Ethiopian Business and investment network (EPN) @ethiopage_business Channel on Telegram

Ethiopian Business and investment network (EPN)

@ethiopage_business


የኢትዮፔጅ አላማ የኢትዮያዊያንን የትምህርት የስራ አንዲሁም የማህበራዊ ህይወት መረጃዎች (Amharic)

የኢትዮፔጅ አላማ የኢትዮያዊያንን የትምህርት የስራ አንዲሁም የማህበራዊ ህይወት መረጃዎች የሚሻለ ለማድረግ የሚረዱ መረጃዎችን የሚረጋገጥ ይችላል። ይህን ቻናል በ@ethiopage_business ብቻ ይመልከቱ። ቻናልዎችን ለማሳወቅ የሚረዱ ቻናልኑ በዚህ ቻናላ ውስጥ ይጫኑ። ድምጻችን ከ@ethiopagedotcom ጋር ይከታተሉ። የስራ ወይም ትምህርት መረጃዎችን የሚከተለውንም በ@ethiopagejobs, በትምህርት መረጃዎቹን ስለማስተዋወቅ በ@ethiopage_education ይጫኑ። ከዚህም በዚህ መነሻ ለሚፈልጉት ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርስ ተመልክተዋል። እናመሰግናለን!

Ethiopian Business and investment network (EPN)

08 Nov, 12:29


በኢትዮጵያ ዉስጥ ላላችሁ አዲስ የንግድ ሀሳብ ላላችሁ የተዘጋጀ እድል ።

አዲስ ድርጅት ሆኖ በቴክኖሎጂ ዙርያ ለሚሰሩ የሚሆን ሲሆን እስከ 12 ሚሊዮን ብር ኢንቨስት ያደርጋሉ ። ለዚህም የድርጅቱን 12.5% ሼር ይይዛሉ ።

እስካሁን ከኢትዮጵያ 3 ድርጅቶች በዚህ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በዚህእድልላይ ለመሳተፍ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ https://thebaobabnetwork.com/apply-now



Subject: Exciting Investment Opportunity for Ethiopian Startups!

Hey everyone,
Sharing some great news for Ethiopian startups looking for funding! Baobab Networks is offering investments of around $12 million in exchange for 12.5% equity.

This is a fantastic opportunity to scale your innovative ideas. Three Ethiopian companies have already benefitted from this program!

Ready to apply?
Click here: https://thebaobabnetwork.com/apply-now/
Let's connect! I'm passionate about supporting positive impact ventures in Ethiopia. Feel free to reach out if you have any questions or want to connect.

Best,
Girum A.
መረጃውን የተገኘው Linkedin ላይ ከዚህ ሊንክ ነው
https://et.linkedin.com/in/girumas

ethiopage.com/business

13 Mar, 13:06


ከጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ .. ለጥንቃቄ .. @ethiopage_admin

ethiopage.com/business

10 Mar, 09:23


THE BAG SHOW featuring top 12 🇪🇹 Ethiopian designers
13-03-2020 6 PM @ SHERATON ADDIS

ethiopage.com/business

05 Mar, 07:40


ኢትዮ ቴሌኮምና በቅርቡ ያደረገው የዋጋ ቅናሽ … የቀረው ነገር ?

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው ሳምንት የዋጋ ማስተካከያ አድርጓል .. ለቤት ተጠቃሚዎች እስከ 69% እንደሆነ ገልጿል … ይህም በጣም የሚበረታታ ነው …

ነገር ግን ከዋጋ በተጨማሪ ብዙዎችን የቤት ኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ እያስቸገረ ያለ ነገር አለ … ይህም ቤት ተከራይተው ለሚኖሩ ሰዎች ይህንን የቤት ኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ቴሌ የአከራይን ፈቃደኝነት ይጠይቃል …

የመኖሪያ ቤት ኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲያድግ ከተፈለገ ከቤቱ አከራይ ፈቃደኝነት ሳይጠየቅ በመታወቂያ ብቻ አገልግሎቱን መስጠት መቻል አለበት … ባይሆን ልክ እንደ ቅድመ ክፍያ የሞባይል ስልክ የወሩን ክፍያ ቅድሚያ ማስከፈል …

ይህንን ለማድረግ በየቤቱ ገመድ ማስገባት ተከራይ ሲወጣና ሲገባ እንዲሁም ሌሎች ትንንሽ የማኔጅመት ነገሮች ለቴሌ ሊከብድ ስለሚችል … ይህን የሚሰሩ ወጣቶችን በማህበራት በማደራጀት እነሱ እንዲሰሩትና ልክ ሞባይል ካርድ እንደሚሸጡት 5 - 10 % ክፍያ እንዲያገኙ ማድረግ …

ይህን አይነት መንገድ ተከትሎ አገልግሎቱን መስጠት ቢቻል በአጭር ጊዜ ውስጥ የቤት ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር እጥፍ እንደሚሆን ጥርጥር የለንም…

በተጨማሪም አሁን የለው ዋጋ ከበፊት ከነበረው ቅናሽ ቢሆንም በእኛ ግምት ተደራሽነቱን በማስፋት ለ1ሜባ 200 -250 ብር በወር ቢሆን ለኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ገቢን እንዲሁም ለተጠቃሚውም አገልግሎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ያስችላል …

ይህም በአገራችን ያለውን የኢንተርኔት ተደራሽነት ይጨምረዋል … እርሶም የሚሰጡትን አገልግሎት ወይም ምርት( በዲጂታል ማርኬቲንግ) በኢንተርኔት አማካኝነት ማስተዋወቅና ስራዎትን ለማስፋት ተጨማሪ መረጃዎችና ምክር ከፈለጉ … ይህንን ቻናል ጆይን ያድርጉ …

ይህን የቤት ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሻሻል የሰጠነውን ሐሳብ ከወደዱት ሼር ያድርጉት …
ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉን https://t.me/joinchat/AAAAAFPPUGmDpHs5-l7aFg
እናመሰግናለን
hahudigital.com

ethiopage.com/business

04 Mar, 14:40


ሰላም ነው ? እንዴት ነው ? ንግዱ እንዴት እየሄደ ነው ?

ምናልባት ” ኧረ እኔ ንግድ አልሰራም ተቀጣሪ ነኝ ” የሚል አይጠፋም … ግን ግን ቅጥርም ቢሆን እኮ ንግድ ነው… ጊዜና እውቀትን በገንዘብ እየለወጥን …
ታዲያ ሁላችንም ንግድ ስራ ላይ ከሆንን ይህንን ንግዳችንን ማሻሻል የምንችልበት መንገድ ስለ ሆነው ስለ ዲጂታል ማርኬቲንግ ትንሽ ነገር እንበል …

ብዙ ሰው ዲጂታል ማርኬቲንግ ሲባል የሚመጣለት fb ወይም ቴሌግራም ላይ የሚለቀቁ ማስታወቂያዎችን ነው .. አዎ እነሱም የዚሁ አካል ናቸዉ ነገር ግን አንድ ድርጅት ማስታወቂያውን ሶሻል ሚዲያ ላይ ስለለቀቀ ብቻ ዲጅታል ማርኬቲንግን በሚገባ ተጠቅሟል ማለት አንችልም

ምናልባት ግን ስለ ዲጂታል ማርኬቲንግ አዲስ ከሆነባችሁ ምን እንደሆነ አይተን ወደ ጥቅሞቹ ከዛም በንግዳችን ላይ እንዴት በአግባቡ መጠቀም እደምንችል እናያለን …

ዲጂታል ማርኬቲንግ ምርት አገልግሎት እንዲሁም ሌሎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ማስተዋወቅ እንዲሁም ከአዲስ ከነባር እንዲሁም ከእጩ ደንበኞች ጋር ዘላቂ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለን መንገድ ነው …

ለምሳሌ … አንድ የቆዳ ጫማ የሚሸጥ ሰው ቢኖር በፊት በነበረ ግዜ .. ስለስራው ሰው ለሰዉ እየነገረ … ማስታወቂያ እየለጠፈ ገፋ ካለ በሬዲዮና በቲቪ ማስታወቂያ እያስነገረ ተደራሽነቱን ያስፋ ነበር … አሁን ደግሞ ከነዚህ በተጨማሪ ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም የተሻለ ተደራሽ መሆን የሚችልበት እድል አለው …

ዲጂታል ማርኬቲንግ ተጠቅሞ ምርትን አገልግሎት ማስተዋወቅ እጅግ በጣም ብዙ ጥቅም አለው … ከነዚህም ውስጥ ከደንበኞች ጋር ዘላቂ ግንኙነት መፍጠር ያስችላል …

ለምሳሌ ቅድም ያነሳነውን ጫማ ሰሪ ብንወስድ በሬዲዮ ቢያስተዋውቅ በአንድ ጊዜ ብዙ ሰው ስለ ንግዱ ሊሰማ ይችላል ነገር ግን በሌላ ጊዜ ለነዚህ ሰዎች አዲስ አይነት ነገር ለማስተዋወቅ አይችልም … ዲጂታል ማርኬቲንግ በሚጠቀም ጊዜ ግን ሰዎች የእሱን ዲጂታል ቻናሎች በቀላሉ እንዲከተሉት በማድረግ አዳዲስ ምርቶችን ማስተዋወቅ ይችላል …

ከወጪ አንጻርም ቢሆን ዲጂታል ማርኬቲንግ በአነስተኛ ወጪ ብዙ ሰዎችን እንድናገኝ ይረዳናል … ሌሎችም ብዙ ጥቅሞች አሉት ወደፊት እናያቸዋለን …

ታዲያ ዲጂታል ማርኬቲንግ ብዙ ጥቅም ካለው ለምን ብዙ ድርጅቶች አይጠቀሙትም ? የሚል ጠያቂ አይጠፋም … አሁን አሁን ጥቂት የማይባሉ ድርጅቶች መጠቀም ጀምረዋል … ነገር ግን ከዋናው ስራቸው ጋር አቀናጅቸው የሚሰሩበት ብዙ አይደሉም … ይህ የሆነው ደግሞ ዲጂታልማርኬቲንግ የሚያስገኘውን ጥቅም ባለመረዳት ፣ ወይም እንዴት ሊተገብሩት እንደሚችሉ ያለማወቅ ሊሆን ይችላል …

