Ikhlas institute @ikhlasikhlas1 Channel on Telegram

Ikhlas institute

@ikhlasikhlas1


🤍 بِسْـــــــــــــمِ اللهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِـــــــــــــيم



For any contact owner
Admin @Dreams080

Ikhlas institute (Arabic)

معهد إخلاص هو قناة تيليجرام تهدف إلى تقديم المعرفة والتعليم في مجالات متنوعة. يمكنك الانضمام إلى هذه القناة للاستفادة من الدروس والموارد التعليمية التي تقدمها. الهدف الرئيسي من معهد إخلاص هو تعزيز التعليم والتعلم الشامل للجميع. سواء كنت طالبًا أو مدرسًا أو مهتمًا بالتعليم بشكل عام، ستجد شيئًا مفيدًا في هذه القناة. يمكنك التواصل مع صاحب القناة عن طريق الاتصال بالمالك @Lunasir أو الإداري @Dreams080. انضم إلى معهد إخلاص اليوم للتعلم والتطور المستمر!

Ikhlas institute

06 Dec, 19:26


ሁሉም ካንተ ስህተትህን ሲጠባበቅ
አላህ ግን...❤️‍🩹
ፀፀትህን ነው ሚጠብቀው

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

06 Dec, 19:02


ያንዳንድ ሰዎች ቀልድ ግን እግር እግር እያለኝ ነው

ዛሬ አንዱን ጓደኛዬን ሰሞኑን መርሳት አብዝቻለው
ምኖኜ ነው አልኩት ምን ቢል ጥሩ ነው " አግባበት " የምርህን ነው 😕

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

06 Dec, 03:30


'
አንዳንድ ውበቶች አሉ...
አላየናቸውም፣አላወቅናቸውምም ነገር ግን እንናፍቃቸዋለንም ፣ እንወዳቸዋለንም 🥺


ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ

Ikhlas institute

05 Dec, 19:08


🔥 ከለር፣ ዋተር፣ መለያ፣ ጋቢ፣ ፍሩት እንዲሁም ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ፤ ! ስለማክበር

አሰላሙአለይኩም ውረህመቱላህ
ቢስሚላህ አልሃምዱሉላህ
ተማሪዎችን አስመልክቶ በተለይ 12 ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የተለያዩ የሚያከብሯቸው ቀኖች አሉ ለምሳሌ ዋተር ደይ፣ ከለር ደይ፣ መለያ ደይ፣ ጋቢ ደይ ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ እነዚህም ቀኖች ሲከበሩ ብዙ ሃራም ነገሮች ይሰራሉ ለምስሌ፦ ዘፈን፣ ጭፍራ፣ ወንድና ሴት ቅልቅል፣ ሴቶችም ሚፈትኑ ልብሶችን ለብሰው መገኘት አለ በዚህም ተግባር ላይ ሙስሊም ተማሪዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሲያከብሩና ሲሳተፉ ይታያል። ወላሂ በጣም ነው ሚያሳፍረው እንዴት አንድ እህት ሙስሊም የሚል ስም ይዛ ማንም ወንድጋ አብራ ትጨፍራለች።!? የቪዲዩም ማስረጃ አለኝ አብረው ሲጨፍሩ የሚያሳይ ይሄ በጣም የሚያም ነገር ነው። እንዴት ይሆናል! እንዴት ከልካይስ የለም።!?

ወድ ወንድም እህቶች መጨፍር ወንድና ሴት ሁኖ መቀላቀሉንና ሌላውንም ወንጀል ቀላል ባይሆንም ግን ከዛ የከበደውን አንድ ያላስተዋላችሁትን ከባድ ነገር ላስታውሳችሁ ማንኛውንም ቀን አላህ የደስታ ቀን ብሎ ከደነገገልን ውጭ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ እጅግ በጣም ከባድ ወንጀል ነው። ምን አልባትም እንደ ዝሙትና ሰው መግደል የመሳስሉ ወንጀሎችንም ሊበልጥ ይችላል እንዴት ካላችሁኝ አንድ ሰው አንድን ቀን የደስታ ቀን አድርጎ ሲይዝ አላህ ደንግጎልናል ብለን ባናውራም እንኳ ተግባራችን ግን የሚገልፀው ያንን ነው ይሄ ደግሞ አላህን ማስዋሸት ነው ለዚህም ከባድ ወንጀል ያደርገዋል።!ሙስሊም ከሆን ኢስላም እንደፈለግን እንዳንሆን ገድቦናል ህይወታችንም ሞታችንም ለአላህ ነውና አላህን እንፍራ። 



በመጨረሻም ወድ እህት ወንድሞች አላህን እንፍራ አላህ ካልደነገገልን ተግባሮች እንራቅ ለጊዚያዊ ደስታ ብለን አኼራችንን አናበላሸው እዛ ሂደን ጨፍረን አስር ደይቃ ልንደሰት እንችላለን ወንጀሉ ግን ይፃፍብናል ነገም እንጠየቅበታለን። ሙስሊም ደግሞ ከአላህ ቅጣት ውጭ የሚያስጨንቀው ነገር የለምና አላህን እንፍራ ከነዚህ ተግባሮች እንራቅ ከኛ የሚጠበቀውም ሰበብ ማድረስ ነውና የሚያከብሩትንም እህት ወንድሞች እንዳያከብሩ እናስታውሳቸው። ያከበራችሁም ካላችሁ ትክክለኛ ተውበት አድርጉና ወድ አላህ ተመለሱ።
ጠቅለል ሲል የተከለከልነውን ወንጀል መስራትና በእምነት ላይ የሌለን ተግባር መስራት የተለያዩ ናቸው። የሌለን ነገር መስራት ከባድ ወንጀል ነው የተከለከልነውን ወንጀል ከመስራት በላይ ነው። ወላሁ አእለም

✍️@Esra4314

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

05 Dec, 18:11


.
ያረብ...
በ ሰው ላይ አይቼ የጠላሁትን ነዉር በኔ ላይ አታሳየኝ ❤️
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

04 Dec, 19:36


እሷ: ሁቢ ግን እንደዚ ደሀ መሆንህን ባቅ ኖሮ አላገባክም ነበር!😤

ባል: ህይወቴ አንቺ ነሽ! አንቺ ብቻ ነሽ ያለሽኝ ስልሽ ምን መስሎሽ ነበር ታዲያ?😏😎


😁😂🤣
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

04 Dec, 19:05


.
ሀቢቢ...ብቻ ጠንክርና ሰርተህ ብር
ይኑርህ እንጂ የሚያኗኑርክ አታጣም 😎

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

03 Dec, 03:49


" ስታድግ ነው የሚገባህ " ተብላቹ ስታድጉ የገባችሁ ነገር ምንድነው ?

Ikhlas institute

02 Dec, 08:18


ተስፋ እንዳትቆርጡ  ትዝ ካላችሁ class አልገባኝም ይደገምልኝ ምትለዋ ልጅ እሷራሱ ስራ ይዛለች
°
°
°
አሁን ቴሌ ገብታ #Please_try again_እያለች እያዛገችን ነዉ አሉ 🤨

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

01 Dec, 20:27


.
ባል :-4 ሚስት ባገባ ካንቺ ምንድነው ምሰማው....
ሚስት:-ምትሰማውማ....
ጌታህ ማነው ??
ዲንክ ምንድነው ??
ነብይክ ማነው ??

dead
.
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

01 Dec, 18:10


ፍቅር #እና ዉዴታ

አንድ ቆንጅዬ  አበባ ሽታዋ የሚያዉድ ዉብ አበባ  ታያለህ ከዛም  ደስ ትልህና ትቆርጣታለህ። የግልህም ታደርጋታለህ
ይህ #ዉዴታ  ይባላል

በተመሳሳይ አንድ ቆንጅዬ  አበባ ሽታዋ የሚያዉድ ዉብ አበባ  ታያለህ ከዛም ዉሐን በማጠጣት ትንከባከባታለህ ሌሎች እንዳይቀጥፏትም ትከላከልላታለህ።

ይህ ደግሞ #ፍቅር ይባላል።

ስትወዳት ትቆርጣታለህ
ስታፈቅራት ግን ትንከባከባታለህ

ወዳጆቼ  በዉዴታ እና ፍቅር መካከል  ሰፊ ልዩነት  አለ  መጀመሪያ ፍቅር ምን እንደሆን እወቁ የወደዳችሁም  የተመቻችሁም ጊዜ አፈቀርን እያላቹህ እንደዉ ዝምብላቹህ  ሚዲያ ላይ #አትነፋረቁብን!  ሲቀጥል  ፍቅር እንዲህ  አታቅልሉት Or አታርክሱት!  ቀላል ነገርኮ አይደለም! ብዙ መስዋዕትነት ብዙ ዋጋ ብዙ ህመም  ብዙ ስቃይ አለዉ። ዛሬ ይዞ ነገ ሚለቅ ዛሬ ፈልጎ ነገ የሚጠላ አይደለም!

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

30 Nov, 20:36


.
ባልየው ስራ ውሎ ሲመጣ ለሚስቱ ምን ላምጣልሽ አላት....

ሚስት 🧕:- ከኔ ሌላ ሴት ሳያዩ የዋሉ ሁለት አይኖችህን 🥰


Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

30 Nov, 19:23


    የሆነ ሰው……………

"አንዴ ብቻህን ላናግርህ ፈልጌህ ነበር"
  ብሎህ ያውቃል? ምን ዐይነት ስሜት ነው የሚሰማህ??

