Amhara Education Bureau @anrse Channel on Telegram

Amhara Education Bureau

@anrse


Quality Education

Amhara Education Bureau (English)

Are you looking for quality education resources and information in the Amhara region of Ethiopia? Look no further than the Amhara Education Bureau Telegram channel! With the username @anrse, this channel is dedicated to providing students, teachers, and parents with valuable educational content and updates. From curriculum updates to exam schedules, you can find everything you need to stay informed and succeed in your educational journey. The Amhara Education Bureau is committed to promoting quality education for all students in the region. By joining this channel, you will have access to the latest news and announcements from the Bureau, as well as educational resources and materials to support your learning. Whether you are a student preparing for exams, a teacher seeking professional development opportunities, or a parent looking to stay involved in your child's education, this channel has something for everyone. Stay connected with the educational community in the Amhara region by joining the Amhara Education Bureau Telegram channel today. With a focus on quality education and student success, this channel is your go-to source for all things related to education in the Amhara region. Don't miss out on the opportunity to enhance your learning experience and stay informed about the latest developments in education. Join @anrse now and start exploring the world of education in Amhara!

Amhara Education Bureau

07 Dec, 08:09


የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
------------------------//---------------------------

(ሕዳር 28/ 2017 ዓ.ም) በትምህርት ሥርዓቱ የሚስተዋለውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር ለመቅረፍ በሚቻልበ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ላይ የሚስተዋለውን ችግር መቅረፍ ካልተቻለ የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና አለም አቀፍ ተወዳደሪ የሆኑ ተማሪዎችን ማፍራት እንደማይቻል ጠቅሰው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩርት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተለይም ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በአግባቡ እንዲረዱና ውጤታማ እንዲሆኑ እንግሊዝኛ ቋንቋን የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የማዳመጥ ክህሎታቸውን በሚገባ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

የቀጣዩ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነው አሁን በሚሰራው ሥራ መሆኑን በመገንዘብ የመማር ማስተማር ሥነ - ዘዴውን ማስተካከል እንዲሁም ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን ምቹ ሁኔታ በትምህርት ቤቶች መፍጠር ይገባልም ብለዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ በትምህርት ዓይነትና በማስተማሪያ ቋንቋነት በትምህርት ሥርዓቱ እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው ነገር ግን ከፍተኛ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር መኖሩን የሚያመላክቱ ጥናቶችን አቅርበዋል።

በዚህም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር በተማሪዎችና በመምህራን ዘንድ እንደሚስተዋል አንስተው ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ትምህርት ቤትን መሰረት ያደረገ ሥልት ቀይሶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴርም https://learn-english.moe.gov.et የተሰኘ ያለ ምንም የኢንተርኔት ክፍያ የሚሰራ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፓርታል አልምቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን የጠቀሱት መሪ ሥራ አስፈጻሚው ይህንን ፖርታል ተማሪዎች፣ መምህራን እንዲሁም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን ማሳደግ የሚፈልጉ ዜጎች እንዲጠቀሙበት በሚገባ በማስተዋወቅ ረገድ ሚድያዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመድረኩም የተለያዩ ጽሁፎች ቀረበው በተሳታፊዎች ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ተሳታፊዎችም ተማሪዎች በክፍል ውስጥና ከክፍል ውጪ ቋንቋውን እንዲጠቀሙበት እና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያበረታታ ሁኔታ አለማኖሩ ችግሩን የጎላ እንዳደረገው ገልጸው ይህንን ለመፍታት መምህራንና ተማሪዎች በድፍረት ቋንቋውን እንዲጠቅሙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያደርጉ ስልቶችን መቀየስ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የቋንቋ ክህሎትን በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ሥራዎችና ሥልቶችን መሰረት በማድረግ ተሞክሮዎች መቀመርና ማስፋት በተለይም ክልል ከክልል፣ ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት ልምድ የሚለዋውጡበት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባም ተመላክቷል።

በምክክር መድርኩ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
MOE

Amhara Education Bureau

06 Dec, 18:36


በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በወቅታዊ የመማር ማስተማር ጉዳዮች ዙሪያ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር የሚመክር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ የሁሉም ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ሱ/ቫይዘሮች፣ የቀበሌ አመራሮች፣ የትምህርት ቤት ወመህ እና ቀትስቦና የሃይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በሪሁን መንግሥቱን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ህዳር 27/2017-ባህርዳር
መረጃው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው

Amhara Education Bureau

06 Dec, 18:25


በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ ወረዳ በወረዳው የትምህርት ስራን ለማጠናከር ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
****

በውይይቱ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ አንተነህ ታደሰን ጨምሮ የመምሪያው ስራና ስልጠና ኃላፊ አቶ እዮብ አግማስ፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስፋው አዱኛ የወረዳው ሱፐርቫይዘሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ ተፅዕኖኦ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ከትምህርት የመማር ማስተማር ስራ ጋር በተያያዘ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በአካባቢው በተፈጠረው የሰላም ችግር ምክንያት የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑ በመድረኩ የተመላከተ ሲሆን ትምህርትን በተገቢው መንገድ ለማስቀጠል የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከየ ቀበሌው ጥሪ ተደርጎላቸው የመጡ የተማሪ ቤተሰቦች ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት መሰረት መሆኑን ጠቅሰው ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንደሚልኩም አስረድተዋል።

ህዳር 27/2017 ዓ/ም
ባህርዳር
መረጃው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው

Amhara Education Bureau

01 Dec, 11:17


የዘንድሮ የዓለም ኤች አይቪ ኤድስ ቀን በሃገራችን ለ36ተኛ ጊዜ "ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤችአይቪ አገልግሎት ለሁሉም!" በሚል መሪ ሃሳብ በኮምቦልቻ ከተማ ተከብሯል

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የዓለም ኤች አይቪ ኤድስ ቀን "ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤችአይቪ አገልግሎት ለሁሉም!" በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን ይህም ማለት ያለምንም ልዪነት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ መብታቸውን ባከበረ መልኩ ተደራሽና ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ በመፍታት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ታሳቢ ተደርጎ መከበሩንም አቶ አብዱልከሪም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በአሁኑ ወቅት 1መቶ 73 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ኤች አይቪ እንደሚኖርባቸው የሚገመት ሲሆን እስከ አሁን በተሰራው ስራ 1መቶ 57 ሺህ 9 መቶ 72 በላይ ሰዎች ውስጥ 1 መቶ 56 ሺህ 91 የሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን የተናገሩት አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ ናቸው።

አቶ አብዱልከሪም አክለውም በየደረጃው ያለው አመራር፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድረሻ አካላት፣ መገናኛ ብዙሃኖች እና አጠቃላይ ማህበረሰቡ በየ ደረጃው የተጣለበትን ሃላፊነት በመወጣት በሽታውን ታሪክ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሁነሽ ደሴ እንደተናገሩት ማሕበረሰቡ ስለ ኤች አይቪ ያለውን አመለካከት በማሳደግ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነ-ልቦና ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ከመቸውም ጊዜ በላይ በአዲስ መልክ መሰራት አለበት ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቤ በበኩላቸው ኮምቦልቻ ከተማ የኢንዱስትሪ እና የልማት ከተማ በመሆንዋ የተለያዮ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ከተማዋ በመግባታቸው ኤች አይቪ ኤድስ ለመስፋፋት ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ቢሆንም ከጤና ተቋማት ጋር በመሆን በሽታው እንዳይስፋፋ የተለያዮ ስራዎች መሰራት መቻሉን ጠቁመዋል።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች እና የሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎች ነበሩ።

በሃገራችን ለ37ተኛው ጊዜ በኮምቦልቻ ከተማ ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በፓናል ውይይቶችና በተለያዩ ፕሮግራሞች ተከብሯል።
መረጃው የአብክመ ጤና ቢሮ ነው

#amharaeducationbureau
#አብክመትምህርትቢሮ
#ትምህርትለትውልድ

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

23 Nov, 07:49


ኢንስቲትዩቱ በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።

ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂዎች መካከል በኢንስቲትዩቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ይገኝበታል።

የአማራ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በሁለተኛ እና በሥስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 222 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው። ከተመራቂዎቹ መካከል 58ቱ ሴቶች ሲኾኑ አንድ ተመራቂ ደግሞ የሦስተኛ ዲግሪ ሰልጣኝ ነው።

ተመራቂዎቹ በፒስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በፐብሊክ ፖሊሲ እና አመራር እንዲሁም በፖለቲካል ኢኮኖሚ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አሚኮ

Amhara Education Bureau

22 Nov, 13:42


«ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም »
የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህር ዋና ስራ አስፈጻሚ
---------------//////-------------
በጎንደር ከተማ አስተዳደር በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተገነባው ባለሁለት ወለል ህንጻ ትምህርት ቤት ተመርቋል ፡፡

በምረቃ ፕሮራሙ ላይ የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፈንታ በንግግራቸው አልማ የራሳችንን ችግር በራሳችን አቅም እንፍታ ብሎ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል። ትልቁ ችግራችን ትምህርት ነው በሚል ጽንሰ ሃሳብ ባለፉት ዓመታት ትምህርት ላይ ሥንሠራ ቆይተናል ብለዋል።

እንደ ሥራ አሥፈጻሚው ገለጻ ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም ብለዋል። አልማ ቁልፍ መሣሪያ አድርጎ እየሄደ ያለው ትምህርትን ከለወጥን ሁሉን ነገር መለወጥ ይቻላል፣ የሁሉ ነገር መሠረት ትምህርት ነው ብሎ ያምናል ሲሉ ገልጸዋል።

ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ሥራ እየሠሩ መኾናቸውን ነው የተናገሩት። አልማ ማኅበረሰቡ የእኔ ነው የሚለው ተቋም መኾኑንም ገልጸዋል። የተማርንበትን ትምህርት ቤት እናልማ በሚል ብሂል ምሁራን እየገነቡ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።

ሁሉንም ማቀናጀት ከቻልን የልማት ችግሮቻችንን እንፈታለን ነው ያሉት። ሁሉም የአልማ ደጋፊዎች ቢኾኑ መልሰው የሚጠቀሙት ራሳቸው መኾናቸውን ነው የተናገሩት።

ከትምህርት ቤቶች ባሻገር በጎንደር ከተማ የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን በአንድ ከተማ ውስጥ ኾነው ነገር ግን የተለያዩ ነዋሪዎችን ያገናኙ ናቸው ነው ያሉት።

መሪዎች ሕዝብን በልማት ማሳተፍ እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል። ሕዝብ የልማት ተሳታፊ ሲኾን ልማቱን ይመራዋል ነው ያሉት። ሕዝቡም የልማቱ ተሳታፊ እንዲኾን ጥሪ አቅርበዋል።የመረጃ ምንጭ አሚኮ፡፡

መረጃው የአማራ ልማት ማህበር(አልማ) ነው

Amhara Education Bureau

21 Nov, 16:50


"ከግሪክ መረሳት፤ ከጃፓን መነሳት ምን እንማር ይኾን"

በጎንደር ከተማ የተገነቡ የመሠረተ ልማት ሥራዎች በከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል። በከተማዋ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የኾኑት ትምህርት ቤቶች፣ ድልድዮች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የመዝናኛ ቦታዎች እና ሌሎች ናቸው።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ደግሞ በትምህርት ቤት ግንባታዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አሥራት አጸደወይን (ዶ.ር) በአስደናቂ የሥልጣኔ ማማ ላይ የነበሩ ሀገራት ከነበሩበት ወርደው በሌሎች ቅኝ አገዛዝ ገብተው ሲማቅቁ ተመልክተናል፤ ይሄን ያመጣው ደግሞ ለትምህርት የሰጡት ትኩረት እየወረደ መምጣቱ ነው ብለዋል።

በቀደምት ሥልጣኔዎች የምትታወቀው ግሪክ በጊዜ ሄደት እየተዳከመች ሄዳ ከነበረችበት ማማ ወረደች፤ ከዚያም አልፋ በቅኝ አገዛዝ ውስጥ ገብታ መከራ ተቀብላለች። የገናናው ሥልጣኔ ባለቤቶች በባርነት እስከ መሸጥ ደርሰዋል፤ ይህ ለምን ኾነ ከተባለ ደግሞ ለትምህርት ይሰጡት የነበረው ክብር እየቀነሰ መምጣቱ እና በጊዜ ሂደት ያልተማሩት ቦታውን እየተረከቡት በመምጣታቸው ነው ይላሉ።

ከግሪክ ውድቀት የተማሩ ሀገራት ለትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥተው በኢኮኖሚው ከፍተኛ ግስጋሴ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት። ዘመናዊ ማኅበረሰብ ፈጥረዋል፣ ፖለቲካቸውም ወደፊት ተራምዷል ነው የሚሉት።

ለአብነት ጃፓን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኒውክለር ተመትታ ከተሸነፈች በኋላ ጃፓኖች የጠየቁት ጥያቄ ለምን ተሸነፍን? የሚል ነበር። ይሄን ጥያቄ ሲጠይቁ የሽንፈታቸው ምንጭ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መበለጣቸው ነበር፤ ይህን ተገንዝበው ድምጻቸውን አጥፍተው ሠርተዋል፤ በዙ ትምህርት ቤቶችን ገንብተው ጥራት ያለው ትምህርትን ሰጠተዋል፤ ዛሬ ላይ ጃፓን በሥልጣኔ የተራቀቀች ሀገር ኾናለች ነው ያሉት።

"ከግሪክ መረሳት፤ ከጃፓን መነሳት ምን እንማር ይኾን?" ኢትዮጵያም እንደ ግሪኮች ሁሉ የአስደናቂ ሥልጣኔ ባለቤት ነበረች የሚሉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቱ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ከፍተኛ ግስጋሴ ተደርጓል፤ ቀይ ባሕርን ተሻግራ የመንንም ጭምር ታሥተዳድር ነበር፤ በባሕር ኃይል እና በምድር ጦር፣ በኪነ ሕንጻ፣ በሥነ ጥበብ፣ በሃይማኖታዊ እና ትውፊታዊ እሴቶች አስደናቂ ደረጃ ላይ ደርሳ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል ብለዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ግሪክ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር ባትገባም ከነበረችበት የሥልጣኔ ማማ ወርዳ በድህነት የምትታወቅ ሀገር ኾናለች ነው ያሉት። ከሺህ ዓመት በፊት የተሠሩ ኪነ ሕንጻዎችን ዛሬ ላይ ከምንሠራቸው ጋር ስናነጻጽራቸው ምን ያክል ወደ ኋላ እንደቀረን ያረጋግጡልናል ይላሉ። ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የተጻፉ መጻሕፍትን ዛሬ ላይ ከምንጽፋቸው ጋር ስናወዳድራቸው ምን ያክል ቁልቁል እየወረድን እንደኾነ ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

በማኅበረሰቦች መካከል የነበረው በጎ መስተጋብር እና የጠበቀ አንድነት ከአሁኑ ጋር ሲነጻጸር ምን ያክል ወደ ታች እየወረድን እንደኾነ ያረጋግጣል ሲሉ ገልጸዋል። ከነበርንበት የከፍታ ማማ ላይ ወርደን እዚህ ላይ የተገኘነው ለምንድን ነው ብለን ብንጠይቅ ሌሎች ምክንያቶች ቢኖሩም ዋነኛው ምክንያት ግን ለትምህርት የምንሰጠው ትኩረት እና ዋጋ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ ነው ይላሉ።

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረበት እስከ አብዮቱ ዘመን ድረስ ለትምህርት ጥራት ትኩረት ይሰጥ እንደ ነበር ነው ያስታወሱት። በሀገሪቱም ታላላቅ ምሁራን የወጡባቸው ታላላቅ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው እንደ ነበር አስታውሰዋል። በጎንደር እና አካባቢው ግን ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን የመክፈት ጉድለቶች እንደነበሩ ገልጸዋል። ለእድገት ዋነኛው መሠረት ትምህርት መኾኑንም ተናግረዋል።

የአደጉ ሀገራት የእድገት ምስጢር ለትምህርት የሰጡት ትኩረት መኾኑንም አንስተዋል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ችግር ፈቺ እንደመኾኑ መጠን የትምህርት ጥራት እንዲሻሻል፣ ተደራሽ እና አካታች እንዲኾን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ መኾኑንም ተናግረዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በገባው ቃል መሠረት ትምህርት ቤት ገንብቶ ማስረከቡንም ተናግረዋል። ትምህርት ቤቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። የትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል እና የትምህርት ጥራት እንዲያድግ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ልማት ማኅበር ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፈንታ አልማ የራሳችንን ችግር በራሳችን አቅም እንፍታ ብሎ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል። ትልቁ ችግራችን ትምህርት ነው በሚል ጽንሰ ሃሳብ ባለፉት ዓመታት ትምህርት ላይ ሥንሠራ ቆይተናል ብለዋል።

