🎤ቦርፎሪኮን🎸 @borforiconn Channel on Telegram

🎤ቦርፎሪኮን🎸

@borforiconn


♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm

🎤ቦርፎሪኮን🎸 (Amharic)

ቦርፎሪኮን ቻናል የቀናት አጠቃቀም አለው። ይህ ቻናል ኢትዮጵያን አስተያየት ለሆነ በሚከተለው ስለሆነ በእርስዎ ቤተሰብና ሀገር በሚጠቅምው ስነ ማፍራት ተመልከቱ። ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ እና በማፍራታዎ ላይ በቅድስና የተያዘ ነገሮች የሚሰጥ እና የወደ። በሚከተለው ስለ ሆነ ራሱን ፍቅር ያስገዛል። ስለዚህ ቦርፎሪኮን ቻናል መጽህፍት ይጀምራል። ማንኛውም እነሱን መልእክት ቢስፋፋው ለምን ይጠይቅ ከናንተ ጋር እና ለእኩል፦ @john11 አማርኛ ትግርኛ ፈን ማህበረሰብ፣ ማቴዎስ መዝሙር ፊልም እና እያንዳንዱን ምስል በወር ለማጠናከር እንዲረዳ ይህን ቻናል ተከተሉ። በእኛ ይበልኑ፣ ሁሉም በእኛ ተወካዮቶችን የቻናሉን አምባለሁ።

🎤ቦርፎሪኮን🎸

19 Nov, 05:15


https://youtu.be/lWTTkpqk38M?si=aytHyg5tnyvgKp3W

🎤ቦርፎሪኮን🎸

16 Nov, 16:43


የጠራ፣ የጠለቀና የተዘጋጀ የነገረ መለኮት ትምህርቱ ጠቅሞታል፡፡

በተጨማሪም፡- ዘመን ዘለቅ ስጦታ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን፣ ወንጌልን፣ ጸጋን፣ ሕግን … በተሻለ ሁኔታ ቤተክርስቲያንን ለመርዳት ሕያው አስተምህሮዎችን በጽሑፍ ያስተላለፈልን ነገረ መለኮትን በመማሩ ነበር፡፡ ስለዚህ የዛሬ የነገረ መለኮት ምሁራኖቻችን ከማርቲን ሉተር ተማሩ። እንማር፡፡ አንታበይ፡፡ ትሁታን እንሁን፡፡ በተማርነው የነገረ መለኮት ዕውቀታችን በቤተክረስቲያን የተሻለ ደሞዝ፣ የተሻለ ወንበር፣ ስም፣ ሹመት፣ ዝና … ለማግኘት ሳይሆን ቀይጥነትን፣ ዓለማዊነትን፣ ሥጋዊነትን … በቀጥታ በፍቅርና በቃሉ በመግጠም ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ እንነሳ፡፡ ተሐድሶ፣ ተሐድሶ፣ ተሐድሶ ።

ቀኑ የካቲት 18/ 1546 ማርቲ ሉተር በሞት አልጋ ላይ ሰዎች ከበውት እያለ ...እግዚአብሔር አንዲያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና" ደግሞም ነፍሴን በእጆችህ አኖራለሁ.." በማለታ የእምነት ጀግናው ወደቀጣዩ ዓለም በድል ተሻገረ።

🔥 ማርቲን ሉተር ሚስቱ ካቲ ሞታ የአስክሬን ሳጥኗ እንደተዘጋ- "ምስማሩ ገብቶ ዘጋው❗️በአዲሱ ቀን እንደገና ትነሣለች❗️"(wa.tr. 5:189)
እንዳለው እርሱም አንድ ቀን እንደገና ይነሣል❗️

ተባረኩ። አመሰግናለሁ፡፡
ሼር
ወንጌላዊ ጸጋአብ በቀለ

🎤ቦርፎሪኮን🎸

16 Nov, 16:43


መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦ "እግዚአብሔር፤ ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ" ("ኢሳ.66:2) ይላል። በቃሉ ብርሃን መገለጥ የሚሆነው እግዚአብሔር ስመለከተን፣ ዘንበል ሲልልን፣ የልብ ዓይኖች ሲበሩና ሓልዎቱ ስከበን ነው።

