***
Personality( ባህርይ/ማንነት): ለህይወት/ለራሳችን ያለንን አመለካከት፣ ለሚያጋጥሙን ሁነቶች የሚኖረንን ግብረመልስ፣ አድራጎታችን፣ ከሰዎች ያለንን ተግባቦት፣ ውስጣዊ ስሜትን የምናስተናግድበት አግባብ፣ ውስጣዊ ተነሳሽነታችንን እና መሰል ጉዳዮችን የሚመለከት እና እኛነታችን የሚገለጥበት መለያችን ነው::
ይህ ማንነት አንድም በተፈጥሮ የምንቸረው፤ ሌላም በኑረታችን እየተገነባ የሚሄድ ነው::
የሰው ልጅ ባህርይ/ማንነት እንደየመልካችን አይነተ ብዙ ቢሆንም፤ ጠቅለል አድርገን ብንቃኘው በሚከተሉት አምስት አበይት መለያ ባህርያት ከፍሎ ማየት ይቻላል::
1- Openness to experience:-
አዳዲስ ነገሮችን በማፍለቅ ፣ በማጠየቅ፣ በመፈላሰፍ፣በመመራመር፣በመራቀቅ፣ጥበብን በማፍለቅ፣ውበትን በማድነቅ ይታወቃሉ::
2- Conscientiousness-
ጥንቁቅ፣ ንቁ፣ በመርህ የሚኖሩ አይነት ናቸው::
3- Extraversion-
ግልጽ፣ ነገረ ስራቸው ፊት ለፊት የሆነ፣ ከሰው መቀላቀል የሚሆንላቸው፣ ተጫዋች እና ተግባቢ አይነት ሰዎች ባህርይን ይወክላል::
4- Agreeableness-
የሌሎች ስሜት ግድ የሚሰጣቸው፣ ሩህሩህ እና ስሜተ ስስ አይነት ሰዎች ባህርይን የሚወክል ነው::
5- Neuroticism -
ጭንቀታም፣ ስሜታቸውን መቆጣጠር የሚያቅታቸው አይነት ሰዎች ናቸው::
ይህ ባህርይ ያለባቸው ሰዎች ለድብርት እና ጭንቀት ህመሞች ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው::
ከላይ የተጠቀሱት አምስቱም ባህርይዎች አቻ ተቃራኒ ባህርያት አላቸው::
ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ እናንተን ይገልጣል ብላችሁ የምታስቡት የቱን ነው?
አሻም ለአለማችን!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ገጾች ይወዳጁ:-
https://t.me/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif