ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 @eliyasshitahun Channel on Telegram

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@eliyasshitahun


#ገጣሚ_ኤልያስ_ሽታሁን ከሁሉም በላይ በዚህ ቻናል ይነግሳል ! ሌሎችም ድንቅ እና እውቅ ገጣምያን ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ፣ ኤፍሬም ስዩም ፣ ገብረክርስቶስ ደስታ ፣
መስፍን ወንድወሰን አስታወሰኝ ረጋሳ እና ሌሎች ገጣሚያን ስራቸው በዚህ ቻናል ይለቀቃል ! እናንተ ቻናሉን ተቀላቀሉ #Share በማድረግ ቤተሰባዊ ሀላፊነታችሁን ተወጡ🙏 እኔ @Henilogy ነኝ 🥰🥰🥰🥰🥰 ኢትዮጵያዊ

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን (Amharic)

እርስዎ የቻናሉን አስተያየትና ማስታወሻ ለምን ቻናሉን ለማከብከብ ስንችል ቤተሰባዊ ሀላፊነታችሁን ተወጡ። ይህን ቻናሉን በመሆን እኛ @Henilogy ሁኔታዊ የመረጃ መምሪያኖችን እና ሁለትኛ ከፍተኛ ተማሪዎችዋን ተናገረ። ቻናሉን ከፍተኛ አድርጉ። ኢትዮጵያዊያዊያዊያዊያዊ

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Jan, 07:04


🖌🖌ዘመነ መንሱት🖌🖌

ለዘመነ መንሱት
ለዚህ ጥቁር ቅኔ
መቼ ቦዘንኩ እኔ
ቦዘኔነቴንስ
አ..ደ..ገ..ኛ..ነ..ቴ..ን..ስ
እጄ ቀርፎልኛል
ከሥራ አስገብቶ ያስወለውለኛል።

🔱ከ የወንድ ምጥ መፅሐፍ 🔱
👉ገጣሚ (ይስማዕከ ወርቁ)👈

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ(ሼር)


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun     @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Jan, 10:43


┈◦◎●◉እራት እና መብራት ◉●◎◦┈

#ከበራሪ ቅጠሎች መፃሃፍ የተቀነጨበ
#አቅራቢ ፦በእውቀቱ ስዩም
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @eliyasshitahun
@eliyasshitahun
➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Jan, 10:42


➛➛እንዲህ ያደርገኛል➛➛

●●◦ግጥም በጃዝ◦●●

✰አቅራቢ፦አበባው መላኩ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @eliyasshitahun
@eliyasshitahun
➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Jan, 14:51


አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል፡፡

አርቲስቱ የእግር እሳት፣ ሥርየት፣ ሰው ለሰው፣ መንጠቆ ቴአትር እና ሌሎች የቴሌቪዥን ድራማዎች እና ፊልሞች ላይ በትወና መሳተፉን የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

በአዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ የተወለደው አርቲስት እንቁስላሴ ÷በኢትዮጵያ የሲኒማ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የራሱን አሻራ አስቀምጧል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ የሶስት ወንድ እና ሶስት ሴት ልጆች አባት የነበረ ሲሆን÷አስራ ሁለት የልጅ ልጆችንም አይቷል፡፡

ቻናላችን ለአርቲስት እንቁስላሴ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል፡፡

VIA ፦ FBC ( Fana broadcasting cooperation )

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Jan, 07:04


ጥምቀትና ሎሚ🍋🍋🍋

ጥምቀቱ ሲከበር ሲደምቅ እለቱ
ቀና ስል አየዋት ታምራለች ልጅቱ
ሰበርሰካ እያሉ ከሚዘዋወሩት
ተውበው ተኩለው ደምቀው ከሚታዩት
ከእንስቶች መሀል ይቺን መልከ ቀና
ከአይኔ ገባችና እጣዬ ሆነና
ስወረውር ሎሚ ላሳይ መከጀሌን
ከመቀመጫዋ አርፎ እንደ እድል
ነጥሮ እኔኑ መታኝ ከአናቴ መሀል😥

አዝኜ በሆነው በአጋጣሚው ስቄ😁
እንደተሳሳትኩ በምርጫዬ አውቄ
ሌላ አማተርኩና ከአንዲት ውብ ሎጋ
ጠጋ አልኩኝና ከጎኗ ላወጋ
አጫወትኳትና ብዙውን ለፍልፌ
እሷም ተመችቻት ብትገባ ከእቅፌ
ልዳብሰው ብዬ ያን ዞማ ፀጉሯን
ወድቆ ሂውማን ሄሩ አየው መላጣዋን😱

በዚህም ተናድጄ በእድሌ አዝኜ😡
ላልላከፍ ብዬ በልቤ ወስኜ
ልክ እንደተጓዝኩ ጥቂት በመንገዱ
ሦስት ሴቶች ባይ ከፊት ሲራመዱ
የመጨረሻ እድል ልሞክር አስቤ
ሎሚዬን አወጣው ከኪሴ ውስጥ ስቤ🍋
አይኖቼን ጨፍኜ ወርውሬ ብገልጠው
ከአንዷ ጡት አርፎ ነጥሮ ሲመጣ አየው
ግራ አይኔን ደቁሶኝ ይኸው በልዣለው
በእለተ በዓሉ አንድ አይና ሆኛለው😵

