ታኦዳኮስ @theothokos Channel on Telegram

ታኦዳኮስ

@theothokos


ታኦዶኮስ (ወላዲተ እግዚአብሔር)

ታኦዶኮስ ይሏታል ትርጓሜውም "የአምላክ እናት" ማለት ነው ለዛም ነው ቅድስት ኤልሳቤጥ ☞ በሉቃ 1፥43 ላይ ''የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?'' ያለችው ስለዚህ ብቸኛዋ የአምላክ እናት ስለሆነች "አንዲት" እያልን እንጠራታለን ።

ታኦዳኮስ (Amharic)

ታኦዳኮስ: የዚህን መልእክት በተናገርን ቦታ በካል ስለተጠበቅንልዎት ወራት በተሽከርንህንስ ወያኔይንዚ!

ታኦዳኮስ አባሊኝ፣ ቸስተአብ እና ትራንስምህ ላይ ይህን ጽሑፍ ላይ ያሉትን የአምላክ እናት በአዲስ ቀናል ለመሳሪያ የብርሃንን ትቢያ እና ለእግዚአብሔር ስለሆነች ። ያለችው ስለዚህ ብቸኛዋ፣ የአምላክ እናት ስለሆነች "አንዲት" እያልን እንጠራታለን ።

ታኦዳኮስ

23 Nov, 13:53


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ኅዳር ፲፭ (15) ❖

+"+ ቅዱስ ሚናስ ምዕመን ሰማዕት +"+

=>ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ
ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን ቅዱስ
ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር
ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::

+ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም
ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ
ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ
ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::

+"ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ
እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው" ሲባልም
ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር
በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት:
በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ
ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ
የምንጠቀምበትን ስንክሳር 80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት
እነርሱ ናቸው::

+አባቶቻችንና እናቶቻችን ኢትዮዽያውያን ቅዱሳን ግን
አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም
ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):-

*በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች
ልጅ::
*በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ::
*በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ::
*ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት
የተወሰነ::
*በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት
ሰማዕት ነው::

+እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ
ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::
የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ
በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን
አደረገ::

+አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን
ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ
ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::

+በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን
አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና
በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ
ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ
አልቻሉም:: ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን
ከሠራዊቱ ጋር ላካት::

ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና
ፈውስን አጥታ ነበር::

+መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን
እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ
አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: ቅዱስ ሚናስ በሌሊት
ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን
አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች::

+ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ
እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም "መርዩጥ" ተባለ:: ጸበሉ
የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ ቤተ ክርስቲያን
ታንጾበት ቅዳሴ ቤ ተከብሯል::

+"+ ቅዱስ ቂርቆስ ሕጻን +"+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሏት ዐበይት ሰማዕታት አንዱ
ቅዱስ ቂርቆስ ነው:: በተለይ በዘመነ ሰማዕታት ተነስተው
እንደ ከዋክብት ካበሩትም አንዱ ነው:: ቅዱስ ወንጌል
እንዲህ ይላል:- "መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን
ያፈራል::" (ማቴ. 7:17)

+መልካም ዛፍ ቅድስት ኢየሉጣ መልካም ፍሬ ብጹዕ
ቂርቆስን አፍርታ ተገኝታለችና ክብር ይገባታል:: ቡርክተ
ማሕጸንም እንላታለን:: የተባረከ ማሕጸኗ የተባረከ ልጅን
ለ9 ወር ተሸክሟልና::

+በዚያ ክርስቲያን መሆን መከራ በነበረበት ዘመን ይህንን
ደግ ሕጻን እርሷን መስሎ: እርሷንም አህሎ እንዲገኝ
አስችላለችና:: አበው በትውፊት እንዳቆዩልን ከሆነ
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚህች ቀን እናታችን ቅድስት
ኢየለጡ ብጹዕ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስን ወልዳለች::

+ፈጣሪ ቢያቆየን የሰማዕትነት ዜናቸውን ጥር 15 ቀን
የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው እንዲለን እንማጸነዋለን::

=>አምላከ ሰማዕታት በምሕረቱ ይማረን:: በይቅርታው
ኃጢአታችን ይተውልን:: ከበረከተ ሰማዕታትም ይክፈለን::

