Ethiopian Digital Library @ethiopian_digital_library Channel on Telegram

Ethiopian Digital Library

@ethiopian_digital_library


በዚህ ቻናል ስለ
👉ትምህርት፣
👉ሥራ እና
👉ማህበራዊ ጉዳይ
መረጃ ያገኛሉ!

For advertisement: @ethiodlbot

Ethiopian Digital Library (Amharic)

ኢትዮጵያዊ ዲግታማችን ቢሆኑ፣ ማንኛውም በእኛ ላይ ትምህርት ያለውን መረጃ ለመስራት የተፈናና እና የአካባቢው ጉዳይን አስተማረ መረጃ በመስራት ይምረጡ። በዚህ ቦታ በትምህርት፣ ሥራ እና ማህበራዊ ጉዳይዎች መረጃ ያገኛሉ። በፈቃደኛ መደብ የተሠራ ቀናት በአገር ተቋማ፣ አካባቢና ከተማን በነገራቸው እንዲሰጡ የፍቅር በሽታ ያላቸውን ጉዳይዎችን ለማስረጃ እና ለማደራደር ጠቅላላ ዝርዝር እና መረጃ ማህበራዊ ያላቸውን መረጃ ለእኛ ያገኛሉ። ጉዳይ እንደዛሬ መረጃዎቻችንን ለማመልከት በ@ethiodlbot እንላክ።

Ethiopian Digital Library

14 Nov, 10:38


መምህሩ የተማሪዎችን 18 ሞባይሎች ይዞ ተሰውሯል!

በወልቃይት ወረዳ የወልቃይት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር የሆነው ብርሀኑ ሙጬ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን "ፈተና ስለምትፈተኑ የያዛችሁትን የሞባይል ስልክ አምጡ" በማለት በቁጥር 18 የሚሆኑ ሞባይሎችን ይዞ ተሰውሯል። የወልቃይት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በጥቆማ ተባበሩኝ ሲል ጥያቄውን ለህዝብ አቅርቧል።

አስፋው አብርሃ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

14 Nov, 10:25


40 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተዋል

ለ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን እና በ2016 በሪሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎቻቸውን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች


👉1. Addis Ababa University - ገብተዋል
👉2. Adama ST University - ገብተዋል
👉3. Addis Ababa ST University - ገብተዋል
👉4. Salale University - ጥቅምት 21 እና 22/2017 - ገብተዋል
👉5. Kebri dehar University - ጥቅምት 25,26/2017 - ገብተዋል
👉6. Mizan Tepi University - ህዳር 2 እና 3/2017 - ገብተዋል
........................................................................
👉7. Hawassa University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉8. Haramaya University - ህዳር 9,10,11/2017
👉9. Raya University - ህዳር 2 እና 3/2017
👉10. Oda Bultum University - ህዳር 4,5/2017
👉11. Jigjiga University - ህዳር 4,5,6/2017
👉12. Dire Dawa University - 16 እና 17/2017
👉13. Kotebe University - ህዳር 4 እና 5 /2017
👉14. Ambo University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉15. Wollega University - ህዳር 4 እና 5/2017
👉16. Aksum University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉17. Borana University - ህዳር 12 እና 13/2017
👉 18. Woldia University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉 19. Dambi Dollo University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉 20. Wolaita Sodo University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉21. Dilla University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉22. University of Gonder - ህዳር 12 እና 13/ 2017
👉23. Arba Minch University - ህዳር 7 እና 8/2017
👉24. Wollo University - ህዳር 13 እና 14/2017
👉25. Debark University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉26. Jinka University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉27. Debre Tabor University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉28. Assosa University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉29. MizanTepiUniversity - ህዳር 11 እና 12/2017
👉30. Werabe University - ህዳር 19 እና 20/2017
👉31. Injibara University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉32. Madda Walabu University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉33. Mattu University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉34. Jinka University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉35. Assosa University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉36. Bule Hora University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉37. Gondar University - ህዳር 12 እና 13 2017
👉38. Bahir Dar University - ህዳር 16 እና 18/2017
👉39. Samara University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉40. Wachemo University - ህዳር 19 እና 20/2017
..................................................................................
👉 Federal Technical and Vocational Training Institute - ህዳር 3 እና 4/2017 ዓ.ም
..................................................................................

N.B: ራያ ዩኒቨርሲቲ አራዝሟል - ቀኑ ህዳር 9 እና 10/2017

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

14 Nov, 09:50


#መምህራን_አልተቻሉም

መምህር አዳነ የ2 ሚሊየን የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ አሸናፊ ሆነ


መምህር አዳነ ደሴ ይባላሉ የመምህርነቱን ሙያ በቅርብ ነው የተቀላቀሉት ፡፡ መምህር አዳነ የቀብሪደሀር ነዋሪ ሲሆኑ በ28ኛው አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛው ዕጣ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል :: በደረሳቸውም ገንዘብ መኖርያ ቤት እንደሚገዙበት ገልጸዋል።

ለማስታወስ - ሎተሪ አሸናፊ መምህራን በጥቂቱ

1. https://t.me/Ethiopian_Digital_Library/3282
2. https://t.me/Ethiopian_Digital_Library/2418
3. https://t.me/Ethiopian_Digital_Library/2294
4. https://t.me/Ethiopian_Digital_Library/2240
5. https://t.me/Ethiopian_Digital_Library/2419

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

13 Nov, 17:09


#Funny

ደብረ ብርሃን - ሰሜን ኮርያ አረቄ ቤት 🤣🤣🤣

እስኪ ባላችሁብት አስገራሚ ስም ያለው ድርጅት ካለ ወዲ በሉ!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

12 Nov, 11:59


#Funny

ትራምፕ በኢትዮጵያ

"ትራምፕ" የሚባል ምግብ በአዲስ አበባ መኖሩ ተነገረ ።

ይህ ትራምፕ የሚባለው ምግብ ለ3 ሰዎች እንደሚበቃ እና ከተለያዩ ዓይነቶች እንደሚሠራ ተገልጿል።

ዋጋው 250 ብር ነው ተብሏል።

#ሸገር_ሬድዮ #DonaldTrump

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

12 Nov, 10:25


#BREAKING

አይገርምም ይሄን ፈፅሞ አልጠበኩም!

👉ክሪፕቶ 28 ቢሊየነሮችን ፣ 325 ሴንቲሚሊየነሮችን
፣ 88,200 ሚሊየነሮችን ፈጥሯል - 28 Crypto Billionaires, 325 crypto centimillionaires, 88,200 crypto-millionaires in 2024. ✍️ አባቴ የብር ቢሊየነር እንዳይመስልህ የዶላር ነው ብርማ ከሆነ ትሪሊየነር ገብተዋል::

ወዳጆቼ ዘመኑ የክሪፕቶ ነው
👉 እንዳይቆጫቹ አሁኑኑ ሞክሩት!

የትራምፕ መመረጥ ለክሪፕቶ አለም ሰርግና ምላሽ ሆኗል!
......................................................................
1 Bitcoin = 91,197 Dollar = 11,071,738.93 Birr
......................................................................
ፍጠኑ ተረጋግጧል - best airdrops

1. https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=eRns78Rg

2. https://t.me/major/start?startapp=812359129

As of 2024, there are 28 crypto billionaires and 325 crypto centimillionaires (individuals with crypto assets exceeding $100 million). The total market cap of all cryptocurrencies is $1.18 trillion. The world has at least 88,200 crypto-millionaires, which is around 0.02% of everyone who owns or trades in cryptocurrencies.

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

11 Nov, 08:57


በዓለም ላይ በጣም አስቸጋሪው ነገር ምንድን ነው?

