም እና ስለ ጥሪዎ ነው። የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለእርስዎ ዘላቂ ተነሳሽነት እና መመሪያ እና ጥንካሬ ይሰጥዎታል። እና ይሄ ከሁሉም አነሳሽ ንግግሮች፣ ራስን የማበረታቻ ቴክኒኮች፣ የማበረታቻ ጥቅሶች ወዘተ የበለጠ በጥልቀት ይነካዎታል። ወደ ጥልቅ መሄድ ከፈለግክ፡ የሚከተለውን አበረታች መልእክት ለራስህ ተመልከት! የሚከተለው መልእክት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለውጦታል። ሕይወትዎ ለዘላለም በተሻለ ሁኔታ ሊለወጥ ይችላል! ይህን ጊዜ ይውሰዱ፣ ምክንያቱም ዋጋ ያለው ነው… ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ ነው የሚወስደው! *የመጀመሪያው መልእክት የዛሬ 2,000 ዓመታት ገደማ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለበለጠ መረጃ መልእክቱን ተመልከት። መልእክቱ የሁሉም ሰዎች መልእክት ነው ለሰው ልጅ ግን ለእናንተም በግል!

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

08 Jan, 17:23


Why are you here?” and “What are you living for?
This is also about the meaning of life and your calling. The answer to these questions will give you lasting motivation and direction and strength for your.
And this will touch you much deeper than all the motivational speeches, self-motivation techniques, motivational quotes etc.
If you really want to go deeper, then check out the following motivational message for yourself!
The following message has already fundamentally changed the lives of billions* of people.
Your life can change forever for the better!
Take this time, because it’s worth it… It takes only a few minutes!
*Since the beginning of the original message about 2,000 years ago, see the message for more information.
The message is for all people, a message for humanity, but also for you personally!

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

08 Jan, 17:17


Part one
This is a real motivational Message for you!
Are you looking for motivation for your life?
New direction, happiness, success, contentment, new hope and strength?
Do you know who or what really motivates you in life and where your path is leading?
Finding lasting motivation and deep change boils down to two questions:
ይህ ለእርስዎ እውነተኛ ማበረታቻ መልእክት ነው! ለህይወትዎ ተነሳሽነት እየፈለጉ ነው?
አዲስ አቅጣጫ፣ ደስታ፣ ስኬት፣ እርካታ፣ አዲስ ተስፋ እና ጥንካሬ? በህይወት ውስጥ ማን ወይም ምን እንደሚያነሳሳህ እና መንገድህ ወዴት እንደሚመራ ታውቃለህ? ዘላቂ መነሳሳትን እና ጥልቅ ለውጥን መፈለግ ወደ ሁለት ጥያቄዎች ይቀነሳል።

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

23 Nov, 16:53


ሳታልፍ በፊት ኑር!

በዚህ አለም የሚያረጋጋ ቃል ቢኖር አንዱ "ሁሉም ያልፋል" የሚለው ነው፤ ሀዘኑም ያልፋል፣ደስታውም ያልፋል፣ ንዴቱም ያልፋል፣ እርካታውም ያልፋል፤ ሌላውን ተወው አንተም እኔም እናልፋለን! በፍጥረት አለም ፀንቶ የሚኖር ነገር ቢኖር አምላክ ብቻ ነው።

ታዲያ ለሚያልፍ ችግር ለምን አብዝተህ ትጨነቃለህ? ለሚያልፍ ቀን ለምን ራስህን ትጎዳለህ? ህይወትህን ነብስ ዝራበት፤ የምትወደውን ስራ፣ የምትወዳትን የራስህ ለማድረግ ተዘጋጅ፣ የምድርን በረከት ሁሉ አጣጥም፤ ሳታልፍ በፊት ኑር ወዳጄ!


...... ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

05 Sep, 17:36



ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች

ይብዛም ይነስም የለውጥና የእድገት ሃሳብ የሌለው ሰው የለም። ይህን
ሃሳቡን ለመጀመርም ቀናትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትንና አመታትን በመቁጠር
ከጊዜ ወደ ጊዜ አንድ ቀን እያለ እድሜውን የሚፈጅ ሰውም ጥቂት
አይደለም።

አንድ አባባል አለ፦ "አንድን ዛፍ የመትከያው ትክክለኛውም ጊዜ የዛሬ ሃያ
አምስት አመት ነው። እርሱ ካልሆነ ግን ሁለተኛው ትክክለኛ ጊዜ ዛሬ ነው።"
አንድን ቀን በመናፈቅ እጅግ በጣም ብዙ የማይመለሱ ቀናት አልፈዋል።

ሃሳብ ሃሳብን እየወለደ ጊዜም በዛው ፍጥነት እየከነፈ ሩጫውን ቀጥሏል፣
እኛም እንዲሁ አንድ ተዓምራዊ ቀን እስኪፈጠርልን በጠበቅን ቁጥር
አቅምና ተነሳሽነታችን እየተመናመነ፣ የኋሊት ጉዟችን እየተፋጠነ፣ እያየን
እየመሸብን፣ ጀምበርም እያዘቀዘቀችብን ትመጣለች። መነሳት ባለብህ ጊዜ
ካልተነሳህ ውዳቂ ሆነህ መቅረትህ የማይቀር ጉዳይ ነው።

አዎ! ወሳኙን ጨክነህ ምረጥ! አንድ ቀን ወይስ ቀን አንድ? One Day or
Day One? የትኛው የሚያዋጣህ ይመስልሃል?