ፍራቻ፣ ድንጋጤ፣ ስጋት፣ ዐስር ዐይነት ሀሳቦች አእምሮህ ውስጥ ይርመሰመሳሉ ኣ?

  ለምን ፈለገኝ?፣ ምን ሊጠይቀኝ ነው?፣ ስለ ምን ሊያወራኝ ነው?፣፣፣ የመሳሰሉ ሀሳቦች ይመላለሱብሃል።

በአጠቃላይ…………
  ለአፍታም ቢሆን መንፈስህ ይረበሻል!!



እንግዲያውስ አላህ የቀጠረንን አስታውስ፦
📖{وَكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا}
{የቂያማ ቀን ሁላቸውም ለየብቻ ሆነው ይመጣሉ።}


  ጓደኛ የለ፣ ቤተሰብ የለ፣ ወዳጅ ዘመድ የለ፣ ከኻሊቀ ሰማዋቲ ወልአርድ ጋ ብቻህን ቆመህ ት ጠ የ ቃ ለ ህ ።
   አስበነው ተዘጋጅተናል ወይ???

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

27 Nov, 18:39


ሁሉም ሰው የርሱ ታሪክ ባልሆነ ነገር ላይ ጠቢብ ነው። [ዓባስ አል-ዒቃድ]
በመከራው ያልተገረፈ ሰው ስለትዕግስት ለማውራት ጠቢብ ይሆናል። የድህነትን ህይወት ያላየ ሰው ድሆችን ስለሀብትና ድህነት በመንገር ሊቅ ይሆናል። ፈተናውን ያልተቋደሰ ሰው ስለፅናት በመምከር አዋቂ ይሆናል። ሁሉም ባልደረሰበት የችግር ህይወትና ታሪክ ውስጥ ጉምቱ ጠቢብ ነው፡፡

http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot

Te~@ikhasikhlas1
Te~@ikhasikhlas1

Ikhlas institute

27 Nov, 18:31


ስልካችሁ #Data ስታበሩ ብር እየጨረሰ ካስቸገራችሁ# Dataውን አጥፍታችሁ ሞክሩት አይበላም!

Te@~ikhasikhlas1
Te@~ikhasikhlas1

Ikhlas institute

26 Nov, 20:12


.
ኢላሂዬ....🤲

የተነፋፈቁ ልቦችን ሁሉ በእዝነትህ
አገናኛቸው🥺

Te~@ikhasikhlas1
Te~@ikhasikhlas1

Ikhlas institute

26 Nov, 20:12




እውቀት ተግባርን ስለመጠየቁ




ስመ ጥሩ ሰዎች ሁሉ አንድን ነገር ባወቁ ቁጥር ነብዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) ቡኻሪ እና ሙስሊም በዘገቡት ሃዲስ { በ አንድ ነገር ሳዛቹህ የ አቅማችሁን ያክል ተግብሩት የ ከለከልኳቹህን ግን ሁሉንም ተዉት። } ያሉትን መመሪያ ለማክበር ብለውና አላህ (እነዚያ ትዕዛዙን የሚጥሱ ሰዎች በ ዱኒያ ቅጣት እንዳይደርስባቸው ወይንም በ አኺራ አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ ) በማለት የተናገረውን ለመተግበር አቅማቸው በፈቀደው ልክ ሲሯሯጡና ሰዎችንም ወደዚያው ተግባር ለመጥራት ሲጣደፉ ነበረ የሚታዩት። በዚህ ጉዳይ ከፍተኛ አርዐያ ነበሩ ከሚባሉ ሰዎች መሃከል; ከነብዩ ( ﷺ ) ሙስሊም በዘገቡት ሃዲስ( በቀን እና በሌሊት አስራ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው በነዚህ ምክንያት በጀነት ውስጥ ቤት ይገበባለታል) ተብሏል። ይህንን ሃዲስ ከነብዩ ( ﷺ )ያወሩት እናታችን ሃቢባ رضي الله عنها (ይህንን ሃዲስ ከሰማሁኝ በኋላ አንድም ቀን አልተውኳቸውም)ይላሉ። (አንድ ሙስሊም ንዛዜ ያለበትን ነገር ሳይናዘዝ ሶስት ሌሊት ሊያልፈው አይገባም) የሚለውን ሃዲስ ያወር ታላቅ ሰሃቢይ አብዱላህ ኢብኑ ዑመር (رضي الله عنه ) [ አንድም ቀን ኑዛዜ ሳላደርግ አድሬ አላውቅም ] ብለዋል። ታላቁ መሪ ኢማም አህመድ ኢብን ሃንበል ( رحمه الله )(አንድም ሃዲስ ጽፌ አላውቅም ፤ የተገበርኩት ቢሆን እንጂ ። ነቢዩ ( ﷺ ) ታግመው ለ አቡጠይባ አንድ ዲናር ስጡ የሚለውን ሃዲስ ስሰማ ታግሜ አንድ ታግሜ አንድ ዲናር ሰጠሁ።) ብለዋል። ታላቁ መሪ ቡኻሪም (رحمه الله ) እንዲህ ብለው ነበረ ( ሓሜት ሃራም መሆኑን ከሰማሁኝ ጀመሬ አንድም ቀን አምቼ አላውቅም ። አንድንም ሰው አምተሃል ብሎ እንደማይመረምረኝ አላህን ተስፋ አደርጋለሁ )
.
.
.
ይቀጥላል ኢንሻላህ
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot
.

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

26 Nov, 19:36


We were so excited to become an adult. Look at us now Tired, lost, confused and anxious at the same time. But remember,

فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا

"For indeed, with hardship comes ease. Indeed, with hardship comes ease." (Quran 94:5-6)

No matter how challenging life may seem, remember that ease always follows difficulty. Hold on to hope and trust in Allah's plan. 💗
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

24 Nov, 20:39


@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

18 Nov, 19:30




እውቀት ተግባርን ስለመጠየቁ

ከዚህ በፊት ያሳለፍናቸውን የዚህን ጽሁፍ ክፍሎች መሰረት አድርገን ፤ የሰሃቦችን ፈለግ ተከትለን እኛም እንዳንሰራቸው የተከለከሉ ነገራቶችን መከልከል መቻል አለብን ከነዚህ ክልከላዎች በጥቂቱ ;

ይውልኝ እና ይስሙልኝ ; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) {ለይስሙልኝ የሰራ ሰው አላህ ስራውን ያሰማበታል፤ ለይዩልኝ የሰራ ሰው ሚስጥሩን ያወጣበታል } ብለዋል።

ላዩን አሳምሮ ውስጡ የተበላሸ; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) { በቂያማ እለት የቲሃማን ጋራ የሚያህል ነጫጭ በጎ ተግባርን ይዘው የሚመጡ ከዚያም አላህ እንደተበተነ ትቢያ የሚያበንባቸው ክፍሎች አሉ ። ሲሉ ሰውባን እነሱን ሳናውቅ እንዳንመስል እነማን እንደሆኑ ይግለጹልን ሲላቸው እነሱ ከናንተው የተወለዱ የናንተው ናቸው። ሌሊት እናንተ እንደምትቆሙ እነሱም የሚቆሙ ነገር ግን አላህ የከለከለውን ነገር ብቻቸውን ሲያገኙት የሚደፍሩ ናቸው } ብለዋል ።

ኩራት ; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) { በልቡ ቅንጣት ያክል ኩራት ያለበት ጀነት አይገባም ። ኩራት ማለት እውነትን ማውገዝ እና ሰዎችን መናቅ ነው።} ብለዋል።

ልብስን ማሰረዘም (ለወንዶች) ; ሽርጥንም ቀሚስን እና ሱሪን ያጠቃልላል። ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) {አንድን ነገር ለ ኩራት ብሎ የጎተተ የቂያም እለት ወደ እርሱ አይመለከትም።} ብለዋል።

ምቀኝነት; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) {ምቀኝነትን ተጠንቀቁ። እሳት እንጨትን እንደሚበላው ሁሉ ምቀኝነት መልካም ስራን ይበላል።}

ወለድ መብላት; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) በይን እና አብይን ረገሙ { እያወቀ በወለድ የሚበላት አንዲት ዲርሃም ቅጣት ከሰላሳ ስድስት ዝሙት ቅጣት የበረታ ነው። } ብለዋል።

አስካሪ መጠጦችን ማዘውተር; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) {አምስት ነገሮችን የሚሰራ ሰው ጀነት አይገባም። አስካሪ ነገር የሚያዘወትር ፤ በጥንቆላ የሚያምን ፤ ዝምድናን የሚቆርጥ ፤ ጠንቋይ ፤ የሚመጻደቅ።} ብለዋል።
.
.
.
ይቀጥላል ኢንሻላህ

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

18 Nov, 18:13


🎯ከአንተ አላህ ይቅር ካለለህማ ያ ፍላጎቶቹህ ያለ ጥያቄ ይመጡሃል። ጌታችን ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ጌታና ይቅር ባይነት የምትወድ የሆንከው ከእኛ ይቅር በለን…🤲
‏فإن عفَا عنك أتتك حوائجُك من دون مسألة...

