አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ @christian930 Channel on Telegram

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

@christian930


የዮሐንስ ራዕይ 22፥11-14

«ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። እንሆ፥ በቶሎ እመጣለኹ፥ለያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋራ አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ፊተኛውና ዃለኛው፥ መዠመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
➘➘➘
☞ @christian930
ግሩፕ፦ @AlphaOmega930
📩☞ @Kyrieelesion

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (Amharic)

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ የወንጌል መልክቻ ላይ በገንቢ አለብን። ይህ ታሪክ ማለታቸው፦ ዮሐንስ ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። ለሁሉም የሚሆነው፦ እኔ ነኝ። እንደዓለምም በዚህ ታሪኮች ፈቃድ እያደረግ፣ የሚሆነው ሀገር ፈቃድ ነው። ወደ ዚህ አገልግሎት እንኳ፣ አንደኛው የሚለውን ለማንኛውም ሰው፣ በተደብቅብ እና ለሁሉም የሚሰጠውን ለማድርግ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ ታሪክ እንደሆነ፦ መዠመሪያው፣ መጨረሻው፣ እና በመጠን አለበት። ለጉልልል፦ @AlphaOmega930. እና ማለታቸው፦ @christian930. እንዴት መጠቀም ይፈልጉ? አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ የዮሐንስ ትክክለኛ ትንሳኤ በማህበር ታሪክ።

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

22 Nov, 08:50


🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🟢.ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር ።

🟢.ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም

🟡.ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን

🔴.ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ
     
➻ሠላም እንዴትሰነበታችሁ እኛ ደና ነንን ልዑል እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን።ዛሬ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ አባት ገድላቸው ላይ የተገለጸውን እስኪ አንብበነው እንማርበት ከበረከታቸውም እናገኝ ዘንድ እንማጸናቸው።

➻እንደ ነብዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማህፀን የተመረጡ ናቸው ብሉይንና ሀዲስ ኪዳንን ያጠናቀቁት በ12 ዓመታቸው ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን አሰናብችኝ ብለው ጠይቀዋል ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደ ሚገኘው ደብረ ፀራቢ ወደ ሚባል ገዳም ገቡ።

➻ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስ የምንኩስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ የከበደ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢነግሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኩስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነግረዋቸው ከብዙ ፈተና በኋላ ጽናታቸውን አይተው አመንኩሰዋቸዋል።

 ➻በገዳሙ እንጨት እየለቀሙ ውኃ እየቀዱ የክርስቶስን ሕመሙንና ሞቱን እያሰቡ በፀሎት ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦ ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ከነገራቸው በኋላ በሽሬ አዲ አቦ በተባለ ስፍራ ሂደው ብዙ አስደናቂ ታምራትን ካደረጉ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡት 16 መነኮሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ።

    ➻ጻዲቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባህር በታምራታቸው ያቃጠሉ አባት ናቸው።
በንጉሡ በአፄ ዳዊት ዘመን ሰንበት አንዲት ናት እያሉ በሰንበት ስራ እንደሚሰሩ ሰምተው ሰንበት አንዲት ናት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው ከግብፅ የመጡት ጳጳሳትም ቀደም ብለው ከአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ አሁን ደግሞ ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ አፄ ዳዊት አከራከሯቸው ጳጳሱም ተረቱ ።

➻ክፉዎችም በአቡነ ፊልጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው በአቁማዳ ጠቅልለው ሀይቅ ውስጥ ጣሏቸው።በዚህ ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባህር በእሳት ተቃጥሎ እንዲታይ አደረጉ።በጽኑ ሥልጣን ህዝቡንም መንግሥቱንም ረገሟቸው።

🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

➻ይህ ውግዘት ለቀድሞዋ ኢትዮጵያ ለአሁኗ ደግሞ ኢትዮጵያና ኤርትራ (ባህረ ነጋሽ) ልጆች የተላለፈ እርግማን ነው።

 ➻ በዚህ ጊዜ ንጉሡም ህዝቡም ሁሉም ተረበሸ።
እንደ ምጽአት ቀን ያስፈራ ነበር። እርግማናቸው ከመባርቅት ጎልቶ በሚያስፈራ ነጎድጎድ ይሰማ ነበር።

 ➻.ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባህር ዳርቻ ላይ የተቃጠሉ ድንጋዮች ይገኛሉ።

➻.በወቅቱም የንጉሡ ሚስት በዋናተኞች አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አሰወጥታቸው እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው።ወዲያውም ከማህፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ይወጣል ብለው ትንቢት ተናግረዋል።በትንቢቱም መሰረት ንጉሡ አፄ ዘርዓያዕቆብ ተወለደ።

➻.በወቅቱ በተፈጠረ አለመግባባትና ክፉዎችም በባህር ውስጥ ስለጣሏቸው እርግማንን በህዝቡ ላይ አምጥተዋል።
ንጉሡ አፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያውም ታርቀዋል።
በዘመናቸውም ርሃብ ስለነበረ ፃዲቁን ከገዳማቸው አስጠርተው ምን ባደርግ ይሻለኛል ብለው አማክረዋቸዋል።
ጻዲቁም የጌታችንን መስቀል ያስመጡ ብለው መከሯቸው ንጉሥ አፄ ዳዊትም በአቡነ ፊልጶስ ምክር መሠረት ከእየሩሳሌም መስከረም 10 ቀን አስመጥተውታል።

➻.አቡነ ፊልጶስ በደብረ ቢዘን ገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኑረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብለዋል።
ላንተ የተሰጠህ ቃል ኪዳን ለማንም አልተሰጠውም
➻.ክብርህ ገናና ነው።

➻.በቃል ኪዳንህ ለተማፀነ የማልፈጽምለት የለም።
➻.ገዳምህን ዘወትር በበረከት ደመና ከብቤ አኖረዋለው ።

➻.ምሕረትን ፈልጎ ደጅህን ለረገጠ አንተን ባከበርኩበት ልክ አከብረዋለሁ።
➻.አስተዋይ ልቦናን እሰጠዋለው።

➻.የኢትዮጵያን ምስጢር እገልጥለታለው ብሎ ጌታ ቃል ገብቶላቸዋል ።

➻.ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር አርፈዋል !!!
           
➻.እንግዲህ ዛሬም እየሆነ ያለውን ማየት ነው እየተፈጸመ ነው እንሰደዳለን :ሀገር እንጠላለን ከውስጥ ይልቅ ውጭነት ይማርከናል ።

➻.እንደ ሀገር እንደ ህዝብ ታመናል ብሎ የሚመረምር ትውልድ እንኳ ጠፍቷል።

 ➻. የእውነተኛ አባቶቻችን ውግዘት ምን ያህል ከባድና ለቅጣት እንደሚዳርግ ከዚህ መረዳት ይቻላል።ዛሬም በዚህ ዘመን የተላለፈውን የአባታችን ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘትን የማናከብር ከሆነ ከዚህ የከፋ መከራ ውስጥ እንገባለን ማለት ነው።ያው እንደምናየው ህዝቡም እያከበረው አይደለም ያው የሚሆነውን ማየት ነው እንግዲህ።
➻. እግዚአብሔር ይመስገንና እኛ ግን እውነትን ሰምተናል በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እውነት እስከመጨረሻው ያጽናን!
➻.የጻዲቁ አቡነ ፊልጶስ በረከታቸው ይደርብን።

➻.በአንድ ወንድም ምክንያት ገድላቸውን ሠማሁና ለሁሉም አስተማሪ ስለሆነ ነው ያጋራሁአችሁ


.ሠላመ እግዚአብሔር ቅን፣ የዋህ፣ ትሁት ከሆነ ኢትዮጵያን ከልቡ ከሚወዳት ጋር ይሁን።
13/03/2017 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

21 Nov, 05:31


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አራት (4)

በድምፅ ንባብ (በትረካ)

(📌 ክፍል 1ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማዳመጥ 👈)

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማነው?

🌿 ሕይወቱና ተጋድሎው
🌻 ቃልኪዳኑና
🌹 ሰማዕትነቱ
...

📌 ቁጥር 1) ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወቱንና ከመድኃኔዓለም የተቀበለውን ልዩ ቃልኪዳን በፅሑፍ ያንብቡ👇

🫴 https://t.me/Ewnet1Nat/14510

PDF ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ (በ1988 ዓ.ም የታተመ)👇

https://t.me/kidusan_page/50

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

20 Nov, 16:09


🟢🟡🔴
ኅዳር 12 | በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ፣ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ #ቅዱስ_ሚካኤል የተሾመበት የበዓሉ መታሰቢያ ነው።


ዳግመኛ በዚህች ዕለት #ቅዱስ_ሚካኤል #ኢያሱ_ነቢይን የተራዳበት መታሰቢያ ነው።

ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው።

ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ።

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ።

ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።

ስለ ልዕልናውና አማላጅነቱ በየወሩ በ፲፪ ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት።

እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናል።


#ቅዱሳን_ዱራታኦስ_እና_ቴዎብስታ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ።


በዚችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ #የጻድቁ_በእደ_ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እኚህም የመጀመርያውን #መልክአ_ማርያም የደረሱ ናቸው።
 ◦🍀

+ የመጥምቁ
#ቅዱስ_ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

14 Nov, 16:25


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አምስት (5)

(📌 ክፍል 1ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማንበብ 👈)

📌 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሰላማ ማን ናቸው?