ዘመንህን ሙሉ አንድ ቀን የቋንቋ ትምህርት እጀምራለሁ፣ አንድ ቀን የእራሴን
ስራ እጀምራለሁ፣ አንድ ቀን ሱሴን አቆማለሁ፣ አንድ ቀን እቀየራለሁ፣ አንድ
ቀን ከእዳዬ እገላገላለሁ እያልክ የአንድ ቀን ናፋቂ የተቀሩትን ቀናት አክሳሚ
ሆነህ አትቅር። "የመዳን ቀን ዛሬ ነው" እንደሚል ቃሉ የለውጥ ቀንም ዛሬ
ነው። ለምንም ይሁን ለማን ከዛሬ የተሻለ ቀን የለም።

አዲስ ክህሎት ለመማር፣ ንባብ ለመጀመር፣ ፍረሃትን ለመጋፈጥ፣ ጭንቀትን
ለማስወገድ፣ ሸክምን ለማራገፍ፣ ውስጥን ለማረጋጋት፣ ወደ ፈጣሪ
ለመመለስ፣ ህልምን መኖር ለመጀመር ከዛሬ በላይ ተመራጭና የተሻለ ቀን
የለም።

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

14 Jul, 05:01


አይ እኛ...

"እንቁላሉ ስንት ስንት ነው?" ስትል ጠየቀቻቸው…
"አንዱ እንቁላል 4 ብር ነው " ልጄ በማለት መለሱ፣ እማማ…
"አምስቱን እንቁላል በ15ብር ልወሰደው?…" ስትል ደግማ
ጠየቀቻቸው …
"አይጎዳኝም ብለሽ ነው ልጄ?"…በማለት ደከም ባለ ድምፅ
መለሱላት…
"ከፈለጉ ይሽጡ፣ ካልፈለጉ ግን በቃ መሄዴ ነው…" አለች፣ ጠንከር ባለ ድምፅ…
እማማ ትንሽ አሰቡና ቀና ብለው አይተዋት…
"እስካሁን ምንም አልሸጥኩም፣ ባያዋጣኝም እንደ መጀመሪያ ገድ ልቁጠረውና ልሽጥልሽ፣ የፈለግሺውን ያህል እንቁላል በፈለግሺው ዋጋ ውሰጂ…" ሲሉ በደከመ ድምፅ ተናገሩ…
ዘንቢሏን አውጥታ 5 እንቁላል መርጣ አስገባች፣ ከበርካታ 100 ብሮች መካከል ነጥላ 15 ብር አውጥታ ወርውራላቸው...
እየተጣደፈች የሚያምረው ዘመናዊ መኪናዋ ውስጥ ገባች…
የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷታል…

ከጓደኛዋ ጋር ወደ አንድ ዘመናዊ ሬስቶራንት ገብተው
የሚፈልጉትን አዘዙ…ትንሽ በልተው ብዙ አተረፉ። ተዝናኑ። ሂሳቡ
ሲመጣ ቢሉ ላይ 1420 ብር ይላል ። ከቦርሳዋ ውስጥ 1500
ብር አውጥታ ሰጠች ። መልሱን ለሪስቶራንቱ ባለቤት ቲፕ
እንዲሆነው ነግራው ወጥተው ሄዱ…

ይህ ድርጊት ለሬስቶራንቱ ባለቤት አዲስ አይደለም፣ ለእንቁላል
ሻጯ እናት ግን አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ነው…
.
.
.
👉ከድሆችና ከምስኪኖች የምንፈልገውን ለማገኘት የበላይነታችንን ለማሳየት የምንጥረው ለምንድን ነው? የእኛን
እርዳታ ለማይፈልጉትስ ቸር ሆነን ለመታየት ለምን እንፈልጋለን?
.
.
.
💥ለሚገባው እንስጥ🙏

