✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 @betetewahdoethio Channel on Telegram

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

@betetewahdoethio


" አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ "/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/ "ዘወትር ፍጹም ሰላምን እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንማልዳለን!!!"
ይኼ ቻናል የተመሰረተው ጥቅምት ፳፱ (29/2015 ዓ.ም).ለማንኛውም @Kokiyemom21 አስተያየተዎ ብቻ ይላኩ።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢እ (Amharic)

የዓለም ተማሪ ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎 የመልክቱን ይሸፍና ድንግል ለእርሱ እና ለዓለም በምንም በራሱ እንቅስቃሴ ከፍታለን። እናመሰግናለን ምክንያቱም እርሱ የሆነችው ልጅ አላዋቅን እና ብለዋቅን መረጥለት እንዳለው ሁሉም እጅግ እንከላከል። በባሊኦይ አምላክ ዘወትር ፍጹም ሰላምን እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንማልዳለን! ይኼ ቻናል የተመሰረተው ጥቅምት ፳፱ (29/2015 ዓ.ም). ማህበረሰብና @Kokiyemom21 አስተያየተዎ ብቻ ይላኩ።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Jan, 19:05


ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ለማነው?

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Jan, 18:14


አምስቱ አዕማደ ሚስጥራት ማን ማን ናቸው?

ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?

የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ሰባቱ አፅዋማት እነማን ናቸው?

አስሩ ቃላቶች እነማን ናቸው?

6ቱ ቃላተ ወንጌልስ ምን ምን ይለናል?


በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉን 👇👇

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Jan, 10:47


እንኳን አደረሳችሁ የሚባልለት ሞት።

ማንም ሰው እናትኽ ለሞተችበት ቀን እንኳን አደረሰኽ ቢሉት ሐዘን እንጂ ደስታ አይሰማውም።

የቅዱሳን ሞት ግን ነቢዩ ዳዊት እንደነገረን"በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው"  የቅዱሳኑ ሞት እንዲኽ ክቡር ከኾነ
አምላክ ሰው የኾነባት የድንግል ማርያም ሞት ከሌሎች እንዴት የከበረ ይኾን?
ክቡር ስለኾነ ክብር እናገኝበታለን::
ለዚኽ ክቡር ሞት ነው እንኳን አደረሳችሁ የምንባባለው።

( ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው )

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Jan, 05:36


ጥር ፳፩ (21) እንኳን የአምላክ እናት ለቅድስተ ቅዱሳን ለንጽኅተ ንጹኀን ወላዲተ አምላክ ማርያም የእረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን።

አስተርእዮ ማርያም አስተርእዮ ማለት√√√√  መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው ••••• ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።

ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ”  የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።

ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ

ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።

ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው ። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።

የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት።

ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው አግችተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል። በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።

የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን። አሜን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

26 Jan, 12:34


‹‹እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባር ዐጽሙ ወይም ዝርወተ ዐጽሙ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ!!››

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ በዚች ቀን ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የምስክርነት ፍጻሜ ሆነ፡፡

የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ አንስጣስዮስ የተባለ ከቀጰዶቅያ ሀገር የሆነ መስፍን ነው፡፡ እናቱም ቴዎብስታ የተባለች ፍልስጥዔማዊ ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ ዐረፈ፡፡

ዕድሜውም ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሄደ፡፡ ንጉሡም ጣዖትን አቁሞ እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው፡፡ ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች፣ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው፡፡

ከዚህ በኋላ በንጉሥ ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ፡፡ ንጉሡም አባበለው ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም፡፡

ለመስማት እንኳ የሚያስጨንቅ ሥቃይን አሠቃየው ጌታችን ግን ያጸናዋል ቍስሉንም ያድነዋል ሦስት ጊዜም እንደሚሞት እርሱም እንደሚአስነሣው በዐራተኛውም የምስክርን አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው፡፡ ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ በተጋድሎና መከራ በመቀበልም ጽኑዕ በሆነ ሥቃይም ሰባት ዓመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው፡፡

ንጉሡም ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ፡፡ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ታላቅ ሥራየኛ አመጣ እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ መልቶ አስማት ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር ቅዱሱም ያንን ጽዋ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም፡፡

ያ መሠርይም በክብር ባለቤት በጌታ በኢየሱስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ከእርሱም ጋር ሌሎች ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሙተው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ ነፍስ ነው፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ፡፡ ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን አሉት፡፡ በዚያን ጊዜ ጸለየ እንዳሉትም አደረጋቸው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ቍጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ በጌታችን አመኑ፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጎድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት፡፡ አቃጥለው አሳርረውም ሥጋውንና ዐጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት፡፡ ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው፡፡ ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ስም ሰበከ፡፡ ቍጥር የሌላቸው አሕዛብ አይተው አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡

ነገሥታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታሥነሣ አምላክህ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በእርሱም እናምናለን አሉት፡፡ ቅዱሱም ጸለየ ከጉድጓድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶችን ጎልማሶችንም አስነሣላቸው እነዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ስም አስተማሩ የገሃነምንም ወሬ ተናገሩ፤ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው ዐረፉ፡፡

ከሀድያን ነገሥታት ግን ሙታንን ያስነሣህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ፡፡ ከዚያም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሣ ከአንዲት ድኃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እርሷም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሔርም መልአክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ ማዕድን አቀረበላት፡፡ የዚያች መበለትም የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ፡፡

ያቺም መበለት በተመለሰች ጊዜ የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ስለ ማዕዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደ እኔ መጣ አለች፡፡ ቅዱስም ‹‹እኔ አምላክ አይደለሁም፡፡ የአምላክ ባሪያ ነኝ እንጂ›› አላት፡፡ እርሷም እንዲህ ብላ ለመነችው ‹‹የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ እለምንሃለሁ፡፡ ዕውር ፣ ደንቆሮ፣ ዲዳ፣ ጎባጣ የሆነ ልጅ አለኝና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡›› ስለ ጌታችን እምነትም አስተማራትና በመስቀል ምልክት አማተበው ያን ጊዜም አየ፡፡ ቅዱሱም በሌላ ጊዜ እንዲሰማ፣ እንዲናገርና እንዲሔድ እንዲአገለግለኝም እኔ እሻለሁ›› አላት፡፡

በዚያን ጊዜ ንጉሡ በሀገሩ ሜዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያቺን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለ እርሷም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእርሷ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቷ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት፡፡ ንጉሡም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አስገረፈው በመንኰራኵርም አበራዩት ሙቶም ከከተማ ውጭ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመለከተ ንጉሡም አይቶ ደነገጠ ስለ ሕይወቱም አደነቀ፡፡

ከዚህም በኋላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግሥቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስም እየዘበተበት ‹‹ነገ በጥዋት ለአማልክቶችህ መሥዋዕትን አቀርባለሁ አንተም ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሠዋ እንዲአዩ›› አለው፡፡ ንጉሡም እውነት የሚሠዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግሥቱም እልፍኝ አስገብቶ አሳደረው፡፡ ለጸሎትም ተነሣ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለስክንድርያ ንግሥት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጒምላት ዘንድ ለመናቸው፡፡ እርሱም እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ጊዜ የሆነውን ሁሉ ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ፡፡ ትምህርቱም በልቡዋ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች፡፡

በማግሥቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሠዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ ዐዋጅ ነጋሪ ዞረ የቤቷን ምሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ እውነት መስሏት እጅግ እያዘነችነ ልጅዋን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም በአያት ጊዜ ፈገግ አለ ‹‹ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው›› አላት፡፡ ከዚያም ልጅዋን ጠርቶ ‹‹ወደ አጵሎን ሂድ ወደ እኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው›› አለው፡፡ ያን ጊዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳዘዘው ወደ ጣዖቱ ቦታ ሄዶ አዘዘው፡፡ በጣዖቱ ያደረ ያ ርኵስ መንፈስም ከማደሪያው ወጥቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አለበት መጥቶ ‹‹እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለሁም›› ብሎ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አመነ፡፡ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው፤ ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋራ አጠፋቸው ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር ዐፈረ፡፡

ብስጭትና ቁጣንም እንደተመላ ወደ ንግሥት ሚስቱ ዘንድ ገባ፡፡ እርሷም ‹‹አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጣላቸው አላልኩህምን›› አለችው፡፡ ይህንንም ከእርስዋ ሰምቶ በእርሷ ላይ እጅግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት ዐወቀ፡፡

ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ እንዲጎትቷትና በመጋዝም እንዲሰነጥቋት አዘዘ፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፡፡

በዚያም ጊዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥራ ነገሥታቱ ሁሉም ደነገጡ ኀፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከእርሱም እንዲአርፍ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉሥ ዱድያኖስን መከሩት፡፡

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

26 Jan, 12:34


ያን ጊዜም የክቡር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡ ድል አድራጊ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው፡፡ እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው፡፡