ቴልስ (Thales/546 B.C.) የተሰኘው ታዋቂው የግሪክ ፈላስፋ በአንድ ወቅት፣ “በዓለም ላይ በጣም አስቸጋሪው ነገር ምንድን ነው?” ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ፣ “ራስን ማወቅ” በማለት እንደመለሰ ይነገራል፡፡

ከዚያም ጠያቂዎቹ ጥያቄውን በመገልበጥ፣ “በዓለም ላይ በጣም ቀላሉ ነገርስ ምንድን ነው?” ብለው ሲጠይቁት፣ “ለሰዎች ሃሳብ ሰንዛሪነት” በማለት እንደመለሰም ይነገራል፡፡

1.  ከባዱ ነገር - ራስን ማወቅ

ራእዬን፣ ፍላጎቴን፣ ዝንባሌዬን፣ የሚቀናኝንና የማይነቀኝን፣ የቤተሰብ አስተዳደጌ በእኔ ላይ ያመጣውን ተጽእኖ፣ ከሕብረተሰቡ የወረስኩትን መልካምና አጉል ተጽእኖና የመሳሰሉትን ማሰብ፣ መለየትና ተገቢውን የጥበብ እርምጃ መውሰድ በሚቀጥለው ዓመት የሚኖረኝን ስኬታማነት ይወስናል፡፡

2.  ቀላሉ ነገር - ለሰዎች ሃሳብ ሰንዛሪነት

ለቅርብ ሰዎችም ሆነ በአካባቢያችን ለሚኖሩ የሕብረተሰቡ አካሎች በማያገባን ነገር ሁሉ ጥልቅ እያልን ሃሳብ ሰንዛሪዎች መሆን በመጀመሪያ በራሳችን ላይ እንዳንሰራ ትኩረታችንን የመስረቅ ጉልበት ሲኖረው፣ ሲቀጥል ደግሞ ያለንን የማሕበራዊ ግንኑነት የማበላሽት አቅም አለው፡፡

ለመደገፍና ለመፍትሄ ራስን ለማቅረብ ፈቃደኞች ባልሆንበት ጉዳይ ላይ የሩቅ ሃሳብ-ሰጪዎች እንደመሆን ቀላልና ቀላልነትንም የሚስከትል የሕይወት ዘይቤ የለም፡፡
Dr. Eyob Mamo

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

11 Nov, 08:42


https://t.me/ethiopian_education2

Ethiopian Digital Library

11 Nov, 07:23


ከ 1000 ቃላት አንድ ምስል ይበልጣል!

A picture is worth 1000 words!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

10 Nov, 18:16


🇺🇸 ለልጆቻችን ተገቢ ያልሆኑ ወሲባዊ ቁሳቁሶችን እና ትራንስጀንደር እብደትን የሚያስተምሩ  ትምህርት ቤቶች ካሉ የፌደራል የገንዘብ ድጋፍን አቋርጣለሁ።

ኘሬዝዳንት ዶናልድ ትራምኘ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

10 Nov, 11:56


The fact!

ዩኒቨርሲቲዎች እንድንማር ነው እንጂ ገንዘብ እንድንሰራ አይፈልጉም - Yonas Moh

ዩኒቨርሲቲዎች እንኳን ለተማሪዎች ለመምህራንም አልሆኑም - EDL

እውነታው ከ 5 ዓመት ዲግሪ የ 6 ወር አጭር ስልጠና ይሻላል - EDL

ወዳጄ ይህ አሁን ካልገባህ አመታት አልፈው ያኔ ይገባሃል - EDL

ደግሞ ይሄን አይተህ ትምህርት አይጠቅምም እንዳትል ትምህርት እማ ይጠቅማል ግን መቼት ይፈልጋል - EDL

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

10 Nov, 09:25


የደመወዝ ማስተካከያው አልቀረም - ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ የሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን ኮሚሽነር

የተፈቀደው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ክፍያ ዘግይቷል፥ ቀርቷል የሚሉ ሃሳቦች እየተራመዱ ነው። በሲቪል ሰርቪስ በኩል የሚለቀቁ መረጃዎች ኦፊሴላዊና የሚተገበሩ መሆኑን መተማመን ጥሩ ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ ክፍያ በጀቱን ለሚመለከታቸው ተቋማት ፈቅዷል። በእኛ መስሪያ ቤትም በኩል የተስተካከለውን የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል። ሌሎችም እንደዚሁ የከፈሉ አሉ። የቀሩት ደግሞ የማጥራት ሥራ እየሰሩ ሊሆን ይችላል። እነዚያም ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ የተስተካከለው የጥቅምት ወር ክፍያ ታሳቢ በማድረግ የሚከፍሉ ይሆናል"ብለዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

10 Nov, 09:20


ማስታወቂያ

50,000 እና በላይ የቴሌግራም ተከታይ ያለው ቻናል ካላችሁ በኢትዮጵያዊ ድርጅት ሞኒታይዝ ማስደረግ ስለምትችሉ በውስጥ መስመር አነጋግሩን:: ድርጅቱ በቅርቡ በቲክቶክ እና ዩቱብ እመጣለሁ እያለ ነው:: contact: @ethiodlbot

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

10 Nov, 09:05


#Breaking

የትራምፕ መመረጥ ለክሪፕቶ አለም ሰርግና ምላሽ ሆኗል!

1 Bitcoin = 89,456.96 Dollar = 10,831,940.73 Ethiopian Birr
......................................................................
ፍጠኑ ተረጋግጧል - best airdrops

1. https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=eRns78Rg

2. https://t.me/major/start?startapp=812359129

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

09 Nov, 16:55


መልካም ዜና - Google Play

ኢትዮጵያ በጎግል ፕሌይ ሊስት ከተዘረዘሩ ሃገራት ውስጥ ተካታለች። ጎግል ፕሌይ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል መጀመሩን አስታውቋል፡፡

Google Play Developer Registration Now Available for Ethiopian Developers!

Ethiopia is now officially supported for Google Play Developer Console registration!

Developers can directly publish apps on Google Play, bringing their innovative ideas to the world!

By Solomon Kassa

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

09 Nov, 10:52


መነጋገሪያ ሆኗል!

በሰሜናዊ የጋዛ ክፍል በተከሰተው ረሃብ ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሰብአዊ እርዳታ መኪኖች ምግብ ለማግኘት ሲሞኩሩ የሚያሳየው ምስል በተለይም በቀድሞው ቲዊተር በአሁኑ የ ኤክስ ሶሻል ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል::😭😭😭

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

09 Nov, 10:41


ለ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን እና በ2016 በሪሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎቻቸውን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች

👉1. Addis Ababa University - ገብተዋል
👉2. Adama ST University - ገብተዋል
👉3. Addis Ababa ST University - ገብተዋል
👉4. Salale University - ጥቅምት 21 እና 22/2017 - ገብተዋል
👉5. Kebri dehar University - ጥቅምት 25,26/2017 - ገብተዋል
........................................................................
👉6. Mizan Tepi University - ህዳር 2 እና 3/2017
👉7. Hawassa University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉8. Haramaya University - ህዳር 9,10,11/2017
👉9. Raya University - ህዳር 2 እና 3/2017
👉10. Oda Bultum University - ህዳር 4,5/2017
👉11. Jigjiga University - ህዳር 4,5,6/2017
👉12. Dire Dawa University - 16 እና 17/2017
👉13. Kotebe University - ህዳር 4 እና 5 /2017
👉14. Ambo University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉15. Wollega University - ህዳር 4 እና 5/2017
👉16. Aksum University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉17. Borana University - ህዳር 12 እና 13/2017
👉 18. Woldia University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉 19. Dambi Dollo University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉 20. Wolaita Sodo University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉21. Dilla University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉22. University of Gonder - ህዳር 12 እና 13/ 2017
👉23. Arba Minch University - ህዳር 7 እና 8/2017
👉24. Wollo University - ህዳር 13 እና 14/2017
👉25. Debark University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉26. Jinka University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉27. Debre Tabor University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉28. Assosa University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉29. MizanTepiUniversity - ህዳር 11 እና 12/2017
👉30. Werabe University - ህዳር 19 እና 20/2017
👉31. Injibara University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉32. Madda Walabu University - ህዳር 09 እና 10/2017
..................................................................................
👉 Federal Technical and Vocational Training Institute - ህዳር 3 እና 4/2017 ዓ.ም
..................................................................................

N.B: ራያ ዩኒቨርሲቲ አራዝሟል - ቀኑ ህዳር 9 እና 10/2017

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

09 Nov, 10:33


የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ

በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ እስካሁን የጠራ ዩኒቨርሲቲ የለም:: ዩኒቨርሲቲዎች በቅርቡ እንጠራለን ብለዋል :: ስለሆነም በትግስት ጠብቁ::

👉አሁን የተጠሩት የ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን እና በ2016 በሪሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ብቻ ናቸው::

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

09 Nov, 05:57


መወዳደር ወይስ መፎካከር?