🍀 ኅዳር 26 - የልደታቸው በዓል
🌼 ታኅሣሥ 18 - ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሊሆኑ
                            የተሾሙበት በዓል
🌺 ሐምሌ 26 - የዕረፍታቸው በዓል

እንደ ተሰጣቸው ክብር ያላከበርናቸው፣ የዘነጋናቸው ባለውለታና ብርሃናችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፦
🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ቃልኪዳን
🌺 ህያው ትሩፋት

ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ያንብቡ👇

📌 https://telegra.ph/ብፁዕ-ወቅዱስ-አቡነ-ሰላማ-ከሳቴ-ብርሃን-11-14-2

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

14 Nov, 15:32


🌿 ዋኖቻችንን እንወቅ❗️
ክፍል 5 (በፅሑፍ)

👇 ዛሬ ይለቀቃል!👇

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

13 Nov, 08:06


ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን እና ካህናት፣ ጳጳሳት ለ29 ዓመታት  ያህል ያልተፈታውን ውግዘት ያላዳመጣችሁት አዳምጡት።

📌 ራሳቸው ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ ከምዕመናን ስለውግዘቱ ምንነትና ምክንያት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በወቅቱ የሰጡት መልስ ነው።

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

13 Nov, 08:02


📌 #ክፉውን_ከመካከላችሁ_አውጡት ❗️
📌
#ያልተፈታው_ውግዘት_ይከበር ❗️👇👇👇

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

13 Nov, 03:20


🟢የአብርሃሙ ሥላሴ እናቱን ያዳምጣል አንዲት ነጥብ ከእናቱ እንድትወድቅበት አይፈልግም።

🟢
ፍላጎቷ የሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ፈጻሚ ስለሆነ ይህን ልብ ልትሉ ይገባል።አታማልድም እያልህ ምትጨማለቅ የዲያብሎስ ግልገል ጠፊ ትውልድ ሁሉ ዋጋህን ታገኛለህ እዚህ ላይ ነው የምነግርህ።በድንግል ላይ አላግጠህ በድንግል ላይ አሹፈህ ክብሯውን ሁሉ ቀንሰህ ያፌዝህ ሁሉ ትውልድ ሁሉ በዚህም ሰዓት አረጋግጥልህአለሁ ዘር ማንዘርህ ሁሉ አያልፍም ትጠረጋለህ።
🟡
እኔ ባሪያው የእግዚአብሔር ባሪያ ለአንዳችሁም አላልፋችሁም። ስትጠናቀቅ ነው ሕሊናዬ ሚያርፈው በእናቴ በድንግል ድርድር አላቅም። ወዮልህ እኔ ፊት አትድረስ ያኔ የሞትህን ብዜት ነው እንጅ ምታየው እሳት እንደሚበላህ ነው እንጅ ምታየው ሌላ ከእኔ ምሕረት የምትባል ለሰንከንድም አትታለምም።
🟡
በእናቴ የመጣ ርህራሄ የለኝም በአይኔ የመጣ ነው።በእምነቴ የመጣ በአይኔ የመጣ ነው።ይህንን እንድናገር አልፈልግም ነበር ግን ሰዓቱ ነውና ግድ መናገር ያስፈልጋል።
እግዚአብሔር እንደ ቃሉ በአደረሰኝ ስፍራ ላይ ስደርስ ወይም አገልግለኝ ባለኝ ቦታ ላይ ሳገለግለው ይህ መመሪያ ነው የማይናወጽ አቋሜ ነው።ዛሬም እንደ አቅሜ በትንሽነቴ አገለግላለሁ እግዚአብሔርን ።
🔴
እግዚአብሔር ደግሞ ነገ እዚህ ጋ ስፍራ አገልግል ባለኝ ስፍራ ስሆን ግን የእምነቴ ጠላት የሆናችሁ በእናንተ በተለይ እናንተ መናፍቃን እናንተ ካቶሊካውያን በተለይ በክርስትና ስም ያላገጣችሁ ክፉ ጠላቶች በቤቱም በልጽጋችሁ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ውስጥም ሁናችሁ ይህንን እርኩሰት ያነገሣችሁ ሁሉ ውዮላችሁ።
🔴
አሁንም ደግሜ ነው ምነግርህ ወዮልህ ለዘርህ ሁሉ ለራስማ ተወው ለዘር ማንዘርህ የሚተርፈውን እሳት ትቀበላታለህ።ደግሜ ነው ዛሬ ምነግርህ ምንም ርህራሄ እንደለለ እስከ ዛሬም እስከዚች ሰዓት ድረስ እግዚአብሔር በትዕግስት እጁን የያዘው መጪውን እሳት ክፋቱን ጥንካሬውን ብርታቱን ስለሚያውቀው የሚያደርጋትን ስለሚያቅ ነው።እኛ ባሮች እጅ ደግሞ የእግዚአብሔር ኃይል ገባ ማለት ወዮልህ ወዮልህ መጥፊያህ...

