✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽ @muslimchannel2 Channel on Telegram

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

@muslimchannel2


           。➴ 。 💡 *    ✧
              。\ | /。 ★
        ೃ✧ ለኡማው ማስታወሻ 💌 ೃ✧
          ★ 。/ | \。 ✧
            。✒️ 。   。    ✫

    -;👥 .° [ @Muslim_group2 ] ୭

─────⊱◈🌟◈⊰─────
┊ ┊ ┊ ┊ ┊
┊ ┊ ✫ ˚♡ ⋆。
🔸
⊹.
📬:አስተያየት ༻

「 @Muslim_comment_bot 」

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽ (Amharic)

እንኳን ወደ Muslim Channel እንደሚሆን እናመሰግናለን! ይህ ቡድን የኢስላማዊ አስተምህሮት ግንዛቤን መጨመር የምንችላቸው ቅድሚያ ስለመሆኑ ይታወቃል ። የታተሙ አጠቃላይ ቡድኖችን በምግብ በትምህርት ችላሉ። ከታሪክ ማህደር, አፖች, ከተማይት መድረስ የመሳሪያ ውድድር የግሩፓ የተዘጋጀ መረጃዎችን ለመስራት መደበኛዎችና ሰባኪዎች አፈላላይ ቡድኖች እንዲከብሩ ይረዳል። ለመሆኑ እናመለከታለን። የቡድን መግቢያ እናመሰግናለን! ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉ ✓ @Muslim_group2

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

25 Jan, 12:43


#ማስታወሻ ✉️

:ቁንጅና ለትዳር ዋስትና አይሆንም።

:መታመም ማለት ትሞታለህ ማለት አይደለም።

:ሃብታም መሆን የጥሩ እድል ትርጉም አይደለም።

:ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር የድሎት ምንጭ አይሆንም።

:ጥሩ መኪና መንዳት ለምትደርስበት ቦታ ዋስትና አይሰጥህም።

:ለቤተሰብህ ዶክተር ብትቀጥር ቋሚ የጤና ዋስትና አይኖርህም።

:ብዙ መማር ጥበበኛ አያደርግህም።

:ሀብታም ማግባት ለደስተኛ ለህይወት ማረጋገጫ አይሆንም።

:ክርክር ማሸነፍ ትክክል መሆን አይደለም።

💡ጀነት የማያሸልም ምንም ነገር ብትሰራ
ጊዜያዊ እና ውሸት ነው። ያለ አምላክ የሚራመድ ሰው ነው፣ አንተ በራስህ ላይ ስልጣን የለህም አንተ ሰውነትህን ታያለህ እሱ ደምስርህን ያያል። ሁሉም ነገር ለርሱ ይቻላል በሁሉም ነገር ውስጥ
#ጌታህን_ጣልቃ አስገባ።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

23 Jan, 12:13


❤️‍🩹

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

22 Jan, 10:36


#💡

:ለበደለህ ሰው አፉ ካላልከው የቂያም ቀን ከመልካም ስራው ትወስዳለህ።

💡አፉ ካልከው ግን ቸር ከሆነው ጌታህ  አጅርህን ታገኛለህ።

 
🔘فمن عفا وأصلح فأجره على الله

🔘ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡(42:40)

ከሁለቱ ከባዱ አጅር የትኛው ነው ?

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

18 Jan, 17:42


🦋

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

11 Jan, 07:45


ከነቢዩ ﷺ ዑመት ትሩፋቶች(በጥቂቱ)

¹:ከነቢዩ በፊት የነበሩ ህዝቦች በቀን 50 ፈርድ(ግዴታ) ሰላት ነበር የሚሰግዱት። #ለነቢዩ ﷺ ግን ሸሪዓውን ሰፊ አድርጎት በቀን 5 ሰላት ነው የሚሰገደው አጅሩም የ50 ሰላት ያህል ነው።

²:ዘካንም በተመለከት የዒሳ(ዓለይሂ ሰላም) ህዝቦች 1/10ኛውን ነበር የሚሰጡት። በነቢይ ሸሪዓ ግን የ1/10ኛ እሩቡን ነው የምንሰጠው። ለምሳሌ አንድ ሰው 100,000ብር ቢኖረው በዒሳ ጊዜ ዘካ ልስጥ ቢል የሚሰጠው 10,000 ብር ነው። በነቢዩ ﷺ ሸሪዓዊ ፍርድ መሰረት ግን 2500 ብር ብቻ ነው የሚሰጠው።

³:ፆምን በተመለከተም ያለፉት ህዝቦች እስከነ ሌሊቱ ጭምር ነበር የሚፆሙት ምሽት ላይ መብላት አይችሉም ነበር ፤ ከተኙም ተነስተው መመገብ አይችሉም ነበር። የነቢዩ ﷺ ዑመት ግን ከመግሪብ ጀምሮ እሰከ ፈጅር ባለው የሌሊት ክፍለ ጊዜ ውስጥ መብላት ይችላሉ።

➡️የታመመ ሰው በጊዜው መፆም አይወጅብበትም ሌላ ጊዜ መፆም ይችላል።

➡️ጭራሽ በሽታውም የማይድን ከሆነ ምግብ ለሚስኪኖች ይመግባል።

➡️ጭራሹንም በሽታ የማይለቀው ዛሬ ነገ እፆማለሁ እያለ ዐመታትን ቢቆይ እና ድንገት ቢሞት ያ ሰው ምንም አይኖርበትም።

⁴:ነጃሳ የነካው ሰው ልብሱን አጥቦ ማስወገድ ይችላል። የድሮ ህዝቦች ነጃሳ ከነካቸው ቆርጠው ነበር የሚጥሉት።
. . .etc

ከነቢዩ ﷺ በፊት የነበሩ ህዝቦች ከባድ ሸክሞች ነበረባቸው። ለነቢዩ ﷺ ግን ይህን በሙሉ አንስቶላቸዋል።

[ከዛዱል መዓድ የትምህርት መድረክ የተወሰደ]
💭

አልሃምዱሊላህ ! የነቢዩ ﷺ ዑመት በመሆናችን ብቻ ከልብ ልንደሰት ይገባናል !

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

10 Jan, 14:15


"እኔ አንዴ ስልጣኑን ልረከብ እንጅ ፍልስጤምን ገሀነም አደርጋታለሁ"
   ይህ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትላንት ለአለም ያስተላለፈው መልእክት ነው።

የአሏህ ተዐምር ደግሞ ዛሬ የራሱን ሀገር ከተማ አሏህ የምድር ገሀነም እያደረጋት ነዉ በሰደድ እሳት! አልሐምዱሊላህ አልሐምዱሊላህ አልሐምዱሊላህ!


وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡(14:42)

منقول

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

09 Jan, 12:09


🥹

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

08 Jan, 18:12


#ማስታወሻ ✉️

አንተ  ብቻ አይደለህም በህይወት ውስጥ ደክሞህ እሚያውቀው ፣አንተ ብቻ አይደለህም እምታዝነው እና እሚከፋ፣ አንተ ብቻ አይደለህም ብዙ ነገር ፈልገህ ያጣህው

⚡️ለሁሉም ሰው የራሱ ፈተና አለው። ማሸነፍ እሚገባው ጦርነት ለሁሉም አለው።

😀የአንተን መንገድ ከሌሎች ጋር አታወዳድር። የአንተን ስኬት በሌሎች ሚዛን አትለካ። የአንተን ደስታ ሌሎች ውስጥ አትፈልግ። አንተን ከ አንተ ጋር ብቻ አወዳድር። ከትላንትህ የተሻለ ለመሆን ሞክር . . . ከሌሎች ተማር

📈ህልምህን እስከምታሳካው ድረስ ለህልምህ ታገል።ለሄደ ነገር አትጨነቅ የመጣውን ተቀበል እሱ ደስተኛ ያደርግሀል።

منقول

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

08 Jan, 08:40


اليوم قصير

والحياة تسير
📆

والذنوب تزيد
📈


وجهنم تقول هل من مزيد ؟ . . .
♨️

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

07 Jan, 09:36


ኢትዩጵያዊ 🇪🇹

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

06 Jan, 06:10


#ፈገግ_ይበሉ 😁

🔖:ያው እንደሚታወቀው #በሻፊኢይ መዝሀብ ሁሉም ኢባዳዎች ላይ ንያን በንግግር ማስገኘት ሱና ነው።

አቡል ፈድል አለመህዛኒይ የሚባሉ የሻፊኢይ መዝሀብ ተከታይ ናቸው እና አባቱ በጣም ፈቂህ ነበሩ ልጅ አቡል ፈድል እንዲህ ይላል ፦

- አባቴ እኔን መምታት ሲፈልግ በምቱ ላይ ድንበር እንዳያል በፍራት እንዲህ ይል ነበር

"ልክ አላህ እንዳዘዘው አደብ እንዲይዝ ብዬ ልጄን ለመምታት ነየትኩኝ" 

يقول:" نويتُ أن أضربَ ولدي تأديباً كما أمر الله"

እና አባቴ ንያውን ጨርሶ እስኪያሟላ ድረስ ሸሽቼ አመልጥ ነበር ይላል።😂

‌✿・
📚⁺ [ አል ቢዳያ ወኒሃያ ] ୭

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

05 Jan, 08:25


:ስጋ በጣም ተወደደብን ምን ይሻላል? ብለው ሰዎች ኢብራሂም ኢብኑ አድሓምን ሲጠይቁት "አራክሱታ ማለትም በቃ!ስጋ አትግዙ።” ብለው መለሱላቸው።

- አልቢዳያ ወኒሃያ
📚

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

01 Jan, 17:32


💡🤲

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

28 Dec, 08:28


🦋

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

27 Dec, 18:05


:አላህ ለእኛ በጣም ጥሩ የሆነውን ያዉቃል ፣ ጥሩ ነገር ለማግኘት ምርጡ ጊዜንም ቢሆን እሱ ያዉቃል! ሶብር በማድረግ እንጠብቅ፡፡

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

24 Dec, 14:28


ዘመኑ. . .
 
:ወላጆች ለልጃቸው ዲን እና ባህሪ የማይጨነቁትን ያህል ስለ ልብስ እና ምግባቸው አብዝተው ይጨነቃሉ

:ጎረምሦች ቀኑን ሙሉ ሲዝናኑና ሲዘሉ ዉለው ሦስት ረከዓ መግሪብ ለመስገድ ኢማሙ አረዘመብን ይላሉ ৲


#ይገርማል . . .🖱️


:ጠዋት ላይ ሠራተኞች ወደ መንግሥት ሥራ ሲሄዱ ወደ ሞት የሚጓዙ ነው የሚመስሉት ৲

:አውቶቡስ ዉስጥ ለደከሙና በዕድሜ ለገፉ እናት አባቶች የሚነሳ ወጣት እየጠፋ ነው ৲

:በመንገድ ይሁን በመስጊድ የሃይማኖት ሰው ጊዜ ወስዶ የሚማከር አታገኝም ৲

:መንገደኞች የጉዞ ሰዓት እንዳያልፋቸው አላርም ይሞላሉ ለሱብሒ ሶላት ግን ችላ ይላሉ ৲

:ተጠቃሚዎች ለአስተናጋጅ ወፍራም ቲፕ ይሠጣሉ፣  ለነጋዴ መልሱን ይተዋሉ ፤ የተቸገረ ለማኝ ግን አይተው እንዳላየ ያልፋሉ ৲

:ዳዒዎች ለደዕዋ ሥራ አበል ይጠይቃሉ ፣ ዑለሞች የአላህን ዲን በትንሽ ጥቅም ይቸበችባሉ ৲

:ኡስታዞች ራሣቸው የማይተገብሩትን ለሌሎች ይመክራሉ ৲

:መንገደኞች አደጋ በዛ ይላሉ ፤ የጉዞን ህግ አያከብሩም ፣ የጉዞን ዱዓ አያውቁም ৲

:መስጊድ እንሂድ ሲባል ወደ ሰማይ እንውጣ የተባለ ያህል ዳገት ሆኖበት ትንፋሽ የሚያጥረው በዛ ৲

:ተው ሐራም ነው ይቅርብን ሲባል “ሁሉም እየሠራው እኛ ብቻ ለምን ይቅርብን” የሚል በረከተ ৲

:ጉቦን “የሻይ” እኮ ነው ብለው ይወስዳሉ ৲

:ወለድን “ፐርሰንት” ነው” ብለው ይበላሉ ৲

:ሙዚቃን “ነሺዳ” ነው ብለው ይጨፍራሉ ৲

:ኢኽቲላጥን ወንድም እህትማማችነት ብለው ያጠናክራል ብለው አደረጉ ৲

:ሲመክሩት ተቆጪውና ገንፋዩ በዛ ৲

:ሲያስታውሱት አትምከረኝ አውቃለሁ ባይ እንደ አሸን ፈላ ৲

:የሚያውቁ አይሰሩበትም ፤ የማያውቁ ደግሞ አናውቅም አይሉም፡፡

:አቀማመጣችን ተፋልሷል፤ ከፊት መሆን የነበረበት ከኋላ ፤ ከኋላ መሆን ያለበት ከፊት ሆኗል ৲

🔎ታዲያ ምን ይሻለናል ?

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

23 Dec, 08:29


🤍ዳመና የውሃን ክብደት መሸከም ሲያቅተው ዝናብ ይጥላል። ልብም የውስጡን ህመም መሸከም ሲሳነው  አይን እንባ ያፈሳል።

ስሜትህ ሲጎዳ ፣ ልብህ ሲሰበርና ሲጨንቅህ እጅህን ወደላይ ከፍፍ አድርግና ጌታህን ለምነው... እርሱ የለመኑትን አያሳፍርምና!

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

22 Dec, 15:00


እናንተ ሰዎች ሆይ !
ሰላምታን አውርዱ
😀
ምግብንም አብሉ
🍱
ዝምድናንም ቀጥሉ
🫂
ሰዎች ተኝተው ሳለ በሌሊት ስገዱ
🤲
.
.
.
ጀነትን ሰላም ሁናችሁ ትገቧታላችሁ
😀

-ነብዩ ሙሀመድ ﷺ

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

22 Dec, 10:18


🔝

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

21 Dec, 11:02


#የእናትነት_ዋጋ

:ስራ መስራት የማይወድ አንድ ህፃን ልጅ በአንድ ምሽት ኩሽና ወዳለችው እናቱ መጣና አንድ ወረቀት ለእናቱ ሰጣት እጇን በማደራረቂያ ካደራረቀችው በኋላ አነበበችው :: ወረቀቱ ላይ የተፃፈው እንዲህ የሚል ነበር፡-

✓ መኝታ ከፍሌን ላፀዳሁበት 10 ብር

✓ ቆሻሻውን ላወጣሁበት 5ብር

✓ እታከልቶቹን ውሃ ላጠጣሁበት 5ብር

✓ ወደገበያ ቦታ አብሬሽ ለሄድኩበት 10 ብር

✓ ወደ ገበያ ስትሄጂ ትንሹን ወንድሜን የጠበኩበት 10 ብር

✓ ጥሩ ውጤት ላመጣሁበት 10 ብር

ጠቅላላ ከፍያ 50ብር ይመጣል የሚል ነበር፡፡ ይህ ህፃን ልጅ ይህን ሁላ ያቀረበው ስራ መስራት ስለማይወድ እና ስልቹ ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ስራው እንዲቀልለት በማሰብ ነበር፡፡ እናቱም ልጁን ለማስተማር መፃፊያ እስኪርብቶ በማንሳት ወረቀቱ ላይ ከጀርባው እንዲህ የሚል ፁሁፍ ፃፈች ፡፡

ልጄ ሆይ !

➢ ለ9ወር አንተን የተሸከምኩበት ከፍያው ስንት ነው?

➢ አንተን ስጠብቅ ያደርኩባቸው ሌሊቶች ከፍያው ስንት ነው ?

➢ ለአንተ ተጨንቄ ላፈሰስኩት እንባ ከፍያው ስንት ነው?

➢ ለመጫወቻ ፤ ለልብስ ፤ ለምግብ እና ለመሳሰሉት ያወጣሁልህ ከፍያው ስንት ነው?

➢ ያንተን ንፅህና የጠበኩበት ከፍያው ስንት ነው?

➢ ከዚህ ሁሉ በላይ ላንተ ያለኝ ፍቅር ዋጋው ስንት ነው? ብላ ወረቀቱ ላይ ፃፈችለት።

➡️ይህ ሀፃን ልጅ እናቱ የፃፈችውን አንብቦ ሲጨርስ አይኖቹ እንባ አቀረሩ ወደ እናቱ እየተመለከተ ለአንቺ ባሪያ ሆኜ ብሸጥ እንኳ, አንቺ ያደረግሺልኝን ውለታ መከፈል አልችልም ከዚያም እስከሪብቶውን አነሳውና ከእርሷ ፅሁፍ በታች በትልቁ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ፃፈ “በሙሉ ተከፍሏል”።

📜:ዲኒያት
╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

20 Dec, 03:00


❤️

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

19 Dec, 11:24


🔝

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

13 Dec, 17:18


ረሱላችን ﷺ ♥️

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

13 Dec, 16:09


:ቤት የለው፣ሚስት የለው፣ልጅ የለው፣ሥልጣን የለው፣ገንዘብ የለው፣ቤተሠብ የለው......።ታዲያ ምን አለው!ካላችሁ በሶሪያ ደማስቆ ከተማ በኡመውዮች መስጊድ አጠገብ ትንሽ የአንገት ማስገቢያ ጎጆ ነበረችው። በሷ ውስጥ ተረጋግቶ የደስታ ኑሮ ይኖራል።አልፎ አልፎም መስጊድ ገብቶ ይተኛል።ወደዚህች ዓለም ለእንግድነት ብቻ የመጣ ትክክለኛ እንግዳ ነበር የሚመስለው። በቀን እንዴ ቢበላ አንድ ዳቦ ቢያገኝ ነው። ከልብስም ሁለት አለው፤አንዷን በሌላኛው ይቀይራል።

🗓:የሆነ ጊዜ የአገሬው ገዥ ሊያስረው እንደሚፈልግ ተነገረው። እሱም በቆራጥነት መንፈስ እንዲህ አለ

❝የትም ብሆን እኔ ወላሒ እንደተመቻት የሱፍ በግ ነኝ።ደስታዬን ማንም ሊነጥቀኝ አይችልም። ቢያስሩኝ እስር ቤት ለኔ ገዳሜ ነው ብቻዬን ተገልዬ አላህን እገዛበታለሁ፤ከሀገር ቢያስወጡኝ ለኔ ቱሪስትነት ነውተፈጥሮን አይቼ የአላህን ችሎታና ጥበብ በማድነቅ አስተነትናለሁ።ከዚህም አልፌ ሰዎች ወደ እስልምና እንዲገብ እጣራለሁ።ቢገድሉኝ ምን ይቀርብኛልን?!በአላህ መንገድ ሸሂድ መሆን የሁልጊዜ ምኞቴ ነውና

🔆:ይህ ሰው ማን መሰላችሁ?

𖥉 ሸይኽ አል ኢስላም ሙሐመድ ኢብን ሱለይማን አት-ተይሚይ (ኢብን ተይሚያህ)
𖤿

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

11 Dec, 03:13


:ኢማሙ ሻጢቢይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«የወንጀሉን ትንሽነት አትመልከት፣ ነገር ግን የምታምፀውን አካል ትልቅነት ተመልከት።»

📚سـيـر أعـلام النبـلاء

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

05 Dec, 11:17


🦋

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

02 Dec, 10:59


#የስራ_ክቡርነት 📈

:የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) በመስጊድ ውስጥ ቁርኣን ለሚቀሩ ነገር ግን ለማይሠሩ ሰዎች እናንተ "ቁራኦች ሆይ! ተነሱና ርዝቅ ፈልጉ ፤ በሰው ላይ ሸክም አትሁኑ" ብለዋል። (ኢማም በይሀቂ እንደዘገቡት)

:"ቂያማ አሁን ልትቆም ነው ቢባል እንኳን በእጅህ ያለችውን ችግኝ ከመትከል ወደኋላ አትበል" ብለዋል፡፡ (ኢማም አህመድ እና ሌሎች በዘገቡት መሰረት)

:ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) በመስጊዱ ውስጥ ለተሰበሰቡ ወጣቶች ውጡና ርዝቅ ፈልጉ /ሥሩ/ ሰማይ ወርቅ አሊያም ብር አታዘንብም፡፡' ይሉ ነበር።

:ሁሉም ነቢያት ሠርተው ያለፉት ሥራ ፍየል ወይም በግ ማገድ ነው።

:ነቢዩ ዘከሪያ (ዓለይሂ ሰላም) አናፂ ነበሩ። ነቢዩ ዳውድ (ዓለይሂ ሰላም) የላባቸውን ውጤት የሚበሉ ጎበዝ አንጥረኛ ነበሩ።

:ነቢያችን (ﷺ) በልጅነታቸው በግ ያገዱ ሲሆን በወጣትነታቸው ደግሞ ለንግድ ወደ ሻም ሀገር ይመላለሱ ነበር

:በእጁ ሠርቶ ከሚያገኘው ወዛደር የሚወጣው የላብ ሽታ ፤ ከሥራ ፈት ሽቶ በላይ ያውዳል።

:የቀን ሠራተኛ አንደበት የሚወጣው የሥራ እንጉርጉሮ ከሰነፍ መዝሙር በላይ ይማርካል።

:"የሰውን እጅ ከማየት በመርፌ🪡 መሬት ቆፍሬ ብዘራ ፤ ሁለት ባሮችን ከጥቁር ወደ ነጭ ለማንፃት በማጠብ ሥራ ብሰማራ ይሻለኛል።"( አንድ ሷሊህ ሰው)

📖:አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል➘

🔹:هُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ ذَلُولًا فَامْشُوا فِي مَنَاكِبِهَا وَكُلُوا مِن رِّزْقِهِ ۖ وَإِلَيْهِ النُّشُورُ

🔸:እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው፡፡ በጋራዎችዋና በመንገዶችዋም ኺዱ፡፡፡ ከሲሳዩም ብሉ፡፡ (ኋላ) መመለሻውም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡(ሙልክ : 15)


╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

01 Dec, 09:04


#ግብረሰዶም (LGBTQ+)

:አላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

«በዑመቴ ላይ በጣም የምፈራው የሉጥ ህዝቦችን ተግባር ነው።»[ቲርሚዚ]

:እንደሚታወቀው ሶዶምነት ወይም በሁለት ወንዶች መካከል የሚደረግ የግብረ - ሥጋ ግንኙነት ሶዶምና ገሞራ የተባሉ የነቢዩ ሉጥ(ዓለይሂ ሰላም) ሕዝቦች የጀመሩት #ወንጀል ነው፡፡

📍:አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) እንዲህ ይላል፦

🔹:وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ

🔸:ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡

🔹:أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ وَتَقْطَعُونَ السَّبِيلَ وَتَأْتُونَ فِي نَادِيكُمُ الْمُنكَرَ ۖ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتِنَا بِعَذَابِ اللَّهِ إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ

🔸:«እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን መንገድንም ትቆርጣላችሁን በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን» (አላቸው)፡፡ የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡[29:28-29]

👍:ከወንጀሉ አስቀያምነትና ክብደት የተነሳ አላህ(ሱብሃነሁ ወተዐላ) እነዚያን የነቢዩ ሉጥ(ዓለይሂ ሰላም) ሕዝቦች ያጠፋቸው በአራት ዓይነት ታላላቅ ቅጣቶች ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የዚህ ዓይነት የከበደና የተደራረበ ቅጣት በሌላ ሕዝብ ላይ ደርሶ #አያውቅም። እነዚህ ቅጣቶችም፦

¹
🔹:የነቢዩ ሉጥ(ዓለይሂ ሰላም) ሕዝቦች ዓይናቸው ታውሮ ነበር፣

²
🔹:ተጠብሰው የተደረደሩ የድንጋይና የሸክላ ጠጠሮች ከወደ ሰማይ በነርሱ ላይ ዘንበው ነበር፣

³
🔹:ነጓድጓዳማ ጩኸት በድንገት ደርሶባቸው ነበር፣

🔹:ከተማቸው ከላይ ወደታች ተገልብጣ ነበር።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

30 Nov, 11:10


🥹

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

28 Nov, 18:16


:የአንተ ሀጢያት የሚያልቅ ነው፡፡ የአላህ #እዝነት ግን ማለቂያ የለውም፡፡ ወንጀልህ የፈለገውን ያህል የከበደና የገዘፈ ቢሆንም አንዳች ደረጃ ላይ ሲደርስ ያበቃል፡፡የሀያሉ አላህ እዝነትና ርህራሄ ግን ሰፊ የሆነና ማለቂያ የሌለው ነው፡፡ አላህም እንዲህ ይላል ፦

╔╦══• • •❀
🌼 ❀• • •══╦╗
... ችሮታዬም ነገሩን ሁሉ ሰፋች ፤...
      / | አል አዕራፍ ፡ 156 | \
╚╩══• • •❀
🌼 ❀• • •══╩╝

🔎:የሀያሉ አላህ እዝነት የፈለገውን ያህል የገዘፈ ቢሆን እንኳ ሀጢአቶችን ይደመስሳል⚡️

-ማለቂያ የለሽ የሆነን ነገር አላቂ ነገር ሊበግረው አይችልምና
!

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

27 Nov, 17:48


#ማህበራዊ_ሚዲያ ™️

➡️:ታላቁ አሊም ሼኽ ሷሊሀል ፈውዛን እንዲህ ይላሉ৲

«የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ልትማርኩት የሚገባ ትልቅ እድላቹ ነው ወደጥመት ለሚጣሩ ተጣሪዎችና ለሸረኞች (በፍፁም) እንዳትተውላቸው ይላሉ »

📚:أهمية العقيدة الصحيحة (١٤٣٧/٧/٢٣)

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

27 Nov, 05:17


#✉️

:ከአዋቂዎችም ከሞኝም ጋር አትከራከር። አዋቂ ያሸንፍሃል፤ ሞኝ ደግሞ ያበሳጭሃል።

:የበታቹን የናቀ ግርማ ሞገሱን (ክብሩን) ያጣል።

:የእውቀት መጀመሪያ ዝም ማለት፤ ከዚያም መስማት፤ የሰማውን መያዝ፤ ከዚያም መስራት፤ በመቀጠል ማሰራጨት ነው ።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

25 Nov, 11:41


💡

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

23 Nov, 15:52


#Uzbekistan 🇺🇿

:#ዩዝቤኪስታን ከ97% በላይ ዜጎቿ ሙስሊሞች ናቸው። ይህም የሙስሊም ሀገር ውስጥ እንድትመደብ ያደርጋታል። የምንሰማው ነገር ግን ተገላቢጦሽ ነው።

አንዲት ሴት ቁርዐንን ለህፃናት በማስተማሯ ብቻ ለ15 ቀናት እስር ተፈርዶባታል። ምን ጉድ ነው ግን ?🤔

ʳᵉᵃᵈ ᵐᵒʳᵉ
╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

22 Nov, 19:10


♥️

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

21 Nov, 18:01


#የጁምዓ_ሱና_ሰላት 🖥

:ከጁምዓ በፊት የሚሰገድ መደበኛ ሱና የለም፡፡ ነገር ግን ወቅቱ ከመድረሱ በፊት መደበኛ ያልሆነ ሱና ቢሰግድ ምንም ችግር የለውም ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) በጥቅሉ ሱና መስገድን አበረታተዋል፡፡ ከጁምዓ በኋላ ግን መደበኛ የሆኑ ሁለት፣ አራት ረከዓ ወይም ስድስት ረከዓ ሱናዎችን እንደሁኔታው ሊሰገድ ይችላል፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ባስተላለፉት ሀዲስ

💡¹‹‹ነብዩ (ﷺ) ከጁምዓ በኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር››[ቡኻሪ ሙስሊም]

በሌላ ሀዲስ ደግሞ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

💡²‹‹ ከጁምዓ በኋላ አራት ረከዓ ሱናዎችን ስገዱ››[ሙስሊም]

ኢብን ዑመርም ከጁምዓ በኋላ ስድስት ረከዓዎችን ይሰግዱ እንደነበር ‹‹ነብዩ ይፈፅሙት ነበር››[አቡዳውድ]እንዳሉ አቡዳውድ ዘግበዋል፡፡

➡️በዚህ መሰረት ከጁምዓ በኋላ የሚሰገድ መደበኛ ሱና ከፍተኛው ስድስት አነስተኛው ሁለት መሆኑን እንረዳለን::

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

21 Nov, 02:41


#✉️

1️⃣መስጂድ ቁጭ ብለህ ሰላት በምትጠባበቅበት ወቅት ፣

2️⃣የታመመን ስትጠይቅ ፣

3️⃣በሰላት ላይ የመጀመሪያው ሰፍ ስትቆም ፣

4️⃣ሙስሊም ወንድምህን  ስትዘይር ፣

5️⃣በሩቅ ለወንድምህ ዱአ ስታደርግ ፣

6️⃣ሰዎችን መልካም ነገር ስታስተምር ፣

7️⃣ውዱእ አድርገህ ስትተኛ ፣

🔖በነዚህ ሁኔታዎች እስከሆንክ ድረስ መላኢካዎች ላንተ ዱዓ🤲 ከማድረግ አይወገዱም።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

17 Nov, 19:42


🔝አላህ እንዲህ እያለ ተስፋ ይሰጠናል. . .አጂብ እኮ ነው !

እኛስ ? በሱ መንገድ ላይ ነን ?

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

17 Nov, 12:33


ከአንድ ሰው ጋር በሀሳብ ስላልተስማማን ብቻ ስሙን ለማጥፋት አንሩጥ። በስድብ፣ በሀሜትም ይሁን ዝናውን ለማፈራረስ አንድከም። ክብሩን ለማውረድ አናሲር። ሰላም ለማሳጣት አናውጠንጥን። ሙስሊም የሆነ ሰው ሁለመናው የተከበረ ነው። አላህ መልካም ባሮቹን ሲነኩበት በእጅጉ ይቆጣል። ከቁጣው ፊት ችሎ የሚቆም ካለ ደጋግ አማኞችን ይዳፈር። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በሀዲሳቸው አላህ(ሱብሃነሁ ወተዐላ) እንዲል ብሏል ብለዋል፦

🟠مَنْ عَادَى لِي وَلِيًّا فَقَدْ آذَنْتُهُ بِالْحَرْبِ

🔘አንድን የኔን ባሪያ ጠላቱ አድርጎ የያዘን ጦርነት አውጄበታለሁ

📚‌✿・⁺ [ ቡኻሪ ]

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

16 Nov, 17:11


💡አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) ከዋለልን ፀጋዎች አንፃር ስናይ የመከራ ዕድሜ ትንሽ ነው። እድሜ ልኩን በምድር ላይ ሲንከራተት ኖሮ የሞተ ሰው የለም። ዱንያ አንድ ቀን ብታስለቅሰን አንድ ቀን ልትስቅልን ግድ ነው። የሚገርመው ፍፁም ፍትሃዊ የሆነ ጌታችን አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) በሷ ላይ በሚያገኘን ትንሽም ሆነ ትልቅ ችግር #ምንዳ ለገሰን😌#የመከራ_ምንዳው በጤናና በድሎት ጊዜ ከሚያገኙት በላይ ነው። ከሱ የሚገኘው ልምድም ከየትኛው የህይወት ትምህርት በላይ ነው፤ ጥቅሙም ከማንኛውም ሀብት የላቀ ነው።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

15 Nov, 18:17


#✉️

:አንድ ሰው ሱንና ሶላትን እየሰገድ ሳለ ኢቃማ ከተደረገና ሱናውን ሶላት ቢያጠናቅቅ የግዴታው ሶላት #ተክቢረተል_ኢህራም ኢማሙን ተከትሎ ወዲያውኑ ማለት እችላለሁ ብሎ ካመነ ሱንናውን ያጠናቅቅ። ተክቢረተል ኢህራሙ የሚያመልጠው ከሆነ ግን የሱንናውን ሶላት ያቋርጠው።

ሸይኽ አልባኒ  رحمه الله ፈታዋ ራቢጝ

ይሄ ማድረግ ሶላትን ከማበላሸት ሳይሆን የተሻለውን መልካም ስራ ከመምረጥ ነው የሚቆጠረው።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

13 Nov, 15:35


🌴

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

13 Nov, 13:16


#✉️

🔺ሰዎችን ለማስረዳት ድምፅህን ሳይሆን አነጋገርህን ከፍ አድርግ፣ ተክሎችን የሚያጠጣው ዝናብ እንጅ መብረቅ አይደለም።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