=>ኅዳር 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
2.ልደተ ቅዱስ ቂርቆስ
3.ብጽዕት ኢየሉጣ
4.አባ ሚናስ ዳግማይ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ቅድስት እንባ መሪና
3.ቅድስት ክርስጢና

=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር:: በፍጹም ልባችሁ
በጾምም: በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም
የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ኢዩ. 2:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn

ታኦዳኮስ

15 Nov, 09:44


እመቤታችን ቅድስት ማርያም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር ከመሰደዷ አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ እንዘ ይጼዐን ዲበ ደመና ቀሊል፤ ጌታችን በፈጣን ደመና (በእመቤታችን ጀርባ) ተጭኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል›› ተብሎም በተናገረው መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩)

ጌታችን ኢየሱስ  በደብረ ቁስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው፤ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቁርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በቁስቋም ተራራ ስድስት ወራትን ያረፈች ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፮  የእነርሱን ስደትና ወደ ሀገራቸው እስራኤል መመለሳቸውን በማስታወስ ታከብራለች፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!

ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም (ትርጉም ፳፻፫ ዓ.ም)
              ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር

ታኦዳኮስ

15 Nov, 09:44


ደብረ ቁስቋም

ኅዳር ፮ ቀን የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የስደት እና የመከራ ዓመታት በኋላ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቁስቋም ላይ ያረፉችበት ዕለት ይከበራል፡፡

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብጽ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

በስደቱም ጣዖታተ ግብጽ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፤ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቡና አውጥቶ አሳደደ፡፡

ታኦዳኮስ

21 Oct, 06:23


"እግዚአብሔር አምላክ የለመኑትን አይነሳምና ሁላችሁም ስለ ሀገር ሰላም፣ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት፣ስለ ሕዝብ ደህንነትና አብሮነት ጸልዩ፤"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

ታኦዳኮስ

12 Oct, 15:58


የምንጸልየው እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለበት ለመንገር ሳይሆን እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲነግረን ነው።
        ቅዱስ አውግስጢኖስ

ታኦዳኮስ

09 Oct, 09:39


ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር -፲ ጥቅምት ፳፻፲ ፯ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ "#የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ነባራዊ ሁኔታ የሚረዳ፣ ከሥጋትም የሚታደግ ትውልድ እናፍራ "በሚለል ዐቢይ ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የደረሰባትን ፈተና ሁሉ እያለፈች ዛሬ ላይ የደረሰችው ከእግዚአብሔር ጥበቃ ጋር የዘመኑን ፍልስፍና ተረድተውና ዘመኑን ዋጅተው ሃይማኖትን ከሥነ ምግባር ጋር አዋሕደው ይዘው ጠላት ዲያብሎስ የሚዋጉ ጠንካራ አባቶች ስለነበሯት ነው፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካትና ለህልውናዋ የሚተጋ፣ ሁለንተናዊ ዕድገትን የተላበሰ ትውልድ ለማፍራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ መሥራትም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር መሆኑን መረዳት ይገባል። በማኅበረ ቅዱሳን ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተስተዋለውን የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፎ በማጠንከር እና የየማዕከላቱ ተወካዮች በተለያየ ችግር ውስጥ ሁነው ሳላ ስለ አገልግሎት ለመመካከር ብዙ ነገሮችን ተቋቁመው መምጣታቸው፣ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመናበብ ማገልገል ከማኅበረ ቅዱሳን የሚጠበቅ ተግባር ነው ። ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ ከአባቶቹ መመሪያ እየተቀበለ ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መጠናከርና ተደራሽነት እያደረገ ያለውን ጥረት ከአሁኑ በተጠናከረና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ማከናወን ይጠበቅበታል።"በማለት ታስነብባለች።