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

06 Jul, 00:54


በቃላችን መሰረት ይኸው ታሪኩን ይዘን ከች ብለናል?
መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።
ሰሜናዊት ሙሽራ
ምዕራፍ 1 (አንድ )
ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
በጠዋት ከ ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን የሚወጣው ህይወትን የሚያለመልም የቅዳሴ ዜማ በጆሮዬ አቀጨለና ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ።ከብርድ ልብሱ ውስጥ ሳልወጣ አይኔን ሸፍኜ ይሔን ጥዑም ዜማ እየኮመኮምኩ ሳለሁ "ዮርዲ ቁርስ ደርሷል" የሚል ድምፅ ከተመሰጦዬ መለሰኝ ።ብርድ ልብሱን ከአይኔ ላይ ቀስ ብየ ስገልጠው መጋረጃውን አምልጣ ሰርጋ ከገባችው የጠዋት ፀሐይ ጋር ተጋጨን።ቢጫ ቀለም ከተቃባው ምኝታ ቤት ጋር ፀሐይ ተደምራ ክፍሉን በብርሀን አሽቆጥቁጣዋለች።"ዋው ደስ የሚል እሁድ "አልኩና ከአልጋየ ላይ ወረድኩ። ................ቁርስ እንደነገሩ ከቀማመስኩ በኋላ አንድ ሲኒ ቡና ፉት ብዬ ወደ ክፍሌ ገባሁና ከውስጥ ዘግቼ ቁጭ አልኩ ።ትንሽ በሀሳብ ስባክን ቆየሁና "ደሳለኝ ያለኝ ነገር እውነት ነው እሱን መስማት አለብኝ" አልኩና በውስጤ ከተቀመጥኩበት በወኔ ተነስቼ ከመሳቢያው ውስጥ እስክሪብቶ እና ወረቀት አወጣሁና በድፍረት ጫር ጫር እድርጌ ወደ ኪሴ አስገባሁት ። ወደ መስታወቱ ተገጠቼ ከምስሌ ጋር ተፋጠጥኩ ።"ድፈር ዮርዲ አንተ እኮ የኔ ወንድም ነህ አንተ እኮ ዮርዳኖስ ነህ ታደርገዋለህ" የደሳለኝ ድምጽ ደጋግሞ ጆሮዬ ላይ ደወለ።በረጅሙ ተነፈስኩ እና መስታወቱ ውስጥ ሆኖ የሚያየኝን የራሴው ምስል "ድፈር ዮርዳኖስ ድፈር ካለመናገር ደጅ አዝማችነት ይቀራል " አልኩት ከሌላ ሰው ጋር የማወራ ያሀል ጮህ ብዬ ።ዛሬ ከየት እንደመጣ የማላውቀው የወኔ ካባ በላዬ ላይ ተደፍቷል ።ግቢያችንን ለቅቄ ጉዞ ጀመርኩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ ተሾመ እባላለሁ ከእናቴ ከ ወ/ሮ አለም አወቀ እና ከአባቴ ከአቶ ተሾመ ታምሩ መስከረም 05,1992ዓ.ም ይችን ዓለም ተቀላቀልኩ ።ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ነኝ አህቴ ቤዛዊት ተሾመ ።በጣም የምወዳት ታላቅ እህቴ ነች በሊትሌቸር ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በዚህ ክረምት ነው የተመረቀችው።አባቴ ነጋዴ ነው እናቴ የቤት እመቤት።ኑሯችን ከደብረ ማርቆስ 15 ኪ.ሜ እርቃ ከምትገኘው ትንሿ አምበር ከተማ ነው።ሀብታሞች አይደለንም ድሆችም አይደለንም የጎደለን የለም ።ቤተሰባችን ውስጥ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች አሉ።እድሜ ጠገቧ አያቴ እና የቤት ሰራተኛዋ እልፍነሽ።ቤተሰባችን ፍቅር ነው። ፍቅር ማለት የእኛ ቤተሰብ ነው ብል ማጋነን አይሆንም! 2007 ማትሪክ ተፈትኜ ውጤት እየጠበኩ ነው ።ብዙ ጓደኞች አሉኝ።ደሳለኝ ግን ከጓዳኛ በላይ ወንድሜ ነው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከግቢያችን በስተሰሜን በግምት 100 ሜትር ያክል ከተጓዝኩ በኋላ ከአንድ ትልቅ ግቢ ላይ ደረስኩ።ትንሽ ከአቅማማሁ በኋላ "አብርሃም አብርሃም " ብዬ እንደተጣራሁ ያ እንደ ጦር የምፈራው ምዕታተኛው የሔዋን ድምፅ ማነው አለኝ።መልስ አልመለስኩም ልቤ አታሞውን ይደልቅ ጀምሯል። በሩም ተከፈተ ወኔየን ሰብሰብ አድርጌ ቆምኩ።
ይቀጥላል...