اللّٰهُمَّ انك عفو تُحب العفو فاعف عنا ..
@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

17 Nov, 18:56




እውቀት ተግባርን ስለመጠየቁ

ውሸት; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) { ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ ውሸትን የሚያወራ ሰው ወየውለት።} ብለዋል።

መሰለል; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) { የሚጠሉትን ወይንም የሚሸሹትን ሰዎች ወሬ ያዳመጠ ሰው የቂያማ ዕለት ነሃስ በጆሮው ላይ ይቀልጥበታል ።} ብለዋል።

ስዕል መሳል; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) {የቂያም ቀን ቅጣት የሚበረታባቸው ሰዐሊያን ናቸው ።} { ስዕል ወይም ውሻ ካላበት ቤት መላይካ አይገባም ።} ብለዋል።

ነገርን ( ማዋከሽ )ማዋሰድ; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) { አዋሻኪ ሰው ጀነት አይገባም ።} ብለዋል ።

ሃሜት; ሃሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? በማለት ነብዩ ﷺ ጠየቁ። ሰሃቦችም; አላህ እና መልዕክተኛው ያውቃሉ አሉ። {ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማንሳት ነው} አሏቸው። { የምናነሳበት ነገር ያለበትስ ቢሆን } ሲሏቸው ; { የምትለው ነገር ካለበት አማሀው ፤ ከሌለበት ደግሞ ጫንክበት ይባላል } አሉ።

መራገም; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) {አማኝን ሰው መርገም እንደ መግደል ይቆጠራል።} {ተራጋሚዎች የቂያም ቀን ሽማግሌም ሆነ ምስክር አይሆኑም።} ብለዋል።

ሚስጥርን ማባከን; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) { የቂያም ቀን መጥፎ ደረጃ ካላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ከሚስቱ ጋር ሚስጥር አውርቶ ሚስጥሯን የሚዘራ ነው። } ብለዋል።

መጥፎ ነገር መናገር; ነቢዩ ሙሃመድ ( ﷺ ) { የቂያማ ዕለት አላህ ዘንድ መጥፎ ቦታ ያለው ማለት ሰዎች መጥፎ ምላሱን ፈርተው የሚሸሹት ነው።} {ከ አደም ልጆች ወንጀሎች ብዙ በ ምላሱ ነው።}
.
.
.
ይቀጥላል ኢንሻላህ

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

16 Nov, 19:59


✓ ክብር ይገባት
ጊዜዋን ሰውታ ሰው ምናለኛ ሳትል እድሜ ሳይገድባት ቁርአንን ሸምድዳ በጭንቅላታ ይዛ ጀግኒት ተብላ ትጠራለች ይችን ጀግኒት ሊይስመርቃት የኢኸላስ መድርሳ ቀጠሮ ይዛ ይገኛል በዝ እለት መቅራት ማይታሰብ ነው እሱም መቼ ነው ካላቹ (እሁድ) ማለትም ነገ (ህዳር 8/2017)ነው እነዛይ ለኢስላም ብርሃን ለሆኑት ሴቶቻችን የአላህ ውዴታ ይስፍንባቸው።
አሜን

ፕሮግራሙ ለ ሴታች ብቻ ነው
ፕሮግራሙ የሚዘጋጅበት ባታ ኢማም አህመድ መስጅድ

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

15 Nov, 20:19


ቤተሰብ እስኪ እኛ እንኳን እንደማመጥ...እ

«አድማጭ እየጠፋ»

ነፃ አውጭው ብዙ ነው ማንም ነፃ አሎጣም፡
አሊም ነኝ ለማለት ሁሉም ለብሷል ጥምጣም፡
ማር ነኝ ይላል እንጂ መሯል እጂግ በጣም፡
ወይ አለመግባባት ጉድ አለመጣጣም!!

.....ይገርማል....!!

ሁሉም ታማኝ ነኝ ባይ ኑዛዜ ያበዛል፡
መሀይም ደንቆሮው በአዋቂ ያፌዛል፡
ሰው እውነትን ሽጦ ውሸትን ይገዛል፡

.....አይገርምም....‼️

ማዳመጥ መረዳት እጅግ ተስኖናል፡
ግን ለሁላችንም ምላስ ተሰጥቶናል፡
ሁሉም በምላሱ እየለፈለፈ፡
ንፁሀን አለቀ ሰው ህይወቱ አለፈ፡
ተናጋሪ ብቻ በሀገሩ ገነነ፡
ዝምተኛ አስተዋይ ጠፋ እየተነነ፡

በዘር ተለያየን ክፋት ቤት ሰራብን፡
እኛነት ከሰመ እኔ ባይ በዛብን፡
ሰው እኩል ነው ይላል የለም አንድም እኩል፡
አንዱን ያጠለሻል አንዱ ነፍሱን ሊኩል፡

.....አይገርምም ..በአሏህ⁉️

ስንቶች ተቀጠፉ እዝነት እየራቀን፡
እንሰሳ ሆነናል ሰውነትን አውቀን፡
መልካም አያወጣም ምላሳችን ከፋ፡
ተናጋሪ በዛ አድማጭ እየጠፋ፡

@mejnun_nn

Tei~@khlasikhlas1
Tei~@khlasikhlas1

Ikhlas institute

15 Nov, 01:57


🌿سنرحل ويبقي الأثر🌿✌️

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

14 Nov, 21:23


🔥እንኳን ደስ አላቹ
💫 እንኳን ደስ አለን

:-እደሚታወቀው በ ikhlas institution ውስጥ በ ተመላላሽነት የሚይስቀራቸውን ሴት ተማሪቻችንን ሊያስመረቅ ፕሮግራሙን ጨረሷ እየጠበቃቹ ይገኛል በ እለቱ እንኳን መቅራት ማርፈድ የማይታሰብ ነው።

(ህዳር 8/2017)


Te~@ikhlasikhlas
Te~@ikhlasikhlas

Ikhlas institute

14 Nov, 13:34


አብዝተን በሰዉ ህይወት
ጣልቃ ባንገባስ 🫨

ወይም ደግሞ ወረቀት እና ደብተር እንስጣቸውና ህይወታችንን ትደርሱት?
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

13 Nov, 15:56


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ተማሪዎች !!!

ሙተነቂብ እህታችን ናት ይህንን ከታች ያያዝኩላችሁን ድንቅ መፅሀፍ የከተበችው። በውስጡ ስለ ህፃናት መብት ሰፊ ዳሰሳን ያደረገና ከአለማዊው እና ከሸሪዓ አንፃር የህፃናት መብት ምን አይነት እይታ እንዳለው ይዳስሳል።

ሀገራዊ ውርጅብኝና ለይቶ ማጥቃት ብሎም ከዲን የማራቅ ዘመቻ እየተካሄደባቸው ሁሉን መሰናክል እያለፉ እንዲህ ለትውልድ የሚወረስ ስጦታን የሚያበረክቱ እህቶችን ማበርታት ይጠበቅብናል።

መፅሀፉን አንብቡት ብዙ ታተርፉበታላችሁ! ጥሩ የሚሰሩትንም ታበረቱበታላችሁ!!!


ወንጀላችን በዝቶ ባመዘነበት ወቅት ከምንም በላይ ፊትናዎችን ተቋቁሞ ለነገ የሚሻገር ስራን ለትውልድ የሚወረስ እውቀትን እንዲህ ባለትጋት የሚሰሩ እህቶቻችንን ማበርታት አለብን ያጀመኣ!

በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባርም!
ኒቃብዋን ለብሳ ትማራለች ብሎ መፎከር ብቻ ሳይሆን ኒቃብዋን ለብሳ አብሪ ኮከብ የዲን ፈርጥ እንድትሆን ማገዝ ማበርታት አለብን!!

ቢያንስ አንዳንድ መፅሀፍ እንግዛ ተማሪዎች!

                               
ይህን  ጠቃሚ የሆነ  እውቀት የያዘና ብዙ የተለፋበትን  መጽሐፍ ለማንበብ የወደዳችሁ 200 ብር  ከታች በተቀመጡት አካውንቶች በአንዱ ካስገቡ እና ደረሰኙን  ከላኩ መጽሐፉ ወዲያውኑ ይደርስዎታል።  @hikbedr or @hikmetulahbedredin በሚል የቴሌ ግራም አካውንት  ወይንም በስልክ ቁጥር (0985430115/0913485309) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።                     

ንግድ ባንክ    
1000483919984
ዘምዘም ባንክ
0002197320101
ሂጅራ ባንክ
1000631650001   
አቢሲኒያ ባንክ
47138418»




Via Bahr

Ikhlas institute

13 Nov, 11:43


የሰው ልጅ  ብዬ ስለ ሰው ላወራ ስል ለካ እኔም እንደነሱ ሰው ነኝ


ብቻ ግን ............
Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

13 Nov, 11:41


ድንገት ቅር ቢልህ ምክኒያቱን ሳታዉቀዉ፤
ልብህ ባርባር ቢለዉ አእምሮህ ቢጨንቀዉ፣
የቀልብህን  ደስታ ሀዘንህ ቢነጥቀዉ፣
ጌታህ ይረዳሀል ሱጁድ ላይ ጠይቀዉ።

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

13 Nov, 04:09


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ከወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ላንተ ሶደቃ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

12 Nov, 18:37


.
መኪና ሲኖረኝ የምደፈጥጣቸው
ብዙ......ሰዎች አሉኝ😐

ጠብቁ ....

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

10 Nov, 20:54


.
ወንድ ስለሆናቸሁ ብቻ
ባል መሆን የምትችሉ የሚመስላችሁ
ሪጃሎች......

እናንተን ሰብስቦ የሚገርፍልን
ወይ የሚያሰለጥንልን ሰው
ጀሊሉ ይላክልን🤲

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

09 Nov, 20:45


እዚያ ጋ ሰው ይታየኛል!
~
"ሰው ሞልቶ ሰው ጠፋ … ሚዛን የሚደፋ
ለእውነት የሚቆም … ላገር የሚለፋ"
እላለሁ እንደ ሰው
ሆዴን ሆድ ሲብሰው።

"ሴት ይርመሰመሳል … ሚስት ነው የጠፋ"
እላለሁ አንዳንዴ
ወንዶችን ወክየ … ቆሜ ሳንቀላፋ።

"ወንድ ይተራመሳል … ግን ባሎች የታሉ?"
እያሉ 'ሚጮሁ … እልፍ ሴቶች አሉ።

ሰው ሁሉ ሰው አድዳኝ … በሆነበት ምድር
ሰው ያልተገኘበት … አለን አንዳች ምስጢር።

ገባኝ ገባኝ

ለካስ ሰው "ነፍ" ነው … "ሰው" ከሰው ለለየ
ክፉን ብቻ ሳይሆን … ጥሩውንም ላየ።

ለካስ ሚስቶች አሉ … ባል ሆኖ ለመጣ
ሐያእ ለሚገባው … ላልሆነ ፈጣጣ።

ለካስ ባል በሽ ነው … ባልነት ለገባት
እራሷን ረስታ እንጂ … ዞራ የዞረባት።

ምልከታ ከራስ ይጀምር!

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

08 Nov, 18:43


ቀጥታ በሚተላለፍ ፕሮግራም ጋዜጠኛዋ፦

«ዘበኛው ለኒቃቢስቷ እንዲያውቃት ፊትሽን ግለጪ የማለት  መብት ኣለው አይደል? ስትል፣

«አዎ! አንችንም እንዲያውቅሽ ፊትሽን የተለቀለቅሺውን ዱቄት ታጠቢው ማለት ይችላል።»

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

08 Nov, 18:41


ጭንቀቱ ሁሉ ስለ ነገ ነበር
እሱ ግን ዛሬ ማታ ህይወቱ አለፈ 💔
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

06 Nov, 20:27


አንዲት አባቷ የመስጂድ ኢማም የሆነች ልጅ ነበረች። ልጁ በቁንጅናዋ ተማርኮ ዚና እንዲሰሩ ይጠይቃታል፤ ቆንጆይቱም "እሺ ነገር ግን ሁለት መስፈርቶች አሉኝ እነርሱን ካሟላህ " ትለዋለች። መስፈርቷንም በዚህ መልኩ ትነግረዋለች።
1ኛ) ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።
2ኛ) እንደምታቀው አባቴ የመስጅድ ኢማም ነው እና ስጠኝ እስካልኩህ ጊዜ ድረስ መስጂድ እየሄድክ በጀምዐህ ሶላትህን ስገድ" ትለዋለች።
:
ልጁም እሺ ብሎ ተስማማ።
ቃሉንና መስፈርቱን ለመጠበቅ ሲል መስጂድ መሄድን አዘወተረ።

በመጨረሻም የሰጣት ጊዜም አለቀ።
"ያንን የሰጠሁህን መስፈርት ተገበርከው ቃልህንስ በትክክል እያከበርክ ነው"? የሚል ጥያቄ አነሳችለት።
እርሱም "አው! እየተገበርኩ ነው ነገር ግን ቃል ያስገባሁሽን ነገር አሏህ ይቅር ይበለኝ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል። መስጂድ በምመላለስበት ሰዓት ወደ አሏህ ተመልሻለሁ" አላት።

አርሷም "ማሻ አሏህ! እኔም እሺ ያልኩህ ዝሙት ለመስራት ሳይሆን "ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች" በሚለው በዚህ በአሏህ ቃል እርግጠኝነት ተሞልቼ ነው።

اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ
ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አሏህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አሏህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡
📒ሱረቱል ዐንከቡት (45)

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

06 Nov, 18:38


18 አመት ሲሞላን እራሳችንን ምንችል መስሎን ነበር ለካ🤭😂

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

05 Nov, 18:52


እመጣልሻለሁ ቆይ ትንሽ ታገሺ
ረፍት ቢነሳኝ ነው ጥሎሽ መህርሽ
የዘገየሁትም የቀረሁ መስሎሽ
ምንም አልፈልግም አትጨነቅ ካልሽ
መህርሽን በሲዋክ ሀላሌ ላርግሽ

ሀቢቢ ቆይ ችግር የለውም
በሲዋኩ ደግሞ ችግርን ፋቅበት።😢😂

@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

05 Nov, 18:44


ተማሪዎች ነገ እሮብ ስለሆነ ዩኒፎርም አይለበስም😂በልብስ ኑ😂😂😂


ይቺን ላይፍ ያሳለፈ አለ😂😊

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

05 Nov, 17:57


=>በመንገድ ላይ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሰውዬ መርዛማ የሆነ እባብ በእሳት ሲቃጠል ተመለከተና ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣው ወሰነ። ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣ ሲያነሳው እባቡ እጁ ላይ ነደፈው። ሰውዬው በድንጋጤ እባቡን ወረወረው እባቡም ተመልሶ እሳቱ ውስጥ ወደቀ።
ሰውዬውም  በድጋሚ ሁለት እንጨቶችን ተጠቅሞ ከእሳቱ አወጣው። እናም የእባቡ ሕይወት ተረፈ።
ቆሞ ድርጊቱን ይመለከት የነበረ አንድ ሰው ወደ ሰውየው ቀርቦ

"ይህ እባብ በመርዙ ነድፎህ ሳለ ድጋሚ ልታድነው የምትሞከረው ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።

ሰውየውም "የእባቡ ባህሪ መንደፍ ነው የእኔ ደሞ ማትረፍ ነው። ሁለታችንም ያለንን ነው ያንፀባረቅነው። ለሱ ክፉ ባህሪ ብዬ የኔን መልካም ባህሪ መለወጥ የለብኝም" ብሎ መለሰ።

መልዕክቱ እንደራስ አረዳድ ቢለያይም ጠቅለል ሲደረግ እንዲህ ነው.....።

ክፉ ነገር በክፉ ሊመለስ አይገባም። መጥፎ ሰዎች በዙሪያህ ቢኖሩም፣ የቱንም ያህል ክፋት ቢሰሩብህ አንተ የራስህን መልካም ብህሪ አንፀባርቅ እንጂ በነሱ ውስጥ አትዋት። እራስህን ሁን!!!!

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

05 Nov, 12:35


ተማሪዎች አንድ ጥያቄ ነበረኝ

የClass ዉስጥ እንቅልፍን እስኪ በተመቻችሁ አማረኛ ግለፁት 🥹😂

te~@ikhlasikhlas1
te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

02 Nov, 19:04


የዓለም ህዝብ ሁሉ በሚተኛበት የለሊት ፈረቃ ስንት ሰው እንደማይተኛ ታውቃለህ?

አንተ ተኝተህ በምትቃዠው ቅዠት የሚቀና እንዳለስ ታውቃለህ?
በምታንኮራፋው እንቅልፍ ድምፅህን እየሰማ እሱ ብቻ የማይተኛ ከህመሙ ጋር የተፋጠጠ ሰው አታውቅም?
ስንት ሰው ለሊቱ አልነጋ ብሎት እንደሚሰቃይስ ታውቃለህ?

ጤና ማጣት በጣም ከባድ ነው😊
አንተ ግን ጤና አለህ ያን ያህል ተኝተህ የንጋት ሶላት ለመስገድ ምን ከበደህ
ጤናህን ሰጥቶህ ሰላማዊ እንቅልፍ እንድትተኛና በሰላም እንድታነጋ ላደረገህ ጌታ 2 ረከዓ መውረድ ከበደህ?
ግን ያ ታማሚ ካሁን አሁን ሞቱን ይጠባበቃል አልያም ህመሙ ከቀን ወደቀን ይብስብኝ ይሆን እያለ በጭንቀት ልቡ ትናጣለች ሆኖም ካንተ ይሻላል ለሊቱን አላህን በመለመን ያነጋል ከፈጣሪው ጋር ይነጋገራል አንተም ብትያዝ ያው ነህ እስካልታመምክ ድረስ ግን አላህን ከስሙ ውጭ በኢባዳ አትከተለውም ነቃ በል ነገ ተረኛ አንተ ትሆን ይሆናል


