♡ @H_Islamic_tube ♡
✍semira
🎀 ክፍል 18
☆ከሳጥን ውስጥ ፋሻ እና ቁስል ማድረቂያ አውጥቼ በዞረበት አቅጣጫ ሄጄ ተቀመጥኩ ትራሱን በግማሽ ጎኑ ተንተርሶ ተኝቷል ቀኝ እጁን እያነሳሁ
<<አላህ ባሮቹን በንብረቶቻቸው፣ በገንዘባቸው(በንግዳቸው ላይ ክስረትን ውድመትን) ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በወዳጆቻቸው ባላቸው ነገር በሙሉ ይፈትናቸዋል በእሱ አታምንም>>
አይን አይኔን እያየ ዝም አለ
<<በፈተናዎች ውስጥ ደግሞ ያለፉትን ያለፈ ወንጀላቸውን ይምርላቸዋል>>
ከአይኖቹ እንባ መፍሰስ ጀመረ
<<والله يحب الصبرين
አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል የሚለውን አያ አስታወስከው?>>
እጁን ሊነጥቀኝ ሞከረ ቁስሉ ተሰምቶት ይመስለኛል
<<ይገባኛል የተፈጠረውን በምንም ልንቀይረው አንችልም ግን ሷብር ብናደርግ አንከስርም ወደ ፊት ብዙ ቀናት አሉ በእነዛ ውብ ቀናት እሷም አብራን ብትኖር ደስ ይለኝ ነበር ግን ደግሞ አላህ አላለም እሱ የወደደውን የፈቀደውን አደረገ እ……… ይጎዳል ይገባኛል እናትን ማጣት ያሳዝናል ግን እንደዚህ አትሁን? እ…? እኔ እኮ ቅድም ስላላለቀስክ ደህና መስለኸኝ ነበር>>
<<ሁለት አመት ሙሉ በድብቅ ትከታተለው የነበረ ህክምና መኖሩን ሳውቅ አቅም አጣሁ እንደምትሞት ቀድማ ታውቅ ነበር ለምን አልነገረቺኝም? ትክክለኛ ልጅ ስላልሆንኩ አይደል? አንድ ቀን ለስራ እንጂ ለእሷ ጊዜ ሰጥቻት ስለማላውቅ አይደል?>>
ድንጋጤዬን ለመደበቅ እየሞከርኩ
<<ለምን እንደዛ ታስባለህ እሷ እኮ ለአንተ አስባ ነው ያልነገረችህ>>
ተነስቶ ትራሱን እያቃና ተቀመጠ
<<ደህና አይደለሁም ዝምታዬ ደህና መሆኔን እያስመለከተ ቢያስዋሸኝም……… በጣም ከፍቶኛል ሚንሃ ይሄ ነው የማልልሽ ህመም እንደዛ ተቆፍሮ የተከመረው አፈር በሙሉ በእናቴ ላይ መጫኑን ሳስብ አቅም አጣለሁ በቃ አልችልም>>
ትከሻውን ተንተርሼ
<<ሁሉም ሰው አልችልም ብሎ በሚያስበው ነገር ላይ ሁሉ ተፈትኗል ከፈተናው ጋር ችሎታን የሚሰጥ ጌታ አለ አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ድረስ ደግሞ አብሬህ ነኝ እሺ?……>> ፈገግ ለማለት እየሞከረ
<<እንድረጋጋ የሚያደርገኝም ብቸኛው ነገር እሱ አይደል?>>
ግንባሬን ሳመኝ
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ረፋዱ ላይ ኢርቫ በስልክ መስመር:-
<<አሰላሙ አለይክ ሃቢብ>>አለችው
<<ወአለይኪሰላም አክስቴ>>
<<እንዴት ነህልኝ?>>
<<አልሃምዱሊላህ እንዴት ነሽ አክስቴ?!>>
<<አልሃምዱሊላህ መጥተናል ልትቀበለን ትችላለህ? ከመጣሁ ስለቆየሁ አንዳንድ ነገሮች ተቀይረውብኛል>>
<<መርሃባ አሁን እመጣለሁ>> ብሏት ወደ እኔ ዞረ
<<አዚዘቲ አክስቴ የአቢ እህት መጥታለች ሄደን ብንቀበላትስ?>>
<<እሺ ልብስ ልቀይር>> ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ሄድን አክስቱ አሚራ ከሁለት ልጆቿ ጋር ሻንጣዋን ይዛ ጠበቀችን ወንድ ልጇ ከኢርቫ በለጥ ይላል 29 አመቱ ሲሆን ሴት ልጇ ደግሞ 20 አመቷ ነው የአሜሪካ ተወላጆች ስለሆኑ አራርቆ መውለድ የሚለው ሃሳብ በእነሱም ላይ ተጽዕኖ እንደነበረው ግልፅ ነው እናታቸው በአባቷ ቁጥጥር የበዛበት ሁኔታ ውስጥ ስላደገችበት የኖረችበትን እና እስልምናዋ ላይ ማሻአላህ ናት እነሱ ደግሞ የእሷ ተቃራኒ ሴት ልጇን በሱሪ ነበር የተቀበልናት መንሱረት ትባላለች ወንድ ልጇ ደግሞ አይመን አይመን እና ኢርቫ ከፊት ሆነው