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

06 Jul, 00:48


የአንድ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ፕሮፌሰር የሚከተለውን
ድንቅ ጥናት እንዳገኘ በቅርቡ ይፋ አድርጓል!!
ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው አስከመጨረሻው
በቅደም ተከተል አስቀመጠA b c d e f g h i j k l m n o p
q r s t u v w x y z። የነዚን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል
ኣስቀመጠ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16
17 18 19 20 21 22 23 24 25 26
በጥናቱም ለያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ
ለ"A"=1 ፣ ለ"B"=2 ......... እያለ አስከ "Z" =26ን
ሰጠ።በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ።
1. ትጉ ስራ
(H+a+r+d+w+o+r+k)
(8+1+18+4++23+15++18+11)=98%
2. እውቀት
(K+n+o+w+l+e+d+g+e)
(11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96%
3. ፍቅር
(L+o+v+e)
(12+15+22+5)=54%
4. እድል
(L+u+c+k)=47%
በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም ለውጥ
መቶ ፐርሰንት(100%)ሊሰጡ አንደማይችሉ አስቀመጠ። ታዲያ
(100%)ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው? ብር ይሁን
እንዴ??
5. ገንዘብ (M+o+n+e+y)
(13+15+14+5+25)=72%
አይደለም ምን አልባት አመራር ይሁን?
6. አመራር
(L+e+a+d+e+r+s+h+i+p)
(12+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97%
አሁንም አይደለም!
ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው። አስተሳሰብ፣አካሄድ አኳኋናችንን
ስንቀይር ይቀየራል። ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ።
7. አስተሳሰብ
(A+t+t+i+t+u+d+e)
(1+20+20+9+20+21+4+5)=100%
እናም ወዳጄ ውጤትና የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው
የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

06 Jul, 00:45


ልጅቷ የቤታቸው በር ይንኳኳና ስትከፍተው ፍቅረኛዋ ነው፤
ግን አባትዋ በቅርብ ርቀት ሰለነበሩ በስነ-ስርአት ሰላም
አላለችውም ወዲያውኑም ልጁ እንዳይቀባጥር በኮድ
# እሷ ፦ሀይ ሰላም ነው " አባቴ እቤት ነው"የሚለውንየበውቀቱ
ስዩም መፅሀፍህን ልትወስድ መጥተህ ነው?
# ልጁ ፦ ወዲያውኑ ይነቃና እር እኔስ የበአሉ "ግርማን ታዲያ የት
ልጠብቅሽ"የሚለውን መፅሀፍ ልወስድ ነበር።
# እሷ ፦ውይ እሱን መጽሀፍ እንኳን ቶሎ አላገኘውም ባይሆን
ያአዳም ርታን" ከማንጎው ዛፍ ጥላ ስር" የሚለውን ልስጥህ"
# ልጁ፦ ጥሩ በዛው" እንደ ደርስኩ እደውላለሁ"የሚለውን
መጽሀፍም እንዳትርሽው.
እሷ፦እር ምንም ችግር የለም የይስማክ ወርቁን ቶሎ መጣለሁ
ጠብቀኝ የሚለውንም ይዥልህ መጣለሁ:
......................ልጅቷ በሩን እንደዘጋች አባቷ አስቆማትና
# አባት ፦በጣም የሚገርም ነው ይህንን ሁሉ መጽሀፍ ያነባን?
# እሷ ፦ አወ አባየ እንዲት ያለ ስማርት ልጅ መሰለህ!
# አባት ፦በጣም ደስ ይላል እንደዛ ከሆነማ እኔም አንድ መጽሀፍ
ልስጥሽና ትወስጅለት አለሽ:
# እሷ ፦ እሽ አባየ የቱን መጽሀፍ ?
አባት፦ እዛ መደርደሪያ ላይ ሀዲስ አለማየሁ የፃፈው በናተ ቤት
በኮድ አውርታችሁ ልባችሁ ውልቅ ብሏል የሚለውን!