👉ተወዳዳሪዎች የሌሎችን ስኬት በማየት ይነሳሳሉ፣ እነሱም ስኬታማ ለመሆን ይሰራሉ፡፡

👉 ተፎካካሪዎች ግን የሌሎችን ስኬት ሲመለከቱ ይቀናሉ እነሱን በመጣል መነሳት የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡

👉ተወዳዳሪዎች የወቅቱን ሁኔታ እያዩ ከለውጥ ጋር አብረው ይራመዳሉ፣ ካለማቋረጥ ራሳቸውን በማዘመን ያሻሽላሉ፡፡

👉 ተፎካካሪዎች ግን ስለሌላው ሰው ሲያወሩ ጊዜ ስለሚያልፍባቸው ወደ ኋላ ይቀራሉ፡፡

👉ተወዳዳሪዎች ራእያቸውንና ዓላማቸውን ያውቃሉ፣ ከዚያም አንጻ ስኬታማነታቸውን ይመዝናሉ፡፡

👉ተፎካካሪዎች ግን ማን ምን እንዳደረገ እና እንዳላደረገ ሲመለከቱ ውለው ያድራሉ፣ ስኬታማነታቸውንም የሚመዝኑት ከማን እንደበለጡ በማየት ነው፡፡

👉ተወዳዳሪ መሆን ማለት የእኛን ስኬታማነት ከራሳችን ዓላማ እና ግብ ጋር በማነጻጸር መኖርና ካለማቋረጥ ወደዚያ ማደግ ማለት ነው፡፡

👉ተፎካካሪነት አሉታዊ ኃይል ሲሆን፣ ተወዳዳሪነት አዎንታዊ ኃይል ነው፡፡

👉ተፎካካሪነት ለመታየት ከመፈለግ ሲነሳ፣ ተወዳዳሪነት በውስጠ-ህልና ራእይን ከማየት ነው የሚነሳው፡፡

Dr. Eyob Mamo

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

08 Nov, 19:34


ፍጠኑ ተረጋግጧል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=eRns78Rg

Ethiopian Digital Library

08 Nov, 13:24


Natural Science Content for Remedial Program

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

08 Nov, 13:24


Social Science Content for Remedial Program

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

08 Nov, 11:51


በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ከሆኑባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) መረጃ መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ ከ6 እስከ 18 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ 244 ሚሊየን ህጻናት እና ወጣቶች ከትምህርት ውጪ ናቸው፡፡ እስካለፈው ሰኔ ድረስ ደግሞ በአፍሪካ 24 ሀገራት ብቻ ከ14300 የሚልቁ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፡፡

በርካታ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉባቸው ሀገራት መካከል ቡርኪናፋሶ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ናይጄሪያ እና ኒጀር ተጠቃሽ ናቸው። ከግጭቶች፣ ከተሳሳቱ የመንግስት ፖሊሲዎች እና የአየር ንብረት ለውጥ ጎን ለጎን ድህነት ለትምህርት ትልቅ እንቅፋት ሆኖ የዘለቀ ችግር ነው፡፡

ዝቅተኛ ኢኮኖሚ በሚገኙባቸው ሀገራት ጦርነት እና ግጭት እንኳን ባይኖር በኢኮኖሚ ሁኔታ የተነሳ ህጻናት ወደ ትምህርት ከሚላኩ ይልቅ ወደ ስራ የሚሰማሩበት አጋጣሚ ከፍ ይላል፡፡ በትምህርት ተደራሽነት ላይ ያለው አስገራሚ ልዩነት በቅርብ ጊዜ በተደረገ ጥናት የተረጋገጠ ሲሆን ፤ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ ለትምህርት ከደረሱ ሕፃናትና ወጣቶች መካከል 33 በመቶ የመማር ዕድል ተነፍጓቸዋል፡፡

በሰላም ዕጦት ከሚዘጉ ትምህርት ቤቶች ባለፈም በበጀት እጥረት ስራ የሚያቆሙት ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ የሚጠቅሰው የዩኒስኮ ሪፖርት፤ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት በ2022 በአማካይ ለአንድ ተማሪ 55 ዶላር ብቻ ሲመድቡ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ደግሞ እስከ 8543 ዶላር ድረስ ያወጣሉ ብሏል፡፡

ሪፖርቱ በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑባቸው የአፍሪካ ሀገራትን ደረጃ ባወጣበት 18.18 ሚሊየን ህጻናት ከትምህርት ውጪ የሆኑባትን ናይጄርያ ቀዳሚ አድርጓታል፡፡11.1 ሚሊየን ህጻናት ከትምህርት የተቆራረጡባት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ደረጃ ስትይዝ ታንዛኒያ ፣ ዲ አር ኮንጎ እና ሱዳን ይከተላሉ፡፡ #ኤራ_ጆርናል

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

08 Nov, 11:42


Ethiopian Digital Library pinned «ለ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን እና በ2016 በሪሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎቻቸውን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች 👉1. Addis Ababa University - ገብተዋል 👉2. Adama ST University - ገብተዋል 👉3. Addis Ababa ST University - ገብተዋል ........................................................................ 👉4.…»

Ethiopian Digital Library

08 Nov, 11:34


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርቶች በECTS ከ900 እስከ 4,615 ብር ሊያስከፍል ነው

ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ ለድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች አዲስ የትምህርት ክፍያ ፖሊሲን እና መመሪያን ነሐሴ 2016 በሴነቱ አጽድቋል። በዚሁ መሰረት ለማስተርስ (ወይም ሁለተኛ ዲግሪ) መርኃ ግብር በሰዓት ከ900 እስከ 3,462 ብር እንደ ሙያ መስኩ የክፍያ ተመን አስቀምጧል።

በተመሳሳይ ለፒኤችዲ መርኃ ግብር በሰዓት ከ1,200 እስከ 4,615 ብር እንደ ሙያ መስኩ የክፍያ ተመን ማዘጋጀቱ ታውቋል። ለመመረቂያ እና ለምርምር ለማስተርስ ከ675 እስክ 900 ብር፣ ለፒኤችዲ ደግሞ 18,000 ብር በሴሚስትር ተመን አውጥቷል።

አዲሱ የክፍያ ተመን ተግባራዊ የሚሆነው ከዘንድሮው የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ1ኛ ወሰን ትምህርት ጀምሮ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ በተጨማሪም የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች በየሴሚስትሩ 300 ብር የመመዝገቢያ ክፍያ ተጥሎባቸዋል። ሁሉም ክፍያዎች ለኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ያስታወቀ ሲሆን ክፍያዎቹ በዚህ ከፍተኛ መጠን ለምን እንደጨመሩ የሰጠው ማብራርያ የለም። #Meseret_Media

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

07 Nov, 12:44


ቤቶን እና ቢሮዎን እናሳምርልዎ

ሳንፎርድ ፈሪኒቸር

👉🏼 ለልጆዎ ምቾት ጥራት ያላቸው አልጋዎች፣
👉🏼 ለቤትዎ ዘመናዊ እና ውብ ቲቭ ስታንዶችን፣
👉🏼 ለቢሮዎ ውበትን ከጥራት ጋር ያዋሃዱ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣
👉🏼 እንዲሁም ለኪችኖ ፤ በፈለጉት ድዛይን የሚያምሩ ኪችን ካቢኔቶችን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክብልዎ!!!

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0978777775/0976777775 አሁኑኑ ይደውሉ!

Ethiopian Digital Library

07 Nov, 07:26


ለ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን እና በ2016 በሪሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎቻቸውን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች

👉1. Addis Ababa University - ገብተዋል
👉2. Adama ST University - ገብተዋል
👉3. Addis Ababa ST University - ገብተዋል
........................................................................
👉4. Salale University - ጥቅምት 21 እና 22/2017
👉5. Kebri dehar University - ጥቅምት 25,26/2017
👉6. Mizan Tepi University - ህዳር 2 እና 3/2017
👉7. Hawassa University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉8. Haramaya University - ህዳር 9,10,11/2017
👉9. Raya University - ህዳር 2 እና 3/2017
👉10. Oda Bultum University - ህዳር 4,5/2017
👉11. Jigjiga university - ህዳር 4,5,6/2017
👉12. Dire Dawa University - 16 እና 17/2017
👉13. Kotebe University - ህዳር 4 እና 5 /2017
👉17. Ambo University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉18. Wollega University - ህዳር 4 እና 5/2017
👉19. Aksum University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉20. Borana University - ህዳር 12 እና 13/2017
👉 21. Woldia University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉 22. Dambi Dollo University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉 23. Wolaita Sodo University - ህዳር 9 እና 10/2017

N.B: ራያ ዩኒቨርሲቲ አራዝሟል

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 13:27


ቤቶን እና ቢሮዎን እናሳምርልዎ

ሳንፎርድ ፈሪኒቸር

👉🏼 ለልጆዎ ምቾት ጥራት ያላቸው አልጋዎች፣
👉🏼 ለቤትዎ ዘመናዊ እና ውብ ቲቭ ስታንዶችን፣
👉🏼 ለቢሮዎ ውበትን ከጥራት ጋር ያዋሃዱ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣
👉🏼 እንዲሁም ለኪችኖ ፤ በፈለጉት ድዛይን የሚያምሩ ኪችን ካቢኔቶችን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክብልዎ!!!

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0978777775/0976777775 አሁኑኑ ይደውሉ!

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 11:41


BREAKING: Bitcoin reaches new all-time high of $75,000 following Donald Trump's winning.

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 08:44


ክልሎች የትምርት መሳሪያዎች ላይ መጠነኛ ክፍያ እንዲያስከፍሉ የሚደነግግ አዋጅ ሊጸድቅ ነው

ክልሎች በሚያወጠት ሕግ መሠረት ለሌሎች የትምህርት መሣሪያዎች የሚውል መጠነኛ ክፍያ ከተማሪ ወላጆች የመክፈል አቅም ጋር በተጣጣመ መንገድ ሊያስከፍሉ የሚችሉበት ህግ ለቋ ኮሚቴ ተመርቷል።

ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው አዋጅ ይህንን አላሟላህም ተብሎ ተማሪው ከትምህርት ገበታው እንዲለይ ማድረግ እንደማይቻልም ተጠቁሟል።

በአገር አቀፍ፣ በክልል ወይም በአካባቢ ደረጃ ያለው የትምህርት ደረጃና ጥራት ከተጠበቀው በታች መወረዱ ሲረጋገጥ የጸጥታ ችግር በሺህ የሚቆጠሩ ትምርትቤቶችን ከመማር ማስተማር ውጪ እንዳደረጋቸው የሚታወቅ ነው፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሰው ሀብት ልማት የሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ በአብላጫ ድምፅ የተላከ ሲሆን ይጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 08:38


@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 08:31


ከእንግዲ ጦርነቶች አይኖሩም ጦርነቶችን ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ - ዶናልድ ትራምፕ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 07:58


🌟 APPLY NOW 🌟
https://app.globedocket.com/jobs/globedock_plc/paid-intern-%E2%80%93-marketing/sales

Job Title: Paid Intern – Marketing/Sales

About Us:
Join GlobeDock Academy, Ethiopia's top eLearning platform, dedicated to providing accessible education. We're looking for passionate individuals to empower students through innovative marketing and exceptional service.

Key Responsibilities:

▪️Assist with customer inquiries about courses and subscriptions.
▪️Create and share educational marketing content.
▪️Support remote marketing initiatives and campaign planning.
▪️Collaborate to enhance customer satisfaction.
▪️Document interactions in our CRM for efficient follow-up.
▪️Participate in training to improve marketing and service skills.

Requirements:

▪️Current student or recent graduate in Marketing, Business, Education, or related fields.
▪️Strong communication and problem-solving skills.
▪️Familiarity with MS Office and CRM systems is a plus.

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 07:49


Donald J Trump - Victory Speech

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 07:39


ትራምፕ ካማላን ሃሪስን በማሸነፍ ቀጣዩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ይሆናሉ ሲል " ፎክስ ኒውስ " ጠቁሟል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

06 Nov, 04:49


#ምርጫ

👉 ካማላ ሀሪስ 224 የምርጫ ጣቢያ ስታሸንፍ

👉ዶላንድ ትራምፕ 277 የምርጫ ጣቢያዎችን አሸንፏል።

👉 Trump wins the election!

#Update #USAelection2024

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

05 Nov, 18:02


የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ግን ፕላኔት ላይ የሚኖሩ አድራሻ የሌላቸው ብቸኛ የሃገሪቱ ተቋሞች ከሆኑ ብዙ አመት ሆኗቸዋል።

ክልሎች ዩኒቨርሲቲዎች የፌደራል ተቋም ስለሆኑ አናውቃቸውም ካሉ ብዙ አመት አልፏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

05 Nov, 07:44


የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥሪ

👉#ሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ - ወደ ተቋሙ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ኅዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ሚዛን አማን በሚገኘው ዋናው ግቢ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ #MizanTepiUniversity

👉#ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ኀዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ #HawassaUniversity

👉#ራያ_ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም በ #ራያ_ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያ ትምህርት (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ህዳር 9/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡#RayaUniversity

👉#ሀረማያ_ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም. በ #ሀረማያ_ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ በ2016 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና በላይ አምጥታችሁ በ2017 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች፤ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በሪሜዲያል(Remedial)ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ አማካይ ውጤት 50% እና በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ በህዳር 09,10 እና 11፣ 2017 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት አንድታደርጉ አሳውቋል፡፡#HaramyaUniversity

👉#ኦዳ_ቡልቱም_ዩኒቨርሲቲ - በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ እና በ2017 ዓ.ም ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 4 እና 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡#OdaBultumUniversity

👉ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ (1ኛ ዓመት) እና የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ከህዳር 4 እስከ 6/2017 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አሳውቋል፡፡ #JigjigaUniversity

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

05 Nov, 07:35


AIRDROP and CRYPTO ቆንጆ ስራ ነው ወጥራችሁ ስሩ እያሉ ነው::

እናንተስ ምን ትላላችሁ?

👉በX Empire 170 ሺ ብር ሰራሁ - big habesha

👉በX Empire ከ200ሺ ብር በላይ ሰራሁ - dinku

1. https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=eRns78Rg

2. https://t.me/major/start?startapp=812359129

3. https://t.me/theZencoin_bot/zencoin?startapp=r=812359129

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

05 Nov, 06:55


ቤቶን እና ቢሮዎን እናሳምርልዎ

ሳንፎርድ ፈሪኒቸር

👉🏼 ለልጆዎ ምቾት ጥራት ያላቸው አልጋዎች፣
👉🏼 ለቤትዎ ዘመናዊ እና ውብ ቲቭ ስታንዶችን፣
👉🏼 ለቢሮዎ ውበትን ከጥራት ጋር ያዋሃዱ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣
👉🏼 እንዲሁም ለኪችኖ ፤ በፈለጉት ድዛይን የሚያምሩ ኪችን ካቢኔቶችን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክብልዎ!!!

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0978777775/0976777775 አሁኑኑ ይደውሉ!

Ethiopian Digital Library

05 Nov, 05:25


ነገረ ደመወዝ

በዚህ ወር ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ።

መንግሥት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ያለው የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ፣ በዚህ ወር ተግባራዊ አለመሆኑን ተሰምቷል።

በአአ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ መንግሥት ሠራተኞች በተወሰኑ ወረዳዎች ከሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ቢሮው፣ ለከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ሰራተኞች ጭማሪው የሚከፈልበት ጊዜ የተራዘመው የሰራተኞችን መረጃ ለማደራጀት ጊዜ ስለሚያስፈልግ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቷል ።

ሆኖም ሰራተኞቹ ቢሮው እስካሁን ምን ያህል የመንግስት ሰራተኛ እንዳለ እና ሌሎች ከደሞዝ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አያውቅም ወይ? የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰምቷል ።

ሰራተኞቹ እስካሁን የተጨመረላቸውን ደሞዝ የሚገልጽ ይፋዊ ደብዳቤ አልደረሳቸውም።

በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሩ አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ አደረጃጀት ጥናት አድርገው የብቃት መመዘኛ ፈተና ለሰጡት ተቋማት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪው ይዘገያል መባሉንም ዋዜማ ተገንዝባለች።

ጭማሪው የሚዘገየው ተቋማቱ የሰራተኞችን የሥራ ደረጃ ምደባ ገና ስላልጨረሱ ነው ተብሏል።
 
ከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያው ዙር የብቃት ምዘና ፈተና የተሰጠው ለቤቶች ልማት አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት፣ የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ፅሕፈት ቤት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅሕፈት ቤት፣ ኅብረት ሥራ ፅሕፈት ቤት እና የመሬት ልማት አስተዳደር ፅሕፈት ቤት መሆኑ ይታወሳል። #ዋዜማ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

04 Nov, 16:31


🇺🇸የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዛሬ ይካሄዳል። አለም በሙሉ ትኩረቱን አሜሪካ ላይ አድርጓል።

ትራምፕ ከተመረጥኩ ህገወጥ ስደተኞችን አስወጣልሁ ብሏል። በዚህም ብዙዎች ጭንቀት ውስጥ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

04 Nov, 14:50


Coming Soon!

All books from all Regions (12) in Ethiopia will be available on

👉 https://waltajobs.com/

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

04 Nov, 14:27


አሁን እየሰራ ነው

የREMEDIAL (የአቅም ማሻሻያ) ፕሮግራም ምደባ

👉በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

👉በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

04 Nov, 12:50


አሁን እየሰራ አይደለም!