@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

02 Nov, 19:03


በአንዳንድ ሰው ልብ ውስጥ አይነኬ ማዕዘን ነን

በአንዳንድ ሰው ልብ ውስጥ ትልቅ ቤት ነን

በአንዳንድ ሰው ልብ ውስጥ የሆነች ትንሽ ክፍል ነን

በአንዳንድ ሰው ልብ ውስጥ ብንታይም የማንታይ ምንም ነን

ዐይን ሁሉንም ያያል። ነጥሎ የሚወደው ግን ልብ ነው

የምትወዱትን ያስወድዳችሁ😍
የአላህን ውዴታ ያገኘ ስለሰው አይጨነቅ አላህ የሰጠነውን ይሰጠናልና🥰

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

01 Nov, 20:30


ስትንቅ ትናቃለህ!
~
"ኩራተኛ ልክ የተራራ ጫፍ ላይ እንዳለ ሰው ነው። ሰዎችን ቁልቁል ሲያይ ትንንሽ ሆነው ይታዩታል። ግና እሱም ለሰዎች ትንሽ ሆኖ ነው የሚታየው።

te~@ikhlasikhlas1
te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

01 Nov, 20:15


ህልፈት
በ1206 ዓ·ሂ  በወርሃ ሸዋል በእለተ ሰኞ ከተወለዱ በ91 አመታቸው በደርዒይያህ ከተማ  ለማንም የማይቀረውን የሞት ፅዋ ተጎነጩ። ለኚህ ሸይኽ ሞት ነጅድና አካባቢዋ በእንባ ወንዝ  ተጥለቀለቁ። ሙስሊሞች በለቅሶ የሀዘን ብርድልብስን ተከናነቡ።
ዝናቸው ሲነገር በሊቃውንት አንደበት
«"ኪታቡ‘ት-ተውሂድ" ና ሌሎች ድርሳኖችን ያጠና ሰው የሸይኹን ደረጃና እውቀት ይገነዘባል። ረቂቅ ግንዛቤና የመጠቀ እውቀት አንዳለውም ይረዳል። በዘመኑ የነጅድ ህዝቦች በሌሎች የእውቀት ዘርፎች ላይ ወደርሱ ነበር ሚመለሱት።» ይላሉ ሸይኽ ዐብዱ‘ል-ለጢፍ
"ሸይኽ፣ መሪና  የለውጥ አራማጅ!  የሐዲስ ጠቢብ የሆነና ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው። በአላህ መንገድ ላይ ታጋይ በሰለፊይያህ (በቀደምቶች የእውነት ፋና) ዳዕዋ ጉዞ ላይ ግንባር ቀደም! ሙሀመድ ቢን ዐብዱል ወሃብ!" ሸይኽ በዲዑ ድዲን አርራሺዲ
"የህዝቡ መሪ!  የዘመኑ ትንታግ ሊቅ! አርአያዬ! የሸይኾች ሸይኽ! ኢማሙ ሸውካኒ (በግጥም መልክ የሰደሩት ቢሆንም ስላልተመቸ በስድ ፅሁፍ አስፍሬዋለሁ)
እኔም እንዲህ ብዬ ስለዝናዎ ልክተብ ስለ ክብሮ ልናገር
"አንቱ የነጅድ ማህበረሰብ በጥቅጥቅ የድንቁርና ጨለማ ተለብዶ ሲባጅ  ከወደ ዑየይናህ የፈነጠቁ የብርሃን ጅረት ነዎት! ከአበባ አበባ ነጥራ ማር እነደምታነጥር አገልጋይ ንብ ለህዝቡ የሚበጀው አሃዳዊ እምነት (ተውሂድን) አስገንዝበዋል። ሁለት መቶ አመታት ተነባብረው ዘመን እንደ ታቦር ተራራ ቢቆለልም የፍካቶት ማህተም ከቶ እስአሁን አልጠፋም።  ከወዳጅ አልፎ ጠላት የመሰከረሎት የዑየይናህ ኮከብ! በተውሂድ ብርሃን የበሩና ለተውሂድ የለፉ የተውሂድ አርበኛ!

te~@ikhlasikhlas1
te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

01 Nov, 20:11


የተውሂድ አርበኛ ፤ የዑየይናው ኮከብ
------------
"የህዝቡ መሪ!  የዘመኑ ትንታግ ሊቅ! አርአያዬ! የሸይኾች ሸይኽ! " ሲሉ  ኢማሙ ሸውካኒ ተደመውባቸዋል።
እኔም ስለዝናቸው ልፅፍ  ብዕሬን ከወረቀት ጋር ባገናኝ "አንቱ የነጅድ ማህበረሰብ በጥቅጥቅ የድንቁርና ጨለማ ተለብዶ ሲባጅ  ከወደ ዑየይናህ የፈነጠቁ የብርሃን ጅረት ነዎት። ሁለት መቶ አመታት ተነባብረው ዘመን እንደ ታቦር ተራራ ቢቆለልም የፍካቶት ማህተም ከቶ እስአሁን አልጠፋም።  ከወዳጅ አልፎ ጠላት የመሰከረሎት የዑየይናህ ኮከብ! በተውሂድ ብርሃን የበሩና ለተውሂድ የለፉ የተውሂድ አርበኛ"  አልኩ!
"ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዐብዱል ወሃብ ቢን ሱለይማን አት-ተሚሚ" ይባላሉ
ሸይኹ በ1115 ዓመተ ሂጅራ  መገኛዋን መካከለኛ ምስራቅ ባደረገችው  የቀድሞዋ ነጅድ ምድር ላይ ከሪያድ በቅርበት የምትገኘው ዑየይናህ ከተማ  ተወለደ።  የቤተሰቡ አባላት መበጠስ በሌለው ጠንካራ የእውቀት ሰንሰለት የተሳሰሩ የምግባረ ልዕልና ባለቤቶች ናቸው። የህፃኑ  አያት ሱልይማን ቢን ዓሊይ  በዐረቢያን ደሴት ላይ ከእውቅ ሊቃውንት መካከል እንደነበር ይወሳለታል።  የህፃኑ ወላጅ አባትም ከከተማው የዳኛነት ሹመቱ ባሻገር በጥልቅ እውቀቱና በመልካም ባህሪው  ታሪክ በደማቁ የምታውቀው ሰው ነበር። በዚህ የጥበብ ዶፍ ባረሰረሰው ጎጆ የተወለደው ልጅ  አስር አመት ሳያልፈው ቁርአንን ለመሸምደድ በቃ። ገና በማለዳ የሽምደዳ ችሎታ እንዳለው ሳያስታውቅ አልቀረም። የመጀመሪያው ትምህርቱን የቀሰመው የእውቀት ማበቢያ ማዐከል ከነበረው የአባቱ ጎጆ ነበር ። የፊቅህና መሰል ዘርፎች ከአባቱና ከአጎቱ ቀሰመ። የአዕምሮ ፍጥነትና መስተዋል ይዞ ነበርና በብዙ ርዕሶች ላይ ነገሮችን በቅጡ ለመረዳት አይከብደውም። በላዕላይ ግንዛቤው አባትዬው ይደነቅበት ነበር። " ከልጄ ሙሀመድ  ብዙ የህግጋት ቁምነገሮችን ገብይቻለሁ።" ሲል በራሱ አንደበት የልጁን የግንዛቤ ምጥቀት መስክሯል። ሊቀ ሊቃውንትን ኮትኩቶ የሚያበቅል  ጎጆ ያስቀናል።
በህፃንነት ዕድሜው የጥበብ ብርሃን ምንጭ የሆነው ቁርአንን የቀመሰው ይህ ልጅ ተጨማሪ ጥበብ እየራበው ቤቱ መቀመጥን አልፈለገም፤ የተለያዩ የእውቀት ዘርፎችን በከተማው  ጠቢባን  ለመማር ደፋ ቀና ይል ጀመር።   ከዚያም አልፎ  ወደ መካ፣ መዲናህ ፣ ወደ ዒራቅና በስራ፣ ወደሌሎችም በመጓዝ ዕውቀት ፍለጋ ተንከራተተ። ከየስፍራው የሸማመተውን  ጥበብ ሰብስቦ ለሊቅነት የመብቃት ራዕይ ከውስጡ የተወለደው ልጅነቱ ሳይጠና ይመስላል። ጥቅጥቅ ባሉ የእውቀት መንገዶች ነጉዶ ሲያሰላስል የኖረ ተመራማሪ በመሆኑና በነጋ ጠባ ያለ መታከት የሚንከራተት ጥበብ ፈላጊ በመሆኑ የተነሳ ከዑየይናህ ሊቃውንት ተርታ በመሰለፍ የላቀ ክብርን ተጎናፅፏል።
(ከአሁን ቡኋላ የኢስላም ሊቅ ሆኗልና በአንቱታ ልጥራው)
  ሸይኹ ህይወታቸው ከእውቀት ጋር ነፍስ ከአካል ጋር የተያያዘውን ያህል የተሳሰረ ነበር። ግን አንድ ነገር ሰላም ነስቷቸዋል። አጠገባቸው ያሉትን የነጅድ ህዝቦች ሲያስተውሉ ፍፁም እሳቸው ከተማሩት ቁርአናዊና ሀዲሳዊ አስተምህሮት የሚጣረስ  የተበረዘ እምነት ውስጥ ተዘፍቀዋል።  ድንጋዮች ፣ ዛፎች፣ የተቀረፁ ጣኦቶችና መቃብሮች እየተመለኩ  የማይገባቸውን ክብርና ዝና ተሰጥተዋል። ማህበረሰቡ ልክ እንደሌሊት ፅልመት በወረረው ማንነት ውስጥ ነው ያለው። ጠንቋዮችና ድግምተኞች አንገታቸውን ቀና በማድረግ የበላይነትን ተችረው ተራውን ህዝብ  ማደንዘዣ ኪኒን አስውጠውታል። ሸይኹ በታሪክ ሰሌዳ ላይ የተማሩት መሰረታዊ እውቀትና የሰዎች ተጨባጭ እጅግ በተራራቁ ሸለቆዎች ውስጥ ሆነባቸው። ያኔም የሸይኹ ምርጫ ሁለት መሆኑ አያጠራጥርም።  ወይ ለማህበረሰቡ የሽርክ አድራጎት እጅ ሰጥተው ከነርሱ ጋር መመሳሰል አሊያ በማህበረሰቡ ውስጥ የተሰገሰጉና የተሰራጩ አጉል እምነቶችን ለማደፍረስ መታተር!  የሸይኹ ምርጫ ግን ሁለተኛው ሆነ። የተኙ ሰዎችን መቀስቀስ እንዳለባቸውና በጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ወደ ብርሃን ለማውጣት መልፋት እንዳለባቸው ራሳቸውን አሳመኑ። በዚህ የተሓድሶ ጉዞአቸው ላይ  ከጠማማ መሪዎች ጋር ሊያስተናግዱት የማይቀርላቸው ፍጭት እንዳለ ጠንቅቀው ቢያውቁም የዳዕዋን ታላቅ ሀላፊነት ለመሸከም ቆርጠው ተነስተዋልና  በስብዕና ጥንካሬ የተደማመረ  ጀግንነት ከውስጣቸው የፈለቀ ይመስላል። 
የዳዕዋ ተልዕኮዋቸውን ጀመረዋል። ሰዎችን ከጨለማው የሽርክ ህይወት በተውሂድ ነፀብራቅ የማድመቅ ዓላማን አንግበው ወደ ተውሂድ ተጣሩ።  የሙት መንፈሶች ፣ ዛፎች፣ ድንጋዮችና መቃብሮች ለሰዎች ጥቅምን ማስገኘት ፣ ጉዳትን መገፍተር እንደማይችሉ አበክረው አስተማሩ።  በከንቱ እምነት ላይ የተገነባውን ባዕድ አምልኮ የመደርመስ ትግላቸውን አስመልክቶ ከበርካታ ምሁራን ጋር በመገናኘት የዳዕዋውን ህልውና  የማጠንከርና የማፋፋት ስራ ለመስራት ተስማሙ።  ራስን ከማሸነፍ ጋር በፅናት የተካኑ ድንቅ ሰው ነበሩና ስኬታማነታቸው በጉልህ ይታይ ጀመር።  "አንተ ብርሃን ብቻ አብራ ጨለማው በራሱ ጊዜ ይወገዳል" አይደለ የሚባለው? ብዙ ሰዎች እውነታው ተገልጦላቸው በዳዕዋው መማረክ ችለው ነበር።
እናም በአንድ ጊዜ ዝናቸው በሁሉም የዓረቢያን ግዛት ውስጥ ተሰራጨ። 
ስለ ስነምግባራቸው ልፅፍ ብዕሬን ስጨብጥ  የሸይኽ ዐሊይ ቢን ዐብዱል-ላህ የምስክርነት ቃል ፊት ለፊቴ ድቅን ይላል። " ሸይኽ ሙሀመድ በፈገግታ የታጀበ ብርሃናማ ፊት ነበረው። ግርማሞገስ የፈሰሰበት ክቡር ማንነት ያለውናለፅድቅ የሚቋምጥ  ተናናሽ ሰው ነበር። ጌታውን እጅግ አምላኪ ሊቅ። ለዱንያ እምብዛም ቦታ የሌለው፣ ጥንቁቅ ና በእውነት ላይ ደፋር ነበር።" ይላሉ ሸይኽ ዓሊይ!
    ሸይኽ ዑስማን ቢን ዐብዱልላህም እንዲህ ሲሉ የኚህን ሸይኽ የስነምግባር ልዕልና መስክረዋል፦ "በጥቅሉ  መልካም ስብዕናውና የደረጃው ምጥቀት ተቆጥሮ አይዘለቅም። በአንደበት ከሚወሳውም ይበልጥ የተሰራጨ ነው።"
ቸርነታቸው፣ ጀግንነታቸው፣ ታማኝነታቸው፣ ፍትሃዊነታቸው፣ ቁጥብነታቸው፣ ቻይነታቸው፣ ቃል አክባሪነታቸው …  ወዘተ    ብዙዎችን ያስደመመና ያስናቀ ነበር።
   ሸይኹ ካበረከቷቸው መፅሃፍት ውስጥ
"ኪታቡ‘ት-ተውሂድ" የተውሂድን ምስጢርና የሺርክን ብክለት የዳሰሱበት ዝነኛና እውቅ መፅሃፋቸው ነው።ከሽፉ‘ሽ-ሹቡሃትኪታቡል ከባኢርነሲሓቱል ሙስሊሚን
መሳኢሉል ጃሂሊይያ
አልሀድዩ‘ን-ነበዊይ
ፈድሉል ኢስላምኡሱሉ‘ስ-ሰላሳህኡሱለል ኢማን
ሙኽተሰሩ ዛዲል መዓድ ና ሌሎችም ለአብነት ተጠቃሾች ናቸው።
በርካታ የሸይኹ ድርሳናት  ከተውሂድ ብርሃንና ከሽርክ ፅልመት ጋር የተያያዘ ነው። የሸይኹን መፅሃፍት ለመቅራት የታደለ ሰው ይህንን በቅጡ ያውቀዋል። መፅሀፍቶቻቸውም ቁርአናዊና ሀዲሳዊ መረጃን መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው የብዙዎችን ቀልብ መሳብ ችለዋል።
ከወላጅ አባታቸው ባሻገር ሸይኹ ላይ አሻራቸውን በደማቁ ካሳረፉ ሊቃውንት መካከል ሸይኽ ዐብዱልላህ ቢን ሳሊም አልበስሪይ፣ ሸይኸ ዐብዱልላህ ቢን ኢብራሂም ሰይፍ ፣ሸይኽ ኢስማኢል ቢን ሙሀመድ ሻሚይ ፣ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሀያት አስሲንዲ ና ሸይኽ ዐብዱልላህ ቢን ፌይሩዝ እንደ ናሙና ይጠቀሳሉ።te~@ikhlasikhlas1
te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