እንደ ሥራ አሥፈጻሚው ገለጻ ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም ብለዋል። አልማ ቁልፍ መሣሪያ አድርጎ እየሄደ ያለው ትምህርትን ከለወጥን ሁሉን ነገር መለወጥ ይቻላል፣ የሁሉ ነገር መሠረት ትምህርት ነው ብሎ ያምናል ሲሉ ገልጸዋል።

ደረጃቸው የወረዱ ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ሥራ እየሠሩ መኾናቸውን ነው የተናገሩት። አልማ ማኅበረሰቡ የእኔ ነው የሚለው ተቋም መኾኑንም ገልጸዋል። የተማርንበትን ትምህርት ቤት እናልማ በሚል ብሂል ምሁራን እየገነቡ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።

ሁሉንም ማቀናጀት ከቻልን የልማት ችግሮቻችንን እንፈታለን ነው ያሉት። ሁሉም የአልማ ደጋፊዎች ቢኾኑ መልሰው የሚጠቀሙት ራሳቸው መኾናቸውን ነው የተናገሩት።

ከትምህርት ቤቶች ባሻገር በጎንደር ከተማ የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን በአንድ ከተማ ውስጥ ኾነው ነገር ግን የተለያዩ ነዋሪዎችን ያገናኙ ናቸው ነው ያሉት። የከተማዋ ሃብት ቱሪዝም ነው የሚሉት ሥራ አሥፈጻሚው ከዓመታት በፊት ቱሪዝምን ማበልጸጊያ ነው ብለን የአጼ ቴዎድሮስን ሐውልት ስናቆም ልማት አንሠራራ ሳይኾን ትምክህት አንሰራራ ነበር የተባልነው፣ ዛሬ ግን ልማታችሁ እያደገ ነው፣ ልማታችሁን መጠበቅ ደግሞ የእናንተ ነው ብለዋል።

መሪዎች ሕዝብን በልማት ማሳተፍ እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል። ሕዝብ የልማት ተሳታፊ ሲኾን ልማቱን ይመራዋል ነው ያሉት። ሕዝቡም የልማቱ ተሳታፊ እንዲኾን ጥሪ አቅርበዋል።

Gondar city communication

Amhara Education Bureau

21 Nov, 11:24


"ከተባበርን ሁሉን ማድረግ የሚያስችል አቅም አለን" ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

ጎንደር: ኅዳር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የተገነቡ የልማት ሥራዎችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶች፣ ድልድዮች እና ሌሎችም የልማት ሥራዎች ተመርቀዋል። የልማት ሥራዎቹ በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የተገነቡ ናቸው።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ክልሉ በትምህርት ዘርፉ እንዳይወዳደር ፈተናዎች እየገጠሙት መኾኑን ተናግረዋል።

ጠላቶች በትምህርት ዘርፉ ፈተና ቢያበዙም ቅን ልቡና ያላቸው ጀግኖች ደግሞ በመተባበር ችግሩን ለመሻገር ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል።

ትምህርት ለመኖር መንገድን የሚያስተካከል ብቻ አይደለም ያሉት ኀላፊዋ ትምህርት የመኖር ያለ መኖር ጉዳይ ነው ብለዋል።

አባቶች ሳይማሩ ከቅኝ ግዛት ነጻ አድርገዋት ያቆዩዋትን ኢትዮጵያን በሠለጠነው ዘመን በትንሽ ዕውቀት አሳልፈን እንዳንሰጥ በትምህርት የሠለጠነ ትውልድ መፍጠር ይገባል ነው ያሉት። ይህ ካልኾነ በስተቀር በዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውስጥ እንደምንገባ መረዳት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ልጆቻችን አዋቂ እና ተመራማሪ እንዲኾኑ፣ በምክንያት የሚደግፉ እና በምክንያት የሚቃወሙ፣ የራሳቸውን መንገድ የሚወስኑ ብሎም ከሌሎች ዓለማት ጋር ተወዳዳሪ እንዲኾኑ ከፈለግን ትምህርት ላይ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን አስተዋጽኦ ለማስቀጠል እና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ትምህርት ላይ አተኩሮ መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ማንንም ሳንጠብቅ ራሳችን በራሳችን መሥራት እንደምንችል ዛሬ የተመረቁት ትምህርት ቤቶች ማሳያዎች ናቸው ብለዋል። ሥራዎችንም በትብብር መሥራትን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ነው ያሉት።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና አልማ በትምህርት ዘርፉ እያደረጉት ላለው አበርክቶም አመሥግነዋል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እያደረገው ያለውን ሥራ መደገፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

መማር ማለት የባሕሪ ለውጥ ማምጣት እና ያስተማረን ማኅበረሰብ መልሶ መደገፍ ነው ብለዋል። ያስተማረን ሕዝብ አለመደገፍ ማንነትን መርሳት መኾኑንም ተናግረዋል።

በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ ወገኖች የተማሩባቸውን ትምህርት ቤቶች እንዲደግፉ ጠይቀዋል። ከተባበርን፣ ወደ አንድ ከመጣን እና ወደ ቀልባችን ከተመለስን ሁሉን ማድረግ የሚያስችል አቅም አለን ነው ያሉት።

ያለንን አቅም ተጠቅመን የሀገር ክብር ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል። ሁሉም ለትምህርት ዘርፉ ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

ትምህርት ቤቶች፣ ድልድዮች፣ የጌጠኛ መንገድን ጨምሮ 67 ፕሮጀክቶች ናቸው ለአገልግሎት ክፍት የኾኑት።

ዛሬ የሚመረቁ ፕሮጀክቶች ለረጅም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄዎች ኾነው የቆዩ ናቸው ተብሏል። በከተማዋ እየተመረቁ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በከተማ አሥተዳደሩ፣ በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ)፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በግለሰቦች እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ናቸው።

አሚኮ

Amhara Education Bureau

21 Nov, 07:22


በጎንደር ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።

ባሕር ዳር: ኅዳር 12/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በጎንደር ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሸ ደሴ (ዶ.ር)፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የቢሮ ኀላፊዎች፣ ከንቲባዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የኾኑት ሥራዎች ለከተማዋ ዕድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ተብሏል። የልማት ሥራዎቹ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው ናቸው። ትምህርት ቤቶች፣ ድልድዮች፣ የጌጠኛ መንገድ ግንባታዎችን ጨምሮ 67 ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች ለረጅም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄዎች ኾነው የቆዩ ናቸው። በከተማዋ እየተመረቁ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በከተማ አሥተዳደሩ፣ በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ)፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በግለሰቦች እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ናቸው።

አሚኮ

Amhara Education Bureau

19 Nov, 13:46


"ዓለም የምትቀየረው በትምህርት ላይ በሚደረግ ያላሰለሰ ጥረት ነው " የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብርን በቁጥር ፩ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በይፋ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ ፣የብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነወርቅ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጀማል መሀመድ ፣ የህዝብ ተሳትፎና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አንሻ ሰይድ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበን ጨምሮ የኃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባለሀብቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ፕሮግራሙ በይፋ ተጀምሯል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዓለም የምትቀረው በትምህርት ላይ በሚደረግ ያላሰለሰ ጥረት በመሆኑ ለትምህርት ስራ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል ።

ዜጎችን ለትምህርት ቅድሚያ የሰጠ ሀገር በምክንያት የሚያምን ትውልድ ለመገንባት ያስችላል ያሉት ከንቲባው በ2016 ዓ.ም እንደ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ 20 ሚሊዮን ብር ተበጅቶ ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን መመገብ መቻሉን አስረድተዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ይመገባሉ ያሉት ከንቲባው ለዚህ ምገባ ከ75 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ እና በ50 ሚሊዮኑ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን አብራርተዋል።

በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ የሚፈጠሩ ችግሮችን ዋናው መፍቻው ቁልፍ ትምህርት በመሆኑ ለዚህ ድጋፍ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበ የትምህርት ጥራት የሚረጋገጠው በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት በመሆኑ ለውጤቱ ስኬታማነት ህፃናትን በኒውትሬሽን የበለፀገ ምግብ ማግኘት አለባቸው ብለዋል።

ተማሪን ትምህርት ቤት ብቻ በመላክ ውጤት አይገኝም ያሉት መምሪያ ኃላፊው በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ማጠናከር እንደሚገባም አብራርተዋል።

በ2015 በበጎ ፈቃደኛ መምህራን በ500 ተማሪዎች የተጀመረው በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ በ2017 የትምህርት ዘመን 12 ሺህ በላይ ማድረስ መቻሉን አቶ መንግስቱ አበበ ገልጸዋል።

በቀጣይ የተማሪዎች ምገባ ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን ሁሉም ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደረግ ጥሪ አቅርበዋል

በመርሃ ግብሩ ላይ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ በትምህርት ቤት ለተማሪዎች ምገባ ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል።

የኮምቦልቻ ከተማ የተማሪዎች ምገባ ገቢ ማሰባሰቢያ አካውንት
ዳሽን ባንክ 0017828838021
ዓባይ ባንክ 2062111141932918
ንግድ ባንክ 1000657605844 መሆኑም ተገልጿል።

Kombolcha city communication

Amhara Education Bureau

19 Nov, 12:44


በአማራ ክልል እየተገነቡ የሚገኙ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በጥራትና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ውይይት ተካሄደ፡፡
==========================================
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን እየገነቡ ከሚገኙ ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች ጋር ትምህርት ቤቶቹ ጥራታቸውን ጠብቀው በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ተገንብተው እንዲጠናቀቁ የሚያስችል ውይይት አካሂዷል፡፡
ውይይቱን የመሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ በክልላችን እየተገነቡ የሚገኙ ሶስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት የሚያስችል በመሆኑ ኮንትራክተሮች በጥራትና በፍጥነት ስራቸውን ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በሰቆጣ፣ ደብረታቦርና ፍኖተ ሰላም ከተሞች በሶስት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊየን ብር በጀት እየተገነቡ የሚገኙ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የግንባታ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ የተገኙ የግንባታ ተቋራጮች ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት በጥራትና በወቅቱ ገንብተው ለማስረከብ ቃል ገብተዋል፡፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

15 Nov, 10:20


በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታ ተገለዉ የነበሩ የዳንግላ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ።

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዳንግላ ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ርቀው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሚናፍቁት ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።

ይህ መልካም ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ እጅጉ ወሳኝ ነዉ ተብሏል።

መረጃዉ የአዊ ብ/አ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነዉ።

Amhara Education Bureau

14 Nov, 08:50


የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በሥነ ምግባሩ ብቁ፣ ታማኝ እና ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ ሙሉነሽ ደሴ ( ዶ.ር) አሳሰቡ።

ባሕር ዳር: ኅዳር 5/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን "የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታን ለማጠናከር ከትምህርት ዘርፉ መሪዎች፣ ከትምህርት ቤት ርእሳነ መምህራን አና ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር ያዘጋጀውን የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እንደ ሀገር እና ክልል የገጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በሥነ ምግባሩ ብቁ፣ ታማኝ እና ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ማፍራት ይገባል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ትምህርት ቤቶች ዋነኛውን ሚና መጫዎት አለባቸው ነው ያሉት።

በሥነ ምግባር ያልታገዘ ትምህርት ጥፋት ያመጣል ነው ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ፡፡ ትምህርት ቤቶች ትውልዱ ለትንንሽ እንቅፋቶች የማይገፋ፣ ነገ ላይ ትኩረት ያደረገ እና ሀገር ወዳድ እንዲኾን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናበው ከሠሩ አዎንታዊ ለውጥ ይመጣል ብለዋል።

የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሐብታሙ ሞገስ የሚስተዋለውን የሥነ ምግባር ችግር ለማስወገድ በየትምህርት ቤቶች በባለሙያ የተደገፈ የሥነ ምግባር ትምህርት እንደሚሠጡም ገልጸዋል፡፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

12 Nov, 10:04


በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻክል ወረዳና በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ መምህራን፤የትምህርት አመራሮች፤አስተዳደር ሰራተኞች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ሰራተኞች ጋር በወቅታዊ የሰላምና ህግ - ማስከበር እንዲሁም የትምህርት ማስጀመር ተግባራት ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ እና የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራና ስልጠና ም/ኃላፊ አቶ አበጀ አላምረው ተገኝተው ውይይቱን እየመሩት ነው።

🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•
#Eastgojjamzoneprosperityparty

Amhara Education Bureau

11 Nov, 12:41


በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻከል ወረዳ መምህራን በአማኑኤል ከተማ ዉይይት እያካሄዱ ነዉ።

በማቻከል ወረዳ የሚገኙ መምህራን የሚያካሄዱት ዉይይት በመማር ማስተማር፣ በልማት፣ በወቅታዊ ሰላምና ጸጥታ ላይ ነዉ።

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

11 Nov, 10:28


የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ባሕርዳር: ኅዳር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዓለም አቀፍ የህጻናትን ቀን አስመልክቶ ለህጻናት የመማሪያ ቁሳቁስ እና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የተደረገው በዐጼ ሰርጸ ድንግል መላክ ሰገድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ድጋፍ የሚሹ ህጻናት ነው።

የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ በዓሉ በዓለም ለ35ኛ በሀገር ደረጃ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበር መኾኑን ገልጸው መሪ ሀሳቡም ''ህጻናት የሚሉት አላቸው፤ እናዳምጣቸው'' የሚል መኾኑን ጠቅሰዋል።

ህጻናትን ማሳደግ ብቻ ሳይኾን የሚሉትንም እንስማቸው ያሉት ኀላፊዋ በእንግድነት ስሜት እንዲያዳምጡ ብቻ ሳይኾን እንዲናገሩ ማድረግም በእድገታቸው ላይ ሁለንተናዊ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ገልጸዋል።

ስለኾነም በየደረጃው ሥራ እየሠራን ሲኾን በዚህ ትምህርት ቤት ተገኝተን በዓሉን ስናከብር የመማሪያ ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎችንም እናደርጋለን ብለዋል።

ህጻናት ለወላጆቻቸው እና ለማኅበረሰቡ የሚነግሩን ካለ የምናዳምጣቸው ይኾናል ነው ያሉት። በቀጣይም ይህንን መደጋገፍ ምክንያት በማድረግ ከተማሪዎችም ከመምህራንም ጋር እየተመካከርን የህጻናትን ሀሳብ እናዳምጣለን ብለዋል።

የዐጼ ሰርጸ ድንግል መላክ ሰገድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ዓባይነህ የሺዋሥ ለተማሪዎቻችን ድጋፉ መደረጉ አስደስቶናል ብለዋል። ይህ ለተማሪዎቻችን ትልቅ ድጋፍ ነው፤ ለአካል ጉዳተኞችም የልብስ ድጋፉ ችግር ፈቺ መኾኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ወርሃዊ የቤት ኪራይ ክፍያ ቢሸፈንላቸው የኢኮኖሚ ችግራቸው ይቀረፋል ነው ያሉት። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው የምገባ ፕሮግራምም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ክትትል ቢደረግበት ብለዋል።

የድጋፉ ተጠቃሚ ተማሪ ዮናስ ተሻገር አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደብተር ይሰጡ ነበር አሁን ደግሞ ብርድ ልብስ መሰጠቱ ጥሩ ነው ብሏል። ለኛም በተደረገልን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ደብተር በበቂ ስላገኘን ለመማሪያ አንቸገርም፤ ቤተሰቦቻችንም እንዳናስቸግር ያደርገናል ብሏል።

ተማሪ ሂሩት ሰማኸኝ በበኩሏ በተደረገው ድጋፍ ደስተኛ እንደኾነች ገልጻለች። በየዓመቱ የትምህርት ድጋፍ መደረጉም በቁሳቁስ እንዳናስብ አድርጎናል ብላለች።

አሚኮ

Amhara Education Bureau

10 Nov, 05:14


"ትምህርት ለሀገር ሰላም እና ዕድገት ፋይዳው የጎላ ነው" ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
-------/////////-------
በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) አስተባባሪነት የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአልማ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ መላኩ ፋንታ፣ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን የገነቡት ባለሃብት ፀደቀ ይሁኔ (ኢ.ር)፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ.ር)፣ የክልል መሪዎች፣ የደቡብ ወሎ ዞን እና የደሴ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የይሁኔ ወልዱ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር በለጠ ኃይሌ ትምህርት ቤቱ በችግር ውስጥም ኾኖ በሦሥት ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

ርእሰ መምህሩ በ2017 የትምህርት ዘመንም 53 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚያስፈትን እና የተለመደውን ውጤታማነት የሚያስቀጥል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ነው የጠቆሙት፡፡

ትምህርት ቤቱ በርካታ ችግሮች እንዳሉበትም ጠቅሰዋል፡፡

ርእሰ መምህሩ በለጠ ኃይሌ ከተማሪዎች አኳያ እና ከመምህራን ጥቅማጥቅም አንጻር አሉ ያሏቸው ችግሮች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ትምህርት ቤቱ አጥር እንደሚያስፈልገውም ነው ርእሰ መምህሩ ያስገነዘቡት።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) "ትምህርት ለሀገር ሰላም እና ዕድገት ፋይዳው የጎላ ነው" ብለዋል፡፡

ትልቁ ኢንቨስትመንት የሰው ልጅ አዕምሮ ላይ መሥራት ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ትምህርት ቤቱን ለገነቡት ኢንጅነር ፀደቀ ይሁኔ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት፣ አልማ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ እና ባለሃብቱ በጋራ በመኾን በትምህርት ቤቱ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

የአልማ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ መላኩ ፋንታ "ትምህርት ቤቱ ያስመዘገበው ውጤት ክልሉ የሚኮራበት ነው" ብለዋል፡፡

"አልማ የሚችለውን ይደግፋል፤ ተረባርበን ትምህርት ቤቱን ማጠናከር አለብን" ነው ያሉት አቶ መላኩ ፋንታ፡፡

ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ ለተበረከተላቸው ዕውቅና አመሥግነው አሉ የተባሉትን በተለይም የማስፋፊያ፣ የአጥር እና የጥገና ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ቃል ገብተዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ ትምህርት ቤቱን ለገነቡት ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ የምሥጋና ሽልማት ተበርክቷል።

የይሁኔ ወልዱ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት 360 ተማሪዎችን ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንደሚገኝ የዘገበው አሚኮ ነው።

አልማ:30/02/2017ዓ.ም

Amhara Education Bureau

09 Nov, 16:43


በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ተገንብተው ለምረቃ የበቁት የትምህርትና የጤና ተቋማት የሚፈውሱ ትውልድን የሚያክሙ ናቸው፡፡
አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው የኩታበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለ ሁለት ወለል የመማሪያ ክፍል የአማራ ክልልና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

ግንባውታው 21 ሚሎዮን ብር ወጭ እንደወጣበትና 15 የመማሪያ ክፍች እንዳሉት በምረቃ ስነ ስርዓቱ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ይመር ተናግረዋል፡፡

የግንባታው ሙሉ ወጭም በወረዳው መንግስትና በማኅበረሰቡ ተሳትፎ እንደተሸፈነ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ለምረቃ የበቃው ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት በአልማ በጀት የተሸፈነ ነው፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዓለምነው አበራ የትምህርት ሰብአዊና ቁሳዊ ግብአት መሟላት ለትምህርት ጥራት የራሱን ድርሻ ያበረክታል ብለዋል፡፡ትምህርት ቤቶችን ምቹ፣ ውብና ማራኪ ማድረግም የዚሁ አካል ነው፡፡ ትምህርት ለትውልድ በሚል ንቅናቄ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡ በተለይም ደግሞ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶችን በአዲስ መልሶ ለመገንባት የተደረጉ ጥረቶች ስለመኖራቸው ተብራርቷል፡፡

በዞኑ 437 የ1ኛ ደረጃና 37 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበርም አውስተዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ስምንት ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ደግሞ በሁለት ወረዳዎች ሁለት ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውንም አቶ ዓለምነው ገልጸዋል፡፡

በወረዳና በዞን ደረጃ በተደረገም ምክክር በራስ አቅም አራት ወረዳዎች ባለ ሁለት ወለል ትምህርት ቤቶችን መገንባት ችለዋል፡፡ የነዚህንም ተሞክሮ ወደ ሌሎች ወረዳዎች ለማስፋት እየተሠራ ነው ብለዋል አቶ ዓለምነው፡፡

ዘመኑ የድልም የትግልም ነው ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ናቸው፡፡ ከባለፈው ዓመት የጀመረ ግጭት በአማራ ክልል ከፍተኛ ጉዳት መስተናገዱን ገልጸዋል፡፡ አሁንም ታጣቂና ዘራፊ ኃይሉ የጥፋት ተልዕኮውን ያላቆመ በመሆኑ መንግስት ሕዝቡን ከጎኑ አሰልፎ መላ ክልሉን ነጻ ለማውጣት የሚደረግ ትግል አንዱ ነው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

በሌላ በኩል የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በዘለለ ምርትን ለገበያ ለማቅረብ የስንዴና ሌሎች ምርቶችን በውጤታማ መንገድ መፈጸምን ጨምሮ ሌሎች በኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማት እየተመዘገቡ ያሉ ድሎችን ዘላቂ ለማድረግ ማኅበረሰቡ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ያስገነዘቡ ሲሆን በዛሬው ዕለት በኩታበር ወረዳ የተመረቁ ተቋማትን በምሳሌነት በማጣቀስ አቅርበዋል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው አንድ ሀገር የሚያድገውና ተወዳዳሪ መሆን የሚችለው የተማረ ትውልድ ሲኖር ነው ብለዋል፡፡ አማራ ክልልን ጨምሮ ኢትዮጵያ እንዳታድግና ከዓለም እንድትነጠል የታሪካዊ ጠላቶቻችንን አጀንዳ ለማስፈጸም ትጥቅ ይዘው ትምህርትን ከማስተጓጎል ጀምሮ በርካታ ጥፋቶችን እየሠሩ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊት መላ ሕዝቡ ሊያወግዝ እንደሚገባም ነው ቢሮ ኃላፊዋ ያመላከቱት፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳን ጨምሮ በትምህርት ተቋማት ግንባታና በሌሎች ሥራዎች ምሳሌ የሚሆን ሥራ እየተሠራ ስለመሆኑ የጠቆሙት ቢሮ ኃላፊዋ ጅምሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በኩታበር ወረዳ በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁ ተቋማትና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ስንመለከት መንግስት የነደፈው ህልም ምን ያህል መሬት እየነካ ስለመሆኑ ያረጋገጥንበት ነው ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) ናቸው፡፡የትምህርት ቤት ግባታው ለትምህርት ጥራት ተደራሽነት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ኩታበር ወረዳ ተገንብተው ለምረቃ የበቁት የትምህርትና የጤና ተቋማት በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ በመሆኑ ትክክለኛ የልማት አስተዳደርን ተከትለው በመሠራታቸው ትውልድን የሚያክሙና የሚፈውሱ ናቸው ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡ እነዚህና መሰል የልማት ሥራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለዘላቂ ሰላም ማኅበረሰቡ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

04 Nov, 07:03


"የመማር ማስተማር ሥራው የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ባለድርሻ አካላት ትብብር ማድረግ አለባቸው" የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ፡፡

ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መምሪያው የበጀት ዓቱን የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሥራዎች ገምግሟል። ከሩብ ዓመቱ እቅድ 68 በመቶ ማሳካት እንደቻለም መምሪያው አስታውቋል፡፡

የፀጥታው ችግር በመደበኛ የመማር ማስተማር ሥራው ላይ መስተጓጎል ከመፍጠሩ ባሻገር የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናት ተገቢውን አውቀት እንዳይሸምቱ አድርጓል ተብሏል።

ህጻናት በትምህርት ገበታቸው ላይ ተገኝተው መደበኛ ትምህርታቸውን መከታተል ቢኖርባውም ይህንን ተግባር ተፈፃሚ ለማድረግ የሰላም መረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደደር በተገኘው አንጻራዊ ሰላም በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ28 ሺህ በላይ ተማሪዎችን መዝገቦ እያስተማረ ይገኛል፡፡

መምሪያው ከ49 ሺህ በላይ ተማሪችን ማስተናግድ የነበረበት ቢኾንም በሩብ ዓመቱ የነበረው አፈጻጸም ዝቅተኛ እንደነበር ተገምግሟል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ያምራል ታደሰ እስካሁን ማስተማር ያልጀመሩ 15 ትምህርት ቤቶች እንዳሉም ገልጸዋል፡፡

የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በማድረግ በኩል ትልቅ ኀላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ከትምህርት ቢሮ ጋር በመነጋገር የመማር ማስተማር ሥራው የተሳካ እንዲኾን የግብዓት ማሟላት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በአዲስ ካሪክለም የተቀረጹ የግብረ ገብ፣ የአይ ሲቲ እና የዜግነት ትምህርት መጽሐፍትን በአጭር ጊዜ ለተማሪዎች እና ለመምህራን ለማቅርብ እየተሠራ መኾኑን ኀላፊው አስረድተዋል፡፡

በአዲስ የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተም የመምህራን ቅጥር ተፈጻሚ እንደሚኾን መምሪያው አስታውቋል፡፡

አሚኮ

Amhara Education Bureau

03 Nov, 12:50


የሰሜን ሸዋ ትምህርት መምሪያ የ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

የግምገማ መድረኩ የዞን ትምህርትመምሪያ ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ እና ምክትል ኃላፊ በተገኙበት ነው የተከናወነው ።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ እንግዳወርቅ በመክፈቻ ንግግራቸው ከመቸውም በላይ ፈተና ውስጥ ብንሆንም የተማሪ ምዝገባ ስራችን እና የትምህርት ማስጀመር ስራችን አበረታች ነበርም ብለዋል።

ትምህርትን ማቋረጥ የትውልድን የእድገት ሂደት ማቋረጥ መሆኑን ሁሉም አካል ተገንዝቦ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ መተባበርና የተመዘገቡ ተማሪዎችም በአግባቡ እየተማሩ ስለመሆኑ መከታተል እንደሚገባ ተገልጿል።

በዞኑ የእቅድ ዝግጅት ቡድን እና የስረአተ ትምህርት ቡድን የምዝገ፣ትምህርት ማስጀመር። ፤የ6ኛ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን የማለፍ ምጣኔ የውጤት ትንተናን እና የኢኮደር የሰልጠና ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በቀጣይም ያልተመዘገቡ ተማሪዎች እንዲመዘገቡ እና ትምህርት እንዲጀምሩ በትኩረት በመስራት የክልላዊ እና አገር አቀፍ ፈተናዎችን ውጤታማ እንድንሆን በትኩረት መስራት እዳለበት እና ሁሉም የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ምክትል ኃላፊዎች በተመደቡበት ወረዳ እንዲሁም ቀጣና ውጤታማ ስራ መስራት እንዳለባቸው እና ሌሎች ተጨማሪ የትምህርት ስራዎችን መስራት ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል የቀጣይ አቅጣጫዎችም ተመላክተው የእለቱ ውይይት ተጠቃሎአል።የመምሪያው መረጃ እንደሚያመለክተው

#northshewaprosperityparty

Amhara Education Bureau

03 Nov, 12:04


"በተባበረ ክንድ ትምህርት ላይ በመሥራት የነገን ተስፋ የሰነቀ ትውልድ እንገነባለን" አቶ አሸተ ደምለው

ባሕር ዳር: ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በቃብትያ ሁመራ ወረዳ በኅብረተሰቡ ተሳትፎ በብዓከር ቀበሌ የተገነባው "የነገ ተስፋ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት" ዛሬ ተመርቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ፣ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው፣ የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ የ503ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ወርቅነህ ጉዴታ፣ ሜጀር ጀኔራል ሰለሞን ቦጋለ፣ የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አሥተዳዳሪ አታላይ ታፈረ እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

"በተባበረ ክንድ ትምህርት ላይ በመኘሥራት የነገን ተስፍ የሰነቀ ትውልድ መገንባት አለብን" ያሉት የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው የአጸደ ሕጻናት ግንባታው ሕፃናት የሀገራቸውን እና የአካባቢያቸውን እሴት፣ ባሕል እና ትውፊታቸውን አውቀው እንዲያድጉ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ያገኘነውን ነፃነት በማስቀጠል በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆችን በማሳተፍ ዞኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሠራ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህም ያለምንም በጀት ታሪክ የሚያወሳው ሥራን እየሠራን ነው ብለዋል።

በተለይም የአፀደ ሕፃናት ትምህርት ቤቱ ሕፃናት የሀገራቸውን ታሪክ አውቀው እና ተረድተው ነገ በጥሩ ሥነ ልቦና አድገው ሀገራችንን ወደ ተሻለ ጎዳና እንዲያሻግሩ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

ህውሃት በሥልጣን መንበሩ በነበረበት ጊዜ ትምህርት ቤቶች እንዳይከፈቱ እና ትውልዱ ወግ፣ ባሕሉን እና እሴቱን እንዳያውቁ ሲያደርግ መቆየቱን አንስተው ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለመፍጠር ህጻናት ላይ ልንሠራ ይገባል ብለዋል።

የቃብትያ ሁመራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አታላይ ታፈረ የነገውን ሀገር ወዳድ ትውልድ የምናፈራበት በመኾኑ ይህንን የአፀደ ሕፃናት ትምህርት ቤት በወረዳችን በኅብረተሰቡን ተሳትፎ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ግንባታውን አጠናቅቀናል ብለዋል።

በኅብረተሰቡ ተሳትፎ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች በወረዳው መሠራታቸውን ያነሱት ዋና አሥተዳዳሪው ከአፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት በተጨማሪ በአዲህርዲ ከተማ ሆስፒታል እያስገነቡ መኾኑን ገልጸዋል።

ግንባታው ህፃናትን ከስር ኮትኩቶ ለማሳደግ ምቹ መኾኑን ያነሱት አቶ አታላይ አራት የመማሪያ ክፍል መኖሩን አንስተዋል። ከ200 በላይ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፤ ምዝገባው ቀደም ብሎ ተጀምሯል፤ በቅርቡም ሥራ ይጀምራል ነው ያሉት።

ያነጋገርናቸው የባዕከር ከተማ ነዋሪዎች በትምህርት ቤቱ ግንባታ እንደተደሰቱ ገልጸው በልጅነት ጊዜያቸው በመልካም ሥነ ምግባር፣ በታሪክ፣ ወግ እና ባሕላቸውን እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

"ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ነው፤ ለሀምሳ ሰው ግን ጌጥ ነው" የሚሉት ነዋሪዎቹ ስንተባበር የማናደርገው የለም አሁንም አንድነታችን አጠናክረን ለመጭው ትውልድ ታሪክ የሚያወሳውን አሻራችንን ያለበጀት እናኖራለን ብለዋል።

በመድረኩ የሀገረ መንግሥቱ የመጨረሻ ምሽግ የኾነው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የተደፈረበትን ጥቅምት 24 ቀን ታስቦ ውሏል። የሠራዊቱ አባላት በመስዋዕትነታቸው ታሪክ የማይሽረው አዲስ የድል ምዕራፍ የከፈቱልን፤ በህልፈታቸውም የኢትዮጵያን ሕልውና ያፀኑልን በሚል ታውሰው ውለዋል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Amhara Education Bureau

03 Nov, 11:56


በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በቃብትያ ሁመራ ወረዳ በባአከር ቀበሌ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባ የአፀደ ህጻናት ትምህርት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሁኗል።

Wolkayt Tegedie Setit Humera Zone Communication

Amhara Education Bureau

29 Oct, 11:50


የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በክልልና በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ።

ኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በ2016 የትምህርት ዘመን በ6ኛ ክፍል፣በ8ኛ እና በ12ኛ ክፍል በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈንቱ ተስፋዬ ፣ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነወርቅ ፣በብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የህዝብ ተሳትፎና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አንሻ ሰይድ፣ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበን ጨምሮ የከቸማ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የወመህና የትምህርት ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት የእውቅና ሽልማት ፕሮግራም ተካሂዷል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ እንደገለጹት ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረጽ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተማሪዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ብለዋል። የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥ ተቋማቱን ግብዓት ማሟላት ፣ መመዘኛውን ፍትሀዊ ማድረግ ፣ በመማር ማስተማር ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን መፍታት ይገባል ብለዋል ከንቲባው።

በ2017 የትምህርት ዘመን 75 ሚሊየን ብር በጀት በመያዝ ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በትምህርት ቤት ምገባ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

የትምህር መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበ በበኩላቸው ከተማችን ሰላም በመሆኑ የተማሪዎች ውጤት የተሻለ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።

በ2016 በጀት ዓመት 924 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተፈትነው 199 ተማሪዎች ከግማሽ በላይ አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲ መግባታቸውን ገልጸዋል። በ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከተፈተኑ 2 ሺህ 309 ተማሪዎች መካከል 1ሺህ 842 ተማሪዎች ወደ ሚቀጥለው ክፍል መዛወራቸውን ገልጸው በተመሳሳይ ከ6ኛ ክፍል ከተፈተኑት 2ሺህ 105 ተማሪዎች 1ሺህ 736ቱ ተማሪዎች መዛዎራቸውን አብራርተዋል።

በማበረታቻ ሽልማቱ ከ1ሺህ ብር እስከ 60ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማትና ሰርትፍኬት ለተማሪዎች የተበረከተ ሲሆን ተቋማትና ግለሰቦችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

መረጃው የኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን ነው

Amhara Education Bureau

29 Oct, 11:50


ተስፋ ሰንቀው ወደ ትምህርት ቤት የሄዱ ተማሪዎች በሰላም እንዲመለሱ፣ አካባቢን ምቹና ሰላማዊ ማድረግ እንደሚገባ የጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ አሳሰበ፡፡