እኛ ሶስታችን ደግሞ ከኋላ ተቀምጠን ቤት ደረስን ያው የሚያርፉት እኛ ጋር ነው እናት እና ልጅ እያወሩ እኔን ዘንግተውኝ ነበር ብቻ ቤት ስንደርስ ነው ማንነቴ የታወቀው ክፍሎቻቸውን አሳይቻቸው ምግብ ላዘጋጅላቸው ሄድኩኝ ግን አሁን ፕሌን ውስጥ በልተናል እንቅልፍ ስለተዛባብን እንተኛ ነበር ያሉኝ እሺ ብዬ ወደ ክፍሌ ገባሁ ኢርቫ ደግሞ አክስቱ እና አባቱ በልጆቿ ምክንያት መጋጨታቸውን እየነገረኝ እንዳለ መታጠቢያ ቤቱን የሚጠግኑ ባለሞያዎች መጡ ስለዚህ ወጣ ብለን እንመለሳለን ብሎኝ ወጣን በጣም ደስ ብሎኝ ነበር ከምንም በላይ ኢርቫ የሚያነሳቸውን ሃሳብ ስሠማ እና ተቀይሯል አሁን አንድ ከመንደራችን ያልወጣ ካፍቴሪያ ውስጥ ፒዛ አምሮኝ ነበር ፒዛ እና ሻይ አዘን መብላት ጀመርን
<<ገዝተን እንውሰድላቸው እንዴ መጨረሻ ላይ ስንሄድ? ካሰብኩት በላይ የሆነ ፒዛ ነው>>
<<እሺ እንይዝላቸዋለን>> አልኩት
<<እህት……… አስተናጋጅ … አንድ ፒዛ ጭማሪ ፈልገን ነበር ልታዘጋጂልን ትችያለሽ?>>
<<እሺ>>አለች እሷም እየበላን እንዳለ በመሃል ኢርቫ
<<ወንድም አይንህን ንቀል እንጂ?>> ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ የሆነ ግርግር ልበላችሁ ብቻ እንደዛ አይነት ወከባ ነገር ፈጠረ ልጁም
<<ኧረ አባት እኔ ማንንም አላየሁም>>
ሰው ወዳለበት መሰብሰብ ሲጀምር
<<ኢርቫ አላህን ፍራ እንጂ ምን እያደረግክ ነው?>>
<<እያየሽ ነበር ለምን ያይሻል? ምንድነው የፈለገው?>> አብዛኛው ጊዜ ስሜት ምክንያታዊ አልሆን ስለሚል ታዛቢ ያፈራል ሳቄ ደርሶ እየተናነቀኝ
<<እ እ እ? ነው እንዴ? በቃ የካፌውን እቃ በሙሉ ከጥቅም ውጪ አድርገው መስታውቱን እዚህ ደግሞ ጠረጴዛ እና ወንበርም አለ የቡና ማሽን አለ የወተት ፍሪጅ…………ቆይ ምን ነክቶሃል? በሰላም ተጠቅመን ብንወጣ ምን አለበት?>>
<<ቀለድሽ በቃ?>>
<<አልቀለድኩም እሱ አላየህም እያለህ ከዛ በኩል የተቀመጡት ሶስት ሴቶች እንኳን ባንተ እየፈረዱ አንተ ተነስተህ ልደባደብ ስትል ያሳፍራል ኢርቫ ምን ሆነሃል?>>
<<ታውቂዋለሽ?>> አለኝ
<<አስተغፊሩላህ………ወደ ራስህ ተመለስ>>
<<የት ነው የተዋወቃችሁት?>>
ለሚናገረው ሁሉ ችላ አልኩት አናደደኝ አውቆ እየሆነ ያለው ነገር አበሸቀኝ
<<እህት ፒዛውን ጨረስሽልኝ? እሺ ሂሳብ ስንት ነው?>>
ፒዛችንን ይዘን ከካፌው ወጣን ቤት ስንደርስ ጠጋኞቹ ጨርሰው ሄደዋል እንግዶቻችንም አልተነሱም ድርሻቸውን ላስቀምጥ ወደ ማዕድ ክፍል ስገባ መንገድ ላይ ዝም ያለው ኢርቫ እየለፈለፈ ተከተለኝ
<<ንገሪኝ እንጂ የት እንደምታውቂው?>> ዝም አልኩት በቃ ይረጋጋል ሁለታችንም ካወራን ጥሩ አይመጣም ብዬ ግን ለውጥ አልነበረውም
<<ኢርቫ አላህን ፍራ እኔ የትም እንደማላውቀው ሁለታችንም እናውቃለን ለምንድነው እንደዚህ አይነት ጥያቄ የምትጠይቀኝ?>>
<<በጣም ተከራከርሽለት አልመሰለሽም?>>
<<እሺ አንተ እንደፈለግክ አስበው አይመለከተኝም>>
<<ለምን? ራስሽ ባመጣሽው ችግር አያገባኝም ስትዪ ትንሽ አታፍሪም ሃያዕ ይኑርሽ እንጂ አንቺ እንደዛ በሆነው ባልሆነው ስትስቂ…>>
ንግግሩን ሳላስጨርሰው ትቼው ወደ ክፍሌ ሄድኩ እና ጋደም አልኩ እንባዬ ደርሶ እየተናነቀኝ ነበር አልቆየም መንታ መንታ ሆኖ መውረድ ጀመረ ሰላም እንደማጣት አልያም በጭቅጭቅ ውስጥ እንደመኖር የሚመር ምንም ነገር የለም እናቱ እንዲህ እንደሚሆን አውቃ ነበር ማለት ነው እንዳትርቂው ያለቺኝ በዚህ ሁኔታ እኮ አንድ ሌሊት በሰላም ማደር አልችልም
@H_Islamic_tube
@H_Islamic_tube
130 🥰
ይቀጥላል☆ ☆ ☆. . . .