የነገረ መለኮት ፕሮፌሰር የነበረው ማርቲን ሉተር እንደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና አስተምህሮ በሥራ ለመጽደቅ እየታገለና እያስተማረ ብዙ ዘመን ቆየ፡፡ በዚህ ህዴት መዝሙረ ዳዊትን፣ ሮሜን፣ ገላቲያን፣ የዕብራውያን መጻሕፍት፣ በጥልቀት ሲያጠና ሲያስተምር ስለ እምነቱና ስለ ካቶሊክ እስተምህሮ ትልቅ ጥያቄ በውስጡ እንደተፈጠረ ይናገራል፡፡ የመዳኑ ጥያቄ እያለ የሮማ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በልቡ እርስ በርስ ሰጋጩ ተሰማው፡፡ ከዚህም የተነሣ "መዝሙረ ዳዊት፣ ገላትያ፣ ሮሜ፣ የዕብራውያን መጽሐፎችና የሮማን ካቶሊክ አስተምህሮ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እውነት መሆን አይችሉም" በሚለው ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡ ከዚያም ሮሜ. 1፡17 ሲያጠና እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ ዓይኖቹን አበራለት፡፡ በዚህ ድንቅ መገለጥና ግኘት መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ለማጥናት የነገረ መለኮት እውቀት እንደጠቀመው ለማንም ግልጽ ነው፡፡

ስለ እግዚአብሔር ለማወቅ መማርና ማንበብ ሲሆን እግዚአብሔርን ለማወቅ ግን መለኮታዊ መገለጥ ይጠይቃል፡፡ ያ ከሰማይ እንጂ ከነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ወይንም መጻሕፍት አይገኝም፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በገማሊያል እግር ሥር ቁጭ ብሎ መማሩ፣ የብሉይ ኪዳን ሊቅ ፈረሳዊ መሆኑ በሐዋ.9 ክርስቶስ እስኪገለጥለት ድረስ ዕውቀት ቢኖረውም መንፈሳዊ ዓይኖቹ አያዩም ነበር። ኢየሱስንም በሕይወቱ አያውቅም ነበር፡፡ ማርቲን ሉተርም እንደዚሁ ነበር፡፡

ሉተር እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ዓይኖቹን እንዳበራለት ሲናገር፡- "በራሴ መረዳት ወይም በጥንካሬ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን ወይም ወደ እርሱ ለመምጣት እንደማልችል፡ ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ በወንጌል እንደጠራኝ በስጦታዎችም እንዳበራልኝ፡ እንደቀደሰኝ፣ በእውነተኛ እምነት እንደሚጠብቀኝ አምናለሁ፡፡" ብሎዋል፡፡ (የቤ/ክ አዳሹ የሉተር ታሪክ 2011 ዓም ገጽ 213 )

✍️ ማርቲን ሉተር በዘመኑ ስለነበሩ ቄሳውስት ሲናገር፦

ኢየሱስ በዘመኑ የአይሁድ የሃይማኖት መሪ የነበሩ ጻሐፊት ፈረሳውያንን "የተሰወረ መቃብር የሚምሱ" (ሉቃ 11:44) መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት የሚዘጉ (ማቴ:5: 20) እንዳለው ማርቲን ሉተር ወንጌል እንደበራለት የሮም ካቶሊክ የቄሳውስቱና ርእሰ ሊቀነ ጳጳሱቱን ኑፋቄ፣ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ወግ፣ የሥነ ምግባር ቀውስና አደገኛ አካሄድ በአደባባይ ቃሉ ላይ ቆሞ ይቃም ጀመር፡፡

ስለ ቄሳውስቱም ሲናገር፡- "አቤት እነዚህ አሳፋር ሆዳሞችና የሆድ አገልጋዮች፣ የነፍሳት ጠባቂዎች ቄሶች ከመሆን ይልቅ የአሳማ መንጋ ወይንም የውሾች ጠባቂዎች ቢሆኑ ይመጥናቸዋል" ይል ነበር፡፡ (የቤ/ክ አዳሹ የሉተር ታሪክ 2011 ዓም ገጽ 214 )፡፡ ስለ ሮም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲናገር፡- "ቀደሚ ሲል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የክርስቶስ ተወካይ ነው ብያለሁ፤ አሁን ግን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የክርስቶስ ተቃዋሚና የዲያብሎስ ሐዋርያ እላለሁ፡፡ ... ጳጳሱ የክርስቶስን ሥልጣን ዘርፈዋል። ስለዚህ ሥጋ የለበሰ የክርስቶስ ተቃዋሚ ናቸው" (WA Br. 2:389) በማለት በግልጽ ተቃውሞውን አሰምቷል።

