اقرأ (አንብብ ) @anbeb_islamic Channel on Telegram

اقرأ (አንብብ )

@anbeb_islamic


☞ዒልም ከባድ ሀላፊነት ነው። ሀላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የፈለገ ሰው ዒልሙን ወደተግባር ሊቀይረው እንድሁም ያወቀውን በቻለው አቅም ለሌሎች ሊያስተላልፍ ይገባል።
«ያ አላህ! ባልሰራበት እንኳ ወደ በጎ ነገር ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ።»🙏

ሀሳብ እና አስታያየት ካላቹ @ibro_smile
ወይም @anbeb_islamic_bot ላይ ማካፈል ትችላላችሁ

اقرأ (አንብብ ) (Amharic)

በላሊበር ደሞዝ ውስጥ የተሳሰረ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የቴሌግራም አስተካክል እና ንግድ አገልግሎት አለው። "አንብብ" የእርሱ የሬሳ ቦታ ነው። ይህ ቦታ ሀላፊነት በእንቅስቃሴ መሆን የሚችል ነው። የሀላፊነትን በሚዋጋበት አስታይ ተግባራት ዙሪያ ነው።nnሀላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የፈለገ ሰው በዒልሙን ማገልገል ያወቀውን በቻለው አቅም ለሌሎች ይሆናል። ሀሳብን እና አስታያየትን በማንበብ ሊቀይረው ይገባል።nnበቻለው ቦታ ለወረቀው ብልጣሪ ሰው ያነንላችኋል ፣ በስምምነት ሲፈልግና የተላከለውን እውቀት እንዳልነበረም መብት ይሆናል። እንደአንብብ ቦታ ከሴቶች የሚስባረም ባህር ሁሉ ይከታተሉልና አገልግሎት ማበልዩን በማወቅ የሚያከናውን ይለውጥ።nnየዒልሙን በቻለው ላይ ለትም ላይ ከሚገኘው በአግባቡ የሚጻፈው የጊዜያት መረጃ ሰፊው ወቅት፣ ጥንታዊ መረጃዎች፣ ሀላፊነን ለመጠቀምና በራሱ ራስ እና ጥበቃለት ነው።nn"አዲሱን የአንብብ ጊዜ፣ አገልግሎትን በመሸፈን እና በአስተምህሮ ሥርዐት ከመስጠት በፊት ይረዳል።"

اقرأ (አንብብ )

11 Jan, 03:00


በምትችለው ልክ ሰዎችን ከረዳህ ሰው ነህ ... ከራስህ አጉድለህ ሰዎችን ከረዳህ ጥሩ ሰው ነህ ።🥰

اقرأ (አንብብ )

11 Jan, 03:00


 Daily therapy 287🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

10 Jan, 18:15


የረመዷን ቀዷ ያለባችሁ ሰዎች ...አሁንም መፆም አልጀመራቹም🥴

اقرأ (አንብብ )

10 Jan, 16:21


እንዴ ደሞ ሳልነግራችሁ ሀረማያ ዩንቨርሲቲ ገባሁላቹ ያው አሁን ብቻዬን ተጋድሜ እያዛኩ ነው😊

اقرأ (አንብብ )

10 Jan, 09:38


ምንም ነገር ለዘላለም አይቆይም ...  ጠንካራ ከሆንክ አንድ ቀን ትደክማለህ። ጥንካሬህ ሚዘልቅ አይደለም:ሀብትህንም አትመነው  ጊዜያዊ ነዉ ይጠፋል። መልክህም,መልክሽም ለጥቂት ግዜ ነው።  በዚህ ምድር ላይ ቋሚ ነገር የለም። ሁሉም ይጠፋል !!  ስለዚህ ለማይጠፋውና ዘላለማዊ ለሆነው ለምርጡ ሀገር ለጀነት እንልፋ ።       
    
መልካም ጁመዐ

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

10 Jan, 02:37


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ».

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

10 Jan, 02:36


Daily therapy 286🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

09 Jan, 20:21


📲አዲስ አፕ ተለቀቀ 𑁍

የሶስቱ አሕካሞች ማብራሪያ

በኢብኑ ሀሽም(امير هاشم) የተዘጋጀ
t.me/IbnuHashm    

ሙሉ ማብራሪያ የተሰጠባቸዉ ፀሁፎች በአንድ ላይ ሰብስቦ የያዘ!
አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ!

اقرأ (አንብብ )

09 Jan, 10:43


ትርርብ ቀንሱ!

ትርርብ እና መዘዙ
@anbeb_islamic
ዝም ብዬ ሳስተውል ብዙ ሰውን አንቆ ከያዘ ነገሮች ውስጥ አንዱ ምን እንደሆነ ታቃላችሁ? በጓደኞች መካከል ያለ ትርርብ።ከድሮ ጀምሮ ያየሁት ነገር ትርርብ በጣም ብዙ ሰውን በሼም እንዲቀመጥ ያደርጋል።

የሆነ ነገር ልትሞክሩ ፈልጋችሁ መጀመሪያ ምትፈሩት የቅርብ ጓደኞቻችሁን ነው።እነሱ ከሚያውቁት ማንነት ውጪ ለማምጣት ሙከራ ካደረጋችሁ ቀልዱን አትችሉትም።በተለይ የከተማ ልጆች ላይ ይበዛል።ምን አልባት በመጥፎ ስሜት ላይሆን ይችላል።just ጨዋታ ሊሆን እንደሚችል ይገባኛል።

ግን ቀልድም ቢሆን still ሰው ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።ደግሞ ቀልዷ ላይ የሆነች እውነት አለች።በመጀመሪያ ቀልድ ራሱ ሚያስቀው የሆነች እውነት ካለችበት ነው፡፡
ቋጣሪ ሰው ላይ ቀልዳችሁ ቀልዱ እንዲያስቅ ከተፈለገ እውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።ስለዚህ እውነት መሆኑ ነው ሚያስቀው።እውነት ከሆነ ደግሞ ሚተረበው ሰው ላይ ተፅዕኖ አለው።

በመሰረታዊነት ትርርብ ችግር የለውም።እንደውም አንዳንዴ ጥቅም አለው።ያለባችሁን ችግር እንድታስተካክሉ ያረጋል።

እኔም ተተርቤ ያስተካከልኳቸው ነገሮች አሉ።በጓደኞች መካከል ምክር ሊያስጨንቅ ስለሚችል ትረባ ነው ሚያስካክላችሁ።ለጨዋታም ደግሞ ትርርብ ደስ ይላል።እየተፈራሩ ጓደኝነት የለም።

ግን አዲስ ነገር እየሞከረ እየጣረ ያለ ሰው ላይ ትረባ አይነፋም።በተለይ ስራ ነክ ነገሮች ላይ።ሊስቅ ይችላል ሚተረበው ሰው ግን እውነት እንነጋገር ከተባለ ፈሪም ያደርገዋል።
እኔ አሁን class ጨርሼ ነው እንጂ ቲክቶክ የጀመርኩት ባልጨርስ ኖሮ አልጀምርም ነበር።ምክንያቱም እስከሚሳካላችሁ ድረስ class ውስጥ ትረባውን አትችሉትም።

እንደዛውም ቢሆን ትረባው አልቀረልኝም።'ፓ ደግሞ ይህን ጀመርሽ አደል? አልተቻልሽም'' ያሉኝ ልጆች አሉ።ይቺ አሁን ጨዋታ ናት እኮ።ግን still የcomment ላይ ስድብ በምን ጣዕሙ።

አሁን የሆነ አዲስ ነገር ሊጀምር ፈልጎ ጓደኞቹን እና የሚያቀውን ሰው ፈርቶ የተቀመጠ ሰው ቤት ይቁጠረው! ''እሺ….እንደዚ ሆንሽ ደግሞ  '' ምትለዋ ንግግር ብቻ ምታሳፍረው ሰው አለ።

ከጀመረ ደግሞ ለጓደኞቹ አይናገርም።ድንገት የሆነ አጋጣሚ ላይ ነው ሚያዩት።ከዛ ሲገናኙ ጉዱ ፈላ  ....እና ባጭሩ ትረባ ቀንሱ ልላችሁ ነው ምፈልገው።እናንተን ፈርቶ አርፎ የተቀመጠ ሰው አለ።

እኔ ካነበብኩት አካፍያለው እናንተም ሼር
✍️ibro smile

@ANBEB_ISLAMIC
@ANBEB_ISLAMIC

اقرأ (አንብብ )

09 Jan, 04:34


እንደ መስታወት ብንሆን እመኛለው ..

የመጡ ሰዎች ማግኘት ለሚፈልጉት ነገር ሁሉ ብቁ ሆነን ..ማየት ለፈለጉት ነገር ሁሉ አይን ሆነን ልክ ሲሄዱ እንደነበርነው ብንሆን...ምንም ባንጎድል እመኛለው ። በመምጣትም በመሄድም ውስጥ የማንቆረስ ብርቱ ብንሆን ...ለሰዎች ጠቃሚ እንጂ ጥቅም ፈላጊ ባንሆን....ጠንካሮች ብንሆን እመኛለው ።

እስቲ እንሞክረው ..አያቅተንም!🥰

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

09 Jan, 04:33


Daily therapy 285🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

08 Jan, 18:42


አረ ሰዎች ብርድ ልብሴም አንሶላዬም እየበራ ነው😭 ልብሴ ሳይቀር እየነዘረኝ ነው
በemhal ስቄ እኔም ደረሰብኝ😅

اقرأ (አንብብ )

08 Jan, 17:57


በነገራችን ላይ ደስታም ፈገግታም ያምርባችኋል!😍😍

اقرأ (አንብብ )

08 Jan, 17:39


« አንቱ ሰው ልክ ነኝ ስል ሰዎች ተሳስተሀል ይሉኛል። ተሳስቻለው ብዬም ስል ልክ ያሰኙኛል። አንቱ ሰው ምን ላድርግ? »
« የኔ ልጅ  ፈፅሞ የማይሳሳተው አላህ ዘንድ ብቻ ልክና ስህተትህን መዝን። ይህን ልብ በል! ባልተገባ ቦታ የተገኘ ልክ በተሳሳተ ቦታ ላይ ልክ ከተደረገ ስህተት ያንሳል። »
« አንቱ ሰው እወዶታለሁ! »
« አል ሀቅ ይጠብቅህ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

08 Jan, 08:36


reposted

አንዳንድ አደራዎች ሲቀመጡ አትንኳቸው ...አትጠቀሟቸው ሳይሆን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው ተንከባከቧቸው ነው ። ምናልባት ነገሩ ከባድ ይሆናል...በአግባቡ ለመጠቀም ጥንካሬና እምነት ይጠይቅ ይሆናል ....ለኔው ፤ የኔው በሚል አመለካከት አላግባብ አደራውን ልናጎድል እንችላለን ። ግን አደራ ያለን አካል ክብሩ ልባችን ላይ ካለ አደራውን ለመጠበቅ ምንም አይነት መስዋዕትነት መክፈል እንችላለን ! አይደለም ስሜትን ሞትን እንጋፈጣለን ። ከነዛም ውስጥ ከታላቁ ሰብ ከጌታው ተወዳጅ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ  የተሰጠን አደራ አንዱ ነው ...እሱም ሴት ልጅ ናት።

አደራን መናቅ እና መጉዳት ለአደራ ሰጪው ካለን ክብርና ውዴታ ጋር ይገናኛል .....ለነሱ ባለን እዝነት ውስጥ ለረሱል ያለን ክብር ይገለጣል ። ለአንድ ኡማ መስተካከል እና መበላሸት ሴትልጅ ትልቅ ተፅዕኖ እያላት በሷ ላይ መጥፎ አሻራን ማሳረፍ በዲኑ ላይ በተዘዋዋሪ መጥፎ አሻራ ማሳረፍ ነው ። አደራ በተሰጠችው አካል መሳደድ አደራ በተሰጠችው አካል መሠበር ...መጎዳት ላይ ከሆነች ይህ የሚያሳየው የአደራውን መበላት ነው ።

አሳዛኝ ባለአደራዎች ነን !

[ባለዕዳው]
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

08 Jan, 02:37


ብታመሰግኑኝ በእርግጥም እጨምርላችኋለው ብሎናልና አልሃምዱሊላህ በማለት ውሏችንን እንጀምር!

አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን🥰

اقرأ (አንብብ )

08 Jan, 02:29


Daily therapy 284🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Jan, 17:51


አባት ከአምስት ሴት ልጆቹ ጋር ይኖራል

ለትዳርም ስለደረሱ አባት ከታላቋ ጀምሮ በቅደም ተከተላቸው እንዲያገቡለት ይፈልጋል

ታላቋ ግን አባቷን መንከባከብ በመፈለግ ማግባት አልፈቀደችም ታላቋ ብቻ ስትቀር አራቱ ልጆቹ አገቡ።
.
እሷም አባቷ አጀሉ ደርሶ እስኪሞት ድረስ ተንከባከበችው ። አባት ከሞተ በኃላ ግን ይቺ ሴት ብቻዋን ቀረች ።

የአባታቸውንም ኑዛዜ አገኙ እሱም " አደራ ራሷን መስዋዕት ያደረገችው እህታችሁ ሳታገባ ቤቱን እንዳትካፈሉ " የሚል ነበር.../
ነገርግን አራቱ እህቶች የትልቅ እህታቸውን ጉዳይ ቦታ ሳይሰጡ ተሽጦ መከፋፈልን ፈለጉ።

ትልቋ እህታቸው ቤቱን እንደሚሸጡት ስትረዳ ለመግዛት ለተስማማው ሰው በመደወል ከምትኖርበት ቤት ውጭ ሌላ እንደሌላትና ያለውን ሁኔታ አስረድታ ነገሮችን እስክታስተካክል ድረስ ጊዜ እንዲሰጣት አስፈቀደች ። ቤቱን የሚገዛውም ሰውም ፍቃደኝነቱን ገለፀላት።

ቤቱ ተሽጦ ለአምስቱ እህቶች ተከፋፈለ። ከተከፋፈለ በኃላ አራቱ ወደ ትዳራቸው ተመለሱ ታላቋ እህታቸው ከቤት ቀረች። ይቺ ሴት ወላጇን በመንከባከብ ባሳለፈችው ጊዜ አላህ ልፋቷን በዱንያም ከንቱ እንደማያስቀርባት ተማምና በአላህ ተስፋ አድርጋለች።

ወራት አለፉ ቤቱን ከገዛው ሰው ስልክ ተደወለላት ቤቱን እንድትለቅ መልክት እንደሚያስተላልፍ በመገመት በፍራቻ 'ይቅርታ እስካሁን ቤት አላገኘውም' አለችው።

እሱም ችግር የለም! የደወልኩም ለሱ ሳይሆን ቤቱን 'መህር' አድርጌ እንድታገቢኝ ልጠይቅሽ ነው ፍቃድሽ ከሆነ ባልሽ እሆናለው ፍቃደኛ ካልሆንሽም ችግር የለም! ቤቱ ግን ያንቺ ነው አላት ።

ይቺ ሴት አለቀስች! ተስማማችም አላህም የመልካም ሰሪዎችን ምንዳ ከንቱ አያስቀርምና በመልካም ተካሰች ።

አባቷን በተንከባከበችበት ቤት ትዳር ይዛ ባሏን መንከባከብ ጀመርች። 💍💍

ጌታችን ሆይ ! በየቤቱ ያንተን ተስፋ ብቻ የሚጠባበቁ እህቶች አሉና መልካምን ትዳር ወፍቃቸው/💍
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Jan, 10:11


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ....




ስለሙ! ወላሂ ብትሰልሙ ነው ሚሻላቹ ሰላማቹን እንድታገኙ ሀቅን ፈልጉ
😄
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Jan, 03:30


« ከመለየትም አብረው እየኖሩ አብሮነት ማጣት ይከፋል። መሄጃ ከማጣት የበለጠ ሰው አለው እየተባሉ ብቸኛ መሆን ውስጥን ያቆስላል። ከመግገፋትም አይጥለኝም ብለው የተደገፉት ሸርተት ሲል አደብ ያሳጣል። ከስቃይም ነበርን ከቀደር ማስበለጥ ይበልጥ ያሰቃያል። ከመራመድ ሁሉም የትላንት ውድቀት ላይ አለመቆየት ይበልጣል።
ከሚገኙ ነገሮች ሁሉም አላህ የመረጠውን መቀበል ሰላም ይሰጣል። »🥰
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Dec, 17:38


መልካም ብትናገር ታተርፋለህ
ዝም ካልክ ደግሞ ትተርፋለህ_
እንደመጣልህ ካወራህ ትጠፋለህ

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Dec, 13:04


አንዲት አባቷ የመስጂድ ኢማም የሆነች ልጅ ነበረች። ልጁ በቁንጅናዋ ተማርኮ ዚና እንዲሰሩ ይጠይቃታል፤ ቆንጆይቱም "እሺ ነገር ግን ሁለት መስፈርቶች አሉኝ እነርሱን ካሟላህ " ትለዋለች። መስፈርቷንም በዚህ መልኩ ትነግረዋለች።
1ኛ) ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።
2ኛ) እንደምታቀው አባቴ የመስጅድ ኢማም ነው እና ስጠኝ እስካልኩህ ጊዜ ድረስ መስጂድ እየሄድክ በጀምዐህ ሶላትህን ስገድ" ትለዋለች።
:
ልጁም እሺ ብሎ ተስማማ።
ቃሉንና መስፈርቱን ለመጠበቅ ሲል መስጂድ መሄድን አዘወተረ።

በመጨረሻም የሰጣት ጊዜም አለቀ።
"ያንን የሰጠሁህን መስፈርት ተገበርከው ቃልህንስ በትክክል እያከበርክ ነው"? የሚል ጥያቄ አነሳችለት።
እርሱም "አው! እየተገበርኩ ነው ነገር ግን ቃል ያስገባሁሽን ነገር አሏህ ይቅር ይበለኝ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል። መስጂድ በምመላለስበት ሰዓት ወደ አሏህ ተመልሻለሁ" አላት።

አርሷም "ማሻ አሏህ! እኔም እሺ ያልኩህ ዝሙት ለመስራት ሳይሆን "ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች" በሚለው በዚህ በአሏህ ቃል እርግጠኝነት ተሞልቼ ነው።

اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ
ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አሏህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አሏህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡
📒ሱረቱል ዐንከቡት (45)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Dec, 07:09


ጌታዬ ለማለት አታርፍድ። ሰጥቶ ሲያቀናጣህ፣ አዘግይቶብህ ሲፈትንህም ጌታዬ ለማለት አታርፍድ!
ጌታዬ ለማለት የማታረፍድ ከሆነ ህይወት አታዝልህም። በከባድ ወቅት ላይ ብትሆን እንኳ ልብህ ፈገግታ አይለየውም። »

اقرأ (አንብብ )

24 Dec, 02:25


Daily therapy 269🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

23 Dec, 15:03


#ሙስሊም ከሆንክ እንዴት ሰላትህን በፍቅር መስገድና ሰላትህ ላይ ቀጥ ማለት እንደምትችል ላመላክትህ> >

1 #በመጀመሪያ_ልክ_አዛን_ስትሰማ

አዛኙ እና ሩህሩሁ የሰማይ እና ምድር የአለማቱ ንጉስ ሊገናኝህ ፈልጎ እየጠራህ እንደሆነ አስታውስ።

2. #ልክ_ውዱዕ_ስታደርግ

ከራስህ ላይ ወንጀልህን እያራገፍክ እና የንጉሶች ንጉስ ፊት ለመቆም እየተዘጋጀህ መሆኑን አስታውስ።

3. #የመጀመሪያውን_ተክቢራ_አላሁ_አክበር_ስትል

ሰሚ እና አዋቂ፣ የፈለገውን አድራጊ የሆነውን የአለማት ንጉስ በግል ልታናግረው እየገባህ እንደሆነ አስብ። ረሱል እንዳሉትም እርሱ አላህም ወዳንተ እንደሚቀጣጭ እና እንደሚያናግርህም አስታውስ።

4. #ልክ_ፋቲሃን_መቅራት_ስትጀምር:

ባንተና በቅርቡ እና ዱዓን ተቀባይ በሆነው ጌታህ መካከል ልዩ ቃለ ምልልስ ላይ እንደሆንክ አስታውስ።

ይህ ትልቅ እድል ለሁሉም ሰው አይደለም:- ለዚህ ቃለ ምልልስም ተመርጠህ እንደሆነ አትርሳ።

5. #ልክ_ለሩኩዕ_ስታጎነብስ

ከእስትንፋስህ ጀምሮ እያንዳንዱን ፀጋ እራሱ የሚለግስህን እና ያንተ ጥቅምም ጉዳትም በእጁ የሆነውን አለቃህን አላህን ለማላቅ ክብርህን እና ተገዢነትህን እየገለፅክ እንደሆነ አስብ።

6. #ልክ_ወደ_ሱጁድ_ስትደፋ

ከብቸኛው ንጉስ፣ አዛኝ፣ ሃብታም እና ሰጪ የሆነው ጌታህ ዘንድ ቅርብ የምተሆንበት እና: (በህይወትህ ትልቁ እና ውቡ ቦታ ላይ) እንደሆንክ አስታውስ።

እዚህ ትልቅ ቦታ ላይ ስትሆን ባንተ እና በምኞቶችህ ሁሉ መካከል ያለው መጠየቅ ብቻ እንደሆነ አስታውስ።

7. #ለተሸሁድ_ስትቀመጥና_ታሂያ_ስትጀምር:

አንተንም፣ ስሜትህንም፣ ማንነትህንም፣ የፈጠረህ እና በእዝነቱ ወደ ህይወት ላመጣህ እና አንተን ከእናትህም፣ ከራስህም በላይ የሚወድህ እና የሚያዝንልህን ጌታህን ሰላምታ እያቀረብክለት እንደሆነ አስታውስ።

8. #ልክ_ስታሰላምት

በድጋሜ ከአለማቱ ጌታ ጋር ለመገናኘት ውስጥህ በናፍቆት እየተቃጠለ እና በጉጉት እየጠበቅክ እንደሆነ አስብ።

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

23 Dec, 05:38


#አንዳንዴ
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
#አንዳንዴ ልባችን የሚፈልገውና የሚጓጓለትን ፍቅር እና እንክብካቤ እኛን ከማይመስሉና ሩቅ ናቸው ብለን ከምንላቸው ዘንድ ይደርሰናል። #አንዳንዴ ፍቅርን ቆንጥረው የማይሰጡ አሉ። ለሚመስላቸው የማያዳሉ፣ ላገኙት የማይነፍጉ ወዳጅ ልቦች አሉ። #አንዳንዴ ባይተዋርነታችንን ሳይመለከቱ ምቾት የሚሰጡን አሉ። መውደድን፣ ማፍቀርን፣ መንከባከብን እነዛ ያውቃሉ በስሌት ምንም ነገር የማይሰጡት። #አንዳንዴ ከቅርብ ወዳጆቻችን የምንፈልገውን ትኩረትና እንክብከቤ ስላጣን በፍፁም ሌሎች ጋር የለም ማለት አይደለም። አላህ ብዙ ፍጥረቶች አሉት በምታውቋቸው ሰዎች ልክ ስለ ሁሉም ልቦች እርግጠኛ አትሁኑ። የሚፈልገውን ያጣው ልባችሁ የሚያስፈልገውን የያዘ ይኖራልና ዞር ዞር በሉ። አላህን እንድታመሰግኑት የሚያስታውሷችሁ ብዙ ፍጥረታት አሉና አላህን በሚያስማርሯችሁ ላይ ስለወደዳችኋቸው ብቻ ችክ አትበሉ። #አንደንዴ…
:
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

23 Dec, 05:30


Daily therapy 268🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

22 Dec, 19:13


ፉደይል ኢብኑ ኢያድ ረሒመሁሏህ
እንዲህ ይላል.......

በሽታ በሰው ልጅ ላይ የተደረገው አላህ ባሪያዎቹን ቀጥቶ ስርዓት ሊያሲዝበት ነው።ደግሞም የታመመ ሁሉ ይሞታል ማለት አይደለም ::

اقرأ (አንብብ )

22 Dec, 16:16


🥹አሳቢው ሌባ ለፈገግታ 


አንድ ታዋቂ  ቃዲ አንድ መስጊድ ሰላት ለመስገድ አዲስ ጫማውን አውልቆ ገባ   ሰግዶ ጨርሶ ጫማውን ለማድረግ ወደ አስቀመጠበት ቢመለከት ቤት ውስጥ ጥሎት የመጣው አሮጌ ጫማው ነው ያለው በጣም ተገርሞ ወደ ቤቱ ተመልሶ እንዴት በአዲሱ ቦታ አሮጌው ተተካ እንዴትስ አሮጌው ከቤት ወጥቶ እዛ ድረስ መጣ ብሎ ልጁን ይጠይቀዋል  ልጁም ከጥቂት ሰዓታት በፊት አንድ ሰው መጥቶ  " ቃዲያችን አዲሱ ጫማ ስለተሰረቀበት አሮጌውን ጫማ ላኩልኝ ብሏል ብሎ ነው " አሮጌውን ጫማ የሰጠነው ብሎ መለሰለት ።
ቃዲውም በጣም ስቆ እና ተገርሞ  እንዲህ አለ
ይሄ ሌባ  በጣም ምርጥና አዛኝ  ሌባ ነው  አዲሱን ጫማ በመውሰዱም ይቅር ቢየዋለሁ😂  እና ምን ለማለት ኧረ እንተሳሰብ ሌባ እንኳን እንዲህ በሀዘኔታ እየሰረቀ😂

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

22 Dec, 03:03


Daily therapy 267🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

21 Dec, 18:48


ወንድሜ የ 40 million ብር መኪና ሲነዱ አትበሳጭ። በወር 1 million ብር ቢከፈልክ እራሱ በ 2 አመት አትገዛውም። ለአላህ መተው ብቻ bro

اقرأ (አንብብ )

21 Dec, 15:03


አንዱ ልጅ ወደ አውሮፓ ለመሄድ ሊቢያ ሲደርስ በአጋቾች ተያዘ።እና ተደራድሮ ገንዘብ ለማስላክ ወደ ቤት እንዲደውል ተደርጎ ከቤተሰቡ ጋር ለማውራት ሲፈለግ ችግር ተፈጠረ።ቤተሰቦቹ ዐረቢኛ አይችሉም።
ታዲያ ከሰፈሩ እንደምንም ተፈላልጎ አንዲት ዐረቢኛ የምትችል ሴት ተገኘች።እና ልታናግረው ስልኩን ይዛ:-"ሄለው!" ስትል በአንድ ቃል ንግግሩን ዘጋው:-
"አጅነቢይ አላናግርም።"

እናንተ በተያዡ ቦታ ብቶኑ ምን ታደርጉ ነበር😄

ወደ ኮሜንት👇👇👇

اقرأ (አንብብ )

21 Dec, 11:06


.
በወንዶች በሆነ ነገራቸው የምቀና ብሆን ኖሮ...
ወደ መስጂድ በሚያደርጉት ጉዞ
እቀናባቸው ነበር።😍

የሕይወት ውጣ ውረድ ሲወጥራቸው
በፈለጉት ሰዓት ወደ መስጂድ ሸሽተው
መንፈሳቸው ያድሳሉ!

አለችኝ ፋጡማ😁

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

21 Dec, 10:55


በእስልምና ውስጥ ስለ እርግዝና እውነታዎች

#1 #አንዲት ሴት ባረገዘች ጊዜ መላኢካዎች ሁሉ በርሷ ላይ እስቲግፋር ያደርጋሉ፡፡

#2 #በእርግዝናው ምክንያት ህመም ሲሰማት አላህ በመንገዷ ላይ ጂሃድ እየሰራች እንደሆነ አርጎ በመዝገቧ ላይ ይፅፍላታል፡፡

#3 #የወለደች ሴት የ70 አመት ሰላት እና የፆም ምንዳ ታገኛለች፡፡

#4 #ህመም በተሰማት ጊዜ አላህ የአንድን ተቀባይነት ያገኘ ሐጅ ምንዳን ይሰጣታል፡፡

#5 #በነፍሰ ጡር ሴቶች የሚደረጉ ሁለት ረካቶች ነፍሰ ጡር ባልሆኑ ሴቶች ከሚያረጉት 80 ረካት ሰላት በላጭ ናት፡፡

#6 #አላህ 1000 መልካም ስራዎችን ይጽፍላታል እና 1000 መጥፎ ስራዎችን ይሰርላዛታል፡፡

#7 #ልጇን በምትወልድበት ጊዜ ሽልማቶች ይኖሯታል _ይህም በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ለመረዳት የማይቻል ነው።

#8 #በምታምጥበት ጌዜ ብትሞት ሸሂድ ናት, በቂያማም ቀን አላህ ንፁህ አድርጓት ከመቃብር ያስነሳታል፡፡

እና ምን ትጠብቃላችሁ ያገባችሁ ውለዱ ያላገባችሁ አግብታችሁ ውለዱ😂

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

21 Dec, 03:09


ረሱል  እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن رَأى مِنكُم مُنْكَرًا فَلْيُغَيِّرْهُ بيَدِهِ، فإنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِلِسانِهِ، فإنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِقَلْبِهِ، وذلكَ أضْعَفُ الإيمانِ.﴾

“ከናንተ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው። ካልቻለ በምላሱ ይቀይረው። ካልቻለ ደግሞ በልቡ ይጥላ። ይሄኛው የመጨረሻ ደካማው የእምነት (ክፍል) ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 49

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

21 Dec, 03:08


Daily therapy 266🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

20 Dec, 18:45


እያገባን ወገን

እንደው በፈጣሪ አይታችሁ አትለፉን
በየ ሰልፉ ሁሉ ከፊት አሳልፉን
ሀይገርና ባስ ላይ ልቀቁልን ወንበር
ግራ ጎን የሌለን አካል ጉዳተኞች...
አለብን መከበር።

ገጣሚ ፦ ላጤ😅

اقرأ (አንብብ )

20 Dec, 16:08


« የምትወደውን፣ ከማንም በላይ አስበልጠህ የምትፈልገውን ስትለይ ያኔ የዱንያን አስቀያሚ መልክ በደንብ ትመለከታለህ። ልብህ የምታመልከውን ምን ያህል እንደምታከብረው ያኔ ታውቃለህ። በጥልቀት መረዳት ከቻልክ "መለያየት" ከሚሰጥህ ትምህርት የበለጠ ላንተ አዕምሮ የተመጠነ ትምህርት አታገኝም። በመለያየት ካልተፈተንክ ተዘጋጅ ፈተናህ ገና ነው። በእርግጥ "መለያየት" ማለት ጥልቅ እና ረቂቅ ነው። በሰው ብቻ የተገደበ አይደለም።
በጊዜ ውስጥ ከፈን የምታይበት፣ ዝም ብለህ ቀብር ስትመለከት ሆድ የሚብስህ፣ በአደባባይ ፍቅራቸውን በሚገልፁት የምትናደድበት፣ ትዝታ እየጠበሰህ የምትስቅበት፣ የማታውቀው የማትገምተው መቻል ይሉት መርሳት የሚሉትን የምትለማመድበት፣ ሁሉንም ፈተናዎችህን የምትመዝንበት አንድ ማጣት የምታገኝበት፣ ትልቁ የደስታና የስኬት ቀን በምትለው ጊዜ የምትወደውን የማትመለከትበት፣ በፊት ከነበረህ አስተሳሰብ ተቀይረህ እራስህን የምታገኝበት ጊዜ አለ። መለያየት እውነት ነው። በየትኛውም ፍልስፍና ልትከልለው ብትሞክር፣ ዘልዓለም አብረን ነን ብለህ ብትሞዝቅ፣ ብትፅፍ፣ ብትደሰኩር መለያየትን ከሕይወትህ መፋቅ አይቻልህም። እንኳን ሰውን እና ሌሎች ነገሮችን ቀርቶ አምላክህን የመለየትን ድፍረት ልታገኝ ትችላለህ። »
(አብዱልሀኪም ሰፋ)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

20 Dec, 08:34


አላህ ብዙ ፀጋዎችን ሠጠን። ከተሠጠነ ፀጋ ዘካ ማውጣት ይጠበቅብናል። ትንሽ ትልቅ ብለን አንናቅ። ዘካ በረከትን ያመጣል። ዕውቀትን፣ ገንዘብን፣ ዕድሜን ያፋፋል።
አላህ በሰጣችሁ ነገር ሁሉ ሰዎችን እርዱ። ማገዝ በምትችሉትም እገዙ። ከችሮታዉም ለወንድም እህቶቻችሁ ቆንጥሩ። እኔ ምንም የለኝም አትበሉ። ሀሳብና ምክር፣ ገንዘብና ጉልበት፣ ጊዜና ዕውቀት፣ ተስፋና ፈገግታ ...እነኝህ ሁሉ ልናጋራቸው የሚገቡ የአላህ ፀጋዎች ናቸው። እናካፍላቸው ወዳጆቼ። ስናካፍላቸው ይበዙልናልና።
ከተሠጣችሁ አካፍላችሁ የምውሉ ሁኑ።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

08 Dec, 01:41


አረ አህባብ እኔም የአስለንን ደገምኩት ወላሂ ነው ምላቹ 10:20 ሲል ፈጅር መስሎኝ መስጂድ ስደርስ በሩ ዝግ ነው።
ገና አንድ ሰዐት ይቀራል ለካ🫣
ደሞ ባባ ሰዐት ደርሷል እንዴ ሲለኝ መብራት ስለሌለ ነው አዛን ያልሰማነው ብዬው እኔ ከመስጂድ ስመለስ እሱም እንደኔ እየሄደ ነበር ከዛ ተመለስን🤦‍♂
አረ እሄማ ዱዐ ያስፈልገዋል እኛስ ወንድ ነን ሴቶቹም አድሚኖች እንደኛው እንዳይሆኑ ነው ምፈራው😁

መልካም ቀን

اقرأ (አንብብ )

08 Dec, 01:07


Daily therapy 253🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Dec, 17:50


በዚህ ሰዐት ስልካችሁ ቻርጅ ካለው እድለኛ ናችሁ😭🥰

اقرأ (አንብብ )

07 Dec, 17:47


.
ወንጀላችን ማለቂያ የለውም...

እንዲያውም የሚሸት ቢሆን ከመኖሪያችን ባልወጣን ነበር!

