በክልላችን በአለፉት አንድ አመት ከ4 ወር የነበረውን የሰላም ችግር ለመመለስ በኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት እና ፅኑ አቋም ባላቸው የክልሉ የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅራችን ለህዝብ በተከፈለው ውድ መሰዋትነት በሰላም ወዳዱ ህዝባችን ሁለንተናዊ ትብብር አሁን እያየነው ላለው የሰላም፣የፀጥታ መረጋጋትና የልማት ስራዎች ውጤታማነት ጉልህ ድርሻ አላቸው።
በክልላችን በሁሉም አካባቢዎች አንፃራዊ የሰላም መሻሻሎች በመኖራቸው የግብርና ምርቶች፣የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ውጤታማ መሆናቸውን አይተናል።ህብረተሰባችንም ለሰላምና ደህንነት ስራው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ከፀጥታና ከአመራሩ ጎን በመሰለፍ በየደረጃው ከፍተኛ ተሳትፎና ባለቤት መሆናቸውን ሲያረጋግጡ ተመልክተናል።ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
የአብክመ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሚያስተባብራቸው የፀጥታ ተቋማት የክልላችንና የሀገራችን ህዝቦች መብትና ጥቅም ማዕከል በማድረግ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ውስጣዊ የፀጥታ ተቋማት የመፈፀም አቅም የአመለካከትና የአስተሳሰብ ግንባታ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
በዚህ መሰረት ተቋማት በየራቸው ከተልኮ ውጤታማነት አንፃር በመገምገም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተልኳቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።ይሁን እጂ አንዳንድ የጽንፈኛ ማህበራዊ ሚዲያዎች በአማራ ክልል ህዝብ ሞት ዳቦ የሚቆርሱ ሀይሎች ዛሬም ሞት እየደገሱ ያለቢሆንም የፀጥታ መዋቅራችን እና ህዝባችን እጅ ለእጅ ተያይዘን በክልሉ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት እየሰራን መሆኑን ቢሮው በአፅንኦት ይገልፃል።
ህዳር 12/2017 ዓ.ም
ባህርዳር
"ሰላም ለሁሉም፣ሁሉም ለሰላም!!
የአብክመ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