እኔ 'ምመክራቹ ለወንዶች በሙሉ
ለከፋውን ጠልተው ትተው ሴቱ ሁሉ
እስፖንጁን ታጥቀዋል ለውበት ለመከታ
እመታለው ብለ ብሮ እንዳትመታ
ለጠበሳ ተብሎ እየወረወራችሁ
ተመልሶ መ'ቶ እንዳያጋጫችሁ
     እናም
ተጠንቀቁ ወገን ይቅርብን ለከፋው
ላይሳካ ነገር ለእኛው ነው እዳው
ሎሚውም ተወዷል አደልእንደ
ድሮ
በገዛ ብራችን ከምንገዛ ሮሮ
መመለስ ይሻላል በሰላም አክብሮ።

😁😁እንኳን አደረሳቹ ውዶቼ😁😁

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
Share &comments

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Jan, 16:54


ጥምቀት

ደረሰልን ቀኑ በዓለ ጥምቀቱ
ከእዳ የነፃንበት ተሽሮ ፅህፈቱ
አምላክ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር
ከንፅህቷ እመቤት ከማህፀኗ ቢያድር
ከስጋዋ ስጋን ነሳና እንደ ሰው
ቃል እንደገባለት አዳምን መሰለው

በሠላሳ ዓመቱ ሄደ ወደ ዮሀንስ
ከገሊላ ተነስቶ ደረሰ ዮርዳኖስ
ከጥምቀቱ ቦታ ናዝራዊው ሲደርስ
ተጠምቆ ሲወጣ ልጅነት ሲያስመልስ
ሰማይ ተከፈተ ተገለጠ ክብሩ
ትህትናን ሲያስተምር አየን መምህሩ
አብም መሰከረ ስለ ልጁ ወልድ
በርግብ አምሳል ታየ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ

የሰው ልጅም በምድር ዳግም ተወለደ
የዲያብሎስ ውሉ ያኔ ተቀደደ
የጨለማ ዘመን በብርሃን ተተካ
የዳዊት ትንቢቱ በኢየሱስ ተሳካ
ከዘመናት በኃላ እኛም የእርሱ ልጆች
እናከብረዋለን ይኸን የምሰራች
ከተራ ጥምቀቱ
ዛሬ ነው እለቱ
ለሁላችን ይሁን ፍስሀ ደስታ
በእደ ዩሀንስ ተጠመቀ ጌታ

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ🥰መልካም በዓል
https://t.me/ortopiyaaa

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Jan, 07:41


መልካም በዓል 🙏☦️

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Jan, 06:35


ለመላው የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🙏

በዓሉ የሰለም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት እንዲሆን ከልብ እንመኛለን 🙏










☦️

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Jan, 17:09


ያጮለቀ ብቻ

ጠቢብ ቤት ሳይኖረው ፣ መስኮት ይከራያል
ግድግዳ ሳያቆም ፣ ሽንቁር ይከራያል
ያጮለቀ ብቻ ሁሉን ነገር ያያል።

∞><><><><><><><><><>><∞

ከ በዕውቀቱ ስዩም

@betagitim
@betagitim


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Jan, 06:09


በእውነት ጦርነት አስቀያሚ ነው ያስጠላል ! . . .ግን የሰው ልጅ ያለ ጦርነት የኖረበት ጊዜ የለም ! የሰው ልጅ ታሪክ የጦርነት ታሪክ ነው። የሰው ልጅ ያለጦርነት የሚኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን ? ምኞት ነው።

የጦርነትን ጥፋት በሰው ልጆች ላይ የሚጋብዙ ሰይጣናዊ ኃይሎች እስካሉ ድረስ ምን ተስፋ ይኖራል . . . ?

በአሉ ግርማ ፤ ኦሮማይ

ግብዣዬ ነው አንብቡልኝ...


🌻📖 @eliyasshitahun 📖🌻
  🌻꧁༻༒༺꧂🌻

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Jan, 06:08


የበአሉ ግርማ የብእር ቱርፋት...

🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
እንባ እንባ ይለኛል
ይተናነቀኛል
እንባ ከየት አባቱ
ደርቅዋል ከረጢቱ:
ሳቅ ሳቅም ይለኛል
ስቆ ላይስቅ ጥርሴ
ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነብሴ::

(በአሉ ግርማ "ኦሮማይ)

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Jan, 06:08


ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር
ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር?
የኔ ውብ ከተማ......
ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር
የኔ ውብ ከተማ......
መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር
የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር
የሰው ልጅ ልብ ነው
የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡
ሕንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ?
የሰውን ልብ ነው፡፡
ምን ቢነድ ከተማው ተንቦግቡጎ ቢጦፍ
ቢሞላ መንገዱ በሺ ብርሃን ኩሬ
በሺ ብርሃን ጎርፍ
ምን ያደርጋል?
ምን ያሳያል?
ካለሰው ልብ ብርሃን ፤

(ኦሮማይ:-  ገጽ 250 - 251)
ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ

Via : #ታሪክን_ወደኋላ

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

16 Jan, 18:23


#ትንሿ_ነበልባል

ውዷ የኔ በአል በግርማ
      የታየች በልቤ አለም ላይ
ድርሰት አይደለችም ፊያሜታ ጊላይ
_//_
*የ
ፊያሜት ጊላይ እውነተኛ መልክ ይህንን ይመስላል

   ኢዛና መስፍን
@topazionnn
@topazionnn
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

16 Jan, 06:41


🔆 #ስለት🔔
በስለት ፀንሰውኝ በስለት ወለዱኝ፣
በስለት አድጌ በስለት አለውኝ፣
መጥፊያዬም በስለት እንዳይሆን ሰግቼ፤
ሌላ ስለት ተሳልኩ ጧፍ ሻማ ገዝቼ።

🔊 #ገጣሚ_ይስማዕከ_ወርቁ🔊
ከወንድ ምጥ መፅሐፍ የተወሰደ
🎥

@eliyasshitahun   
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

16 Jan, 06:12


በነገራችን ላይ...
አንድ ያልገባን ነገር ያልተገነዘብነው
ሂያጅም ምክንያት አለው
ከመሬት ተነስቶ ሰው ሰውን አይርቅም
ቀድሞ አለመሄድ ፃድቅ አያስብልም!

ምስር🥰

t.me/yemispoems

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

15 Jan, 17:22


#Vest of civil

Scared to the village
tide strange
Indeed ! it not gossip
All admit a hand tip
Either charming or kind fate
Infront of God No! bait
Never Pleeding gossip
fake news up!
Grace of Poor justice
never more equity balance
sin sink within it slavery
Saint wears laughs delivery

poem from Dt
24/7/2013E.c

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

15 Jan, 10:45


ላንቺ የምመኘው

የሰው ሚዛን የነፍስ ልክ፤
የልብ አድባር ዕረፍት የሰርክ።
ፍቅር ሲሆን ድፍረት ያለው፤
በትሁት አንደበት ሞገስ የተሰጠው።
ለዓለም ትጋት የማያሙት፤
ከእግዜር ሲነጋገር ሰማያት የሰሙት።
እናት አባት የደገፈ፤
ገመና ሸፍኖ ክፉ ቀን ያለፈ።
ከወዳጁ የተስማማ በሰፈሩ የሚከበር፤
ክፉን በደግ የሚመልስ ቢጎዱት የሚምር።
ዲግሪ ጭኖ የጠበበ በዕውቀቱ የሚጠራ፤
እውነት ተናጋሪ ምን ይሉኝን የማይፈራ።
ጊዜውን መንዝሮ ሀብቱን ያካበተ፤
በኑሮ ውድነት ያልተንሸራተተ።
ድምጹ አንጀት አርስ ነፍስ የሚያረጋጋ፤
ቃሉም የድህነት(ላ) አዕምሮ ሚጠጋ።
ልብሱ የመኳንንት ንጉሳዊ አረማመድ፤
አኗኗሩ እንደ ካህን ስለ ፍቅር የሚሰደድ።
ስራው ከዳር የወጣለት የእጁን ፍሬ የሚበላ፤
ለማህተቡ የታመነ ቅጥፈት የሚጠላ።
ትከሻው ፈርጣማ የጸናለት ጫንቃው፤
ዓለምን ሚሸከም ለፍቅር አለቃው።
መምህር ተማሪ አዛኝ ደስተኛ፤
ቢናደድ ቢጫወት ሁሌም እውነተኛ።
ዘላለምን የሚያሳጥር ከዋክብትን የሚያዛቸው፤
አድማስ ሠማይ እቅፉ ስር ስሜቶችን የገዛቸው ።
ሰውነቱ አምላካዊ ቅድስናን የለበሰ፤
በሙቅ ትንፋሽ ስልጣን ያለው ነፍስ አስክዶ የመለሰ።
ራስ ሆኖ ሊከብርባት አክሊል የምትሆነው፤
ከውድም ውድ የወርቅ አምባር አንቺን የተሰጠው።
የመቅደስሽ ካህን ላንቺ ምመኝልሽ፤
ለነፍስሽ ማደሪያ ነፍሱ እንዲሆንልሽ።