ምስጋና ወንጀላችንን ሰትሮ
በውዴታው ለሚያኖረን አላህ🤍

አልሀምዱሊላህ❤️
.
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Dec, 17:39


.
በህይወቴ በአንድ ነገር ላይ ብቻ እርግጠኛ ነኝ....
ስህተት እየሰራሁ እንኳን ሳይሰለች የሚምረኝ አንድ አላህዬ ብቻ እንደሆነ አውቃለው::

አላህምምም 🥰

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Dec, 10:18


በእስልምና በወላጆች ላይ ሀራም የሆኑ ነገርግን አሁን ላይ ሲደረጉ የምንመለከታቸው ነገሮች

1. ልጆች ኢባዳ ላይ ሲሳነፉ ዝም ማለት

የአላህ መልእክተኛ ( ) እንዲህ ብለዋል፡-

“ልጆቻችሁ ሰባት አመት ሲሞላቸው እንዲሰግዱ አስተምሯቸው፣ 1ዐ ዓመትም ሲሞላቸው ካልሰገዱ (በቀላል) ቅጧቸው እና ብቻቸውን መተኛት ____ (እንዲጀምሩ) አድርጓቸው።''

ምንጭ᎓ አቡ ዳዉድ (495) እና አህመድ (6650

2. ልጆችን ከልክ ባለፈ ሁኔታ መቀጥቀጥ

ማንኛውም አይነት በልጆች ላይ የሚደረግ አካላዊ ጥቃት በእስልምና በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይህ በተለይ በፊታቸው ላይ መምታት፣ መደብደብ ወይም በሀገራችን የምንሰማው በርበሬ ማጠን የተባለው አቀጣጥ በአላህ ያስጠይቀናል።

ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል᎓

"ልጆቻችንን የማይምር ፣ ሽማግሌዎቻችንንም የማያከብር ከእኛ አይደለም"

[ጃሚ` አት-ቲርሚዚ 1920፣ ኪታብ 27፣ ሀዲስ 25]

3. የልጆችን ስሜት መጉዳት

ስሜታዊ ጥቃት እንደ አካላዊ ጥቃት በልጆች ላይ ጎጂ ነው። ልጆችን መስደብ፣ የራስ መተማመን ማሳጣት፣ ያለማቋረጥ መተቸት ወይም በልጆች ላይ አደብ የሌለው ቃላትን መጠቀም በልጆች ላይ ጎጂ ነው።

ስለዚህ የልጆችን አእምሮ መንካት በአላህ ያስጠይቀናል።

4. በልጆች መካከል ማበላለጥ

በልጆች መካከል አድልዎ ማሳየት በእስልምና በጣም የተጠላ ስራ ነው። ይህ በልጆች ላይ ስሜት መጎዳት፣ መቀናናት እና የቤተሰብ ግንኙነቶችን ሊያበላሽ ይችላል። የቤተሰቡ መጨረሻ ልጅ ቢሆን እንኳን በእኩል አይን መታየት አለበት።

የአላህ መልእክተኛም () በዚህ ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፡-

“አላህን ፍሩ እና ልጆቻችሁን በእኩልነት ተመልከቱ።“

ምንጭ : ሳሂህ አል ቡኻሪ 2587፣ ኪታብ 51፣ ሀዲስ 26

5. ልጆችን በጋብቻ ላይ ማስገደድ

በእስልምና ልጆችን ያለፍላጎታቸው ወደ ጋብቻ ማስገደድ በጥብቅ የተከለከለ ነው። በሸሪዓው ህግ መሰረት ጋብቻው እንዲፀና ሁለቱም ወገኖች ነጻ ፈቃዳቸውን መስጠት አለባቸው።

ነብዩ () በዚህ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡-

" አግብታ ምታቅ ሴት ካላማከሯት በቀር ለጋብቻ ሰጠት የለበትም። ድንግልም የሆነች ሴት ከእርሷ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር አታግባ።“

ምንጭ: ሳሂህ አል ቡኻሪ 5136፣ ኪታብ 67፣ ሀዲስ 72

5. የልጆችን ውርስ መብት መከልከል

በዲናችን ልጆችን የውርስ መብታቸውን መከልከል የተከለከለ ነው። ነገርግን ውርስ የሚከለክልበት ሦስት ምክንያቶች አሉ ፡-

1. ግድያ፡- ሆን ተብሎ የሚደረግ ግድያ ውርስ የሚከለክልበት ምክንያት እንደሆነ በሁሉም ኡለማዎች የተስማማ ነው።

2. ባርነት፡- ድሮ የባርነት ነት ሥርዓት በነበረበት ዘመን አንድ ሰው ባሪያ ከነበረው ይሄ ባሪያ ንብረቱን መውረስ አይችልም ነበር።

3. ወራሹ እና ሟቹ ዘመድ የተለያየ እምነት ያላቸው ከሆነ መውረስ አይችልም።

ገ. ኢስላማዊ ያልሆኑ ተግባራትን ማስተማር ወይም ማበረታታት

ወላጆች ለልጆቻቸው ኢስላማዊ አስተምህሮትን የሚቃረኑ ነገሮችን ማስተማር ወይም እንዲያደርጉ መፍቀድ የለባቸውም። ይህንንም ሚፈቅዱ ከሆነ በእስልምና የተከለከሉ ተግባራትን መዳፈር እንዲሁም ከቀጥተኛው መንገድ ሊያስታቸው ይችላል፡፡

ወላጆች ልጆቻቸውን በእስልምና ህግጋት መሰረት ትክክል የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ መምራት እና ኢስላማዊ እሴቶችን የሚከተሉበት ቤት መፍጠር አለባቸው።

8. ልጆችን መዋሸት

ታማኝነት የእስልምና ዋና እሴት ነው እና ወላጆች ይህንን ለልጆቻቸው በማስተማር ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

ልጆች ወላጆቻቸውን በመመልከት ይማራሉ ስለዚህ ወላጆች ሁልጊዜ እውነተኞች በመሆን ልጆቻቸው እውነትን እንዲከተሉት ጠንካራ ምሳሌ መሆን አለባቸው።

ትናንሽ ውሸቶች እንኳን ልጆች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ስለዚህ ለልጆች ሁልጊዜ እውነቱን መናገር አስፈላጊ ነው። ይህ በቅንነት እና በመልካምነት የተሞላ ቤት ይፈጥራል።

9. ብቻቸውን እንዳይሆኑ መከልከል

ልጆች እያደጉ ሲሄዱ ብቻቸውን መሆን ያዘውትራሉ እና ይህንንም ወላጆች ከእስልምና ትምህርቶች ጋር ማመጣጠን አለባቸው፡፡ ለልጆች የግላቸውን ቦታ መስጠት በራሳቸው ላይ ያለውን እምነት ያጎለብታል፣ ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመናፈቅ ጥሩ ያደርገዋል እንዲሁም ኃላፊነት እና ለራሳቸው ክብርን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች አትግቡ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እናንተ ተ ትገነዘቡ ዘንድ (በዚህ ታዘዛችሁ)፡፡'

ሱረቱ አን ኑር 24:27

10. በሙያ ምርጫቸው ላይ ማስገደድ

የወላጆች መመሪያ አስፈላጊ ቢሆንም ልጆች ከአቅማቸው ውጪ ወደሆኑ ሙያዎች ማስገደድ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ከችሎታቸው እና ከፍላጎታቸው ጋር ወደሚስማማ ሙያ መምራት አለባቸው ይህም በስራቸው እርካታን እንዲያገኙ ያስችላል።

ይህን ልጆች ላሏቸው ወንድሞች እና እህቶቻችን ሼር በማድረግ እናሳውቃቸው። ልጆች ለሌለንም saved message ውስጥ እናስቀምጠው ኢንሻአላህ ልጅ ይኖረን ይሆናል።

“አስታውስም፤ ማስታወስ ምእመናንን ትጠቅማለችና።

[ሱራቱ አዝ-ዛሪያት 51:55]

ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል: “አንድን ሰው ወደ መልካም ነገር የመራ ሰው ከመራው ሰው እኩል ምንዳ አለው (ምንም ሳይቀንስበት)።*

[ሳሂህ ሙስሊም 1893]

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Dec, 03:02


እውቀትን ማሰራጨት ወንጀል እንዲማር ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው።
: ኢብኑ ኡሰይሚን

ቢያንስ በቀላሉ ሶሻል ሚዲያ ላይ የምናገኛቸውን ኢስላማዊ ትምህርቶችን ሼር በማድረግ ወንጀላችንን እናስምር ::

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Dec, 02:58


Daily therapy 252🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 17:42


ወንዶች ሲያረጉት ኖርማል የሆነ ሴቶች ሲያረጉት ግን የሚደብር ነገር ምንድን ነው?

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 17:41


ሴቶች ሲያረጉት ኖርማል የሆነ ወንዶች ሲያረጉት ግን የሚደብር ነገር ምንድን ነው?

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 17:40


" ስንተክል የሚነቅልን እናስተውል!!! "
:
መንግስት ይህንን የአረንጓዴ አሻራ ቀን ከማለቱ በፊት ለረጅም አመታት ሳልታክት አረንጓዴ አሻራዬን ሳሳርፍ ነበር ። እንደውም ለዘመናት በሞኖፖል ይዤው የነበረውን ትጋቴን ህዝቡ ስላወቀልኝ በአረንጓዴ አሻራ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ። ስማ እኔ እኮ እንደ አንዳንድ ቀሽም ሰዎች እዚህ ሀገር ላይ የተተከለ አይበቅልም የሚል ቀሽም አስተሳሰብ የለኝም ። የተተከለ ይበቅላል ይኸው እኔም ለዘመናት የተከልኩት እስካሁን እንደበቀለ ነው ። የተከልኩት ፍሬ እንዳፈራ ለማየት የአፍ ጠረኔና ጥርሴን ማስተዋል በቂ ነው ። እዚህ ዝም ብለህ የሚተክልን አትንቀል ። የተከልኩት መብቀሉን የሚያሳይ የሀኪም ማስረጃ አለኝ ። ለዚህ ደሞ ምስክሩ ባለቤቴ ነች ፣ ምንም ትዝ አትለኝም በመትከል ስላልቦዘንኩ ስሜቴ መትከል ላይ ብቻ ነው ። አዳሜ " ምን ሊያደርግ አረንጓዴ ነገር ይተከላል?" የምትለው ምስክርህ እኔ ነኝ ። የሚተክለው ካልቦዘነ የተተከለ ይበቅላል ። የሚተክል ሰው የሚተክለውን እንጂ የሚጥለውን ልብ አይልም ። ይህንን ያወቅኩት ለረጅም ዘመን እየተከልኩ የጣልኩት ገረባ ሌላ አሻራ ሆኖ ሳየው ነው ። አጋጣሚ ሆኖ የኔ የዘመናት አረንጓዴ አሻራ ብዙ ነገር ስላናጋ አቁምያለው(አልቅምም ማለቴ አልተክልም) ። በዚህም የተነሳ የሀገሪቱ የገረባ መጠን ቀንሶዋል  ። አሁን ደሞ አረንጓዴ አሻራ ላይ ችግኝ ተክዬ ፌስታሉ የድሮውን የኔን ገረባ ስላስታወሰኝ የአረንጓዴ አሻራዬን እንዳያበላሸው ሰጋሁ ። በቃ ምን ላድርግ በተሳሳተ መንገድም ቢሆን የተሳሳተ ነገር ስተክል ስለነበርኩ የሚጣል ነገር ያሳስበኛል ። እና ሰምተሀል ወዳጄ የተተከለ ይበቅላል ፣ የሚጣለው ፌስታልም አሻራ ይሆናል ተጠንቀቅ!!!
              
#ስንተክል_የምንጥለውን_ልብ_እንበል!!!
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 15:47


አንድ ዐሊም፦ "አላህ እኔን የሚያወሳበትን ቅጽበት አውቀዋለሁ" በማለት ተናገሩ። "መቼ ነው?" ተብለው ሲጠየቁ ተከታዩን የቁርአን አንቀፅ ጠቀሱ፦

فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ

"አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና፤" (አልበቀራህ 152)

አላህን ስናስታውስ እርሱም ያስታውሰናል። ስናመሠግን ይጨምርልናል።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 12:10


የአዲስ አበባ የመጀመሪያውን መስጂድ ሊያፈርሱ ነው....

ሙሉ መረጃ 👇
https://t.me/c/1607023664/22986

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 11:20


ለቻናላችን ቤተሰቦች  በሙሉ ። ኪስን የማይጎዳ ምንም አይነት Side Effect የሌለው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ የሰውነት ለውጥ የሚያሳያችሁን ኦርጅናል የየመን ማር ይዘንላችሁ መተናል። እዘዙን ያላቺሁበት እናመጣለን!!

በተፈጥሮአዊ መንገድ በአጭር ቀናት ለመወፈር የሚረዳ ንፁህ ማር ለወንድም ለሴትም የተዘጋጀ ይዘዙን...በየክፍለሀገሩም እናደርሳለን ።

በብዛት ለሚፈልግ  በቅናሽ እናስረክባለን

ስልክ ፦0986703904

ቴሌግራም፦ @Jentit1
ነፃ delivery አላቸው ስትገዙ ከኢቅራ ቻናል አይቼ ነው በሉ ቅናሽ አለው።

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 03:12


የሆነ ቀን ይመጣል....

ስትገባ ስትወጣ ቀንህን ብቻ ታስቆጥርህ የነበረችው ያቺ ፀሀይ..
የሰላት አውቃትን ለመለየት ትጠቀምባት የነበረችው ፀሀይ
ለመለኮች የማያቋርጥ ስራ ምልክት የነበረችው ፀሀይ ተግባሯ ይለወጣል!
ትንሹንም ትልቁንም ይፅፋሉ እንዴ ብለህ የተብሰለሰልክላቸው መለኮች..ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መፃፍ እንዲያቆሙ የምትመኛቸው መለኮች ለመጨረሻ ጊዜ ፅፈው ስራቸውን ያጠናቅቃሉ! ያኔ ምን ይዋጥህ?
ያኔ ትልቁ ፍላጎትህ መለኮችህ መክተባቸውን እንዲቀጥሉ አጥብቆ መመኘት ነው አዎ ምናልባት ለአንድ ቀን ብቻ ምናልባት ለአንድ ሰዓት ብቻ ምናልባት ለአንድ ደቂቃ ብቻ መፃፋቸውን ትሻለህ "ቀጥሉ እንጂ ገና እኮ ተውበት አላረደረኩም ገና እኮ ሀጥያቴን አላሰረይኩም ገና እኮ ወደ ጌታዮ አልተመለስኩም ፃፉ እንጂ ተውበት ላደርግ አይደል ? ፃፉ እንጂ ወደጌታዮ ልመለስ አይደል?" መለኮች ግን ብዕራቸውን አስቀምጠው መፅሀፍህን ዘግተዋል ! ያቺ ትዝ ያላለችህ ፀሀይ አቅጣጫዋን ቀይራ የህይወት ልፋትህን ባልታሰበ ቅፅበት እንድታቆም ታስገድድሀለች !

አህህ ፀሀይ! በነ'ፃው አካሌ ሙቀትሽን ሳልቀበል የነፃሁበት ቀን ባንቺ ንጋት ሳይታጀብ እያየሁሽ ከሰርኩ !

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

06 Dec, 03:09


Daily therapy 251🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

05 Dec, 16:47


ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላና አህያ የሳር ቀለም እንዲህ ነው እንዲያ ነው በሚል ክርክር ውስጥ ገቡ ። አህያ ፡- “ የሳር ቀለም ቢጫማ ነው ” አለ ። ተኩላ ፡- “ በፍፁም ! አረንጓዴ ነው ” አለ ።

ክርክራቸው እየጦፈ መጣ ። ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ላይ መድረስ አልቻሉም ። በመጫረሻም የጫካ ንጉስ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው መሸማገል እንዳለባቸው ወሰኑ ። ሽምግልናው ተጀመረ ። ሁለቱም የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቀረቡ ። አንበሳም የሁለቱን የመከራከያ ነጥብ በጥሞና አዳመጠ ። የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል የታደሙት እንስሳት በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን ጣል አደረጉ ።

አንበሳው ታዳሚውንም ሆነ ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ ። ተኩላው በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ ሲወሰንበት አህያው ደግሞ በነፃ ተሰናበተ ። በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በሚል ስሞታ አቀረበ ፡- “ክቡር አንበሳ ሆይ ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን ? ” አንበሳም “ አዎ በእርግጥ አረንጓዴ ነው ” በማለት መለሰ ። ተኩላውም “ ታዲያ በየትኛው ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያክል ዘብጥያ እንድወርድ የወሰንክብኝ ” በማለት ጠየቀ ።

አንበሳውም “ ትክክል ነህ ፤ በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት አላስተዋልኩም ። ጥፋትህ በዚህ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር ውስጥ መግባትህ ነው ። ነገሮችን በጥልቀት መረዳትና መገንዘብ ከማይችል አካል ጋር መከራከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዘን እንደሚችል ትምህርት ትቀስም ዘንድ ብዬ ነው የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ ” አለው።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

05 Dec, 07:19


አንድ ሰው ካህሊል ጂብራንን ጠየቀው፡-


"በሰዎች ውስጥ በጣም አስደናቂው ነገር ምንድነው?"

እርሱም፡

“ ሰዎች በልጅነት ጊዜ ይሰለቻቸዋል ለማደግ ይቸኩላሉ፤ ከዚያም _ እንደገና ልጅ ለመሆን ይናፍቃሉ። ስለ ወደፊቱ ጊዜ በጭንቀት ያስባሉ እና የአሁኑን ይረሳሉ። ስለዚህ በአሁንም ሆነ በወደፊቱ ውስጥ አይኖሩም፤ የማይሞቱ መስለው ይኖራሉ ያልኖሩም ሆነው ይሞታሉ . . ።


@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

04 Dec, 14:54


اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
    አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
=============================
  📖 ራሀቱል ቀልብ የቁርአንና የተጅዊድ ማእከል*

               ማእከላችን በኦን- ላይን ከ አሊፍ ጀምሮ እስከ ተጅዊድ ትምህርት ድረስ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል። እርሶም ፈጥነው ይመዝገቡና ትልቁን የቁርዐን እውቀት ይሸምቱ።

     👉  ቃኢደቱ ኑራኒያ ለጀማሪዎች
     👉  ነዝር ከመሰረታዊ ተጅዊድ ጋር
    👉 ሂፍዝ
👉  የተሟላ የተጅዊድ ትምህርት
    
————————————————
👉  የቁርዐን ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ

   ☆ አንድ ተማሪ ከተመዘገበ በኋላ የተመደበለት ኡስታዝጋ
👉 በቴሌ ግራም
      ኦን -ላይን ወይም ላይቭ የሚሰጥ ይሆናል
  ለወንድም ለሴትም ተማሪዎች በቂ ቦታ አለን
   የቁርዐን ጊዜው በሳምንት 5 ቀን ወይም በሳምንት 3 ቀን

                ተማሪው በሚመቸው ሰአት
=============================

ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
               👇👇👇👇👇
                  @Rahatulkalbe
@Rahatulkalbe
=============================
       


  *ራሀቱን ቀልብ የonline ቂርአት ማእከል*
=============================

اقرأ (አንብብ )

04 Dec, 14:44


☞የትንሽ እውቀት በሽታ!

    ሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ፦

አንድ ሰው እውቀቱ አነስተኛ በሆነ ቁጥር  በራስ መደነቁና መገረሙ ይጨምራል። እሱ የማያውቀው የትኛውም ነገር ሲያጋጥመው ስህተት ነው ብሎ  ያስባል። ለምን መሰላቹህ? ይህ ነገር ስህተት ሆኖ ሳይሆን እሱ ስለማያውቀው ብቻ ነው። እሱ ከሚያውቀው ዉጪ እውነት የለም ብሎ ይገምታል። እውቀት ሁሉ እሱ ዘንድ የተሰበሰበ ይመስለዋል።

[تفسير المفصل: ٥٤٦]

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

04 Dec, 11:02


አሳ በደንብ አጽድታ መመገብ የምትወድ አንዲት ሴት ነበረች፡፡ አንድ ቀን አሳዉን  አመጣችና  ጭንቅላቱንና ጭራዉን ቆርጣ በደንብ አጥባ ድስት ዉስጥ አድርጋ ለመሥራት አዘጋጀችው፡፡
ይህን ስታደርግ ልጇ ታያት ነበር፡፡ ልጅት አደገች፤ አገባች፣ ወለደችም፡፡ እሷም አሳ ስታዘጋጅ አሳዉን ወስዳ ጭንቅላቱንና ጭራዉን ቆርጣ አጥባ ድስት ዉስጥ ማድረግን ልምዷ አደረገች፡፡ 
በዚህን ጊዜ ልጇ ታያት ነበር፡፡ ልጇም አደገች፡፡ እሷም አሳ ስታዘጋጅ የእናቷን መንገድ ተከተለች፡፡ ጭንቅላቱን ጭራዉን በመቁረጥ አጥባ ድስት ዉስጥ መክተት፡፡ (የልጅ ልጅ መሆኗ ነው፤ አያቷን ያየች)
አንድ ግን ቀን ባሏ ጠየቃት፡፡ “አሳ ስታዘጋጂ ጭንቅላቱንና ጭራዉን የምትቆርጪው ለምንድነው?” አላት፡፡
“ምክንያቱን እንጃ፡፡ ግና  እናቴ አሳ ስታዘጋጅ እንዲህ ስታደርግ ስላየሁ እሷ ስር የተማርኩት ነው” አለችው፡፡
እናትም ተጠየቀች፡፡ እሷም “አይ እናቴ (የልጇ አያት) እንዲህ ታደርግ ስለነበር ነው” አለች፡፡ 
ተሰባስበው ስለዚሁ ጉዳይ ለመጠየቅ ብለው ለአንዷ  እናት ለሌኛዋ  አያት ወደሆነችው  ዘንድ ሄዱ፡፡
ጠየቋት ፡፡ “አሳ ስታዘጋጂ ጭንቅላቱንና ጭራዉን የምትቆርጪ ለምንድን ነው” አሏት፡፡
ቀለል አድርጋ መለሰች፡፡ 
“ልጆቼ ሆይ በዚያን ጊዜ ድሆች ነበርን፡፡ የነበረችኝ ድስት ትንሽ ስለነበረችና ትልቅ አሳ ስለማትይዝልኝ ጭንቅላቱንና ጭራዉን መቁረጡ ግድ ስለነበረ ነው” አለቻቸው፡፡

ጥያቄ 
ከአንድ ሰው የሆነ ልምድና ትምህርት ስንወስድ ለምን ብለን የምንጠይቅ ስንቶቻችን ነን?
ስንት ባህልና ልምድ አለ ምንጩንና ምክንያቱን ሳናውቅ የወረስነው??
ቀደምቶቻችንና ወላጆቻችን ስላደረጉ ብቻ ትክክል መስሎን ሙጭጭ ያልንበት ስንት ነገር አለ ? ? ?
ሌሎችም ጋር በማድረስ ጥሩውን እናካፍል

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

04 Dec, 02:54


ትናንት ታሪክ ነው፤ ነገ ደግሞ እንቆቅልሽ ነው፤ ዛሬ ግን የአላህ ስጦታ ነው! ስጦታህን መጠቀምም ማባከንም ያንተ ምርጫ ነው።

አላህ አመስግነህ፤ ስለሚያስደስትህ ነገር እያሰብክ ስሜትህን ቀይረህ የሚጠበቅብህን ሁሉ ካደረክ መቼም አይቆጭህም ምክንያቱም ታላቅነት የሚገነባው ዛሬን በመጠቀም ነው።❤️‍🩹

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

04 Dec, 02:54


Daily therapy 249🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 18:59


እንደው ምን አይነት ሀያዕ ነው በኮመንት ከመናገር ያገዳቹ  😂 የምር ይህ ቻናል የኛ ሀሳብ መለዋወጫ ካልሆነ ይደብራል ለብቻ እንደመለፍለፍ ምን ስህተትን ያስታቅፋል? እኔ ሀሳቦችን በራሳችን እይታ እያወጣን እያወረድን ልንፋጭ ከጅዮ ነው የቆረቆርኩት ብቻዮንማ አታሳስቱኝ አህባብ🥹

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 18:59


አንድ ሰው ሰላት ላይ ግዴታ የሆነ ነገር ረሰቶ ግን የእርሳና ሱጁድ ማድረግ ሀራም ይሆንበታል በምን አጋጣሚ ነው ?

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 18:39


መእሙም ከኢማሙ ፊት ወደ ኢማሙ ዙሮ የሚሰግደው ሰላት ምንድን ነው ?

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 18:31


ሙስሊሙ ኡማ ትልቅ ከፍታ ላይ እንዳይደርስ ያገደው ነገር ምንድነው?

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 18:22


እንደ ወጣትነትነታችን የሚጠበቅብንን እያደረግን ነው?

እስኪ ኮመንት ላይ

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 18:11


አንድ ጥያቄ በ inbox ላኩልኝ እስኪ ከዛ ቻናሉ ላይ post አደርገዋለው ሰውን ሊያሳትፍ የሚችል

መላኪያ @ibro_smile

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 16:12


^_^:
‍ ከተስተካከልክ ይወዱሃል👍
       ስታስተካክል ይዋጉሃል🤛

ይህ የብዙሀኖች አመለካከት ነው። እምነትህ፣ ስራህ፣ ስነ ምግባርህ በአጠቃላይ ያማረና የተስተካከልክ ሆነህ፤ ማንንም ሳትነካ፣ ማንም ላይ ሳትደርስ፣ ማንንም ሳትቃወም የራስህ ህይወት የምትመራ ከሆንክ
ከእምነትህ፣ ከአመለካከትህና ከአካሄድህ በተቃራኒ ያሉ ሰዎች ሳይቀሩ ይወዱሃል። ግን

አንተ በቻልከው ተስተካክለህ ሌሎችም እምነታቸው፣ ስራቸውና ስነ ምግባራቸው እንዲያስተካክሉ የምታስተምርና የምትንቀሳቀስ ከሆንክ በሁሉም ዘርፍ ከአንተ ተቃራኒ ያሉት ከቻሉ ሊያስቆሙህ ካልሆነም ሊጋደሉህ ይነሳሉ።


ለምሳሌ፦
አንተ አላህን ብቸኛ አድርገህ የምታመልክ ሆነህ ዝም ብለህ በእምነትህ ብትቀጥል የሚቃወሙህ በጣም ጥቂቶች ይሆናሉ አንዳንዴ ላይኖሩም ይችላሉ።
ግን
አንተ አላህን በብቸኝነት እያመለከው ሌሎችም ከአላህ ውጪ የሚያመልኩትን ትተው አላህን ብቻ እንዲያመልኩ የምትጣራ ከሆንክ ሁላቸውም በአንድነት ይዋጉሃል።

ጫት የማትቅም ብትሆን "ለምን አልቃምክም?" ብሎ የሚቃወምህ የለም።
ጫት አትቃሙ። ካልክ ግን ቃሚዎች ይቃወሙሃል።

ከሴቶች የማትተሻሽ ብትሆን "ለምን?" ብሎ ሚቃወምህ የለም። እንደውም ያደንቁሃል።
መተሻሸት አይቻልም። ብትል ግን ይቃወሙሃል።

ጣዖት (ታቦት) የማታመልክ ከሆንክ "ለምን?" ብሎ የሚጠይቅህ የለም።
ጣዖት ማምለክ አይቻልም አታምልኩ ካልክ ግን ይቃወሙሃል።

ለምን ከተባለ
ሰዎች ካሉበት ጥፋትና ስህተት እንዲመለሱ *እንዲስተካከሉ* በምታስተምር ጊዜ የብዙሃኖች ስሜት ስለ ምትቃረን
ነው‼️‼️


ለዚህም ቆንጆ ምሳሌ ልስጥህ;
ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነብይ ተደርገው ከመላካቸው በፊት የመካ ህዝቦች በአጠቃላይ ይወዷቸው ነበር። ከመውደድም ስማቸው “ታማኙ ሙሐመድ” እያሉ ነበር የሚጠሯቸው። ምክንያቱም
👉ለራሳቸው የተስተካከሉ ሰው ስለ ነበሩ‼️
ነገር ግን አላህ መልእክት አውርዶላቸው ሰዎችን ወደ እስልምና መጣራት *ማስተካከል* ሲጀምሩ ግን ሁላቸውም ተቃዋሚና ተጋዳያቸው ሆነው ተነሱ።
ምክንያቱም
👉ሚያስተካክል አይወደድምና።


ለዚህም ነው ከቀደምት አስተካካዮች መሃል አንዱ እንዲህ ይላል
"እጅግ በጣም ብዙ ጊዜ ልገደል 🗡️ሰይፍ ወደ አንገቴ ቀርቦብኛል። ሁሌም የምባለው ግን ከአቋምህ ተመለስ ሳይሆን ከንግግርህ ተቆጠብ ነው"

🤲አላህ ያስተካክለን
🤲ከአስተካካዮችም ያድርገን‼️

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 10:08


ሁሌም ቢሆን በተወሰኑ ሰዎች ጥፋትና ክፋት አንድን ሙሉ ማኅበረሰብ መወንጀል ተገቢ አይደለም። ይህ በደል ነው።

በያንዳንዱ ማኅበረሰቡ ዉስጥ አጥፊዎችና ወንጀለኞች ይኖራሉ ። በድመቶች መካከልም ጥቁር ድመት አለ።

ክፋትም ሆነ በጎነት የባለቤቱ ነው።
በአንዱ ወንጀል ሌላው አይጠየቅም፤
በአንዱ ክፋት ሌላ አይነወርም።
የአንዱን ኃጢአት ሌላው አይሸከምም።
ሌላው ቀርቶ አንድን ሰው ዘመዶቹ ወይም ቤተሰቦቹ እንዲህ ናቸው ብሎ ማነወርና እርሱንም ከነርሱ ደምሮ ሥሙን ማጥፋት ፤ በስብዕናው መዘባበት ተገቢ አይደለም ።
አላህ ሁሉን በየመልኩ ፈጠረ።
የኑሕ ልጅ ከአባቱ ጋር አልተመሳሰለም።
ወንድሞቹ እንደ ዩሱፍ መልካም አልሆኑም
አስተዋልን አይደል !

   ለሌሎችም እያደረስን እንማማር
ሰላመትኩም አሕባቢ😊

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 03:17


ባለትዳር ነህ ? ያ ማለት ከወጣህ በኋላ መመለስ አለብህ ማለት ነው አዎ ባለትዳር ከሆንክ ከስራ በኋላ ሻይ ቡና እያልክ ቆይተህ አምሽተህ የመግባት መብቱ የለህም!

እቤት እየጠበቀችህ ያለችው ሚስት ብቻ አይደለችም በየሆነ ቦታ ልጅ፣እህት ናት።
በሆነ ቦታ እንክብካቤ እስከጥግ የሚሰጣት መኖሯ ለቤቱ ድምቀት የሆነች..... ለሰከንድ እንድትደበር የማይፈልጉ ቤተሰቦች ነበሯት አላህ ሲሻው ከቤቷ በክብር ወሰድካት እወቅ! የወሰድካት የአባቷን የእናቷን የወንድሟንና የእህቷን ሀላፊነትና እንክብካቤን ጨምረህ ነው ስታዝን አባቷም እናቷም ነህ! ስትደበር ወንድሟም እህቷም ነክ ስትወስዳት አንዲት ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉን ነገሯን ባንተ እንድትጥል አድርገህ ነውና ካንተ ማግኘት ያለባትን ሁሉ አትንፈግ ትዳር ምትኖርበት ሳይሆን ምትኗኗርበት ነው 🙂

አኺ ትኩረት !
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

03 Dec, 03:15


Daily therapy 248🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

02 Dec, 18:27


ከባዱ ነገር መናገር መቻል ነው ወይስ አለመናገር መቻል?

اقرأ (አንብብ )

02 Dec, 15:52


ደገምከዋ ? ላትመለስ ምለህ ተገዝተህ በሰራኸው ተሸማቀህ ራስህን ጠልተህ ነበር ..ግን ተመለስካ ?
እምባሽን በፀፀት ግፊት አዝንበሽው ነበር ! በድርጊትሽ አፍረሽ ላትመለሽ ምለሽ ነበር ..በሸይጣን ላትሸነፊ ከሱ ብዙ በብዙ ልትርቂ ወስነሽ ነበራ ?  ግን ተመለሽ ..ለአንድ ደቂቃ..ሰዓት..ወይ ቀናት ደስታ ረጅም ዘመን ተሳቀቅና ? ደካማ ሰነፍ ወንጀለኛ የሚሉት ቃላቶች ቤታቸው በኛ ተቀለሰ አይደል ? ከሰራነው ወንጀል ይልቅ የሰይጣን ስላቅ አሳቀቀና ..በሱ ደስታ ተሸበርና ? ለሰዎች ደስታ መሆን ቢያስደስተንም ለሸይጣን ደስታ ሰበብ እንደመሆን ምንም አያምማ ? ያንቺ ያንተ እንዲሁም የጌታህ ጠላት ባንተ ስህተት ስኬቱን ሲቆጥር በስኬቱ ልክ ውድቀትል ሲፋጠን ህመምህ በረታ አይደል ?

ግንኮ አሁንም ቢሆን ጌታህ መመለስህን እየጠበቀ ነው! ያቺ አስከፍተሀት ከቤት ወጥተህ ስታመሽ አይኗን ከበሩ ተክላ መመለስህን  እንደምትጠብቅው እናት ..መመለስሽን እንደምትጠብቀው እናት ጌታሽም በተውበቱ በር ዳግም ስትመላለሺ ለማየት እየጠበቀ ነው ሺ ጊዜ ወድቀን ሺ አንድ ጊዜ ሊያነሳን እየጠበቀን ነው ! ጌታዮ ስንለው ባርያዬ ሊለን እየጠበቀን ነው ! ወንጀል ውስጥ ነሀ ? ውጣ ጌታህ ግድ የለውም ብቻ ተመለስ ! ተመልሰህ ኖሮ ዳግም ወደወንጀል ሰጠምካ ? አሁንም ጌታህ ግድ የለውም መመለስህን ይጠብቃል በመመላለስህ ጌታህ አይሰለችልም ጠቅልለህ እስክትመለስ ግን ተመላለስ ሄደህ አትቅር ጌታህ እየጠበቀህ ነውና! አንቺንም🙂

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

02 Dec, 08:57


#ሙስሊም_ከሆንክ_አቂዳህን_አስመልክቶ_ማወቅ_እና_ማስተካከል_ያለብህ_ወሳኝ_ነገሮች።

1 ጌታህ ማነው?

ጌታዬ አላህ ነው።

2 ሃይማኖትህ ምንድነው?


ሃይማኖቴ ኢሰላም ነው።

3 ነብይህ ማነው?

ነብዬ ሙሃመድ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው።

4_አላህ ለምንድነው የፈጠረን?

አላህ የፈጠረን እርሱን እንድንገዛው ነው።

5 አላህን በምን አወቅከው?

በተዓምራቶቹ (እንደ ቀን እና ለሊት) እና በፍጡራኖቹም (እንደ ፀሃይ እና ጨረቃ) አወቅኩት።

6 በኛ ላይ ትልቁ ግዴታ ምንድነው?

አላህን በብቸኝነት መገዛት።

7 አላህ ዘንድ ከሁሉም በላይ ትልቁ ወንጀል ምንደደነው?

ሺርክ (ከአላህ ጋር ማጋራት)።

8 የዲን ደረጃዎች ስንት ናቸው?

3 ናቸው።

1-ኢስላም

2 -ኢማን

3 -ኢህሳን

9_ኢስላም ማለት ምን ማለት ነው?

ኢስላም ማለት- ለአላህ በተውሂድ እጅ መስጠት፣ በትዕዛዝም ወደ እርሱ ማዘንበል፣ ከሺርክ እና ከሺርክ ባለቤቶችም መሰፅዳት ነው።

10 የኢስላም መዓዘኖች ስንት ናቸው?

5 ናቸው።

11_ (ላኢላሃኢለላህ) ማለት ምን ማለት ነው?

ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም ማለት ነው።

12 በነብዩ ሙሃመድ(ሰዐወ) ነብይነት መመስከር ማለት ምን ማለት ነው?

