ዝማሬ ዳዊት✝⛪⛪ @zemaredawit Channel on Telegram

ዝማሬ ዳዊት

@zemaredawit


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች፣ወረባቶችን ፣ ዝማሜዎች፣አጫብር ወዘተ..... ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

እናመሰግናለን!

ለማንኛውም አስታየት ወይም መዝሙር ለመላክ ስትፈልጉ፦ @zemaredawi
________________
@zemaredawit @zemaredawit

ዝማሬ ዳዊት✝⛪⛪ (Amharic)

ዝማሬ ዳዊት✝⛪⛪ ወደሚያመልኩ ተማሪዎች እና ወደሚከታተሉ እምነት ያግኙን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮችን፣ ወረባቶችን ፣ ዝማሜዎችን ፣ አጫብርን ወዘተ ዝማሬ ዳዊት✝⛪⛪ አማካኝ እና አዝናኝ መዝሙሮች እና መረጃዎች እንዲሰጡ በማስተካከል፣ ከቻናላችን ይቀላቀሉ። የሚቀጥሉትን አዝናኝ መዝሙሮችን እና መረጃዎችን፣ ለመላክ ስትፈልጉ እባኮት በ@zemaredawit ላይ እንደገና የሚለዋወጥ ቀላል መረጃ ያለውን መልእክተኞችን ዝማሬ ዳዊት✝⛪⛪ በቅማል እንደሚገባው አስተናጋዮች ይጠቀሙ። እናመሰግናለን! @zemaredawit @zemaredawit

ዝማሬ ዳዊት

25 Aug, 15:16


https://youtu.be/lTFVdxpwFsQ?si=GFh7u816CcCkjbhZ

ዝማሬ ዳዊት

27 Sep, 16:34


🔴 አዲስ ዝማሬ " መስቀል ነው ኃይላችን " ዘማሪ ዲያቆን አቤኔዘር ፍቃዱ @-mahtot
https://youtube.com/watch?v=-XlyZqLr01s&si=024x9HSArNuiPH57

ዝማሬ ዳዊት

27 Aug, 07:08


https://vm.tiktok.com/ZMjRM6PSQ/

ዝማሬ ዳዊት

05 Dec, 11:05


https://youtu.be/TLm-WRLjgCY

ዝማሬ ዳዊት

18 Aug, 19:54


💐እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ💐
​​ ✟ ደብረ ታቦር ​​✟ #በመዝሙር_እና_ኪነጥበብ_ክፍል_የተዘጋጀ @mezmurtinat1
#ግጥም
● #በእህታችን_ፋሲካ ●
══◉❖◉══

ዝማሬ ዳዊት

17 Jul, 05:47


https://vm.tiktok.com/ZMNuByrvF/?k=1

ዝማሬ ዳዊት

18 Jun, 19:23


"ወደ ተራራ ውጡ ዕንጨትም አምጡ ቤቴንም ስሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል"
ት.ሐጌ 1፥8
በዚህ አምላካዊ ቃል መሠረት የቤተክርስቲያናችንን መቃኞ ለመስራት ሁላችንም ትብብር በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ!
#share

ዝማሬ ዳዊት

17 Apr, 16:56


#ሆሳዕና

ሆሳዕና በእብራይስጥ 'አሁን አድን' በግዕዝ ደግም 'መድኃኒት' ማለት ነው።

ሆሳዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሳዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ለምን ከረቡዕ ጀምሮ ይታሰባል ቢሉ ጌታችን ሐዋርያትን አህያይቱንና ውርንጫዋን ያመጡ ዘንድ ወደ ቤተፋጌ እንዲሄዱ ያዘዛቸው ረቡዕ ነው እነሱም ፈልገው ያመጧቸው በዕለተ እሁድ ነው።

በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ "ሆሳዕና በአርያም" "ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት" "ዕለተ ሆሳዕናሁ አርዓየ… " ወዘተ... በማለት እየተጠቀሰና እየተዘመረ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበት ሁኔታ እየተተረከረ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሳዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።

🔖በአህያ መቀመጡ፦
1, ትህትናን ለማስተማር።
2, የሰላም ዘመን ነው ሲል(በብሉይ ዘመን ነቢያት የክፋት ዘመን መምጣቱን ሲናገሩ በፈረስ ላይ ተጭነው ይታያሉ፤ የሰላም ዘመን የምህረት ዘመን መምጣቱን ለማሳየት በአህያ ላይ ይቀመጣሉ።)
3, በአህያ ላይ የተቀመጠ ሰው ሮጦ አያመልጥም ክርስቶስም ከፈለጋችሁኝ እገኛለሁ ሲል በአህያ ላይ ተቀምጧል ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል ነው፡፡

🔖ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፦ ዘንባባ እሾሃም ነው፤ አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤ በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ፤ አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡

🔖የተምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦
ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡ አንድም፤ ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መልቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡

🔖የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦
ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡

🔖ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፦
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?