ዛሬ ከለባው፣ ከአጭበርባሪው በወንጌል ስም ከውሃ፣ ከዘይትና እራፍ ጨርቅ ሻጩ፣ በድንቅና ተአምራት ስም የመብለትና የአሮጊቶችን መቀነት ከሚፈቱ፣ ሌላ ወንጌል ከሚሰብኩት ጋር በጓዳ ኪዳን ገብተን በአደባባይ ተሐድሶ፣ ተሓድሶ ...የሚል የውሸት ሙዝሙራችንን ማርቲን ሉተር ምን ይለን ይሆን

✍️ ማርቲን ሉተር በዘመኑ ስላመጣው ተጽዕኖ ራሱ ሲናገር፡--

"በመጀመሪያ ደረጃ የሮማ ካቶሊካውያንን በገዛ መጽሐፋቸው በተለይም በቅዱሳት መጻሕፍት ሞግቻቸዋለሁ፤ …. ሁለተኛ የትኛውም ጉባኤ ሊነካው ያልፈለገውን ሁከትና ጸያፍ የነበረውን የስርየት ጽሑፍ ሽያጭ አስቆምኩ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ፡- ሃይማኖታዊ ጉዞንና የጣዖት መሠዊያዎችን ከሞላ ጎደል እቀርቻለሁ፡፡ …. በሌላ በኩል በእነዚህ ጊዜያት በዐሥራ አምስት ዓመት ወንድና ሴት ልጆች ከእነርሱ ከቀደሙት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የነበሩ ምሁራንና አስተማሪዎች ያወቁ ከነበረው በበለጠ ስለ ክርስትና አስተምህሮ እስኪያውቁ ድረስ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ አብዝቼ አስትምሬአለሁ፡፡"የቤ/ክ አዳሹ የሉተር ታሪክ 2011 ዓም ገጽ 215 )፡፡ ብሎዋል

ተሐድሶ፡- ከውሸት ጋር በመጋባት፣ ውሸትና እውነትን፣ ብርሃንና ጨለማን በማቻቻል፣ ደግሞ በማመቻመች፣ ከሁሉ ጋር በመወዳጀትና ሰውና እግዚአብሔርን አንድ ላይ ለማስደሰት በመጣሪ ሳይሆን እውነትን ይዞ ውሸትን በመጋፈጥና በመግጠም፣ በቃሉ ላይ በመቆም ብቻ እውን ይሆናል፡፡ የሉተር ግልጽነት፣ አቋም፣ እምነት፣ ዱካ፣ ድፍረት፣ ... የሚያስተምረን ይህ ነው፡፡

እውነተኛ ተሐድሶ በጸሎትና በመዝሙር ብቻም አይመጣም፡፡ በቃሉ ላይ በመቆም ቤቱን ባጨናነቁ ኑፈቄ፣ ንግድ፣ የተሳሳተ የጸጋ ስጦታ አጠቃቀምና የሥነ ምግባር ቀውስ ላይ በግልጽ መንፈሳዊ ጦርነትን መክፈት የግድ ይላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ "ጸልዩ" ወይንም "እወቁ" ብቻ ሳይሆን "መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል"(1ጢሞ.6፡12) "በእምነት ተቃወሙት"(1ጴጥ.5፡9)፣ የጨለማን ሥራ ግለጡት (ኤፌ.5፡11) በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ክፍ ያለውን ነገረ ሁሉ አፍርሱ (2ቆሮ.10፡5) ጸንታችሁ ቁሙ(ገላ/5፡1) … ብሎም እንዳዘዘን አንዘንጋ፡፡

✍️ የማርቲን ሉተር መወገዝና የፕሮቴስታንት ልደት

በመጨረሻም ማርቲን ሉተር እ.ኤ.አ ኖቨምበር 31/1517 95 የተሐድሶ ነጥቦችን ከቃሉ በማውጣት በዊተንበርግ ቤተክርስቲያን በር በመለጠፍ ቀይ መስመር በአደባባይ አሳየ፡፡