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ ‹‹በምድር መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ በመከራም ውስጥ ሁኖ በባሕርም ሆነ በየብስ ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለሁ፡፡›› ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፡፡
ከዚህ በኋላ ራሱን ዘንበል አድርጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ፡፡ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሥጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሀገሩ ልዳም ወሰዱት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው በውስጥዋ አኖሩት ከእርሱም ቍጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊዮርጊስም በረከቱ፣አማላጅነትና ተራዳኢነቱ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ከሥጋና ከነፍስ መከራ ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን፡፡

ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ወርኃ ሚያዚያ

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

24 Jan, 16:58


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

20 Jan, 13:42


ዛሬ የቃና ዘገሊላ በዓል ነው። ይህ በዓል በእመቤታችን ምልጃ ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበት በዓል ነው።

ቃና ዘገሊላ ማለት ሁለቱም ቃና እና ገሊላ የቦታ ስሞች ናቸው። ቃና ዘገሊላ ስንል በገሊላ ውስጥ የምትገኝ ቃና የተባለች ቦታ(ከተማ) ማለት ነው። ይህ ቦታና እለት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያውን ተዓምር በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ለዓለም ያሳየበት እና አምላክነቱንም የገለጠበት ዕለት ነው።

እመቤታችን ሆይ! ውኃ የተጠሙትን በምልጃሽ አስቢያቸው። አንቺው የጎደላቸውን ሁሉ በርኅሩኅ ልብሽ ጎብኚ። በየሥፍራው ከቀያቸው ተፈናቅለው በረሃብና ጥም የሚንገላቱትን የሚጎድላቸውን የሚነግርሽ አትፈልጊምና ለልጅሽ ንገሪላቸው።

ኢትዮጵያውያንንም በምልጃሽ ጎብኚን። ለልጅሽ "ወይን እኮ የላቸውም" ባልሽበት አንደበትሽ፦ "ሰላም እኮ የላቸውም፣ ፍቅር እኮ የላቸውም፣ መተዛዘን እኮ የላቸውም" በይልን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

19 Jan, 10:33


የተቀደሰችው ሃይማኖታችን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ


" አባትህን ጠይቅ ፥ ያስታውቅህማል ፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ ፥ ይነግሩህማል።" ዘዳ.፴፪፥፯

እግዚአብሔርን ባለማወቅ ፣ ፈቃዱንም ባለማስተዋል ፣ በክህደት ፣ በኑፋቄ ፣ በአመጻ ሥራና ይህን በመሰሉ ጥንተ ጠላት በሚያስነሳቸው የጥፋት ነፋሳትና ማዕበላት ተወስደን እንዳንጠፋ ደገኛዋን ጥበብ የሚያስተምሩን አባቶች ሊቃውንትን በዘመኑ ሁሉ የሚሰጠን የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመሥገን።

" ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።" [ ፪ቆሮ.፱፥፲፭ ]


የዓመት ሰው ይበለን

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

18 Jan, 17:48


ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

14 Jan, 04:33


ጥር 6 በዚህች ቀን ሰማዕትነትን በወጣትነቷ  የተቀበለች፣ የእርሷን አርአያነት ተከትለው ብዙ ደናግላን ከእርሷ ጋር ሰማዕትነት የተቀበሉ፣ በአማላጅነቷ ፈጥና የምትደርስ፤ ስለ ክርስቶስ ስትል በከፈለችው ሰማዕትነት፣ ድንግልናን በብጽዐት ለመጠበቅ ስትል በተቀበለችውን መከራ፣ ወጣትነቷ ሳያጓጓት ለእምነቷ በከፈለችውን ዋጋ፣ ንጽሕናዋን ቅድስናዋን ለመጠበቅ ባሳየችው ጽናት፣ በሕይወቷ ሳለች ከሠራችውም በላይ በሰማዕትነቷ ባፈራችው ፍሬ ልናስባትና ልንማርባት ደግሞም እንደ ዓቅማችን ልንመስላት የሚገባ ታላቋ ሰማዕት #ቅድስት_አርሴማ ከእናቷ ከቅድስት አትናስያ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስ የተወለደችበት ቀን ነው።

አማላጅነቷ አይለየን!

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

10 Jan, 20:14


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

10 Jan, 20:05


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️

         

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

10 Jan, 08:02


«ጥር ፪ እረፍቱ ለዳድቁ ቅዱስ አቤል ሰማዕት»

በኵር ጻድቁ ቅዱስ አቤል ምክንያቱም አዳም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላልፎ እንዳይበላው የታዘዘውን ዕፅ በላ ያን ጊዜ በእርሱና በልጆቹ ላይ ሞት ሠለጠነ ለኃጢአትም ተገዥ ሆነ። ሰይጣንም ሰውን ለማሳት ሠለጠነ ከዚህም በኋላ አዳም ከገነት ወጥቶ ወደታችኛዋ ምድር ወረደ ስለ በደለና የፈጣሪውንም ትዕዛዝ በመተላለፉ ፈጽሞ እያዘነና እያለቀሰ መቶ ዓመት ኖረ።

ከዚህም በኋላ አዳም ሔዋንን በግብር አወቃት ፀንሳ ቃየልንና እኅቱን ኤልዩድን ወደለች ሁለተኛም ዐወቃት አቤልንና እኅቱን አቅሌማን ወለደቻቸው አዳምም ሔዋንን "እነሆ ልጆችሽ አካለ መጠን አደረሱ ጐለመሱ ቃየል የአቤልን እኅት አቅሌማን ያግባት አቤልም የቃየልን እኅት ኤልዩድን ያግባት" አለ። ቃየልም እናቱን ሔዋንን እንዲህ አላት "ለእኔ ከእኔ ጋር የተወለደች እኅቴን ማግባት ይገባኛል አቤልም ከእርሱ ጋር የተወለደች እኅቱን ያግባ" ቃየል ከእርሱ ጋር የተወለደ ኤልዮድም እናቷ ሔዋንን የምትመስል እጅግ የምታምር መልከ መልካም ናትና።

አዳምም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ ጭንቅ ሆነበት ቃየልንም "አብራህ የተወለደች እኅትህን ታገባት ዘንድ አይገባህም አለዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቅርቡና መሥዋዕቱን ለተቀበለው ይሁን" አለው። መሥዋዕትንም በአቀረቡ ጊዜ የአቤልን መሥዋዕት እግዚአብሔር ተተቀበለ የቃየልን ግን አልተቀበለም ስለዚህም ቃየል ፈጽሞ አዘነ ሰይጣንም ተገናኘውና "ምን ያሳዝንሃል?" አለው ቃየልም "ለወንድሜ ለአቤል እኅቴን እተውለት ዘንድ አባቴ አዘዘኝ" አለው። ሰይጣንም "ምክርን ከኔ ስማ ወንድምህን ወደ ውኃ ምንጭ ይዘኸው ሒድ ውኃንም ሲጠጣ ራሱን በደንጊያ ምታው በሞተ ጊዜ ሁለቱንም ታገባቸዋለህ የሚከለክልህ ማነው" አለው ለቃየልም የሰይጣን ምክር ደስ አሰኘው ልቡም በዝሙት እሳትነት ነደደ ሰይጣን እንዳስተማረውም ወንድሙን አቤልን ገደለው ለሴት ስለ መቅናትም ጻድቁ አቤል በወንድሙ እጅ ሞተ እንዲህም ሞት ወደ ዓለም ገባ።

እግዚአብሔርም ቃየልን "ወንድምህ አቤል ወዴት ነው" አለው። ቃየንም "አላውቅም በውኑ እኔ የአቤል ጠባቂው ነኝን" አለው። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው "ቃየል ምን አድርገሃል የወንድምህ የአቤል ደም ጩኸት ከምድር ወደኔ ደርሷል። አሁንም በእጅህ የፈሰሰውን የወንድምህን ደም ትጠጣ ዘንድ አፍዋን የከፈተች ምድር የተረገመች ትሁን አንተ ታርሳታለህና በረከቷን ትሰጠሰህ ዘንድ አትጨምርም በምድር ላይ ፈሪ ተቅበዝባዥ ሁን"። ይህም መርገም ዘሩ በጥፋት ውኃ ከምድር ገጽ እስከ ሚደመሰስ በቃየል ላይ የበዛ ሆነ።

የክብር ባለቤት ጌታችንም ጸሐፍት ፈርሳውያንን ሲዘልፋቸው እንዲህ አላቸው "ስለዚህ ነቢያትን፣ ሊቃውንትን፣ ጥበበኞችን ወደናንተ እልካለሁ ከነርሱ የምትገድሉት አለ የምትሰቅሉትም አለ በምኵራባችሁ የምትገርፋት አለ ካንድ አገር ወዳንድ አገር ታሳድዷቸዋላችሁ። ከጻድቁ ከአቤል ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እሰሰከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በዓለም የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርስ ዘንድ"።

ቅዱስ ጳውሎስም አለ "ቃየን ካቀረበው መሥዋት ይልቅ አቤል በሃይማኖት ለእግዚአብሔር ያቀረበው መሥዋዕት ተሻለ" ስለ እርሱም ደግ እንደሆነ መሰከረለት መሥዋዕቱንም በመቀበሉ ምስክሩ እግዚአብሔር ነው ደግ እንደሆነም ከሞተ በኋላ ተናገረ።

ከዚህም በኋላ አዳም ልጁን በአጣው ጊዜ "ወንድምህ አቤል ወዴት አለ" ብሎ ቃየልን ጠየቀው ቃየልም በቁጣ "አላውቅም" ብሎ መለሰ አዳምም ልጁን ይፈልግ ዘንድ ወደ ዱር ሮጠ በወንዝ ዳርም በድንኑን አገኘና አንገቱን አቅፎ "ማን ገደለህ?" አለው ከበድኑም "ወንድሜ ቃየን ገደለኝ" የሚል ቃል ወጣ። አዳምና ሔዋንም በልጃቸው በአቤል ሞት ሃያ ስምንት ዓመት ያህል ሲያለቅሱ ኖሩ።

ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ አዳም መጥተው "የዓለሙ ሁሉ አባቶች አባት አዳም የምሥራች እነሆ ልጅህ አቤል የገነትን ዛፎች ተሳለመ ነፍሱም እንደ ተወደደ መሥዋዕቶ ወደ እግዚአብሔር ዐረገች" አሉት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባቶቻችንም በረከት ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

06 Jan, 18:54


ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ....
.
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!

ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!

ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!

የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››

እንኳን ለአምላካችን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

06 Jan, 14:05


የአእላፋት ዝማሬ ቀጥታ ስርጭት ከቦሌ መድኃኔዓለም!

https://www.youtube.com/live/t2M4jDPcH6E?si=sLgeQsFgycymbRTb

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

05 Jan, 18:58


እንኳን ለቅዱስ "አምላካችን አማኑኤል" "ዕለተ ማርያም" እና "ዕለተ ጌና ስቡሕ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን

" ቅዱስ አማኑኤል "

አማኑኤል የሚለውን ስም መረዳት የሚቻለው በአንድ መንገድ : እርሱም ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን ጠንቅቆ በመማር ነው:: ምሥጢራት ደግሞ በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም

እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው ጊዜ ሣይሠፈር: ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው

ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው

ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ:- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ባለቤቱ ያውቃል

እግዚአብሔር በሁዋለኛው ዘመን ሰው የሆነበት ምሥጢር እኛን ለማዳን ቢሆንም ይሔው ተግባሩ ዓለም ሳይፈጠር ያሰበው እንጂ በአዳም ውድቀት ምክንያት ድንገት የታሰበ አይደለም

እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ: በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ: በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው

ከዚህ በሁዋላ ለ5,500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር: ሱባኤ ይቆጠር ምሳሌም ይመሰል ገባ

ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት / ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል

ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል መድኅን ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል

"አማኑኤል" የሚለው ቃል ከእብራይስጥ ልሳን (ከጽርዕ የሚሉም አሉ) በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም "እግዚአብሔር ምስሌነ - እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ" እንደ ማለት ነው ኢሳ. 7:14, ማቴ. 1:22 ምሥጢሩ ግን ከዚህ የሠፋ ነው

"አማኑኤል" ማለት "እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋን: ከነፍሳችን ነፍስን ነስቶ በፍጹም ተዋሕዶ እኛን መሰለን" ማለት ነው በሌላ አነጋገርም "አምላክ ሰው ሆነ: ሰውም አምላክ ሆነ" እንደ ማለት ነው

ይሕንን ሲያደንቁ ቅዱሳን ሊቃውንት "ወዝንቱ ስም ዓቢይ: ወኢይደሉ ፈሊጦቶ-ይህ ስም ታላቅ ነው:: ወደ ሁለት ሊከፍሉት (ሊለዩት) አይገባም" ብለው ምሥጢረ ተዋሕዶን አስረድተዋል (ሃይ. አበ. ዘሳዊሮስ)
ስለዚህም ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ እኛን ያድን ዘንድ በተለየ አካሉና በከዊነ ቃልነቱ ፍጹም የድንግል ማርያምን ሥጋ ተዋሕዶ የሰውነትንም: የአምላክነቱንም ሥራ ሠርቶ አድኖናል

በማሕጸነ ድንግል ከተቀረጸባት ደቂቃ ጀምሮም ፍጹም ተዋሕዶን ፈጽሟልና መቼም መች አምላክም: ሰውም ነው እንጂ ወደ ሁለትነት: ማለትም አምላክን ለብቻ: ሰውን ለብቻ አናደርግም ስለዚህም ዛሬም: ዘወትርም እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደው ሥጋችን በዘባነ ኪሩብ ሲሠለስና ሲቀደስ ይኖራል እርሱ ጌታችን እስከዚህ ድረስ ወዶናልና
ፈጣሪያች በሦስትነቱ:- ሥላሴ (አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ): በአንድነቱ:- እግዚአብሔር: ኤልሻዳይ: አልፋ: ወዖ: ቤጣ: የውጣ: ኦሜጋ . . . እያልን እንደምንጠራው ሁሉ በሥጋዌው ምክንያት:- አማኑኤል: መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ: ክርስቶስ እያልን እንጠራዋለን

ዕለተ ጌና ❤️
ከሳምንታት በፊት ጀምረን የክርስቶስን የማዳን ሥራ ለመገንዘብ እየሞከርን ቆይተናል በተለይ ታኅሳስ 7 ቀን "ስብከት" በሚል ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን ትንቢት መነገሩን: ምሳሌ መመሰሉን: ሱባኤ መቆጠሩን ተመልክተን ነበር

ቀጥለን ደግሞ ታኅሳስ 14 ቀን "ብርሃን" በሚል አምላካችን እንደ ምን ባለ ጥበቡ ብርሃኑን እንደ ሰጠን: አንድም ወደን ወደ ጨለማ በገባን ጌዜ ሥጋችንን ተዋሕዶ ብርሃን እንደ ሆነልን ለማየት ሞክረናል

ታኅሳስ 21 ቀን ደግሞ በበደላችን ምክንያት የነፍሳችንን እረኛ አጥተን ነበር ለእኛው በደል እርሱ ክሶ ድጋሚ መልካም እረኛችን ሆኖ በሥጋ ማርያም መለገለጡን አየን የዛሬው በዓል ዕለተ ጌና ደግሞ ማሠሪያው ነው

"ጌና" ማለት በቁሙ "ዕለተ ልደት ስቡሕ: ማለትም አምላክ ሰው የሆነበት ምስጉን ቀን" እንደ ማለት ነው:: ይህ ቀን ሁሌም በየዓመቱ "አማኑኤል (ጌና)" እየተባለ ይከበራል ምክንያቱ ደግሞ ጌታ የተጸነሰ መጋቢት 29 ቀን በመሆኑና ከዚህ ቀን 9 ወር ከ5 ቀናት ብንጨምር ይህ ዕለት ታሕሳስ 29 ቀን ይመጣል

ነገር ግን በ4ኛው ዓመት ዘመነ ዮሐንስ ዻጉሜን 6 ስትሆን 9 ወር ከ6 ቀን ስለሚሆን ቀኑን እንዳይለቅ በዘመነ ዮሐንስ ዕለተ ልደቱ ለክርስቶስ ታሕሳስ 28 ቀን ይከበራል፡ ያም ሆኖ በዘመነ ዮሐንስ ታኅሳስ 28ን አክብረናል ብለን 29ን አንተወውም እርሱም ይከበራል

በዚያው ልክ ደግሞ በ3ቱ አዝማናት (በማቴዎስ: በማርቆስና በሉቃስ) ልደቱ በ29 ነው ብለን 28ን አንሽረውም "ጌና-አማኑኤል-ዕለተ ማርያም" እያልን እናከብረዋለን እንጂ ብዙ ጊዜም በተለምዶ በዓለ ልደትን "ጌና" በማለት ፈንታ "ገና" የምንል ብዙዎች አለን
ግን አበው ባቆዩልን ትውፊት "ጌና" ልደቱን የሚመለከት ሲሆን "ገና" ግን ባሕላዊ ጨዋታውን የሚመለከት ቃል ነው

ዕለተ ማርያም ❤️
ዳግመኛ ይህ ቀን ዕለተ ማርያም ይባላል:: "ማርያም" የሚለው ቃል ብዙ ትርጉምን ያዘለ የእናታችንና የእመቤታችን: የተስፋችንና መመኪያችን: የድንግል እመ ብርሃን ስም ነው

ክርስቶስ ተጸነሰ ተወለደ ስንል ለዚህ ሁሉ ምሥጢር ማካተቻና የድኅነታችን መጀመሪያ: የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናትና ከፈጣሪ ቀጥሎ ታላቅ ክብር: ምስጋና: ስግደትና ውዳሴ ለእርሷ ይገባታል: መድኅናችን ክርስቶስ ያዳነን በእርሷ ምክንያት ነውና
​​ሠለስቱ ምዕት (318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት) ይህንን ምሥጢር ሲያደንቁ እንዲህ ብለዋል:-
በሥጋ ማርያም ጌታ ተጸነሰ
በሥጋ ማርያም ጌታ ተወለደ
በሥጋ ማርያም ጌታ አደገ
በሥጋ ማርያም ጌታ ተጠመቀ
በሥጋ ማርያም ጌታ ተነሳ
በሥጋ ማርያም ጌታ ዐረገ
በሥጋ ማርያም ጌታ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ
በሥጋ ማርያም ጌታ ዳግመኛ በሕያዋንና ሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ይመጣል (መጽሐፈ ቅዳሴ)

የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ክርስቶስ በርሕራሔው ይማረን ከበረከተ ልደቱም ያሳትፈን

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

02 Jan, 11:46


አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ 

ስም ፍስሐ ጽዮን በኋላ ተክለሃይማኖት፤ የተወለዱበት ቀን ታኅሣሥ ፳፬ ፲፩፻፺፯፤ የትውልድ ቦታ ቡልጋ፤ የአባት ስም ጸጋዘአብ፤ የእናት ስም ቅድስት እግዚእ ኃርያ፤ ያረፉበት ነሐሴ ፳፬[1]፤ ንግሥ ነሐሴ ፳፬፤ የሚከበሩት በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኮፕት ቤተክርስቲያን በየኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥንክሳር።

‹ተክል› ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣ የሚበላ፣ የሚሸተት፣ ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ፤ ሥርዓት ማለት ነው [ማቴ.፲፭፥፲፫]፡፡ ‹ሃይማኖት› ማለት ደግሞ በሀልዎተ እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር የሁሉ አስገኚ መሆኑን፣ በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት፣ በቅዱሳን ተራዳኢነት ማመን አምኖም መመስከር ማለት ሲሆን ‹ተክለ ሃይማኖት› የሚለው ሐረግም የሃይማኖት ተክል፣ ይኸውም የጽድቅ ፍሬን ያፈራ፣ ከኃጢአት ሐሩር ማምለጫ ዛፍ፣ ምእመናንን በቃለ ወንጌል ያጣፈጠ ቅመም፣ መዓዛ ሕይወቱ የሚማርክ፣ ቢመገቡት ረኃበ ነፍስን የሚያስወግድ ቅጠል፣ የጻድቃን መጠለያ ዕፅ የሚል ትርጕም አለው፡፡‹‹ተክለ ሃይማኖት ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ማለት ነው›› ሲል የጻድቁን ስም ይተረጕመዋል፡፡

በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በዐሥራ አምስት ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ በዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ ዱር አደን ሄደው ሳለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መረጣቸው። ስማቸውንም «ተክለ ሃይማኖት» አለው፡፡ ትርጓሜውም በሃይማኖት ፍሬ ማለት ነው፡፡

አባታችንም ሐዋርያዊ ጉዟቸውን ሲጀምሩ
«አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ . . . ደካማ ለሆንኩ ለእኔ ያለ አንተ የሚያፀናኝ የለም። ለምፍገመገም ለእኔ ያለ አንተ ደጋፊ የለኝም። ለወደቅሁ ለእኔ ያለአንተ የሚያነሳኝ የለም። ለአዘንኩ ለእኔ ያለአንተ የሚያረጋጋኝ የለም። ለድሀው ለእኔ ያለ አንተ መጠጊያ የለኝም፡፡» [ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪ - ፫] ይህን ብለው ትሕትና በተሞላበትና በተሰበረ ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ከለመኑ በኋላ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ከኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሰዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ፀሐይ ተብለዋል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን ክታቡ ስለ ቅዱሳን መንፈሳዊ ተጋድሎ ሲገልፅ:-
«እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሱ» [ዕብ. ምዕ ፲፩ ቁ ፴፫ ] እንዳለ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም በመንፈሳዊ ተጋድሎ እንዲሁም በትህትና በተአምራት አላዊ የነበረውን ንጉሥ ሞቶሎሚን ወደ ክርስትና መልሰዋል፡፡
«ጽድቅን አደረጉ» እንዳለው አባታችን ወንጌልን በተጋድሎ ሕይወታቸው ተርጉመዋል፡፡
«የአንበሶችን አፍ ዘጉ» [ምዕ ፲፩ ቁ ፴፫ /ምዕ ፲፩ ቁ ፴፬] እንዳለው አባታችንም የአውሬውን፥ የዘንዶውን ራስ ቀጥቅጠዋል።
«ከሰይፍ ስለት አመለጡ» እንዳለው አባታችንም ሞቶሎሚ ከወረወረው ጦር በተአምራት ድነዋል፡፡
«ከድካማቸው በረቱ» እንዳለው አባታችንም ያለ ዕረፍት በብዙ ተጋድሎ በጾምና በስግደት በብዙ መከራ በርትተዋል፡፡
ይህን ሁሉ ገድልና ትሩፋት እየፈጸሙ ዕረፍታቸውም በደረሰ ጊዜ ደቀመዝሙሮቻቸውን «ልጆቼ ሆይ ሁሉም መነኮስ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት አይደለም፤ ዓለምን በሚገባ የናቀ ብቻ ይገባል እንጂ መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ጽድቁን ብቻ ፈልጉ፤ ጾምና ጸሎትን አዘውትሩ፤ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ እያሉ ይመክሯቸው ነበር. . .» በኋላም «ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ፤ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ፣ ከእውነተኛው ዳኛ ከጌታዬ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ?» እያሉ በፍጹም ትህትና እና በልዩ መንፈሳዊ ተመስጦ ይጸልዩ ነበር፡፡

ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቃንን እንድናስባቸው፣ በስማቸውም ለድሆች እንድንመጸውት፣ መታሰቢያቸውን እንድናደርግ የምትመክረን፤ የምታስተምረን [ማቴ.፲፥፵፩-፵፪]፡፡ ቅዱሳን ጻድቃን በሕይወተ ሥጋ ሳሉም ሆነ ከሞቱ በኋላ በዐጸደ ነፍስ ሆነው በጸሎታቸው ለሚታመኑ፣ በቃል ኪዳናቸው ለሚማጸኑ ምእመናን በመጸለይና ወደ እግዚአብሔር በማማለድ ድኅነተ ሥጋ፣ የድኅነት ነፍስን የሚያስገኙልን የችግር ጊዜ አማላጆቻችንና አስታራቂዎቻን ናቸው፤ ከእነዚህ ቅዱሳን መካከል ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንደኛው ናቸው፡፡

አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው፣ በብሕትውና ኖረዋል፡፡ በተጨማሪም እንደቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፣ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሚታወሱባቸው በዓላት መካከልም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን የሚከብረው በዓለ ልደታቸው አንደኛው ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ዜና ልደታቸውን ሲናገር ‹‹ሐዲስ ሐዋርያ›› በማለት በክብር ጠርቷቸዋል፡፡
                                            
                                           ✥••┈••●◉  ✞  ◉●••┈••✥

ምንጭ፡– ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ መጽሐፈ ስንክሳር (ታኅሣሥ ፳፬፣ ጥር ፳፬፣ መጋቢት ፳፬፣ ግንቦት ፲፪ እና ነሐሴ ፳፬ ቀን)፤ መለከት መጽሔት ፲፰ኛ ዓመት፣ ቍጥር ፱፡፡

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

01 Jan, 20:03


​​❤️ እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። ✞✞✞🙏🏻

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ
❤️

                     ልደት ❤️

መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና
ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ:  #‎ጸጋ ዘአብ ካህኑና  #‎እግዚእኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው
#‎ቅዱስሚካኤል : ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24, በ1206 (1196) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ 24, በ1207 (1197) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

                  ዕድገት ❤️

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " #‎ፍሥሃ
ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ  #‎አባጌርሎስ  ተቀብለዋል::

                  መጠራት ❤️

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን
ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት  #‎ጌታችንኢየሱስክርስቶስ  አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:

"ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ)
ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

                አገልግሎት ❤️

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ ( #‎ጽላልሽ ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ  #‎ኢትዮዽያ  2 መልክ ነበራት::

1.ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::

2.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት  #‎ሐዲስ ሐዋርያ  አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

             ገዳማዊ ሕይወት ❤️

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል
ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

እነዚህም በአቡነ #‎በጸሎተሚካኤል  ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ  #‎ኢየሱስሞዐዘሐይቅ  ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ  #‎ዮሐኒ  ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ  #‎ዞረሬ  ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::

             
ስድስት ክንፍ ❤️

ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ  #‎እሥራኤል  የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት #‎አባሚካኤል  ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-

¤በቤተ መቅደስ ብስራቱን
¤በቤተ ልሔም ልደቱን
¤በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
¤በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
¤በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው  #‎ቀራንዮ  ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ  #‎እመቤታችንድንግልማርያም  ፈጥና ደርሳ ጻድቁን ወደሰማይ አሳረገቻቸው::

በዚያም:-
¤የብርሃን ዐይን ተቀብለው
¤6 ክንፍ አብቅለው
¤የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
¤ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

                   ተአምራት ❤️

የጻድቁ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
ሙት አንስተዋል
ድውያንን ፈውሰዋል
አጋንንትን አሳደዋል
እሳትን ጨብጠዋል
በክንፍ በረዋል
ደመናን ዙፋን አድርገዋል::


ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

                  ዕረፍት ❤️

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24, በ1306 (1296) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች :-

1.ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ
2.ፍስሐ ፅዮን
3.ሐዲስ ሐዋርያ
4.መምሕረ ትሩፋት
5.ካህነ ሠማይ
6.ምድራዊ መልዐክ
7.እለ ስድስቱ ክነፊሁ (ባለስድስት ክንፍ)
8.ጻድቅ ገዳማዊ
9.ትሩፈ ምግባር
10.ሰማዕት
11.የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
12.ፀሐይ ዘበፀጋ
13.የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
14.ብእሴ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ሰው)
15.መናኒ
16.ኤዺስ ቆዾስ (እጨጌ)

እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በረከታቸው፡ አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን ። አሜን³🙏❤️

           Join share

     @Maryam_Maryam2127
     @Maryam_Maryam2127

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

31 Dec, 23:41


"#ቅድስት_ድንግል_ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ በምሕረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን፤ ዓለም የጥፋት፣ የሞት፣ የክስረት፣ የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምጽን ያሰማናልና አንተ ግን ጎስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምጽህን አሰማን እንድንጽናናም አድርገን፡፡"

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

30 Dec, 23:04


ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከ፯ቱ ሊቃናት አንዱ: በራማ አርባብ በሚባሉ ፲ ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ: በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና: ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ: ሠለስቱ ደቂቅን: ዳንኤልን: ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::+ከምንም በላይ ቤተ ክርስቲያን "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: የስሙ ትርጏሜ "አምላክ ወሰብእ-እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::
መልዐኩ እመቤታችንን ከመጸነሷ ጀምሮ ባይለያትም ከእግዚአብሔር ተልኮ አብስሯታል::

- ቅዱስ ገብርኤል ዛሬ የብሥራቱ መታሰቢያና ዳናህ በተባለ ሃገር ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ነው::
"ገብርኤል ዜናዊ ምጽዓተ ክርስቶስ አንበሳ::
ለዛቲ በዓልከ በዘይትሌዓል ሞገሳ::
በዓለ ማርያም አንበረ ደቅስዮስ በርዕሳ::" እንዲል:: [አርኬ]

ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን : ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አዕምሮውን: ጥበቡን በልቡናችን አሳድሪብን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

28 Dec, 05:42


ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እጅግ አጽናኝና አስደሳች የሆነውን
ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈጸም ደስ የምንሰኝበትን ጸጋ አሰጠን።

ጠበቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የሃጢያት እሳትም አጥፋልን፡፡ የኑሮአችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን፣ ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች፣ ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን። ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና ጥበቃ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን።

ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብኝ ቁጥር እያለቀስሁ
እጠራሃለሁ ፡፡ ጎስቋላ የምሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ
የምገኝ ልጅህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት ያሻኛልና ፈጥነህ ናልኝ፡፡ ቅድስት ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበስር ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ይዤሃለሁ በዚህች ሰዓት ፀሎቴንና ልመናዬን ስማ፡፡

"#ቅድስት_ድንግል_ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን፤ ዓለም የጥፋት፣ የሞት፣ የክስረት፣ የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምጽን ያሰማናልና አንተ ግን ጎስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምጽህን አሰማን እንድንጽናናም አድርገን፡፡"

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

27 Dec, 20:06


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

27 Dec, 19:49


📌ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ«እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ  ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....READ MORE

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

27 Dec, 18:49


​​እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችኹ አደረሰን!

√√√ታኅሣሥ ፲፱ (19) ቀን ••••• በዚህ ቀን ሰለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው።

ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ነገሩ እንዲህ ነው። ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር ሰዎች የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሥም አይጣላልናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ነበሩ። ት/ዳንኤል 3፡1-30 ታሪኩ እንደሚግረን ንጉስ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሣት ውስጥ ብሎ አወጀ።

በዚህ መካከል ሰልስቱ ደቂቅ ነበሩ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር። የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻል?" ባላቸው ጊዜ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳን አንተ ለመታመልከው ጣኦት አንሰግድም አሉት።

በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሣት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሣቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠልስቱ ደቂቅን ግን መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው።

በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል እንዲያውም የአማልክትን ልጆች ይመስላል " አለ። የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ተብሎ የነበረው "ጉልበት ሁሉ ለሰልስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" ተባለ ይህን ሁሉ ታህሳስ 19 ቀን ሆነ በዚህም ምክንያት በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን!

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የመላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድኤት በረከቱ ይደርብን

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

15 Dec, 13:15


ታኅሣሥ ፮ ቅዳሴ ቤቷ ለቅድስት አርሴማ ሰማዕት

እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ታኅሣሥ ፮ በዚህች ዕለት የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያኗ የከበረችበት እና የሥጋዋ ፍልሰት የተከናወነበት ፤ ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳስ የአባ አብርሃም ሶርያዊ የዕረፍቱ እና የቅዱስ ስምዖን ጫማ ሰፊውም መታሰቢያ ነው።

"ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ፤
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ፤
ዘፈጸመት ግርማ በጻማ፤
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ "።

(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቁመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው።)
               ( ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ )

ከሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ያሳትፈን መልካም  በዓል እና መልካም ቀን ይሁንልን

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

12 Dec, 08:25


በዓታ ለማርያም

ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡   
በዓት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ቤት ማለት ነው፡፡ ደጋጎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው ለብዙ ዘመናት ከመኖራቸው የተነሣ በኀዘን ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ ቃል በመግባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት በእግዚአብሔር ቤት ትኖርና ታገለገል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ስለሰጧት በዓሉም ስያሜውን በዚያ መሠረት አግቷል፡፡  

በዚያን ጊዜም በቤተ ክርስቲያን ያገለግል የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ስዕለታቸውን አስተውሶ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሊቀበላት ሲቀርብ እንደ ፀሐይ የምታበራ ሕፃን ሆና አገኛት፤ በመገረምና በመጨነቅም ከወላጆቿ ጋር ምን ሊመግቧት እንደሚችሉ በመጨነቅ ላይ ሳሉ ሕዝቡ በተሰበሰበበት መካከል መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ መና መስሎት ሲቀረብ ወደ ላይ ተመለሰበት፡፡ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም እያንዳንዳቸው ቢሞክሩ በተመሳሳይ መልኩ ተመልሶ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ‹‹ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ›› ብለው ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እንዲቀርቡ ቢደረግም ለእነርሱም ራቀባቸው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ቅድስት ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፤ ሆኖም ግን ቅድስት ማርያም እናቷ ትታት ስትሄድ መከተል ጀመረች፤ ምርርም ብላ አለቀሰች፡፡

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

10 Dec, 08:29


እንኳን ለርእሰ ባሕታዊ ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ኤልያስ በእስራኤል ፊት ለተገለጠበት ለልደቱ ዓመታዊ በዓል አደረሳችኹ አደረሰን            
                            
#ነቢዩ_ቅዱስ_ኤልያስ፦ ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ ቶና ነው። ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ በእሳት ሲጠቀለሉበት አባቱ አየ። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም "ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን" ተባባሉ።

በእስራኤለሰ ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፎአል። ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል። በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ ዮሐንስ ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግአል። "ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ በእግዚአብሔር ፊት የማያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው" አለ።

"ከጠላቶቻቸው ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸውዋለች የሚጣሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ። ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል። ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከባሕር የወጣው አውሬ ከሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል። አስከሬናቸውም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምስጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት። አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በአገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም።

በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስበርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ ሁለቱ ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አጽንተውባቸዋልና ይላሉ። ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል። ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ። በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው የሰማይ አምላክ ፈጽመው ያመሰግናሉ"። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ነቢይ በቅዱስ ኤልያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

01 Dec, 18:33


https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=0Go7sSnRgmJ6VFe7

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Nov, 18:44


ኅዳር ፳፩ እንኳን ለቅድስተ ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችኹ አደረሰን


"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

➦ እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።

➦ ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።

➦ ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።

➦ ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።

➦ "ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19)

✝️ ኅዳር 21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች በዚህች ቀን:-

1.ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን። ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው። (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19)

2.በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች። ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች። (1ሳሙ. 5:1)

3.በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት። በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል። (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል።

"ሰላም ለኪ ማርያም እምነ።
ዘሰመይናኪ ጸወነ።
ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ።
ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ።
ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ።" እንዲል። (አርኬ ዘኅዳር 21)

4.በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል። እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1)

5.በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል።

6.በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል።

7.በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል።

8.በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር። ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው።

"አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን"

➦ "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና።

➦ ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች። ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበል።ጣቸዋለች። እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና

✞ እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው።

1."ንጽሕት" ትባላለች። ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም። እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት።

➦"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል። (ተአምረ ማርያም)

2."ጽንዕት" እንላታለን። ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና።

•"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት።
(ቅዱስ ያሬድ)

•ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ። (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው። እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና።
4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና።

አምላከ ቅዱሳን የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን ያሳድርብን አሜን።

     https://t.me/BeteTewahdoEthio

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Nov, 18:42


https://www.youtube.com/live/TmH_ve1kHwg?si=xqXA6bdgJWCQNtmc

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Nov, 16:51


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

29 Nov, 16:24


📡 በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️🀄️
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥

🔑 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘማሪዎች ውስጥ የማንን ዝማሬ ማግኘት ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔴የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
⚫️የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
ዝ?የቀዳሜጸጋ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔴የኪነጥበብ መዝሙር
⚫️የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔴የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ እና      ወ.ዘ.ተ......
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️🀄️
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥


         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █       

 
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

23 Nov, 17:35


https://youtu.be/gboQSVKAyEc

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

23 Nov, 12:23


​​​​ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
ኅዳር ፲፭ ቀን

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡

ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡

እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል። ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡

በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡- ፍት.ነገ ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡
ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡

ጾሙን የበረከት እና የምሕረት ያድርግልን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

23 Nov, 09:52


የአእላፋት መዝሙር ጥናት ተጀመረ!!!