12 Nov, 18:11


#ምኞትሽን_ያሳካልሽ 💐

🌻ልታይ ልታይ በበዛበት የኢስላምን ስም እያጠፉ እርቃናቸውን የሚሄዱ ሴቶች በበዙበት አንቺ የፀሀዩን መክበድ ሳይበግርሽ በሙሉ ሂጃብ ክብርሽና እምነትሽ ለጠበቅሽው #እህቴ አላህ በዱንያም በአኼራ ያሰብሽውን ኸይር ያሳካልሽ . . .🦋

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

11 Nov, 11:35


♥️

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

10 Nov, 17:27


#መልካም_ጥርጣሬ 🦋

:"በጌታችሁ ላይ መልካም ጥርጣሬ ቢኖራችሁ እንጂ አትሙቱ " ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ﷺ። እናም የሙዕሚን አስተሳሰቡ እንዲህ ነው ፦

💡:ብደሀይ ያልፍልኛል*

💡:ብታመም እድናለሁ*

💡:ብፈተን አልፋለሁ*

💡:ባዝን እስቃለሁ*

💡:ብወድቅም እነሳለሁ*

💡:ከርሃብ ቡሀላ ጥጋብ አለ*

💡:ከጥም ቡሀላ እርካታ አለ*

💡:ከእንባ ቡሀላ ሳቅ አለ*

💡:ከድካም ቡሀላ ረፍት አለ*

:አላህም እንዲህ ብሏል ፦

🔸{. . . ﻭَﻣَﻦ ﻳَﻘْﻨَﻂُ ﻣِﻦ ﺭَّﺣْﻤَﺔِ ﺭَﺑِّﻪِ ﺇِﻻَّ اﻟﻀَّﺎﻟُّﻮﻥَ}°

🔹«ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው?»...*።[
#አል_ሂጅር፡56]°
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

10 Nov, 12:02


📉የሙስሊም ቻነሎች Algorithm(አልጎሪዝማቸው) ምን ሁኖ ነው የቀነሰው ?

❤️ቴሌግራም ላይ ያሉ የሙስሊም ቻነሎች ብቻ አይደሉም። እኔ የማቃቸው የYoutube❤️ ኢስላማዊ ቻነሎች በሙሉ በሚያስብል ደረጃ View(እይታቸው)ከሚታሰበው በላይ በጣም ቀንሷል። እኔ ለራሱ እዚህ ቻነል የሆነ ነገር ፖስት ሳረግ ከ24 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ1ሺ - 2ሺ ሰው ያየው ነበር። ነገር ግን አሁን በምፖስትበት ሰዓት 5 ቀን ሁኖት እንኳ ከ1ሺ view(እይታ) አይበልጥም። ይሄ ቻነል ብቻ አይደለም ሌሎችም እንዲህ እየሆኑ ነው።

አልጎሪዝሙ ይሁን ፣ የኛ ከዲን መራቅ ይሁን ወሏሁ ተዓላ አዕለም . . . ዋናው ቁምነገሩ የእይታ ብዛት እና ሼር ሳይሆን ምን ያህል ሰው ነው የሚጠቀመው የሚለው ነው። በእርግጥ View (እይታ) በበዛ ቁጥር በዛው ልክ የሚጠቀሙት እየበዙ ይሄዳሉ በሚል እሳቤ ነው።

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

05 Nov, 20:14


ኑ ጌታችንን እንወቅ

:የሰው ልጅ አዕምሮ አስተሳሰቡ የተገደበ ነው ወይም limit አለው ሲባል አይገባኝም ነበር። ነገር ግን ይሄን ጉድ ስሰማ የአዕምሮ የማሰብ ገደቤን በሚገባ አውቄዋለሁ። እናንተም እዩት የአዕምሮ ገደባችሁን ታገኙበታላችሁ።


©Copyright Free ነው በዚህ Video ላይ(Link አልጨመርኩበትም)

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

05 Nov, 19:21


ያሸባብ

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

30 Oct, 17:43


መከራ ያልፈታው ነቢያዊ ሕይወት 🍃

➣:እኛና አላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

:በምድር ላይ እያለን ጉዳት ደርሶብናል ፤ ብዙ መከራ አይተናል የምንል ሰዎች እስቲ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማስተዋል የኛን እና ከአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ሁኔታ እናነፃፅር፡፡ ምን እንደረሰባቸውና ምን እንደደረሰብን እናመዛዝን

🪴:እናት አባትህ አሉ?

➣:እርሣቸው እኮ ያለ እናትና አባት ነው ያደጉት፡፡ አባታቸው ሳይወለዱ ፣ እናታቸው ደግሞ ገና
#የአምስት እና ስድስት ዓመት ልጅ እያሉ ነበር የሞቱባቸው፡፡

🪴:ልጆችህን አጥተሃል?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሁሉም ስድስት ልጆቻቸው እርሣቸው በህይወት እያሉ  ሞተዉባቸዋል፡፡ ከሴት ልጃቸው ፋጢማ በስተቀር፡፡

🪴:ሥምህ ጠፍቷል አሊያም ተሰድበሃል፣ ተደብድበሃል?

➣:እርሣቸው እኮ ተሰድበዋል፣ ተደብድበዋል፣ ገጣሚ፣ መተተኛ/ደጋሚ ተብለዋል፡፡ የመካና የጣኢፍ ምድሮችም የሚመሰክሩት ይህንኑ ነው፡፡

🪴:በቤተሰብህ የመጣብህ ችግር አለ?

➣:ባለቤታቸው በመናፍቃን በዝሙት ሥማቸው ጠፍቷል፡፡ በዚህም የእርሣቸውም የታላቁ ነቢይ
#ክብር ተነክቷል፡፡

🪴:ዕዳ አለብህ?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሲሞቱ ዕዳ ነበረባቸው፡፡ የጦር ልብሳቸው አንድ አይሁዲ ዘንድ በዕዳ ተይዞ ነበር፡፡

🪴:ተቸግረህ ፣ ተርበህ ታውቃለህ?

➣:ረሱሉ እኮ ከርሃብ የተነሳ ሁለት ሶስት ድንጋዮችን በሆዳቸው ላይ ያስሩ ነበር፡፡ ለምግብ ማብሰያ የሚሆን እሣት በቤታቸው ሳይቀጣጠል ተምርና ውሃ ብቻ እየተመገቡ ወራትን ያሳልፉ ነበር፡፡

🪴:ልጅህ ወይም የቅርብ ዘመድህ ተፈታ በሷ ሥነልቦና ተጎድተህ ታውቃለህ?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እስልምናን በመስበካቸውና የአላህን የሐቅ መንገድ በማሳየታቸው ብቻ ተጠልተው  ሁለት ሴት ልጆቻቸው በባሎቻቸው ተፈተዋል፡፡

🪴:ሳትወድ በግድ ከምትወደው የትውልድ ሀገርህ ተሰደህ ታውቃለህ?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እኮ ተከታዮቻውን ይዘው እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ ተሰደዋል፡፡ ለዓመታትም የስደት ሕይወት ገፍተዋል፡፡ 

🪴:የግድያ ሙከራ ተደርጎብህ ያውቃል?

➣:ነቢዩ (ﷺ) ከአንድና ሁለት ሶስት ጊዜ በላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡

🪴:በአደባባይ ቆሻሻ ተጥሎብህና ተስቆብህ ያውቃል?

➣:
#ነቢዩ እኮ ሰላት በመስገድ ላይ እያሉ ሱጁድ ላይ ሆነው ቆሻሻ ተጥሎባቸዋል፡፡ለዛውም የግመል ፈርስ።

🪴:የእምነት ነፃነትህን ተነፍገሃል?

➣:የአላህ መልዕክተኛ
#ለሶስት አመታት እምነታቸውን ደብቀው ኖረዋል፡፡

🪴:ማዕቀብ ተጥሎብህ ያውቃል?

➣:ረሱሉ እኮ
#ለሦስት አመታት ያህል ማዕቀብ ተጥሎባቸው ከማህበረሰቡ እንዲገለሉ ተደርገዋል፡፡

🪴:አካልህ ላይ ጉዳት ደርሶ ያውቃል?