1-ያዘዙትን መታዘዝ፣

2-የከለከሉትን መከልከል፣

3-የተናገሩትን ማመን፣

4-አሳቸው ባሰቀመጡት

ህግ እንጂ አላህን አለመገዛት።

13 የዲን ምሶሶ ምንድነው?

ሰላት።

14 አላህን እና ረሱልን የታዘዘ ምንዳው ምንድነው?

ጀነት መግባት።

15 አላህን እና ረሱልን ያመፀ ምንዳው ምንድነው?

እሳት መግባት።

16 የኢማን መዓዘኖች ስንት ናቸው?

6 ናቸው።

17 (ኢህሳን) ማለት ምንድነው?

አላህን እንደምታየው አድርገህ መገዛት ነው; አንተ ባታየው እንኳን እሱ ያይካልና።

18 የአላህ ስሞች ስንት ናቸው?

ብዙ ናቸው ገደብ የላቸውም።

19_አላህ መላዒካዎችን ከምንድነው የፈጠራቸው?

ከብርሃን።

20 ከመላኢካዎች ውስጥ 4 ጥቀስ?

ጅብሪል

ሚካኢል

አስራፊል

መለኩል መውት።

21 አላህ ያወረዳቸው መፀሃፎች የቶቹ ናቸው ማንስ ላይ ነው ያወረደው?

1- ተውራት በሙሳ ላይ

2- ኢንጂል በኢሳ ላይ

3- ዘቡር በዳውድ ላይ

4- ቁርዓን በሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ።

22_(ኡሉል-ዓዝም) የቆራጥነት ባለቤቶች የሚበሉት ነብያቶች እነማን ናቸው?

1- ነብዩላህ ኑህ

2- ነብዩላህ ኢብራሂም

3- ነብዩላህ ሙሳ

4- ነብዩላህ ዒሳ

5- ነብያችን ሙሃመድ (ሰ.ዐ.ወ)።

23 የመጀመሪያው ነብይ እና የሰዎች አባት ማን ናቸው?

ነብዩላህ አደም።

24_አላህ አደምን ከምን ፈጠራቸው?

ከጭቃ።

25 ያለ አባት የተወለደው ነብይ ማነው?

ዒሳ የመርየም ልጅ።

26 _ አላህን በቀጥታ ያናገረው ነብይ ማነው?

ሙሳ (ዐ.ሰ)።

27_የነብያቶች አባት እና የአላህ ሚስጥረኛ ሚባሉት ነብይ ማን ናቸው?

ነብዩላህ ኢብራሂም።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

02 Dec, 03:00


ነጋ አይደል? በህይወታችን ሌላ አንድ ቁም ነገር የምንሰራበት እድል ተሰጠን ! ምናልባት ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው ምናልባት ነገ የሚባል ቀን የሌለን ሰዎች ነን እና አህባቢ ዛሬን እንኑራት

መልካም ንጋት🥰

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

02 Dec, 02:59


Daily therapy 247🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Nov, 14:01


🔐

ወደት ሄድክ

ወደ ትላንት

ለምን

ነገ አስፈራኝ አሳቀቀኝ

ዛሬህስ

ዛሬ? ትላንትን እየናፈቀ ነገን እየፈራ ለሚኖር ዛሬ ምኑ ነው ያ ሸይኽ

ልክ ነህ በትላንት እየተጎተትክ በነገ እየተሳቀቅክ መኖር ዛሬን ይቀማል አዎ በትላንት ላለመቅረት ወደ ነገ ላለመውደቅ በሚደረግ ትግል ያልፋህ ዛሬህ አንተ ነህ አንተ ዛሬ እንጂ ትላንት አይደለህም ! ማነህ እንጂ ማን ነበርክ አይደለም ቁምነገሩ::
አንተ ወጣት አይንህን ግለጥ ዛሬህ ሳያልቅ!