የREMEDIAL (የአቅም ማሻሻያ) ፕሮግራም ምደባ

👉በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

👉በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

04 Nov, 12:46


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦

በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል። ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

04 Nov, 08:18


በአለም ላይ ከ10,000 በላይ ሐይማኖት እንዳለ ያውቃሉ?

በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙት ሰዎች መካከል 85 በመቶው የሚሆኑት አንድ ሃይማኖት አላቸው። በአለም ላይ ወደ 10,000 የሚጠጉ የተለያዩ ሃይማኖቶች ሲኖሩ ከሶስት አራተኛ በላይ የሚሆነው የአለም ህዝብ ከአራቱ አንዱን - ክርስትና (31%)፣ እስልምና (24%)፣ ሂንዱይዝም (15%) እና ቡዲዝም (7%) ይከተላሉ።

Today, some 85 percent of people around the globe identify with a religion. While there are around 10,000 distinct religions in the world, over three-quarters of the global population adheres to one of these four – Christianity (31%), Islam (24%), Hinduism (15%), and Buddhism (7%).

Source: populationeducation.org

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

04 Nov, 08:10


አለም ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተፅእኖ ላይ ላለመውደቅ አዲስ ሐይማኖት ያስፈልገዋል - ቢል ጌትስ

ቱጃሩ የማይክሮሶፍት  መስራች ቢልጌትስ ከግራ ዘመሙ ቢልየነር ሬድ ሆፍማን ጋር ሰሞኑ ባደረጉት የፖድካስት ውይይት ላይ እንደተናገሩት

"አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ብዙ ነገር እየተቆጣጠረ ነው በዚህም ሰዎች ለወደፊት ብዙ ስራ ላይሰሩ ይችላሉ።

ብዙ ጊዜያቸውን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ  ክንዋኔች ላይ በማዋል የገሀዱን  አለም ሊረሱ ይችላሉ።

ስለዚህ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ባህሪያቸውን ቀይሮ ብዙ ነገራቸውን እንዳያበላሽ አዲስ ሐይማኖት ወይም ፍልስፍና ያስፈልጋቸዋል ባይ ነኝ "ሲሉ ተደምጠዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

02 Nov, 07:41


መምህራን በምገባ መርሐግብር እየታቀፉ ነው

በሸገር ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪና መምህራን የምግብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል።

በሸገር ከተማ በሚገኙ 256 ትምህርት ቤቶች የመምህራን ምግብ ፕሮግራም እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ለ3 ሺ 707 መምህራን መስጠት ተችሏል ተብሏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

02 Nov, 07:06


አሊባባ የመጀመሪያውን Showroom በአዲስአበባ ከፍቷል

በህዳር ወር መጨረሻ የፈለጋቹትን እቃ ከውጪ በኢትዮጲያ ብር ማስመጣት ትችላላችሁ እያለ ነው።

ይህ ዜና ከወዲሁ የአስመጪና ላኪ ባለሃብቶችን ስራ ማበላሸቱን ተከትሎ ቅሬታቸውን ለተለያዩ ሚዲያዎች እያቀረቡ መሆኑን አዲስ ኢንሳይደር አረጋግጧል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

02 Nov, 06:00


የልጆዎ ምቾት ያሳስቦታል?

ለልጅዎ ምቾት ሳንፎርድን ቀዳሚ ምርጫዎ ያድርጉ!
ጥራት፣ ውበት፣ እና ምቾት በአንድ ላይ አሟልቶ ለልጆት ሰላማዊ እንቅልፍ በመጨነቅ ዘመናዊ የልጆች አልጋ በተመጣጣኝ ዋጋ እየሰራን እንገኛለን።
ምን ይሄ ብቻ፣
ሶፋ ፣ አልጋ ፣ የቲቪ ማስቀመጫ ፣ የመመገብያ ጠረጴዛ እና ወንበር ዲዛይኖቻችን ከምቹነት፣ ከጥራት እንዲሁም ከውበት ጋር የተጣመሩ ናቸው።

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።
አሁኑኑ ይደዉሉ ፦ +251978777775 / +251976777775

Ethiopian Digital Library

01 Nov, 19:27


ምሽት 3:55 ላይ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

" የዛሬውስ ያስፈራ ነበር ፤ ...  በጣም ነው ያስደነገጠን ፤ ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው " የሚሉ መልዕክቶች በውስጥ የመጡ ናቸው። ንዝረቱ አዲስ አበባም ነበር። #Tikvah

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

01 Nov, 10:49


በቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ አካባቢ የእሳት አደጋ

👉በቦሌ ክፍለ ከተማ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አጋጥሞ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

👉የአደጋው መንስኤ እና የውድመት መጠኑ እየተጣራ መሆኑን አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

👉አደጋው በቆርቆሮ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።

👉የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች እና ሁለት የውኃ ቦቴ ከ70 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጋር መሰማራታቸውንም ተነግሯል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

01 Nov, 09:19


#Fake_News Alert

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም አይኖርም በሚል በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች እየተዘዋወረ የሚገኘው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ የሆነው የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም "በዚህ ዓመት በበጀት እጥረት ምክንያት ተቋርጧል" በሚል የተሰራጨው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቹ ባጋራው መረጃ አረጋግጧል፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

01 Nov, 09:16


በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ከስምምነት ላይ መደረሱን መጅሊሱ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ በአለባበስ ምክንያት ለሁለት ሳምንት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት መደረሱን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥቅምት 20/ 2017 ዓ/ም በጻፈው ደብዳቤ፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ እንዳንድ ትምህር ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያት “ጫናና እንግልት” እየደረሰ ነው ሲል ገልጿል።

ምክር ቤቱ አዲስ ባወጣው መግለጫ ከያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ በጊዜያዊነት ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት ተደርሷል ሲል አስታውቋል።
#AddisStandard

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

01 Nov, 07:29


ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንን ማባረር አለባቸው - ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ትናንት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎች እና የተሰጡ ምላሾችን ምንጮች ተከታዩን መረጃ አድርሰዋል፦

👉ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ከመጡ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በበጀት እጥረት ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸውን መስራት አልቻሉም።

👉ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ ብቻ መመደብ ወደፊት ስራ ቅጥር ላይ ችግር አይፈጥርም ወይ? የተወሰኑ የትምህርት ክፍሎች ተማሪ የላቸውም ይሄ ነገር ትምህርት ሚኒስቴር እንደት ያየዋል

👉 ትምህርት ሚኒስቴር ለሶስተኛ ድግሪ ተማሪዎች የሚከፈለውን የምርምር ገንዘብ ማለትም ለማህበራዊ ሳይንስ 45000 ብርና ለተፈጥሮ ሳይንስ 60000 ብር እና ጥቅማ ጥቅም ሳያሻሽል ሀገር ውስጥ ፒኤችዲ ተማሩ የሚለው በጤናው ነው ወይ?

👉ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች ምርምር እንዲሰሩ አቅጣጫ ቢያስቀምጥም ከሶስት አመታት ወዲህ ለምርምር የሚከፈለው ገንዘብ እጅግ በጣም ቀንሷል።

👉አሁን ያለው ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንን መሰረታዊ ጥያቄዎች ከመመለስና ከተግባር ስራ ይልቅ መመሪያና ደንብ ማውጣት፣ወሬ ላይ ያተኮረ ነው።

የፕሮፌሰሩ ምላሽ❗️

👉ፕሮፌሰሩ ለዩኒቨርሲቲ መምህራን የተለየ ጭማሪ አልተደረገም፤ለሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ሲጨመር ለዩኒቨርሲቲ መምህርም የተጣራ 1000 ብር አካባቢ  ጭማሪ ተደርጓል ብለዋል።

👉በተጨማሪም ፕሮፌሰሩ ወርሃዊ ደመወዝ ያልበቃቸው መምህራን ከማስተማር ስራቸውን ጎን በጎን የባጃጅ ስራ፣የፀጉር ቤት ስራ፣የእርሻ ስ፣የንግድ ስራ ወዘተ እንደሚሰሩ እናውቃለን፤ ዩኒቨርሲቲዎች በአግባቡ የሚያስተምሩትን መምህራን ይዘው መቀጠል አለባቸው ሌሎቹን ማባረር አለባቸው ብለዋል።

👉ፕሮፌሰሩ በተደጋጋሚ ስለ ደመወዝ ጥያቄ (የማድ ባት ወሬ) እንዳትጠይቁኝ ሲሉ ተደምጠዋል።

👉በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች autonomous ሱሆኑ የተወሰነ መምህር ብቻ ያስፈልጋቸዋል፤የዛኔ ለቀሩት መምህራን ጥሩ ደመወዝ መክፈል ይችላሉ"ማለታቸውን ተሳታፊዎቹ ገልፀውልኛል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