ባሕር ዳር: ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ትምህርት ሀገር የሚገነባበት ትልቅ መሣሪያ ነዉ፤ ትምህርት ማኅበራዊ ልማት ነዉ። ለሀገርም፣ ለቤተሰብም፣ ለአካባቢም ተስፋ ሰንቀዉ ወደ ትምህርት ቤት የሄዱ ተማሪዎች በሰላም እንዲመለሱ ምቹና ሰላማዊ የኾነ አካባቢ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመምህራን እና በርእሰ መምህራን የሚሞላ አይደለም። ከዚህም ከፍ ባለ እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ኃላፊነቱን መወጣት አለበት፡፡

የጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ነጻነት መንግሥቴ በመምሪያው በ2017 በጀት ዓመት 122ሺህ 143 ተማሪ ለመመዝገብ በማቀድ ወደ ሥራ እንደተገባ ገልጸዋል፡፡

ከታቀደው ዕቅድ ውስጥ 89ሺህ 215 ተማሪዎችን ብቻ በመመዝገብ ወደ ትምህርት ገበታ ማስገባት እንደተቻለ ነው የገለጹት፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትምህርት ከተዘጋባቸው አካባቢዎች ወደ ከተማ መጥተው የሚማሩት ተማሪዎችን በመመዝገብ ትምህርት እንዲጀምሩ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

በመምሪያው እስካሁን ባለው መረጃ 89 ሺህ 215 የሚኾኑ ተማሪዎች ትምህርት ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ሥራ የክረምት ተግባራትን መሠረት በማድረግ የትምህርት ቁሶችን በመጠገን፣ ትምህርት ቤቶችን ምቹና ማራኪ በማድረግ እና የተለያዩ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት በርካታ ሥራዎች እንደተሠሩ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 20 ሺህ ለሚኾኑ አቅመ ደካማ ተማሪዎች ከተለያዩ ተቋማትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ ከክልሉ መንግሥት እና ከአካባቢዉ ባለሃብቶች በማሠባሠብ 20 ሚሊዮን ብር ሊያወጣ የሚችል የትምህርት ቁሳቁስ እንዳሰራጩ ተናግረዋል፡፡

በግጭቱ ምክንያት በክልሉ ብዙ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፡፡ በዚህ ከቀጠለ ከፍተኛ የኾነ የትውልድ ክፍተት ይፈጠራል፡፡ ይህ ክፍተት ዘመን የሚሻገር ጠባሳ ጥሎ ነው የሚያልፈው ይላሉ፡፡

በመምሪያው አሁንም በተለያዩ የፀጥታና የደኅንነት ስጋቶች የተዘጉ 2 ሁለተኛ ደረጃ እና 9 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ነው የተናገሩት፡፡

የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ለማስከፈት መጀመሪያ ከተማውን ከስጋት ነጻ በማድረግ የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስቀጠል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ሀገር የሚገነባበት ትልቅ መሣሪያ በመኾኑ ማንኛውንም ዜጋ ለትምህርት አስፈላጊ እና አጋዥ የኾኑ ሥራዎችን በመከወን፤ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማምጣት ሚናውን እንዲወጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

አሚኮ

Amhara Education Bureau

27 Oct, 12:38


ተወዳዳሪ ተማሪ ለማፍራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ

ባህርዳር _ ጥቅምት 17/2017(ትምህርት ቢሮ)፡-የደብረብርሃን ከተማ ትምህርት መምሪያ በ2016 ዓ.ም በ6ኛ፣በ8ኛ እና በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ።

የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ ብዙነህ እንደተናገሩት ለዚህ ውጤት መመዝገብ ከትምህርት መምሪያው ጋር ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ አካላትን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በ2016 ዓ.ም ክልል አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እንዲመዘገብ ትምህርት መምሪያው በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን አንስተዋል።

ለአብነትም ለ6ኛ፣ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍሎች ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት፣ ወርክሽቶችን በማዘጋጀት፣ ሞዴል ፈተናዎች እና ሌሎች ስራዎች በስፋት መከናወናቸውን አብራርተዋል።
በሂደቱ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ የደብረብርሃን ማህበረ ቅዱሳን እንዲሁም አጋር ድርጅቶች ሚናቸው ክፍተኛ እንደነበር ጠቅሰው አመስግነዋል።

ተማሪዎቹ የሀገር ኩራት ስለሆኑ ከተማ አስተዳደሩ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር መድቦ የገንዘብና እና የሰርተፍኬት ማበረታቻ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑን አመልክተዋል። ፕሮግራሙ እንዲሳካ ከንቲባው ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

በ2016 ዓ.ም ክልል አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ 52 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 21ዱ ትምህርት ቤቶች ሁሉንም ተማሪዎች ማሳለፋቸውን አንስተዋል። እንደ ከተማም ጥሩ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው በአጠቃላይ ከ85 በመቶ በላይ ተማሪዎች ወደ ሚቀጥለው ክፍል መዛወራቸውን ጠቁመዋል።

በ12ኛ ክፍል ፈተናም በሀገር አቀፉ እና በክልሉ ከተመዘገበው ውጤት የተሻለ ከ14 በመቶ በላይ ተማሪዎች ማለፋቸውን አስታውቀዋል።

በ2017 ዓ.ም ከዚህ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የትምህርት ባለሙያዎች እና አጋር አካላት የድርሻቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ወይዘሮ መቅደስ አደራ ብለዋል።

የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ የተከበሩ በድሉ ውብሸት በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት በራሳችሁ ጥረትና በሌሎች እገዛ ለዚህ ውጤት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በፀጥታ ችግር ውስጥ ሆነው ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ለሰሩ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አጋር አካላት ድካማቸው ፍሬ በማፍራቱ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከስታናዳርድር አንፃር ከዚህ በላይ ውጤት ማምጣት የሚጠበቅ ቢሆንም አሁን ላይ ብዙ ተማሪዎች ተወዳዳሪ መሆን እንዳልቻሉ አንስተዋል፡፡ ተወዳዳሪ ተማሪ ማፍራት ካልቻልን የትውልድ ቅብብሎሽ እንደማይኖር ጠቁመዋል፡፡

ተወዳዳሪ ተማሪ ለማፍራት የትምህርትን ስራ ለመምህራን ብቻ የሚተው ሳይሆን ወላጆች፣የፖለቲካ አመራሩ እና ሁሉም ባላድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ከንቲባ በድሉ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል በክልሉ ተማሪዎች እንዳይማሩ፣ በከተማውም በገጠር ቀበሌዎች ትምህርት እንዳይጀምሩ የሚሰራ ሃይል መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ይህ ትክክል አለመሆኑ ጠቅሰው ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመጡ ተጋግዘን መስራት አለብን ብለዋል፡፡

ውጤት እንዲቀጥል በተለያዩ ምክንያቶች አመርቂ ውጤት ያላስመዘገቡ ትምህርት ቤቶች ከውጤታማዎቹ ትምህርት ሊወስዱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ስራ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል፡፡

በ6ኛ እና በ8ኛ ከፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 6 ተማሪዎች ከ8 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ5 መቶ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 17 ተማሪዎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር እና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ስራ ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ መምህራን የማበረታቻ ሽልማት፣ የዋንጫና የዕውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል።

በፕሮግራሙ የክልልና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ መምህራን፣ ተሸላሚ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መረጃው የደብረብርሐን ከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው

Amhara Education Bureau

26 Oct, 09:05


ጾታ ተኮር ጥቃቶችን ማስቆም የሁሉም ድርሻ እና ኀላፊነት መኾኑን ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ገለጹ።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዛሬ የዓለም አቀፍ የታዳጊ ልጃገረዶችን ቀንን አስመልክቶ ክልላዊ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው፡፡

"ታዳጊ ሴቶች ላይ መሥራት የነገን የተሻለ ሀገር መገንባት ነው" በሚል መሪ መልዕክት ነው መርሐ ግብሩ በባሕር ዳር የተጀመረው፡፡

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ የክልሉ መንግሥት የታዳጊ ሴቶች ርዕይ የተሳካ እንዲኾን እና ድምጻቸው እንዲሰማ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኀላፊዋ አሁንም በአንድ ሀገር እና ክልል ቁጥራቸው ቀላል ያልኾኑ ሴቶች ጾታን መሠረት ላደረገ ጥቃት ሲጋለጡ ይታያሉ። እናም በሁሉም ዘርፍ ታዳጊዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መሥራት ግድ ይላል ነው ያሉት።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እንዳሉት ሴቶች ለሰላም፣ ለልማት እና ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ መሥራት አስፈላጊ ነው።

ዶክተር ሙሉነሽ ጾታ ተኮር ጥቃቶችን ማስቆም የሁሉም ድርሻ እና ኀላፊነት እንደኾነም አስገንዝበዋል።

በዚህ ዓመት በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበው ከተሸለሙት 219 ተማሪዎች መካከል 55ቱ ሴቶች ስለመኾናቸውም ተናግረዋል። ይህም ጥሩ ማሳያ እንደኾነ ነው ዶክተር ሙሉነሽ የጠቆሙት።

ዓለም አቀፍ የታዳጊ ልጃገረዶች ቀን በዓለም ለ14ኛ በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ በአማራ ክልል ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከበረ ነው።

አሚኮ

Amhara Education Bureau

25 Oct, 13:31


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ለተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።
በዚህ መሠረት አቶ ደምስ እንድሪስ ይማም የአብክመ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን!!