ዝማሬ ዳዊት

04 Apr, 17:53


#እኔ ማነኝ
ልመናዬን ያልከለከልከኝ
ጌታ ሆይ በፊትህ እኔ ማነኝ/፪/

ዳዊት የልብህ ሰው እኔ ትል ነኝ ካለህ
ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ ጭንጋፍ ነኝ ካለህ
ታዲያ እኔ ማነኝ ጌታ በፊትህ

የቀደሙት አበው ክብራቸውን ጣሉ
ብንኖር ብንሞት ላንተ ነው እያሉ
በፍቅር ተይዘው ቁልቁል ተሰቀሉ

በብዙ ተጋድሎ ክብርህን ወረሱ
እየሞቱ ጠሩህ ስምህን ሳይረሱ
እንደምን አመንከኝ እኔን እንደነሱ

እንዳላሰናክል ሌላውን በከንቱ
ይቀድሰኝ ዛሬ የፀጋህ እሳቱ
ናዝራዊው ኢየሱስ አስበኝ አቤቱ

ዝማሬ ዳዊት

27 Mar, 10:17


የዓቢይ ጾም ፭ኛ ሳምንት

ደብረ ዘይት

ምስባክ ፦ መዝ ፬ ÷፲፪

እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ።
ወአምላክነሂ ኢያረምም።
እሳት ይነነድድ ቅድሜሁ።

የዕለቱ ምንባባት

፩፦፩ኛተሰ.፬÷፲፫-ፍ.ም
፪፦፪ኛ ጴጥ.፫÷፯-፲፭
፫፦ግብሐዋ.፳፬÷፩-፳፪
ወንጌል፦ ማቴ.፳፬÷፩-፴፮
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

ዝማሬ ዳዊት

27 Mar, 10:17


https://telegra.ph/ደብረ-ዘይት-ዳግም-ምጽአት-03-23

ዝማሬ ዳዊት

27 Mar, 10:17


https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-መጋቢት-03-23-4

ዝማሬ ዳዊት

25 Mar, 17:15


Watch "🛑 አዲስ ዝማሬ "በአባቴ ቤት" ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) ◈New Mezmur Babate bet Zemari D Zelalem Takele (Zegola)" on YouTube
https://youtu.be/HGlvzuEQ-p0

ዝማሬ ዳዊት

20 Mar, 13:14


https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-መጋቢት-03-17-2

ዝማሬ ዳዊት

14 Mar, 07:15


አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)

ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል::

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ዝማሬ ዳዊት

14 Mar, 07:10


https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-መጋቢት-03-09-5

ዝማሬ ዳዊት

13 Mar, 11:00


የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት (መጋቢት 4/2014 ዓ.ም ) የቤተክርስቲያኗ ሥርዓተ ቀኖና በሚያዘው መልኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈጽሟል።

ዝማሬ ዳዊት

13 Mar, 11:00


#ምኵራብ


በመምህር አብርሃም በዕውቀቱ
መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

ኢየሩሳሌም በሚገኘው መቅደስ አይሁድ ስግደትና መሥዋዕታቸውን የሚያቀርቡት እንደሆነ ቢያምኑም በየተበተኑበት ቦታ ምኵራብ (ሰቀላ መሰል አዳራሽ፣ የአይሁድ የጸሎት ቤት) እየሠሩ ትምህርተ ኦሪትን በመማር ሃይማኖታቸውን ያፀኑ ነበር። (ዮሐ.፬፥፳) በብሉይ ኪዳን ዘመን የእነርሱ አምልኮ በኢየሩሳሌም በነበረው ቤተ መቅደስና በሥርዓቱ የተመሠረተ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትj እንደሚገልጸው ናቡከደነጾር የአይሁዳውያንን ቤተ መቅደሱን አፍርሶ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን ካፈለሰ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚገኙባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማኅበረተኛነት ልዩ ቤት ሊሠሩ እንደጀመሩ ይገልጻል፡፡


አይሁድ በምኲራቦቻቸው የሕግንና የነቢያትን መጻሕፍት (የብራና ጥቅሎች) በአንድ ሣጥን ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡ በመሆኑ የጸሎት ሥፍራዎቻቸውን ለትምህርትና ለአምልኮ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በሕገ ኦሪት የአይሁዳውያን ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ ሕግ ነበር፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ ተግባራት ከሚሄዱበትም ይልቅ በዓመት አንዴ የሚቀርበውን መሥዋዕትና መብዓ ለመስጠት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሕግ ሊፈጽም ወደ ቤተ መቅደስ ይሔድ ነበር፡፡ ‹‹ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሞላው ጊዜ እንዳስለመዱ ወደ ኢየሩሳሌም ለበዓል ወጡ›› እንዲል (ሉቃ.፪፥፵፪) ‹‹ዕለት ዕለትም በቤተ መቅደስ (ምኵራብ) ያስተምር ነበር፡፡›› (ሉቃ.፲፱፥፵፯)

በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ አይሁድ፤ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ›› እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኵራብ ማስተማሩን እያነሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኵራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ስለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ስለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ ነው፡፡ (ማቴ.፳፩፥፲፪)


ጌታችን በምኵራብ እየተገኘ ሲያስተምር ትምህርቱን ሕግን አውቆ እንደሚያሳውቅ ሠራዔ ሕግ ስለሆነ በሙሉ ሥልጣንና ኃይል ያስተምር ነበር፡፡ ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕትአነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለየሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው)፤ ወደ ምኵራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ። የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)


ቅዱስ ዳዊትም አስቀድሞ በተናረው ትንቢት መሠረት ጌታ ለቤተመቅደሱ ቀንቶ አጽድቶት ነበር፡፡ ‹‹እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፤ የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡›› (መዝ.፷፰፥፱)

ምንጭ:- ማኅበረ ቅዱሳን ድህረ ገጽ

ዝማሬ ዳዊት

13 Mar, 11:00


https://telegra.ph/ስንክሳር-ዘወርኀ-መጋቢት-03-09-4