31 Oct, 18:55


¿ ሀሙስን በ ለያል
° ጁምአን በ ሰለዋት
[ሰ.ዐ.ው]

te~@ikhlasikhlas1
te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

31 Oct, 03:58


صباح الخير ❤️

Ikhlas institute

30 Oct, 20:13


ኒቃብ የሙስሊሞች  አንድ መገለጫ ነው። "ፈርድ ነው  ወይስ ሱና ነው" የሚለው ሀሳብ ላይ ጠይቀህ፣ መርምረህ  ሚዛን የደፋልህን አቋም መምረጥ ትችላለህ። መብትህ ነው።  አሁን ነጥቤ እሱ አይደለም። በእንደዚህ አይነት ወቅት ግን ግዴታነቱን አምነው ለለበሱት እህቶች ድምፅ መሆን እንጂ  ጉዳዩን የኺላፍ ርዕስ አድርጎ የማይመለከታቸውን ሰዎች ሀሳብ በሚደግፍ መልኩ ማቅረብ ሞኝነትና ደዩስነት ነው። ወደድክም ጠላህም  በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የኢስላም ሺዓር እንዲታይ የማይፈልጉ ሰዎችን እየደገፍክ ነው። በእንዲህ አይነት ወቅት ወይ ዝም በሉ  ወይም ለእህቶቻችሁ ደጋፊ ሆናችሁ ኑ። አጉል አሽቃባጭ አትሁኑ። የኺላፉን ጉዳይ ከናንተ በላይ ለባሾቹ ያውቁታል።
✍️@mejnun_nn

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

30 Oct, 19:06


ሰላም ለነዛ 😊


ቀጥሉት እስኪ....
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

30 Oct, 19:01


🌿.........🌿

ሰላም ለነዛ ✌️

ሰላም ለነዛ
ለአቅሷ ክብር ሲሉ ግፈኛውን አለም ብቻቸውን እየተጋፈጡ ላሉት ሙጃሂዶች🥹

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

29 Oct, 19:48


ነገ ተውበት አረጋለሁ ብሎ ተኛ

ግን አልነቃም😢

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

29 Oct, 18:32


ከመጅሊስ ለትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ደብዳቤ

Te~@ikhlasikhlas1
Te~@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

29 Oct, 17:30


ሁላችንም እኮ የራሳችን የሆነ ሩጫ አለን
ድንገት ተከስታችሁ ሁሉን ትታችሁ ተከተሉን አትበሉ
እየተሳሰብን እንጂ

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

28 Oct, 19:44


ህይወት አጭር አይደለችም !።

የኛ የዱኒያ ቆይታ እንጂ ህይወት አጭር አይደለችም  - የሰው ልጅ ህይወት ይጀመራል ነገር ግን ማብቂያ የለውም ። ሞት ከአንደኛው ሀገር ወደሌላኛው የሚያሻግረን ድልድይ እንጂ ጨርሶ መጥፋት አይደለም። 

Life is too short enjoy it - ህይወት አጭር ነች ፈታ በሉ - የሚለው አባባል የኤቲስቶች ዲስኩር ነው ። ህይወት አጭር አይደለችም ኸሊፋው ዑመር ኢብኑ አብዱልዐዚዝ እንደሚሉት የተፈጠርነው ለዘልዓለም ልንኖር ነው ። ሞት! ከጠፊው ወደ ቀሪው ሀገር የሚያዘዋውረን ማለፊያ በር እንጂ ሌላ አይደለም

وما الموت إلا رحلة ، غير أنها   من

المنزل الفانى إلى المنزل الباقى

ሁሉም ነገር እዚህ አልተጀመረም
እዚህም አያበቃም ! ይሄን በጥልቀት መረዳት ብዙ ነገሮችን ያቀላል

✍️
@Mejnun_nn

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

28 Oct, 18:34


"ውሸታሞች ናቸው። ውሸታም እንደሆኑም ያውቃሉ። ውሸታም መሆናቸውን እንደምናውቅም ያውቃሉ። ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ደግሞ ይዋሻሉ።"

@Mejnun_nn

Te-@ikhlaseikhlase1
Te-@ikhlaseikhlase1

Ikhlas institute

28 Oct, 18:20


ጥበብ ነው ወይ?
---
ለአንድ ጥበበኛ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበለት፦
  "(በንግግርም ይሁን በተግባር)  ትንኮሳ የሚያካሂዱብህን ግለሰቦች ለምን በመቃወም አትበቀልም?"
  እርሱም ፈገግታን በተላበሰው ፊት እንዲህ አለ፦
"ﻭﻫﻞ ﻣﻦ ﺍﻟﺤﻜﻤﺔ ﺃﻥ ﺃﻋﺾ ﻛﻠﺒﺎً
ﻋﻀﻨﻲ"
  "የነከሰኝን ውሻ ብነክስ ጥበብ ነው ሊባል ይችላልን?"