ሀሁዲጂታል በዚህ ዙሪያ ያለውን ክፍተት ለመሙላት … በንግድ ስራ ላይ ያሉ ድርጅቶችን እንዴት ዲጂታል ማርኬቲን ተጠቅመው ምርትና አገልግሎትቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ ያማክራል … ( ሌሎች ተጨማሪ መሬጃዎችን እና ምክር ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን +251-118-447-432 ይደውሉልን )

በዚህ ቻናል ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዴት ዲጂታል ማርኬቲንግን ተጠቅመው ንግዳቸውን የተሻለ ማድረግ እንደሚችሉ እናያለን … የዲዲታል ማርኬቲንግ ቴክኖሎጂዎች ይተነተኛሉ … ጥያቄዎችን እንመልሳለን … በዚህ ዙሪያ የምናወጣቸው ተከታታይ ጽሁፎች እንዲደርሳችሁ ከዚህ ስር ባለው ሊንክ ቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉን https://t.me/joinchat/AAAAAFPPUGmDpHs5-l7aFg

ethiopage.com/business

05 Feb, 14:26


በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (part1)

ድርጅቴን ማስተዋወቅ እፈልጋለሁ.. በምን መልኩ ባስተዋውቅ ጥሩ ነው?

ድርጅቶን ለማስተዋወቅ ብዙ አማራጮች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ብዙ ሰው በአንድ ጊዜ ለመድረስ የሚያስችሉት እንደ ራዲዮ ቴሌቭዥን ጋዜጣ ናቸው። እነዚህ በተጨማሪ ደግሞ በዲጂታል ማርኬቲንግ አማካኝነት ማስተዋወቅ ይችላሉ።

ዲጂታል ማርኬቲንግ ምን ማለት ነው ?

ዲጂታል ማርኬቲንግ ማለት ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ተጠቅመን ማስተዋወቅ ነው ። አላማውም በቀላሉ ደንበኞችን ለማግኘት ያስችላል ፣ ቢዝነሱን ለማሳደግ ይረዳል፣ ድርጅቶችን የተሻለ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረክታል።

ዲጅታል ማርኬቲንግን ተጠቅሜ ድርጅቴን ማሳደግ እችላለሁ ?

አዎ .. ብዙ ድርጅቶች ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን በዲጂታል ማርኬቲንግ ተጠቅመው በማስተዋወቃቸው ትርፋማና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ እድገት ያሳያሉ። (ይቀጥላል) https://t.me/joinchat/AAAAAFPPUGmDpHs5-l7aFg

ethiopage.com/business

05 Dec, 08:29


2nd Hotel & Tourism Industry Job Fair And Networking Event
🗓December 9-10,2019|at the millennium hall

ethiopage.com/business

14 Nov, 13:22


ኢትዮ አዲስ የገና ንግድ ትርኢት በሚኒየም አዳራሽ በምዝገባ ላይ ይገኛሉ

ethiopage.com/business

30 Oct, 13:15


Trade logistics facilitation for competitiveness in manufacturing

ethiopage.com/business

28 Oct, 12:45


Textile value chain conference

ethiopage.com/business

28 Oct, 12:43


Leather and footwear industry conference

ethiopage.com/business

28 Oct, 12:40


ኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ባዛርና ኤግዚብሽን በጁባ

ethiopage.com/business

16 Oct, 14:20


Channel photo updated

ethiopage.com/business

12 Oct, 08:34


የእንስሳት ልማት ላይ ለተሰማራችሁ ኤግዚቢሽን ምዝገባው ኦንላይን ነው በዚህ ዌብሳይት https://www.pranaevents.net ይጠቀሙ

ethiopage.com/business

08 Oct, 09:35


የኮንስትራክሽን አቃዎች ኤግዚቢሽን… ሌሎች የንግድና ተያያዝ መረጃዎችን ለማግኘት ይህን ቻናል ጆይን ያርጉ t.me/joinchat/AAAAAFRCCGthJmppCWOkig

ethiopage.com/business

07 Oct, 12:18


ይህ የኢትዮፔጅ የንግድ ስራ ቻናል ነው። በመሆኑም ከናንተ ሀሳብ አስተያየት እንፈልጋለን እንዴት ብናገለግላችሁ መልካም ነው? ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት በ@ethiopage_admin ይላኩልን
public poll

ስለ ንግድ ስራ ጠቅለል ያሉ ምክሮች – 105
👍👍👍👍👍👍👍 45%

ብድር እና ቁጠባን በተመለከተ – 78
👍👍👍👍👍 33%

ስለ ንግድ ፈቃድ እና ግብር የተያያዙ መረጃዎችን ማግኘት – 51
👍👍👍 22%

👥 234 people voted so far.

Ethiopian Business and investment network (EPN)

14 Aug, 02:52


Channel created