ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟 @tunbi_love_media Channel on Telegram

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

@tunbi_love_media


"፤ እግዚአብሔርም፦ አሞጽ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ ቱንቢ ነው አልሁ። ጌታም፦ እነሆ፥ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱንቢ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ደግሞ አላልፋቸውም፤" (ትንቢተ አሞጽ 7: 8)
______________
ለማንኛውም ሀሳብና አስተያነት ✍️
📞 +251 932000657 ወይም
በቴሌግራም @byitref ያገኙናል::

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟 (Amharic)

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟 በኢንተርኑት እና መረጃዎቹ መሰረት የእርስዎን ዝግጅት ድምጻችን እና ተጠቃሚነት ዉስጥ መዳረስ ያለው ነው። አሞጽ 7:8 'ወንድም ሲነጋገሩ ከአርጎል ሲያነሣሽ ወደ አፎስ ላለለት አምላኩ ላእምላዎቹ ተይዘብቦልናል።' ትንቢተ አሞጽ እውነተኛ መጽሐፍ በሚቀጥሉበት ሁኔታ ለሁለት የተጠቀሱ ገጽ፦ ፊልሞቻችን እያደረጉ እና ለማንኛውም ወቅታዊ መረጃ እንዲሆኑ የቴሌግራም ቦታ ነኝ። ከሰብሣችን እና ከታላቅ ቀጥሎች በኋላ፣ ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟 የቴሌግራም ቦታ ነው። ምንም አልተሰማንም? እርስዎ ስለሚደረግ ከሌሎች ቋንቋዎችን ብቻ እንደሚከብድ እንደማያደርጉ ይመስላል።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

05 May, 04:08


"ጥቂት የደም ጠብታ መላውን ዓለም ዐደሰው። በወተት ውስጥ ኾኖ ወተትን እንደሚያጣብቀው ፈሳሽ ደሙ የሰውን ዘር አንድ ላይ አያያዘው።" … ኢየሱስ ነው!
          🎁 እንኳን ለትሳኤ በዓል አደረሰን 🎉
___
TUNBI_LOVE_MEDIA 💟

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

19 Feb, 07:49


"እርሱ አፅናኝ የሆነው"

የክርስትና ህይወት ያለ መንፈስ ቅዱስ መሪነት አይታሰብም።

እኛ ወዴት እንደምንሄድ እንዴት መሄድ እንዳለብን አናውቅም።

ነገር ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል።

የመንፍስ ቅዱስን መራነት ሆንብለን እንለማመድ።
እናማክረው፤እንጠይቀው፤እናውራው።ድምፁን ያሰማናል።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

16 Feb, 10:23


ያለ መንፈስ ቅዱስ በድን ነኝ።

ይህን ፀሎት የዘወትር ፀሎት በማድረግ በእርሱ ላይ ያለንን ፍፁም መደገፍ ለመንፈስ ቅዱስ እንግለጥ።

እኔ አሁን አልኖርም፤መንፈስ ቅዱስ አንተ በእኔ በሙላት ኑርብኝ ብለን በየእለቱ ራሳችንን እናቅርብ።የመንፈስ ቅዱስ ህይወት እንለማመዳለን።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

11 Feb, 10:36


“ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት #እየጠበቃችሁና #እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤”
— 2ኛ ጴጥሮስ 3፥11-12

የጌታን ቀን ማስቸኮል እንችላለን።

እንዴት ?

ስለኢየሱስ ሰዎች እንዲሰሙ በተለይም ያልሰሙ እንዲሰሙ በማድረግ

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

19 Jan, 19:52


https://youtu.be/XhK_qeuPi4Q?si=uNoZAHtcjrXcMKSJ
____
🔹 please Subscribe the Channel 👆

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

06 Jan, 20:12


አትፍሩ "፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
(የሉቃስ ወንጌል 2: 11)
🎁 መልካም በዓል 🎁
___

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

20 Dec, 22:03


እየወደድሁህ መጣሁ Eyewededhuh Metahu
https://youtube.com/watch?v=2syRUAAB6vY&si=QE2nCFZvJOAYc8Fl

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

20 Dec, 22:02


ይችላል Yichlal
https://youtube.com/watch?v=OnigaE3RO6o&si=rdYOoAyh9p6x63LB

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

07 Nov, 13:06


መንፈስ ቅዱስ፡ የህይወት መንፈስ

“ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።”
— ዘፍጥረት 1፥2

ምንም ያልነበረው፣ቅርፅ አልባ፣ጭለማ የሸፈነው ባዶ አለም ከቃሉ የተነሳ ሙሉ እና ብርሀናማ ወደ መሆን የመጣው መንፈስ ቅዱስ ስለሰፈፈበት ነው።

ዶሮ በእንቁላሎቿ ላይ በምትብበት ጊዜ ነጭ እና ቢጫ ፈሳሽ የነበሩት እንቁላሎች ህይወት ያለው ዶሮ ይሆናሉ።ካለመኖር ወደ መኖር ይመጣሉ።