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Nov, 09:03


የተሰረቀ እቃ ስለ መግዛት
~~~
ነብዩ ﷺ ሰዎች በሐላል ይሁን በሐራም ምንም ሳይጨነቁ ገንዘብ የሚያጋብሱበት ጊዜ እንደሚመጣ መናገራቸው ይታወቃል፡፡ ይሄው የዚህ ዘመን አይነተኛ መገለጫ ሆኗል፡፡ ገንዘብ የሚገኝበትን መንገድ “ሐላል ነው ወይስ ሐራም?” ብሎ ለማጣራት የሚሞክር ሰው ሲበዛ ቀሏል፡፡ ከኖረም ብዙሃኑ ዘንድ እንደ ሞኝ የሚቆጠር እየሆነ ነው፡፡ የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን፣ ሞባይል ስልኮችን፣ አልባሳትን፣ ጫማዎችን፣ … እያወቁ ምንም ሳይመስላቸው የሚሸምቱ ብዙ ናቸው፡፡ ለድሃው ህዝብ የሚቀርቡ የእርዳታ ምግቦች በባለ ስልጣናት እየተዘረፉ ለነጋዴ ይከፋፈላሉ፡፡
ኣኺራውን የሚያስብ ሙስሊም እነዚህን ሌቦችና ዘራፊዎች እቃቸውን በመግዛት ሊተባበራቸው አይገባም፡፡ ሌቦቹ ቢያመጡትም መግዛት አይቻልም፡፡ በቀጥታ ከነሱ በመግዛትም ሆነ በሌላ መንገድ ከያዘ ሰውም መግዛት አይቻልም፡፡ የሌላ ሐቅ እንደሆነ እያወቀ የተዘረፈን ወይም የተሰረቀን ወይም በማጭበርበር የተገኘን እቃ የገዛ ሰው ያለ ጥርጥር ወንጀለኛ ነው፡፡
ከሌባ/ ዘራፊ/ አጭበርባሪ መግዛት
1. የሰው ሐቅ መብላት ነው፡፡
2. ወንጀለኛውን በወንጀሉ እንዲቀጥል ማበረታታ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ)
“በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡” [ማኢዳህ፡ 2]

በኢስላም የተሰረቀን እቃ መገበያየት እንደ ግብይት አይቆጠርም፡፡ ምክንያቱም ሻጩ ባለቤት አይደለምና፡፡ ስለዚህ ግብይቱ በራሱ ውድቅ ነው ማለት ነው፡፡ ወንድሜ ሆይ ይሄ ግብይት ሐራም ስለሆነ ገንዘብህን አታውጣ፡፡ ያለበለዚያ የሰው ገንዘብ ነው እየወሰድክ ያለኸው፡፡ ስለዚህ እቃውን ከመመለስ ውጭ መጠቀም አይቻልም፡፡
ይሄ እቃው የተሰረቀ እንደሆነ ያወቀን ብቻ የሚመለከት አይደለም፡፡ ይልቁንም እቃው የተሰረቀ እንደሆነ ጥርጣሬያችን ካደላም ልንነካካ አይገባም፡፡ ልክ እንዲሁ የተሰረቁ እቃዎች ከሚሸጡባቸው ሱቆችና ቦታዎችም እቃዎችን ልንገዛ አይገባም፡፡ ምክንያቱም:-
አንደኛ፡- የሰው ሐቅ በመግዛት ሐራም ላይ የመውደቅ እድላችን ሰፊ ነው፡፡
ሁለተኛ፡- ወንጀለኞቹን ማበረታታት ነው፡፡

በሌባ በኩል የሚሸጥ እቃ የቀረበለት ሰው ምን ያድርግ?
1. ሌባው እቃውን ለባለቤቱ እንዲመልስ ሊያግባባው አላህን እንዲፈራ ሊገስፀው ይገባል፡፡
2. ፈቃደኛ ካልሆነና የሚቻል ከሆነ በጉልበትም ነጥቆ ቢሆን ለባለቤቱ መመለስ ይገባል፡፡ ፈተና የማይከተለው ከሆነ ማለት ነው፡፡
3. ካልተቻለ ለሚመለከተው ክፍል ሊጠቁመው ይገባል (ምናልባት ከኖረ)
4. ሌሎች ሰዎች እንዳይገዙት ሊያስጠነቅቅ ይገባል
5. ሌባው የሚታወቅና በተግሳፅ የማይመለስ ከሆነ ሰዎች እንዲጠነቀቁት ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡

ከሌባ/ ዘራፊ/ አጭበርባሪ የገዛ ሰው ተውበት ማድረግ ከፈለገ የሚያውቅ ከሆነ እቃውን የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ ባለቤቱን መለየት ካልቻለ በዋጋው ልክ መሰደቅ እና ኢስቲግፋር ማድረግ አለበት፡፡ በኢስላም ወንጀለኛን ከወንጀሉ እንዲመለስ ካልሆነ በስተቀር መተባበር አይፈቀድም፡፡
እቃው የተሰረቀ መሆኑን ከገዛን በኋላ ብናውቅስ?
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “አዎ! የተሰረቀ እንደሆነ ካወቀ ግብይቱ ውድቅ ነው፡፡ እናም ገንዘቡን ወደ ባለቤቱ መመለስ ግዴታ ነው፡፡ የሸጠለትን ሰው ብሩን እንዲመልስለት መጠየቅ አለበት፡፡ የተሰረቀ እንደሆነ ያወቀውን እቃ መጠቀም አይፈቀድለትም፡፡ይልቁንም ለባለቤቱ ይመልስ፡፡ ይህ ነው በሱ ላይ ያለው ግዴታ፡፡…” https://binbaz.org.sa/index.php/fatwas/14772/حكم-من-اشترى-شيىا-مسروقا-وهو-لا-يعلم-بذلك-ثم-تبين-له-انه-مسروق

ሌሎችም እንዲህ የሚል ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው ፈትዋዎች አጋጥመውኛል፡-
ባለንብረቱ ከታወቀ እሱን ማናገር ያስፈልጋል፡፡ “እንዲህ አይነት እቃ ካንተ ተሰርቆ ሳላውቅ በገንዘቤ ገዝቼ ነበር፡፡ ይቅር ትለኛለህ? ወይስ ልመልስ?” ብሎ መጠየቅ፡፡ ስለዚህ ወይ ይቅርታውን ማግኘት፣ ወይ እቃውን መመለስ፣ ወይ ዋጋውን መክፈል፣ ወይ ደግሞ ሌባውን በመጠቆም ፍትህ እንዲያገኝ ማድረግ ይገባል፡፡
ይበልጥ አዋቂው አላህ ነው፡፡

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Nov, 02:53


ንስር አሞራ ለማደን ሲፈልግ ወደታች ይምዘገዘጋል ... ካደነ በኃላ ደግሞ ተመልሶ በከፍታ ይበራል ... ያደነውን አጥንት በድንጋይ ለመስበር ከከፍታ ላይ ሆኖ በመልቀቅ ያጋጫል ... የተሰባበረውን አጥንት ለማንሳት ደግሞ ዝቅ ይላል ... ካነሳ በኃላ እንደገና ወደላይ ይምዘገዘጋል ...

የንስር አሞራ ከፍታውም ዝቅታውም ምክንያታዊ ነው ... ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለህይወትህ አስፈላጊና ምክንያታዊ እስከሆነ ድረስ ከፍም ዝቅም ብለህ ለመኖር ድፍረቱ ይኑርህ ...

ህልምህ ተሳክቶ ስኬትህን ከፍ ብሎ በመብረር ማረጋገጥ እስከምትችል ድረስ ከፍ ማለት ብቻ ሳይሆን ዝቅ ብሎ መብረርን ተለማመድ

          መልካም ቀን❤️‍🩹
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Nov, 02:51


Daily therapy 241🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Nov, 18:04


ሴቶች ከወንድ ልጅ በጣም የምትጠሉት ነገር ምንድን ነው ? ወንዶች ደግሞ ማስታወሻ ያዙ።

ከተፈጥሮአዊ ነገር አይደለም ያልኩት( አላህን በማያሳምፅ መልኩ አርጉት)

اقرأ (አንብብ )

25 Nov, 18:04


ወንዶች ከሴት ልጅ በጣም የምትጠሉት ነገር ምንድን ነው ? ሴቶች ደግሞ ማስታወሻ ያዙ።

ከተፈጥሮአዊ ነገር አይደለም ያልኩት( አላህን በማያሳምፅ መልኩ አርጉት)

اقرأ (አንብብ )

25 Nov, 17:37


ስንረዳ እናጠማለን ...

ሁለተኛ ...ሶስተኛ እድል የሰጡን ሰዎች ያለኛ መሄጃ የሌላቸው ይመስለናል...
  ስህተታችን እያዩ የሚያልፉን ሁሉ ያለኛ መተንፈስ የማይችሉ ይመስለናል...
የሚንከባከቡን ሁሉ እንክብካቤ የማያሻቸው ይመስለናል...
የረዱን ሁሉ እርዳታ የማያስፈልጋቸው ይመስለናል ..
የወደዱን ሁሉ ሊጠሉን የማይችሉ ይመስለናል...

የሚመስለን ነገር ሁሉ ያመንበት ነገር ሁሉ
በደቂቃ ውስጥ ሊገለበጥ ይችላል ማጣትን በነሱ እንዳትቀምሱ አደራ !
  
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Nov, 13:06


መሠበር

አንዳንዴ ለአንዳዱ መሠበር አንቂ ደውል ነው። ባልተሰበረ እቃ መጠቀም ያለውን ፋይዳ ማንረዳበት ጊዜ አለ በመሠበሩ የምናጣውን ነገር ስንገነዘብ ለተሰበረብን ነገር ክብር ይኖረናል በድጋሚ ጠግነን ለሰባሪዎች ስጦታ አንሰጥም ጥንቃቄ እናረግለታለን ። ምናልባት ስለ ልብ ነው ያወራሁት....❤️‍🩹

(ባለዕዳው)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Nov, 10:07


🔐

ፍቅር የለም!

የት ፈልገህ አጣኸው ?

ሰው ሁሉ ይከዳዳል ያሸይኽ ፍቅር ከ ጥቂት አመታት በላይ አይዘልቅም

ፍቅርን አትውቀስ አፍቃሪን ውቀስ አንተ ወጣት!*ፍቅር የሁለት ደቃቃ ፍጡሮች መሳሳብ አይደለም ፍቅር ወደ አልጋ ተኳሽ መድፍ አይደለም ወጣቱ ፍቅር በሰዎች አይገለጥም ፍቅር በ ወንድ እና ሴት አይገደብም ፍቅር ከጌታህ የፈለቀ አለማትን ያካበበ ነው አንተ ወጣት የጌታህ ፍቅር እንጥብጣቤ አለምን እያጣቀመ ነው አንዱ የፍቅር እንጥብጣቤን መጠቀም አቅቶን ሀያሉን ፍቅር አንውቀስ ፍቅር የመኖራችን ቁልፍ ነው አንተ ወጣት ፍቅር ከጌታህ ነው!

(ባለዕዳው)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Nov, 03:04


" ነጋ እንግዲህ አቦ ኤጭ ……" የዕለቱን ጅማሬ ገና ውሉን ሳያውቀው በምሬት የሚጀምር አበዛዙ ። ትላንት ውሎ ጥሩ ስላልነበረ ዛሬም ጥሩ አይሆንም ብሎ የሚያስብ ምስኪን እንጭጭ አዕምሮ አለ ። ስማ እኔ እኮ አምስቴ አግብቼ ፈትቼ ገና አገባለሁ የምል ብቸኛው ኢትዮጵያዊ እኮ ነኝ ። ምን ዝም ብሎ ማማረር ነው!!! ብሶት ሰውን የሚቀይር ቢሆን ኖሮ ምድር ትጠበን ነበር ። አታማርሩ ይልቅ ተማሩ ፣ አታኩርፉ እረፉ ፣ አትወዘጋገቡ ከራሳቹህ ጋር ተግባቡ!!! ሲነጋ የሚጨንቃቹህ ከጨለማ ጋር የጀመራችሁት ነገር አለ እንዴ??? መጠርጠር ነው ወዳጄ!!! ፊታችሁን የምትዘፈዝፉ አስቲ አስጡት!!! ወደ ንጋቱ ስንገባ ጅማሬያችን አካሄዳችንን ይወስናል ። ስንጀምር ከእግር አጣጣላችን ጋር የሚስማማውን እንምረጥ!!! ነጋ እንግዲህ……አቦ ኤጭ የሚገርም ውሎ ልውል ነው!!!! ደስ ሲል………
       አብዱልሀኪም ሰፋ

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Nov, 03:03


Daily therapy 240🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Nov, 17:59


ህይወት ምን አስተማረቻችሁ ?

اقرأ (አንብብ )

24 Nov, 17:35


.
ፈገግታህስ

ቀሙኝ

ቀሙኝ ? ቀሙህ ወይስ ሰጠሀቸው?

አምኛቸው ነበረ ከዱኝ ረዳታቸው ለመሆን ጥሬ ነበር እርዳታቸውን ስሻ ሸሹኝ ለደስታቸው ተደስቼ ነበር ለሀዘኔ ተደሰቱ

ፈገግታህ ከክህደታቸው ይልቅ ውድ ነው አንተ ወጣት! ጥሩነትህ ከ ክፋታቸው የላቀ ነው ፈገግታህን ለመቀማት የሚችል አቅም የላቸውም ከቀሙህ ባንተ እርዳታ ነው ወጣቱ

እንዴት ያ ሸይኽ በኔ እርዳታ?

አንተ ወጣት እምነትህ ቦታው ከፈጣሪህ ነው እርዳታህ ምንጩ ከ ጌታህ ነው አንተ ወጣት ደስታህ በሰዎች ጫንቃ ላይ ላለመውደቅ እንዲያጣጥር ወስነህ አትስቀለው አንተ ወጣት ተዓደብ

(ባለዕዳው)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Nov, 12:25


ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (aic aill oj) እንዳስተላለፉት የአላህ

መልእክተኛ ()

እንዲህ ብለዋል:-

“ውዱእ በስትክክል አድርጎ _ አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢል አሏህ ወህዳሁ ላ ሻሪክላህ ፣ ወአሽሀዱ አና ሙሀመድን አብዱሁ ረሱሉሁ (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፣ አጋርም የሌለው ጌታ ነው፣ ሙሐመድም የሱ ባሪያና መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ) ያለ ሰው ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለታል በፈለገውም ይገባል።"

[ሳሂህ ሙስሊም 234]

8ቱ የጀነት በሮች

1. ባብ አስ-ሰላት

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ ሰላታቸውን በትኩረት ፣ በወቅቱ እና ሳያቋረጡ የሚሰግዱ ናቸው፡፡

2. ባብ አል-ጂሃድ

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ በአላህ መንገድ ተዋግተው ህይወታቸውን የሰዉት ናቸው፡፡

3. ባብ አስ-ሰደቃህ

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ ለአላህ ሲሉ ምስኪንን ሲመግቡ የነበሩ ወይም ሰደቃ ሰጪዎች ናቸው፡፡

4. ባብ አር-ራያን

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ የአላህን በረካ ፈልገው ብቻ ፆማቸውን አብዝተው የሚፆሙ ናቸው፡፡

5. ባብ አል-ሃጅ

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ ሃጅ እና ኡምራቸውን በስነ-ስርዓቱ ያደረጉ ናቸው፡፡

6. ባብ አል-ካዚሚን አል-ጋይዝ ዋል አፊና አኒን ናስ


7. ባብ አል-አማን

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ በአላህ ላይ ባላቸው እምነት የሚፀኑ ፣ በአላህ ቀድር እምነት ያላቸው እና የአላህን ትእዛዝ የተገበሩ ናቸው፡፡

8. ባብ አል-ዚክር

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ አላህን ያለማቋረጥ ሲያስታውሱ የነበሩ እና ዚክር የሚያበዙ አማኞች ናቸው፡፡

"ማስታወስህን ቀጥል፤ ማስታወስህ ሙእሚኖችን ይጠቅማልና።"

[ሱራህ አል ኢንሳን 51:55]

ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል᎓ "አንድን ሰው ወደ መልካም ነገር የመራ ሰው ከመራው ሰው እኩል ምንዳ አለው (ምንም ሳይቀንስበት)።"

[ሳሂህ ሙስሊም 1893]

#በየትኛው_መግባት_ትፈልጋላችሁ?

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Nov, 06:53


ለሁሉም ሰው መልካም ነገርን እንድመኝ ሕይወት አስተማረችኝ ።

የነርሱ መደሰት ከኔ ደስታ አይቀንስም።

የነርሱ ማግኘት ከኔ ሲሳይ አያጎድልም።

የነርሱ ጤና መሆን የኔን ጤና አይረብሽም።

የነርሱ ሰላም መሆን የኔን ሰላም አያደፈርስም።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Nov, 06:51


Daily therapy 239🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

23 Nov, 18:37


.
ናፍቆትን ለፆመ ማፍጠሪያው ምን ይሆን?💔

اقرأ (አንብብ )

23 Nov, 18:30


ibro smile የሚለውን ስም ልቀይረው አስቤያለው ማን ይሁን? ወይስ ራሱ ይቆይ ?

اقرأ (አንብብ )

23 Nov, 17:51


የሬሳ ሳጥን ሻጩም በልቶ ማደር ስላለበት ነው!

اقرأ (አንብብ )

23 Nov, 16:33


#የጀናዛ_ሰላት_አሰጋገድ
አራት ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤
☞ ከመጀመሪያ ተክቢራ በመቀጠል አል ፋቲሀ (የመክፈቻው ምዕራፍ) ይነበባል።
ከዚህም በተጨማሪ አጠር ያለ የቁርአን ምዕራፍ ወይም አንድ ወይም ሁለት አንቀፅ
ቢያነብ ጥሩ ነው። ይህንን በማስመልከት ከአብደላህ ኢብን አባስ የተዘገበ ትክክለኛ
ሀዲስ ስላለ ነው።
☞ ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤
ከተሸሁድ ቀጥሎ እንዳለው በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳል። ከዚያም በሶስተኛው ተክቢራ
ከተደረገ በኃላ እንዲህ ይላል
( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟِﺤﻴﻨﺎ ﻭﻣﻴﺘِﻨﺎ، ﻭﺷﺎﻫﺪﻧﺎ ﻭﻏﺎﺋﺒﻨﺎ، ﻭﺻﻐﻴﺮﻧﺎ ﻭﻛﺒﻴﺮﻧﺎ، ﻭﺫَﻛَﺮِﻧﺎ ﻭﺃﻧﺜﺎﻧَﺎ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻣﻦ ﺃﺣﻴَﻴﺘَﻪُ ﻣﻨﺎ ﻓﺄﺣﻴﻪ
ﻋﻠﻰ ﺍﻹﺳﻼﻡ، ﻭﻣﻦ ﺗﻮﻓﻴﺘﻪ ﻣﻨﺎ ﻓَﺘَﻮَﻓﻪُ ﻋﻠﻰ ﺍﻹﻳﻤﺎﻥ، ﺍﻟﻠﻬَﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻪ، ﻭﺍﺭﺣﻤﻪ، ﻭﻋﺎﻓﻪ، ﻭﺍﻋﻒ ﻋﻨﻪ، ﻭﺃﻛﺮِﻡ
ﻧُﺰُﻟَﻪ، ﻭَﻭَﺳﻊ ﻣُﺪﺧَﻠَﻪ، ﻭﺍﻏﺴﻠﻪ ﺑﺎﻟﻤﺎﺀ ﻭﺍﻟﺜﻠﺞ ﻭِﺍﻟﺒﺮﺩ، ﻭﻧﻘﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﺨﻄﺎﻳﺎ ﻛﻤﺎ ﻳﻨﻘﻰ ﺍﻟﺜﻮﺏ ﺍﻷﺑﻴﺾ ﻣﻦ ﺍﻟﺪَﻧﺲ،
ﻭﺃﺑﺪﻟﻪُ ﺩﺍﺭﺍ ﺧﻴﺮﺍ ﻣﻦ ﺩﺍﺭﻩ، ﻭﺃﻫﻼ ﺧﻴﺮﺍ ﻣﻦ ﺃﻫﻠﻪ، ﻭﺃﺩﺧﻠﻪ ﺍﻟﺠﻨﺔ، ﻭﺃﻋﺬﻩ ﻣﻦ ﻋﺬﺍﺏ ﺍﻟﻘﺒﺮ، ﻭﻋﺬﺍﺏ ﺍﻟﻨﺎﺭ،
ﻭﺍﻓﺴﺢ ﻟﻪ ﻓﻲ ﻗﺒﺮﻩ، ﻭﻧﻮﺭ ﻟﻪ ﻓﻴﻪ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻻ ﺗَﺤﺮﻣﻨَﺎ ﺃﺟﺮﻩ ﻭﻻ ﺗُﻀِﻠﻨﺎ ﺑﻌﺪﻩ )
(አላሁመ ኢግፊር ሊሐይና ወመይቲና ወሻሂድና ወጋኢቢና ወሰጊሪና ወከቢሪና ወዘከሪና
ወኡንሳና አላሁመ መን አህየይተሁ ሚና ፈአህይሂ አለል ኢስላም ወመን ተወፈይተሁ
ሚና ፈተወፈሁ አለል ኢማን አላሁመ ኢግፊር ለሁ ወግሲልሁ ቢልማኢ ወሰልጂ
ወልበረዲ ወነቂሂ ሚነል ዙኑቢ ወል ኸጣያ ከማ ዩነቀሰውቡል አብየዲ ሚነደነሲ
ወአብዲልሁ ዳረን ኸይረን ሚን ዳሪህ ወአህለን ኸይረን ሚን አህሊህ ወአድኺሉሁል
ጀነተ ወአዒዙሁ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወዓዛቢ ናር ወፍሰህ ለሁ ፊ ቀብሪሂ ወናዊርለሁ ፊህ
አላሁመ ላተህሪምና አጅረሁ ወላቱዲለና ባዕደሁ።)
ትርጉሙም: “አላህ ሆይ በህይወት ያሉትንም፣ የሞቱትንም፣ በቅርብ ያለውንም ሩቅ
ያለውንም፣ ትልልቆችንም፣ ትንንሾችንም፣ ወንዶችንም ፣ ሴቶችንም ማርልን። አላህ ሆይ
ከመካከላችን የምትገለውን በእምነት ላይ እንዲሞት አድርገው። አላህ ሆይ ምህረት
አድርግለት፣ እዘንለትም፣ ከእሳት ጠብቀው፣ ይቅርም በለው፣ መስተንግዶውን አሳምርለት፣
መግቢያውንም አስፋለት፣ አጢአቱንም በውሃ፣ በበረዶና በቀዝቃዛ ውሃ እጠብለት፣ ነጭ
ልበስ ከቆሻሻ እንደሚፀዳው የእርሱንም ወንጀል አፅዳለት፣ ከቤቱ የተሻለ ቤት ከሚስቱ
የተሻለ ሚስት ቀይርለት። ወደ ገነት አስገባው፣ ከቀብር ውስጥ ቅጣትና ከእሳትም ቅጣት
ጠብቀው ቀብሩንም አስፋለት፣ አብራለት። አላህ ሆይ ምንዳውን አትንፈገን ከእርሱም
በኃላ እጣችንን ጥመት አታድርግብን።”
ማለት ነው።
☞ ከአራተኛው ተክቢራ በኃላ በቀኝ ጐኑ ብቻ “አሰላሙአለይኩም” በማለት
ያጠናቅቃል።
ተክቢራ በሚደረግበት ጊዜ እጅን ማንሳት ይወደዳል።
√ ሴት ከሆነች ዱዓው ላይ እንዲህ ይባላል፤
( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻬﺎ . . ) (አላሁመ እግፊርለሃ)
√ ሁለት ከሆኑ ደግሞ ( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻬﻤﺎ . . . ) (አላሁመ እግፊር ለሁማ)
√ ከሁለት በላይ ከሆኑ ደግሞ ( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻬﻢ . . ) (አላሁመ እግፊር ለሁም) ይባላል።
√ ሟቹ ህፃን ከሆነ ለእርሱ ምህረትን በዱዓው ውስጥ ከመለመን ይልቅ እንዲህ
ይባላል።
( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺟﻌﻠﻪ ﻓﺮﻃﺎ ﻭﺫُﺧْﺮَﺍ ﻟﻮﺍﻟﺪﻳﻪ، ﻭﺷﻔﻴﻌﺎَ ﻣُﺠَﺎﺑﺎ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺛﻘﻞ ﺑﻪ ﻣﻮﺍﺯﻳﻨﻬﻤﺎ، ﻭﺃﻋﻈﻢ ﺑﻪ ﺃﺟﻮﺭﻫﻤﺎ، ﻭﺃﻟﺤﻘﻪ
ﺑﺼﺎﻟﺢ ﺳﻠﻒ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ،

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

19 Nov, 11:07


ስሚኝ ሴትዋ😊

ነብያችን  ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የረገሟቸው የሆኑ 10 ሴቶች


እነሱም

1 ጅስሟን የምትነቀስ ተነቃሿም ነቃሿም

2 ቅንድቧን የምተቀነደብ ቀንዳቢዋም ተቀንዳቢዋም

3 አርቲፊሻል ፀጉር የምትቀጥል  ቀጣይዋም ተቀጣይዋም

4 ባሏን የምታስቀይም የምታናድድ  የሱን ሀቅ የማትጠብቅ

5 በአለባበሷም ሆነ በማንኛውም ነገር ከወንድ ጋር የምትመሳሰል

6 ቀብር የምትዘይር

7 ሰው ሲሞት እየጮሀች እያለቀሰች ልብሷን እየቀደደች ሰውን የምታስለቀስ

8 ባሏ 3 ጊዜ  ፈቷት የሸሪአን ህግ ጥሳ ሌላ ሳታገባ እሱጋ የምትመለስ

9 ጥርሷን የምትጠረብ ለጌጥ ጥርሷን የምትቀይር

10 ሙተበርጃ  ተገላልጣ የምትሄድ   የምትራቆት ለአጅነብይ

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

19 Nov, 09:04


🗣 ስማኝ ወንዱ...

የ አንድን ሴት ህይወት ስታበላሸው እንደ ባንክ
ብድር አስበው ከነ ወለዱ ትከፍለዋለህ።
#ጠብቅ!

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

19 Nov, 03:06


#የበረካው_ወቅት

አሰላቱ ኸይሩን ሚንነውም

ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች

ሲል የፈጅር ሙዓዚኑ

ምላሻችን፦ “ሰደቅተ ወበረርተ” “

ዐሊሞቹ ይህን ሲያብራሩ "ሰደቅት" ማለት አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያሉት ነገር ትክክል ነው። "ወበረርት" የሚለው ደግሞ አንቱ እኛን በማስተማርዎ ሰበብ ከተመረጡት ባርያዎች መካከል እንድንሆን አደረጉን ይህንን ቃል እንድንመልስ ከእንቅልፍ የምትበልጠውን ሰላትም እንድንሰግድ አደረጉን።

አላህ ከዚህ ምርጥ በረከት አይከልክለና!

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

19 Nov, 03:05


Daily therapy 234🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

18 Nov, 17:47


ምንም እንኳን ብዙ ተከታይ ባይኖረኝም በየጊዜው የሚጠብቀኝና የሚከታተለኝ በኔ የሚጠቀም አንድ  ሰው ሊኖር ይችላል ብዬ ስለማስብ ብቻ እንደምንም ብዬ በየቀኑ የሆነ ነገር እጽፋለሁ።
ሰው ሁሉ ቢያንስ አንድ ወዳጅ አለው።
አይደለም እንዴ!
ቢሆንም ግን አልሃምዱሊላህ 😊

ibro smile

اقرأ (አንብብ )

18 Nov, 17:40


የፍርድ ቤት ዳኛው የገዳይን እጅ እያለቀሰ
                የሳመበት ክስተት

   እንደ አውሮጳውያን የዘመን ቀመር 1910 በቤሩት ምድር በአንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ የሚርመሰመስ ሰው የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ድምፁን ከፍ አድርጎ ይሳደባል።

    አንድ መንገደኛ ውስጡ በግኖና በንዴት ጦፎ ከኋላ ኋላ ይከተለዋል። ቢላ በሚሸጥበት ሱቅ በኩል ሲያልፍ ወደ ውስጥ አቀናና አንዱን ቢላ መዞ በተሳዳቢው ጉሮሮ ላይ ሰካው። ወደ ውስጥ በመሰምጠጥ ደምስሩን በጥሶ ገደለው።

   ጉዳዩን ሲመረምር የነበረው የቤሩት ከፍተኛ ወንጀል ችሎት ከሁለት አመታት በኋላ ወንጀለኛው ለውሳኔ ይቀርብ ዘንድ አስጠራው። ተከሳሹ ችሎት ፊት ቆመ። አዳራሹ በሰው ተጨናንቋል። ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቷል።

"ሰውየውን ለምን ገደልከው?" የዳኛው ጥያቄ ነበር

"የአላህን መልዕክተኛን(ሰ.አ.ወ) ሲሳደብ ሰማሁትና በእጅጉ ተናደድኩ ስለረሱል ክብር ስል ገድዬ ለመሞት ራሴን አዘጋጀሁ በንዴት ገንፍዬ ጉሮሮውን በጠስኩት" ሲል መለሰ።

ዳኞቹ እርስ በርሳቸው ከተወያዩ በኋላ
"ሆን ብለህ የግድያ ወንጀል ፈጽመሃል ፍርድ ቤቱ የ15 አመት ጽኑ እስራት ፈርዶብሀል። ድርጊቱን የፈፀምከው በንዴት ነውና ቅጣቱ ግማሽ በግማሽ ተቀንሷል። ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ባመነበት ምክንያት የታሰረበት ጊዜ በቂ ስለሆነ እንዲለቀቅ ወስኗል መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት" የሚል ውሳኔ አስተላለፈ።

ዳኛው ከውሳኔው በኋላ "ፖሊስ ሆይ ወንጀለኛውን ፍታው" ሲል አዘዘ ከፍርድ ቤቱ የመቀመጫ ወንበርና ቅስት ወርዶ። ወደ ሰውዬው ቀረብ አለና "ልጄ ሆይ የምንወዳቸው ነቢን(ሰ.አ.ወ) የተሳደበውን ሰው በየትኛው እጅህ ነው የገደልከው?" ሲል ጠየቀ
"በቀኝ እጄ" አለ
"ልጄ እጅህን ዘርጋልኝ"
  እጁን ዘረጋ
     ዳኛው እያለቀሰ እጁን አቅፎ ይስመው ጀመር።

በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት ሁሉ በእንባ ተሞልተው ተላቀሱ። የቤሩት ፍትህ ሚኒስትር የፍርድ ቤቶች ዋና ሀላፊ ዳኛው የገዳዩን እጅ በመሳሙ ወደ መዲና እንዲዛወር ውሳኔ ተላለፈ። የዳኛው የዘወትር ህልም ተፈፀመ። አላህ ዱዓውን ተቀበለው።

"ጌታዬ ሆይ! የህይወቴን የመጨረሻ ቀናት ረሱል ባሉበት ከተማ ላይ አድርግልኝ ከሳቸው ጋርም አጎራብተኝ" በማለት ዱዓ ያደርግ ነበር።

ዳኛው ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን እሱ ዩሱፍ አን-ነብሃኒ ይባላል።
የአላህ እዝነት በእርሳቸው ላይ ይሁን

 @anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

18 Nov, 02:56


« በትክክለኛው መንገድ ለሚገባሽ ሰው እንዳታልቂ፣ የልብሽን ቀሚስ ላላፊ አግዳሚው አትግለቢ። አላህ ለማያዝንብሽ ግንኙነት ገላ ብቻ ተሸክመሽ እንዳትኖሪ፣ ልብሽን ዘልዛላ አታድርጊው። እቴ ከአጉራ ዘለል ፍላጎትሽ ጋር አኩኩሉ አትጫወቺ።
ልብሽ አደብ ካልያዘ ዝሙት አይከብድሽም።
እቴ ውበት እና ክብርሽን ካጣሽ፣ ዳግም መታደስ ከፈለግሽ በተውበት በር ዝለቂ። አላህ በቃ እስካላለ ድረስ ምንም የሚያበቃ ነገር የለምና ሰዎች ተስፋ ሲያስቆርጡሽ አላህ ዘንድ ተሸሸጊ። አላህ ጥፋቶችን በመላ ይምራልና ለተውበት አትኩሪ! እቴ ልብሽን ጠብቂ! የምወድሽዋ ሰላም ለልብሽ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

18 Nov, 02:54


Daily therapy 233🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 18:31


ከየትኛው ናችሁ?

1 አባዬ መውጣት እችላለሁ?  (🙏)

2 አባዬ እየወጣው ነው!  (👏)

3 አልወጣም (🥰)

4 ሳትናገሩ ላጥ  (😂)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 18:28


አሁን የምትኖረው ህይወት ነገ የምትተርከው ምርጡ ጊዜህ ነው

የስኬት መንገድህ ላይ ታገል ልፋ🦋

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 18:21


ህይወት የምትወደውን ነገር ሁሉ አትሰጥህም 
መብቃቃት ግን ያለህን ነገር ሁሉ እንድትወድ ታደርግሃለች ❤️‍🩹

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 16:20


የውስጤን የማወራ አይነት ሰው አልነበርኩም....ለምወዳቸው ሰዎች ሳቄን እንጂ መከፋቴን ማጋባት በደል የሚመስለኝ....ሲከፋቸው ቀድሜ ብደርስም....ሲከፋኝ ብቻዬን መብሰልሰልን የምመርጥ አይነት...

ልቤ ላይ የገዘፈ ቦታ ላላቸው የኔ ሰዎች ማዘኔን አውርቼ በማምናቸው ልክ ባይደነግጡስ?....በማስበው ልክ ጉዳዬን እንደጉዳያቸው ባይቆጥሩትስ? ደና እንድትሆኚ ምን እናግዝሽ ይሉኛል ብዬ ስጠብቅ....ግድ ባይሰጣቸውስ? ለራሴ ቢተውኝስ ብዬ እፈራለሁ....አብረውኝ አልነበሩም አልሆኑም ማለትን አልሻም!

ጉዳዬን አቅልለውት ከልቤ ላይ ግዙፍ ቦታቸው ቢጎልብኝስ? መውደዴ ቢቀንስስ? በፈተናዬ ተፈትነው ቢወድቁብኝስ እላለሁ።
(ቸልተኝነት ገዳይ በሽታ ይመስለኛል!)

መውደዴን እወደዋለሁ....የሁሉንም ጉዳይ እንደራሴ ቆጥሬ መብሰልሰሌ ህመም ቢፈጥርብኝም ከነ ህመሜ በሌሎች ደስታ መፈንጠዜን ፥ በሌሎች ሃዘን መከፋቴን እወደዋለሁ።
" ነፍሴን ጠብቅልኝ " እያልኩ ዘወትር በለሆሳስ አንሾካሽካለሁ!

ታዲያ ወዳንተ ስመጣ ብዙ ነገሬ ተቀየረ....ድብቅነቴን ፥ እሩቅነቴን ሸነቆርከው መሰል ሁሉ ነገሬ ማብቂያው ላንተ ማውራት ሆነ።

ይገርመኛል.......
እራሴን ማበርታት እንደምችል እያወኩት ጥንካሬዬን በአይዞሽ ማንሾክሾክህ ውስጥ ቀበርኩት....የቀኔን ድምቀት እያወኩት " መልካም ቀን " ከሚለው የማለዳ መልዕክትህ ላይ ቋጠርኩት....የሰላማዊ እንቅልፌን ሰበብ ሳልረሳ " እደሪልኝ " መባሌን ተንተራስኩት......
ልቤን ስለማምነው ተከትዬው ዛሬ ላይ አቁሞኛል! የልቤን ያህል አምኜሃለሁ!
ከሙላትህ እንዳትጎድልብኝ.....
      Sadiya

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 13:38


እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል አልሀምዱሊላህ

ዛሬ ህዳር 8/2017 ዓ.ም በመርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ ጀርባ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በአካባቢው ህብረተሰብ እና በእሳት አደጋ ሰራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እሳቱን ለመቆጣጠር ተችሎል ።

መርካቶ በተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎ እየተነሳ ስለሆነ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊያበጅለት ይገባል ። እሳት ተነስቶ መጥፍቱ ትርጉም የለውም እስኪጠፍ በርካታ ገንዘቦች እየጠፉ ስለሆን ጥንቃቄ ቢደረግ የሚመለከተው አካል ዘላቂ መፍትሄ ያብጅለት።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 10:31


< ከዘመናት በፊት አንድ ባለ ሀብት ነበር። ይህ ባለ ፀጋ ድንገት በአንዱ እለት አንዲትን ውብ ባሪያ ይመለከታል። ባለ ፀጋው በውበቷ ስር ወደቀ። በነጋ በጠባ ቁጥር ምስሏ በምናቡ ይመላለሳል። ትውስታዋ ከልቦናው ሊፋቅ ተሳነው። የፍቅሯ ታሳሪ ሆነ። በፍቅርና በናፍቆት መሀል የምትናወጥ ልቡን ይዞ ወደ አሳዳሪዋ አመራ። ባሪያይቱን ከፍ ባለ ገንዘብ ሊገዛት ጠየቀው። የባሪያዋ አሳዳሪም ባለ ፀጋው ከባሪያዋ ጋር በፍቅር መውደቁን ከአይኖቹ ተረዳ። አሰብ አደረገና። " አይ በዚህ ዋጋ አትሸጥም! " በማለት ያለውን ሁሉ አስረክቦ ባሪያይቱን እንዲገዛው አደረገ። ባለሀብቱ የለበሰውንም ባርኔጣና ኩታን ሳይቀር አስረክቦ ተፋቃሪውን ይዞ ተጓዘ። >

  አየህ አይደል! አፍቃሪ ላፈቀረው ነገር ያለውን ሁሉ ይሰዋል። ሚሰዋው ቢጠፋ የቀረችው አንዲትን ነፍስ እንኳን ብትሆን እርሷንም አይሰስትም። የርሱ መሻት የተፈቃሪው ደስታና ውዴታን መጎናፀፍ ነው። ታድያ በፍጡራን መካከል ላለ አላቂ ፍቅር ይህን ያህል ቤዛ የሚደረግለት ከሆነና ሀብትና ንብረትን እስከማጣት ካስደረሰ ፡ ስለምን የጌታህን ፍቅር ያለ ምንም ክፍያ ትሻለህ? ክልከላውን ስትዳፈር ልብህ ላይ ያለው የማፍቀር ሂማ እየሞት እንደሚጠፋ ተሰወረህ? የትዕዛዙን በትር ስትይዝ የኩራትን ኩታ ከደረብክም በራስህ ላይ የፅልመት ካባን ነው የደረብከው። እኔነትህን ጥለህ ቅረበው። መሻትህን ግደለው። ምንምነትህን ገልጠህ ከዱንያ ፍቅር ተራቁተህ ቅረበው። ጣላት ይህችን ነፍስ! ተዋድቀህ የእውነት ሚስኪንና አሳዛኝ ባሪያ ሁንለት። እንዲያ ነው ፍ ቅ ሩ ን የምታገኝ!

(አብዱ ሩሚ)

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 02:31


« አንቱ ሰው እስቲ ምከሩኝ? »
« የኔ ልጅ አንድ ሰው ነበር። እሱም ዝሙት ፈፀመና ስላረካኸኝ ተመስገን ጌታዬ አለ። »
« ጌታውን እንዴት ቢንቀው ነው? »
« አለማወቅ ጌታን ያስንቃል። የኔ ልጅ ጌታህን እንዳትንቀው እወቀው! »
« አንቱ ሰው እወዶታለሁ! »
« ከጌታህ ዘንድ ክብር አትጣ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 02:30


« ጌታዬን በደንብ እንዳውቅ ሰበብ የሆነኝ ሰው ከሰዎች ሁሉ በላጩን ውለታ ውሎልኛልና ባለ ዕዳው ነኝ። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:

اقرأ (አንብብ )

17 Nov, 02:29


Daily therapy 232🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

16 Nov, 19:02


አላህ ይዘንልን💔

اقرأ (አንብብ )

16 Nov, 18:40


ታሪኩን ወደዳችሁት? እንዴት ነበር?ከታሪኩ ምን ተማራችሁ?

اقرأ (አንብብ )

16 Nov, 18:35


ካይኖቹ የሚሰፈው እምባ ባንገቱ ላይ ቁልቁል ወደ ደረቱ ይወርዳል፡፡ በፊቱ ላይ እንደ ሀረግ የተጋደሙት የደም ስሮቹ ተወጣጥረዋል፡፡ ጨርቁን የጣለላትን ለይላ በሞት ያጣው መጅኑን አቅሉን ስቶ ይጮሀል....ለይላላላላላ ለይላዬ እባክሽን ጥለሺኝ አትሂጂ እባክሽ! ... ስንት ጊዜ ነው ብቻዬን ጥለሺኝ የምትሄጂው? ለምንስ እንደዚህ አምርረሽ መሄድን ወደድሽ??? ለይላ.....  እያለ ይንሰቀሰቃል፡፡ ሙሉ የሷ ዘመዶች የመጅኑን ቤተሰቦች ጨምር ከነጅድ በለይላ ሞት ምክነያት ዲመሽቅ ተገኝተዋል፡፡ እናትና አባቷ ሙሽራዋ ልጃቸውን ድንገት ሞት ነጥኳቸው ድንዝዝ ብለው ለበድንነት ቀርበዋል፡፡ መጅኑን ክፉኛ ልቡ ተሰብሮ እስከምትቀበር ድረስ ያለ ሟቋረጥ ሲጮህ ለቀስተኛው ሁሉ ልቡ ፈንድቶ እንዳይሞት ፈርተው ስጋት ገብቷቸው ነበር፡፡

ለይላ ተቀብራ ከሳምንት በኀላ ቤተሰቦቹ ሁሉ ወደ ነጅድ ሲመለሱ መጅኑን ግን ዲመሽቅ ከለይላ መቃብር ቦታ ቀረ፡፡ ቀሪ ህይወቱን ከሷ ዘንድ መቆየትን ወደደ፡፡ ቀኑንም ሌሊቱንም መቃብሯን እየዞረ ያለቅሳል፡፡ ሲሻው ወደ መኖሪያ ቤቷ ሂዶ ሙሾውን ያወርዳል፡፡

አሙሩ አለዲያሪ ዲያሪ ለይላ
ኡቁቢሉ ዘልጂዳራ ወዘልጂዳራ
ወማሁቡ ዲያሪ ሸገፍነ ቀልቢ
ወላኪን ሁቡ መን ሰከነ ዲያራ

እግሮቼ በለይላ መኖሪያ አካባቢ ይጓዛሉ በዛ መንገድ በምጓዝ ጊዜ ቤቷን ሳየው ከቤቷ ውስጥ ባትኖርም ጎራ ብዬ ፈልጋታለሁ፡፡ የቤቷንም ግድግዳ እስመዋለሁ ፣ ምሶሶውን አቅፈዋለሁ፡፡ ነገር ግን ቤቱን የምስመው እንጨት የመሳም ፍቅር ኖሮብኝ ሳይሆን ይህ ቤት አንድ ወቅት ለይላን ይዞ የነበር ቤት ስለሆነ ነው፡፡ እሱ ከንጨትነትም በላይ ለኔ ትርጉም አለውና ነው፡፡ እያለ ያለማቋረጥ ያነባል፡፡

በዚህ ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ብዙ ቀን እና ምሽቶች ተፈራረቁ፡፡ ከሷ ሞት በኀላ እንደሷው ሁሉ ከምግብ እና ከውሀ እርቆ የሞት አፋፍ ላይ ደርሷል፡፡ እሷ የሌለችበት ህይወቱ ለሱ ምንም ነውና የሞቱን ቀን በናፍቆት ይጠባበቃል፡፡ በዛለ ሰውነቱ ወደ መቃብሯ ያዘግማል፡፡ በአንዱ ቀን ካለበት ጫካ ወደሷ ዘንድ ሲሄድ አቅም አጥቶ ካንድ ዲንጋ ስር አረፍ አለ፡፡ በርሀቡ ላይ ህመም ተጫጭኖታል፡፡ እንደዛም ሁኖ ለይላ ጋር ለመድረስ ይፍጨረጨራል ሆኖም ግን ከተቀመጠበት እንኳን መነሳት ተሳነው፡፡ መጅኑን እየሞተ እንደሆነ ተሰምቶታል፡፡ እዛው የተደገፈው ዲንጋይ ላይ እንዳለ ከኮሮጆው ውስጥ መድ እና ቀሰሙን አውጥቶ በወረቀት ላይ ግጥሞቹን እየሞነጫጨረ ሳለ በሰመመን አይኑን ከደነ፡፡

ተወሰደ አህጃረል መሀሚሂ ወልቀፍሪ
ወማተ ጀሪሀል ቀልቢ መንደሚለ ሶድሪ
ፈያልይተ ሀዘል ሁበ ዩእሸቁ መረተን
ፈዩእለም ማ የልቀል ሙሂቡ ሚን ሀጅሪ

ይህ ባካኝ የለይላ አፍቃሪ በዚህ በረሀማ ጫካዎች ዲንጋዮችን ተንተራሰ፡፡ ልቦናው ቆስሏል ፣ ከደረቱም ላይ የስቃይ ደም ይንቆረቆራል፡፡ እንዲህ እያደረገ የሚያሰቃይ ፍቅር ካሁን በኀላ እንዴት ነው ሊወደድ የሚገባው? ያፈቀረ ሰው እኮ ምን ያክል መንገላታት እና መከልከል እንደሚደርስበት መታወቅ አለበት! ያፈቀሩትን ሰዉ የማጣት መሪርነቱ ሊታወቅ ይገባል! እኔ በጣም ተጎድቻለሁ ፣ የማፈቅራትን ለይላ አጥቼ ስሰቃይ በዚህ መልኩ ነው እየሞትኩኝ ያለሁት፡፡ የሚል ግጥሙን ሞነጫጭሮ የሞተችው ፍቅሩን ተከትሏት ይቺን አለም ተሰናበተ፡፡ በህመም እና በስቃይ የተሞላው ፍቅራቸው በሞት ተቋጨ፡፡🥺😔  በመጨረሻም በህይወት ሳሉ የሚመኙትን አብሮነት መጅኑንን ከለይላ አጠገብ በመቅበር በሞታቸው ጊዜ ሞሉላቸው፡፡


ተፈፀመ!


For  any comment  👉
@anbeb_islamic_bot
@ibro_smile

اقرأ (አንብብ )

12 Nov, 18:18


ምን ድረስ ወይም ምን ያኽል ሐብታም መሆን ትፈልጋላችሁ?

اقرأ (አንብብ )

12 Nov, 18:00


(መጅኑነ ለይላ)

ክፍል 4 መሊኩ

ለምሽት የስግደት ፀሎት ሰርክ ከመስጂድ እንደሚመላለስ ፅኑ ምዕመን መጅኑንም ጨለማን እየጠበቀ ከለይላ ቤት መመላለሱን ተያይዞታል፡፡ ሆኖም ግን ከዛን ምሽት በኀላ ለይላ የውሀ ሽታ ሆና ቀረች፡፡ ስለሷ የሚያወራን አንደበት ጆሮው ፈልጎ አጣ፡፡ በየቀኑ ወደ ቤቷ ሄዶ ሲያጣት የቀንዲሉ#1 ሞራ እንዳለቀበት የሌሊት ፀሀፊ በብስጭት ፀጉሩን እየነጨ ይመለሳል፡፡ ባንዱ የተረገመ ቀን አባቷ ወደማይታወቅ እሩቅ ሀገር እንደላካት ሰምቶ ቁርጡን አወቀ፡፡ ግን የት? አያውቅም፡፡ ሳይታክት ሰርክ ፈለጋት ፣ አስፈለጋት ለይላ ግን የለችም፡፡ ቀናት ፣ ሳምንታት ፣ ወራቶች ነጎዱ....... በህመሙ ላይ ድርብ ስቃይ ታከለበት ፣ ሰው ጉድ እስኪል ድረስ እንዳይሆኑ ሆኖ ከሰውነት ተራ ወጣ፡፡ ክፉኛ ተጎሳቆለ፡፡ ለወራቶች ዋቢ ያጣው ፂሙ እስከ ደረቱ ድረስ ተንዠረገገ ፣ በቀን አስር ጊዜ የሚበጠር የነበረ ቄንጠኛ ፀጉሩ አመድድድ መስሎ ተንጨባረረ፡፡ ጠኔ እንደያዘው እራብተኛ ሰው ከመነመነው ሰውነቱ ላይ የሚዋልለው ዲባዲቦ ልብሱ የቀይይስን መጅኑንነት ገሀድ አወጡ፡፡ ፀሀይ ወጥታ እስክትገባ ለይላ ለይላ ብቻ እያለ ዋተተ ፣ ከሀገር ሀገር ተንከራተተ ፣ በጎዳና ተንኳተተ ፣ እየቃተተ....

በልጃቸው መባከን ክፉኛ ልባቸው የተሰበረው ወላጆቹም መጅኑንን ወደ ሰውነት ተራ ለመመለስ ሳይታክቱ ተጣጣሩ፡፡ ነገር ግን እንኳን ሊሻለው ከቀን ወደቀን ህመሙ በረታበት፡፡ በለይላ ለታመመው መጅኑን መድሀኒት የሚዘይድ ሀኪምም ጠፋ፡፡ እሱን የሚያድን መድሀኒት ታጣ፡፡ በርግጥም በፍቅር ለታመመ ልብ ከተፈቃሪው ውጭ ማን ሊያክመው ይችላል!! አል-ሀኪሙ ጌታችንም እያንዳንዱን በሽታ ሲፈጥር ከነ መድሀኒቱ እንደሆነው ሁሉ ለፍቅር ህሙማኖችም መድሀኒታቸውን ከአስታማሚአቸው ዘንድ አስቀምጧል፡፡ ምን አልባት በእቅፋቸው ውስጥ ፣ ምን አልባትም በቅፅበታዊ እይታ ላይ ፣ አልያም ደግሞ የአንድ ጊዜ መሳም...ምን አልባት.......ነገር ግን ቤተሰቦቹ መላ ሲያጡ በግረ ሙቅ ክርችም አድርገው ከቤታቸው አስረው አስቀመጡት፡፡ በነጅድ ከተማ የመጅኑንን እብደት እሙን ሆነ፡፡

<<ከፍቅር ቃሬዛ ወድቆ ለደከመ፣
ለይላን ላፈቀረ ለይላን ለታመመ፣
የምን ደማከሴ የምን እጣን ቅጠል፣
የምን ቱፍታ ዘምዘም ወይ ሂርዝ ማንጠልጠል፣
አቢድ ያሰመረው፣
ሀኪም የቀመመው፣
መዳኒት ምኑ ነው?
መዳኒቷ እርሷ ነች መዳኒትም የለው!
በሷ እንደታመመ በሷ ነው ሚድነው፡፡>>

ከጊዜ በኀላ የመጅኑንን በሽታ የተረዱ ህመም አዋቂያን የሱ ፍቱን መድሀኒት ለይላ እንደሆነች ገብቷቸዉ ለይላን ለመጅኑን መዳር "መፍትሄ" ብለው ዘየዱ፡፡ የልጃቸው መዳን በለይላ የተበየነላቸው የመጅኑንም ቤተሰቦች ከለይላ አባት ከሰዕድ ቢን መህዲ ላይ ሂደው ወደቁ፡፡ ልጅህን ለልጄ ብለው ጠየቁ፡፡ ሰዕድም እምቢታውን አበክሮ ገለፀ፡፡ ፍፁም አይሆንም ሲል እምቢኝ አለ፡፡ የልጃቸው ድነትና እጣፋንታ በሰዕድ እሺታ የተወሰነባቸው የመጅኑን ቤተሰቦችም ደጋግመው የሰዕድን ደጅ ጠኑ፡፡ አበክረው ተማጠኑ ፣ ተመላልሰው ለመኑ ፣ በዘመድ አዝማድ አስለመኑ!! ሰዕድ ግን "በፍፁም"!! ሲል ገነተረ፡፡ እንደውም እንዴት አንድያ ልጄን ለእብድ ዳር ትሉኛላችሁ ብሎ በሽማግሌዎቹ ላይ ለቁጣም ተጋበዘ፡፡ የመጅኑንንም ነገር መላ አጣ፡፡
__
                                ፡

ከሳምንታት አድካሚ ጉዞ በኀላ ከሻሟ ዲመሽቂ(ደማስቆ) የተነሳው የንግድ ቅፍለት#2 ነጅድ መድረሱ ተሰማ፡፡ የከተማውም ነዋሪዎች ወደ ነጋዴዎቹ ዘንድ በነቂስ ተመሙ፡፡ አዲስ ከደረሰው ቅፍለት አዲስ ነገር ለመሸመት ሰው ተሽቀዳደመ፡፡ የቅፍለቱን መድረስ የሰማችው የመጅኑንን እናትም በሶሪያ የሚገኙ የቱርክ ስጋጃዎችን እንዲያመጣላት ወዳዘዘቺው ነጋዴ መጅኑንን አስከትላ ሄደች፡፡ እግረ መንገዷን ለቀናት ከደጅ ያልወጣውን ልጇን ከሰው ተራ ለመቀላቀል ብላ ነበር፡፡ ወደ ገበያው በሚያመሩም ጊዜ መጅኑንን ያዩት ሁሉ ጥርሳቸውን እየመጠጡ አዘኑለት፡፡ አንገታቸውን እየወዘወዙ አግራሞታዊ ሀዘናቸውን ገለፁ፡፡ ህፃናቶችም ሸሹት፡፡ እናቱ ከነጋዴው ጋር ስታወራ መጅኑን ከገባያው ግርግር ለመሸሸግ ከአንዱ ግድግዳ ስር ጭንቅላቱን ጉልበቱ ላይ አንተርሶ ኩርትም አለ፡፡ በተቀመጠበት ከዛ ሁላ ጩኸት ውስጥ የሱን ስም የሚጠራ ድምፅ ደምቆ ከጆሮው ገባ.. "ቀይስ"? "ቀይስ ? ... አንተ የቃላት አሚር#3 የሆንከው ጓደኛዬ ሆይ!" እያለ ጓደኛው አሊ ወደ እሱ ተጠጋ፡፡መጅኑን ካቀረቀረበት ቀና ብሎ የሚጠራውን አሊ ባይኑ ገርመም አድርጎት መልሶ አንገቱን ወደ ጉልበቱ ሰበረ፡፡ ወደ መጅኑን ተጠግቶ ምነው ወንድሜ ምን ሁነሀል? ገና ከዲመሽቅ መግባቴ ነው፡፡ ብዙ አፈላልጌ እኮ ነው ያገኘሁህ እንዲህ ነው ጓደኛህን የምትቀበለው? ደግሞ ምንድን ነው የተፈጠረው ምን መስለሀል እያለ አከታትሎ አታካራ ጥያቄዎችን ጠየቀው፡፡ ለዚች ቆሻሻ አለም እንደምገባት ነዋ የሆንኩት!! ሌላ ምን እሆናለሁ? ሰው ሁሉ ለይላን ከኔ ወስዳ የበላች ቆሻሻ ምድር ላይ እየኖረ ቆይ የኔ ማደፍ ፣ መቆሸሽ ምኑ ነው ሚገርመው? ተወኝ አሊ ማውራት አልፈልግም አለ መጅኑን ፊቱን አጨፍግጎ፡፡ አልተውህም ደግሞስ ለይላ እንደሱ ሁነህ ብታይህ ምን ይሰማታል? በል አሁን ያን ለይላ የምትወደውን ቀይስ ሁን አለው፡፡ መጅኑንም ለይላ እዚህ የለችም!! ብሎ አጭር መልስ መለሰለት፡፡ ነጅድ ነዋ የሌለችው ዲመሽቅ አየኀት እኮ! አለ አሊ ወደተቀመጠው መጅኑኝ ጎንበስ ብሎ ትከሻውኝ ቸብ ቸብ እያደረገ፡፡ አሊ የለይላን ዜና አውርቶ ሳይጨርስ መጅኑን ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነሳ፡፡ ለይላ? ለይላ...እርግጠኛ ነህ? የኔ ለይላ ዲመሽቅ? ዲመሽቅ ለይላ? እየቆረጠ ፣ እየቀጠለ ጠየቀው፡፡ አዎ እራሷ ነች ከዲመሽቅ ባዛር አይቻታለሁ፡፡ እኮ የኔዋ ለይላ? መጅኑን ሙቶ እንደተነሳ ሰው መገኘቷን አላመነም፡፡ አዎ በደንብ ነው ያየኀት ስልህ ብሎ ካፉ ሳይጨርስ አሊን በቆመበት ገትሮት በሩጫ ተፈተለከ፡፡ እንዴ የት ነው ምትሄደው ጠብቀኝ እንጂ? "ቀ..ይ..ስ" እያለ እየጮኸ ተከትሎት እሮጦ፡፡ የመጅኑንን እሩጫ ያዩት ገባያተኞች "እብድ መጣ" "እብድ" "እብድ" እያሉ የእግሬ አውጭኝ እሩጫቸውን ወደየትም አስነኩት፡፡ እብድ መጣ የሚለውን ቃል እየተቀባበሉ ገበያው በሙሉ በሩጫ ታመሰ፡፡ ግማሹ ለምን እንደሚሮጥ አያውቅም ፣ ግማሹ ደግሞ ወዴት እንደሚሮጥ አያውቅም፡፡ አሊ ከመጅኑን ኀላ ተከትሎ ከተማ መውጫው ላይ ደረሰበት፡፡ ወዴት ነው የምትሮጠው አለው ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ፡፡ ወደ ለይላ እየሄድኩኝ ነው ለይላ ከዛ ሁና እየጠበቀችኝ ነው ዞር በል አሊ ከመንገዴ አታዘግየኝ አለው  መጅኑን ሊበር እንደሚያሽኮበኩብ አሞራ አከንፍፎ፡፡ ምን ሁነሀል ቀይስ! ተረጋጋና እኔ ጋር አብረን እንሄዳለን፡፡ በዚ ሳምንት እዚህ የሚደርስ ሌላ ቅፍለት አለ የቅፍለቱ መሪ ወርድ ቢን መህዲ ላይ ያልተቀበልኩት ዲርሀም#2 አለኝ እነሱ እንደመጡ ተቀብዬ አብረን እንሄዳለን አለው፡፡ መጅኑን ግን በፍፁም አለ፡፡ ጉዞው ሳምንታትን እኮ ይፈጃል! በዛ ላይ ስንቅም ያስፈልግሀል አለ አሊ መጅኑንን ለማስቀረት እያስፈራራ፡፡ መጅኑን ግን ምን እያለም እንደነበር ጭራሽ አልሰማውም የለበሰውን እንደለበሰ የሻምን እረጅም በረሀ አሊፍ ብሎ በግሩ ጀመረው፡፡ ወደ ለይላ.......

ይቀጥላል.....

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

12 Nov, 10:23


ጥቂት ነጥቦች ለሃብት ባለቤቶች
~
1- በቅድሚያ እጅህ ላይ ያለው ሃብት ባንተ ልፋት ብቻ የመጣ እንዳይመስልህ። በልፋትም ካንተ የበለጠ የሚለፉ፣ በእውቀትም ካንተ የሚበልጡ ሆነው ሳለ ሃብት የሌላቸው ብዙ ሰዎች ዙሪያህን እንዳሉ አትርሳ። እወቅ! ገንዘብህ የፈለገ ሰበብ ብታደርስ ከአላህ የመጣ ችሮታ ነው። ይህንን እውነታ ልብህ ውስጥ አርቀህ ትከለው። ይህንን እውነታ ካልተቀበልክ ካንተ ጋር መግባባት ከባድ ነው።

2- ሃብትህ ትእቢትና ኩራት አያውርስህ። ኩራትና ንቀት ብዙ ሃብታሞችን የሚያጠቃ በሽታ ነው። በኩራት የተለከፈ ሰው ምክር ይፀየፋል። እወቅ! "ልቡ ውስጥ የብናኝ ክብደት ታክል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም" ብለዋል ነብያችን ﷺ። [ሙስሊም፡ 91] ደግሞም ኩራት ለአኺራ ቀርቶ ለዱንያም አይጠቅምህም። የቸገረው ወይም የረከሰው ቢያሸረግድልህ እንኳ "እሱ ቀብራራ፣ ጢባራም ነው" እያለ ያወቀህ ይጠላሃል። የኣኺራው ደግሞ የከፋ ነው። ዱንያ ላይ አገር አይብቃኝ፣ መሬት አይንካኝ ያለው በጥራራ በቂያማ ቀን እንደ ጉንዳን አንሶ ሰዎች እየረጋገጡት፣ ከያቅጣጫው ውርደት አካቦት ጀሃነም ይወርዳል ብለዋል ነብያችን ﷺ። [ቲርሚዚይ: 2492]

3- ሃብትህ በየትኛውም ዘርፍ ድንበር አያሳልፍህ። ስትናገር አደብ ይኑርህ። በሰው ላይ አትተላለፍ። ስትራመድ አደብ ይኑርህ። ስለነጠርክ ተራራ አትደርስም። በየትኛውም ጉዳይ ላይ በሃብትህ መነሻ የተለየ ለመሆን አትጣር። ከሰው የተለየ ነገርም አትጠብቅ።

4- ዘካህን አውጣ። ዘካ ከኢስላም አምስቱ ምስሶዎች ውስጥ መሆኑን አትዘንጋ። እወቅ! ራስህን ብታስለምድ ደስ እያለህ በጉጉት ትሰጣለህ። ኢማንህ ይጨምራል። ኣኺራዊ ምንዳህ ደግሞ እጅግ የላቀ ነው። በተቃራኒው ግዴታ ከሆነበት በኋላ ዘካ የማይሰጥ ሰው ነገ የቂያማ ቀን የገዛ ገንዘቡ መሰቃያው ነው የሚሆነው።

5- አቅምህ እስከቻለ ድረስ በሌሎችም ኸይር ስራዎች ላይ ተሳተፍ። ከማንም በላይ የምታተርፈው ራስህ ነህ። ስለዚህ ችግረኛ ዘመድ፣ ጎረቤት፣ የዲን አስተማሪዎችን፣ ኢማሞችን፣ ሙአዚኖችን፣ ችግረኛ ወገኖችን፣ ... እርዳ። የምታውቀው ኸይር ስራ ላይ ለመሳተፍ ጎትጓች አትፈልግ። ወደ ጀነት ለሚደረግ ጥሪ ደስታ እንጂ ቅሬታ አትያዝ። ገንዘብህ ጠፊ፣ አንተም ሟች እንደሆንክ አትርሳ።

6- ገንዘብህ የልጆችህ መጥፊያ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። በወላጅ ገንዘብ ተበላሽተው ከመስጂድ የራቁ፣ በሱስ የደነዘዙ፣ አኺራቸው ቀርቶ ዱንያቸው አደጋ ላይ የወደቀባቸው ብዙ የሃብታም ልጆች አሉ። ስለዚህ ጥንቃቄ ይኑርህ።

7- ገንዘብህን አመጣጡንም አወጣጡንም ተከታተል። በሐራም እንዳይመጣ። በሐራምም እንዳይወጣ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
" لَا تَزُولُ قَدَمَا عَبْدٍ يَوْمَ الْقِيَامَةِ حَتَّى يُسْأَلَ عَنْ عُمُرِهِ فِيمَا أَفْنَاهُ، وَعَنْ عِلْمِهِ فِيمَ فَعَلَ، وَعَنْ مَالِهِ مِنْ أَيْنَ اكْتَسَبَهُ وَفِيمَ أَنْفَقَهُ، وَعَنْ جِسْمِهِ فِيمَ أَبْلَاهُ"
"በቂያማ ቀን የትኛውም ባሪያ አራት ነገሮችን እስከሚጠየቅ ድረስ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንደቋጨው፣ እውቀቱን ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና በምን ላይ እንዳዋለው እና አካሉን በምን እንደፈጀው።" [ቲርሚዚይ: 2417]

8- የዱንያ ወከባ አኺራን አያስረሳህ። ከመስጂድ አትራቅ። ዝምድናህን ቀጥል። ሐጅ ካላደረግክ ዛሬ ነገ ሳትል ባስቸኳይ ፈፅም። ባጭሩ እጅህ ላይ ያለው ሃብት ካወቅክበት የአኺራህን ቤት የምትገነባበት ነው። ካልሆነ ግን ዘላለማዊ ህይወትህን የምታበላሽበት ነው። የሚሻልህን መምረጥ ያንተ ድርሻ ነው። የቂንህ አይድከም፣ አኺራህን ምረጥ። ሰላም ላንተ ይሁን።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

12 Nov, 02:22


« በህይወት ውስጥ ዝነኛ መሆንን ያን ያህል ልንጓጓለት አይገባም።
ዝና የማይጎዳ የሚመስል አደገኛ መርዝ ነው። ዝና የገቢ ምንጭ ነው። ዝና ውሸታም ለመሆንም፣ አጉራ ዘለል ላለመሆንም ሰበብ ይሆናል። ዝና እስር ቤት ነው። ዝና ውስጥ ሁሌም ደስታ የለም፣ ሁሌም መከፋት የለም። ዝና ሊጠጡት የሚያጓጓ ኮሶ ነው። ዝና ክብርም፣ ውርደትም ነው። ዝና ሰዎችን ወደ ጥፋት መምርያም፣ ወደ መልካም ነገር ማመላከቻም ነው። ዝና አንዳንድ መንገዶችን ሊያቀል ይችላል፣ ነገር ግን በዛውም ልክ ውስብስብ ትብታቦችን ያመጣል። ምንም ሰርታችሁ ዝነኛ መሆንን ስትፈልጉ እጅጉን በጥልቀት አስቡ። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

12 Nov, 02:21


Daily therapy 227🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

11 Nov, 18:02


ግጥሞቹን ሀዘን ባሰለለው ድምፁ እያንጎራጎረ ወደመጣበት ተመለሰ፡፡ ታዳ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሲሄድ እየሰገዱ ያለፋቸው ሰዎች ሲመለስም ተቀምጠው አገኛቸው፡፡ አንተ እብድ የሆንክ መጅኑን ሆይ? እንዴት እኛ ስንሰግድ እያየኽ የለይላን ውሻ ተከትለህ በፊታችን ታልፋለህ ሲሉ አበክረው ወቀሱት፡፡ መጅኑንም በጭራሽ እዚህ አልነበራችሁም ሲል አስተባበለ፡፡ ምነው አሁን በዚህ እረግጠኸን አልፈህ አሁን ባሁን ትክዳለህን?? ብለው ሁሉም በያፋቸው አጉመተመቱ፡፡ ሀያል በሆነው በለይላ ፈጣሪ እምላለሁ! እዚህ እንዳላችሁ አላስተዋልኩም ነበር፡፡ እንዳላችሁት እዚህብትኖሩም እንኳን እኔ የምወዳትን ለይላን ለመገናኘት ስከንፍ እናንተን ችላ ብዬ ነበር፡፡ ነገር ግን እናንተ እንወደዋለን የምትሉትን ጌታችሁን ለመገናኘት ቁማችሁ እኔን አያችሁ፡፡ ስለዚህ የናንተ የጌታችሁ ዉዴታ ከኔ የለይላ ፍቅር በታች ነውና ነፍሳችሁን አጥሩ ብሏቸው አለፈ፡፡

ኦውውውው መጅኑንንንንንን!!!!

ይቀጥላል....


አስረጅ፥
1#ገህዋ/ቀህዋ (ቡና)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

11 Nov, 18:01


(መጅኑነለይላ)

ክፍል 3 መሊኩ

ኢስቢር ያ ቢንተ ሀላል! እባክሽ ተረጋጊ! ተረጋጊ ለይላ ሆይ፡፡ እስትንፋሱ አሁን ድረስ አለ ብሎ ሰውዬው ለይላን ካረጋጋ በኀላ መጅኑንን ወደከበቡት ሰዎች ዙሮ.... "አየር  ያስፈልገዋል እስኪ ሌሎቻችሁ ዘር ዘር በሉለት አትፈኑት"፡፡ እያለ የከበቡትን ሰዎች በተናቸው፡፡

ከመጅኑን የሚፈሰው ደም በለይላ የሀር ቀሚስ ላይ ቀልሞ እሷ ትሁን እሱ የደሙት መለየት እክኪያቅት ድረስ በደም ተለቃልቀዋሉ!! እሷ ግን በዛ ሰዐት መላ አካላቷን ያጠመቃትን ደም ልብ አላለችውም፡፡ በርሷ መውደድ የባተለላት የሽሽግ ፍቅሯ መጅኑን ከጇ ላይ ሲያጣጥጥር ማየቱ አቅሏን ነስቷታል፡፡ የሴትነት ይሉኝታዋን አሳጥቶ አሳብዷታል፡፡ ሰውዬው ካቀፈቺው ጀሰዱ ውስጥ ነፍሱ እንዳለች ሲግራት በጭንቀት ልትሾልክ የደረሰችው ነፍሷን አሳርፋ በእዝነ ልቧ እፎይ ብላ በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ ከደይቃዎች በኀላ ቤተሰቦቹ  ዜናውን እንደሰሙ መጥተው ከለይላ ጭን ላይ የዘነጠፈውን ቀይስ አንስተው ወደቤት ወሰዱት፡፡ የዛን እለት የነጅድ አፈ ቀላጤዎችም በገህዋ#1 መሰብሰቢያ ቦታቸው ስለ መጅኑን እና ለይላ ሲያነሱ ሲጥሉ ዋሉ፡፡ ነገሩም ከገህዋ ቤት ወጥቶ ሳይውል ሳያድር የተፈጠረው ሁሉ ከለይላ አባት ጆሮ ደረሰ፡፡ በከተማው እንደ ንጉስ የሚከበረው ሰዕድ ቢን መህዲም (የለይላ አባት) ባደባባይ ስሙ መጉደፉ ክፉኛ አበሳጨው፡፡ እጅጉን አስቆጣው፡፡  በቅርቡ ባገኛት ለይላ ላይ እስኪበቃው ድረስ ቁጣውን ከተወጣ በኀላ ፈረሱን ጭኖ ወደ ሙለወህ ቤት ኮለኮለ፡፡

ከሙለወህ ቤት ሲደርስ በፋሻ ተጠቅልሎ በረንዳ ካለ የጠፍር ሀልጋ ላይ ተንጋሎ መጅኑንን አገኘው፡፡ በንዴት ትንታግ እየተናጠ የሰላ ሰይፉን መዘዘና በመጅኑን አንገት ላይ ቀስሮ እንዲህም አለው.... "አንተ ቀውስ እንዴት ብታብድ ነው በነጅድ መሊኮች ፊት ባደባባይ ያዋረድከኝ ? እንዴትትትትትትትትትት እንደዛ እረክሰህ ታረክሰኛለህ አንተ ከንቱ"! እያለ አምባረቀበት፡፡ አዎ አጎቴ በርግጥም አብጃለሁ፡፡ አንተ ደግሞ አብዷል ብለህ እንደኢብራሂም ላንገቴ ቢላ ካነሳህ ይሄው እኔም እንደስማኢል አንገቴን እሰጥሀለሁ፡፡ ግና "ሰዕድ አጎቴ ሆይ!.... ያንተ ሰይፍ እኔን መቁረጥ አይቻለውም፡፡ ምክነያቱም እኔ ሙት ነኝና!! ካንተ በፊት ቀድማ ልጅህ ለይላ ገላኛለች፡፡ ታዳ አንተ አንዴ የሞተን ሰው ዳግመኛ መግደል ይቻለሀልን? ሲል መለሰለት፡፡ በዚህን ጊዜ ከደጁ ጩኸት የሰማው ሙለወህ (የመጅኑን አባት) ከቤት ውስጥ ሲወጣ የገዛ ወንድሙ ከልጁ አንገት ላይ ሰይፍ ደግኖ ተመለከተ፡፡ የናቴ ልጅ የሆንከው ሰዕድ ሆይ ምንድን ነው የምትሰራው??? አለ ሙለወህ ባየው ግርግር ደንግጦ፡፡ ይህ እረኛ ልጅህ የኔንም ሆነ የቤተሰባችንንም ስም ዛሬ ባደባባይ ከትብያ ቀላቅሎታል፡፡ ይህን ሳታውቅ ቀርተህ ነው? ልጅህ  አብዷል ፣ ለይቶለታል፡፡ የኔዋን ለይላንም አስብዷታል፡፡ ደግሞ ምንም ሳያፍር እብደቱን ይናዘዝልኛል እኮ! በተከበርንበት ሀገር በሱ እብደት ከምንዋረድ እሱም አብዶ ከሚሰቃይ እንግዲያውስ በሻሞላዬ ይህን ቅል የተሸከመ አንገቱን ልቅላለት እና ልገላግለው፡፡ አለ በንዴት አይኑን እያጉረጠረጠ፡፡ ምነው ሰዕድ ከቀልብህ ሁን እንጂ! ለሸይጧን አትውደቅ ወንድሜ! ተው ትፀፀትበታለህ፡፡ ባትወልደውስ ልጅህ አይደል የልጅህን ደም ታፈሳለህን? በል ካንገቱ ላይ ያሳረፍከውን ስለት ለዐላህ ብለህ ወደ ሰገባው መልሰው አለ እያስተዛዘነ፡፡ ሰዕድ የቁጣ እሳት የሚረጩ አይኖቹን ከመጅኑን ላይ ተክሎ ለሙለዋህ እንዲህ አለው... ካሁን በኀላ ከመሬት እንደቀላቀለው ክብሬ ከእንግዲህ በኀላ እሱም ለኔ ሙቷል፡፡ ቀይስ የሚባል ልጅ የለኝም፡፡ ዳግም ከዛሬ ጀምሮ አይደለም ለይላን ማግኘት ቀርቶ በለይላ አጠገብ እንኳን ሲያልፍ ባየው በጌታዬ ስም እምላለሁ የሱን አንገት ሳይቀላ ሰይፌ ወደ ሰገባው አይገባም! ሲል ዝቶ ሄደ፡፡ ወድያው ከሙለወህ ቤት እንደወጣም ወደ ንጉስ አብደል መሊክ ኢብኑ መርዋን ዘንድ ሄዶ መጅኑንን ከሰሰ፡፡ ንጉስ አብደል መሊክ መርዋንም የመጅኑንን ከባህላቸው ያፈነገጠ ተግባር አውግዞ በመጅኑንን ላይ መዐቀብ ጣለበት፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ መጅኑን ከለይላ ተከለከለ፡፡ እሷ ካለችበት አካባቢ ሁሉ እርሱ በግዞተኝነት ተፈረጀ፡፡ በዙሪያዋ ከተገኘ ደመ ከልብ ሆኖ እንዲሞት ታወጀ፡፡ ፍርዱም በዚህ ተባጀ፡፡ ግና የመጅኑን ፍቅር ዋጀ....
መጅኑን ይህን ፍርጃ ሲሰማ እንዲህም አለ፡፡..... አንቺ በሴትነትሽ ለፍፅምና የቀረብሺው ለይላ ሆይ! ፍፁም የሆነው ጌታዬ ባንቺ እረግሞኝ ፣ ያንቺን መወደድ ፈርዶብኝ ሳለ ሰዎች ግን ለምን ተረገምክ ብለው ሌላ መሪር ፍርጃን በኔ ላይ  አነባበሩብኝ፡፡ ቆይ ግን ወድጄ ይመስላቸዋልን? ፈራጆቼ ጨካኝ ናቸውና ህመሜ ይገባቸው ዘንድ ለኔ የሰጠውን በጥቂቱ በሰጣቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ አለ እያቀሰ፡፡

ከዛን ቀን በኀላ ለይላ ለይላም ወደውጭ እንዳትወጣ አባቷ በአፅኖት አስጠነቀቃት፡፡እሷም ከምግብ ጋር ተቆራርጣ ፣ ከሰው እራሷን አግልላ ከክፍሏ ውስጥ እንደቆረበች ቀናቶች አለፉ፡፡  ቀኑንም ሌቱንም ስለ መጅኑን እያሰበች ስታነባ አይኖቿም ሟሙ፡፡ እንደሷው ሁሉ ስለሷ ሲል ያበደው መጅኑንም በናፍቆቷ ሰክሮ በድብቅ ቤቷን ሲዞር ያመሻል፡፡ በምን አልባት ተስፋ ካሁን ካሁን ትወጣለች እያለ ሌሊቱን ሙሉ ሳይታክት ይጠብቃል፡፡ ከሷ አካባቢ የተገኘ እንደሁ እጣ ፋንታው ምን እንደሚሆን ባይጠፋውም እሱ ግን ያ አይገደውም፡፡ ምክነያቱም ናፍቆትም ያን ያክል ይገድላልና!! ወደ ለይላ የሚያደርገው የጉዞዉ ትርጉም ከሞቱ ወደ ሞቱ ቢሆንም እንኳን...ከናፍቆት ሞት ለመትረፍ በሚደረግ የሞት ጎዞ የናፈቁትን ሰው አንዴ ለማየት ፣ አልያም አንዴ ጠረኑን ለመማግ ፣ ወይ ደግሞ ድምፁን ለመስማት.... ተራራ ቢወጣ ፣ ውቅያኖስ ቢቋረጥ ፣ ሰማይ ቢታረግ ፣ መሬት ቢሰረግ ለናፍቆተኛ ተጓዥ ኢምንት ነው፡፡ በርግጥም ናፍቆት ከባድ ስቃይ ነው!!

መጅኑን ከደጇ መመላስ ከጀመረ ጀምሮ ለይላን ባያገኛትም ነገር ግን በየሌሊቱ ሁሉ ደጇን ሳይሳለም አያድርም፡፡ ባያገኛት እንኳን በሷ አካባቢ መሆኑ ብቻ እንዳበደ ውሻ የሚያካልበው ናፍቆቱን ገርገብ ያደርግለታል፡፡ ዛሬም እንደተለመደው የፀሀዯን ግባት ጠብቆ ወደ ለይላ ቤት መንገዱን ጀምሯል፡፡ ያለወትሮው የነጅድ ወብቅ የቀላቀለ ነፋሻ አየርም በብርድ ተተክቷል፡፡ የከተማውን አደባባይ አቋርጦ ገበያው አካባቢ ሲደርስ የለይላን ውሻ ከሩቅ ያስተውላል፡፡ እናም ውሻውን እንዳየው ለይላ ካለችበት ቦታ ይመራው ዘንድ ዳናውን ተከትሎ ከነፈ፡፡ የለይላን ውሻ  ተከትሎ ሲሮጥ በመንገዱ ላይ ተሰብስበው የምሽት ሶላት የሚሰግዱ ምዕመኖችን ከነመኖራቸውም ልብ አላለም ነበር፡፡ ልክ እሷ ወዳለችበት ቦታ ሲቃረብ በድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ከሰማይ እንደወደቀ የኮከብ ፍንጣቂ ከሩቅ ደምቃ ተመለከታት፡፡ ከሰዎች ሁሉ ተለይቶ የገላዋ መዐዛ አወደው፡፡ አይኑን ጨፍኖ ወደ ውስጡ በረጅሙሙሙ ጠረኗን ማገው፡፡ "አህህህህህህ ለይላ"!! ተንደርድሮ ሂዶ ካንገቷ ጥምጥም ብሎ ሊስማት ከጀለ፡፡ ዙሪያዋን ካሉ ጠባቂዎች እና ካጎቱ ሰርቋት ሊጠፋም ዳዳው፡፡ ግን አይችልም!! በዚህ መሀል ወድያው ካሽከሮቿ ጋር ያቺ ተወርዋሪ ኮከቧ ለይላ ካይኑ ራቀች፡፡ አንፀባራቂ ብርሀኗ ቀስ በቀስ እየደበዘዘ አይቶ ሳይጠግባት ጭል ጭል እያለች እርቃ ጠፋችው፡፡ እሱም እጁን ወደምትሄድበት ዘርግቶ በሎህሳስ ድምፅ "ለ...ይ....ላ" እያለ ለደይቃዎች ባይኑ ሸኛት፡፡ ከዚያም ልብ ሰርስረው የሚገቡ

اقرأ (አንብብ )

11 Nov, 15:39


ዛሬ ዛሬ ማግባት ቀላል ነዉ።
ከባዱ ግን ለአላህ ያለንን ፍራቻና ኢማናችን እንዲጨምር የሚረዳንን ትክክለኛ የትዳር አጋር ማግኝት ነዉ ።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

11 Nov, 06:28


ገብያ መሀል በተነሳ ግርግር እንቁላል ነጋዴ እና ድንች ነጋዴ እኩል አይደነግጥም

اقرأ (አንብብ )

11 Nov, 03:21


« ስለውስጥ ጩኸቶቻችሁ፣ በቃላት ስለማይገለፁ ህመሞቻችሁ፣ በጥልቁ ስለምትሹት ምኞታችሁ ሁሉ አብሽሩ። የምወድሽዋ የከፋሽ፣ የተሰበርሽ፣ ድክም ያለሽ ቢመስልሽም በአላህ ፍቃድ ለደስታሽ ይነጋል። ትንሽ… ብቻ ታገሽ።
የምንወድሽ፣ የምናከብርሽ፣ የምርሽን ፈገግ ስትይ ልናይሽ የምንፈልግ አለን።  አብሽሪ! የምወድሽዋ ሰላም ለልብሽ! የምወድህዋ ሰላም ለልብህ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

11 Nov, 03:20


Daily therapy 226🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

10 Nov, 18:35


🥰

اقرأ (አንብብ )

10 Nov, 18:01


(መጅኑነ ለይላ)

(ክፍል ሁለት) መሊኩ

ከምድር እምብርቷ መካ በስተ ደቡብ አቅጣጫ የምትዋሰነው የነጅድ ገጠራማ ከተማ እንደ ወትሮው ደንገዝገዝ ብላ ቀኗን እየገፋች ነው፡፡ ጊዜው ገና ልጅ ቢሆንም ፀሀይዯ ግን  ጠንክራለች፡፡ የነጅድ ሻኢሮች ከፀሀዯ ለመከለል በየበረንዳው እና በየቴምሩ ዛፍ ስር ተቀምጠው የተለመደውን የግጥም እንካ ስላንትያቸውን ማዶ እና ማዶ ሁነው ይወራወራሉ፡፡ ክፍት ጀለብያ ሳሳ ካለ ነጭ ሱሪ ጋር ለብሶ ጥቁር ጫማ የተጫማ ሸጋ ወጣት "ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እናንተ የብዕር ጌቶች"፡፡ እያለ  በመሀላቸው አልፎ ካደባባይ ሚንበሩ#1 ላይ ቆመ፡፡ ከሚንበሩ ላይ የቆመውን ገጣሚ ለማዳመጥ ባንድ ጊዜ ጠባቧ የነጅድ አደባባይ በሰው ጎርፍ ተራወጠች፡፡ መጅኑን ነበር፡፡ ውሀ ጠምቶት በበረሀ እንደሚጓዝ የንግድ ቅፍለት የግጥም ጥም ያሰከራቸው የነጅድ ነዋሪዎች ከመጅኑን ፊት ተጀገጀጉ፡፡ መጅኑን በቋንቋ ጥልቀቱ እና በጠንካራ መልዕክቱ እስከዛሬ ድረስ ተወዳጅነትን ያተረፈ ጉምቱ ገጣሚ ነው፡፡ በአረቡ አለም ያለ የአንድ ወጣት እጣፋንታ ከሶስት ነገሮች ሊወጣ አይችልም፡፡ ወይ ነጋዴ ነው ፣ አልያም ጀይሽ#2 ነው ፣ ወይ ደግሞ ሻዒር#3 ነው፡፡  ታዳ እንደ ለይላ እና መጅኑን ላሉ የፍቅር ውድቅተኞች ብዕር ከማነቅ ውጭ  ምን አይነት እጣ ፋንታ ሊፃፍላቸው ይችላል!! ጥሩ ስነ-ግጥም ከጥልቅ የስሜት ባህር ይቀዳል፡፡ ለ14 ክፍለ ዘመናት እንደጣፈጠ ዛሬ ድረስ የቆየው የመጅኑነ-ለይላ ጥዑም ስነ-ግጥምም የተጨለፈው ከዛ ጥልቅ የስሜት ባህር ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ (ከፍቅር ፣ ከህመም ፣ ከናፍቆት ፣ ከእጦት)!  መጅኑን እሱን ለማድመጥ ያሰፈሰፉትን የግጥም ዛረኞች  ትኩረታቸውን እንዳገኘ እንዲህ ሲል ..... በአራት ስንኝ ብቻ የህይወቱን ትልቅ ሚስጥር ባደባባይ አነቦጨው፡፡

ተዐለቅቱ ለይላ ወሂየ ጊሩን ሶጊረቱን
ወለም የብዱ ሊልአትራቢ ሚንሰድይሀ ሀጂሙ
ሶጊረይኒ ነርአልበሂመ ያ ለይተ አነና
ኢለል የውሚ ለም ነክቡር ወለም ተክቡሪል በሂሙ!!

እንዲህ የሚል ሀሳብ አለው..."እኔ ለይላን የምወዳት ያኔ ነው፡፡ ያኔ ገና ህፃን ሳለች ፣ ህፃን ሳለሁ፡፡
ምንም ጓደኛ ሳታፈራ ፣ ምንም ጓደኛ ሳይኖረኝ፡፡
ገና ጡቶቿ እንኳን ብቅ ብቅ ሳይሉ በእረኝነት ጊዜአችን ያኔ.... ጀምሬ ነው የምወዳት፡፡
ታዳ ዛሬ ላይ እንዲህ ስል አምርሬ ተመኘሁኝ "ያ ጊዜ ባለበት በቆመ ፣ እንሰሳዎቹም ሳያድጉ ፣ እኛም ሳናድግ በዛ ሁናቴ ለዘላለም በኖርን ብዬ ተመኘሁኝ"፡፡ ብሎ እንደጨረሰ እድምተኛው ሁሉ እያልጎመጎመ ቅሮቱን ገለፀ፡፡ ከግጥሙ ባሻገር የቀይስ መደዴነት አስገርሟቸዋል፡፡ እሱ ግን ምንም አልደነቀውም፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየለየለት ነው፡፡ ከለይላ መውደድ የተገፋ ከነጅድ ቢነጠል ተገፋሁኝ ብሎ አያለቃቅስም፡፡ እንኳን ከነጅድ ከአለም ቢጣል ኢምንት ታክል አይገደውም፡፡ "እንኳን ከዚች ትንሽ አለምና ከግዙፏ ለይላም ተገፍቻለሁ"!! ሲል ለይላ የለለችበትን ባዶ አለም ያቀላታል፡፡  ከዛው ሚንበር ሳይወርድ ከእድምተኞቹ መሀል እንደ ሙዚቃ የሚስረቀረቅ ሌላ የልጅ አገረድ ድምፅ በለቅሶ ታጅቦ ተሰማ፡፡ ሁሉም ድምፁ ወደመጣበት አቅጣጫ ሀሳቡን እና ጆሮውን ቀስሮ የልጅ አገረዷን ጥዑም ግጥም በትኩረት ማድመጥ ጀመረ፡፡ ለይላ ነበረች፡፡ የመጅኑንን የፍቅር ኑዛዜ ስትሰማ አላስችልሽ ብሏት ከቆመችበት ጥጋት መደ መጅኑን እየተራመደች በጀበሉ ሰውባን የቋጠረችውን የፍቅር ቁጥርጥር ፈትታ ባደባባይ ተናዘዘች፡፡ ለዘመናት ያረገዘችውን ፍቅር ወለደች፡፡
ፈኣጃበት ለይላ ወሂየ ባኪየቱን ለማ ሰሚአት ሺእረሁ.....

ወኩሉን ሙዝሂሩን ሊናሲ ቡግዶን
ወኩሉን ኢንደ ሷሂቢሂ መኪኑ
ተኽቡሩነል ኡዩኑ ቢማ አረድና
ወፊል ቀልበይኒ ሰመ ሀወን ደፊኑ

"ሁላችንም ሌሎች ሰዎች ስለ ፍቅራችን እንዳያውቁ እንጥራለን፡፡ ማወቃቸውን እንፈራለን ወይም አያስደስተንም፡፡ ግና በልቦቻቸው ውስጥ ጥሩ እና ምቹ ቦታ አላቸው፡፡ የኔና አንተም ፍቅር ምንም እንኳን ይፋ ባይወጣ አይኖቻችን ግን ያሳብቃሉ፡፡ በውስጣችን እጅግ የጋለ ፍቅር እንደተቀበረ አይኖቻችን ይናገራሉ"፡፡ ስትል ፊቷ በእምባ እየታጠቡ ሽሽጉን መውደዷን ገለፀችለት፡፡ የእድምተኛው ሹክሹክታ እና ጉምጉምታ በርክቶ ተሰማ፡፡
በአረባውያን ወግ ከትዳር በፊት ያለ የፍቅር ግንኙነት በፍፁም ውግዝ እና ቅባሎት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት ያለን ወዳጅነት ተቀብለው በፍፁም ለትዳር አያበቁትም፡፡ ምድር ተገልብጦ ሰማይ ቢደፋ አይታሰብም!! ለይላም ይህን ፈርታ ነበር እንደ ጀሂም#4 እሳት የሚፋጅ ፍቅሯን በልቧ ውስጥ አዳፍናው የቆየችው፡፡  ከእርሱ ጋር ጀነት የሆነን ነገ አልማ ነበር ከሬት የሚመረውን መሪር ውሳኔ እየመረራት የተጋተችው፡፡ መጅኑን ግን የሷን ሽሽት እና  ቸልታ ባለ መፈለግ ወስዶት ተስፋ ቆርጦ ለእብደት እየዳዳው ነው፡፡ ለዛም ነው ውስጡ የሚንተከተከውን ፍቅራዊ ጎመራ ባደባባይ በግጥም ያስተነፈሰው፡፡ እሷም የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ብላ የውስጧን እውነት ገለፀችለት፡፡