    ጥበብ የፈሰሰበት ማራኪ መልስ!
ውሻ ነከሰኝ ተብሎ አይነከስም፤ ውሻ ጮኸም ተብሎ አይጮህም!
ለጮኸ ሁሉ መልስ መስጠት ራስን ከማድከም ባሻገር ክብርን ማርከስ ነው!
የአንዳንዶቹ ጩሀት ምንም ያህል ቢንር ከመሰቅጠጥ በስተቀር ምንም አይፈይድም። የአዋቂ ዝምታው ግን ከጩኸት በላይ ከመልዕክት  ጋር ጆሮን ኮርኩሮ ወደ ውስጥ ይዘልቃል።
   በረቀቀ ዓይን የሚታዩ ብልሹ አካሄዶች ይፋ የሚሆኑትም  በዝምታ ነው!
t.me/ikhlaseikhlase1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

27 Oct, 19:04


ነገ ሰኞ ነዉ የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ 😊

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

27 Oct, 18:58


❗️❗️❗️
በሕይወታችን ድንገት የሆነ ሰው
ይመጣና ሌሎች ጥለውን ስለሄዱ
  #እንድናመሰግን ያደርገናል።
@ikhasikhlas1
@ikhasikhlas1

Ikhlas institute

26 Oct, 19:49


ብዙ ሰው ትኩረት ነፍጎታል። በተቃራኒው በማይረባ ነገር ተጠምዷል። መረጃው ያለው ሰው ትንሽ ስለሆነ ይመስለኛል።

አመናችሁም አላመናችሁም ሰሞኑን በበርካታ ትምህርት ቤቶች ኒቃብ ተከልክሏል። የሚደርስላቸው ተቋምም ሆነ ድምፅ የሚሆናቸው ግለሰብ አጥተው በርካታ ኒቃቢስቶች ትምህርት ካቆሙ ሳምንት አልፏቸዋል።

ለማን ቢነገር ይሻላል? መጅሊስ ይህን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ በቋሚነት ለምን አይፈታም? ምን እየተካሄደ ነው? ዛሬስ በምን እናመካኝ?

እህቶቻችንን ስልታዊ በሆነ መልኩ ከትምህርት ገበታ ማገድ እስከ መቼ?

ትኩረት ለኒቃቢስት ተማሪዎች!

ኒቃቧንም ትለብሳለች፣ ትምህርቷንም ትማራለች።


(ይህን መልዕክት በማሰራጨት ቢያንስ ሰዎች ዘንድ እየሆነ ስላለው ነገር መረጃው እንዲኖር እናድርግ። በዱዓችንም እናግዛቸው።

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

26 Oct, 19:38


አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላለፍት ሶስት አመታት ኒቃብ ለብሰው ሲማሩ የነበሩ ተማሪወች ወይ አውልቁ ወይ ትምህርት ቤት አትምጡ ተብለዋል ።

ከትምህርት ከታገዱም ሳምንት አለፍቸው መጅሊሱም መረጃ ቢደርሰውም  ዝምታን መርጠዋል።

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

25 Oct, 20:36


የሚጠልቅ ፀሐይ

ብዙ ጊዜ እኛ የሰው ልጆች ብዙዎቻችን ማለት በሚቻል ሁኔታ አንድ ነገር ከተከናወነ ወይም ከተከሰተ በኋላ ስንጨነቅና ስንጠበብ ይታያል።

ውስጣችን ላይ ብዙ ጥያቄዎች ይመላለሳሉ።
➘ ለነዚህ ጥያቄዎች ለአንዳዶቻቸው መልስ ሲኖራቸው ለአንዳዶቻቸው መልስ ሳይኖራቸው እንዲሁም ደግሞ አንዳዶቻቸውን ጭራሹንም የማንረዳበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ይፈጠራልም ጭምር።

ውስጣችን ላይ ከሚመላለሱት ጥያቄዎች ውስጥ መልሳቸውን ያወቅናቸው ቢሆን እኳን በድጋሚ ራሳችንን ከመጠየቅ አንቆጠብም።
“እንዲህ ለምን ሆነ”፣
“እንዲህ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው”፣
“እንዲህ ቢሆን ኖሮ ለኔ የተሻለ ነበር”፣
“እንዲህ የተከሰተው በነ እገሌ ክፉነት ነው”፣
“ከነ እገሌ ርቄ እነ እገሌን ቀርቤ ቢሆን ኖሮ አኔ ላይ እንደዚህ አይነት በደል አይፈፀምብኝም ነበር” እያለን “በቢሆን ኖሮ” ዓለም ራሳችንን ከልለን እንኖራለን።

“ቢሆን ኖሮ” የምትለዋ ሀረግ መርዘኛ ናት፣ እኛን በቢሆን ኖሮ ዓለም ውስጥ እያኖረች ተዋርደን፣ ዝቅ ብለን፣ በቁማችን ሞተን፣ ህልማችንን ቀብረንና ዓላማ 🎯 ቢስ እንድንሆን ታደርገናለች።

➝ ወዳጆቼ ይችህ “ቢሆን ኖሮ” መርፌ 💉 ናት፤ ሰበብ ሆና ከበሽታ የምታድን መርፌ ሳትሆን በሽተኛ እንድንሆን መምታደርገን ናት‼️
➝ ወንድምና እህቶቼ ይቺህ “ቢሆን ኖሮ” በቅዠት ዓለም ውስጥ እንድንኖር የምታደርገን በቅዠት የተለከፈች በሽታም ናት።
➝ ጓደኞቼ ይችህ “ቢሆን ኖሮ” በህይወት ስንኖር ተስፋ ካለን የፀሐይና የጨረቃ ብርኃን እንዳለ ረስታ በጨለማ ህይወት የምታኖረን ጨለምተኛ አስተሳሰብም ጭምር ናት‼️

➻ አዎ በርግጥ ፀሐይ በሆነ ሰዓት ትጠልቃለች ለዛውም በአይናችን እያየን አየሩ እየጨለመ ነው የምትጠልቀው ከዛም ጨለማ (ምሽት) የሚተካው!
ነገር ግን ወዳጆቼ ይቺህ ፀሐይ እኮ እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ነገ ተመልሳ መውጣቷ አይቀሬ ነው።

➽ ታዲያ ለምን እኛ እንቅፋቶች በገጠሙን ሰዓት እቅፋቶችን የህይወታችን የአኗኗር ዘይቤ አንዱ አካል አድርገነው ወደፊት የማንቀጥለው⁉️
➽ ታዲያ ለምን ፀሐይ ተመልሳ መውጣቷ የማይቀር መሆኑን እያወቅን ጨለማውን በትዕግስት ማለፍ የሚያቅተን።

⚙️ እኔ ይህን እያልኩ አደለም እኛ ለይ የሚደርሱ ወይም ሊደርሱ የሚችሉ እንቅፋቸቶ በጣም ቀላል ናቸው፤ እኔ ይህን እያልኩ ነው በፈጣሪ እምነት ኖሮን የምንታገስ ከሆነ የማናልፈውና በድል የማንወጣው ችግር እዚህ ዓለም ላይ ፈጣሪ አልፈጠረም አይፈጥርምም።


እናም እላችኋለሁ .........
● ለሚጠልቀው ፀሐይ አናስብ፤ ድጋሚ ፀሐዩ ሲወጣ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወቅ እናስተውል ጭምር።

✍️@mejnun_nn

@Ikhlasikhlas1
@Ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

25 Oct, 20:18


የምትወዷቸውን ሰዎች ከመሞታቸው በፊት ተንከባከቧቸው ምክንያቱም ምድር የወሠደችውን አትመልስምና

@Ikhlasikhlas1
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot
@Ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

25 Oct, 19:29


ሰሞኑን በአዲስ አበባ በርካታ የመንግስት ት/ቤቶች ማስክ አውልቁ ጭምር እየተባለ ኒቃቢስቶችን ከትምህርት የመከልከል ወንጀል እየተፈጸመ ነው። ከብዙ ት/ቤቶች ጥቆማዎች ደርሰውኛል።

የፌዴራሉና የአዲስ አበባ መጅሊስ ከትምህርት ሚኒስተር እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግረው የኒቃቢስቶችን መብት ለምን በቋሚነት አያስከብሩም⁉️

እስከመች ነው በየአመቱ በኒቃብ ምክንያት የእህቶችን እንግልትና ስቃይ የምንሰማው? ይህ ነገር መቋጫው መቼ ነው? እስከ መቼ ሁሌ ሮሮ! አይበቃም ወይ?

ፍትሕ በትውልድ ሃገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠሩ ትምህርት የመማርና ሥራ የመሥራት መብታቸው በተደጋጋሚ ለሚነፈጉት ኒቃቢስት ሴቶች

@Ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1

Ikhlas institute

25 Oct, 07:07


ተማሪነት( ያንብብ)

◉ ያለንበት ቦታ፣ ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ለተስፋ-ቢስነት ምክንያት ሊሆን አይችልም!!