📌መንፈሳዊ ህይወት ያለ መንፈስ ቅዱስ መገኘት አይታሰብም።

📍በእንቁላልና በዶሮ መካከል ያለውን ልዩነት ያህል በመንፈሳዊ ህይወትና በፍጥረታዊ ህይወት መካከል ልዩነት አለ።

📍በቅርፅ አልባው ምድር እና በቃል በተፈጠረው ምድር መካከል ያለውን ልዩነት የሚያህል ልዩነት በመንፈሳዊ ሰውና በፍጥረታዊ ሰው መካከል አለ።


📌መንፈስ ቅዱስ ይክበበን፣ ይሸፍነን፣ ክርስቶስን በኛ ይግለጥ።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

06 Nov, 14:04


6
መንፈስ ቅዱስ፡ #የነፍሳት መዳን

“ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ #በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥12

😊መንፈስ ቅዱስ ነፍሳትን ለማዳን እኛን ለመጠቀም ከሰማይ ወርዷል።

መንፈስ የሌለበት የወንጌል ስርጭት፡
👉የሰውን ልብ አይወቅስም
👉የመንፈሳዊ ጭለማን አይገፍም
👉ከተለመደ ንግግር የዘለለ ተፅዕኖ የለውም።

📌በፀሎት የተደገፈ እና የተመራ ወንጌል ስርጭት መላእክት እንኳ ሊያዩት የሚጓጉት አገልግሎት ነው።

📍ከመለኮት ጋር ለመስራት በመንፈስ የሆነ የወንጌል ስራን እንናፍቅ እንራብ።

የመንፈስ ቅዱስ መገኘት መገለጫው የነፍሳት መዳን እና ወደ ህብረት መጨመር ነው።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

05 Nov, 06:14


5
መንፈስ ቅዱስ፡ የእግዚአብሔር መንፈስ

“ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜም ፍልስጥኤማውያን እልል እያሉ ተገናኙት። #የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት ክንዱም የታሰረበት ገመድ በእሳት እንደ ተበላ እንደ ተልባ እግር ፈትል ሆነ፥ ማሰሪያዎቹም ከእጁ ወደቁ።”
— መሳፍንት 15፥14

📍እንደ ሰው መኖር ካልፈለግን መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል።

📍በመፅሀፍ ቅዱስ ታላላቅ ታሪክ ያላቸው ሰዎች የሆኑትን የሆኑት ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ ነው።

📍ያለመንፈስ ቅዱስ እግሩም እጁም እንደታሰረበት ሰው አቅም አልባ ጠላት እልል የሚልብን በብዙ ድካም የተከበብን ነን።

📍የድላችን ሰንደቅ የድላችን ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።

📌መንፈስ ቅዱስ ሆይ ናልን ውረሰን!!!

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

04 Nov, 05:31


4
መንፈስ ቅዱስ፡ የቅድስና መንፈስ

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ #እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4

📍መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደ አብ እና ወልድ በማንነቱ ቅዱስ ነው፤እንደሚባላ እሳት ነው።

📍ቅድስና ስሙ ነው።ቅድስና ማንነቱ ነው።

📍መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ያለው ሊቀድስህ ነው።በራስህ በፍፁም ልትደርስበት የማትችለውን ህይወት በአንተ ሊገልጥ ከሰማይ ወርዷል።

📌ቅድስና የመንፈስ ቅዱስ መገኘት ማረጋገጫ ነው።

ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።


¹¹ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

01 Nov, 06:09


3
መንፈስ ቅዱስ

ዮሐንስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

¹⁴ #እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።

📍መንፈስ ቅዱስ የስላሴ አንድ አካል ነው።

ኢየሱስ ከአብ ወጥቶ በስጋ መጥቶ ስለ ሀጥያታችን በመስቀል ሞተ።

📍መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ወጥቶ በእኛ ውስጥ አደረ።

📍በእኛ ውስጥ አድሮ ከክርስቶስ ይናገራል፤ ክርስቶስንም ያከብራል።

"መንፈስ ቅዱስ ሆይ አንተ አምላኬ ነህ።ራሴን ለአንተ ሙሉ በሙሉ አስገዛለው።ክርስቶስን በህይወቴ ግለጠው፤ክርስቶስን አክብረው።"

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

31 Oct, 05:22


2
መንፈስ ቅዱስ

“ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።”
— ኤፌሶን 4፥30

“And grieve not #the holy Spirit of God, whereby ye are sealed unto the day of redemption.”
— Ephesians 4:30 (KJV)

📍መንፈስ ቅዱስ የስላሴ 3ኛ አካል ነው።
ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚለው አገላለጥ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር መሆኑን ያስረዳናል።

📍መንፈስ ቅዱስ በቅድስና እንድንኖር፣ ክርስቶስን እንድንመስል እና መንፈሳዊ እንድንሆን በእኛ ይሰራል።

📍ደካማነታችንን አምነን እንዲረዳን ከፈቀድን ራሳችንን በፊቱ ካዋረድን ያግዘናል።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