.#ዐውደ ስብከት ሥር” #ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊት ” በሚል ርእስ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ሰፊ ጽንሰ ሐሳብ ያለው ከመሆኑ የተነሣ በአጭር ዐረፍተ ነገር ለመግለጽ አስቸጋሪ እንደሆነ ያሳያል ። ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን አንዲት፣ ጋራ ተራራ፣ ድንበር ወሰን፣ ቋንቋ፣ ዘርና ቀለም የማይገድባት ዓለም ዐቀፋዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት፣ ሰላማዊት፣ እና ርትዕት ናት፡፡ “ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ” ነት ከዓለም ፈጣሪና መጋቢ ከልዑል እግዚአብሔር እና ካከበራቸው ቅዱሳን ጋር አሁን በረድኤት ኋላም በመንግሥተ ሰማያት በክብር መንግሥቱ አብሮ መኖር ማለት መሆኑን ያሳያል።

#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# "ዘመነ ጽጌ " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ #ደጀኔ ሺፈራው #የደንቨር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ይህን ወቅት(ዘመነ ጽጌን) ቤተ ክርስቲያን:-እመቤታችንን በምድር አንድም በአበባ፥ተወዳጅ ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስንም በአበባ አንድም በፍሬ እየመሰለች ዘመነ ስደታቸውን በየዓመቱ በማኅሌት፥ በቅዳሴ በመዝሙርና በትምህርት በልዩ ኹኔታ ታስበዋለች።የሚፈጸመውም አገልግሎት ለጊዜው ዘመነ ጽጌ ምነው ባላለቀ የሚያሰኝ፥ ለፍጻሜው ደግሞ የከርሞው መቼ በደረሰ የሚያስብል አገልግሎት እንዳላት ያስተምራሉ ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#ለመማከር ተሰበሰቡ "በሚል ዐቢይ ርእስ ብፁዓን አባቶችም ከሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚቀርበው ሪፖርት ምን ያህል በአደራ የተቀበሏቸውን የክርስቶስን ግልገሎች ጠቦቶችንና፣ በጎችን የማገልገል ጉዳይ ሆኖ ቀርቧል የሚለውን ነጥብ ይፈትሻሉ፡፡ ከዚህ ያፈነገጠ ሪፖርት፣ ዕቅድ፣ ውሳኔና አቋም ሁሉ ብፁዓን አባቶች የሚመሯትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንደማይመለከት በግልጽ ያሳያሉ፡፡ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሪፖርትም ለዚህ በአደራ የተሰጣቸውን ከባድ ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል ምላሽ የሚሰጥ መሆን ይገባዋል፡፡ በዚህ ጉባኤ ከሚገኙት የሪፖርት ምላሽ ተነስተው አባቶቻችን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን አጀንዳ ይቀርጻሉ፡፡

አገልጋዮች ለአገልግሎታቸው ምን ዓይነት ማነቆዎች አጋጠሟቸው? የትኞቹስ ቀኖናዊ መፍትሔ የሚፈልጉ ናቸው? የትኞቹ በጸሎት የሚፈቱ ናቸው? የትኞቹ በምክርና ተግሣጽ የሚፈቱ ናቸው? …ወዘተ ብሎ በዓይነትና በመልክ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ጭንቀት ክፍል_ ፩ "በሚል ርእስ መጋቤ ሐዲስ #አእምሮ ደምሴ #የኳታር ጸርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መ/ር ደግሞ ሥጋዊ ጭንቀት፦ከልብ የሚመነጭ በሕሊና የሚወጣና የሚወርድ ፣በረቂቁ አእምሯችን የሚመላለስ ፣ በሐሳብ መሥመር የሚንቀሳቀስ፣ በሕሊና ቦይ የሚፈስ፣ ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው። ጭንቀት፦ ክብደቱና ቅለቱ ይለያያል እንጂ በሁሉም ሰው ላይ የሚታይና የሚገለጽ ነው።ጭነቀትት ፦ መጠኑ ከሚገባው በላይ እየጨመረ ከሄደ ሰውነትን የሚያዛባ፣ አእምሮን የሚያቀውስ፣ ሕሊናን የሚያዘነጋ፣ ራስን እስከመጣል የሚያደርስ፣ ከቤተሰብ፣ ከትዳር፣ ከጓደኛ፣ ከጎረቤት፣ ከማኀበራዊ ኑሮ የሚለይ ፣ በብቸኝነት መኖርን እንዲመርጡ የሚያደርግ፣ ከፍ ሲልም ተስፋ እስከ መቁረጥ የሚያደርስ አደገኛ እንደሆነ በጹሑፋቸው ይጠቁማሉ። ስማችን፣ አለባበሳችን፣ ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ ነገር ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ውጭ በሆነ እሳቤ ብዙ ጉድለቶች እንዳሉብን ያሳያሉ ።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የምሥራቅ አፍሪካ ፈርጥ #ናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን " በሚል ርእስ በኬንያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረቱ ምክንያቶችና የአመሠራረት ሁኔታውን ፣የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ፣ በአብነት ትምህርት ፣ የደብሯን የሰበካ ጉባኤ የልማት እንቅስቃሴ ፤በሰንበት ትምህርት ቤት እና በየዘመናቱ የነበሩ ተግዳሮቶች ፣ወቅታዊጉዳዩች፣ የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጉት ጉዳዮችን ፣-በደብሩ የሚገኙት የሰበካ ጉባኤ አባላት ፣የሰንበት ት/ቤት አባላትና በማኀበረ ቅዱሳን የኬንያ ማእከል አባላት በፍጹም አንድነት ያለ ምንም ልዩነት አገልግሎት የሚሰጥበት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፣ የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መልካም አጋጣሚዎችን ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር "ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ሚና _ክፍል ፪ " በሚል ስብከተ ወንጌላችን ተደራሽ እንዲሆን ምን መደረግ እንዳለበት የተወሰኑ ነጥቦችን ያነሳል ።ተልዕኮ ተኮር የስብከት ዘዴን መከተል ፤የቋንቋ እንቅፋትን ማስወገድ፣ በቦታ ያልተገደደበ አገልግሎት መስጠት ይገባናል ።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# ትንሣኤ_፪ "በሚል ታስነብባለች ።
• # በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን “ወርኃ ጽጌን ክፍል -፩ ” በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ #ተስፋ ሚካኤል ታከለ ጋር የተደረገውን ምልልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል

ታኦዳኮስ

09 Oct, 09:39


ሐመር መጽሔት በጥቅምት ወር እትሟ!

✍️".....በዚህ ዓመት  ምን ያህል ገንዘብ ፈሰስ አደረገ ከሚለው ይልቅ በዚህ ዓመት ስንት ነፍስ በንስሓ አተረፍን? ስንት የሥላሴ ልጆችን በጥምቀት አፈራን  ወይም ቅድስት  ቤተ ክርስቲያን ስንት ኢአማንያንን በጥምቀት ወለደች??  ...."✍️ #ሐመር #መጽሔት ዐቢይ ጉዳይ ጥቅምት  ፳፻፲፯ ዓ.ም  )
                      ༺ ༻ 
#የኅትመት ዘመን ፦#ጥቅምት ፳፻፲፯ ዓ.ም ቁ.፲ 
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል #በየወሩ የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡

ታኦዳኮስ

10 Sep, 16:27


እንኳን ለአዲሱ ለዘመነ ማቴዎስ በሰላም በጤና አደረሰን!!

አዲሱ ዓመት ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የተሰጠን ሌላ አዲስ ዕድል ነው። አማኑኤል ከእኛ ጋር ለመሆን የእኛን ሥጋ ተዋሕዷል። አምላክነቱ ሳያሳስበው የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አድርጉዋል። በደሃ ቤት አድሯል፣ በበረት ተወልዷል፣ ከብርድ መከለያ ጨርቅን ፈልጓል፣ ፍጥረትን የሚመግብ እርሱ ከእናቱ የድንግልናዋን ወተት ለምኖ አልቅሷል፣ እንደ ሕፃናት በጉልበቱ ድኋል፣ ለእናቱ እየታዘዛት ጥቂት በጥቂት አድጓል። ከአደገም በኋላ ራሱን የሚሰውርበት ጎጆ ሳይኖረው በተራራ ተንከራቷል፣ ተርቧል፣ ከኃጢአተኞች በደረሰበት ተቃውሞ ተሰድቧል፣ ተገፍቷል። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ሆኗል።

ከእኛ ጋር ለመሆን ብቻ ሳይሆን በእኛ ውስጥ ለመኖር ደግሞ በዕለተ አርብ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ተሰጥቶናል። እኛስ ወደ እርሱ ሊያቀርበን ይህን ሁሉ ከሆነልን አምላክ ጋር ለመኖር ምን አደረግን? ለእርሱ ብለን ክፋትን አወገዝን? የተሸከምነውን ኃጢአት በንስሐ አራገፍን? ሥጋ ወደሙን ተቀበልን? 

