በሀገሪቱ ከተሞች የሚስተዋለውን ያልተረጋጋና ፍትሀዊ ያልሆነ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ የሚያስቀር እዲሁም የአከራይ እና የተከራይን መብት በፍትሀዊነት የሚያስጠብቅ ነዉ የተባለለት "የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን" ማጽደቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በሶስት ድምጸ ታቅቦ አብላጫ ድምፅ በዛሬው ዕለት አፅድቋል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ ከ25 እስከ 30 በመቶ በላይ ለቤት ኪራይ ማዋል እንደማይጠበቅባቸው ገልፀው አንድ ተከራይ ለሁለት ዓመት ያክል ያለምንም ጭማሪ በተከራየው ቤት ውስጥ ተረጋግቶ የመኖር መብት የሚሰጠው አዋጅ ነዉ ብለዋል።