በቤተ ክርስቲያን በሞሉ አደገኛ ኑፋቄ ትምህርቶች፣ ልማዶችና በጳጳሳት ሊቅ የአኗኗር ዜይቤ ላይ ገሃዳዊ መንፈሳዊ ጦርነት ከፈተ፡፡ ታላቅ መንፈሳዊ ፍንዳታ በዓለም ላይ ሆነ፡፡ ወንጌል ለአንድ ሺ ዓመታት ከተያዘበት ዋሻ በኃይልና በድል ወጣ፡፡ በዚህም ማርቲን ሉተር አምስቱ "Solas - ብቻዎች"፡- 1. ድነት በእግዚአብሔር ቃል ብቻ፣2. ድነት በጸጋ ብቻ፣ 3. ድነት በእምነት ብቻ፣ 3. ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ 5. ድነት ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ በማለቱ ተወልዶ፣ አድጎ፣ ተምሮ፣ ለአገልግሎት ከተሾመበት ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተባረረ፡፡ በዚህም ፕሮቴስታንት(የሐሰት ተቃዋሚ) የተባሉ አብያተ ክርስቲያናት በዓለማችን ተወለዱ፡፡

ዛሬ 1.5 ቢሊዮን ፕሮቴስታንቶች በዓለማችን ላይ እንዳሉ መረጃዎች ቢጠቁሙም ከሉተር ዘመን በላይ ተሐድሶ በሚያስፈልጋቸው ብዙ ግሳግስ እንደተሞሉ ይነገራል፡፡

❗️ማጠቃለያ

የዶ/ር ማርቲን ሉተር ነገረ መለኮትን ተምሮ ማስተማር የጀመረው በሕይወቱ ክርስቶስን ከማወቁ በፊት እንደሆነ ተመልከተናል፡፡ የሉተር፡- ጥልቅ የነገረ መለኮት ምልከታዎች ለአገልግሎቱ ስኬትና ለቤተክርስቲያን ተሐድሶ እግዚአብሔር ተጠቅሞበታል፡፡ የነገረ መለኮት ጥልቅ እውቀቱን፣ ራሱን ዝቅ አድርጎ በትህትናና በፍቅር በእግዚአብሔር እጅ በማድረጉ ለዘመናት የፈረሰውን ድልድይ ገንቢ አድርጎ እግዚአብሔር በኃይል ተጠቅሞበታል፡፡ ማርቲን ሉተር በቃሉና በመንፈሱ በመደገፍ ገለባን ከፍሬው፣ ብርሃንን ከጨለማ፣ የአጋንንትን፣ የሥጋን፣ የመንፈስ ሥራዎችን በመለየት ረገድ የሰከነ፣

🎤ቦርፎሪኮን🎸

16 Nov, 16:43


መጽሐፍ ቅዱስ ተሰወሮበት የነበረው የመጽሐፍ ቅዱስ
ኘሮፌስር ማርቲን ሉተር ❗️

✍️ የሉተር ልደት፣ ትምህርትና የገዳም ሕይወት

የኘሮቴስታን ተሐድሶ አባት የተባሉ ጀርመናዊው ዶ/ር ማርቲን ሉተር የተወለደው በኖቨምበር 10/1483 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1501 በላቲን ሥነ ጽሑፍና በፍልስፍና ከኤርፍርት ዩኒቨርሲቲ ፣ በማስተርስ ዲግሪ የተመረቀው ገና በለጋ ዕደሜው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1507 በሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህን ሆኖ ተሾመ፡፡ ማርቲን ሉተር ብሩህ አዕምሮ የተቸረው ወጣት፣ ብዙ የፍልስፍና ሥራዎችን ያጠናና የቤተክርስቲያንም ካህን ቢሆንም ወንገል ያልገባው "በሞት፣ በመለኮታዊ ፍርድና በገሃነም ፍርሃት" ይሰቃይ እንደነበር ታሪኩ ያወሳል።

ከዚያም የሞት ፍርሃት ለማምለጥ ሁሉን እርግፍ አደርጎ በመተው መነኩሴ ሆኖ በኤርፎርት የቅዱስ ኦገስትን ገዳም ገባ፡፡ ከተሰማው የነፍስ ፍርሃት ለማምለጥ ዕለት ዕለት በኑዛዜ፣ በብርቱ ጾምና ጸሎት፣ ሥጋውን በመጨቆንና በመልካም ሥራ ለመጽደቅ ይታገል ነበር፡፡ ውስጡ ግን እረፍት አልነበረውም (Here I Stand: a Life of Martin Luther. New York: Penguin, 1995, 40–42.)፡፡