ከእግዲህስ በኃጢአት ያረጀ ማንነታችንን እንተው። አዲሱን ዓመት  "ማለዳ ማለዳ አዲስ" ከሆነው ፈጣሪያችን ጋር ለመኖር ለራሳችን ብሩህ ተስፋ እንሰንቅ። እስኪ አምና ወድቀን ከተሰበርንበት የዘር፣ የጥላቻ ጉድጓድ ወጥተን ዘንድሮን ተዋድደን፣ ተፋቅረን በሰላም እንኑር። እስኪ ደግሞ ወደ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርበን ይህችን ዓመት በሰላም ጀምረን እንፈጽማት።

መልካም አዲስ ዓመት!!!

ታኦዳኮስ

08 Sep, 11:57


የዕለቱን ወንጌል እናንብብ!
ጳጕሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም
የሉቃስ ወንጌል ም 17 ቁ 11 - 37
መልካም ዕለተ ሰንበት !

#ethiopianorthodoxtewahedochurch #የዕለቱ_ወንጌል
#tewahedomediacenter#sunday

ታኦዳኮስ

08 Sep, 11:56


ኢየሱስ ክርስቶስ:
ለሚጠራው ስሙ ጣፋጭ ነው።
ለሚበላው የሕይወት እንጀራ ነው።
ለሚጠጣው የመድኃኒት ጽዋ ነው።

ታኦዳኮስ

07 Sep, 21:11


🕊እንኳን አደረሳችኹ ወርኃ ጳጒሜን በሰላም ያስፈጽመን የንስሐ ልብ ይሰጠን::

🕊"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

💥ስለ ንስሐ💥

ከቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንማራቸው 7 ነገሮች።

፩, 🌿ቅዱስ አብርሃምን መምሰል( ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘ)::

፪,  🌿ዓለምንና የዓለምን ነገሮች መታው።

፫, 🌿የንስሐ ሕይወት( ንስሐን በትጋት መፈጸም)።

፬, 🌿መታዘዝ (የሚታዘዘውን ሳያጓድል መስራትን)።

፭, 🌿ለሌሎች መኖርን።

፮, 🌿በሰው አለመፍረድን።

፯, 🌿ትሕትናን።
          

🌿ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!


1,💥ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡

2,💥ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡

3, 💥በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡

4,💥የበጎ ለውጥ እናት ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ ናቸው

4 ነገሮችን በደንብ ልብ እንበል!
    1, አላማ

    2 ,እምነት

    3,ጥረት

    4 ጥንቃቄ

❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️

💥ሃይማኖት
💥ጾም
💥ጸሎት
💥ስግደት
💥ምጽዋት
💥ፍቅር
💥ትህትና
💥ትዕግስት
💥የዋህነት

እነዚኽን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት
🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)


🔗https://t.me/zikirekdusn
▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

ታኦዳኮስ

07 Sep, 21:11


እንኳን አደረሳችሁ !

ጳጒሜን ፫፦

አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ዝክረ ስሞሙ ሕይወት፤
ወሩፋኤል መልአክ ፈዋሴ ቁስሉ ለጦቢት፤
ለሰራጵዮን ወጦብያ ወለሣራ ማኅቶት፤
መልከ ጼዴቅ ሊቀ ካህናት ንጉሠ ሳሌም ኅሪት፤
ዘርዓያዕቆብ ጻድቅ ንጉሠ አዜብ አግዓዚት፤
ዮሐንስ ወአኖሬዎስ ወቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት

1,398

subscribers

5,433

photos

79

videos