ገጣሚ : እኔ
       😇

@topazionnn
@topazionnn

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

15 Jan, 06:17


ከትውስታዬ መሃል
ከትዝታዬ አድማስ
የራቀኝን ሳቀርብ
የራቅኩት ላይ ልደርስ

ሀ ብዬ
ብራናዬን ይዤ ከልቤ ሰው የፃፍኩት
ሀ ብዬ ፍቅር ስጀምር
አንቺኑ ያቀፍኩት

ነበር ብቻ ...ሆነ
የልቤ መሰበር የልቤ በሀዘን መከፈል
አሁን ትዝታ ነው የትውስታዬ ማህከል።

✍️ዳዊት @YOTORAWIII

@betagitim
@betagitim

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

15 Jan, 04:44


#መገናኛ
#ወግ
#ክፍል አንድ
በጠዋት የመነሳት በሽታዬ አሁንም ድረስ አልወጣልኝም ። አይደለም ለስጋዬ ለነፍሴ ራሱ መነሳት እጅግ ከባድ ፈተና ነው። በነገራችን ላይ ስጋዊ ህይወትና መንፈሳዊ ህይወት ተብሎ የአንድን ግለሰብ የመኖር የመሰንበት ዕድሜ ነጣጥሎ ለሁለት ከፍሎ ማየት እንደእኔ ሀሳብ ትልቅ ስህተት ነው ። ነፍስና ስጋ አይቀዳደሙም። ሁለቱ አይነጣጠሉም። ከለያየንማ ሰው መሆን ይቀራል ። ሁለቱ ተዋህደዋል።
በጠዋት መነሳት ሆኖልኝ አያውቅም ። በኦርቶዶክስ ሀይማኖት በምስጢረ ትንሳኤ ሙታን ጊዜ ጌታ ክርስቶስ በታላቅ ግርማ ሆኖ ለፍርድ ይመጣል ። ያኔ ታዲያ ፈጣሪ ሲመጣ መንፈቀ ለሊት ሲመጣ እኔን ተኝቼ እንዳያገኘኝ ለሊት ቶሎ አልተኛም ። አንዳንዱ ሰው ሲጠጣ ይሞታል ። ሌላው ጥሪት ሲሰበስብ ፡ ሌላውም ሲሰርቅ ከፊሉ ሲገድል እንዲሁ ያልፋል ። ሰው ማለት ሙሉ ማለት ነው ። ግን ለእኔ ሰው ጎደሎ ፍጡር ይመስለኛል ። ሰው ደካማም ሆኖ ሳለ በሁሉ ፍጥረት ላይ የሰለጠነ መሆኑ ያስደንቃል። በአንዲት ስንጥር ነፍሱ ልትወጣ የሚችል ፍጡር ነው ሰው ። ከሁሉ ከሁሉ መልካም ሰናያትን በአንድ ላይ የታቀፈ ሰው ማግኘት ከባድ ነው ። ገንዘብ ያለው ከሆነ አጠቃቀሙ ፡ ደስታው ይሰወርበታል። ደሃው ደግሞ ተስፋን ታቅፎ ተፈጥሯዊ ሆነ ሰው ሰራሽ ናዳዎች ህይወቱን ኳስ ሜዳ ያደርጉታል። ለዚህ ነው ሰው ጎዶሎ ፍጡር ነው የምለው።
        ረፋድ አራት ሰዓት አካባቢ በአንዱ ደረጃው ባልታወቀ መኪና ወደ መገናኛ ተሳፈርኩ ። መገናኛ በዓለም ቅርስነት መመዝገብ ያለባት መንደር ናት ። ሰው እንደ ጉንዳን የሚርመሰመስባት ከተማ ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለን የመኪና ቁጥር በአማካይ ለማወቅ ፡ ሰርቶ የሚበላውን ከሚሰርቀው ጋር ለማነፃፀር ጭብጥ ያለው ጥናት ለማካሄድ መገናኛ መገኘት በቂ ነው ። ችግር አጎሳቁሎት መሬት የተነጠፈውን ለመታዘብ ፡ ረከስ ያሉ ቁሶችን ለመሸመት ተመራጭ ናት ። ደግሞ አባሮሹ ዘና ለማለት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መርሃግብር ከመቶ እጅ ይበልጣል ። ሰው አባረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ቅጥረኞች ከለፍቶ አዳሪዎች ጋር የሚያደርጉት አሸናፊ አልባ ደርቢ!
የእግር ኳስ ጠበብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና የሚደርጉት ግጥሚያ ትልቁ ሸገር ደርቢ ይህ ነው ብለው በነፋሰ ድምፅ አየር ላይ ይሞሉናል። ምናአለበት መገናኛ መጥተው ቢያዩት የአባራሪና ተባራሪ ፡ የተሳፋሪና የተሽከርካሪ ፡ የችግርና የፅናት አውድማ ሀሳባቸውን በሽርፍራፊ ሰኮንድ ይቀይሩ ነበር ።  በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ ያሉ አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ምንም ጥቅም ዬላቸውም። ለምሳሌ፤ ሰላም ሚኒስትር ፡ ስራ ፈጠራ ኮሚሽን ፡ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ፤ የይዞታ ማረጋገጫ ኤጀንሲ ፡ የወጣቶች ሚኒስቴር ፤ከተማ ልማት …… ወዘተ እነዚህ ተቋማት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እምብዛም የሚረባ ነገር ሲሰሩ አላይም ። በመገናኛ ትልቅ በትር ተሸክመው አንድ አይነት ልብስ ለብሰው ለፍቶ አዳሪውን አሳደው የወር ደመወዝ የሚቀበሉ ተቆጥረው አያልቁም ። ከሁለት ቀን በፊት አንዲት ደርባባ ሴትዬ ቁጭ ብሎ ሎሚ የሚሸጠውን ልጅ መጣችና ከፊቱ አንባረቀችበት። ይባስ ብሎ ሌላው ባልንጀራዋ ተከትሏት መጣና በያዙት አጠና ልጁን ከሚነግድበት አዋክበው አባረሩት ። ሎሚውን ታቅፎ ሊሸሽ ሲሰናዳ በያዙት በትር ብትንትኑን አወጡት። በዚህ ሁሉ መሃል አንዱ ከለብላባ መጥቶ አንዷን ሎሚ ከአፉ እንደሰደደ መልሰው ከአፉ ነጠቁትና በያዙት በትር በመንገድ የተበተኑትን እንደመሰብሰብ ጀማመሩ ። የዕውነት ለመናገር መሰብሰብ ሳይሆን የገና ጨዋታ የሚጫወቱ ይመስሉ ነበር ። መገናኛን ዓለም ካሉ አደባባዮች ልዩ የሚያደርጋት ወከባና ግርግሩ  ገደብ አልባ መሆኑ ነው። ያም ቢሆን ግርግሩ ሰላማዊ ነው።
በአዲስ አበባ ውስጥ የትኛውም የኢትዮጵያ ንጉሥ ያላፀደቀው ለዘመናት የሚተገበር ህግ አለ። ጠዋት እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ ባለው ባለታክሲዎችና ረዳቶቻቸው ይለመናሉ። ከፋዩ ተሳፋሪ እየተሽማጠጠ እየለመነ ያቺን ጭንቅ ሰዓት ያሳልፋታል ።በማታው መርሃግብር ይህ ህግ ድጋሚ ይቀጥላል። ከዛ ውጪ ሰው ሰውን እስኪረግጥ ድረስ መጫኑ በረዳቱ የምኞት ጥግ ይወሰናል ።
YIKETLAL
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
#ከዲቲ/፩፪/፭/፼፩፫/ ተፃፈ
👍👍👍👍👍👍👍👍

Share ✔️✔️✔️join

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

14 Jan, 15:51


ገራሚ ግጥም 👉 ለወዳጆ ያጋሩ!
@eliyasshitahun @eliyasshitahun
@eliyasshitahun @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

13 Jan, 18:50


ከ..ዛ..ስ..?
@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

13 Jan, 08:43


ተወኝ

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

ጥኡም ግጥም ነች ተጋበዙልኝ🔥

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

13 Jan, 08:30


ኤልያስ ሽታሁን

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

12 Jan, 14:53


ካቲካላ የለም

ገጣሚና አቅራቢ ኤልያስ ሽታኹን 😍🔥🥰

ይችህን ሸጋ ግጥም ተጋበዙልኝ 🔥

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

12 Jan, 10:19


😮😮😮👏👏👏

🇪🇹

ኢትዮጵያውያን አጥለቀለቁት

የኢትዮጵያውያን መድረክ ነው
የሚባለው የዱባዩ ማራቶን ዛሬ የተካሄደ ሲሆን

1. በወንዶች:-
* ከ 1-10 ኢትዮጵያውያን

2. በሴቶች :-
* ከ1- 10 ኢትዮጵያውያን

በመግባት ዛሬም የበላይነታቸውን
አስጠብቀው ወጥተዋል::

አልፍ መብረክ
Congratulations 🎉🎊🍾

👏👏👏

🇪🇹

🌴🌴🌴

https://www.facebook.com/share/p/19r6kir8qN/?mibextid=wwXIfr

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

12 Jan, 10:03


ውዴ
ፍቅሬ አንዴ ልመርቅሽ
ይሰማል አይደል
ፍጣሪ...... ዝቅ ያርግሽ
አፍቃርሽን እንድታውቂ ወዳጅሽን እንድትለይው
እፉዬ ኑሮሽን እፍታ እንዳይወስደው
ውዴ
ፍቅሬ አንዴ ልመርቅሽ
ይሰማል አይደል
ፍጣሪ..... ዝቅ ያርግሽ!!
ግርጌውን ያዘናጋሽን ይሄን የከፍታ ኑሮ
ዝቅ አድርጎት ለአፍታ እንኳን ቀይሮ
ያስተምርሽ እንድሆን
ታስተምርሽ እንድሆን
ህይወት በላይ ታች ምህዋሯ
ህመምን ትካፈያት
ትቀምሽው እንድሆን እሾህ ከሆነው ስር
እንግዲያውስ ፍቅሬ አንዴ ልመርቅሽ
ይሰማል አይደል
ፍጣሪ.... ዝቅ ያርግሽ!!
ዝቅ ያርግሽ
የረገጥሽውን የአፍቃሪሽን ትከሻ ያሳይሽ
አዎ ውዴ
ከፍታ ያሳወረውን ዝቅታ ይመልሰዋልና
ምርቃቴ ነው ይህ ከሰማሽኝ በቀና
ዝቅ ያርግሽ ፈጣሪ በሃይሉ
ያስተምርሽ እንድታውቂው አፍቃርሽን በውሉ
አዎ ውዴ
አዎ ፍቅሬ
አንዴ ልመርቅሽ
ይሰማል አይደል
ፍጣሪ.... ዝቅ ያርግሽ!!!

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

11 Jan, 09:54


#አንተን ብቻ ስማ !!!
---------------------------------------------
ስትቀጥን ከስተሃል ገርጥጠህ ወድቀሃል ፤
ወዝ ብታወጣ በምቾት ደልተሃል ፤
ይሉሃል ሰዎች አንተኑ ያሙሃል ።
ቀልዱን ቀልደህ አፍ ባታስከድን ፤
ሳቅን ብትሞላው  ለከፋበት ቀን ፤
ቁምነገር የሌለህ ደረቅ ቧልተኛ ፤
ብለው ያንጓጡሃል ከንቱ ጓደኛ ።
ሸጋ ተጎናፅፈህ አጊጠህ ሲያዩህ፤
ስም ሊያወጡልህ ትተው ላይፋቱህ ፤
ጉረኛ ይሉኋል ለምድ ያለብሱሃል ።
ምግባር ለጠፋበት ለተሰወረበት ፤
ተግፃፅ ምክር ቢጤ ብትበትንበት፤
ጭቅጭቅ ንትርክ ወግህ ሰለቸኝ ፤
ከንፈር ሲመጥብህ ቀን ጎደለብኝ  ።
አንተኑ ይከስሃል ወጌኛ ጣለብኝ ።
አንተን ብቻ ስማ! ከልብህ ተማከር፤
የሚረዳህ! ዬለም ከራስህ በስተቀር ።
ሌት ተቀን ደክመህ ስታፈራ ጥሪት ፤
አይደለም ከላቡ ከሙስና ቅሌት ፤
ከምንዱባን ጉሮሮ በሌብነት ልባስ ፤
አውርደው ሲሰቅሉህ ለወሬያቸው ሱስ ፤
ደምረው ይጥፉሃል ከሹማምንቱ በረት ፤
ሀብት ካካበቱት ከመኳንንቱ ቤት ።
አንተን ብቻ ስማ ! በሞት ጠላት ዬለም፤
በህይወት እስትንፋስ ወዳጅ አይፀናም።

---------------------------------=--------------
ተፃፈ በዲቲ/
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

11 Jan, 09:54


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

10 Jan, 17:23


እርሱ ነው!

ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጥ
እህህ ብሎ አስብቦት መልስ ሚሰጥ
ለኔ ህይወት ግድ ሰጥቶት የሚጨነቅ
ወደኩ ስል አብሮኝ ሚወድቅ

ከዚያ ደሞ የሚያነሳኝ ሆኖኝ ድጋፍ
ወደር የለሽ ልክ የሌለው እልፍ ኣዕላፍ
እናት አባት ወዳጅ ጓዴ
አለው ብሎ ሚደግፈኝ ቅርብ ዘመዴ

እግዚያብሄር ነው መቆሚያዬ
የ'ሱ እቅፍ ነው ማረፍያዬ
ጥሎ ማይሄድ መሃል መንገድ
ጥግ የሌለው እኔን ሲወድ
ተስፋ ቆርጦ የማይተወኝ
ጥዬው ስሄድ እየማረ ሚመልሰኝ
ደሞ እንዳዲስ ልጄ ብሎ
ክፉ መጥፎ ማንነቴን ተቀብሎ
የሚወደኝ የሚያኖረኝ
አለው ብሎ ሚደግፈኝ
የሰራኝን እኔን ሸክላ
ላንዲት ቅፅበት ማይል ችላ
እግዚያብሄር ነው መቆሚያዬ
የሱ እቅፍ ነው ማረፊያዬ!

ምስር🥰
t.me/yemispoems

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

10 Jan, 15:15


እያነሱ ጣሉክ
ከእነሱነት ደጃፍ
ባትገኝ ከዕስቢያቸው
ከዕምነታቸው ጠረፍ
የበጎነት የመታመንን
ትርጉም
ባይረዱት ባያውቁት
እነሱ ፍጹም
ይሰብኩና ወፍ ዘራሽ ንግግር
ባይተዋር ቢያደርጉህ ብቻህን ብትቀር

አትፍቀድ በከንቱ  ውዳሴ አትሸንገል
ዞርህ ከራስህ ነው...
ኮራ ብለህ የኔ መንግድ ያዋጣኛል በል።

by ᵈᵃʷⁱᵗ

@betagitim

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

09 Jan, 18:41


Discussion Note...

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

09 Jan, 14:09


14 ሺ ስንገባ ትልቅ Surprise ይኖረናል

Let go to 14 ሺ....🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

09 Jan, 14:05


ደቀ መዝሙርህ ነኝ

ገጣሚት ህሊና ደሳለኝ


ለነብስ የምትሆን ምርጥ ግጥም ነች ተጋበዙልኝ 🙏 ☦️

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

08 Jan, 13:13


ይሄንን ምርጥ ግጥም ተጋበዙልኝ 🔥💞🔥

በተለይ ፍቅር እስከ መቃብር ላነበባችሁ🙏

ርዕስ ፦ ውድነሽ በጣሙን
ገጣሚ ፦ ባለቅኔው ሙልጌታ ተስፋዬ

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

04 Jan, 14:37


ዘምሪ

ከንፈርሽ ሲላቀቅ ግጥሙን ሊያዜመው
ሊቀፅል ሲነሳ ፍክት ሊያደርገው
ዜማን ሊሞሽራት ሲኩላት ሲያስጌጣት
የድምፅሽን ብርሃን አልብሶ ሲያስውባት
      