መናኝ ሆኖ ለነፍሱ ጩኼት በገዳም እየታገለ በነበረበት በዚያን ወቅት ከዊተንበርግ ዩኒቨርስቲ በbiblical studies ሁለት ዲግሪ ከዚያም የዶከትረት ዲግሪ አግኝቶ በዊተንበርግ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮት ፕሮፌሰር ሆኖ ያስተምር እንደነበር ታሪክ ይመስክራል (James L. Schaaf, Philadelphia: Fortress Press, 1985–93, p. 93)::

ሉተር ስለዚያ ጊዜ በሕይወቱ ስለነበረው ጨለማና ባዶነት ሲናገር፡- "I lost touch with Christ the Savior and Comforter, and made of him the jailer and hangman of my poor soul." (Luther The Reformer. Minneapolis: Augsburg Fortress Publishing House, 1986, 79. ብሏል፡፡ የፍልስፍና፣ የቋንቋና የነገረ መለኮት ፕሮፌሰር መሆኑ በልቡ ከተፈጠረው ቀውስና ባዶነት አልታደገውም፡፡ ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እግዚአብሔርን በሕይወት ማወቅ አይደለምና፡፡

ማርቲን ሉተር የነገረ መለኮት ዶ/ር ቢሆንም በኢየስሱ ክርስቶስ የቤዛነት ሥራ ላመኑት ሁሉ ቃሉ "አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና" (ሮሜ.8:15) የሚለው ቃል አልበራለትም ነበር። ደግሞም "ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም"(1ዮሐ.4:18) አልተገነዘበሞ ነበር።

✍️ ዛሬም በነገረ መለኮት ዕውቀት መጥቀው ክርስቶስ አልባ ልቦች

ብዙዎች ዛሬም እንደ ኢየሱስ ዘመን አይሁዶች ከኢየሱስ ይልቅ ስለ አየሱስ በሚናገሩት መጻሕፍት ላይ ልባቸው ወድቆዋል። መንፈሳዊ መጻሐፍት መልካም ናቸው የአዕምሮ ዕውቀት ብቻ ሆነውብን ክርስቶን በሕይወታችን ካልገለጡ ግን አድካሚ ሸክም ናቸው። ለዚህ ነበር ኢየስሱስ በቶራ የሕግ መጻሕፍት ዕውቀት ተደግፈው እርሱን ለገፉት ለአይሁድ የነገረ መለኮት አዋቂዎች- "እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም። "(ዮሐ.5: 39-40) ችግራቸው መጽሐፉን ያነበንቡታል እንጂ አያምኑበትም። ዛሬም ችግሩ ተመሳሳይ ነው።

አንድ ሰው በሕይወቱ ክርስቶስን የግል ብቸኛ አዳኙ አድርጎ አምኖ ተቀብሎ ሳያርፍ የነገረ- መለኮትን ሊቅ፣ ቀማር፣ መምህር መሆን እንደምችል የሉተር ሕይወት ትልቅ ምሳሌ ነው። ዛሬም ጌታን በሕይወታቸው የማያውቁ ወይም የማያሳዩ በነገረ መለኮት እውቀታቸው፣ የመቀመርና የመተንተን ችሎታቸው እጅግ የላቁ፣ ያልታረመ ሕይወት ይዘው የሰዎችን ሰብከትና ትምህርት ለማረም የበረቱ፣ የቃሉ ሊህቃኖች በአብያተ ክርስቲያናት፣ በዓለማችን ዕውቅ ሰሜነሪዎችና የቲኦሎጂ ትምህርት ቤቶች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ እውቀታቸው መልካም ነው፤ ሕይወታቸው ግን ዕውቀታቸውን አይመስልም፡፡ ሲያገለግሉ አይታዩም ሲተቹ አይደክሙም፡፡ በእውቀት የገነቡትን በሕይወት ያፈርሳሉ፡፡ በዘመናችን ይህ አንዱና ትልቁ የቤተክርስቲያን ፈተና ሆኖዋል። ብዙዎቻችን ነገረ መለኮት የተማረ፣ በአመክንዮ የሰላ አዕምሮና አንደበት እንጂ ጨውና ብርሃን ሆነን ከሩቅ የሚስብ ሕይወት የለንም፡፡