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

25 Oct, 11:54


ስርጭቱ እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ለመግታት ሁሉም መረባረብ እንዳለበት ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) አሳሰቡ።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና የኀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ የተዘጋጀ ክልላዊ ጤና ጣቢያ መር ማኀበረሰብ አቀፍ የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ወቅት በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት እና ለመቆጣጠር ሁሉም የኅብረተሰብ አካል የመፍትሔ መንገዶችን አውቆ በጋራ መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል።

የክልሉ መንግሥት ማንኛውንም ወባን የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራን እንደሚደግፍም ተናግረዋል።

በመርሐ ግብሩ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴን ጨምሮ የክልሉ ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አሚኮ

Amhara Education Bureau

23 Oct, 04:58


ትምህርት ቤቱ 2 ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የአንድነት ትምህርት ቤት ከቻይና ፋውንዴሽን ግብረ ሰናይ ድርጅት ባገኘው 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ 2 ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የአንድነት ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ባዩ ሃይለጊዮርጊስ እንደገለጹት፤ ቻይና ፋውንዴሽን የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ከባለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት መስተት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ የምገባ አገልግሎት መሰጠት በመቻሉ የመማር ማስተማሩን ስራ ውጤታማ እንዳደረገው የገለጹት ሃላፊው ከበፊቱ በተሻለ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል አድርጓልም ብለዋል፡፡

የቻይና ፋውንዴሽን ፎር ሩራል ዲቨሎፕመንት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ወርቁ በበኩላቸው፤ በ2015 ዓ.ም ለ1 ሺህ 750 ተማሪዎችን ለመመገብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተፈራርመው ወደ ስራ መግባቱን አውስተው በዚህ ዓመት ከ10 ሚሊዮን ብር ላይ በጀት በመመደብ 2 ሺህ ተማሪዎች ተመሳሳይ የምገባ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ ከቻይና ፓክ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ከምገባ አገልግሎት በተጨማሪ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉንም ነው የገለጹት፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የምገባ ፕሮግራሙን እንደ መልካም ተሞክሮ ወስዶ ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች ለማስፋት በእቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ከደብረ ብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

19 Oct, 17:21


በትምህርት መስተጓጎል የትውልድ ክፍተት እንዳይፈጠር ሁሉም ኀላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በአማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ እስከ መስከረም 8/2017 ዓ.ም በክልሉ መመዝገብ የተቻለው በ89 በመቶ በሚኾኑ ወረዳዎች፣ 55 በመቶ በሚኾኑ ትምህርት ቤቶች 2 ሚሊዮን 295 ሺህ 150 ተማሪዎችን ብቻ መኾኑን በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

በተለይም ደግሞ ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር እንዳላቸው በሚታመንባቸው ሰሜን፣ ምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ደቡብ ጎንደር ዞን እና ከፊል አዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተማሪ ምዝገባው ዝቅተኛ መኾኑን አስረድተዋል።

በሰሜን፣ ምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች ደግሞ 10 በመቶ እንኳ ምዝገባ ማካሄድ አለመቻሉን አንስተዋል።

በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተሟላ መንገድ ወደ ሥራ እንዲገቡ ከማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሠራ መኾኑን ኀላፊዋ ገልጸዋል።

ዘግይተው ለሚመዘገቡ ተማሪዎች ቢሮው የተለየ አሠራርም እንደሚከተል ተናግረዋል። ይዘቶችን ከጊዜ ጋር መከለስ፣ ቅዳሜ እና እሑድን ጨምሮ ትርፍ ሰዓትን ማስተማር፣ ክፍለ ጊዜ በመጨመር እና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ሊተገበር እንደሚችል ነው የገለጹት።

ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በፍጥነት ተመዝግበው ትምህርት እንዲጀምሩም ሁሉም አካል ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ዘገባው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው

Amhara Education Bureau

19 Oct, 08:56


በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ እየተዘጋጀን ነው - የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች

ደሴ፤ ጥቅምት 9/2017(ኢዜአ)፡- በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወደ ዩኒቨርሲቲ ማስገባት የሚያስችል ውጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ እየተዘጋጁ እንደሚገኙ በደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች ተናገሩ።

የመማር ማስተማር ስራውን የተሳካ በማድረግ ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለማፍራት እየሰሩ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ገልጸዋል።

በትምህርት ቤቱ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ብሩክታዊት ሀብቴ፤ ጠንክራ ተምራ በዲጅታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ የማጥናትና የመመራመር ራዕይ እንዳላት ለኢዜአ ተናግራለች።

ለዚህም ቀጣይ ለምትወስደው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ እየተዘጋጀች እንደምትገኝ ገልጻለች።

በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራው በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተሰጣቸው መሆኑን ጠቅሳ፤ ይህን በመጠቀም የበለጠ ውጤታማ ለመሆን በመትጋት ላይ እንደምትገኝ አመልክታለች።

ሌላው የ12ኛ ክፍል ተማሪ ወርቁ ሙሉሰው በበኩሉ፤ ትምህርት ቤቱ በውድድር የተሻለ ውጤት እንድናስመዘግብ እድል እየፈጠረልን ነው ብሏል።

ትምህርቴን በአግባቡ ተከታትዬ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ እየተዘጋጀሁ ነው ሲል ገልጿል።

ችግሮችን በመቋቋም የሚፈልጉት ደረጃ ላይ ለመድረስ የራስ ጥረት ወሳኝ መሆኑን የቀደሙ ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት መረዳቱን የተናገረው ሌላው የ12ኛ ክፍል ተማሪ ከፍያለው ጓዴ ነው።

በህክምናው ዘርፍ ከአንገት በላይ ቀዶ ህክምና ዶክተር ለመሆን እንደሚፈልግና ይህንን ለማሳካትም ትምህርቱን ጠንክሮ እያጠና መሆኑን ገልጿል።

በደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የባዮሎጂ መምህር ሐጅ ማሞ፤ የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት፣ አቀባበል፣ ተነሳሽነትና ራዕያቸውን ለማሳካት እገዛ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከመደበኛው መማር ማስተማር ጊዜ በተጨማሪ በትርፍ ጊዜያቸው ጭምር ለተማሪዎቹ እገዛ እያደረጉላቸው መሆኑን አስረድተዋል።

በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራውን የተሳካ በማድረግ የማሳለፍ አቅሙን ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ በለጠ ሀይሌ ናቸው።

ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም በትምህርት ቤቱ የተሻለ የሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ መመቻቸቱን ተናግረዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሙሉ ተማሪዎችን በማሳለፍ ከፍተኛውን ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት ደግሞ ብሔራዊ ፈተናውን ከወሰዱት 65 ተማሪዎች ማለትም 70 በመቶ የሚሆኑት ከ500 በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።

ዘንድሮም ብሔራዊ ፈተናውን የሚወስዱ 56 ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፤ ተሞክሮና ልምዳችንን ለሌሎች ትምህርት ቤቶችም እያካፈልን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በደሴ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ያሲን አህመድ እንዳሉት፤ በከተማው የ2017 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል።

በዚህም ቀጣይ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎች በየክፍል ደረጃቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በተለይ የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ተሞክሮና ልምድ በማስፋት በሌሎች ትምህርት ቤቶችም የተሻሉ ተማሪዎችን በመለየት ልዩ ክፍል እየተፈጠረ ነው ብለዋል።

በዚህም ባለፈው ዓመት በመምህር አካለወልድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 76 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በልዩ መምህርና ክፍል በማስተማር 70 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማድረግ እንደተቻለ ጠቅሰዋል።

ዘንድሮ በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ልዩ መማሪያ ክፍል እንዲኖር በማድረግ የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን ተናገረዋል።

የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል 400 ተማሪዎች ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ ከትምህርት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

መረጃው የኢዜአ ነው