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@janyared

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

21 Nov, 16:27


መስቀሉን  ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ መስቀሉን  ይጫኑ Join ይበሉት
/Start      

                  🔳🔳
                  🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳

         መስቀሉ አርማችን ነው።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

21 Nov, 15:58


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

21 Nov, 13:19


ህዳር 12
እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)
የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ አለ "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት፥ ዘንዶውም አልቻላቸውም፥ ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘለትም። ራእ 12፤7 ነቢዩ ዳንኤልም እንዲህ አለ "በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል" ዳን ፲፪፥፩። በዚህም የመልአኩ ስልጣን በህዝቡ ላይ በሐዲስ ኪዳንም ፀንቶ እንደሚኖር ነቢዩ ዳንኤል አስቀድሞ ነግሮናል፡፡

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

21 Nov, 12:13


💒 ባሕረ ኤርትራን በበትሩ ከፍሎ እስራኤልን ያሻገረው❓️



✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

20 Nov, 18:45


​​💛 እንኳን ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏🏻❤️

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ❤️

ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን እንደ ረዳው ታስተምራለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 5 ላይ እንደ ተጻፈው ቅዱሱ መልአክ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: እሥራኤልን በምድረ በዳ የመራ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሲያርፍ ታላቅ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር:: እግዚአብሔር ግን ኢያሱን አስነስቶ አረጋግቷቸዋል:: ቅዱስ ሚካኤል 40ውን ዘመን እሥራኤልን ደመና ጋርዶ: መና አውርዶ: ክንፉን ዘርግቶ: ጠላትን መክቶ ከሙሴ ጋ እንደ መራቸው ከኢያሱ ጋርም ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወረደ::

በኢያሪኮ አካባቢም የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በግርማ ለኢያሱ ታየው:: ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ "አንተ ከእኛ ወገን ነህን? ወይስ ከጠላቶቻችን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ ሚካኤልም መልሶ "እረዳህ ዘንድ እነሆ የሠራዊት አለቃ ሆኜ ተሹሜ መጥተቻለሁ" አለው::
ያን ጊዜ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰገደለት:: ቅዱሱ መልአክም አክሎ "ፍታሕ ቶታነ አሳዕኒከ እም እገሪከ: እስመ ምድር እንተ ትከይዳ ቅድስት ይዕቲ - የረገጥካት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ" አለው::

ኢያሱም የተባለውን አደረገ:: ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን "ለመላእክት የጸጋ (የአክብሮ) ስግደት ይገባል: በቅዱሳኑ ፊትም ጫማ ተለብሶ አይቆምም" የምትለው:: ያ መሬት ሊቀ መላእክት ቢቆምበት ተቀድሷል:: ዛሬም ቤቱ በታነጸበት: ታቦቱ በተቀረጸበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱ መልአክ አለና ጫማን አውልቆ: ባጭሩ ታጥቆ መግባት ይገባል::

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከኢያሱ ጋር ሆኖ አማሌቅን ጨምሮ የእሥራኤልን ጠላት አጥፍቷል:: ጥቅመ ኢያሪኮን (ቅጥሩን) አፍርሷል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: በገባኦን ፀሐይን: በቆላተ ኤሎምም ጨረቃን ሲያቆም ከእርሱ ጋር ሆኖ ረድቶታል::

         ዱራታኦስና ቴዎብስታ❤️
ቅዱሳኑ ዱራታኦስ (ዶርታኦስ) እና ቴዎብስታ (ቴዎብስትያ) የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ:: በድርሳነ ሚካኤልና በመጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ እንደምናገኘው 2ቱ ቅዱሳን በተቀደሰ ትዳር ተወስነው: ሕጉን ትዕዛዙን ፈጽመው: ለነዳያን ራርተው: ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ ነበሩ:: ይልቁኑ ግን የጌታችን: የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያለማስታጐል ያደርጉ ነበር:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ሐብት ንብረታቸው አልቆ ተቸገሩ:: ግን የጨነቃቸው መቸገራቸው ሳይሆን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ሊያቆሙ መሆናቸው ነው::

አማራጭ ሲያጡ ተቀምጠው ተመካከሩ:: የቅዱሱ መልአክ ዝክር ከሚቀር ልብሳቸውን (ያውም የክብር ልብሳቸውን) ሊሸጡ ተስማሙ:: በዚህ መሰረት ቅዱስ ዱራታኦስ ወደ ገበያ ሲሔድ ወዳጁ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወረደለት:: መንገድ ላይም የጦር መኮንን ሃገረ ገዢ መስሎ ተገናኝቶ አጫወተው:: ችግሩን ጠይቆም መፍትሔውን ነገረው:: "እኔ እዋስሃለሁና ለበዓል የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሁሉ ገዝተህ አሰናዳ" አለው::

"እኔ ወደ ቤትህ መጥቼ ስለምስተናገድ አንድ አሣ አምጥተህ አቆየኝ:: እኔ ሳልመጣ ግን አትረደው" አለው:: ቅዱስ ዱራታኦስ የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ ወደ ቤቱ ሲሔድ ድንቅ ነገርን ተመለከተ:: ሚስቱ ቅድስት ቴዎብስታ በቤቱ መካከል ሁና ቤቱ በበረከት ሞልቷል::
ማሩ: ቅቤው: እሕሉ ሁሉ በየሥፍራው ሞልቷል:: ባልና ሚስቱ ደስ ብሏቸው:: ነዳያንን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ዋሉ:: በሁዋላ ያ መኮንን (ቅዱስ ሚካኤል) በቤታቸው መጥቶ ተስተናገደ::

በእርሱ ትዕዛዝ የአሣው ራስ (ሆድ) ሲከፈት በውስጡ 300 ዲናር ወርቅ (እንቁ) ተገኘ:: ቅዱሳኑ ይህን ተመልክተው ሲደነግጡ ቅዱስ ሚካኤል ክንፉን ዘርግቶ ራሱን ገለጸላቸው:: ደንግጠው በግንባራቸው ተደፉ:: እርሱ ግን "በተገኘው ሃብት እዳችሁን ክፈሉ:: ከዚህ በሁዋላ ግን በምድር አትቸገሩም:: በሰማይም ክፍላችሁ ከእኔ ጋር ነው" ብሎ ባርኩዋቸው ወደ ሰማይ ዐረገ:: እነርሱም በሐሴትና በበጐ ምግባር ኖረው ዐርፈዋል:: ለርስቱም በቅተዋል::

          ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ❤️
የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::
በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
ምጽዋትን ያዘወተረ::
አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

         አፄ በእደ ማርያም❤️
በዕደ ማርያም" ማለት "በማርያም እጅ" እንደ ማለት ነው:: እኒህ ሰው የኢትዮዽያ ንጉሥ ሲሆኑ የነገሡትም በ1460 ዓ/ም ነው:: ደጉ አባታቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሲያርፉ በመንግስቱ ተተክተው ሃገራችንን አስተዳድረዋል:: ድርሰት ደርሰዋል:: አብያተ መቃድስ አንጸዋል::
በተለይ ለቅኔ ትምሕርት ማበብ ልዩ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይነገራል:: ልክ በነገሡ በ10 ዓመታቸው ግን መንግስተ ምድር በቃኝ ብለው በምናኔ በርሃ ገብተዋል:: በዙፋናቸውም አፄ እስክንድር ተተክተዋል:: ጻድቁ ንጉሥ ግን ቅዱስ ሚካኤልን ይወዱት ነበርና በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከቅዱሳኑ በረከታቸውም አይለየን
🌺💚💛❤️🌺
@Maryam_Maryam2127
@Maryam_Maryam2127

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

17 Nov, 20:55


ከጌታ ልደት በፊት ያለው ሳምንት ዘመነ __ተብሎ ይጠራል?

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

17 Nov, 19:18


📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........

የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
                   👇👇👇

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

17 Nov, 19:04


🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

15 Nov, 15:10


#ኅዳር_6

#ደብረ_ቁስቋም

ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡

ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡

ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡

እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡

ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡

(ስንክሳር ዘተዋሕዶ እና #ገድላት_አንደበት)

https://t.me/BateTewahdoEthio

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

15 Nov, 12:22


"ቁስቋም ማርያም" በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው ።

"የህፃኑን ነፍስ የሚፈልጉት ሞተዋልና ተነስ እናቱንና ህፃኑን ይዘህ ወደ እስራኤል ተመለስ።"#ማቴ_2÷19

ልመናዋ ክብሯ የልጇ ቸርነት በሁላችን በህዝበ ክርስቲያን ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን 👏

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

11 Nov, 19:08


🧕👉🏾 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች⁉️
👉🏾 ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን
👉🏾 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን
👉🏾 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን‼️
👉🏾 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል
👉🏾 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው
👉🏾 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው⁉️
👉🏾 ቁርባን ቆርበን ሕልመ ሌሊት እንዳይጸናወተን ምን ማድረግ አለብን⁉️❤️በማርያም ይህን ቻናል ይቀላቀሉ❤️
            👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

         ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █          
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
      
         👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
         👇👇👇
             🔔
     🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

🤗ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🤗
❤️ፊላታዎስ ሚዲያ❤️
👳🏽‍♂ በግሩም እና በተወዳጅ ዘማሪያን ይቀርባል ከታች
ባለው ሊንክ ሰብስክራቭ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
         👇🏽👇🏽

https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW

https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

11 Nov, 18:34


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

09 Nov, 18:50


ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ..

ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ  ስሙር  ተፈጸመ ናሁ አክሊል አክሊል  ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግስቱ

እነሆ በእመቤታችን ስም ተሰባስበን አበባ ይዘን ልጅዋን በአበባ እርስዋን በጽጌረዳ እየመሰልን የምንዘምርበት ያ የተወደደው የምስጋና የዝማሬ ወር አለፈ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ የጊዮርጊስ የክብር ዘውድ ነሽ! እያሉ በተመስጦ እንደ ቅዱስ ያሬድ የቅዱስ ያሬድ ልጆች ሊቃውንቱ  እናታቸውን ሲያመሰግኑ የሚያሳይ ግሩም (ማኅሌተ ጽጌ)

እመቤታችን ዘውድነቷ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን  ውዳሴዋን ቅዳሴዋን እየደገመ ስሟን እየጠራ ለሚማጸን በአማላጅነቷ በቃል ኪዳኗ ለሚያምን ሁሉ ዘውድ ናት!

ምዕመናንም ትምክህተ ዘመድነ! እያሉ ይዘምሩላታል፤ ያመስግኗታል! ድንግል ሆይ የባህርያችን መመኪያ ነሽ! ተስፋችን ነሽ! የድህነታችን ምልክታችን ነሽ! እያሉ በእናትነቷ ጥላ ስር ያሉ ምዕመናን ይዘምሩላታል! እርስዋም እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ትባርካቸዋለች!  ሁላችንም እናታችን ትባርከን!

ለእኛም ለልጆችሽ ሞገስ ሁኝን  አማላጅነትሽ ቃልኪዳንሽ አይለየን!!

https://t.me/BeteTewahdoEthio

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

08 Nov, 18:55


ጥቅምት 30
✞ ይህች ዕለት ለቅዱሱ ዮሐንስ መጥምቅ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::
<<በረከቱ ይደርብን።>>
https://t.me/zikirekdusn

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

06 Nov, 09:05


ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

04 Nov, 20:19


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

04 Nov, 20:12


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

08 Oct, 17:24


"ድንግል ሆይ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደው ልጅሽ ፊት የፈሰሰውን መሪር እምባ አሳስቢ " ድንግል ሆይ ክፉ በሆነ በሔሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ ለጻድቃን አይደለም ለእኛ ለኃጥአን አሳስቢ ለንጹሃን ያይደለ ለተዳደፍን ለእኛ አሳስቢ" አሜን ድንግል ሆይ አሳስቢልን

አባ ሕርያቆስ

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

01 Oct, 09:49


አማላጂቱ ሆይ፦ በጭንቅ፣ በኃጢአትና በበደል ውስጥ ያለን እኛ ምልጃሽን እንፈልጋለንና ይቅር ባዩ ተወዳጅ ልጅሽ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን፣ ይቅርታውንና ምህረቱን ይልክልን ዘንድ ለምኝልን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

01 Oct, 09:49


#መስከረም_21

#ብዙኃን_ማርያም

በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤

#ጉባዔ_ኒቅያ
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አር*ዮስ የሚባል መ*ና*ፍ*ቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህ*ደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አር*ዮስ ክህ*ደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአር*ዮስ ክህ*ደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአር*ዮስ ክህ*ደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡

ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡

፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮ*ስን አው*ግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡

#ዕፀ_መስቀል
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤

ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡

ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡

መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡

(በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው  - #ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረገጽ)

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

27 Sep, 09:24


መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው።
መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው።
መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው።
መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው።

መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው።
መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው።
መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው።

መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

22 Sep, 17:20


"መርዓዊ ሰማያዊ
መርዓዊት ሰማያዊት
ለእመ ገብረ በዓለ በዓለ
ይኑሩ በሰላም
ይኑሩ በፍቅር
ጸንተው ዘለዓለም!"

Congratulations Dn Abel Kassahun Mekuria 🎊

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

11 Sep, 11:10


" እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን!! "

አዲሱ ዓመት ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የተሰጠን ሌላ አዲስ እድል ነው። አማኑኤል ከእኛ ጋር ለመሆን የእኛን ሥጋ ተዋሕዷል፣ አምላክነቱ ሳያሳስበው የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አድርጉዋል። በደሃ ቤት አድሯል ፣ በበረት ተወልዷል፣ ከብርድ መከለያ ጨርቅን ፈልጓል ፣ ፍጥረትን የሚመግብ እርሱ ከእናቱ የድንግልናዋን ወተት ለምኖ አልቅሷል ፣ እንደ ሕፃናት በጉልበቱ ድኋል፣ ለእናቱ እየታዘዛት ጥቂት በጥቂት አድጓል። ከአደገም በኋላ ራሱን የሚሰውርበት ጎጆ ሳይኖረው በተራራ ተንከራቷል ፣ ተርቧል ፣ ከኃጢአተኞች በደረሰበት ተቃውሞ ተሰድቧል ፣ ተገፍቷል። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ሆኗል።

ከእኛ ጋር ለመሆን ብቻ ሳይሆን በእኛ ውስጥ ለመኖር በእለተ አርብ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ተሰጥቶናል። እኛስ ወደ እርሱ ሊያቀርበን ይህን ሁሉ ከሆነልን አምላክ ጋር ለመኖር ምን አደረግን? ንስሐ ገባን? ሥጋ ወደሙን ተቀበልን?

ከእግዲህስ በኃጢአት ያረጀ ማንነታችንን እንተው። አዲሱን ዓመት " ማለዳ ማለዳ አዲስ " ከሆነው ፈጣሪያችን ጋር ለመኖር ለራሳችን ብሩህ ተስፋ እንሰንቅ። እስኪ አምና ወድቀን ከተሰበርንበት የዘር ፣ የጥላቻ ጉድጓድ ወጥተን ዘንድሮን ተዋድደን ፣ ተፋቅረን በሰላም እንኑር። እስኪ ደግሞ ወደ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርበን ይህችን ዓመት በሰላም ጀምረን እንፈጽማት።

አዲሱ ዓመት የሰላምና  የፍቅር  እግዚአብሔርን  በቅንነት የምናገለግልበት ዓመት እንዲሆንልን እንመኛለን

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

11 Sep, 11:02


#መስከረም 1 - ርዕሰ አውደ ዓመት

#ዕንቁጣጣሽ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉና ተራ በተራ እንያቸው፡፡

አንደኛው በኖህ እና በልጆቹ ዙሪያ የሚያጠነጥን፡፡ ሴም፣ ካምና ያፌት ሶስቱ የኖህ ልጆች ናቸው፡፡ ኖህ አህጉራትን ለሶስቱ ልጆች አከፋፍሎ ሲሰጥ ለካም አፍሪካ ደረሰው፡፡ ካም ወደ አፍሪካ የገባው እና መጀመሪያ የረገጠው #ኢትዮጵያን ሲሆን ወሩም ምድሪቱ #በአደይ_አበባ ያሸበረቀችበት #የመስከረም ወር ነበር፡፡ በምድሪቱ ውበት በመደመሙና ይህ ዕጣም ለእሱ ስለደረሰው ተደስቶ “ዕንቁ ዕጣ ወጣልኝ” አለ፡፡ እንግዲህ እንቁጣጣሽ ለሚለው ቃል አንዱ የየት መጣ ሀሳብ /#Etymology/ እንዲህ የሚል ነው፡፡

ሁለተኛው ምድሪቱ በአደይ ፈክታ ሲመለከት #ዕንቁ_ዕፅ_አወጣሽ ከሚል ነው #እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ የመጣ የሚል ነው፡፡

በዚህኛው አካሄድ “ዕንቁ” ከኦይስተር ቅርፊት /pearl/ ውስጥ የሚገኝ ትንሽ ድቡልቡል፤ ጠንካራ አንጸባራቂ፤ ነጭ ውድ ጌጥ/ ለጌጥነት የሚያገለግል ነገር/ ሲሆን “ዕፅ” ደግሞ በግዕዝ የአማርኛው “ተክል” አቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተክሉን መልክ ከዕንቁ ጋር በማነጻጸር የምድሪቱን ውበት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው፡፡

ሶስተኛው ደግሞ #የቀዳማዊ_ምኒሊክ እናት ንግስት ሳባ ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሄደችበት ጊዜ ንጉሱ “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ” ብሎ መስጠቱን መሰረት አድርጎ የሚነሳ ሃሳብ ሲሆን ወሩም ወርሃ #መስከረም ነበር።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼  #መልካም_አዲስ_ዓመት🙏 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

03 Sep, 09:46


የአብርሃም የይሥሐቅ የያዕቆብ አምላክ ሆይ! ፍረድ!!!

#ጎንደር 😭

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

01 Sep, 13:22


“የ2016 ዓ.ም የመጨረሻ  #ዕለተ ሰንበት”

☞︎︎︎ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የ ዓለማት ሁሉ ገዢ ልዑለ ባሕርይ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣቸው አሐዱ ብሎ የጀመረበት ቀን እሑድ ነበር። ፍጥረታትን ፈጥሮ የጨረሰበትና ያረፈበት ቀን ደግሞ ቀዳሚት ሰንበት ነው።

☞︎︎︎ ዳሩ ግን በሐዲስ ኪዳን የጠፋውን አዳምን ፍለጋ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህች ምድር ሲመጣ የማዳኑን ሥራ አጠናቆ ሞትን በሞቱ ደምስሶ የሕይወትን ብስራት ያበሰረበት ለትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በክብር የተነሣው በዕለተ እሑድ ነውና ይህም እለት በሐዲስ ኪዳን ሰንበተ ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። እለቱን እንቀድሰው ዘንድም  "የሰንበትን ቀን አክብር" በማለት ትዕዛዝ ከኦሪት ጀምሮ በተሰጠን መሰረት ማክበር የክርስቲያኖቹ ሁሉ ኃላፊነት ነው።

☞︎︎︎ "ሰንበት" እረፍተ ነፍስ የምናገኝባት የገነት አምሳል ነውና እረፍተ ሥጋ እያደረግንበት ሰማያዊቷን ሀገራችንን በማሰብ ቀኑን ልናሳልፈው ይገባል።
💚💛❤️

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን 

             ꧁ የዓመት ꧂
               ꧁  ሰው ꧂
          ꧁  ❣️ይበለን❣️

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

17 Aug, 15:54


#ፍትሕ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ ለተገደለችው ለህጻን #ሔቨን!

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

15 Aug, 16:14


እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየውም።
                   { ማር 10÷9  }

ጋብቻን ባርኮና ቀድሶ ለሰው ልጅ የሰጠው እግዚአብሔር ነው። በመሆኑም ጋብቻ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለምና የምትረዳው ጓደኛ እንፍጠርለት ብሎ እግዚአብሔር ሔዋንን ከአዳም አካል ፈጠራት። ዘፍ ፪፡ ፲፰። አዳምም ከአካሉ የተፈጠረችውን ሰው አይቶ እንዲህ አለ፡ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋም ከስጋዬ ናት፤ እርሷ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።” ዘፍ ፪፡ ፳፫-፳፭። እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በመልኩ ፈጠረ። ወንድና ሴትም አድርጎ ፈጠራቸው። ከዚያም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፡ “ብዙ ተባዙም፣ ምድርንም ሙሏት፣ ግዟትም፣ የባህር አሦችና የሰማይ ወፎችን፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ግዟቸው።” ዘፍ ፩፡ ፳፮-፴፩።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ ተገልጦ ወንጌለ መንግስትን እየሰበከ በዓለም ላይ በሚዘዋወርበት ወቅት ጋብቻ እጅግ የተቀደሰ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በተቀደሰ ጋብቻ አንድ የሆኑ ተጋቢዎች በመንፈሳዊ ሕይወት የተሳሰሩ አንድ አካል መሆናቸውን ገልጿል፤ “የገዛ ሚስቱን የወደደ ራሱን ይወዳል፣ ማንም የገዛ ስጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና” ሲል ባልና ሚስት አንድ አካል መሆናቸውን መስክሯል። ኤፌ ፭፡ ፳፩-፴፫። በሌላ መልእክቱም በሕገ ቤተክርስቲያን የተፈጸመ ጋብቻ ንጹሕና ክቡር መሆኑን አስተምሯል። ዕብ ፲፪፡ ፩-፮። ስለዚህ በሥርዓተ ተክሊል ማለት በቤተክርስቲያን ሥርዓት የሚፈጸም ጋብቻ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም የተባረከ በመሆኑ ሊፈርስ አይገባውም።።

መራዊ ሰናይ መራዊት ሰናይ
ወመራቱ ትመስል ፀሐይ

እግዚአብሔር አምላክ የአባታችን የአብርሃም እና የእናታችን የሳራ ጋብቻ ያድርግላችኹ !!!

https://t.me/BeteTewahdoEthio

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

10 Aug, 18:29


✥ እንሆ የሱባኤው በረከት ✥

❖ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን አእምሮውን ልቡን በልቦናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡

ቅድስትን ጽሕት ጽንዕት ክብርት ልዩ ሲል ነው

♥️ንጽሕት አለ 

❖ ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነፁ ከሐልዮ አይነጹም፤ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ንጽሕት ናትና፡፡

♥️ጽንዕትም አለ

❖ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው፤  እርሷ ግን ቅድመ ፀኒስ፣ ጊዜ ፀኒስ፣ ድኅረ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ፣ ጽንዕት ናትና፡፡

♥️ክብርትም አለ

❖ ሌሎችን ሴቶች ብናከብራቸው ጸድቃንን ሰማዕታትን ወልደዋል ብለን ነው፤ እርሷን ግን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ብለን ነውና፡፡

♥️ ልዩም አለ

❖ እናትነት ከድንግልና አስተባብራ የምትገኝ ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡

በጾመ ፍልሰታ በሱባኤው ወቅት ያፈስነውን በረከት ያራገፍነውን ኃጢአት ወደኛ እንዳይቀርብ ሁሌ በክርስቶስ ቃል በቃለ ወንጌሉ እየለመለምን እያደግን እያፈራን ጠላታችንን ዲያብሎስ ድል መንሳት አለብን::

ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን፤ አእምሮውን ልቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
         ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን

https://t.me/BeteTewahdoEthio

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

06 Aug, 18:00


የእመቤታችን ወዳጆች እንኳን ለምንናፍቃት ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን።
      “ጾመ ፍልሰታ (ጾመ ማርያም)”

✝️ ፍልሰታ የሚለው ቃል "ፈለሰ" ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም "መለየት፣ ማረግ፣ ወደ ላይ መውጣት፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ" ማለት ነው

✝️ ጾመ ፍልሰታም የእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋዋ ከመቃብር መለየት እና ማረግን ተመልክቶ የሚጾም የዓመቱ የመጨረሻው የዓዋጅ ጾም ነው

✝️ እመቤታችን ካረፈች በኋላ ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ሴሄዱ አይሁድ "እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች፣ ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነው" በማለት ሥጋዋ እንዲቃጠል አዘዙ

✝️ ይህን ጊዜ መላእክት ሥጋዋን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ስር ወስደው አስቀመጡ

✝️ ሥጋዋ ያለበትን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው ሐዋርያት ከነሐሴ ፩ እስ ፲፬ ቀን ከጾሙ በኋላ ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ቀበሩ

✝️ በተቀበረች በ፫ኛውም ቀን እንደ ልጇ ተነስታ ስታርግ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከስብከተ ወንጌሉ ሲመለስ አገኛት፤ ያን ጊዜም ትንሣኤዋን ያየ እርሱ ብቻ መሆኑን ነግራው ሰበኗን ለምልክትነት ሰጠችው

✝️ የትንሣኤዋን ነገር ሳያዩ ቅዱስ ቶማስ ብቻ በማየቱ መንፈሳዊ ቅናት የተሰማቸው ሐዋርያት በዓመቱ ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው እስከ ፲፮  ቀን ማረጓን ያዩ ዘንድ ጾሙ

✝️ ለእኛም ይህ ጾም የሐዋርያትን ጾም ምሳሌ አድርገን  የእመቤታችንን እረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷን የምናስብበት ነው

➻ ከበረከትዋ እንድንካፈል፣ ምልጃ ጸሎታችን እንዲሰማልን በየዓመቱ ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፮ እንጾማለን።

የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን።

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

26 Jul, 10:25


"ገብርኤል ሆይ! ከጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክህ መልአክ ነህና ሠለስቱ ደቂቅ በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ ሁለቱ ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንሃቸው እኔንም አገልጋይህን በረድኤትህ ኃይል አድነኝ።"

[ መልክአ ገብርኤል ]

“ቅዱስ ገብርኤል ይጠብቀን የዓመት ሰው ይበለን”

✞︎ቤተ ተዋሕዶ/𝐁𝐄𝐓𝐄 𝐓𝐄𝐖𝐀𝐇𝐎𝐃𝐎✞︎︎︎❥︎𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨

25 Jul, 18:26


“ሐምሌ 19 (፲፱) የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል እንኳን አደረሳችኹ አደረሰን”

❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።

❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡

❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡

❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡

❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡

❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡

❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሦስት ዓመቱ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል።

❖ ጥር ፲፮ በ304 ዓ.ም. ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ሌሎችም በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡
ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ
ወስምዖ መጥበቤ
ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ
ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ
ለአባልከ ሰላም እቤ”
(እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ)  እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡

❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦
“ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ
በልደት ንዑስ፤
ንጹሕ ከመ ዕጣን
ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡
(በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል)

❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡
(ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨
[የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨

[ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ]


https://t.me/BeteTewahdoEthio

28,755

subscribers

1,395

photos

41

videos