ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ወደሀገር ውስጥ እያስገባቸው ከሚገኙት 330 ገልባጭና የጭነት ከባድ ተሸከርካሪዎች መካከል 36 ገልባጭ ተሸከርካሪዎች መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የሳይት ቦታ ወደሚገኝበት ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎ የሁለተኛ ዙር ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ሂደት ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. 30 ተጨማሪ ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎች ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ከባድ ተሽከርካሪዎች የሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሆነውን ማዕድን ከማምረቻ ጣቢያው - ማከማቻ ቦታ የሚያጓጉዙ እጅግ ግዙፍና ዘመናዊ የሆኑ ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎች ሲሆኑ፣ የግብዓት ምርቱ የሚመረተው በፕሮጀክቱ አካባቢ በሚገኘው ጀማ ወንዝ ሸለቆ ውስጥ በመሆኑ የቦታው መልክዓ-ምድር አስቸጋሪ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለሥራው የሚመጥንና ደረጃውን የጠበቀ ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎችን ለማሰማራት ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለበት ትልቅ ሥራ ነው፡፡
በሳይት ላይ የሚሰማሩትን ከባድ ተሸከርካሪዎች ታሳቢ በማድረግ በለሚ ከተማና አጎራባች ወረዳዎች ከሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ 61 አሽከርካሪዎች በቋሚነት የተቀጠሩ ሲሆን በዚህም ለአካበቢው ማህበረሰብ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ጋር ተያይዞ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡
join👉https://t.me/Ethiomine2