➣ነቢያችን እኮ ተፈንክተዋል፣ ጥርሣቸው ተሰብሯል፡፡

❦ ════ •⊰
🌴⊱• ════ ❦

📌:ምናልባት አንተን እና እኔን አንድ ችግር አግኝቶን ያንኑ ችግር መቋቋም ተስኖን ይሆናል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ግን ከነኚህና መሰል ብዙ ችግሮች ጋር  ምንም እንዳልሆኑ ሆነው እያመሰገኑ ደስተኛ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዐለይሂ~~~৲
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

29 Oct, 10:43


ሰላት ውስጥ መሳቅ 🔍

📌:ሶላት ውስጥ ብዙ ጊዜ ሳቅ ያስቸግረኛልና ሶላቴን ያበላሸዋልንዴ ፣ ከዚህስ ነገር ምን ባደርግ መከላከል እችላለሁ

#መልስ 💬

¹:ሶላት ውስጥ መሳቅ #ድምፅን በማውጣት ወይም ሁለትና ከዛ በላይ #ፊደላትን በማውጣት ከሆነ ይህ እንደ ንግግር ይቆጠራልና ሶላቱን #ያበላሸዋል። ድምፅና ፊደል የሌለው #ፈገግታ ግን ሶላቱን #አያበላሸውም። ሳቁን መቆጣጠር ያልቻለና #ከአቅሙ_በላይ የሆነ ግን ከፍላጎቱ ውጭ ስለሆነ ሶላቱ #አይበላሽም

²:ሶላት ውስጥ በተደጋጋሚ በመሳቅ #የተፈተነ ሰው ደግሞ በተደጋጋሚ ውዱእ በመፍታት እንደሚቸገር ሰው አይነት ፍርድ ይኖረዋልና ሶላቱ #አይበላሽም። በዚህ የተፈተነ ነው ሶላት ውስጥ #በማስተንተን ፣ ሀሳብን #በመሰብሰብ ፣ አሏህ #ፊት መቆምንና በአሏህም #እይታ ስር መሆንን በማሰብ ሳቅን #ለመከላከል መሞከር ተገቢ ነው።

📗。*。📙
📘。\|/。📒
        ▽{ምንጭ🗂}
📔。/|\。📕
📓。*。🗃 °

[ሸርሁል ሙምቲዕ ፣ ለኢብኑ ዑሰይሚን ፣ 3/366 ፤ ኒሀየቱል ሙህታጅ ፣ ለኢማሙ አሽሻፊዒይ ፣ 3/39 ፤  ኪታቡል ሙግኒ ፣ ለኢብኑ ቁዳማህ ፣ 1/741]

©MJUD
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

27 Oct, 19:11


100 መፅሀፍ 📔

📝:ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነውና #ትዕግስትን በተላበሰ ህሊና ይነበብ፡፡

─━━━━━━⊱
🖱️⊰━━━━━━─

¹:በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።

²:ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንክ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።

³:የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን #አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ #አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል።

⁴:ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

⁵:የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።

⁶:ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት 💡

⁷:ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስክ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።

⁸:ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።

⁹:#እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ።

¹⁰:ሥልጣን ሲሰጥህ #መሪ(leader) እንጂ አለቃ(boss) አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምክ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ። ለበለጠ ለመረዳት👉 ⎡ @Better_understanding

¹¹:በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።

¹²:የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።

¹³:ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! 👏

¹⁴:መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠሉሃል ።

¹⁵:ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።

¹⁶:#ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ።

#እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ~ ⚠️

¹⁷:#ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው።

¹⁸:#ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ #ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ #ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

¹⁹:የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ። የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

²⁰:ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን።

²¹:ሁሉን #ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

²²:#ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።

²³:እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

26 Oct, 08:46


ጀነት ውስጥ . . .🍀

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

23 Oct, 05:56


📨:ወደ መልካም ነገር ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው። መሥራት ባትችሉ አመላክቱ ፣ መፃፍ ባትችሉ ሌሎች የፃፉትን አጋሩ።

↬ዱንያ ላይ የምንቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። ምድር ላይ እንደሁለተኛ ዕድሜ ሆኖ የሚያገለግለን ዛሬ እዚህ የምንጽፈው ነገር ነው። ከሶላታችን ፣ ከፆማችን ምንም ምንዳ ላይኖረን ይችላል። መልካም ነገሮችን ማጋራት ወደ አኺራችን ከምናስቀድማቸው ጠቃሚ ስንቆች መካከል አንዱ ነው። ብልህ እንሁን። አላህ ያፅናን።

🔴 ዓለማዊ ጥቅም አለው ብዬ አልወተዉታችሁም፣ በስነልቦናም ሆነ በዲኑ ጉዳይ ሊጠቀምበት የሚችል ሰው ሊኖር ይችላልና ይህን #ቻናል አጋሩት።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

22 Oct, 16:29


ሙሉ ለማዳመጥ ⬇️

T.me/Muslimchannel2/1843

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

21 Oct, 18:23


#ጭንቀት 😣

💥:በመጨነቅና በማማረር ያመጣነው ለውጥ የለም፡፡ ተነስቶ መንቀሳቀስ እንጂ ዘግቶ ማልቀስ የፈየደን ነገር አላየንም፡፡ በጭንቀት ስንዝር ያህል እንኳን ነገሮችን መግፋት አንችልም፡፡ የጎደለ ኑሮ የሚሞላው #በሥራ እንጂ በጭንቀት አይደለም፡፡ ተጨንቀን ብዙ አየን፡፡ ጭንቀትን ትተንም አየን፡፡ ሰፊ ልዩነቱን በርግጥም አስተዋልን፡፡ ዘና ብለን ስንስቅላቸው ረጃጅም ቀናቶች አለፉ፡፡ ትላልቅ ሸክሞች ረገፉ፡፡ ከባባድ ችግሮችም ተረሱ፡፡ እናም ፈታ በል ፤ ዘና በል፡፡ አትጨነቂ ፣ አትጨነቅ 🦋

:የነገሮች ዋና መሰረታቸው ቀደር ነው፡፡ ቀደር ማለት ደግሞ ቀድሞ የተላለፈ የአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ውሳኔ ነው፡፡ ለተወሰነና ላለፈ ነገር "መዐልኤሽ!" ምንም ማለት አይደለም በል፡፡

❗️ብርጭቆ ሰበረ ብለህ ልጅህን ከቤት አታባርር፡፡

❗️እንጀራው አረረ ብለህ ከሠራተኛህ ጋር ቦክስ አትግጠም፡፡

🔎አንዳንድ ሰዎች ይገርሙኛል ፤ ሳይመቱ ከተመቱት በላይ ይጮሃሉ፡፡ መቶኝ ነበር ፈንክቶኝ ነበር ለጥቂት ነው የሳተኝ ብለው ቂያማ ያቆማሉ፡፡ እንኳንም የሳተህ ባይስትህ ኖሮ ጣጣህ ብዙ ነበር፡፡ ሳይፈነክትህ እንዲህ የሆነክ ቢፈነክትህ ኖሮ እንዴት ትሆን ነበር!፡፡ በዚህች ዓለም ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ በርሱ ፈቃድ ነው፡፡ በፈቃዱ ተማረን ምን ልናመጣ ነው?፡፡ የወደደውን አንወድም ብለን ምን ልንሆን!፡፡ ፌንጣ ብትቆጣ ክንፏን ጥላ መብረር ካልሆነ ምን ልታመጣ!

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

💡:እስልምና አትጨነቁ ይላል፡፡ የፈጠረን ጌታ ‹እመኑ፣ በርቱ፣ ትጉ፣ ተስፋ አትቁረጡ፣ አትስነፉ፣ አትድከሙ፣ አትዘኑ፣ አይዟችሁ፡፡ …› ብሏል፡፡ በመልካም ትዕግስትና ተስፋ አደራ ይላል፡፡ በጥሩ መጨረሻና ስኬት ቃል ይገባል፡፡ ነቢዩ (ﷺ) ምንም ሊረዷቸው ባልቻሉ ጊዜ ‹የያሲር ቤተሰቦች ሆይ! ትእግስት አድርጉ ቀጠሮአችሁ ጀነት ነው፡፡› ብለዋቸዋል፡፡

:ሞኝ የሆነ ይጨነቅ፡፡ እኔ ሞኝ አይደለሁም አልጨነቅም፡፡ ዕድሜዬ አጭር መሆኗን አውቃለሁ፡፡ መሞቴ ላይቀር ለምን ቀድሜ እሞታለሁ፤ ለማንስ ለምንስ ብዬ እታነቃለሁ፡፡ መድረሱ ላይቀር ለምን ቀድሜ ፈግማለሁ፡፡ አልጨነቅም - ተጨንቄ ምን አገኘሁ! ተበሳጭቼስ ምን አተረፍኩ፡፡ ተናደውና ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቶአቸው ሰው የደበደቡ እስር ቤት ናቸው፡፡ ተበሳጭተው የተሳደቡ ‹ምኑ ባለጌ ነው?› ተብለው በሰዎች ትዝብት ዉስጥ ገብተዋል፡፡ ስብእናቸውን አስንቀዋል፡፡ ምን አስጨነቀኝ፡፡ ቦታዬ አላህ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ አላህ ዘንድ አልጉደል እንጂ እዚህ ኪሎዬን ቢቀንሱ ስድባቸው አይለጠፍብኝም፡፡ ከአላህ ጋር እስካለሁ ዘና እላለሁ፡፡

:የደስታችን መሰረቱ አላህ ብቻ ይሁን፡፡ ከሁሉም በላይ ከርሱ ጋር የሚኖረንን ግንኙነት እናሳምር፣ እሱ እንዳለውና እንዳዘዘው ለመኖር እንሞክር፣ ህግጋቱን ከመጣስ እንጠንቀቅ፣ ድንበሩን አንጋፋ፡፡ ከአላህ ጋር ስንሆን አካላዊ ለውጥ ላይኖረን ይችል ይሆናል፣ ኪሎ ላንጨምር እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ዉስጣዊ ሰላምና የበዛ ደስታ ይኖረናል፡፡ በዚህ ደግሞ ሁሉንም ነገር ማሸነፍ እንችላለን፡፡ ጣሉት ጃሉድን ያሸነፈው፣ ሙሳ ፈርዐውንን የረታው፣ ኢብኑ መስዑድ አቡጀሀል አንገት ላይ የወጣው … በሥጋ ግዝፈት ሳይሆን በኢማን ጥንካሬ ነው፡፡ የኢብኑ መስዑድ እግር ቅጥነቱ ቢያስገርምም ‹የቂማ ቀን ሚዛን ላይ ከኡሑድ ተራራ በላይ ክብደት አለው፡፡› ብለዋል ነቢዩ (ﷺ)፡፡

┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

20 Oct, 12:21


#መልካም_ኒያ ❤️‍🩹

:አንድ አማኝ መልካም #ኒያ እስካለው ድረስ በእያንዳንዱ ተግባራቱ ከአላህ #ምንዳን ይሸለማል። በኒያው ማማርና በቀልቡ መስተካከል ምክንያት ፍቁድ የሚባሉት ነገራቶች በሙሉ ከመልካም ስራዎቹ ይመደቡለታል።

𖡇 ኢብኑ ተይሚያህ
🌿

#ይህም_ማለት

😎:መብላት፣ መጠጣት፣ መተኛት፣ ዱንያዊ ስራን መስራት፣ መልበስ፣ መጫወት፣ መዝናናት----- በመልካም ኒያ ምክንያት አጅር የሚያስገኝ መልካም ስራ ሆኖ ይመዘገባል ማለት ነው።

📑:አልወሷያ ሰለፊያ

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌 

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

19 Oct, 15:08


ገራሚ ቲላዋ😍

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

19 Oct, 13:04


📌:መልካም ስራ በ3 ነገሮች ቢሆን እንጂ የተሟላ አይሆንም፦

: ስራውን በማፍጠን ¹

:ትንሽ አድርጎ በማየትና ²

:በድብቅ መፈፀም ³

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌 

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

17 Oct, 06:43


🦋

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

16 Oct, 17:09


💠አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና። የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን ስታስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

አላህ መልካም የምንስራ ያድርገን
~🤲

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

15 Oct, 18:53


🥹

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

15 Oct, 10:45


ጂን | جن 👺

:"ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው። “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ኢብሊስ ደግሞ ተፈጥርዎ #ከጂን ነው፦

🔹:وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ . . .

🔸:ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ከጋኔን (ጎሳ) ነበር፡፡ . . .(18:50)

:ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፦

🔹:وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ

🔸:ጃንንም (ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡(አል ሂጅር)

🔹:يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

🔸:እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡(2:21)

🔹:وَاتَّقُوا الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالْجِبِلَّةَ الْأَوَّلِينَ

🔸:«ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች (የፈጠረውን) ፍሩ፡፡»(26:184)

   ─━━━━━━⊱
⬇️⊰━━━━━━─

:ጂኒዎች እንደ ሰው ነፃ ፈቃድ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው ፤ እንደ ሰው አላህን ሊያመልኩ የተፈጠሩ ፍጡሮች ናቸው፦

🔹:وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

🔸:ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡(51:56)

:በመቀጠል #ኢብሊስ በአላህ ላይ ሲያምፅ #ሸይጧን ሆነ፤ “ሸይጧን” شيطان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شياطين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ ሸይጧን የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም።

:ጂኒዎች ህይወት እንዳላቸው ሁሉ ይሞታሉ፦

🔹:أَوَلَمْ يَنظُرُوا فِي مَلَكُوتِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ مِن شَيْءٍ وَأَنْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ قَدِ اقْتَرَبَ أَجَلُهُمْ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ

🔸:በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛው ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜያቸውም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መኾኑን አያስተውሉምን ከእርሱም (ከቁርኣን) ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ፡፡(7:185)

:የሞት ጊዜ ካለበት ፍጡር መካከል አንዱ የጅን ሞት ነው፤ ነብያችንም”ﷺ” ይህንን ነግረውናል፦

📗:ኢማም ቡኻሪይ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ነብዩﷺ እንዲህ ይሉ ነበር፦

"በሃያልነትህ እጠበቃለው፤ በእውነት የሚመለክ ከአንተ ከማትሞተው ሌላ የለም፤
#ጂን እና #ሰው ግን #ይሞታል

أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ “‏ أَعُوذُ بِعِزَّتِكَ الَّذِي لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، الَّذِي لاَ يَمُوتُ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ يَمُوتُونَ ‏”‌‏.‏

   ─━━━━━━⊱
⬇️⊰━━━━━━─

:የትንሳኤ ቀንን ቀጠሮ ጂኒዎች ማወቃቸው የምናውቀው የትንሳኤ ቀንን የሚያሳስቡ ከጂኒዎች መካከል የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞች ለጂኒዎች ተልከው እንደ ነበር አላህ መናገሩ ነው፦

🔹:وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ قَدِ اسْتَكْثَرْتُم مِّنَ الْإِنسِ ۖ وَقَالَ أَوْلِيَاؤُهُم مِّنَ الْإِنسِ رَبَّنَا اسْتَمْتَعَ بَعْضُنَا بِبَعْضٍ وَبَلَغْنَا أَجَلَنَا الَّذِي أَجَّلْتَ لَنَا ۚ قَالَ النَّارُ مَثْوَاكُمْ خَالِدِينَ فِيهَا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ

🔸:ሁሉንም የሚሰበስብባቸውንም ቀን (አስታውስ)፡፡፡ የአጋንንት ጭፍሮች ሆይ! ከሰዎች (ጭፍራን በማጥመም) በእርግጥ አበዛችሁ (ይባላሉ)፡፡ ከሰዎችም የኾኑት ወዳጆቻቸው፡-«ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ፡፡ ያንንም ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን» ይላሉ፡፡ እሳት አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ መኖሪያችሁ ናት ይላቸዋል፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡(6:128)

🔸:የጋኔንና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ!፡- «አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን (ቅጣት) ማግኘትን የሚያስፈራሩዋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን» (ይባላሉ)፡፡ «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን፤ (መጥተውልናል)» ይላሉ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታለለቻቸው፡፡ በነፍሶቻቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ፡፡(6:130)

:ይህ የትንሳኤ ቀን ቀጠሮ ለሁሉም የተቀጠረ ነው፦

➣(44:38-40) ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም። ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፤ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።”
#የመለያው #ቀን #ለሁሉም #ቀጠሯቸው” ነው።

➣(55:31-39) እናንተ ”
#ሁለት ከባዶች ሰዎችና ጋኔኖች” ሆይ፥ ለናንተ መቆጣጠር በእርገጥ እናስባለን፤ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? #የጋኔንና #የሰው ጭፍሮች ሆይ ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፤ በስልጣን እንጅ አትወጡም። ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?”#በሁለታችሁም” ላይ ከእሳት ነበልባል ጭስም ይላክባችኋል፤ ሁለታችሁም አትረዱምም። ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፥ እንደታረበ ቆዳ በሆነች ጊዜ፤ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? “#በዚያም #ቀን #ሰውም “ጃንም#” ከኃጢአቱ ገና አይጠየቅም።