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

28 Jun, 00:32


የማያበቃ የፍቅር ጥበቃ❗️
(ዳንኤል ታረቀኝ)
😭
ቱርክ ውስጥ እንደ ሮሚዮ እና ጁሊየት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ እንደ በዛብህ እና ሰብለ ወንጌል ልብ የሚያሞቅ ታሪክ እንካ❗️
ይህ ልብ ወለድ አይደለም። የሮሚዮና ጁሊየትን እና የበዛብህና የሰብለወንጌልን ልብ ወለዳዊ ትርክት ትውስታ የሚቀሰቅስ ልብ የሚያሞቅ እውነተኛ ታሪክ እንጂ።
ነገሩ እንዲህ ነው። ቱርካዊው ኢሴክ ኦኩዙኩ፣ ከፍቅረኛው ጋር እዚያው ቱርክ ውስጥ፣ ጥቁር ባህር ዳርቻ፣ በሲኖፕ አውራጃ በሚገኝ የአውቶቡስ ማቆሚያ ቦታ ተዋወቀ። ህይወቱን ያመሰቃቀለው አሳዛኙ ክስተት እስኪከሰት ድረስ ፍቅራቸው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነበር። (አንባቢ ሆይ፦ ፍቅራቸው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነበር ማለቴ፣ "አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ"፣ "መሬት አይንካሽ/አይንካህ" ይባባሉ ነበር ማለት እንደሆነ ልብ በል)
አሳዛኙ ክስተት፣ የኢሴክ ኦኩዙኩ ዐይን መታመም ነበር። ገና በወጣትነቱ አይኑን በጠና የታመመው ኢሴክ ኦኩዙኩ፣ በርካታ ምርመራዎችን እና ህክምናዎችን ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቶ በግዜ ሂደት የዐይን ብርሐኑን አጣ።
አበው "የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል" እንዲሉ፣ ስቃይህ ይብዛ መከራህ ይደራረብ ሲለው፣ ፍቅረኛውም ላትመለስ ወደ ኢስታምቡል ጥላው ሄደች።
ከዚያን ግዜ ጀምሮ፣ ይኸው ኢሴክ ኦኩዙኩ፣ ፍቅረኛውን አንድ ቀን ትመለሳለች በሚል ተስፋ፣ ለመጀመሪያ ግዜ ያገኛት አውቶቡስ ማቆሚያው ቦታ ላይ ቆሞ ላለፉት 24 አመታት እየጠበቃት ይገኛል።
ኢሴክ ኦኩዙኩ ከአንድ ወንድም በቀር ሌላ የቅርብ ዘመድ የለውም። ወንድሙም ቢሆን አብሮት አይኖርም።
ኢሴክ ኦኩዙኩ በዚህ አሳዛኝ ታሪኩ ልባቸው የተነኩ፣ በጎ አሳቢዎች፣ ባቀረቡለት የኮንቴነር ቤት ቢኖርም፣ ዕለት ዕለት መገኛው እዚያው አውቶቡስ ማቆሚያው ስፍራ ሆነ። የአካባቢው ማህበረሰብም ፍቅረኛውን በማጣት ላሳለፈው ሀዘንና ለፅናቱ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ የአውቶቡስ ማቆሚያውን በስሙ "ኤሲክ ኢሴቪት መቆሚያ" በሚል መጠሪያ ሰይሞታል።
የዚህን ተመሳሳይ ታሪክ አዲስ አበባ ጎፋ ሰፈር ታገኙታላችሁ።
ስሙ ለማ ይባላል። ኢንጂነር ነበር። ለብዙ አመታት(ባልሳሳት ለ20 አመታት አካባቢ) አሁን በቆመበት ቦታ ላይ ቆሞ ትታው ወደ ውጭ ሀገር የሄደችውን ፍቅረኛውን የሚጠብቅ።
ከተለያዩ ምንጮች እንዳገኘሁት ለማና ፍቅረኛው በጋብቻ ተሳስረው ለመኖር እቅድ የነበራቸው ሲሆን፣ በአንድ ክፉ ቀን ላትመለስ ጥላው ሄደች። የለማ ህይወትም ተመሰቃቀለ። ስራውን ተወ። ውሎውንም ቀድሞ በፍቅር ግዜያቸው ይጠብቃት እና ያገኛት በነበረበት ቦታ አደረገ። ይኸው እስከ ዛሬ የዘለቀውን፣ የማያልቀውን ጥበቃ ጀመረ። ዛሬም እንኳ ይህንን ታሪክ እየፃፍኹ፣ በጎፋ መስቀል ክትፎ አካባቢ ሳልፍ፣ በመንገዱ አካፋይ ላይ ቆሞ አይቼዋለሁ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የለማ ፍቅረኛ ከረጅም አመታት በኋላ መጥታ እርሱ እንዳላወቃት እና እርሷም አግብታ ወመውለዷንም ሰምቻለሁ። ለማ ግን ጥበቃ ላይ ነው። አሳዛኝ፣ ነገር ግን ለፍቅር የተከፈለ ዋጋ❗️
ቱርክ ውስጥ እንደ ሮሚዮ እና ጁሊየት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ እንደ በዛብህ እና ሰብለ ወንጌል፣ የሚያሳዝን ነገር ግን ልብ የሚያሞቅ ታሪክ ያልኩህ የፍቅርን ኃያልነት የሚያጎሉ፣ የእነዚህን በማያበቃ የፍቅር ጥበቃ የተጠመዱ፣ ሁለት ሰዎች እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ነው❗️
አበቃሁ❗️
ከተመቻችሁ እናንተም የፍቅር ሰዉ ሁኑ

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

01 Jun, 06:37


https://t.me/+RS2MZ3b1qSCzdBy7

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

21 May, 23:52


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላችሁ🙏

📌አንዳንዴ አሁን ባለንበት ህይወት ደስተኛ አንሆንም፤ ነገር ግን በአለም ላይ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች የእኛን ህይወት ለመኖር በፀሎት ላይ ናቸው።

📌በእርሻ ውስጥ ያለ አንድ የገበሬ ልጅ ከጭንቅላቱ በላይ የሚበር አውሮፕላን አይቶ መብረርን ያልማል። ነገር ግን የአውሮፕላን አብራሪው ካፒቴን የገበሬዎቹን ጎጆዎች ተመልክቶ በሰላም ወደ ቤቱ መመለስን ይመኛል።

📌ህይወት ማለት ያ ነው። ያለንን እንደሰትበት፤ እናመስግንበት። ሀብት የደስታ ምንጭ ቢሆን ባለፀጎች በመንገድ ላይ በነሱ ነበር። ነገር ግን ደሃ ህፃናት ናቸው ያን ሲያደርጉ የሚታየው።

📌ስልጣን ደንነትን የሚያረጋግጥ ቢሆን መሪዎች ያለ አጃቢ ይሄዱ ነበር። ግን ቀላል ህይወት የሚኖሩት ናቸው በነፃነት ሲንቀሳቀሱ ውለው የሰላም ዕንቅልፍ የሚተኙት።

📌ቆንጆና ታወቂ መሆን አስደሳች ግንኙነት ለመፍጠር ዋስትና ቢሆኑ ታዋቂ ሰዎች ሁሉ የተሳካ ትዳር ይኖራቸው ነበር።

በጠቅላላው አሁን እየኖርነው ያለው ህይወት ከምንመኘው ሌላ ህይወት የተሻለ ቢሆን እንጂ አያንስም። ከሁሉም ከሁሉም ደሞ የእኛን ህይወት ለመኖር ሌት ከቀን ፈጣሪያቸውን የሚለምኑም እንዳሉ አንርሳ።
🙏ለተደረገለን ሁሉ እናመስግን🙏

🙌በሰላም አምሹ🙌

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

21 May, 23:51


ራስህ ላይ አትጨክን!

ትልቁ ነጥብ ስህተት መስራትህ አይደለም ወይ መውደቅህ፣ ጥፋት ማጥፋትህ አይደለም ግን መልሰህ መነሳትህ ነው፤ ልብስም እኮ ይቆሽሻል ግን አጥበህ መልሰህ ትለብሰዋለህ።

አንተም ስትሳሳት ራስህ ላይ አትጨክንበት፤ ያጠፋ ሰው አንዴ ነው የሚቀጣው፤ በየቀኑ "እኔኮ አልረባም" እያልክ ራስህን አትውቀሰው! ልብሱ ከታጠበ አንተ የማትለወጥበት ምክንያት የለም!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

21 May, 23:46


ጩኸት እና ንግግር
#ክፍል 1
በታክሲ እየሄድኩ ነው፡፡ መካከለኛው ወንበር ነው የተቀመጥኩት፡፡ አንዲት ሴትዮ በስልክ በንዴት
ያወራሉ፡፡ በጩኸታቸው መጨረሻ «እንዲያውም ካሁን በኋላ ካንተ ጋር መኖር አልችልም፤ በቃ» ብለው
ዘጉት፡፡ በታክሲ ውስጥ የነበርነው ሁሉ በድንጋጤ እያየን ነበር ያዳመጥናቸው፡፡
ወዲያው አንዱ ቀልደኛ «እናቴ ይህንን በቃ የሚል ቃል እንኳን ቢተውት፤ ሌላ ትርጉም ያመጣል» ሲል
ሁላችንም ከድንጋጤው ወጥተን ሳቅን፡፡
ስልኩን ሲጨርሱ ሁላችንም ወደርሳቸው መዞራችንን ሲያዩ ደንገጥ አሉ፡፡ አጠገባቸው ተቀምጠው የነበሩት
አዛውንትም ፈገግ አሉላቸው፡፡
«ልጄ ልበልሽ ወይስ እናቴ?» አሉ አዛውንቱ በነጭ ሪዛቸው ውስጥ ፈገግታቸውን እያሳዩ፡፡
«ኧረ ልጄ ይበሉኝ» አሉ ተናደው የነበሩት ሴትዮ
«በጣም ጥሩ» አሉና አዛውንቱ ከወንበራቸው ላይ ተመቻቹ፡፡
«እይውልሽ በጣም ስትናደጅ እና በጣም ስትደሰች እባክሽ ውሳኔ አትወስኝ» አሏቸው፡፡ የሁላችንም ጆሮ
ወደ አዛውንቱ አቀና፡፡
«ቅድም እየተናገርሽ አልነበረምኮ፣ እየጮኽሽ ነበር፡፡ ጩኸት እና ንግግር ይለያያሉ፡፡ መናገር ተረጋግቶ፣
አስቦ፣ ውጤቱን አስልቶ ነው፡፡ መጮኽ ግን አፍ እንዳመጣ ነው፡፡» አሏቸው፡፡
«አሁን ምን እንደተናገርሽ ብጠይቅሽ አታስታውሽውም፤ ምክንያቱም አንደበትሽ ሳይሆን ምላስሽ ብቻ ነበራ
የሚናገረው»
«በአንደበት እና በምላስ መካከል ልዩነት አለ እንዴ» አለች አንዲት ወጣት፡፡ሌሎችም ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡ «ምላስ እና አንደበትማ ይለያያል፡፡ ምላስ ማለት ይቺ ቅልብልቢቱ ናት፡፡» አሉና ምላሳቸውን አውጥተው
አቅለበለቧት፡፡ ሁላችንም ሳቅን፡፡ ሾፌሩ በተለይ ከልቡ ሲስቅ ጊዜ፡፡ «ሾፌር ይኼ ጨዋታ አንተን
አይመለከትም ዝም ብለህ ንዳ» አሉት፡፡
«ይቺ እንዳ መጣላት የምትለፈልፈው ናት ምላስ፡፡ አንደበት ግን ልብ አውጥቶ አውርዶ ያቀበለውን
ለሰሚው የሚናገረው ነው፡፡ አንደበት ምላስን ይጨምራል፤ ምላስ ግን አንደበትን አይጨምርም» አሉ፡፡
ይኼ እኔ በሥነ ልሳን ከተማርኩት የተለየ ፍልስፍና ነው ብዬ መከታተል ቀጠልኩ፡፡
«ታድያ ሰው ሲናደድ ወይንም ሲደሰት ምንድን ነው ማድረግ ያለበት?» አላቸው አንደኛው፡፡
«ቢቻል ዝም ቢል መልካም ነው፤ »
«ካልቻለስ»
«ካልቻለ ደግሞ ውሳኔ የሌለው ነገር መናገር፡፡»
«ለምሳሌ ምን ዓይነት?»
«አየህ ልጄ እጅግ በጣም በተደሰትክ ጊዜ የምትወስነውን ቀርቶ የምትናገረውን አታውቀውም፡፡ ስሜት
መንፈስን ይጫነዋልና፡፡ ስሜት መንፈስን ከተጫነው ደግሞ ልቡና አይሠራም፡፡ በል በል አድርግ አድርግ
የሚል ነው የሚመጣብህ፡፡ ስለዚህ ምንም አለመወሰን ነው፡፡ እነዚህ ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰዎች ምን
እንደሚያደርጉ ታውቃላችሁ?» ብለው ሲጠይቁ አናውቅም በሚል ስሜት ሁላችንም አየናቸው፡፡
«የሚያደርጉትኮ ሁላችንም እንድንደሰት ወይንም እንድናዝን ማድረግ ነው፡፡ ስሜታችንን መቀስቀስ ነው፡፡
ያን ጊዜ እኛ እጅግ በማዘንም ሆነ እጅግ በመደሰት ይህንን ያህል እንሰጣለን ብለን ቃል እንገባለን፡፡
ታድያ አንዳንዱ ሰው ስሜቱ ተረጋግቶ መንፈሱ ሲያንሠራራ ምን ነክቶኝ ነው ይላል፡፡ ለዚህ ነው
ስትደሰቱ ወይንም ስታዝኑ አትወስኑ ያልኳችሁ፡፡
«ግዴላችሁም አሳልፉት፡፡ ንዴት ዘላቂ አይደለም፡፡ ደስታም ጊዜያዊ ነው፡፡ ሰው አንድን ነገር ከመናገሩ
በፊት አምስት ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡»
«ምን ምን» አልናቸው፡፡
«የቀደመ ዕውቀት፣ የቀደመ ልምድ፣ ያለበት ሁኔታ፣ የሚያመጣው ውጤት እና መፍትሔው መናገር ነው
ወይ?» የሚሉት ናቸው፡፡
«ይተንተኑ» አለ ሾፌሩ በንግግራቸው ተስቦ፡፡
#ይቀጥላል

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

21 May, 23:39


ሁለቱ ክህሎቶች፡- ሁለት አይነት ክህሎቶች አሉ፡- አንደኛው የሞያ ክህሎት ሲሆነ፣ ሌላኛው ግን ማሕበራዊ ክህሎት ነው፡፡ የመጀመሪያው ስራን በስኬታማነት እንድንሰራ ሲያደርገን፣ ሁለተኛው ግን ማሕበራዊ ግንኙታችን የሰመረ እንዲሆን ያግዘናል፡፡ ማንኛውም የሞያ ክህሎት ከማሕበራዊ ክህሎት ውጪ ብዙ ርቀት አያስኬደንም፡፡ ለማብራሪያውና ለግንዛቤው መጽሐፉን ማንበብ ጠቃሚ ነው፡፡

ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . .

ምን ዋጋ አለው?!

የሕክምና ባለሞያው ምን ያህል አዋቂና “ፈዋሽ” ቢሆን፣ ለሕመምተኞች ካለው ርህራሄ ተነስቶ ሕብረተሰቡን ከማገልገል ይልቅ ለክብሩና ለጥቅሙ ካደረ ምን ዋጋ አለው …

የሕግ ባለሞያው ሕግን ጠንቅቆ ቢያውቅ፣ ከፍትህ ይልቅ በጠማማነት የሚገኘውን የግል ጥቅም ካስቀደመ ምን ዋጋ አለው …

መሃንዲሱ በፈጠራ ብቃቱና በቅልጥፍናው በሰው ሁሉ ተፈላጊ ቢሆን፣ ከጥራትና ከደህንነት ይልቅ አስተርፎ የሚያተርፈውን ካሳደደ ምን ዋጋ አለው …