● ለተስፋ-ቢስነታችን ምክንያት ሊሆን የሚችል ነገር ካለም የኛ ድክመትና ራሱ “ተስፋ-ቢስነታችን” ብቻ ነው!!

ውድ ተማሪዎች
➤ ❝ እኔ ባነብም አይገባኝም ❞
➤ ❝ እኔ ሒሳብ አልችልም ❞
➤ ❝ እኔን እንግሊዝኛ ይከብደኛል ❞
➤ ❝ መማር የኔ እጣ-ፋንታ አይደለም ❞
➚እንዲህ በሚሉ የደካሞችና የቀሽሞች አስተሳሰብ ውስጣችን ከሞላነው፤ በርግጥም ሁሉም ነገር ይከብደናል። ነገር ግን ከፊት ለፊታችን ያለውን ችግር በመጋፈጥ፣ ድክመታችንን ሊሸፍንልን የሚችል ስራ በመስራት፣ ይከብዱናል ያልናቸውን ትምህርቶች ቆራጥነት በተሞላበትና ቀጣይነት ባለው ጥረት የምንችለውን ያህል በማንበብ ስንፍናችንን መበቀል እንችላለን!

● ተማሪዎች አንድ ነገር እወቁ፦ እናንተ የማትችሉት የትምህርት አይነት ምንም የለም። እናንተ መስራት የማትችሉት ምንም አይነት ስራ የለም። እናንተ መድረስ ማትችሉበት ምንም አይነት ቦታ የለም።
➻ እናተ ዘንድ የሌለ ጉብዝና ሌላ ቦታ ሊኖር አይችልም!
➻ እናተ ዘንድ የሌለ መልካም ስብዕና ሌላ ቦታ መኖሩ የማይታመን ነው።
ወንድሞቼና እህቶቼ ተማሪነት ነገሮችን ሁሉ ለይተን የምናውቅበት ሽልማት ነው!

ተማሪነት የስኬትን መንገድ የሚያቅጣጨን ኮምፓስ ነው!!
ተማሪነት እራሳችን፣ ቤተሰባችንን፣ ማህበረሰቡን ብሎም ሀገራችንን ልንረዳበት የተሰጠን ስጦታ ነው!!
ተማሪነት በአላህ ፍቃድ ከችግር የምንወጣበት መሰላል ነው!!
ተማሪነት ድጋፍ የሚሹትን የምንደግፍበት ኃይል ነው!!
ተማሪነት መጥፎ ነገሮችን የሚያጠፋ መሣሪያ ነው።
ነገር ግን ከላይ ያልናቸውን ሽልማቶች ልንሸለም የምንችለው ጊዜያችንን በአግባቡ ስንጠቀምና በወደቅን ወይም በተሸነፍን ጊዜ ተስፋ ሳንቆርጥ ጥረታችንን ስንቀጥል ነው።

ያሳደገንን ማህበረሰብ እንዲሁም ተንከባክባ የጠበቀችንን ሐገር ለመርዳት መፍትሄው ተማሪነት ብቻ ነው።

እኛ የሰው ልጆች፦
◆ ከመታገል ይልቅ ለመሸነፍ ቅርብ...
◆ወድቆ ከመነሳት ይልቅ እዛው ለመቅረት...
◆ ደጋግሞ ከመሞከር ይልቅ ቶሎ ተስፋ ለመቁረጥ ቅርብ ነን።

➊ ዛሬ እኛ ለመብራት የምንጠቀመውን አምፖል የፈጠረው ሰውዬ አንድ ሺህ (1,000) ጊዜ ሞክሮ ነው በአንድ ሺህ አንደኛው (1,001) ነው የተሳካለት። ይህን ሁሉ ጊዜ ሙከራ ባያደርግ ኖሮ እኛ ዛሬ የምናበራው ነገር ባልኖረን ነበር!!
➋ ገናናው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ምንስትሪን (8ኛ ክፍልን) 8/9 ደጋግሞ ከወደቀ በኋላ ነው ተሳክቶለት ለዓለም ብዙ ፈጠራዎችን ያበረከተው።

ወንድምና እህቶቼ፦
ሳይታገል፣ ሳይለፋ፣ መስዋዕትነት ሳይከፍል ስኬትን የሚጎናፀፍ የለም!!
ደጋግሞ ወድቆ፣ ደጋግሞ ሳይነሳ ከፍ ብሎ የሚበር የለም።

⭕️ ቱርኮች ❝ከፈለክ ህይወትህን እጣ እንጂ ተስፋ እንዳታጣ❞ ይላሉ። አዎ ተስፋ ከቆረጥን ይችህ ዓለም ለኛ ቦታ አይኖራትም። ስለዚህ ውድ ተማሪዎች ውስጣችሁ ላይ ያለውን “አይሳካልኝም” የሚለውን ፍርሃታችሁን ጠንክሮ በማንበብ በስኬት ቀይሩት። ደግሞም ነገሮችን በመቀየር ከአናንተ የተሻለ  ብቃትና ክህሎት ያለው አካል ፈፅሞ የለም!!

◉ እናም በዚህ ብቃታችሁና ክህሎታችሁ ተጠቀሙበት። ለስንፍናችሁ ማንንም ተወቃሽ አታድርጉ፤ ምክንያትም አትደርድሩ!!

✍️
@Mejnun_nn

@Ikhlasikhlas1
@Ikhlasikhlas1
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot

Ikhlas institute

25 Oct, 07:04


የበለሁትን ስለማልከፍል ነው ቤተሰቦቼ እቃ ሚያሳጥቡኝ "🙃😂


አለችኝ👇
እህቴ

@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot

Ikhlas institute

25 Oct, 04:37


#ይህን_ያውቁ_ኖሯል

ሳይኮሎጂስት የነበረው "ሲግመንድ ፍሮይድ'' ባጠናው ጥናት መሰረት ሴት ህፃናት 3 ዓመት ከሞላቸው ጀምሮ በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያፈቅራሉ::

እርሱም አባታቸውን ነው:: አባት ባያውቅም ልጅቷ ግን እስከ 6 ዓመቷ ድረስ በአይን ፍቅር ትቀልጣለች:: እኗቷንም እንደ ተቀናቃኟ ትቆጥራታለች ሴቶች?

@Ikhlasikhlas1
@Ikhlasikhlas1
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot

Ikhlas institute

25 Oct, 04:27


((ሱረቱል ከህፍ))📖🎧

በቃሪእ አፊፍ ታጁ
@ikhlasikhlas1
@ikhlasikhlas1
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot

Ikhlas institute

25 Oct, 03:59


ጨለማውን ገፎ ብርሀንን ለሚያሳየን ሀያል አምላክ አሏህ  ምስጋና ይገባው!!

      አልሀምዱሊሏህ
@Ikhlasikhlas1
@Ikhlasikhlas1
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot

Ikhlas institute

24 Oct, 19:23


ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍️በሐዲሥ የመጡ ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው ሁነት፣ ቀንና ወቕቶች፦
①) ከውዱእ በኋላ፣
②) ሱጁድ ላይ፣
③) በእኩለ-ለሊት፣
④) የዓረፋ ቀን ላይ፣
⑤) ዝናብ ሲዘንብ፣
⑥) ፆመኛ ሲያፈጥር፣
⑦) ከፈርድ ሶላቶች በኋላ፣
⑧) ለሌሎች ዱዓ ስታደርጉ፣
⑨) የታመሙትን ሲትጎበኙ፣
⑩) በዩኑስ ዱዓ አላህን የለመነ፣
⑪) ከሓጅ ወይም ከዑምራ በኴላ፣
⑫) የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት፣
⑬) በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር፣
⑭) በጁሙዓ ቀን ከዓስር ሶላት በኋላ፣
⑮) በአዛንና በኢቃም መካከል ባለው ጊዜ።
@ikhlasikhlase1
@ikhlasikhlase1
http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot

Ikhlas institute

24 Oct, 18:44


ሰላም ለእነዛ.....

ክፍል ውስጥ አስተማሪ እየገላመጣቸው፣ እያሳቀቃቸው፣ በውጤታቸው እየተጫወተ፣ አትችይም እያለ በተማሪ ፊት ክብራቸውን ዝቅ ሊያደርግ እየሞከረ፣ በማስክ አውልቂ ምክኒያት ቢሮ ለቢሮ እያንከራተታቸው ከዳይሬክተር እስከ ጥበቃ በስድብ ሊያንቋሽሿቸው እየሞከሩ........ይሄን ሁሉ ችለው ሂጃባችንን አናስነካም ብለው አላማቸውን ሰንቀው ፣ በጌታቸው ተመክተው፣ ለካፊር እጅ አንስጥም ፤ተምረን ሙስሊሙን ኡማ እናገለግላለን ፤ ኢስላምን እንኻድማለን የሚል ትልቅ ተስፋ አንግበው ጥርሳቸውን ነክሰው ብዕር እና ማቅለሚያቸውን ይዘው በማለዳ ትምህርት ቤት ለሚመላለሱት ልእልት የhighschool ተማሪዎች



እነዚህን ጀግኒቶች ምን ብለን እንጥራቸው!!!

@ikhlasikhlas1
@Ikhlasikhlas1

http://t.me/Ikhlas_Institute_Bot/Ikhlas_Institute_Bot