ከለይላ የወጡትን ቃላቶች ሲሰማ ከቆመበት ሚንበር ላይ ጣረ ሞት እንዳየ ሰው ሰውነቱ ዝሎ ፣ እግሩን ብርክ ብርክ እያለው ቁልቁል ትክክክክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም እምባ በሚያወርዱት በመንታ አይኖቿ ሽቅብ አስተዋለችው፡፡ በገሀድ አለሙ እና በህልሙ መሀል ያለ ጭንብርብር ምስል እያየ መሰለው፡፡ በሆነ አንድ ለሊት ላይ ምናቡ የፈጠረው ክስተት ነገር!! በዛች ደቂቃ ደስታ ፣ አለማመን ፣ ፍርሀት ፣ ቁጭት ፣ ግርምት እየተፈራረቁ አናወዙት፡፡ ከፊቱ የቆሙት ሰዎች ተገለባበጡበት፡፡ አይኑ ላይ ቀለማቶች ተንቦዣቦዡ፡፡ ያይኖቹን ሽፋሽፍት ገርበብ አድርጎ አስለምልሞ ከድኗቸው ከቆመበት ሚንበር ቁልቁቁል ተዝለፍልፎ ተፈጠፈጠ፡፡ በደስታ ብዛት ካሳበደቺው አለሙ ከእግሯ ስር እራሱን ስቶ ተዘረረ፡፡ ያ.....ቀይ መልከኛ ገፁንም የደም ጎርፍ አጨቀየው፡፡

ኣካባቢው በጩኸት እና ግር ግር ሲናጥ ለይላ በድንጋጤ ከወደቀበት መሬት ላይ አፋፍሳ እየጮኸች ጭኗ ላይ አስተኛችው፡፡ በእጆቿ ደሙን እየጠረገች ስቅስቅቅቅቅቅቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ከመጅኑን ጭንቅላት የሚፈሰው ደም እንደ ዘምዘም ውሀ ያለ ማቋረጥ ፈለቀ፡፡ ከከበቡት ሰዎች ውስጥ አንድኛው እጁን ወደ መጅኑን አንገት ሰዶ በደም ዝውውሩ የሞት ሽረቱን ጉዳይ ቸክ አደርጎ ዝም አለ፡፡ ለይላ እንደ እብድ እየጮኸች ምን ሆነ???? በህይወት አለ????? ተናገር እንጂ! እያለች የጥያቄ መዐት አዥጎደጎደችበት፡፡

ክፍል ሶስት ይቀጥላል....

አስረጅ ፦
#1"ሚንበር" (መንበር / ከፍታ ቦታ)
#2"ጀይሽ"  (ወታደር / ጦረኛ)
#3"ሻኢር" (ገጣሚ)
#4"ጀሂም" (ጀሀነም / ገሀነም)፡፡

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

10 Nov, 13:53


ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የስሜት መለዋወጥ
==========================
ከ80 እስከ 90 ከመቶ ሴቶች የወር አበባ ከመምጣቱ በፊት ያለው ሳምንት ላይ ምቾት አለመሰማት ያጋጥማቸዋል። መጠነኛ ራስ ምታት፣ የጡት መወጣጠር፣  ሆድ መነፋት ሊያግጥማቸው ይችላል። ልክ እንደ አካላዊ ለውጦች የስሜት ለውጦችም ይኖራሉ። መነጫነጭ፣ መከፋት፣ ከማህበራዊ ነገሮች ራስን ማግለል ...ወዘተ። እነዚህ ምልክቶች ብዙ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አያደርሱም። ይሁን እንጂ ከ20-30 አመቶ የሚሆኑት ላይ በስራቸው ወይም በትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ ይችላል።

ይህ ህመም የሚያጋጥማት አንዲት ሴት የወር አበባ ከ15 አመቷ እስከ 50 አመቷ ብታይ በህይወቷ ይሄ ህመም 420 ጊዜ ያጋጥማታል ማለት ነው። ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው?

1) ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህመምና የስሜት መለዋወጥ በህክምና የሚስተካከል ስለሆነ በዝምታ ከመሰቀያት ሀኪምን ማማከር።

2) ራስን መንከባከብ፣ እረፍት ማድረግ።

3) የወር አበባን ተከትሎ አንዳንድ ሴቶች ላይ የምግብ ፍላጎት ሊጨመር ወይም አንዳንድ ምግቦች ሊያምራቸው ይችላል። ሀይል ሰጪ (ካርሀይድሬት) የምግብ አይነቶች የድብርት ስሜትንና ጭንቀትን ስለሚያባብሱ በተቻለ አቅም መቀነስ።

4) ቫይታሚኖችን መውሰድ። አንዳንድ ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች በተለይ ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚመጡ አካላዊና አእምሮዊ ምልክቶችን ለመቀነስ ያግዛሉ። ከሀኪም ጋር ተማክሮ መውሰዱ ጥሩ ነው።

ዶ/ር ዮናስ ላቀው

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

10 Nov, 07:03


አንድ ሰዉ ሱና ሶላት እየሰገደ ኢቃም ቢል ምን ማድረግ አለበት....?

መልስ

:-ሁለተኛዉ ረክዓ ላይ ከሆነ ቀነስ(ቀለል) አድርጎ ይሞላል [ይጨርሳል] ::የመጀመሪያው ረክዓ ከሆነ ይቆርጠዋል[ያቋርጣል] ::

ጠያቂ:- እንዴት ነዉ የሚቆረጠዉ??

አሰላምቶ ነዉ ወይስ ሳያሰላምት?

ሼኹ ሲመልሱ:-ሳያሰላምት ይዉጣ በንያ [በማሰብ] ብቻ ::

اقرأ (አንብብ )

10 Nov, 04:58


Daily therapy 225🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

09 Nov, 18:00


(መጅኑነ ለይላ)
ክፍል 1 መሊኩ

ፍቅር |መሀባ|
የፍቅር ምንድንነት ሲፈታ ህመምነቱ ይገለፃል፡፡ አዎ እውነትም ፍቅር ህመም ነው፡፡ ከሰውነት ጀምሮ እስከ ውሳጤያዊ ነፍሳችን የሚዘልቅ ረቂቅ ደዌ!! ህመሙ በተሰማን ቁጥር ደስ በሚያሰኝ ስሜት በያንዳንዷ ህዋሳችን ደርሶ ሀሴት የሚያስደርግ ህመም!! እኛም ያን ህመም እያደር ይበልጥ እንዲያመን ወደን እንመኘዋለን፡፡ ለህመሙ ስጋ እና ነፍሳችንን እንፈቅዳለን፡፡ ምን አይነት ያማረ  ህመም!! እነዛም እውነተኞቹ ታማሚያን(አፍቃሪ) ከዛ ህመም መዳንን እና ማገገምን አይሹም፡፡ ይልቁንስ ትክክለኛው ስቃይ ፣ መጥፎው ስቃይ....ከፍቅር ህመም ውስጥ በመውጣት በሚዳነው ድነት ውስጥ ባለው እውነተኛ አለም ላይ ነው፡፡ (መዳን ማለት ለነሱ መታመም ነው)፡፡ የፍቅር ህመም ማለት ደግሞ ለነሱ ሲገለፅ ከእያንዳንዷ የስቃይ ፍሬ የፍቅርን ጣፋጭ ወይን  ጨምቆ በፍቅር ፅዋ መጎንጨት ነው፡፡

ለይላ እና መጅኑን ያን አይነት ህመም የታመሙ ፅኑ የሁብ ህሙማን ነበሩ፡፡ ካራቱ ሁለፋዑ ራሺዲን#1 አገዛዝ በኀላ የኡመውዮች ሀገረ መንግስት በሚያስተዳድረው የአረቢያ ግዛት ውስጥ ነጅድ (ሪያድ) በምትባል ከተማ ውስጥ ለፍቅር ኑረው ለፍቅር የሞቱት ህያዋውያን፡፡ በፍቅር አለም ድሙቅ ታሪክ የፃፉ አሳዛኝ ስብዕናዎች፡፡ በአረባዊ የፍቅር ወቄት ሲመዘኑ ከአልፈን ኡሉፋ#2 ጥንዶች አንድ እነሱ ሚዛን የደፉ የፍቅር መለኪያዎች፡፡ "ሹዐዳኡል ሁብ"፡፡ (የፍቅር መስዋዕት)የተሰኙት መጅኑን እና ለይላ፡፡

የውልደት ጊዜአቸው በዘመነ ሂጅራ#3 አቆጣጠር 24ኛ ሂጅራ ገደማ ላይ በሞቃታማዋ የገጠር ከተማ ነጅድ ውስጥ ነው፡፡ በኢሮጵያኑ የዘመን ቀመር ደግሞ 645 ዐ.ም ላይ፡፡ (የሰዕድ ቢን መህዲ ልጅ ለይላ ቢንት ሰዕድ እና የሙለወህ ልጅ ቀይስ ኢብኑል ሙለወህ)፡፡ ሲወለድ ካባቱ ዘንድ ቀይስ ኢብኑ ሙለወህ የተሰኘ ሙሉ ስም ወጣለት፡፡ በኀላ ላይ በለይላ ፍቅር ደግሞ በሰዎች ዘንድ "መጅኑን"#4 የሚል ቅፅል ስም ታክሎለታል፡፡ ከለይላ ጋር ከነፍሳዊ የፍቅር ቁርኝት ባሻገር በስጋ ዝምድናም ጭምር ይተሳሰራሉ፡፡ ለይላ ለቀይስ (ለመጅኑን) የአጎቱ ልጅ ነች፡፡ ከመጅኑን ቤተሰቦች አንፃር የርሷ ቤተሰቦች በሀብታቸው የታፈሩ እና የተከበሩ መሊካውያን ቢሆኑም በአረባዊ የልጅ አስተዳደግ ባህል መሰረት ከልጅነታቸው ጀምሮ በጀበሉ ሰውባን#5 ኮረብታዎች ላይ በፍየል እረኝነት መጅኑን ጋር አንድ የበረሀ አሸዋ ተራጭተው ፣ ባንድ አኮሌ የፍየል ወተት ተጎንጭተው ፣ አንድ የጋራ ንፋስ ምገው ነው ያደጉት፡፡  ያ ጊዜ ለቀይስ የህይወቱ አስኳል ነበር፡፡ ቀይስ የሚለውን የወላጆቹን ስም አስፍቆ "መጅኑን" ያስባለው ፍቅር በጮርቃ ልቡ ውስጥ የተጠነሰሰው ያኔ ነበር፡፡ ኮልታፋ አፉን በግጥም እንዲፈታ ያደረገው የለይላ ፍቅር.... ያኔ ነበር አሊፍ ያለው፡፡ በአለም ኑረቱ ላይ ያሳለፈውን እድሜ ሲቆጥር ያንን ዘመን ብቻ አስልቶ ይናገራል፡፡ እጅግ የሚናፈቅ እና አይረሴው የህይወቱ ክፍል ነውና ከዛ በኀላ እንደሞተ ነገር ......"በህይወት የነበርኩት ያኔ ነበር!" ሲል እነዛን ወርቃማ ጊዜያቶች በግጥሞቹ ይቀኛቸዋል፡፡ በጀበሉ ሰውባን የረኝነት ወቅት በለይላም ልብ ውስጥ የቀይስ ደዌ ተጋብቶባት በሴት የልጅነት ልቧ ፍቅሩን ቋጥራለች፡፡

በዚህ ሁኔታ የልጅነት እረኝነት ጊዜያቸው አልፎ ወጣትነትን ተላበሱ፡፡ ለይላ እና መጅኑን ላይ የአካል እና የሥነ-ልቦና እድገት ተስተዋለ፡፡ ከእድሜአቸው ጋር ፍቅራቸውም እኩል አብሮ ገዘፈ ፣ ጦፈ፡፡ ቀይስ በእሳታዊው ወጣትነቱ ላይ ልቡ ውስጥ የሚፏፏመው የፍቅር እሳት በጅጉ ተቀጣጠለ፡፡ የለይላም እምቡጥ አበባነት በእድሜ ፍካት ፈነዳ፡፡ እንደ አረቢያን ሰህራ#6 ባዶ ሜዳ በነበረው ሰውነቷ ላይ ጡቶቿ ጉች ጉች አሉ፡፡ እንደ ተወርዋሪ ፍላፃ ጭብጥ የማይሞላ ወገቧ ዳሌዋን አጎላ፡፡ ፀጉሯ የኮንያን ሀሮች አስንቆ ዳሌዋ ላይ ተጎዘጎዘ፡፡ ያቺ....ሙጫዋ#7 ፣ እረኛዋ ለይላ ዛሬ....ላይ ሌላ! ሆነች፡፡ ውብ ውጫዊ ገጿ ከጥልቅ ግጥም አዋቂነቷ ጋር የነጅዱን ቀይስ መጅኑን አደረጉት፡፡ ጠዋት..."ለይላ" ፣ ቀትር... "ለይላ" ፣ ማታም... "ለይላ"፡፡ እንደ ደረሳ ሲዋክ ሁል ጊዜ ለይላ ከመጅኑኑ አፍ ላይ ዋለች፡፡ ከፊል ወጣትነታቸውንም ያለ ማንም ከልካይ በሰመሪን እና ገዷ ውብ ቦታዎች አይረሴ ውብ የፍቅር ጊዜያትን አሳለፉ፡፡  ነገር ግን እነዛ ውብ ጊዜያቶች ለመጅኑን እና ለይላ አይንን ጨፍኖ እንደመግለጥ ያክል ቅፅበታዊ ነበሩ፡፡ ውብ የሆኑ ነገሮች ምንንን ቢረዝሙ አጭር ናቸው፡፡ ውድ የሚያደርጋቸውም ይህ ተዐምራዊ ጠባያቸው ነው፡፡

እናም ጊዜው በሄደ ቁጥር እድሜ እሚሉት ክፉ ዳኛ በጉርምስና ወግ አጥሮ መተያየትን ከለካላቻው፡፡ ዳር የሌለው መነፋፈቅን ፈረደባቸው፡፡ ከጀበሉ ሰውባን የፍቅር መቅደሳቸው ነጥሎ ለይላን ከቤት አዋላት፡፡ መጅኑንም ለይላን በየቀኑ እንዳሻው ማየት ተስኖት ፣ ሀሩር በሆነ መውደዱ ላይ ናፍቆት ታክሎበት ከውስጡ እሳት ጎመራ፡፡ ነደደ ፣ ተቃጠለ ፣ ተንገበገበ !!  ናፍቆት ጥፉው ፣ ናፍቆት ክፉው!!....ይሉኝታ አሳጥቶ እያክለፈለፈ ከለይላ ደጅ ያደርሰዋል፡፡ በግጥሞቹ ደጋግሞ ለይላን ያስቀኘዋል፡፡ ለይላ ይህንን ስትሰማ እንዳልሰማች ታልፈዋለች፡፡ መጨረሻም ለቀይስ ፊት ነስታ ጀርባ ሰጠቺው፡፡ መልስ የሚሹ ግጥሞቹን ሰምታ እንዳልሰማች አለፈቻቸው፡፡ በዚህ ድርጊቷ ክፉኛ ልቡ ተሰበረ፡፡ የልጅነት ፍቅራቸው ለይላ ላይ ተዳፍኖ እሱ ላይ ብቻ እንደተጋጋመ ተሰማው፡፡ በለይላ አለመወደድ ፣ በለይላ አለመፈለግ አይነት ስሜት ደበተው፡፡ ሰርክ አይኑ እምባ ቀረዘዘ ፣ ልቡg ተሰብሮ ተሰቀዘ ፣ ህይወት ኑረቱ ቀዘቀዘ ፣ ገፁ ፈዞ ደበዘዘ......ሙሉ አለሙ ተቃወሰ፡፡ የወጣት አሞቱ ፈሰሰ፡፡ በቃ!! ያ..ጅንኑ ቀይስ መጀነነ!! በዚህም ሳቢያ "መጅኑን" ተሰኘ፡፡ 

ነገር ግን ያኔ...ለይላም  ከመጅኑኑ ያላነሰ የፍቅር እሳት እየበላት ማንም እንዳያውቅና እንዳይሰማባት በውስጧ ቀብራዋለች፡፡ የማትተነፍሰው የሚያቃጥል ረመጥ ሆኖባት ሁሉን ስሜቷን በሽሽግ እንደተፀነሰ ልጅ በሆዷ አርግዛ ሚስጥሯን ደግሞ ከልቧ ማጀት ደብቃዋለች፡፡ ግና በሆድ ያለን የፍቅር ሽል አፍ ባያወራው ፍቅራዊ ህጉ እርግዝናን ያሳብቃል፡፡ ለይላም ምንም እንኳን ለመጅኑን ግድ እንደሌላት ነገር ፊት እየነሳች ብትገፋውም ስለሱ የሚሰማት ውስጣዊ ፍቅር  ናፍቆቷን ፣ መሻቷን ፣ መውደዷን .... አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ወጣትነቷ ከመጅኑኑ ደረት ላይ ሊጥል ይገፋታል ፣ ከውስጧ የሚንጣት የግጥም ዛር "ቀይስ" ፣ "ቀይስ" እያስባለ ሊያስለፍፋት ይዳዳዋል፡፡ ግና አትፈቅድለትም፡፡ ግን ደግሞ በሌላ በኩል በሷ እጦት ወደ እብደት ጎዳና ዳዴ የሚል የነፍሷ ሰው አለ፡፡

ታዳ ለምን ደበቀችው??? ክፍል ሁለት ይቀጥላል...

አስረጅ ፦
#1"ሁለፋኡ ራሺዲን" አራቱ  የኢስላሙ አለም ነገስታት (አቡበክር ፣ ኡመር ፣ ኡስማን ፣ አልይ)፡፡
#2 "አልፈን ኡሉፋ" ሺህ እና ከሺህ በላይ፡፡
#3"ሂጅራ" የአረቢያን(ኢስለማዊ)የዘመን መቁጠሪያ፡፡
#4"መጅኑን"እብድ፡፡
#5"ጀበሉ ሰውባን" የሰባንን ተራራ(በአረብያ ግዛት የሚገኝ) ቦታ፡፡
#6"ሰህራ" በረሀ፡፡
#7"ሙጫዋ" ህፃኗ፡፡

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

09 Nov, 16:07


እነሱ:- ራስህን አስተዋውቅ

እኔ:- 1000558898147
ኢብራሂም🫣

اقرأ (አንብብ )

09 Nov, 13:38


🍃 'በራስ መተማመን'
.
በአንድ ወቅት፣ አንድ የዳኝነትን ሹመት የተሰጠው ግን እውቀቱ የሌለው ሰው ነበር። እና አንድ ቀን ሁለት ሰዎች ተጣሉና ለፍርድ ወደዚህ ሰው ይመጣሉ። በመጀመሪያ ከሳሹ ክሱን ለዳኛው አቀረበለት። የተናገረው ሁሉ ዳኛውን አሳምኖት ነበርና አምኖ ተቀበለው። “ማሻ አላህ! ሐሳብህ ጥሩ ነው። ወላሂ አንተስ እውነትም ተበድለሃል። እውነቱ ያለው አንተ ጋር ነው!” አለው።

አሁን ተከሳሹ ተራ ደረሰውና ራሱን ለመከላከል፣ ንጽህናውን ለማረጋገጥና
ክሱን ውድቅ ለማድረግ ንግግሩን አቀረበ። አሁንም የዚህ ሰዉየ ንግግር
ዳኛውን አሳመነው። ሃሳቡ ተዋጠለት። ስለዚህ ለዚህኛውም ሰውየ፣ “ትክክል
ነህ፣ ሀቁ ያለው ካንተ ጋ ነው።” አለው።
እውነቱ ያለው ከተበዳዩ ወይም ከበዳዩ ሆኖ ሳለ ለሁለቱም ፍርድ ሰጠ።

ይህን የፍርድ ሂደት ከመጋረጃው ጀርባ ሆና ትክታተል የነበረችው የዳኛው
ሚስት፦ “አንቱ ሰውየ! ምን አይነት ፍርድ ነው የምትሰጡት፣ የመጀመሪያውን አንተ ነህ ትክክል አልኩ፣ ሁለተኛውንም እንደዛው። ይህ እዴት ይሆናል?” አለች። ሰውየውም፣ “ወላሂ፣ አንችም ትክክል ነሽ። የተናገርሽው በጣም ልክ ነው።” አላት።

ግፍ የተሰራበትም ትክክል ነው፣ በዳዩም ትክክል ነው፣ ፍርዱን የነቀፈችውም
ሴት ትክክል ናት። ሌላም አራተኛ ሰው መጥቶ ቢናገር ትክክል ነው። እንዲህ
አይነቱ ሰው እንግዲህ በራሱ ውሳኔ የማይተማመን እና በሰዎች ሃሳብ ብቻ
የሚመራ ሰው ይባላል። በራሱ ሀሳብ የማይመራ እና የራሱ ጠንካራ እምነት
የሌለው ሰው እንዲህ ነው። በሰው ሀሳብ ይመራል፣ ወደነፈሰበት ይነፍሳል።
ዝም ብሎ ማንኛውንም ሰው በጭፍን መከተል ስኬታማ አያደርግም፣ በራስ
መተማመንንም ይገድላል።

በራሱ የሚተማመን ሰው በሰዎች አስተያየትም ሆነ አመለካከት በቀላሉ
አይሸወድም፣ የራሱ የሆነ ጠንቃራ አመለካከት አለው። የሰዎችን ጭብጨባና ማዳመቂያ አይፈልግም። እያንዳንዱን ርምጃ በራሱ ተነሳሽነት ነው የሚወስደው። የሚያደርገው ነገር በሙሉ ትክክል ለመሆኑ ደግሞ የሰዎችን ማረጋገጫና ይሁንታ አይፈልግም፤ ምክንያቱም የሚያደርገውን ያውቃል።
ያመነበትን ነገር ያለ ምንም መሸማቀቅና እፍረት ይሰራል፣ መናገር ያለበትን ይናገራል። ሰዎች ያዘዙትን ነገር ሁሉ እሽ ብሎ አይቀበልም፣ “አይሆንም፣ የራሴ የምሰራው ስራ አለኝ፣ እንደዚህ አላደርግም።” ብሎ የሰዎችን ሃሳብ
ውድቅ ማድረግ ይችላል። “ኖ” ማለቱን ይችልበታል።

በራሱ የሚተማመን ሰው ራሱን ያውቃል። ስለራሱ ጥሩ ግንዛቤ አለው። ጥንካሬውንና ደካማ ጎኑን ለይቶ ያውቃል። ስለራሱም በጎ ምልከታ አለው። ራሱን ይወዳል፣ ራሱን ያከብራል። ለመሻሻል ይጥራል። ተጨባጭ ግቦችን ያስቀምጣል፣ ተጨባጭ ውጤቶችን ይጠብቃል። እንዲሁም የሰዎችን ትችት
በቀላሉ ተቋቁሞ ያልፋል። በራሱ የሚተማመን ሰው እንግዲህ እንዲህ ነው። የሚያወራውንም ሆነ የሚሰራውን ነገር ያውቃል።

በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች፣ ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ ከፍ ያለ ነው።
እንደዚህ አይነት ሰዎች ህይወትን በደስታ ይኖራሉ። ሁሌም ለህይወት ጥሩ የተነሳስሽነት ስሜትም አላቸው። በራስ መተማመን የሌለው ሰው ደግሞ በተቃራኒው ነው። ለራሱ ክብር የሌለው ወይም በራሱ የማይተማመን ሰው
በሌሎችም ዘንድ ዋጋ እንደሌለው ያስባል።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

09 Nov, 03:08


እስቲ ትንሽ ..ትንሽ ብቻ ቁሙ! ትንሽ ብቻ ገለል ብላቹ የምትሄዱበትን መንገድ አስተውሉ ! እስከመንገዱ መጨረሻ ሄዳቹ የመጣቹበትን የስህተት መንገድ ርዝመቱን በቁጭት መመልከት ካልፈለጋቹ ትንሽ ብቻ ቆማቹ አስተውሉ .....

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

09 Nov, 03:04


Daily therapy 224🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

08 Nov, 17:24


መጅኑን ለይላ🥰
ከ 200 ላይክ በኋላ ነገ ማታ 3 ሰአት ላይ እንጀምረዋለን
ታሪኩን እስከጀምረው እስኪ ትንሽ ላጓጓዋቹ 😆

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

08 Nov, 03:13


እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጁምአ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ ። ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡
(ሱረቱ አል-ጁሙኣህ 62:9)

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا نُودِىَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَوْمِ ٱلْجُمُعَةِ فَٱسْعَوْا۟ إِلَىٰ ذِكْرِ ٱللَّهِ وَذَرُوا۟ ٱلْبَيْعَۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

08 Nov, 03:12


Daily therapy 223🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Nov, 19:34


ነገ ጁሙዓ ነው የቻለ በጊዜ መስጂድ ይግባ ከህፍንም ይቅራ

اقرأ (አንብብ )

07 Nov, 17:55


እስኪ ዛሬ ደግሞ .......

አንድ ጥያቄ ብቻ እንድትጠይቁኝ እድሉን ብሰጣችሁ ምን ትጠይቁኛላችሁ ??
አንድ ጥያቄ ብቻ
ከታች ጥያቄያችሁን ፃፉልኝ። ኢንሻአላህ ሁሉንም ለመመለስ እሞክራለሁ

ibro smile

اقرأ (አንብብ )

07 Nov, 16:59


ሰላም አለይኩም እንዴት ናችሁ እስኪ ይሄንን ቻናል የሚገልፅ አጠር ያለ ፅሁፍ በኮመንት ፃፉ ያበረታታናል🥰

اقرأ (አንብብ )

07 Nov, 16:28


#ግዴታ😭

የስዋዚላንዱ ንጉስ የሀገሪቷ ወንዶች 5 ሴቶች ማግባት እንዳለባቸዉ ማዘዛቸው ተሰምቷል።

ትዕዛዙን ያልተቀበለ ማረፊያዉ እስርቤት መሆኑን ገልጸዋል ተብሏል።
ንጉሱ እንዳሉት የሠርጉን ወጪ እና ለእያንዳንዱ ተጋቢ ቤት ለመስጠትም ቃል ገብተዋል።

፨ይህ እንዲሆን የተደረገዉ በስዋዚላንድ የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ሴቶች ባል እንዲያገኙ ለማድረግ ነዉ።

የስዋዚላንዱ ንጉስ 15 ሚስት ያላቸዉ ሲሆን 25 ልጆች ደሞ አሏቸው፡፡

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Nov, 04:06


ቁርዓን መስማት በልባችን ውስጥ ውብ የአበባ ስፍራ እንደመገንባት ነው ። ከሌላው ጫጫታ ተነጥለን በልባችን የአበባ ስፍራ እንደሰት ዘንድ ከቁርዓን ጋር እንወዳጅ ።

اقرأ (አንብብ )

07 Nov, 04:05


አዎ ነገሮች ከበድ ይላሉ

ሁሉም ምቶች የሚያርፉብን..ሁሉም ስድቦች የሚነኩን..ስለሁሉም ሰው ሀላፊነት ያለብን የሚመስለን ጊዜ አለ...አዎ ያ ወጣትነት ነው ። ወጣትነት ከዚ አለም ጋር ለሚደረግ ትውውቅ በር ከፋች ነው ያበር ሲከፈት ብቅ ብቅ የሚሉ መጥፎ ስሜቶች ብዙ ናቸው ...ተስፋ መቁረጥ...መሰበር...መለያየት ሁሉም ራሳቸውን ይገልጣሉ ።

ጠንክሩ😊
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

07 Nov, 04:01


Daily therapy 222🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

06 Nov, 18:00


بِسْمَِّ اللهِ الرحْمَنِ الرحِيم

  💢 ሂጃብ ክፍል - 7 💢

ኢንሻ አላህ በዚኛው ክፍላችን  ሸሪዐዊ ሂጃብ (ኒቃብን ) ሱና ነው የሚሉ አካላት የሚያቀርቡትን ማደናገርያ እስከመልሳቸው እናያለን


☞ ኒቃብ ግዴታ አይደለም፣ፊትን መክፈት ይቻላል ለማለት የሚነሱ መረጃዎች እና እርማታቸው ከሸይኽ ሷሊህ አል–ዑሰይሚን ረሂመሁላህ :-

☜ الاول: قوله تعالى {ولا يبدين زينتهن إلا ما ظهر منها }

☞ አንደኛ ማደናገርያቸው "ከጌጦቻቸው ግልፅ የወጣውን እንጂ እንዳይከፍቱ" የሚለውን የአላህ ንግግር ነው ።

☜ قال ابن عباس رضي الله عنهما هي وجهها وكفاها والخاتم .

☞ ዓብደላህ ኢብኑ ዓባስ ይህ(ግልፅ የሆነው) ማለት ፊቷ እና መዷፎቿ በማለት ፈስሮታል ይላሉ :-

☞ መልስ :- ይህ ተፍሲር ሂጃብ በግዴታነት በሌላ የቁርኣን አንቀጽ ከመደንገጉ በፊት የተነገረ ነው።
ይህንንም ኢብን ተይሚየህ መጅሙኡል ፈትዋ ላይ ተናግሯል።

ሲቀጥል ኢብን አባስ በሌላኛው የቁርኣን አንቀጽ ተፍሲር ላይ ሴቶች ፊታችውን መሸፈን እንዳለባቸው ተናግሯል ።
ስለዚህ የቀድሞው ንግግሩ ከኋላው ባለው ንግግር ተሽሯል ።

እንደዚሁም የአብደሊህ ኢብን መስኡድንም ተፍሲር ይጋጫል ( ማለትም ፊት መሸፈን ዋጂብ እንደሆነ የሚናገረውን )  
☞ ይህ ተፍሲሩ መቀበሉ በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆን አይደለም ምክንያቱም
የአንድ ሶሃባ ተፍሲር ሌላ ሶሀባ ከተቃረነው የምንቀበለው ከሌሎች ማስረጃዎችም አንፃር የተሻለ የሚሆነውን ነው።

ይህንን የኢብኑ ዓባስ ተፍሲርም ዓብደላህ ኢብኑ መስዑድ "ግልፅ የሆነው ሲቀር" የሚለውን ከላይ
የሚታየው ልብሷ ወይም ኩታዋ ነው ብሎ ፈስሮት ተቃርኖታል።

ስለዚህም ከሌሎች ማስረጃዎች አንፃር
ራጂህ የሚሆነው የኢብኑ መስዑዱ ተፍሲር ነውና እሱን እንይዛለን።

☜ الثاني : ما رواه أبو داود في في سننه عن عائشة رضي الله عنها أن أسماء بنت ابي بكر دخلت على رسول الله  صلى الله عليه وسلم وعليها ثياب رقاق فأعرض عنها وقال  . يا أسماء إن المرأة إذا بلغت سن المحيض لم يصلح أن يرى منها إلا هذا وهذا واشار الى وجهه وكفيه

☞ ሁለተኛው ማደናገርያቸው :- አቡዳውድ አላህ ስራዋን ይውደድላትና ከአዒሻ ይዞ በዘገበው ፤አስማዕ ቢንት አቢበክር ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም 
ዘንድ ገባች ከላይ ላይ ስስ ልብስ ነበርና ከእርሳ ዞር አሉ። ከዛም አስማእ ሆይ ሴት ልጅ ሀይድ የምታይበት እድሜ ላይ
ከደረሰች ከዚህ እና ከዚህ ውጪ ብለው ከእርሷ ሊታይ አይገባም ብለው ወደ ፊታቸው  እና ወደ እጃቸው አመላከቱ።

                 ☞ መልስ 

ይህ ሃዲስ በሁለት መልኩ ዶዒፍ ነው።

  ☞ አንደኛ: በአዒሻ እና ባስተላለፈው ኻሊድ ኢብኑ ዱረይክ መሀከል የሰነድ መቆረጥ አለበት ። ይህንንም አቡዳውድ
እራሱ ኻሊድ ኢብኑ ዱረይክ ከአዒሻ አልሰማም ብሎ ገልጿል።

☞ሁለተኛ: በሰነዱ ላይ ሰዒድ ኢብኑ በሺር ነስሪይ አለበት ኢብኑ መህድይ ትቶታል(ከሰነዱ አውጥቶታል) አህመድ፣
ኢብኑ መዒን፣ ኢብኑ መደንይ፣ነሳእይም ዶዒፍ አድርገውታል። በዚህ ሃዲስ ማስረጃ አይደረግበትም።

☞እንዲሁም አስማእ ቢንት አቢበክር ወደ መዲና ስትሰደድ 27 አመቷ ነበር። በዚህ ትልቅ እድሜዋ ላይ ሆነ በስስ ልብስ ነብዩ ዘንድ ትገባለች ማለት የሚከብድ ነገር ነው።

አላህ በላጩን አዋቂ ነው።

☜ الثالث : ما رواه البخاري وغيره عن ابن عباس رضياالله عنهما أن أخاه الفضل كان رديفا للنبي صلى الله عليه وسلم
في حجة الوداع فجاءت امرأة من خثعم فجعل الفضل ينظر إليها وتنظر إليه فجعل التي صلى الله عليه وسلم يصرف وجه الفضل الى الشق الاخر ففي هذا دليل على أن هـذه المرأة كاشفة وجهها . { رواه أحمد وابو داود وترمزي }

☞ ሶስትኛው ማደናገርያቸው <<ከጃቢር ኢብኑ ዓብደላህ ስራውን አላህ ይውደድለትና ይዘው ቡኻሪም ሌሎችም ያስተላለፉት ሃዲስ ነው። ነብዩ ሰዎችን የዒድ ሶላት አሰገዱ ከዛም ሰዎች መከሩ፣ አስታወሷቸውም ከዛም ወደ ሴቶች
መጡና መከሯቸው፣ አስታወሷቸውም። ከዛም አሉ: እናንተ ሴቶች ሆይ ሶደቃ አውጡ እናንተ በጀሃነም ውስጥ ትበዛላቹና አሏቸው። ከሴቶች መሃከል አንዲት ፊቷ ማድያት የሆነች ሴት ቆመችና ፤ለምን የአላህ መልክተኛ ሆይ አለቻቸው። እሳቸውም ምክንያቱም እናንተ ስሞታን ታበዛላቹ ፣የባሎቻችሁን ውለታ ትክዳላቹ አሉ። ከዛም ከጌጦቻቸው ከቀለበት እና ከጆሮ ጌጦቻቸው በቢላል ልብስ ላይ እየወረወሩ ሶደቃ ማውጣት ጀመሩ።>>


ታድያ ፊቷ ክፍት ባይሆን ኖሮ የፊቷን ሁኔታ ባላወቀ ነበር ይላሉ :-

☞ መልስ :-  ይህ ሃዲስ መቼ እንደሆነ አልተወሳም። ይህ ክስተት ምን አልባትም የመሸፈን ህግ ከመውረዱ በፊት ሊሆነ 
ይችላል። ይህ የሂጃብ ድንጋጌ የወረደው በአምስተኛው ወይም በስድስተኛው አመተ ሂጅራ ነው። የዒድ ሶላት ደግሞ
በሁለተኛው አመተ ሂጅራ ነው። አልያም ደግሞ ይህች ሴት በእድሜ ከገፉ ለትዳር ከማይከጀሉ ሴቶች ሆና ፊቷን መክፈት ስለሚፈቀድላት ከፍታው ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ሌሎች ሴቶች ላይ መሸፈን ግዴታ መሆኑን አይከለክልም።

ይህ ማስረጃ እየጠቅስን ያብራራነው ብዙዎች በዚህ ጉዳይ በሰፊው ፅፈው ስለሚያወዛግቧቸው ፍርዱን ማወቅ
ስለሚፈልጉ ነው። እያንዳንዱ ጥናት የሚያደርግ ሰው አንድን ነገር አምኖ ከመቀበሉ በፊት ማስረጃዎችን ማየት
የሚኖርበት ቢሆንም እነዚህ መገላለጥ የሚፈልጉ ሰዎች ግን ከጥናት እና ከእይታ በኩል ትክክለኛ የሆነ አስተውሎን አይሰጧትም።

በትንሹ የሚያቀርቡትን ማደናገርያ ከነ መልሳቸው አይተናል አላህ ሁላችንንም ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን....


ሂጃብን በተመለከተ ያዘጋጀሁላቹ ፅሁፍ ይሄንን ይመስል ነበር
ማንኛውንም እርምት ሚደረግበት ነገር ካለ በዚ ያድርሱኝ

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

06 Nov, 13:52


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ

የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

06 Nov, 11:56


اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
    አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
=============================
  📖 ራሀቱል ቀልብ የቁርአንና የተጅዊድ ማእከል*

               ማእከላችን በኦን- ላይን ከ አሊፍ ጀምሮ እስከ ተጅዊድ ትምህርት ድረስ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል። እርሶም ፈጥነው ይመዝገቡና ትልቁን የቁርዐን እውቀት ይሸምቱ።

     👉  ቃኢደቱ ኑራኒያ ለጀማሪዎች
     👉  ነዝር ከመሰረታዊ ተጅዊድ ጋር
    👉 ሂፍዝ
👉  የተሟላ የተጅዊድ ትምህርት
    
————————————————
👉  የቁርዐን ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ

   ☆ አንድ ተማሪ ከተመዘገበ በኋላ የተመደበለት ኡስታዝጋ
👉 በቴሌ ግራም
      ኦን -ላይን ወይም ላይቭ የሚሰጥ ይሆናል
  ለወንድም ለሴትም ተማሪዎች በቂ ቦታ አለን
   የቁርዐን ጊዜው በሳምንት 5 ቀን ወይም በሳምንት 3 ቀን

                ተማሪው በሚመቸው ሰአት
=============================

ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
               👇👇👇👇👇
                  @Rahatulkalbe
@Rahatulkalbe
=============================
       


  *ራሀቱን ቀልብ የonline ቂርአት ማእከል*
=============================

اقرأ (አንብብ )

06 Nov, 07:55


"  ከናተ በላጩ ቁርአንን አውቆ ያሳወቀ ነው"

        [ሀቢቡና ሰለዋቱ ረቢ ወሰለም]


     
    🔺አል - አማና  ኦንላይን የቁርአን  ማዕከል
በተለያዩ ምክንያቶች ቁርአንን አልቀሩም እንግዲያውስ አል - አማና ኦላይን የቁርአን ማአከል ባሉበት ሆነው ቁርአንን  ሊያስተምሮ ቤቶ ድረስ መቷል እንግዲያውሰ ከእርሶ የሚጠበቀው በእጆ ያለውን 📱ሞባይል ብቻ በመጠቀም ቁርአንን ይማሩ
    
   መድረሳችን ብቁና ልምድ ባላቸው ኡስታዞች እየሰጠ ያለውን የቂርዐት ሁኔታ በ3 ደረጃ የከፋፈለ ሲሆን ፦
 
🔺በደረጃ 1
ለጀማሪዎች ቃኢዳ መሰረታዊ የቁዐን አነባበብ
🔺በደረጃ 2
የቁርዐን ንባብ ከመሰረታዊ የተጅዊድ ትምህርት ጋር እንዲሁም
🔺በደረጃ 3
የቁርዐን ሒፍዝ

📚የቁርአን ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ

  ♦️አንድ ተማሪ ከተመዘገበ በኋላ የተመደበለት ኡስታዝጋ በጉግል ሚት ወይም በዙም አፕልኬሽን ኦንላይን ወይም ላይቭ የሚቀራ ይሆናል።
 
   ♦️ እንዲሁም አንድ ተማሪ በመዓከሉ የሚሰጠውን ትምህርት በአግባቡ ተከታትሎ ከጨረሰ የመዓከሉን እውቅና ያለው ሰርከትፌት ይበረከትለታል
 
   የቁርዐን ጊዜው በሳምንት 5 ቀን እንዲሁም በቀን ለ30 ደቂቃ አንድ ተማሪ የሚቀራ ይሆናል።

በአላህ ፍቃድ በዚህ በተወሰነ ጊዜ ቁርአንን  ያነባሉ

📕 በቴሌግራም ለመመዝገብ
                    👇  
       @Alamanamerkez

📕 ማንኛውም ሃሳብ አስተያየት ካሎት
                  👇
      @Allamanaabot

📕 የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
                    👇
     https://t.me/Alamanamerkez34

اقرأ (አንብብ )

06 Nov, 02:57



  በደረቀው መሬት  ከሞተ በኋላ
ከዝናቡ ጠጥቶ  እንደ ሚበቅል ሁላ

ችግር መከራውን  እጦቱን ተሻግረህ
  የትግስትህ ፍሬ  በስሎ ታየዋለህ!!
ታገስ ብቻ!!




🖊አቡ ሙስሊም!!

اقرأ (አንብብ )

06 Nov, 02:55


Daily therapy 221🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

05 Nov, 18:02


بِسْمَِّ اللهِ الرحْمَنِ الرحِيم

  💢 ሂጃብ ክፍል - 6💢

እስካሁን ሂጃብ(መሸፈን ) በተመለከተ የወረዱትን የቁርኣን አንቀፆችን    በትንሹ ተመልክተናል አሁን ደግሞ  አላህ ካለ የምልክተኛውን ሰለላሁ  አለይሂ ሰላም ሀዲሶችን እንመልከት :-

           የመጀመርያው ሀዲስ

☜ إذا خطب أحدكم امرأة فلا جناح عليه أن ينظر إليها إذا كان إنما ينظر إليها لخطبته   و إن كانت لا تعلم. قال العالمة األلباني في "السلسلة الصحيحة"1/152 :أخرجه الطحاوي و احمد 5 -424

☞ ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ አንዳቹ አንድን፣ሴት ባጨ ጊዜ ፤የማትታወቅ ከሆነችና አላማው ለማጨት ብቻ እስከሆነ ድረስ ቢያያት ችግር የለውም።
ይህ ሀዲስ የሚያሳየው ለማጨት ብሎ እንጂ ለሌላ አላማ ማየት እንደማይችል ነው።
እሷን አይቶ ለመደሰት ብሎ ከሆነ ወንጀለኛ ይሆናል። ስልሆነም እርሷ ልትሸፈን እና እርሱም ከማየት ሊቆጠብ ይገባል።


             ሁለተኛው ሀዲስ

☜ وقد ثبت أن النبي صلى الله عليه وسلم لما أمر بإخراج النساء إلى مصلى العيد قلن يا رسول الله إحدانا لا يكون لها جلباب فقال النبي صلى الله عليه وسلم :
"لتلبسها أختها من جلبابها"[  رواه البخاري ومسلم]

☞  ነብዩصلى الله عليه وسلم ሴቶች በዒድ ቀን ወደ መስገጃ ቦታው እንዲሄዱ ባዘዟቸው ጊዜ አንዳችን ስትወጣ የምትለብሰው ጅልባብ ከሌላትስ ሲባሉ ፤እህቷ ከጅልባቧ ታልብሳት (ትስጣት) አሉ። { ብኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል}

ይህ ሀዲስ የሶሃባ ሴቶችበጅልባብ እንጂ የማይወጡ መሆናቸው ነው የሚያሳየን። ምክንያቱም የምትለብሰው ጅልባብ ባይኖራትስ? ነበር የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ፣ ነብዩም صلى الله عليه وسلم ወደ ኢድ ሶላቱ መውጣት የተደነገገ ከመሆኑም ጋር አይ ችግር የለውም ያገኘችውን ትልበስ ወይም ተገላልጣ ትውጣ ብለው አላቀለሉትም።
እህቷ ከትርፍ ጅልባቧ ታልብሳት ነው ያሉት።

ታድያነብዩ صلى الله عليه وسلم ያልፈቀዱትን አለባበስ  ማን ይደፍረው ይሆን?

      ሶስተኛው ሀዲስ

☜ عن ابنِ عُمَرَ رضي الله عنهما، قال: قال رسولُ الله صلى الله عليه وسلم :
"مَن جَر ثَوبَه خُيَلاءَ لم ينظُرِالله إليه يومَالقيامة
فقالت أمُّسَلَمةَ: فكيف يَصنَعْنَ النِساءُ بذُيولهِن؟ نه؟ قال: يُرخِينَ شِبرا، فقالت:  إذا تنكَشِفُ أقدامُهن، قال: فيُرخينَهَِ ذراعا
لا يَزِدنَ عليه" {أخرجه الترمذي 1731 والنسائي  5336، وأحمد 5173 }

☞ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ልብሱን ለኩራት ብሎ የጎተተ
(ከቁርጭምጭሚቱ) በታች ዝቅ ያደረገ ወንድ የቂያማ ቀን አላህ ወደ እርሱ
አይመለከትም አሉ። ኡሙ ሰለማም ረድየላሁ አንሃ  ሴቶችስ እንዴት ያደርጋሉ አለቻቸው እርሳቸውም ስንዝር ያክል ያስረዝሙት አሉ። ተረከዛቸው የሚከፈት ከሆነሳ አለቻቸው። በቃ አንድ ክንድ ያስረዝሙት ከዛ እንዳይጨምሩ አሉ።
ቲርሚዚ ነሳኢ እና አህመድ ዘግበውታል።

☞ በ ዚህ ሀዲስ ነብዩ ሴቶች ተረከዛቸው እንዳይታይ ሲባል አንድ ክንድ ታስረዝመው ካሉ ፤ትልቁ የውበት መገለጫ የሆነው እና ለፈተናም ከተረከዝ በላይ የሚያጋልጥ የሆነው ፊቷን መሸፈኑ ይበልጥ ግድ ይሆናል።

      አራተኛው የሀዲስ ማስረጃ

☜  عن عائشة رضي الله عنها قالت : كان الركبان يمرون بنا ونحن محرمات مع الرسول صلى الله عليه وسلم فإذا جاؤونا سدلت إحدانا جلبابها على وجهها من رأسها فإذا جاوزونا كشفناه {رواه أحمد وأبو داود وابن ماجه ففي قولهـا , فإذا حاذونا تعنى الركبان  { سدلت إحدانا جلبابها على وجهها }

☞ አዒሻ አላህ መልካም ስራዋን ይወደድላትና እንዲህ ትላለች እኛ ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ጋር ሀጅ ኢህራም ያደረግን ሆነን ወንድ ጋላቢዎች በአጠገባችን ያልፉ ነበር። ፊት ለፊታችን ሲመጡ ከእኛ አንደኛችን ጅልባቧን ከጭንቅላቷ ላይ ወደ ፊቷ ታወርድ ነበር፣ ባለፉን ጊዜ ደግሞ ከፊቷ ላይ ትገልጠው ነበር።

አህመድ፣ አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።

እስካሁን ባየነው ክፍላችን አራት የቁርኣን እና አራት ይሀዲስ ማስረጃዎችን ተመልክተናል አላህ ቅኑን መንገድ ለመራው በጣም ከበቂ በላይ ነው እነዚህ ማስረጃዎች ።

አንድ ታላቅ አሊም እንዲህ ይላሉ " ሀቅን ለፈለገ ሰው አንድ ማስረጃ በቂው ነው ሀቅን ላልፈለገ ግን ሺ ማስረጃዎችን ብታመጣለት አይቀበልህም"
ሀቅን ያልፈለገ ሰው  የተለያዩ ማወዛገብያዎችን በማምጣት ለማምለጥ ይፈልጋል ኢንሻ አላህ እኛም የሚያመጡትን ማወዛግቢያዎች ኢንሻ አላህ በቀጣይ ክፍላችን እናያለን።

አላህ ሁላችንንም ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን......

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

ክፍል ሰባት ይቀጥላል ............

اقرأ (አንብብ )

05 Nov, 16:26


መልሶቻችሁን ከምክንያት ጋር ብታረጉት የበለጠ ተመራጭ ነው

اقرأ (አንብብ )

05 Nov, 16:24


ሴቶች እንደ አባታቹ አይነት ባል እሺ ትላላቹ ? 

اقرأ (አንብብ )

05 Nov, 16:23


ድጋሚ ብትፈጠሩ የእናንተ ወላጆች ድጋሚ ወላጅ እንዲሆኑ ትፈልጋላቹ ?

اقرأ (አንብብ )

05 Nov, 11:01


በድጋሚ የተለጠፈ

🔗ሶላት የማይሰግድ  ሁኖ የሞተ  ሰዉ ፍርዱ..?

መልስ

ሶላት የማይሰግድ ሁኖ የሞተ ሰዉ ገላዉን ማጠብ  ሀራም ነዉ : ጀናዛዉን ማጠብ ሀራም ነዉ : በእሱ ላይ ሶላተ ጀናዛ መስገድ ሀራም ነዉ : የሙስሊሞች ቀብር መቅበር  ሀራም ነዉ : አሏህ እንድምረዉ እና እንድያዝንለት ዱዓ ማድረግ ሀራም ነዉ ::

ምክንያቱም:- ከእሳት ሰዉዎች  ነዉ : በኩፍር ለሞተ  ለአንድም ሰዉ አሏህ እንድያዝንለት ይቅር እንድለዉ ዱዓ ማድረግ አይፈቀድም : አሽሀዱ አላ ኢላሀ ኢለሏሁ ወአነ ሙሀመድ ረሱሉሏህ   ቢል እንኳ ካፊር ነዉ ::


ይሄ ምስክርነት ስራዉ ዋሽቷል እና : ሙናፊቆች ላኢላሀ ኢለሏህ ይላሉ...ለረሡል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንተ የአሏህ መልዕክተኛ እንደሆንክ እንመሰክራለን ይሉ ነበር ::

እንደዚሁ ሶላት የማይሰግድ ሁኖ  የሞተዉ ሰዉ ቅርብ ዘመዶች የሟቹን ንብርት መዉረስ አይፈቀድላቸዉም ::


ቡኻሪ እና ሙስሊም የተስማሙበት ሀዲስ የኦሳማ ቢን ዘይድ አሏህ መልካም ስራዉን ይዉደድለት:- ሙስሊም የሆነ ሰዉ ካፊር ንብረት መዉረስ አይፈቀድለትም :ካፊር የሆነ ሰዉ የሙስሊም ንብረት ሊወርስ አይፈቀድለትም ::

ሶላት የማይሰግድ ሁኖ የሞተዉን ሰዉ  ታድያ ምን እናድርግ?

ከሀገሩ ዉጭ እንሸከመዋለን : ጉርጓድ እንቆፍራለን እንደፍነዋለን : ጀናዛዉን ሳናጥብ:ጀናዛዉን ሳንከፍን : በጀናዛዉ ላይ ሶላት ሳይሰገድ ::አሏህ ይጠብቀን 🤲

@anbeb_islamic
@furqan_oficial

اقرأ (አንብብ )

05 Nov, 05:02


ዱንያን የጀመረው እንጂ የጨረሰው የለም!
ተዋደዱ ተፋቀሩ 🙌

اقرأ (አንብብ )

05 Nov, 04:58


Daily therapy 220🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

04 Nov, 19:02


መጡም አይጠቅሙኝም ቀሩም አይጎዱኝም እኔ አላህን ይዤ እየሰራው ነው!🙌

اقرأ (አንብብ )

04 Nov, 18:02


بِسْمَِّ اللهِ الرحْمَنِ الرحِيم

           💢 ሂጃብ ክፍል - 5💢

ሂጃብ(መሸፈን)ለመደንገጉ የወረዱ
   የቁርአን አንቀፆች ስንመለከት

             ሶስተኛ ማስረጃ

☜ ﴿وَقَرنَ في بُيوَِتكُن وََلََاتبَرجنَََ تبَرُّجَ الجاهِلِيةِألولى ....  األحزاب 33
☞" በቤታችሁ እርጉ የቀደምት ጃሂሊዮችን አይነት መገላለጥ አትገላለጡ" ። (አህዛብ 33)

☞ ጃሂልያ ማለት አንድ ነብይ ተልኮ ሌላ ነብይ እስኪላክ በመሃከል ሰዎች ከመልእክተኞች አደራ ተዘንብለው
ስሜታቸውን በመከተል የሚያሳልፉት ጊዜ ሲሆን በዚህ አንቀፅም ነብዩላህ ሙሳ እና ዒሳ የአላህ ሰላም በእነርሱ ላይ ይሁንና ከተላኩና መልእክታቸውን አድርሰው ወደ አላህ ከሄዱ በኋላ
ነብዩ صلى الله عليه وسلم እስኪ ላኩ ድረስ የእነርሱን መልእክት በመተው ሰዎች ስሜታቸውን ብቻ በመከተል ፣ጣዖታትን በማምለክ ይጓዙ ነበር እናም ያ ዘመን የጃሂልያ(የአለ አዋቂነት፣ የድንቁርና) ዘመን ይባላል።

እናም ያኔ ሴቶቻቸው የሴትነት ባህሪ የራቃቸውና መገላለጥን ባህላቸው ያደረጉ ነበሩና እንደ እነርሱ አትገላለጡ ሲል ያመላክተናል።

አሁን ያሉት እህቶች የሚለብሱት  አለባበስኮ አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ  ያኔ በጃሂሊያ ዘመንኮ መገላለጥ የሚባለውን አለባበስ የሚለብሱ እህቶች አሉ አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራቸውና ሞት አለብኝ ሂሳብ አለብኝ በአላህና በመልክተኛው አምኛለው ከምትል እንዲት እንስት ይህ አለባበስ አይጠበቅም ስለዚህ ቆም ብለን እናስብ እህቶቼ ሞት አለብን ሂሳብ አለብን ጀነት እና ጀሀነም ገና አለ መች እና የት እንደምን ሞት አናቅም።

              አራተኛው ማስረጃ
☜ 

﴿َلا جُناحَ عَلَيهِنه في آبائِهِن ولا أَبنائِهِن
وَلاإِخوانِهِن وَلا أَبناءِإخَواَِهِن وَلا أَبناءِأَخَواتهِن ولا نِسائِهِن ولا  ما مَلَكَت أَيمانُهُن وَاتقينََّ الله إِن اللهَ كانَ عَلى كُل ِشَيءٍ شَهيدا}[ األحزاب 55]

☞ በአባቶቻቸው፣በወንድ ልጆቻቸውም፣ በወንድሞቻቸውም፣ በወንድሞቻቸው ወንድ ልጆችም ፣በእህቶቻቸው ወንድ
ልጆችም፣ በሴቶቻቸውም (አማኝ በሆኑት)፣በእጆቻቸውም በያዟቸው ባሮቻቸው ፊት በመገለጣቸው ሀጢአት
የለባቸውም አላህን ፍሩ አላህ በሁሉም ነገር ላይ መስካሪ ነውና ።
(ሱራ አል -አህዛብ 55)

☞  ታላቁ የቁርአን ተንታኙ ኢብኑ ከሲር ይህንን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ: አላህ አማኝ ሴቶችን ከባዳ (ሊያገቧቸው
ከሚችሉ) ወንዶች እንዲሸፈኑ ካዘዘ በኋላ እነዚህን የቅርብ ዘመዶቿ ዘንድ ሙሉ አካሏን መሸፈን ግዴታ እንደማይሆንባት ገልፇል።

የትኛዋም አማኝ ሴት ለእርሷ የቅርብ ዘመድ የሆኑ ወንዶች ዘንድም ቢሆን በግልፅ ከሚታዩ እና የተለመዱ አካላቶቿ ማለትም ፊቷ ፣ እጆቿን እስከ ክንዷ፣እግሯ እና ፀጉሯ እንጂ ከዛ ውጪ ያለውን መግለጧ ስርአት አይደለም።

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

ክፍል ስድስት ይቀጥላል...
...

اقرأ (አንብብ )

04 Nov, 09:48


"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!"
~~
በነብያችን ﷺ ላይ
የሚሳለቅ እራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም። የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል።

ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው። ትላንትም የዛሬዎቹ ውሾች አያቶች የመልእክተኛውን ክብር ሊያንቋሽሹ ሞክረው ነበር። አላህ ግን እራሱ ለመልእክተኛው ﷺ ተከላካይ ጠበቃ ይሆንና መልእክተኛው ግን ነገሩን ንቀው እንዲተውት እንዲህ ይጠቁማቸዋል፡-

(فَٱصۡدَعۡ بِمَا تُؤۡمَرُ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ۝  إِنَّا كَفَیۡنَـٰكَ ٱلۡمُسۡتَهۡزِءِینَ ۝  ٱلَّذِینَ یَجۡعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَۚ فَسَوۡفَ یَعۡلَمُونَ ۝  وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّكَ یَضِیقُ صَدۡرُكَ بِمَا یَقُولُونَ ۝  فَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِینَ ۝  وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ یَأۡتِیَكَ ٱلۡیَقِینُ)

"የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለፅ፤ አጋሪዎችንም ተዋቸው። እኛ ተሳላቂዎችን ሁሉ በቅተነሃል። (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፤ በርግጥም (የስራቸውን ዋጋ) ወደፊት ያውቃሉ። አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በርግጥም እናውቃለን። ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ከሰጋጆቹም ሁን። እውነቱም (ሞት) እስከሚመጣህ ድረስ ጌታህን አምልክ።" [አልሒጅር 94-99]

ስለዚህ ተሳላቂዎቹ ውሾች ቢሳለቁም የነብያችን ﷺ ዝና የበለጠ ይገናል። የውሾቹ ስም ይከስማል። ውሻ ደግሞ ምን ታሪክ አለውና?!! እስኪ የነብያችንና የትላንት ጠላቶቻቸውን ዝና አወዳድሩ።

ሲጀመር መወዳደር ይችላሉ? በጭራሽ!! “የሰማይና የመሬት ያክል ነው” ብንል እንኳ በትክክል አይገልፀውም።

ግን የነብያችንን ﷺ ክብር ለማጉደፍ ተፍ ተፍ የሚሉ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን? መልሱ ግልፅ ነው።

1.  አንዳንዶቹ በነብዩ ﷺ እውቅና ሂሳብ እውቅና መሸመት የሚፈልጉ ናቸው። “አንዳንዶች ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ” ሲባል አልሰማችሁም?

2.  ሌሎቹ ደግሞ የኢስላም ውበቱና ሁለንተናዊነቱ የሚያስቀናቸው፤ ከፍተኛ ግስጋሴው የሚያስበረግጋቸው ናቸው። ስለሆነም ሙሐመድን ﷺ ሲያንቋሽሹ የኢስላም ውበቱ የሚደበዝዝ፣ ግስጋሴው የሚገታ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ተቃራኒው ነው። ኢስላም ዛሬ ጠላቶቹን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው። ስለዚህ ውሾቹ አመል ሆኖባቸው ይጮሃሉ እንጂ የኢስላምን ግስጋሴ ሊገቱት አይችሉም!! ውሾቹ ይጮሃሉ፣ ዋው! ዋው!....።

ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል። ውሻ ግመልን ማስቆም ከቻለች ትሞክር። ባይሆን ከኛ አንድ ነገር ይጠበቃል። ከሃዲዎችን የነብያችንን ﷺ ስም ለመዘለፍ ያበቃቸው ለነብዩ አስተምሮ ያላቸው ጥላቻ መሆኑ ይታወቃል።

አዎ የነቢዩ ﷺ ሱና እጅጉን ያስቆጫቸዋል!! እውነቱ ይህ ከሆነ ከሃዲዎችን የበለጠ ለማስቆጨት የሚጓጓ፤ ለሙሐመድ ﷺ እውነተኛ ወዳጅነቱን ማንፀባረቅ የሚፈልግ፣ ብሎም የአላህን ውዴታ ማትረፍ የሚሻ የበለጠ ወደ መልእክተኛው ሱና ይቅረብ፤ ትእዛዛቸውንም ይፈፅም፤ ከከለከሉትም ይራቅ። ይህን የሚያደርግ ጠላቱን የበለጠ ያስቆጫል። የአላህንና የመልክተኛውንም ﷺ ውዴታ ያፍሳል።

ያ ሱብሓላህ!!! የአላህና የመልክተኛውን ውዴታ ያገኘ ምን የቀረበት ነገር አለ?!!!! ያ ወሃ፞ቡ አንተ ወፍቀን!!! ኣሚን

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

04 Nov, 08:01


አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ ወበረካትሁ

ቁርአንን ልምድ ባላቸው ሴት ኡስታዛዎች ባላችሁበት ሆናችሁ በስልካችሁ መቅራት የምትፈልጉ

ቃኢደቱል ኑራኒያ ለጀማሪዎች

ቁርአን በነዘር

ቁርአን በተጅዊድ

ቁርአን በሂፍዝ

መቅራት የምትፈልጉ እህቶች @Ha2947 ላይ አናግሯት

اقرأ (አንብብ )

04 Nov, 02:45


Daily therapy 219🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

03 Nov, 19:06


ገንዘብ የሚፈልግ ካለ ያናግረኝ የምሬን ነው አብረን እፈልጋለን😁

اقرأ (አንብብ )

03 Nov, 18:01


بِسْمَِّ اللهِ الرحْمَنِ الرحِيم

           💢 ሂጃብ ክፍል - 4💢

  ሂጃብ(መሸፈን) ለመደንገጉ የወረዱ
      የቁርአን አንቀፆች ስንመለከት

           ሁለተኛው ማስረጃ:

☜ ﴿وَقُل لِلمُؤمِناتِ يَغضُضنَ مِن أَبصارِهِن وَيَحفَظنَ فُروجَهُن ولا يُبدينَ زينَتَهُن إِلا ما ظَهَرَمِنها وَليَضرِبن بِخُمُرِهِن عَلى جُيوبِهِن ول يُبدينَ زينَتَهُن إِلا لِبُعولَتِهِن أَو آبائِهِن أَو آباءِبُعولَتِهِن أَو أَبنائهن أو أبناء بعلتهن أو إخوانهن أو بني إخوانهن أو بني أخواتهن أو نسائهن أَو ما مَلَكَت أَيمانُهُن
أَوِالتابِعينَ غَير ألى الإربة من الرجال أو الطفلى  الذينَ لَم يَظهَروا عَلى عَوراتِا
النساءِولا يَضرِبنَ بِأَرجُلِهِن لِيُعلم ما يخفين من زينتهن وتوبوا إلى الله جَميعا أَيُّهَا لمُؤمِنونَ لَعَلكُمَُ تفلِحونَ﴾[النور:31]
☞ "ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይስበሩ (ይከልክሉ) ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡
ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡የውስጥ ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለእነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ "።
በሱራ አል– ኑር ምእራፍ 24፥አንቀፅ 31


☞ ይህ አንቀጽ ሲወርድ ሴቶች በኒቃብ ተሰትረዋል፥ "ኒቃብ"نقاب ማለት "መሸፈኛ" ማለት ነው፦ ኢማም ቡኻርይ
መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4759
ሶፊያህ ቢንት ሸይባህ እንዳስተላለፈችው : "ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንዲህ ትል ነበር፦ "ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ" የሚለው አንቀጽ በወረደች ጊዜ ሴቶቹ ከወገቦቻቸውን ጨርቆች በኩል ይቆርጡና ጭንቅላታቸውን እና ፊታቸውን በተቆረጡት የጨርቅ ቁርጥራጮች ይሸፍኑ ነበር"።
(ሶሂህ ቡኻሪ  ገጽ፡4758)

☞<<በዚህ አንቀፅ እንዳየነው አላህ አማኞችን ብልቶቻቸውን እንዲጠብቁና ወደርሱ መዳረሻዎቹንም እንዲርቁ
አዟቸዋል። እንዲሁም ጉፍታቸውንም በአንገትጌዎቻቸው እንዲያጣፉ አዟቸዋል። እናም አንገታቸው እና
ትከሻዎቻቸው በመሸፈን ከታዘዙ ፊታቸው መሸፈናቸው ደግሞ ይበልጥ የተገባ ነው ምክንያቱም ፊት ትልቁ የቁንጅና እና የፈተና ቦታ ነውና።

ሰዎች ስለ ሴት ልጅ ቁንጅና ሲጠይቁ የሚጠይቁት ስለፊቷ ነው እንጂ ስለ ሌላ አይደለምና።

እንዲሁም መታየቱ የማይቀረው ልክ ከላይ የምትደርበው ልብስ ይመስል ያሉ ጌጦቿ እንጂ ሌሎች ጌጦቿን በአጠቃላይ እንዳትከፍት ከለከለ >>
(ሪሳለቱ አ–ሂጃብ ኢብኑ ዑሰይሚን።)

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic
ክፍል አምስት ይቀጥላል................

اقرأ (አንብብ )

03 Nov, 12:39


ከአላህ ሌላ በማንም ሊማል አይገባም!
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡

1. “አዋጅ! አሸናፊና የላቀው አላህ በአባቶቻችሁ መማላችሁን ይከለክላችኋል፡፡ የሚምል ሰው በአላህ ይማል፣ ያለበለዚያ ዝም ይበል” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. “ከአላህ ሌላ ባለ የማለ በርግጥም ክዷል ወይም አጋርቷል” (አልባኒ “ኢርዋእ” ላይ “ሶሒሕ” ብለውታል)

3. “በአባቶቻችሁ፤ በእናቶቻችሁና ያለአግባብ ሰዎች ለአላህ ብጤዎች ወይም አቻዎች አድርገው በሚይዟቸው አትማሉ፤ በአላህ እንጂ አትማሉ፤ እውነተኞች ሆናችሁ እንጂ አትማሉ” (አልባኒ “ኢርዋእ” ላይ “ሶሒሕ” ብለውታል።)

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

03 Nov, 09:22


👉አሳታፊ ጥያቄ

ነብዩ ሙሀመድ ﷺ በስንት አመታቸው ወደ አኺራ ሄዱ?

اقرأ (አንብብ )

03 Nov, 05:07


5k member islamic chanal መግዛች የምትፈልጉ አዋሩኝ

@yam7473

اقرأ (አንብብ )

03 Nov, 04:55


ለጭንቀቱም.. ለማጣቱም.. ለመከፋቱም.. ለመደሰቱም.. ለማዘኑም.. ለመሳቁም.. ለማግኘቱም ለሁሉም ነገር አላህ ይመስገን! 🙏

አልሀምዱሊላህ
Semir ami🌜🌘

اقرأ (አንብብ )

03 Nov, 04:55


Daily therapy 218🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:27


ግመል?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:27


ፈረስ?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:27


አይጥ?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:27


ድመት?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:26


አህያ?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:26


ላም?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:25


ፍየል?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:25


ዶሮ?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:25


በግ?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:25


በሬ?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:25


እሺ ዛሬ ስለ ቋንቋችን በደንብ እንወቅ በብሄራችሁ ቋንቋ እነዚህን እንስሳዎች ፃፉ የቋንቋውንም ስም ተናገሩ?

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:22


የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እስኪ ኮመንት ላይ አንድም ፊደል ብትሆን በመፃፍ እና ላይክ በማድረግ ንቁ መሆናችሁን አሳዩን

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 18:01


بِسْمَِّ اللهِ الرحْمَنِ الرحِيم
         
          💢 ሂጃብ ክፍል - 3 💢

         ሂጃብ(መሸፈን)ለመደንገጉ
           የወረዱ የቁርአን አንቀፆች
        
                  ስንመለከት

       የመጀመሪያው ማስረጃ:-

☜ ﴿ياأَيُّهَا النهبِيُّ قُل لَِأزواجِكَ وَبَناَِك وَنِساءِالمُؤمِنينَ يُدنينَ عَلَيهِن مِن جَالبيبِهِن ذلِكَ أَدنى أَن يعرفن فلا يُؤََزينَ وَكانَ اللهُ غَفورا رَحيم ا﴾ ]األحزاب:59

☞ { አንተ ነብይ ሆይ ለሚስቶችህ፣ለሴት ልጆችህ፣ለምእመናን ሴቶችም ከላያቸው ላይ ጅልባባቸውን (መከናነቢያቸውን) እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዲታወቁና በባለጌዎችም እንዳይደፈሩ በጣም የቀረበ ነውና፤ አላህም መሃሪና አዛኝ ነው። (ቁርአን 33:59)

ይህን የቁርኣን አንቀጽ አብዛኞቻችን እናቀዋለን ነገርግን ችግሩ አብዛሀኛው ሰው " مِن جَالبيبِهِن " ይህችን ቦታ ጅልባብ ብለው ይፈስሩታል ይህ ስህተት ነው ታላቁ ሰሀባ ኢብን መስኡድ እና ሌሎችም ሰሀቦች እንዲህ ይፈስሩታል እነዝያ ሰሀቦች ቁርኣንን ከነሱ በላይ የተገነዘበም ሆነ የቀራ የሌለ የሆኑት:-

☞ " ኢብኑ መስዑድ እና ሌሎችም ኩታ ብለው የሚጠሩት፣ ተራው ማህበረሰብ ደግሞ ሽርጥ ብሎ የሚጠራው ፤ ትልቅ የሆነ ሽርጥ ሲሆን እራሷንና ሙሉ ሰውነቷን የሚሸፍን ነው።
☞ አቡ ዑበይድ እና ሌሎች ደግሞ ከላይ ለቃው አንድ አይኗ ሲቀር ሙሉ ሰውነቷን የሚሸፍን ልብስ ነው ብለዋል።
(ኢብኑ ተይሚያ መጅሙዑል ፈታዋ 22/110–111)

☞ ኡሙ ሰለማህ (የመልእክተኛውصلى الله عليه وسلم ባልተቤት) አላህ ስራዋን ይውደድላትና ይህንን አንቀፅ (ከላያቸው ላይ መከናነቢያቸውን ይልቀቁ የሚለው) በወረደ ጊዜ የአንሷር ሴቶች ከላያቸው ቁራ ያረፈባቸው ይመስል ጥቁር በጥቁር ለብሰው ወጡ።
አቡ ዳውድ ዘግበውታል (ሶሂህ አቢ ዳውድ 4101)።

☞ዑበይደተ ሰልማኒ እና ሌሎችም እንዲህ ሲሉ ያወሳሉ :-  አማኝ ሴቶች ከራሳቸው ላይ ጅልባባቸውን ይለቁ ነበር። መንገዱን ለማየት ሲባል አይናቸው ብቻ እስኪታይ ይሸፈኑ ነበር።

የእነዝያ እንቁ ሰሀቦች እጅ እግራቸውን ለዲነል ኢስላም የሰጡት ሙሉ መታዘዝን የታዘዙት በዚህ መልኩ ነበር የተረዱት እኛም ዲነል ኢስላም መያዝ ያለብን ከአላህ ከዛም ከመልክተኛው ከዛም  ከሰሀቦች ነው ።

አንዳንድ ግለሰቦች ምን ይላሉ ሰሀቦች የራሳቸው ግንዛቤ አላቸው እኔም የራሴ ግንዛቤ አለኝ ይህ ስህተት ነው ከላይ እንደገለፅኩት ቁርኣንን ከሰሀቦች በላይ የቀራም ሆነ የተገነዘበ የለም።

አላህ ሱብሀነሁ ወተዕላ እኔም በፃፍኩት እናንተም ባነበባቹት ተጠቃሚዎች ያድርገን።

@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

ክፍል አራት ይቀጥላል.......

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 14:37


ሁሉንም social media አጥፍታቹ አንድ አስቀሩ ብትባሉ የቱን  app ታስቀራላቹ🤔🫣

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 12:34


ምንም ያህል ወንጀልህ ቢበዛ እንኳ ተውበት ማድረግ (ንስሃ መግባት/ ወደአላህ መመለስን) ግን አዘውትር!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿كلُّ بني آدمَ خطّاءٌ، وخيرُ الخطائين التوابونَ﴾

“የአደም ልጅ ሁሉ ተሳሳች ነው። ከተሳሳቾቹ የተሻሉት ተውበት (ንስሃ) የሚያደርጉት ናቸው።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 4515

اقرأ (አንብብ )

02 Nov, 02:42


ነቢያችን عليه الصلاة والسلام እንዲህ ብለዋል

የትም ብትሆን አላህን ፍራ !
በመጥፎዋ (ስራህ ) ላይ መልካሟን አስከትል - (መጥፎዋን ) ታብሳታለችና ።

ሰዎችን በመልካም ባህሪ ተኗኗራቸው

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

27 Oct, 18:01


🌍 የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ 🌍
            ✔️ [ክፍል 10] ✔️

ይህን ስልት ሰዎች ቁርአንን እንዳይሰሙና ትኩረታቸው ወደ እሱ እንዳያደርጉ የሰዎን ህሊና ለመጥመድ የተጠቀሙበት መንገድ ነበር። ነድር ቢን አል-ሐሪስ በአንድ ወቅት ለቁረይሾች እንዲህ አላቸው፡-

“እናንት የቁረይሽ ህዝቦች ሆይ፤ ወላሂ ዘዴው ያልተሰጣችሁ የሆነ ነገር ነው እናንተ ላይ የወረደው። ሙሀመድ እኮ እናንተ ውስጥ የነበረ ያደገ የምትወዱት የነበረ ወጣት ነበር። ከሁላችሁም በላይ በንግግሩ እውነተኛና በአደራ ታማኝ ነበር። ባመጣላችሁን ነገር ሲመጣላችሁ ግን ድግምተኛ አላችሁት በእርግጥ የድግምተኞችን ንፍስታ እና ትብታብ አይተናል፤ ወላሂ! በፍጹም ድግምተኛ አይደለም። ጠንቋይ አላችሁት በእርግጥ የጠንቋዮችን ማስፈራሪያ አይተናል ማጓራታቸውንም ሰምተናል፤ ወላሂ! በፍጹም ጠንቋይ አይደለም። ገጣሚ አላችሁት በአላህ ይሁንብኝ ገጣሚም አይደለም፤ እብድ አላችሁት በእርግጥ እብዶችን አይተናል ከመተናነቁም ሆነ ንግግሩም ከማምታታትና ነገር ከማደበላለቅ የጸዳ ነው እናንተ ቁረይሽ ጎሳዎች ሆይ በሚገባ ወደራሳችሁ ተመልከቱ በእውነቱ ትልቅ ዱብዳ ነው የወረደባችሁ።”
ቀጥሎም ነድር ጉዞውን ወደ ሒይራህ (ኢራቅ) በማድረግ የፋርስን የጥንት ንጉሳን ወሬዎች፣ የሩስቱምንና የአስፈንድሪያን ታሪክ ተምሯል። እናም ረሱል (ሠ.ዐ.ወ) ስለ አላህ ሊያስታውሱና ቅጣቱን ሊያስጠነቅቁ ከሰዎች ጋር ቆይታ አድርገው ሲያጠናቅቁ ነድር ቢን አል ሀሪስ እርሳቸውን በመተካት እንዲህ ይላል፡- “በአላህ እምላለሁ ሙሀመድ ከኔ ይበልጥ ያማረ ወግ የለውም።” ከዚያም ስለ ፋርስ ንጉሳን፣ ስለ ሩስቱምና አስፈንደሪያስ ያወጋቸዋል። እንዲህም ሲል ይጠይቃቸዋል “ታዲያ ሙሀመድ በወግ ከኔ የሚበልጠው እንዴት ሆን ነው?
የኢብኑ አባስ ዘገባ እንደሚያመላክተው ነድር ዘማሪ እንስት ገዝቶ ነበር። አንድ ሰው ለመስለም እንደሚፈልግ በሰማ ጊዜ ወደዚህች ዘፋኝ ይሄድና “አብይው፣ አጠጪው፣ ዝፈኝለት። ሙሀመድ ከሚጋብዝህ ነገር የተሻለ ነውም በይው።” ይላታል። እርሱን በማስመልከት የቁርአን መልእክት ተላልፏል፡-

“ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አልለ። እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው።” (📚ሉቅማን 31፤6)

4. የድርድር ፖለቲካ
┉✽‌»‌🌸»‌✽‌┉

በሲራ ዑለማኦች ዘንድ እንደተዘገበው ዑትባ ኢብኑ ረቢዕ በህዝቦቹ ዘንድ የተከበረ ጥበብና ብልሀት ያለው ሰው ነበር። በቁረይሾች ስብሰባ ላይ “እናንተ ቁረይሽች ሆይ፣ ሙሃመድ ጋር ሄጄ ባናግረውስ? አንዳንድ ነገሮችንም በድርድር አቅርቤለት ከፊሉን ቢቀበለኝና ብቻ የፈለገውን ሰጥተነው ቢተወን?” አላቸው። እነሱም እንዴታ አንተ የወሊድ አባት ሆይ ተነስ ሂድና አናግረው አሉት። 🎤ዑትባም ወደ ረሱል (ሠ.ዐ.ወ) ጋር መጥቶ ቁጭ አለና፡-

“የወንድሜ ልጅ ሆይ እስከማውቀው ድረስ አንተ እኛ ውስጥ በዝምድናም ሆነ በጎሳ ትልቅ ቦታና ክብር ያለህ ሰው ነህ በእርግጥ ወደ ህዝቦችህ ከባድ የሆነን ነገር ይዘህ መጥተሀል በእርሱም ሀብታቸውን በትነሀል፣ አስተሳሰባቸውን ቂላቂል አድርገሀል… አስኪ አንዳንድ ነገሮችን በድርድር አቀርብልሀለሁ ስማኝና አስበህበት ምናልባት ከፊሉን ትቀበለኝ ይሆናል” አላቸው።

ረሡልም (ሠ.ዐ.ወ) ተናገር የወሊድ አባት ሆይ ተናገር እሰማሀለሁ አሉት። “የወንድሜ ልጅ ሆይ በዚህ ይዘኸው በመጣኸው ጉዳይ ገንዘብ ከሆነ የፈለግከው ከኛ የበለጠ ሀብታም እስክትሆን ገንዘብ እንሰበስብልሀለን፣ ክብር ከሆነ የምትፈልገው በማንኛውም ጉዳይ ከአንተ ላንወጣ ከኛ በላይ እንሾምሀለን፣ ንግስናም ከሆነ የምትፈልገው ከላያችን እናነግስሀለን፣ ይህ የሚመጣብህን ራዕይ ስትመለከተው መከላከል የማትችለው ከሆነ ገንዘባችንን አውጥተን ሀኪም እንፈልግልህና ከእርሱ ነጻ እስክትሆን ድረስ ሁሉን እናድርግልሀለን።” ረሡልም (ሠ.ዐ.ወ) “የወሊድ አባት ሆይ ጨረስክ” አሉት “አዎ” አላቸው እንግዲያውስ ስማኝ አሉትና የሚከተሉትን የቁርአን አንቀጾች አነበቡለት፡-

“ሐ.መ.(ሓ ሚም)። (ይህ ቁርኣን) እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው። አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው። ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው። አብሳሪና አስፈራሪ ሲኾን (ተወረደ)። አብዛኛዎቻቸውም ተዉት። እነርሱም አይሰሙም። አሉም ‘ልቦቻችን ከእዚያ ወደእርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው። በጆሮዎቻችንም ላይ ድንቁርና አልለ፤ በእኛና ባንተም መካከል ግርዶሽ አልለ። (በሃይማኖትህ) ሥስራም፤ እኛ ሠሪዎች ነንና።’ (እንዲህ) በላቸው ‘እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ። አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ወደእርሱም ቀጥ በሉ ምሕረትንም ለምኑት ማለት ወደእኔ ይወረድልኛል። ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው።” (📚ፉሲለት 41፤ 1-6)

ከዚያም ረሱል (ሠ.ዐ.ወ) ሲያነቡ ዑትባም እያዳመጠ

“(ከእምነት) እንቢ ‘ቢሉም እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የኾነን መቅሰፍት አስጠነቅቃችኋለሁ’ በላቸው።” (ፉሲለት 41፤ 13) ሲደርሱ አፋቸውን ያዛቸውና ማንበብ እንዲያቆሙ ተማጸናቸው። ይህም የሆነው ከአንቀጹ አስፈራሪነት የተነሳ ነው።