31 Oct, 10:19


"በሆያሆዬ እና አበባይሆሽ ዉስጥ ያሉ ግጥሞች መቀየር አለባቸዉ" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

31 Oct, 08:05


"እኛን የከበደን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መቀየር ሳይሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እየተቀየረ እንደሆነ ማንበብ የማይቸሉ ሰዎችን መቀየር ነዉ" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

30 Oct, 15:01


በ2017 ዓ.ም በድህረ ምረቃ ፕሮግራም አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፉ እና በተከታታይ ትምህርት (ማለትም በማታ፤ ቅዳሜ እና እሁድ) በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ለሚማሩ አመልካቾች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 21 እና 22 ቀን መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

28 Oct, 19:19


"ይህንን ብዙ የደከምኩበትን መጽሃፍ በምትችሉት መንገድ ሁሉ ለተማሪዎች፣ ለመምህራንም ሆነ ለወላጅ እንድታስታዉቁልኝ ስል በታላቅ ትህትና ትብብራችሁን እጠይቃለሁ።

መጽሃፉ ላይ ያለው ዋጋ 560 ብር ቢልም ገበያ ላይ እየተሽጠ ያለው ግን በ450 ብር ነው።"

ከመምህር ዮናስ ንብረት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

28 Oct, 11:31


14 Famous Ethiopian Scientists

1. Kitaw Ejigu (PhD)
2. Gebisa Ejeta (Prof)
3. Rediet Abebe
4. Zeresenay Alemseged (Zeray) (PhD)
5. Berhane Asfaw (PhD)
6. Sebsebe Demissew (PhD)
7. Senait Fisseha (PhD)
8. Timnit Gebru (PhD)
9. Segenet Kelemu (PhD)
10. Aklilu Lemma (PhD)
11. Melaku Worede (PhD)
12. Jelani Nelson
13. Birhanu Bulcha (PhD)
14. Sosina Haile (Prof)

ሌሎች ያልተጠቀሱ እንዳሉ ልብ በሉ!

Source: ethiopiangobgnu.com

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

28 Oct, 10:45


ነፃ ማስታዎቂያ

👉Zeha Graphics and Poster
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች :
💥Logo design, Banner, YouTube thumbnail, Photo editing, Business cards design, Poster design, Video editing, Background remove, T-shirt design and Books cover በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰራለን
contact: @outsideof145prinze or @Abenatty or @zehagraphics145

👉አዳማ ውስጥ ለልጅዎ አስጠኚ ይፈልጋሉ ?
ከሀገራችን ዩንቨርስቲዎች ቀዳሚው በሆነው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ(astu) የ3ኛ አመት የcomputer science and engineering(CSE) ተማሪ ነኝ። ልጅዎን እስከዛሬ ባለኝ ስኬታማ የጥናት ዘዴ ውጤታማ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ። እኔን ለማናገር : @abilak12

👉የተለያዪ የtelegram group logo እንሰራለን!! በ 0963853814 ይደዉልልን @kdb logo maker በስራችን እንደሚደሰቱ በራስ መተማመን አለን

👉ጆኒ ጠቅላላ የፍሪጅ ልብስ ማጠቢያ ኦቨን ጥገና እንዲሁም የኤሌክትሪክ ዝርጋታና የዲሽ ሙሉ ጥገና contact +251973951053 ይደውሉ አስተማማኝ አገልግሎት መለያችን ነው!!!

👉ለ6ተኛ፣ 8ተኛ እና 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን መዘጋጃ
የ2017 አገር አቀፍ እና ክልል አቀፍ ተፈታኞችን ከጥቅምት 1 እስከ ፈተናው ድረስ ያለሙትን ውጤት እንዲያሳኩ ብቁ አድርጎ ሊያዘጋጅ ዝግጅቱን አጠናቋል! ለመመዝገብ ስልክ: +251951068598 ቴሌግራም: @weanswertg or @WeAnswerTutor

👉የኔታ
የቀደመው ዘመን የቀለም ቀንድ የነበረ ሥም ለሁሉም ቀለምን ለማሳወቅ ከማንም ቀድመው መምህርም ርዕሰ መምህርም የነበሩት የቀደመው ዘመን የቆሎ ፣ የአብነት እና የቄስ ትምህርት ቤት ከፊደል እስከ ንባብ አስጠኚ የነበሩት የኔታ
በዚህ በኛ ዘመን ስማቸውን ተውስን በማስጠናትና በማስተማር ግብር ተማስለን ከ kG እስከ 12 ኛ ክፍል የትኛውም ት/ቤትቢማሩ ፣ የትም ሰፈር ቢኖሩ ፣ የቱም ትምህርት ቢቸግሮ የኔታ አሉልዎ አዲሱን ሥርዓት ትምህርት በልዩ ልዩ የማስረዳት ዘዴ ከ 4 ዓመት የማስጠናት ልምድ ጋር ስልክ ቁጥሮች +251984063388 or +251912398467 አሜይል አድራሻ [email protected]

👉🔥FULL GRAPHIC DESIGN COURSE🔥
>> 2 MONTHS - Evening Class <<
BIG DISCOUNT until November 20
ONLINE LIVE SESSIONS getting feedback on assignments & projects LIVE from your home with only 4000 Birr. REGISTER NOW
https://forms.gle/DeV6mHBWemZKhYNCA
Contact @jonathanAsefa |  JOIN @byfor_hv

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

28 Oct, 10:34


ለተማሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ ማስታዎቂያ

ተጨማሪ ስራ እየሰራቹ ያላችሁ ተማሪዎች ምርትና አገልግሎታችሁ ማስታዎቂያ የሚፈልግ ከሆነ በዚህ ቻናል ለአንድ ሳምንት በነፃ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ:: ማስታዎቂያው ሳቢ ሆኖ ቢዘጋጅ መልካም ነው:: Contact: @ethiodlbot

የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብራሪ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

28 Oct, 10:01


#Notice

⚠️ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል

Only one week is left for American Diversity Visa Lottery #DV_lottery 2026. Last Date: November 5, 2024

የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ሊጠናቀቅ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል!

👉 Link: https://dvprogram.state.gov/

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

27 Oct, 13:22


በምንም ምክንያት ተስፋ አትቁረጥ!

ጃክ ማ (Jack Ma) ይባላል። ለሁለት ጊዜ የኮሌጅ መግቢያ ውጤት አልመጣለትም። 30 ግዜ ለስራ አመልክቶ አልተሳካልለትም። KFC ቻይና ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍት ከእሱ ጋር 24 ሰዎች ለስራ ተወዳድረው እሱ ብቻ እድሉን አጣ። ለፖሊስነት አመልክቶ እሱ ብቻ ተቀባይነት አጣ። አሜሪካ ለሚገኘው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ለመቀጠል ጠይቆ he was rejected በሕይወቱ ውስጥ በጣም ብዙ ውድቀቶችን አስተናግዷል:: ግን ተስፋ ቆርጦ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም።

በ1994 ስለ ኢንተርኔት ሰማ። በ1995 ከትውልድ አገሩ ቻይና ወደ አሜሪካ ባጋጣሚ ያቀናል:: በዚህም ጊዜ በጓደኛው እርዳታ ስለ ኢንተርኔ ምንነት ማወቅ ቻለ። ኢንተርኔትን እንዳወቀ መጀመርያ የፈለገው ቃል "beer" የሚል ነበር። በዚህም ስለ ቢራ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ አገሮች ያገኝ ቢሆንም ከአገሩ ቻይና ግን ምንም አይነት መረጃ ማግኝት አልቻለም።

በዚህም ተበሳጨና ስለ ቻይና አጠቃላይ መረጃ መፈለግ ተያያዘ አሁንም ውጤቱ 0 ነበር። በዚህም ቁጭት ከጓደኛው ጋር ሆኖ ሰለ ቻይና መረጃ የሚሰጥ ድህረ ገጽ ፈጠሩ፡፡ ድህረ ገጽ በተከፈተ በአምስት ሰዓት ውስጥ ከተለያዩ ቻይናዊያን የአብረን እንስራና እንተዋወቅ ጥያቄዎች ቀረቡለት። በዚህም ኢንተርኔት አዋጭ ስራ እንደ ሆነ ተገነዘበ፡፡ እንደዚህ እያለ የአለማችንን ግዙፍ ተቋም የሆነውን ALIBABA GROUP ለማቋቋም በቃ፡፡ አሁን የ 25.6 billion USD ቢሊየን ዶላር የተጣራ ተቀማጭ እረብጣ owner የሆነው ማክ የአለማችን 45ተኛ ቱጃር ነው። በማንኛውም ሁኔታ በምንም ምክንያት ተስፋ አትቁረጥ ዛሬ ባይሳካ ነገ ሌላ ብሩህ እና መልካም ቀን ነው።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

27 Oct, 11:12


ሳንፎርድ፡ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ለ ቤትዎ

ጥራት እና ጥንካሬ መለያችን የሆንን ሳንፎርድ ፈርኒቸር ለቤትዎ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ይዘን ከች ብለናል።

ሶፋ ፣ አልጋ ፣ የቲቪ ማስቀመጫ ፣ የመመገብያ ጠረጰዛ እና ወንበር ዲዛይኖቻችንን ከምቹነት ከጥራት እንዲሁም ከውቤት ጋር የተጣመሩ ናቸው።

ከ15 አመት በላይ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እርሶዎን በሚመጥን ዋጋ ቤቶትን እናሳምርልዎ!!!