አዕምሮአችንን አራሚ፣ መርማሪ፣ ጠያቂና መላሽ ብቻ አድርጎ የሠራ የነገረ መለኮት ትምህርት የወንጌል ሰባኪ፣ አስተማሪ፣ መስካሪና በሕይወታችን ክርስቶስን ለዓለም ካልገለጠ ተምረናል ለማለት ካልሆነ በቀር ዋጋ የለውም።

✍️ ከአዕምሮ እብጠት የተሰበረ ልብ ይቅደም❗️

ልቡ በጌታ ፍቅር የተነካና የተሰበረ ሰው በአዕምሮ ዕውቀት መታበይ አይችልም። መስቀልና መታበየ አብረው አይሄዱምና። የጠራ፣ ክርስቶስ ተኮር፣ ለተግባራዊ አገልግሎት አጋዥ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ምሪት የተደገፈ የነገረ መለኮት ትምህርት ለቤተክርስቲያን አማራጭ የለሌው መለኮታዊ ስጦታና አቅም ነው። በዓለም ላይ ያለው ሊብራል(ለቀቅተኛነት) አመለካከት ብዙ የነገረ መለኮት መምህራንን፣ ተማሪዎችንና ትምህርት ቤቶችን እየመታ ንዝረቱ በቤተክርስቲያን መድረክም ላይ በገሃድ እየተሰማ ነው። በወሳኝ ጉዳዮችና ጥያቄዎች ዙርያ ማመቻመች፣ በአንድ ጊዜ ሁሉን ማስደሰት መሞከር፣ መቀየጥ ...የሊብራል አመለካከት ተጽዕኖዎች ናቸው።

ከ40 ዓመታት በላይ በዓለማችን እውቅ የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ያስተማሩ ፕሮፌሰር ኢግሁን አች. ፔትርሶን "Subversive Spirituality 1994" በሚል መጽሐፋቸው፡- "የሰሚኔሪ ትምህርት አደገኛ ነው፡፡ ብዙዎች በመማሪያ ክፍልና በቤተመጻሕፍት ክፍል ውስጥ እምነታቸውን አጥተዋል" ብለዋል፡፡ ይህ እጅግ ያስደነግጣል፡፡ ቤተክርስቲያን ቃሉን ተምረው መጥተው ያስተምሩኛል ብላ ወደ ሰሜነሪ የላከቻቸው ተማሪዎች እምነታቸው ጥለው ዲግሪ ይዘው ሲመጡ

እኚህ እውቅ የዘርፉ ፕሮፌሰር የነገረ-መለኮት ትምህርት እያጣጣሉ ወይንም እየተቃወሙ ሳይሆን አዎንታዊ ጥቅሙ ብቻ ሳይሆን አሉታዊ ተጽዕኖውንም ለማሳየት ፈለገው ነው፡፡ ይህም ነገረ-መለኮት እንዳይበረዝ ተግተን መጠበቅ፤ ደግሞም መማርና ማስተማር ብቻውን የሰውን ሕይወት እንደማይለውጥ በግልጽ ያሳያል፡፡ እውቀት ጥሩ ነው፤ ከሕይወት ጋር ካልሄደ ዋጋ የለም፡፡ ሚዛናዊ መሆን ያሻል፡፡

ማርቲን ሉተር በእውነት የነገረ መለኮት ትምህርት መማር ማለት ምን እንደሆነ ሲናገር፡- "አንድ ሰው የሥነ መለኮት ዐዋቂ የሚያደርገው ማወቁ፣ ማንበቡ፣ ወይንም ማመዛዘኑ ሳይሆን መኖሩ፣ እንዲያው መኖሩ ሳይሆን ለራሱ መሞቱና በሕይወቱ ሌላውን መኮነኑ ነው" (WA 2:28b) ብለዋል፡፡

በአጭሩ ከዕውቀት፣ ከማንበብ፣ ከማመዛዘንና ከመተንተን ችሎታ ይልቅ ነገረ መለኮት መማራችንን በሕይወት፣ ለራሳችን ምኞትና ፈቃድ በመሞትና ሌላው ምሳሌ በሚሆን ሕይወት መግለጥ ነው ይለናል፡፡ ወገኖቼ፡- እኛ ምን እንመስላለን? በተለይ ነገረ መለኮትን የመማር ዕድል ያገኘን ሰዎች?

