ጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/SG-41/2017
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ለድርጅቶች የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሲሆን ለግለሰብ ደግሞ መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚመጣ ተዛማጅ የሆነ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም ተጫራች ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው ፡፡
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ-1 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ-1 የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ አንድ ቢሮ
አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ
አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት-ለፊት
ስልክ ቁጥር 0118 72 29 91/ 0118-72 29 58