በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ለወታደራዊ ስልጠና በግዳጅ የሚወሰዱ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሰሜን ሸዋ ዞን ያያ ጉለሌ ወረዳ የፍታል ከተማ ነዋሪ ተማሪዎችን እና አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ ሰዎች በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ስልጠና መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
በ #አዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንዲት እናት ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የ17 አመት ልጃቸው ጌታቸው ተድላ ሂሪጎ በመንገድ ላይ ቆሎ እየሸጠ በነበረበት ወቅት በፖሊስ መታሰሩን ለማስለቀቅ 30,000 ብር መክፈል ባለመቻላቸው ልጃቸው ለውትድርና ስልጠና መወሰዱን አስረድተዋል።
በተመሣሣይ በጅማ ዞን ሰጠማ ወረዳ የግጦሽ ቦታ ለባለሀብቶች መሰጠቱን የተቃወሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ቤተሰቦቻቸው እስከ 70,000 ብር እንዲከፍሉ የተጠየቀባቸው ሲሆን መክፈል የማይችሉ ከሆነ ግን “ወታደራዊ ግዳጅ እንደሚጠብቃቸው” ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
https://t.me/merejadote