አሁኑኑ ይደዉሉ ፦ +251978777775 +251976777775

Ethiopian Digital Library

27 Oct, 06:29


C++ ኘሮግራሚንግ በአማርኛ ክፍል አንድ (C++ Programing In Amharic Part I)

https://t.me/ethiopian_education2

Ethiopian Digital Library

27 Oct, 06:02


" መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ እኛ መኖር ከብዶናል !! " - መምህራን

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን አድርጎ ነበር። የማህበሩ ስብሰባ ላይ

👉 መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣
👉 ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣
👉 በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣
👉 ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት፣
👉 ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣
👉 በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣
👉 የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች ...ወዘተ በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተው ነበር።

በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የትምህርት ሚንስቴር አመራሮች ተገኝተው ምላሽ እንደሰጡ በማህበሩ ተገልጿል። ስብሰባው የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀው።

ይህንን የማህበሩን ስብሰባ መደረግ የሰሙና ማህበሩም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠውን ቃል ያነበቡ በርካታ መምህራን መልዕክታቸውን ልከዋል። ላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ መምህራን ፥ " እኛ መግለጫና የማይጨበጥ ወሬና መስማት ሰልችቶናል የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

" እኛ መኖር ከብዶናል !! ስብሰባ ከዛ መግለጫ ምን ይሰራልናል ? ምን ያህል ዋጋ እየከፈልን እንዳለን እኛ ነን የምናውቀው ልጅ ማሳደግ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር እጅጉን ፈተና ከሆነብን ሰንብቷል " ሲሉ ገልጸዋል። " ይህ ማህበር በየጊዜው መግለጫ ነው የሚሰጠን ምንድነው ጠብ የሚል ስራ የተሰራው ? ይሄን ይመልሱልን " ሲሉ ጠይቀዋል።

" መግለጫና ወሬ ምንድነው የሚሰራልን ? ችግራችንን ደጋግሞ መናገር መፍትሄ ከሌለው ጥቁሙ ምን ላይ ነው ? የማይታወቅ ችግር ያለ ይመስል ሁሌ አንድ አይነት ነገር መናገር ያሰለቻል ደክሞናል " ብለዋል።

" መብታቸውን የእንጀራ ጥያቄያቸውን የላባቸውን ደመወዝ ስለጠየቁ ብቻ መምህራን መታሰራቸውን ሰምተናል ይህ ሲሆን እንኳን መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም " ሲሉ አማረዋል። ቃላቸውን የሰጡ መምህራን ፥" በሚዲያው መግለጫ ሳይሆን ተግባራዊ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ ብቻ ነው የምንፈልገው " ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

" ሰራተኛው ኑሮው ቢከድበውና የሚጮኽበት እዲሁም ችግሩን ሰምቶ መፍትሄ የሚሰጠው ቢያጣ ነው ወደሚዲያ የሚቀርበው ስለዚህ እባካችሁ ድምጻችንን ይሰማና መፍትሄ ስጡን " ሲሉ አክለዋል።

Credit: tikvahethiopia

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

26 Oct, 12:26


ያለንበት ሁኔታ በጨረፍታ!

ሰላም ኤሊያስ እንዴት ነህ? አንድ ነገር ላነፃፅርልህ የንግድ ባንክ ሰራተኛ በተቀጠረ በ 1 ዓመት ከ 7 12,ዐዐዐ የተጣራ ደሞዝ እጁ ላይ ደርሶ ለመኖር እየታገለ ነው፡፡ የኔን ልንገርህ :የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ። የት/ት ደረጃ MA ኮሙሌቲቭ 3.97 አለኝ ከ6 አመት በላይ ሰርቻለሁ 2ዐ አመት የሠራ ሌክቸረር ቢሆንም እጁ ላይ 9965 ብር ይደርሳል።

PhD ለመማር NGAT አልፌ ነበር ግን ለበለጠ ሰቆቃ ለምን ልማር? ቡና አትጠጣም ጫማ አታስጠርግም አታስቀባም ልብስ ታናናሾችህ የጣሉትን ትለብሳለህ ከቤት ጠዋት ትወጣለህ ማንንም ሳታገኝ ወደቤት ምግብ ቅናሽ ቤት ተደብቀህ እየተሳቀክ ትገባለህ ሌላው ይቅር የባጃጅ የለህም በእግር ሁሌም ተማሪ ጋ ሚስኮል ነው የምናረገው ብልህ ታምናለህ። ባይገርምህ መማሬን ረገምኩት ኤሊ!

Credit: Elias Meseret

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

26 Oct, 10:08


#ማሳሰቢያ

የዳግም ምዝገባ ለመመዝገብ ያልቻላችሁበትን ምክንያት ለባለሥልጣን መ/ቤቱ በደብዳቤ እንድታሳውቁ


ባለሥልጣን መ/ቤቱ የዳግም ምዝገባ የሰነድ ማሰባሰቢያ የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ተቋማት በወጣው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ተደርጎ በዚሁ አግባብ የወጣውን የጊዜ ሰሌዳ በየቀኑ ያሳወቅናችሁና እና በተቀመጠላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የዳግም ምዝገባ ሰነድ እንድታስገቡ በማህበራዊ ገጾቻችን በተደጋጋሚ ያሳወቅን ቢሆንም ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረ ተቋማት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጥተው ያልተመዘገባችሁ መሆኑ ታውቋል፡፡

በመሆኑም በዳግም ምዝገባ የሰነድ ማሰባሰቢያ የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ያልተመዘገባችሁ 102 ተቋማት ከሰኞ ጥቅምት 18 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወቅቱ ለመመዝገብ ያልቻላችሁበትን በቂ ምክንያት ለባለሥልጣን መ/ቤቱ በደብዳቤ እንድታሳውቁ እያሳሰብን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማያመለክት ተቋም አንቀጽ 2(11) መሠረት ከባለሥልጣኑ የወሰደው የማስተማር ፈቃድ በገዛ ፈቃዱ እንዳቋረጠ ተቆጥሮ የሚነጠቅ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በኢፌድሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

26 Oct, 06:07


በወላይታ ዞን መምህራን በፖሊስ እየታሠሩ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶይቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል

እስሩ የተፈፀመ ያለው መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል። ፖሊስ መምህራኑን የሚያስረው፥ "አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል፤ የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል" በሚል መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ለደህንነታችን ሲባል ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሌላ ሁለት የዚሁ ወረዳ ነዋሪዎች ባሎቻቸው ደሞዝ ይሰጠን ብለው የዳቦ ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ታሰረውብናል ብለዋል።

"የመምህራን ደሞዝ ይከፈል" በሚል የፊርማ ማሰባሰብ ስራ ሲያከናውኑ ከነበሩት መካከል 3 በቅርብ የሚያውቋቸው መምህራን መታሰራቸው የተናገሩ አንድ የዳሞት ወይዴ ወረዳ መምህር አስተባባሪዎቹ ከመታሠራቸው በፊት "እረፉ" የሚል መልዕክት ከወረዳው አመራሮች ተልኮባቸው እንደነበር ጠቁመዋል።

የወረዳው እና የዞን ኃላፊዎች ለቀረበው ክስ ምላሽ አልሰጡም። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለሬድዮ ጣቢያው ፤ "መምህራን ደሞዝ የመጠየቅ መብት መንግሥትም የመክፈል ግዴታ አለበት፤ የደሞዝ ጥያቄ በማቅረባቸው እሥርና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል የሚል መረጃ እስከአሁን እኛ አልደረሰንም፤ ነገር ግን ድርጊቱ ተፈጽሞ ከሆነ ትክክል አይደለም፤ እኛም የምንታገለው ይሆናል" ብለዋል። #DW

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

25 Oct, 09:50


አሁን እየሰራ ነው - የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ #ምደባ

Website: https://placement.ethernet.edu.et

Telegram: https://t.me/moestudentbot

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

25 Oct, 07:41


የሰርቨር መጨናነቅ ተፈጥሮ ስለሚሆን ደጋግማችሁ ሞክሩት አሁን እየሰራ አይደለም!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

25 Oct, 06:40


ሀሰተኛ የ8ኛ፣ 10ኛ፣ 12ኛ ክፍል፣ ዲፕሎማ፣ ዲግሪ እና ማስተርስ የትምህርት ማስረጃዎች
             
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ዝግታ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ አንድ ግለሰብ  ልዩ ልዩ ማህተሞችና ቲተሮችን በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደሚያዘጋጅ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በጥናት ላይ የተመሠረተ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ከሰራ በኃላ የተገኘ ውጤት መሆኑን  ከፖሊስ መምሪያው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፖሊስ ተገቢውን የህግ ስርዓት ተከትሎ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ/ም  በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባደረገው ብርበራ በርካታ የተዘጋጁ እና ሊዘጋጁ የተሰናዱ ሀሰተኛ ሰነዶችን እንዲሁም ግለሰቡ  ሀሰተኛ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምባቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችም ተይዘዋል፡፡

ተጠርጣሪው ሀሰተኛ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምባቸው የመንግስትና የግል ተቋማት 51 ክብ ፣ 73  የግርጌ ማህተሞች፣ አምስት ፕሪንተሮች ፣ አንድ  ኮምፒተር፣ አንድ  ላፕቶፕ  እንዲሁም   በሃሰተኛ መንገድ የተዘጋጁ  የ8ኛ ፣ የ10ኛ እና  የ12ኛ ክፍል እንዲሁም የዲፕሎማ፣   የዲግሪ፣  የማስተርስ የትምህርት ማስረጃዎችን በተጨማሪነት መያዙን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ በሀሰተኛ ሰነድ አማካኝነት የሚፈፀሙ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመከላከል ህገ-ወጦችን ተጠያቂ የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቆ የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባና ተቋማት ለተለያዩ ጉዳዬች የሚቀርቡላቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት ሊያረጋግጡ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ 

መረጃው የአዲስ አበባ ፖሊስ ነው

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

24 Oct, 19:08


ለሪሚዲያል ተማሪዎች - 100% ከማዕከል

ከዚህ በፊት ለሪሚዲያል ተማሪዎች በተቋማት የሚሰጠው ውጤት 30% ሲሆን 70% ደግሞ የሚሰጠው ከት/ት ሚኒስቴር ነበር።

አሁን ግን ይህ አሠራር ተሻሽሎ 100% ከማዕከል (በትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጡ ምዘናዎች) በኩል እንዲሰጥ ተወስኗል።

ተማሪዎች በሚማሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው 30% የውጤት ምዘና  አሰጣጡ ወጥነት ስለሚጎድለው ይሄን ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አክሎ ገልጿል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

24 Oct, 16:53


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ወደ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ገብተው የሚሰለጥኑ አዳዲስ ሰልጣኞችን ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀበል አስታውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለሚገቡ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል።

የኦንላይን ምዝገባው ከዛሬ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት ይካሔዳል።

ሰልጣኞች በከተማዋ በሚገኙ 14 የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተዘጋጀው ሊንክ በመግባት ምዝገባ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል፡፡

በከተማዋ በዚህ ዓመት ከ23 ሺህ በላይ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከደረጃ 5 እስከ ደረጃ 2 ስልጠናዎችን እንደሚከታተሉ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ገልጿል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

24 Oct, 14:05


#ምደባ

አሁን እየሰራ አይደለም ሌሊት ሞክሩት! It is not working now!

👉Website: https://placement.ethernet.edu.et

👉Telegram: https://t.me/moestudentbot

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

24 Oct, 14:01


የሪሜዲያል ምደባም በቅርቡ ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

24 Oct, 12:51


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ #ምደባ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

Website: https://placement.ethernet.edu.et

Telegram: https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። #MoE

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

24 Oct, 10:49


መምህሩ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ በተከራየበት ቤት ውስጥ ተደብቆ በመቀመጥ በአጋች ሃይሎች ታግቻለሁኝ በማለት ከቤተሰቦቹ በርካታ ገንዘብ የጠየቀው መምህር በቁጥጥር  ስር መዋሉ ተገልጿል።

የነቀምት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የላከው መረጃ እንደሚያመላክተው  ተጠርጣሪ  ሰለሞን በንቴ የተባለው  የነቀምት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር  የሆነው ግለሰብ ከጎደኛው ጋር በመነጋገር በተከራየው ቤት ውስጥ ተደብቆ በአጋች ሃይሎች  እንደተያዘ በማስመሰል ለማጭበርበር   መሞከሩ  ተገልጿል ።

ግለሰቡ በጎደኛው ለቤተሰቦቹ በማስደወል 1 ሚሊዮን ብር  እንዲልኩ  መጠየቁ ተረጋግጧል ። ተጠርጣሪው  ወደ ባለቤቱ ስልክ በማስደወል  መታገቱን  በመግለጽ እንዲሁም በተጨማሪ  የባለቤቱ  እህት የሆነችው እና ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ የምትኖረዋን ግለሰብ በማስደወል  በሶስት ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን ብር እንድትልክ በተደጋጋሚ እየደወሉ  ሲያስጨንቋት እንደነበረም ተገልጿል።

የተጠርጣሪው  ቤተሰቦች ገንዘቡን  መክፈል ባለመቻላቸው ጉዳዩን ለፖሊስ  በማስታወቅ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪው ከነተባባሪው በቁጥጥር  ስር ሊውል ችሏል።

ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን እና በቅርቡ መዝገቡ ውሳኔ እንደሚያገኝም የነቀምት ፖሊስ የላከው መረጃ ያመላክታል። #ብስራት_ሬዲዮ_እና_ቴሌቪዥን

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

24 Oct, 09:40


በመምህርነት ለመቀጠር ሰባ ሺህ (70,000) ብር ጉቦ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመምህርነት ለመቀጠር ሰባ ሺህ (70,000) ብር ጉቦ እየተጠየቀ ነው :: በዚህም ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው ጭምር ጉቦ ከፍለው እየተቀጠሩ ነው ተብሏል:: #MeseretMedia

Source: Link

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

23 Oct, 18:16


ለሌባ መርዶ ለስልክ ባለቤቶች መልካም ዜና ነው ተብሏል

ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አሳወቀ።

ኩባንያው ኤአይን (AI) በመጠቀም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች ወደ ስልኩ አምራች ተቋም ሪፖርት የሚያደርጉበት አሰራርን ዘርግቻለሁ ብሏል

አዲሱ የጎግል አሰራር የስልክ ንጥቂያ ወንጀሎችን ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል።

እንደ አልዓይን ዘገባ ከሆነ ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩ እና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡

ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡ #alain

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

23 Oct, 09:22


ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በ7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

👉ኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር 24.83 ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎችን በማፍራት ከአፍሪካ 7ኛዋ ሀገር ሆናለች።

👉ናይጄሪያ 103 ሚሊዮን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን በማፍራት በአፍሪካ 1ኛ ነች።

👉ከናይጄሪያ በመቀጠል ግብፅ ስትሆን 82.01 ሚሊዮን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አሏት።

👉ደቡብ አፍሪካ 45.34 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን በማግኘት በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። #Capital

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

22 Oct, 16:00


በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ እና የማህብረሰብ ት/ቤቶች

International and community schools in Addis Ababa and regions of Ethiopia

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

21 Oct, 18:42


👉 “በመርካቶ የደረሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር አዳጋች በመሆኑ ሂሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን ነው!” - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

👉 ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ገደማ የተነሳውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር የተቻለው፣ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት በኋላ እንደነበር ታውቋል።

👉በአደጋው በ7 ሰዎች ቀላል፤ በ2 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል!

👉"በቃጠሎው ወቅት ዘረፍ ሲያከናውኑ የነበሩ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዘናል" ፖሊስ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethiopian Digital Library

21 Oct, 16:49


#Final

ከጥቅምት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የደሞዝ ማሻሻያ @ethiopia

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library