:ለጂኒዎችም ጀነት ወይም ጀሃነም አለ፦

➣(11:119) የጌታህም ቃል፣ ገሀነምን ከጂኒዎና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ በማለት ተፈጸመች።

➣(55:45-46) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው፥ ሁለት ገነቶች አሉት።

🔎:በተለይ “ጌታችሁ” የሚለው ቃል “ረቢኩማ” رَبِّكُمَا ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ “ታስተባብላላችሁ” የሚለው ቃል “ቱከዚባኒ” تُكَذِّبَانِ ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል።

منقول
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
📌
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

14 Oct, 12:56


🐏የበግ ሽንት🤔

📌:የበግ እና የፍየል #ሽንታቸውና #በጠጣቸው ይነጅሳልን? ከነጀሰስ በሱ የተሰገደ ሶላት #መድገም አለብን

➡️≠「 #መልስ  」∬

:ስጋቸው #የሚበላ ማንኛውም እንስሳ ሽንታቸውም ሆነ ሰገራቸው #አይነጅስም። ለዛም ነው ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም  ወደ መዲና ገብተው የታመሙትን ሰዎች የግመል #ሽንትና ወተት እንዲጠጡ ያዘዟቸው። ሽንቱ ነጃሳ ቢሆን ኖሮ እንዲጠጡት ባላዘዟቸው ነበር።

➡️በሌላም ወቅት #የበግ ጉረኖ ወይም ማደሪያ ሽንታቸውና በጠጣቸው ያለበት መሆኑን #እያወቁ ውስጡ #መስገድ እንዴት ይታያል ተብለው ሲጠየቁ ችግር እንደሌለውና እንዲሰግዱ አመላክተዋቸዋል ። ይህ ሽንትም ሆነ ሰገራ የነካውን #ልብስ ማጠብም ግዴታ አይደለም። በሱም መስገድም #ይቻላል። ሶላቱንም መድገም አይጠበቅበትም።

📗。*。📙
📘。\|/。📒
       
🖱{ምንጭ🗂}
📔。/|\。📕
📓。*。🗃 °

➡️[ 📚ኢብኑ ተይሚያ ፣ መጅሙኡል ፈታዊ ፣ 21/542 ፣ 📚ኢብኑ ቁዳማ ፣ ኪታቡል ሙግኒ ፣ 2/492 ፣ 📚የሳዑዲ የኢልም ጥናትና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ፣ 6/414 ]⬅️
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
📌
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

12 Oct, 15:46


💡ልብ በል ! #ጀነት ተውበት በሚያደርጉ ወንጀለኞች የተሞላች ናት። በአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ !

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

12 Oct, 12:35


⚡️

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

09 Oct, 19:14


#ካገኘሁት 🖥

:መልካምነት ደግ መስራት ብቻ ሳይሆን ክፉም አለመስራት ነው።

:መኖርን እንደተቀበልቅ ፈተናዋንም ተቀበል።

:እየሳቀ ሀጢአት የሰራ እያለቀሰ ጀሀነም ይገባል።

:ለማወቅ ተቸገር ለማገኘት ጣር ከትልቅ ባህር ምርጥ አሳ ይገኛል።

;አጀማመርህን ካሳመርክ ከፊሉን ጨረስክ ማለት ነው።

:ለራበው ሰው ሁሉም ነገር ጣፋጭ ነው።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

07 Oct, 13:59


سبحان الله 🦋

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

06 Oct, 13:08


#ከቁርኣን_ጋር 📖

¹: #ቁርኣን የማን ቃል ነው

🔸:ذَٰلِكَ الْكِتَابُ لَا رَيْبَ ۛ فِيهِ ۛ هُدًى لِّلْمُتَّقِينَ

🔹:ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመኾኑ) ጥርጥር የለበትም ፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡ [በቀራህ 2]

²: ለምን ወረደ

🔸:هَٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

🔹:ይህ (ቁርኣን) ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ (ሊመከሩበት)፣ በእርሱም ሊስፈራሩበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት (የተወረደ) ነው፡፡ [ኢብራሂም 52]

³: መቼ ወረደ

🔸:شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ . . .

🔹:ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ . . . [አል በቀራህ 185]

⁴:በምን መልኩ ወረደ

🔸:إِنَّ الَّذِي فَرَضَ عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لَرَادُّكَ إِلَىٰ مَعَادٍ ۚ . . .

🔹:ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ኾኖ ባንተ ላይ ያወረደው (አምላክ) ወደ መመለሻ (ወደመካ) በእርግጥ መላሽህ ነው።. . .[አል ቀሶስ 85]

⁵:በምን ቋንቋ ወረደ

🔸:قُرْآنًا عَرَبِيًّا غَيْرَ ذِي عِوَجٍ . . .

🔹:መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን (አብራራነው)፡፡. . .[አል ዙመር 28]

⁶:ከአላህ ዘንድ ስለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለ

🔸:أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

🔹:ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡[አል ኒሳዕ 82]

⁷:ለመረዳት አያስቸግርም

🔸:وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

🔹:ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?

[አል ቀመር 17]

⁸:ቋንቋውን ለማያውቁት ለመያዝ አያዳግትም

🔸:فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لِتُبَشِّرَ بِهِ الْمُتَّقِينَ وَتُنذِرَ بِهِ قَوْمًا لُّدًّا

🔹:በምላስህም (ቁርኣንን) ያገራነው በእርሱ ጥንቁቆቹን ልታበስርበት በእርሱም ተከራካሪዎችን ሕዝቦች ልታስፈራራበት ነው፡፡

[አል መርየም 97]

⁹: ተመሳሳዩን መፍጠር አይቻልም

🔸:وَإِن كُنتُمْ فِي رَيْبٍ مِّمَّا نَزَّلْنَا عَلَىٰ عَبْدِنَا فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِّن مِّثْلِهِ وَادْعُوا شُهَدَاءَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

🔹:በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ፡፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን ጥሩ፡፡

🔸:فَإِن لَّمْ تَفْعَلُوا وَلَن تَفْعَلُوا فَاتَّقُوا النَّارَ الَّتِي وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ ۖ أُعِدَّتْ لِلْكَافِرِينَ

🔹:(ይህንን) ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች፡፡

[አል - በቀራህ 23-24]

¹⁰:በሰዎች ሊበረዝ አይችልም

🔸:إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

🔹:እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

[አል - ሂጅር 9]

¹¹:ለሰዎች ምን ትመክራለህ

🔸:يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِن رَّبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ وَإِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

🔹:እናንተ ሰዎች ሆይ! መልክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ፡፡ እመኑም ለናንተ የተሻለ (ይኾናል)፡፡ ብትክዱም (አትጐዱትም)፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡[ኒሳዕ 170]

📕:ይህን ይመስላል ከቁርዐን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
📌
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

06 Oct, 05:41


➡️:ከጠፋህም ይጨነቃሉ ፣ ብዙ ከታየህም ይጨነቃሉ ፣ ችግር ላይ ነኝ ካልካቸዉም ይጨነቃሉ፣ አሞኛል  ስትላቸዉም ይጨነቃሉ ፣ ከተናገርክም ይጨነቃሉ ፣ ዝም ካልክም ይጨነቃሉ።  የአንዳንድ ሰው መጨነቅ ለተጨነቀ ወይም ችግር ላይ ላለ ሰው ተጨማሪ ጭንቀት ወይም ችግር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ጭንቀታቸው እስኪያልፍላቸው ጠብቋቸው። በጥያቄም አታሰልቿቸው። ምን ሆና/ሆኖ ነው ብላችሁም እንደ እናት ሆድ አትንቦጅቦጁ።

🍀:የቀናት ማለፍ ብቻ የሚፈቷቸው ችግሮቻችን ብዙ ናቸው ወዳጆቼ። ዱንያ እንደሆነች ክብ ነች። ደስታና ሐዘን፣ ችግርና እፎይታ፣ ማግኘትና ማጣት፣ መውደቅና መነሳት ዞሮ መምጣት ልማዳቸው ነው። ዱንያ ጀነት አይደለችም፣ ዘወትር አንደላቃ አታኖርም።

منقول

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽

04 Oct, 18:58


⚡️

5,113

subscribers

183

photos

314

videos