የደሀውን ለቅሶ ~ የምስኪኑን ጩኸት
አላሰማም ብሎህ ~ የቢላዎች ፉጨት
ነብስህ ተከልላ ~ በስጋ አለም ስላቅ
ከታናሽ ላይ ቆርጠህ ~ አጉርሰህ ለታላቅ
ለማወራረጃ ~ ብርጭቆ ብትይዝም
ቀዝቀዝ ያለ ሁሉ ~ አያቀዘቅዝም
አያጠፋልህም
የነብስህን እሳት ~ ከስጋህ ነጥሎ
አያበርድልህም
የውጪው ቀዝቃዛ ~ የውስጥን ቃጠሎ
እውነቱ እንደዚህ ነው ~ እመነኝ ግዴለም
ከእርዛት ነጥቆ ~ በሚደርብ አለም
የሚያልበው ሁሉ ~ የሞቀው አይደለም
#ዛሬ
በንብረትህ ብዛት~ፍቃድ ስር ብትወድቅም
በጉብዝናህ ወራት ~ ለማሰብ ባትፈቅድም
ልክን ማሳወቅ ነው ~ የመለኪያ ጥቅም
#ከሰማህ #ልንገርህ
ግፍ እንደ ፍግ ሆኖህ
ከእድሜህ በላይ በቅለህ~ከሀገሬው ብትበልጥም
ደሀ ባፈሰሰው
የእንባ በረዶ ~ ውስኪ አይጨለጥም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•