ሂሳብ አዋቂዋ ቁጥርን ከቁጥር በማጋጨትና በማስማማት ብቃቷ ወደር ባይገኝላት፣ በስንፍናዋና በግድ የለሽነቷ የድርጅቱን ስራ በሰዓቱ የማድረስ ፍላጎትና ዲሲፕሊን ከሌላት ምን ዋጋ አለው …

የሕብረተሰቡና የሃገር መሪዎች ምን ያህል ፖለቲካን ቢያውቁ፣ ደጋፊ ቢሰበስቡና በፖለቲካ ሳይንስ ቢራቀቁ፣ እውነተኞች፣ ሕዝብን አስቀዳሚና ሕብረተሰቡን አገልጋይ ለመሆን ራሳቸውን ካላቀረቡ ምን ዋጋ አለው …

በእውቀት፣ በብቃትና በሞያ ላይ ብቻ የምናተኩርበት ጊዜ አልፎ የስነ-ምግባር፣ የተግባቦትና የመልካም ዜግነት ጉዳይ እያሳሰበን የመጣበት ዘመን ነው፡፡ አንዱን ይዘን ሌላኛውን ችላ ስንል የሚያስከትለውን ቀውስም እጅ በእጅ እየተቀበልን ስለሆነ መፍትሄውን ፍለጋ በሚገባ ልናስብበት ይገባል፡፡

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

21 May, 18:36


ሰው ሁኖ መፈጠርና ሰው ሁኖ መኖር ሰው ሁኖ መፈጠር፦ ጥበብም፣ምርጫም፣ችሎታም ፍላጎትም አይደለም ከሰው ወገን ሰው ሁኜ ልፈጠር ብሎ የተመኘ የለም፡፡

🙏 ፈጣሪ ግን ሰው ሁኖ ይኖር ዘንድ ሰው አድርጎ ፈጠረው ፡፡ ሰው ሁኖ መኖር ግን ፦ እነዚህን ነገሮችን ያጠቃለለ ነው፡፡ ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ ከራስ አልፎ ለሌሎችም ማሰብ መቻል ነው፡፡

🙏 ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ ጊዜና ቦታን፤ ነገሮችንና ሁኔታዎችን አመቻችቶ ሰውን መግደልና መግፋት ፣ ማንገላታትና ማሸማቀቅ ሳይሆን ማዳንና መደገፍ ፣ ማበረታታትና ማረጋጋት ነው፡፡ ሰዎችን ገንዘብንና ስልጣንን ፣ ጉልበትንና ጊዜን ተጠቅመው መከራ የሚያሳዩ ሰዎች ሰው ሁነው ተፈጥረው ዳሩ ግን ሰው ሁነው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ናቸው፡፡

🙏 ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ መብላትና መጠጣት፣ መተኛትና መነሳት ብቻ አይደለም፡፡ ይኸማ በእስሳት የኑሮ ሥርዓትስ አለ አይደል እንዴ ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ መርጦ መብላት፣ መልበስ፣መናገርና ማግባት ማለት አይደለም፡፡

🙏 ለሰው ማሰብ አለመቻል እንስሳነትና ኅሊና ማጣት ነው፡፡ አንተ ያስፈለገኽና የሚያስፈልግኽ ለሌሎች የሚያስፈልጋቸው የሚመስልህ ከሆነ ራስህ ፈትሽ ወይ 'እምነት' ወይ 'እውቀት' ጎሎሐል፡፡

🙏 መብላት ያስፈልግኽ ይሆናል! ያስፈልግኻልም አንተ ሰው አይደለህ? ሌሎችስ ሰዎች አይደሉም? ናቸው፡፡ ታዲያ የማያስፈልግኽን እያገኘኽ ለምን የሚያስፈልጋቸውን ከለከልካቸው ራስህን መርምር ሰው ሁነህ ተፈጥረኽ ሰው ሁነህ አልኖርክም፡፡

🙏 ሰው አድርጎ መፍጠር የፈጣሪህ ድርሻ ሲሆን ሰው ሁኖ መኖር ያንተ ድርሻ ነው፡፡ ሰው ሁኖ የተፈጠረው ናቡከደነፆር ሰው ሁኖ መኖር ስላልቻለ ለ7 ዓመት እንስሳ ሁኖ ኑሯል ይኸውም ሰው ሁነው የተፈጠሩ ሰዎች ለሰው ማሰብና እንደ ሰው ማሰብ ካልቻሉ ምንም እንኳ ገፅታቸው ባይቀዬር ከሰውነት ተራ ወጥተው እንደ እንስሳ የሚኖሩና የሚያስቡ መሆናቸውን ለማጠየቅ ነው
https://t.me/+RS2MZ3b1qSCzdBy7

ልብ ወለድ (fiction) english to amharic

05 May, 04:23


ደሀ ሆነህ ከተወለድክ ምንም ያንተ ጥፋት የለበትም ደሀ እንደሆንክ ከሞትክ ጥፋተኛ እራስክ ነክ ::