✍️ ለማርቲን ሉተር የእግዚአብሔር በቃሉ መገለጥ❗️

🎤ቦርፎሪኮን🎸

05 Nov, 20:51


https://user266117.psee.ly/6nebxc

🎤ቦርፎሪኮን🎸

05 Nov, 04:12


https://youtu.be/sbN0nL1rtUQ?si=xdi1QAzx0NS835h4

🎤ቦርፎሪኮን🎸

02 Nov, 19:25


🎤ቦርፎሪኮን🎸 pinned Deleted message

🎤ቦርፎሪኮን🎸

28 Oct, 14:57


https://youtu.be/XTYe7IjX1Eo

🎤ቦርፎሪኮን🎸

27 Oct, 10:58


https://user266117.psee.ly/6m32mg

🎤ቦርፎሪኮን🎸

19 Oct, 10:54


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🎯 የእግዘብሔር ቃልና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች❗️
"ዋናው የእግዚአብሔር ቃል ነው" ብለው ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ከስጦታዎች በተለየ መጽሐፍ ቅዱስ የማስተማር ዕውቀትን በመተንተን ስጦታ ብቻ ከሚደገፉ ከተማሩ አገልጋዮች፤ እንዲሁም "ዋናው የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ስጦታዎች መገለጥ ነው" በማለት በእጃቸው ከሚገለጠው አንዳንድ ምልክቶች የተነሳ ከእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት ጋር ሊያፋቱን ከሚከጅሉ ካልተማሩ አገልጋዮች እጅግ እንጠንቀቀ። ሚዛንን የሳቱ ሚዛን እንዳያስቱን እንጠንቀቅ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ በቁንጽል መረዳትና ልምምድ ላይ ቆመን መጽሐፉንና ደራሲውን የማለያየት እብደት ውስጥ አንዳንገባ እጅግ እንጠንቀቅ። ለራስ ግራ ተጋብተን ትውልዱንም ግራ አናጋባ። በትህትና፣ በፍቅርና በወንጌል ላይ ትኩረት በማድረግ እንጂ በውድድር ሜዳ እግዚአብሔር አይገኝም። በዚህ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ትምህርትና የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ስጦታዎች ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እኩል ስለሚያስፈልጉን ሁሉንም የሰጠን ጌታ ይባረክ። ሚዛናዊነት❗️

✍️ እውነት በቃሉ እንጂ በትፎዞ ብዛት አይጸናም❗️
ወንድማችሁ
ወንጌላዊ ጸጋአብ በቀለ

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

🎤ቦርፎሪኮን🎸

16 Oct, 13:58


🎤ቦርፎሪኮን🎸 pinned Deleted message

🎤ቦርፎሪኮን🎸

12 Oct, 11:54


https://user266117.psee.ly/6jrsz9

🎤ቦርፎሪኮን🎸

09 Oct, 01:01


https://user266117.psee.ly/6j9py4

🎤ቦርፎሪኮን🎸

06 Oct, 12:06


https://youtu.be/oLIKvQkzMvo?si=HyoVlwSDbmgbn4j_

🎤ቦርፎሪኮን🎸

02 Oct, 19:58


https://user266117.psee.ly/6hlfzv

🎤ቦርፎሪኮን🎸

28 Sep, 04:31


🎉በሰአታት ውስጥ ብቻ ብዙዎች ጀምረውታል!🎉
list day ሳይጠብቁ በየሳምንቱ እስከ200$ መስራት ይችላሉ የተረጋገጠ ቶሎ ሚከፍል Airdrop ነው!

Start ይበሉና spin ይበሉት ከዚያ የሚመጣላችሁን Gift ተቀበሉ አለቀ!
                                                       
ለመጀመር⬇️⬇️
https://t.me/lucky_gems_official_bot/app?startapp=27VfppY93oGUXdpBk6c85HmvWobK7xPVoNnRtJHpLYe3wjR

🎤ቦርፎሪኮን🎸

17 Sep, 18:55


https://user266117.psee.ly/6flj7v

🎤ቦርፎሪኮን🎸

14 Sep, 19:05


https://user266117.psee.ly/6fbb9b

🎤ቦርፎሪኮን🎸

13 Sep, 06:03


https://user266117.psee.ly/6f79hp

🎤ቦርፎሪኮን🎸

10 Sep, 10:19


https://youtu.be/0GofUoP4JVc