4/03/2017 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

10 Nov, 13:24


አዋጁ ከታወጀበት ከሚያዝያ 7/2007ዓ.ም ጀምሮ ራሱን ለመትከል እንደ ልዑል ፍርድ ዓለምን በየደረጃው እያበጠራት ይገኛል፡፡ለዚህ ምስክሩ አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበት ሁኔታ ነው፡፡ ቀድማም የምትወጣውና በአዋጁ የተገለፀው የሽግግሩም ሆነ ቋሚው ሕግጋተ ሥላሴ በመጀመሪያ የሚፀናው እዚሁ ኢትዮጵያ አገራችን ላይ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕግጋተ ሥላሴ በአገራችን ዙሪያ ባሉ አገሮችም ጭምር የሚፀናና ለመላው ዓለም እንደ ፀሐይ የሚያበራ ሆኖ ይቆማል፡፡ ይህንን ለማየት በውስጡም ለመኖርና እድሜን ለመቀዳጀት የሚታደለው ማን እንደሆነ የሚያውቀው ማንም አይደለም ልዑልና ድንግል በግንባሩ ያተሙበት ብቻ ነው፡፡ ለዛሬው ከሃዲ ትውልድ ይህ ተረት ነው፡፡ለዚህ ነው አዋጁም የማይገለጠው ፤ ወገኖቼ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እምነት አሻግራችሁ ለማየት የታደላችሁ ወንድም እህቶቼ እናንተ ተስፋችሁ የፀና የማይናወፅ ነው፡፡ ራሳችሁን ከዚህ ዓለም ጉድፍ ስለጠበቃችሁ ሕይወታችሁ ሥጋዊ ኑሮአችሁ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሆነ እኔም የምመሰክረው ነውና ፅኑ እንጂ አትናወጡ፡፡
የሚጠፋው ጠፍቶ ፤ የሚሻገረው ደግሞ የተፈቀደለት ብቻ ይሆናል፡፡የመከራው ክብደት ተስፋን ያጨልማል ሥጋ ነንና እንደክማለን እንወድቃለን ፤ ነገር ግን የምንታመንበት አምላክ የምንወዳት እናታችን በቃላቸው የታመኑ ስለሆኑ ብንወድቅም ያነሱናል፤ ብንቆስል ብንጎዳ ይጠግኑናል፡፡
📌ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቁጥር-8 ከገጽ 3-4

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

05 Nov, 17:02


🟢🟡🔴
ጥቅምት 27 | ቤተ ክርስቲያን
#የመድኃኔዓለምን የስቅለት በዓል ታከብራለች። ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ሥጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው። ነገር ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታልናለች፡፡
 
🍀 #አባ_መብዓ_ጽዮን
የጻድቁ መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከመድኃኔዓለም የስቅለት በዓል ጋር ይከበራል። ጥቅምት ፳፯ ቀን ለወዳጆቹ እውነተኛውን ዋጋ የሚከፍል መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለጻድቁ አባ መብዓ ጽዮን ብዙ ቃል ኪዳን የገባበት ቀን ነው።


አቡነ መብዓ ጽዮን በይበልጥ የሚታወቁት ሁልጊዜ ወር በገባ በሃያ ሰባት መድኃኔዓለምን አብልጠው በመዘከራቸው ነው፡፡

በዚህም ቀን ‹‹እንደ አንተም በየወሩ በሃያ ሰባት የሞቴ መታሰቢያ ለሚያደርግ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣለታለሁ›› የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ከጌታችን ተቀብለውበታል፡፡ ይኸውም የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ሲነግራቸው ነው፡፡

በኋላ አባታችን እንዲህ መከሩን፦ ‹‹ክርስቲያኖች ሁሉ የፈጣሪያችንን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የመታሰቢያ በዓሉን እናድርግ፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ ግን የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ በሞቱም ጊዜ ሥቃይን አያያትም፡፡

🍀 #አባ_ጽጌ_ድንግል ዕረፍታቸው ነው።
በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ሊቅ ሲኾን፤ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት (ያላመነና ያልተጠመቀ) ነበር።

በኋላ ግን አቡነ ዜና ማርቆስ አሳምነውት ማኅሌተ ጽጌን የደረሰ ቅዱስ ኢትዮጵያዊ አባት ነው።

🍀 ግብፃዊው ጻድቅ #አቡነ_ሐራ_ድንግል ዕረፍታቸው ነው።

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ

01 Nov, 18:51


📌ማስታወሻ፦

👑 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ቀዳማይ የልዑል ባሮች ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከተላለፈው "ፍርድ አዘል መግለጫ" ከ46ኛው - 51ኛው ደቂቃ ተቀንጭቦ የተወሰደ!