         እኔ እጨነቃለሁ
ድምፅሽ ሴጣን ይመስል ደርሶ እለከፋለሁ
  
.......አንቺ ስትዘምሪ......
ዛር በውስጡ እያለ ጠበል እንደገባ
የማወራው ቆቦ ስሜቴ አራምባ
  
   ዘምሪ አንቺ ብቻ
  ቀፅይ አንቺ ብቻ
  ተቀኚ ያለ አቻ


የዳዊት በገና ድምፅሽ ላይ ተገኘ
የዕዝራ መሰንቆ በለዛሽ ተቀኘ
      
ምነው ባደረገኝ ጥርስ ወይ ከንፈርሽን
ድምፅሽ በኔ ሲያልፍ እንዳያት ገነትን

      የምሬን ነው ምልሽ
ዘፈን ሀጢአት ሳለ ባንቺ ከከበረ
ማረኝ አምላኬ እያልኩ አሰማሽ ነበረ

         እባክሽ🥺
ድንገት እንኳ አንዴ
      ቢቻል ድምፅ'ን መሳም
ከከንፈርሽ ሲደርስ
       እኔም አንዴ ልሳም።


     ✍️ [👉   @henila31]

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

04 Jan, 09:44


..............
ፍቅርና ጥላቻ

እዲያ ስከራተት እኔ ያተ ወዳጅ
ግን አተ ሁነሀል የሌላ ወዳጅ
አወ አፍቅሬሀለው
በመገዱ ቁሜ ስምህን እጠራለው
ወይ ጉዴ..
ወደድኩህ አልኩ እንጅ ሌላ ምን ሰርቸ
ሰምህን ሰጠራ በመሰመር ወጥቸ
ሂጅ አልከኝ ሄድኩልህ ሀሜቱን ፈርቸ
እኔ ግን ከሄድኩኝ ከግዲህ በኋላ
ብጠራኝ አልመጣም ጭራሽ ወደኋላ
እዲያውም ልገርህ...
      ጭራሹን ጠላውህ
ጊዜ ተመልሶ አተ አፈቀርክና
ስሜን እኮ ጠራህ ቁመህ  ከጎዳና
አወ...     አተ እኔን ወደድከኝ
          እኔ ግን ጠላውህ
አየህ ..እኔ እያፈቀርኩህ አተ እኔን ስጠላኝ
         ትመጣለህ ብየ  ስት አመት ጠበኩኝ
አወ.....አሁን ትቸሀለው
በመገድህ መሀል ላልገባ ምያለው
ዳግም እዳትመጣ እራሴን ሁኛለው

#ገጣሚ_ዙፋን_ደጀን

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

04 Jan, 06:19


ህልምና ቅዠት😢

መኖር ሲሰለቸኝ ህልምን እየቃዡ
ማሰብ ሲታክተኝ በዝቶ አወዛዋዡ
ወዲያም ወዲህም ሳልል
በአንድ ቦታ ቆሜ ብዙ ስሽከረከር
ሲሰለቸኝ ማሰብ ሲሰለቸኝ መኖር
ቅዠት አይደለ ህልም
በማላውቀው አለም
ህልምና ቅዠቴ ቢደበላለቅም

ቅዠቴን ህልም ነው እያልኩኝ 'ኖራለሁ
በአንድ እንቅልፌ ላይ ብዙ ህልም አያለሁ
ህልምና ቅዠቴን መለየት ታክቶኝ
በሁለት አለም ላይ መኖርም ሰልችቶኝ
ከመሃል ላይ ቆሜ እወዛወዛለሁ
በአንድ ቦታ ሆኜ ሩቅ እሄዳለሁ

ለነገሩ እኔ ህልም ሆነ ቅዠት
እውነት ሆነ ተረት
ሲመሽ እየተኛሁ ሌት እነቃለሁ
ምን አገባኝ እያልኩ ህልምና ቅዠቴን ዝም ቢዬ 'ኖራለሁ