30 Oct, 04:55


1
#መንፈስ ቅዱስ

“እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።”
— ዮሐንስ 16፥7

መንፈስ ቅዱስ አካል/ስብእና ያለው አምላክ ነው።

እርሱ የተባለው የስላሴ አንድ አካል መንፈስ ቅዱስ ነው።

📍ስላንተ ሁሉን ያውቃል።

📍እጅግ በጣም ይወድሀል።

📍በህይወትህ ሊፈፅም የሚፈልገው ፈቃድ አለው።

ገላትያ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።
¹⁷ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።
¹⁸ በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።

📍ታዘዘው።

📍ከልብህ ፈልገው።

📍ተከተለው።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

21 Oct, 07:31


#በደም ያጌጠ ልብሴ
አንተ ነህ እየሱሴ🎼🎼🎼🎼

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

26 Sep, 11:16


📌“ስለዚህ ሕፃን ጸለይሁ፤”

— 1ኛ ሳሙኤል 1፥27

ሀና ህፃን ያለችው ሳሙኤል አድጎ ነቢይ እና ፈራጅ እንደሚሆን፥ የመሳፍንትን ዘመን ቀይሮ የነገስታቱን ዘመን እንደሚያስጀምር አስባ አልነበረም።

ግን

📍ልጅ ስጠኝና ልስጥህ ብላ ፀለየች።

📍የፀሎቷ መልስ እሷ ጋ የሚቀር ሳይሆን እግዚአብሄር ጋ የሚመለስ ነበር።

የምትሰጠውን እንዲሰጣት አጥብቃ ለመነችው።

📍ናዝራዊ ልጅ ወለደችለት።

📍ነገ ውስጥ የሚገባ የእግዚአብሄርን ልብ የሚያሳርፍ ፀሎት በአንደበታችን ይሙላን።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

16 Sep, 10:43


📌አለቅህም

“እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው።”
— ዘፍጥረት 32፥26

📍ሰዐት አልቆአል ልጄ ፀሎት አቁም በእግዚአብሔር የተባለ ብቸኛ ሰው ያዕቆብ ነው።

እግዚአብሔርን ታገለ።

📍ለመፀለይ ከመፀለይ ያለፈ ፀሎት ታሪክን ይቀይራል።

📍ብቻውን ፀሎት ጀመረ(ያዕቆብ)፤ፀሎቱ ሲያልቅ ግን ሀገር ሆኖ ነበር።(እስራኤል)

📍በላባ ቤት የአመታት ትግል፣ በሀብት ብዛት፣ በሚስቶች እና በልጆች ብዛት ያልተመለሰ ጥያቄ በአንድ ለሊት መነካት ተመለሰ።

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

15 Sep, 15:35


#ብዙ_ተምረናል! … 🌼

🔹 የምህረት አምላክ እግዚአብሔር የትላንት ዓመታችንን በምህረቱ አሳልፎ ዛሬ በእርሱ ምህረት በሕይወት እንድንቆይ ስለረዳን በጌታችንና በመድሀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ውዳሴም ይሁንለት፡፡

🔹 ባሳለፍነው ዓመታት ጥሩም በጥፎውንም በእግዚአብሔር ምህረት አልፈናል፡፡ በግል ፣ በቤተሰብ ፣ በቤተ-ክርስቲያን እንዲሁም በሀገር ደረጃ ጌታችን ምህረት እርጎልናል፡፡ በፀሎታችን ብዛት ፣ የቃል እውቀታችን ፣ በእዕምሮአችን ብስለት ፣ የዘራችን ቀለም ወይንም የሀገራችን ሁኔታ ሳይሆን ያራቀ የእግዚአብሔር ምህረት አመቱን አሳልፎናል፡፡

🔹 በመጪውም ዓመት ብዙ እንደተማረ ሰው የምህረት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለብዙዎች በኑሮአችን የምንመሰክርበት በጌታ ለሆኑ ወንድሞቻችን ምህረት የምናደርግበት ዓመት ይሁንል፡፡

‹‹ ብዙ የተማረ ብዙ ይምራል ››
_
🌻 መልካም ዓዲስ ዓመት 🌼

ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

15 Sep, 09:24


📌እረኛዬ

ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።
⁴ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤

📍እረኛ የሌላቸው በጎች፡
ይቅበዘበዛሉ
ይባዝናሉ
ይጠፋሉ
ተኩላ ሊነጥቃቸው ይችላል
የሚበሉትን ሳር እያዩ ገደል ሊገቡ ይችላሉ።

📍ከእ/ር ድምፅ የራቀ ህይወት፣ምሪት የሌለበት ህይወት እረኛ እንደሌላቸው በጎች መኖር ነው።

📍እ/ር በእረኝነቱ በድምፁ ከፊታችን ይቅደም።

📍ከማለዳ እስከ ምሽት ከፊት ፊታችን ኢየሱስ አይታጣ፤ይምራን።