ከዛም ዑትባ ወደ ጓደኞቹ ተመልሶ በተቀመጠ ጊዜ “የወሊድ አባት ሆይ ከምን ደረስክ፣ ምን ነካህ” አሉት። ዑትባም “የነካኝማ.. ሰምቼ የማላውቀውን ንግግር መስማቴ ነው፤ ወላሂ ግጥም አይደለም፤ ድግምትም ጥንቆላም አይደለም፤ ወላሂ ጥፍጥና አለው ሰርጾም ይገባል፤ የሰው ልጅ ንግግርም አይደለም። የበላይ ይሆናል እንጂ የበላይ አይኮንበትም። እናንት ቁረይሾች ሆይ እሽ በሉኝና ይህን ሰዉ ከነ ጉዳዩ ተውት፤ ልቀቁት። ወላሂ የሰማሁት ነገር ትልቅ ይሆናል አረቦች ጉዳት ካደረሱበት (ከገደሉት) ተገላገላችሁት። ከአረቦች የበላይ ከሆነ ንግስናው ንግስናችሁ ነው ክብሩም ክብራችሁ ነው” አላቸው። “ወላሂ የወሊድ አባት ሆይ በምላሱ ደግሞብሀል” አሉት ዑትባም “ይህ የኔ ሀሳብ ነው የፈለጋችሁትን አድርጉ” አላቸው።

ጦበርይ፣ ኢብኑ ከሲር እና ሌሎችም እንደዘገቡት ወሊድ ኢብኑል ሙጊራ፣ አስ ኢብኑ ዋኢል እና ጥቂት ሙሽሪኮች ለረሱል የሚከተለውን የድርድር ሀሳብ አቀረቡ። ከነርሱ በላይ ሀብታም እስኪሆኑ ድረስ ብር ሊሰጧቸው እና ቆንጆ ድንግል ሴት ሊያጋቧቸው በምላሹ አማልክቶቻቸውን መስደብና ባህሎቻቸውን ማቄል እንዲተው ጠየቁ። ረሡል (ሠ.ዐ.ወ) የተላኩበትን ወደ ሀቅ ደዕዋ ማድረግ እንጂ አሻፈረኝ አሉ በዚህን ጊዜ “እኛ አምላክህን አንድ ቀን እንገዛውና ሌላ ቀን የኛን አማልክት ተገዛ አሏቸው” ይህንንም አሻፈረኝ አሉ። አላህም የሚከተለውን ቃል አወረደ፡-

“በላቸው ‘እናንተ ከሓዲዎች ሆይ! ‘ያንን የምትግገዙትን (ጣዖት አሁን) አልግገዛም። እናንተም እኔ የምግገዛውን (አምላክም አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም። እኔም ያንን የተገዛችሁትን (ወደፊት) ተገዢ አይደለሁም። እናንተም እኔ የምግገዛውን (ወደፊት) ተገዢዎች አይደላችሁም። ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ። ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ።’” (📚አል-ካፊሩን)


@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

27 Oct, 10:04


ከጠቢባን አንደበት


🔜    «  የአንተ መስተካከያና መታነጫ ዛሬ እንጅ ነገማ የፍፃሜህ ዕለት ሊሆን ይችላል ። »

🔜   « ራስህን ድል ሳታደርግ በሌላው ላይ አትዝመት ።»

🔜   « መታገስ ለራስ ጊዜ መስጠት ነው ። »

 
🔜    « ንደት ለችግሮች መፍትሔ ሳይሆን መንስኤ ነው ። »

🔜   « የውሸት እየኖርን የእውነት እንሞታለን ። »

🔜   « ደስታ ዱርዬ አይደለም ፤  ሰዎች ግን  ዱርዬ እየመሰላቸው በየ መጠጥ ቤቱ ይፈልጉታል ። »

🔜  « ጠላቶችህን ባትወዳቸው እንኳን አድንቃቸው ፤ ስህተትህን ለመመልከት የመጀመሪያዎቹ ናቸውና ። »

🔜   «  ጠላቶችህ ወደ አንተ ቢገሰግሱ ወደ ኋላ አታፈግፍግ  ወደነሱም አትንደርደር ባለህበት ሆነህ ተዘጋጅና ጠብቃቸው ። »

🔜   «  ብዙ ሰዎች  ከአድማስ ማዶ የማይታያቸውን ቀን ይናፍቃሉ ። ዛሬን የሚንቋት በእጃቸው ስለገባች ነው ። »

🔜   « ዘልዓለም  ለመኖር ዕድሉ ለሌላት ህይወትህ ሰላምን  አትንፈጋት  ። »

🔜    « ለሌሎች ይቅርታ የማያደርግ እራሱ የሚሸጋገርበትን ድልድይ የሚያፈርስ ነው ። »

🔜    « ቁጠኛ ጓደኛ  የተረጋጋ ጠላት ነው ። »

🔜   « የቁጣ መድሀኒት ዝምታ ነው ። »

🔜    « ከመዝለልህ በፊት አስተውል ። »

🔜   « ገንዘብ መናገር ሲጀምር  እውነት ዝም ትላለች  ። »

🔜    « ትዕግስት  ማለት ችግርህን ለአሏህ መንገር ማለት ነው ። »

🔜    « እምነት ማለት ግማሹ ትዕግስት ሲሆን ግማሹ ምስጋና ነው ። »

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

27 Oct, 02:56


መብረቅ በርቶ ከጠፋ በኋላ ምን ይፈይዳል? መብረቅ በበራበት ሰዓት ላይ ትኩረትን ቢስብም ካለፈ በኋላ ሁሉም ትኩረት ወደአሁን ይመለሳል ። አዎ በመብረቁ መገረምም ሆነ መደነቅ ውስጥ አሁን አይባክንም !

አዎን ትላንት መብረቅ ነው !

ነገ በዳመና ውስጥ እንደታዘለ የዝናብ ጠብታ ነው ....ወይ ይዘንባል ወይ አይዘንብም ። እኛ ያለነው አሁን ላይ ነውና ስለአሁን እናተኩር ።
[ባለዕዳው]

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

27 Oct, 02:55


Daily therapy 210🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Oct, 18:00


🌍 የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ 🌍
•════•••🌺•••════•

           ✔️ [ክፍል 9⃣] ✔️

🕋ጥሪውን ለማኮላሸት ጥቅም ላይ የዋሉ ልዩ ልዩ ስልቶች🌴
••┈┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈┈••

ቁረይሾች ሙሀመድን (ሠ.ዐ.ወ) ማስዋሸታቸው እና ችላ ማለታቸው ከዳዕዋው እንደማይነቀንቀው ሲያዩ በድጋሚ ቆም ብለው ማሰብ ጀምሩ፤ ይህንን ደዕዋ ለማቆምና ለማኮላሸት የሚረዱ ዘዴዎችንም መረጡ። ይህም እንደሚከተለው ይቀርባል።

1. ማፌዝ፣ ማናናቅ፣ ማላገጥና ማስተባበል
┄┄┉┉✽‌»‌🌺»‌✽‌┉┉┄┄

የዚህ ስልት ጠቀሜታ ሙስሊሞችን ማዋረድና ውስጣዊ ጥንካሬያቸውን ማዳከም ነበር። ነብያችንንም (ሠ.ዐ.ወ) የዘቀጡ ቅጥፈቶችን እና የቂል ስድቦችን ሰደቧቸው። እብድ ብለውም ይጠሯቸው ነበር።

وَقَالُوا يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ
“‘አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ’ አሉም።” (📚አል-ሂጅር 15፤ 6)

ደጋሚና ቀጣፊ ይሏቸው ጀመር፡-

وَعَجِبُوا أَن جَاءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ وَقَالَ الْكَافِرُونَ هَٰذَا سَاحِرٌ كَذَّابٌ
“ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ። ከሓዲዎቹም ‘ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነው’ አሉ።” (📚አሷድ 38፤ 4)

በጥላቻ እይታና ስሜት ይሸኟቸዋል፤ ይቀበሏቸዋል።

وَإِن يَكَادُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَيُزْلِقُونَكَ بِأَبْصَارِهِمْ لَمَّا سَمِعُوا الذِّكْرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُ لَمَجْنُونٌ
“እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ። ‘እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነው’ ይላሉ።” (📚አል-ቀለም 68፤ 51)

ነቢዩ በደካማ ባልንጀሮቻቸው ተከበው በሚቀመጡ ጊዜ አቀማማጮቹ እነዚህ ናቸው እያሉ ያፌዙባቸው እንደነበር ቁርአን ሲገልፅ

وَكَذَٰلِكَ فَتَنَّا بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لِّيَقُولُوا أَهَٰؤُلَاءِ مَنَّ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّن بَيْنِنَا

“እንደዚሁም ‘ከመካከላችን አላህ የለገሰላቸው እነዚህ ናቸውን?’ ይሉ ዘንድ ከፊላቸውን በከፊሉ ሞከርን።” (📚አል-አንዐም 6፤ 53)

አላህ እንዲህ በማለት ይመልሳል

أَلَيْسَ اللَّهُ بِأَعْلَمَ بِالشَّاكِرِينَ
“አላህ አመስጋኞቹን ዐዋቂ አይደለምን?” (📚አል-አንዐም 6፤ 53)

ሁኔታቸውን አላህ እንዲህ ሲል ተርኮልናል


إِنَّ الَّذِينَ أَجْرَمُوا كَانُوا مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا يَضْحَكُونَ ﴿٢٩﴾ وَإِذَا مَرُّوا بِهِمْ يَتَغَامَزُونَ ﴿٣٠﴾ وَإِذَا انقَلَبُوا إِلَىٰ أَهْلِهِمُ انقَلَبُوا فَكِهِينَ ﴿٣١﴾ وَإِذَا رَأَوْهُمْ قَالُوا إِنَّ هَٰؤُلَاءِ لَضَالُّونَ ﴿٣٢﴾ وَمَا أُرْسِلُوا عَلَيْهِمْ حَافِظِينَ
“እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ። በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር። ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር። ባዩዋቸውም ጊዜ ‘እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው’ ይሉ ነበር። በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ።” (📚አል-ሙጠፊፊን 83፤ 29-33)

2. አስተምህሯቸውን ጥላሸት መቀባት፣ ብዥታዎችን መፍጠር
┄┄┉┉✽‌»‌🌺»‌✽‌┉┉┄┄

በመልእክተኛውና በስብእናቸው ዙሪያ የሀሰት ወሬዎችን መንዛት፣ ጥርጣሬን ማንገስ ተራው ሰው ቆም ብሎ ለማሰብና ለማስተንተን ፋታ በማያገኝበት አኳኋን የሀሰት ዘመቻውን በስፋትና በብዛት ማሰራጨት። ቁርአንን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡-

وَقَالُوا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ اكْتَتَبَهَا فَهِيَ تُمْلَىٰ عَلَيْهِ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
“አሉም ‘የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት። አስጻፋት። እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች።’” (📚አል-ፉርቃን 25፤ 5)

وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَٰذَا إِلَّا إِفْكٌ افْتَرَاهُ وَأَعَانَهُ عَلَيْهِ قَوْمٌ آخَرُونَ فَقَدْ جَاءُوا ظُلْمًا وَزُورًا
“እነዚያም የካዱት ይህ (ቁርኣን ሙሐመድ) የቀጠፈው በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ። በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ።” (📚አል- ፉርቃን 25፤ 4)

وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّهُمْ يَقُولُونَ إِنَّمَا يُعَلِّمُهُ بَشَرٌ
“እነርሱም ‘እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው’ ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን።” (📚ነህል 16፤ 103) ይሉ ነበር።

🎤መልእክተኛውን (ሠ.ዐ.ወ) አስመልክቶ

وَقَالُوا مَالِ هَٰذَا الرَّسُولِ يَأْكُلُ الطَّعَامَ وَيَمْشِي فِي الْأَسْوَاقِ لَوْلَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكٌ فَيَكُونَ مَعَهُ نَذِيرًا
“ለዚህም መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን ምን (መልክተኛነት) አለው? ከርሱ ጋር አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ወደርሱ መልአክ (ገሃድ) አይወረድም ኖሯልን? አሉ።”
(📚ፉርቃን 25፤ 7) ይሉ ነበር።

ለነዚህና መሰል እብለቶቻቸው የተሰጡ ምላሾችን ቁርአን ውስጥ በብዛት እናገኛለን።

#ኢንሻ_አላህ_ክፍል_አስር
                  
#ይ...#ቀ...#ጥ...#ላ..#ል.....

ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ  ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። 👇
@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Oct, 12:36


ሚስቶች ግን😅
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Oct, 12:35


ጥፋተኛው እኔ!
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Oct, 09:28


:
🌷ከምርጥ  አንደበት🌷

👉"የሰው ልጆች እንደማበጠሪያ እኩል ናቸው።"
💚(ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)

👉"ከትግሎች ሁሉ በላጩ የራስን እኩይ ፍላጎት መታገል ነው፣"
  (ዐሊ ኢብን አቡጧሊብ)

👉"ለራሱ ያለውን መብት ያክል አንተ እንዳለህ ከማያስብ ሰው ጋር መወዳጀት መልካም አይደለም።"
💚(ነቢዩሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ))

👉"አላህን ፍራ።ሌላ ማንንም የምትፈራበት ምክንያት የለህምና።"
(ዐሊ ኢብን አቡ ጧሊብ)

👉"ታላቅ ምንዳ ከታላቅ ፈተና ጋር ነው።"
💚(ነቢዩሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ))

👉"ታጋሽ ሁን! ትዕግስት የእምነት መሠረት ነውና።"
(ዑመር ኢብኑል ኸጣብ)

👉"አዕምሮ ሲበስል ምላስ ወሬ ይቀንሳል።"
(ዐሊ ኢብን አቡጧሊብ)

👉"ለሰዎች መልካም ሁን! አላህ ዘንድ ተወዳጅ ትሆናለህ።"
(አቡበክር ስዲቅ)
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

26 Oct, 02:42


ብዙ ጊዜ ሰናጠፋ ይቅር የሚሉን ወዳጆቻችን አንዳንዴ በትንሽ ጥፋት ይለዩናል። ይህኔ በትንሹ ጥፋታችን ሰበብ ፈልገው ተለዩን እንላለን። ግን ከትንሽ ጥፋታችን በፊት በሰራናቸው ብዙ ትላልቅ ጥፋቶች በኛ ላይ ያላቸው ተስፈ ተዳክሞ መሆኑን ስለ ማናቅ ነው።

اتمنا لكم يومن سعد

اقرأ (አንብብ )

26 Oct, 02:39


Daily therapy 209🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Oct, 18:01


🌍 የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ 🌍
•════•••🌺•••════•

           ✔️ [ክፍል 8] ✔️

🕋ሚስጥራዊው የዳእዋ ሂደት🌴
••┈┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈┈••

ነብያችን (ሠለላሁ .ዐለይሂ .ወሰለም ) ለአላህ ትእዛዝ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ጀምረዋል፤ አላህን አንድ ብቻ አድርጎ ማምለክና ጣኦታትን ወደ መተው መጣራትን ተያያዙት። ነገር ግን ቁረይሾች ለጣኦቶቻቸው እና ለሽርክ አምልኮቶቻቸው ካላቸው ጭፍን ታማኝነትና ወገንተኝነት አንጻር ጥሪው ድንገተኛ እናዳይሆንባቸው በመስጋት ዳዕዋውን በሚስጥር ያካሂዱ ነበር። በቁረይሾች መቀማመጫ አደባባዮች በግልፅ ዳዕዋ አያደርጉምም ነበር። በጣም የሚቀርባቸው ዘመድ ወይም ከዚህ በፊት ለሚያውቁት ሰው ካልሆነ በስተቀር ጥሪያቸውን አያደርጉለትም ነበር።

🔺የመጀመሪያዎቹ መጀመሪያዎች
┄┄┉┉✽‌»‌🌺»‌✽‌┉┉┄┄

መጀመሪያ ወደ ኢስላም ከገቡት ውስጥ፤ ኸዲጃ (ረ.ዓ)፣ ዐሊይ ኢብኑ አቡጧሊብ የነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) ያሳደጉትና ኻዲማቸው (አገልጋይ) የነበረው ዘይድ ኢበኑ ሐሪሳ፣ አቡበክር ኢብኑ አቢቁሀፋ፣ እና አቡበክር ሲዲቅ ወደ ኢስላም የጠሯቸው ዑስማን ኢብኑ ዐፋን፣ ዙበይር ኢብኑል ዐዋም፣ ዐብድረህማን ኢብኑ ዐውፍ፣ ሰእድ ኢብኑ አቢወቃስ … እንዲሁም ሌሎችም ይጠቀሱ ነበር።

▪️የተርቢያ ስብስብ በአርቀም ቤት
•✿❒❀❒✿•••🌼•••✿❒❀❒✿•

እነዚህ ሰሀቦች ከነብያችን ጋ በሚስጢር ይገናኙ ነበር። አንድኛቸው መስገድ አልያም ኢባዳ ማድረግ ሲፈልግ ከቁረይሾች እይታ ለመደበቅ መካ ውስጥ ከሚገኙ ገደላ ገደሎች ወደ አንዱ ይሄዱ ነበር። ወደ ኢስላም የሚገቡት ወንድና ሴቶች ቁጥር ከሰላሳ መብለጡን የተመለከቱት ነቢይ ከእነርሱ መካከል የአርቀም ኢብኑ አቢ አርቀምን ቤት በመምረጥ እዚያ እየተገናኙ የዳእዋውን ጉዳይ ያስተምሯቸውና ተርቢያን ይሰጧቸው ገቡ። በዚህን ወቅት ዳዕዋው ደርሷቸው ወደ ኢስላም የገቡ ሰዎች ቁጥር አርባ አካባቢ ይደርስ ነበር። ታዲያ አብዛኞቹ ድሆችና ባሪያዎች በቁረይሽም ዘንድ ቦታ የማይሰጣቸው ግልሰቦች ነበሩ።

የዳእዋው ድብቅነት ለዳዕዋው ችግርን ከመስጋት እንጂ ለነፍስ ከመፍራት የመነጨ አልነበረም። ነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) በመጀመሪያዎቹ ሶስት አመታት የድብቅ ዳዕዋን የመረጡበት ምክንያት ለነፍስ ጉዳትን ከመስጋት የመነጨ አልነበረም። ዳእዋውን ከጅምሩ ለሁሉም አይነት ሰዎች ግልጽ እንዲያደርጉት ከጌታቸው ትእዛዝ ቢመጣ ኖሮ ከፊታቸው ሞት ቢጠብቃቸው እንኳን ለመፈጸም ምንም ሰዓት አያባክኑም ነበር።

ነገር ግን የመጀመሪዎቹን የዳዕዋ ግዜያት ዳዕዋውን በድብቅና በሚስጥር ያምኑልኛል እንዲሁም ዳዕዋውን ይቀበሉኛል ብለው ለጠረጠሯቸው ሰዎች ብቻ እንዲያደርጉ አላህ አሳወቃቸው። ይህም የሆነው በአላህ ላይ የሚኖረን መሰረታዊ ኢማን እንዳይበረዝና ቀጥሎ የሚመጡ ዳዒዎች በአላህ ላይ ብቻ መተማመን እና መታገዝ ላይ እንዲያተኩሩ ትምህርት እዲሆን ነው።

ከዚህ በመነሳት በየትኛውም ዘመን የሚኖሩ የኢስላማዊ ዳዕዋ ባለቤቶች ዳእዋቸውን የሚያደርጉበትን ስልት (በሚስጢር ወይስ በግልፅ የሚለውን) ካሉበት ዘመን ሁኔታና ተጨባጭ አንፃር መወሰን ይችላሉ ማለት ነው። ይህ የኢስላም ሸሪዐ ገር ከመሆኑ አንፃር የተቀመጠ ሲሆን ስልቱ የነብያችን (ሠለላሁ .ዐለይሂ .ወሰለም ) ሲራ ላይ የተመረኮዘ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን አራት ሂደቶችን መሰረት ያደረገ በዋነኝነት የሙስሊሞችና የዳእዋውን መስላሀ (ጥቅም) ከግምት ያስገባ መሆኑ ነው።

ለዚህም ነው አብዛኛዎቹ የፊቅህ ምሁራን፤ ሙስሊሞች በቁጥር ሲያንሱ ወይም በዝግጅት ደካማ ሲሆኑ፣ ጠላቶቻቸው ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ መፍጠር ሳይችሉ እንሸነፋለን ወይም ጠላቶቻችን ይጎዱናል ብለው ከጠረጠሩ ነፍስን የመጠበቅ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ የተስማሙት። ምክንያቱም ዲንን ጠብቆ ለማቆየት በየትኛውም መልኩ ህይወትን ጠብቆ ማቆየት የግድ ይለናልና።

እውነታው ላይ ላዩን ስንመለከተው ለነፍስ ቅድሚያ መስጠት ይመስላል። ነገር ግን ጉዳዩን በጥልቀት ከተመለከትነው በተጨባጭ ዲንን ጠብቆ ማቆየት ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህ እይነት የሙስሊሞችን ነፍስ በሰላም ጠብቆ ማቆየት፤ ወደፊት እንዲጓዙና ሌሎች ክፍት የሆኑ ሜዳዎች (የዳእዋ ዘርፍና ስልቶች) በተገኙ ጊዜ ትግል እንዲያደርጉ እድል ስለሚሰጣቸው ለዲኑ ቅድሚያ ተሰጥቷል እንላለን። ይህ ሳይሆን ቢቀርና ሙስሊሞች ቢጠፉ በዲኑ ላይ የመጣ ጉዳት ተደርጎ ይወሰዳል።

ደካሞችና ድሃዎች ቀድመው ለምን ተቀበሉ?
┄┄┉┉✽‌»‌🌺»‌✽‌┉┉┄┄

የሲራ ድርሳናት እንደሚገልፁልን በመጀመሪያዎቹ የዳእዋ ወቅቶች ወደ ኢስላም የገቡት ሰዎች በአብዛኛው ድሆች ደካሞችና ባሪያዎች የተቀላቀሉበት ነበር። ታዲያ ከዚህ ጀርባ ያለው ጥበብ ምንድን ነው? ኢስላማዊ መንግስቱስ ሲመሰረት በነዚህ ሰዎች መሰረት ላይ የመገንባቱ ሚስጥርስ ምንድንነው?

🎤 መልሱ፡- ይህ የነቢያት ዳዕዋ የመጀመሪያው ሂደት የሚያሰተናግደው ተፈጥሮኣዊ ክስተት ነው። ሚስጥሩም፤ አላህ ሁሉንም መልእክተኞች ሲልካቸው ከሰው ልጅ አገዛዝና የስልጣን ተፅእኖ ወደ አላህ ብቸኛ አስተዳደርና ስልጣን ነፃ ያወጡ ዘንድ ነው። ራሳቸውን አማልክትና ፈላጭ ቆራጭ አድርገው የበላይ ነን የሚሉትን አምባገነኖች ምንነት የሚያዋርድና የሚያንኮታኩት ጥሪ ነው።

ይህም ከደካሞች፣ ከተዋረዱ እና ከባሪያዎች ሁኔታ ጋር ስለሚገጣጠም ለጥሪው አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ በአፀፋው እነዚያ አምለክ ነን አስተዳዳሪ ነን ባዮች ከመኩራራትና ከጥላቻ በዘለለ ለኢስላማዊው ጥሪ መሰናክል ሆነው ይቆማሉ።

ይህ እውነታ የበለጠ ግልፅ እንዲሆንልህ በፋርሱ ጦር መሪ ሩስቱም እና በሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ ጦር ተራ ወታደር ረቢዕ ኢብን ዓምር መካከል በቃዲሲያ ጦርነት ወቅት የተካሄደውን ንግግር ተመልከት። ሩስቱም እንዲህ አለው “ምንድን ነው እኛን እንድትዋጉን እና ሀገራችንን ዘልቃችሁ እንደትመጡ ያደረጋችሁ?” ረቢዕ ኢብኑ አሚርም “እኛ የመጣነው በፍላጎት ሰዎችን ከሰዎች ባርነት ወደ አላህን ብቻ ወደ ማምለክ ነፃነት ለማምጣት ነው” አለው፤ ከዚያም ከቀኝ እና ከግራ ለሩስቱም ሩኩዕ ያደረጉ ሰዎችን ሰልፋ ተመለከተና በመገረም “በእርግጥ ከዚህ በፊት ስለናንተ ህልሞች ይደርሱን ነበር፤ አሁን በተጨባጭ ሳያችሁ ግን ከናንተ በታች ቂል የሆነን ህዝብ አልተመለከትኩም። እኛ ሙስሊሞች እኮ ከፊላችን ከፊሉን ባሪያ አደርጎ እኮ አይገዛውም! እናንተም እንደኛ በመካከላችሁ በመልካም እንደምትውሉ ነበር የማስበው ምናልባትም በጣም ጥሩ ከሰራችሁት ነገር አንዳችሁ የአንዳችሁ ጌታ (አምላክ) እንደሆናችሁ እየነገራችሁኝ መሆኑ ሊሆን ይችላል ……”

ይህኔ ደካሞቹ እርስበርሳቸው መጠቃቀስና ማጉረምረም ጀመሩ “ወላሂ ይህ አረብ እውነት ተናገረ” ነገር ግን መሪዎቹ እና አስተዳዳሪዎቹ የረቢዕን ንግግር ውስጣዊ ማንነታቸውን ያፈራረሰ መብረቅ ሆነባቸው። እርስበርስም “በእርግጥ ረቢዕ የወረወረው ንግግር ባሮቻችንን ወደ እርሱ ሳይጎትታቸው (ሳያዘናብላቸው) የሚቀር አይደለም” አሉ::

#ኢንሻ_አላህ_ክፍል_ዘጠኝ
                  
#ይ...#ቀ...#ጥ...#ላ..#ል.....

ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ  ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። 👇
@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Oct, 11:07


ጁምዐን በጀመዐ ሰግደን ንዳድ በሆነው የጁምዐ ፀሀይ ተጠብጥበን ገብተን እርፍ ቅዝቅዝ የምንልበት ቤት የሰጠን አላህ ምስጋና የተገባው ይሁን

اقرأ (አንብብ )

25 Oct, 03:36


ጁምዐ ነው ሰሉ አለ ነቢዩና ሙሀመድ🥰
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

اقرأ (አንብብ )

25 Oct, 03:33


እንደከማቹ...እንደተሰበራቹ...በጭንቀት ውስጥ እንሆናቹ...እንደታመማቹ...የሚያበረታ አካል እንደፈለጋቹ ...መጠንከር እና በራስ መቆም እንደፈለጋቹ አላህ ያውቃል ! ይህን ሁሉ የሚያውቅ ጌታ አላቹ ...ስለናንተ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ አላቹ ። እናንተ ማወቅ ያለባቹህ አላህ እንዳላቹህ ነው ። አዎ አላህ አለላቹ❤️

ጁምዐ
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

25 Oct, 03:27


Daily therapy 208🤍

@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Oct, 20:02


√ ሰላት

የዱንያ እና የአኼራ ጥቅሞችን ለማግኘት፤ የሁለቱ ሀገር አደጋዎች በመከላከል ላይ ትልቅ አጋዥ ነው።

«ኢብኑል ቀዪም/ "ዛዱል ሚዓድ" «4/209»
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

اقرأ (አንብብ )

24 Oct, 18:38


እናትህ ካንተምትጠላው ነገር ቢኖር አሁን በእጅህ የያዝከውን ነገር ነው 😁

اقرأ (አንብብ )

24 Oct, 18:08


ምን ሆናችሁ ነው ከቻናሉ የምትወጡት በዚህ ወር ብቻ 200 ሰው ወጥቷል

اقرأ (አንብብ )

24 Oct, 18:01


🌍 የታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ 🌍
•════•••🌺•••════•

           ✔️ [ክፍል 6] ✔️

🕋የነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) በሂራዕ ዋሻ መገለል /ኸልዋ/ 🌴
••┈┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈┈••

የነብያችን (ሠለላሁ ዐለይሂ ወደለም ) እድሜያቸው ወደ 40 እየተቃረበ ሲመጣ፤ ከወትሮው በተለየ ከሠው መነጠልን በተለያዩ ጊዜያት እየወደዱት መጥተዋል። አላህም ለመገለያው ቦታ የሂራዕ ዋሻን እንዲወዱት አድርጓቸዋል። ሂራዕ ማለት ከመካ በሰሜን ምዕራብ የሚገኝ ተራራ ሲሆን ነቢያችንም ዋሻው ውስጥ ለብዙ ሌሊቶች አንዳንዴም አስር ሌላ ጊዜም ከዘያ ለሚዘልቁ ቀናት አላህን በመገዛት ያሳልፉ ነበር።

ወደ ቤታቸው ሲመለሱም ብዙም ሳይቆዩ ለሚቀጥለው ኸልዋ በአዲስ ስንቅ ይቋጥሩ ነበር። በእነዚህ ኸልዋዎች (ብቸኝነት) በአንደኛው ላይ ወህይ እስከመጣላቸው ድረስ በዚህ ሁኔታ አሳልፈዋል።

ኸልዋ ማለት /አላህን ለመገዛት ብቸኝነትን በመምረጥ መገልል/
┄┄┉┉✽‌»‌🌺»‌✽‌┉┉┄┄

ያኔ የነብያችን ቀልብ እንዲህ በፍቅር የገዛው ኸልዋ፤ ለአጠቃላይ ሙስሊሞች በተለይ ደግሞ ወደ ኢስላም ለሚጣሩ ዳዒዎች እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ያለበት ነው። ከዚህም ውስጥ፡-

▪️1. በቀልብ ውስጥ የአላህን ሙሀባ /ውዴታ/ ማሳደግ

አእምሮን ብቻ በእውቀት ማጥገብ በቂ አይደለም። ይህማ ቢሆን ኖሮ ኦረይንታሊስቶች /ሙስሊም ያልሆኑ ኢሰላምንና ሌሎች የምስራቅ ሀይማኖትን የሚያጠኑ/ ከሙስሊሞች የበለጠ አሏህና የነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ .ወሰለም) ወዳጅ ይሆኑ ነበር። ለመሆኑ ከምሁሮች አንድም እራሱን አሳልፎ ለአንድ ሂሳባዊ የስሌት ህግ አለያም አልጀብራ ጥያቄ መስዋእትነት የሠጠ ሰምተሀልን?…

ይልቁንም በአላህ ከማመን በኋላ ወደ እሱ ውዴታ መዳረሻ መንገዶች በዋነኝነት፡-

የታላቅነቱ ማረጋገጫ የሆኑ ምልክቶችን፤ ውለታውና ፀጋዎቹን በሠፊው ማስተንተን
በምላስና በቀልብ በብዛት እሱን ማውሳት
ፈርድ የሆኑ ነገሮች በጥንቃቄ ተጠባብቆ መስራት ሡና /ነዋፊል/ የሆኑትንም ማባዛት
ይህ ሁሉ ሊገራ የሚችለው በተደጋጋሚ ከአላህ ጋር ብቸኝነትን /ኸልዋ/ በማዘውተር ነው።

▪️2. ነፍስን መተሣሠብና በሽታዎቿን ማከም

የሰው ልጅ ነፍስ የብዙ በሽታዎች መናኸሪያ ናት። ታዲያ ከነዚህ በሽታዎች መካከል ከሰዎች ተነጥሎ ነፍስን በመተሳሰብና ያለፈቻቸውን ድንበሮች እያሰታወሱ ጉድለቶቹዋን በማሰተዋል እንጂ የማይታከሙ አሉ። ብቻውን ሆኖ ሲያስተነትን ግን የሰው ልጅ የነፍስያ እውነታ ይገለጽለታል። ምን ያህል ነፍስ አላህን ፈላጊና ደሀ እንደሆነችና በእያንዳንዷ ቅጽበት የእሱን (አላህ) እርዳታ ፈላጊ መሆኗ፤ ሠዎች እሱን ለመጥቀምም ሆነ ለመጉዳት የማይችሉ ደካሞች መሆናቸውን ይደርስበታል። ስለሆነም ሙገሳቸውም ሆነ ወቀሳቸው ውጤት አልባ እንደሆነ ይገለጥለታል፤ ይህና ሌሎችም መሠል እውነታዎች ፍንትው ብለው ሲታዩት ስራውን ለአላህ ብቻ አጥርቶ ይሰራል፤ ይተናነሳል… በተደጋጋሚ መገልልን /ኸልዋን/ በማብዛቱ የተነሳ ባገኘው ብርሃን የነፍስን እውነታ ሲረዳ አብሮ የነፍስ ጣጣ /መዘዞች/ አብረው ይገረሰሳሉ /ይወገዳሉ/።

            ተግባራዊ ልምምድ፡-
┄┉┉▪️✽‌»‌🌼»‌✽ ▪️┉┉┄┄

ይህ ሁሉ የሚሆነው ከዱንያ ጭንቅንቅ፣ ከጩኅቷ፣ ከከንቱ ብለጭልጯ በቀን፣ በለሊት፤ በወራትና፤ በዓመታት ለተወሰኑ ግን ተደጋጋሚ ለሆኑ ወቅቶች ገለል ብሎ ራስን መመልከት ሲቻል ነው። ለዚሁም ለምሳሌ

🔺እዕቲካፍ በረመዷን የመጨረሻው አስር ቀናት ወይም አንዲት ምሽት ከሁሉም ወራት በመስጂድ ውስጥ ማሳለፍ
🔺 በሁሉም ሌሊቱ የመጨረሻው 1/3ኛ ክፍል ላይ የማገባደጃ ጥቂት የኢስቲግፋር ወቅት
🔺በጠዋት እና በማታ ውዳሴ /አዝካር/ ወቅት
🔺ከመኝታ በፊት ነፍስን በመተሳሰቢያና የመኝታ ዚክር በሚደረግበት ወቅት
🔺መስጂድ ቀደም ብሎ ለሰላት መግባትና ሰላትን ቁጭ ብለው እየተጠባበቁ
🔺ከሰላት በኋላ ቁጭ ብሎ ዱዓ በማድረግ ወቅት ላይ
🔺 ሌላው ቢቀር አዛን እየሰማ ከሙአዚኑ ተከትሎ ካለ በኋላም ሊሆን ይችላል።

ከላይ የተጠቀሱት ጊዜያት ሁሉም ቀልብ ከዱንያ ጋ ያለውን መገናኛ በመቁረጥ ትኩረቱን ትልቅና አሸናፊ ወደ ሆነው አላህ በአዲስ መልክ የሚያቆራኝበት ነው።

       🔺 የወህይ መጀመር
┈┈•••✿❒❀❒✿•••┈┈

ኢማሙል ቡኻሪ እንደዘገቡት እናታችን ዐዒሻ /ረ.ዐ./ የወህይ አጀማመር እንዴት እንደነበር ስትገልፅ እንዲህ ትላለች።

أول ما بدء به رسول الله  الرؤيا الصالحة في النوم، فكان لا يرى رؤيا إلا جاءت مثل فلق الصبح، ثم حبب إليه الخلاء وكان يخلو بغار حراء فيتحنث فيه الليالي ذوات العدد قبل أن ينزع إلى أهله ويتزود لذلك ثم يرجع إلى خديجة فيتزود لمثلها، حتى جاءه الحق وهو في غار حراء . فجاءه الملك فقال له اقرأ : فقال ما أنا بقارئ قال فأخذني فغطني حتى بلغ منى الجهد ثم أرسلني فقال: اقرأ : فقلت ما أنا بقارئ، فأخذني وغطني حتى بلغ منى الجهد فقال اقرأ: فقلت : ما أنا بقارئ فأخذني وغطني الثالثة ثم أرسلني فقال : اقْرأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ . خَلَقَ الإنسَانَ مِنْ عَلَقٍ . اقْرَأْ ورَبُّكَ الأَكْرَمُ . الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ . عَلَّمَ الإنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ.

“መጀመሪያ ጥሩ ጥሩ ህልሞች በእንቅልፋቸው ያዩ ነበር ታዲያ ያዩዋቸው ህልሞች ልክ እንደ ንጋት ጎህ በእውን ይከሰቱ ነበር። ከዚያ በኋላ በሂራ ዋሻ ዉስጥ መገለልን ወደዱ በዚህም ዋሻ ዉስጥ ብቻቸውን ለዚህ የሚሆን ስንቅን ለመሰነቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሳይመለሱ ብዙ ሌሊቶችን ያሳልፉ ጀመር። ከዚያም ወደ ኸዲጃ (ረ.ዐ) ይመለሱና ስንቅ ይሰንቃሉ በእንዲህ አይነት ሁኔታ በሂራ ዋሻ ዉስጥ ከጌታቸው የሆነው ሃቅ እስከመጣላቸው ድረስ ቀጠለው ነበር።

መላኢካው መጥቶ ‘አንብብ’ አላቸው ‘እኔ አንባቢ አይደለሁም’ በማለት መለሱ፤ ይዞኝ ነፍሴ እስክትወጣ ድረስ ጭምቅ አደረገኝና ለቀቀኝ። እንደገና ‘አንብብ’ አለኝ ‘እኔ አንባቢ አይደለሁም’ ስል መለሰስኩኝ። ይዞኝ በድጋሚ ነፍሴ እስክትወጣ ድረስ ጭምቅ አድርጎኝ ለቀቀኝና ‘አንብብ’ አለኝ እኔም ‘አንባቢ አይደለሁም’ አልኩት። ለሶስተኛ ጊዜ ነፍሴ ልትወጣ እስክትደርስ ጨምቆ ለቀቀኝና እንዲህ በማለት ተናገረኝ ‘አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። አንብብ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን።’”


#ኢንሻ_አላህ_ክፍል_ሰባት
                  
#ይ...#ቀ...#ጥ...#ላ..#ል.....

ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ  ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። 👇
#Share ይቀላቀሉ ↘️
@anbeb_islamic
@anbeb_islamic

اقرأ (አንብብ )

24 Oct, 17:27


ከ 11794 ወደ 11599 ያሳዝናል😕