t.me/yemispoems
by ምስር🙄🙄

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

03 Jan, 10:50


🤭
😳
😫

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

03 Jan, 10:50


ይሄ ግጥም

😁

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Jan, 16:50


#ስንት_ገባ_ልብሽ

የት ገባ ወገብ ዉሎ የት አደረ
አካል ና እርምጃሽ በኔ ተፈቀረ
ስንት ገባ ጸባይ
ስንት ገባ ዳሌ
ዳሌ ና ወገብ  ሲባል
      ሁሉም አንቺን ያረጋል ምሳሌ
ገበያ ይወጣል አንቺን ተከትሎ
ወገብ እና ዳሌ ስንት ገባ ብሎ?
ደማምቀሽ ያበራሽ እንደሆን
   መወደዱ አይቀር
ምኔን ነክተሺኝ ነዉ እንጃ የኔ ነገር
እግርሽን የጣልሺበት
    እግሬ መች ያርፍና
ቀኔ ፈክቶ ይዉላል
   አይንሽን አይና
መልክና ዳሌሽን ቁማር ብታሲሺዢዉ
የአለም መንግስታትን ነበር ምታሰልፊዉ
ስንት ገባ እንደዉ ወገብ ና እርምጃ
ከፍለዉ ይዩሽ ቢባል የት ይኬዳል ምልጃ
ቢተመንም ረክሶ ዋጋዉ እጅግ ቢንር
ገበያ ከወጣ መነገዱ አይቀር
ስንት ገባ ግን
   ጨረቃ ሚሰዉር ...የዉበትሽን ስንኝ
   ሰምና ወርቁን ለይቶ ሚያዉቅለኝ
ስንትም እከፍላለዉ
   የሳቅሽን ዜማ በጋሽ ጥላሁን ፊት
   ተደርጎ ሳይቆጠር አምስተኛ ቅኝት
ጠይቄ ...እግዜርን
  ማፍቀር ምን ነበረ ብለዉ
ከሰማይ ላይ አንድ
     ከዋክብት መርጦ ጨረቃ አርጎ ማምለክ
ልክ እንደ መዚቃ
    የልብን ዜማ ጥም መቁረጫ መድረክ
የእርቅ ሸንጎ ሸምጋይ ታድሞበት
እርቁ በፍቅር ሲፈጸም እንደማየት
ነበረ ምኞቴ
ስንትም ከፍላለዉኝ
  ያማረማ አካል ተገምቶ ስንትም ይነገዳል
  እስቲ ልጠይቅሽ ልብሽ ስንት ያወጣል??
ሐሴት ተሞልተሽ ምርኮ የምትገቢዉ
ከከዋክብቱ መሀል አንዱን ምታመልኪዉ
ጨረቃ ስታዪ ትዉስ ትዝ የምልሽ
ስንት ገባ ልብሽ ንገሪኝ ገምተሽ??
ስንት ገባ ዳሌ
ስንት ገባ ወገብና ጸጉር
የጸጉርስ ይሁን
መች ነዉ ዋጋ የወጣለት ግን ፍቅር??


#ስንት_ገባ

✍️ከዳዊት @YOTORAWIII

@betagitim
@betagitim


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Jan, 12:58


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Jan, 11:18


ለግጥም አፍቃሪዎች 😍

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን  ቻናሉን
join ብለው እንዲቀላቀሉ እጋብዛለሁ።
በብዙ ይዝናኑበታል ያተርፉበታልም።

😍 join/ጆይን /👇👇👇
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Jan, 17:53


ቢሆንም ባይሆንም!


ስንት ሀኪም   ፣  ስንት ሺ አየር አብራሪ
ኢንጂነር     ፣   እልፍ አእላፍ ተመራማሪ
ስንት ህልም  ፣    ስ ን ት ድንቅ ሀሳብ
ሲመክን ገደል ሲገባ በኑሮ ሰንሰለት ሲሳብ

እያየው በየ ገመናው እያየው በየጎዳናው
እንደዚ ብትሆን አትበሉኝ እንዲ ነው ሰው ይሉት ዳናው።

ቢሆንም አለን እንደዚው

@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Jan, 14:01


ውበት ቃል ቢኖረው አውቃለው ልክሽ ነው
ማስተዋል ስም ኖሮት ቢጠራም ባንቺው ነው
ቁመትም ቢለካ ውበትስ ቢመዘን
እንድ አንቺ ጋር ሚደርስ አላቅም በዘመን
ታሪክ ያወራሉ ታሪክ ይነገራል
በጨርቅም ሸራ ላይ ስዕልስ ይቀራል
ስዕልስ ይቀራል በጨርቆች ሸራ ላይ
እንዴት አመለኩሽ ከአምላኬ በላይ
ድርሳን ተፃፈለሽ ያለምንም ገድል
ሴት አምላክ የሆንሽው በልባችን በኩል

ጠዋት 3ሰዓት ላይ ጥለሺኝ ስትሄጂ
ከግቢ ስትወጪ
ምትሸጪኝ መሰለኝ በ30 ዲናር ዳግም ማትመጪ
ትዝ ይልሻል ውዴ ያኔ ተቀምጠን
ምን አንዳልኩሽ ያኔ
ትናቴም ይፈርሳል, ዛሬዬም ይወድቃል
ነገ ያልኩት ሁሉ ብቻውን ይቀራል
ትናፍቂኛለሽ ብዬ ነግሬሽ ነበር ያኔ ስትለይኝ
ክብደቱን ሳላውቀው ነበር  ያልኩሽ ያኔ አሁን ይቅር በይኝ
ትናፍቂኛለሽ ከአምላኬ በላይ ከደመኛዬ እኩል
7 ቀን ሆኖሻል ለአምስት ስድስት ተኩል

ትናፍቂኛለሽ ከ የአቆብም በላይ
እንደው ባገኘሁኝ 14አመት ሆኜልሽ አገልጋይ
ልክ እንደ አብርሃም በ መቶ አመቴ ካንቺ በወለድኩኝ
ልክ እንደ ሮሚዬ አይንሽን አያየው ኑሬዬን በሞትኩኝ
ልክ እንደበዛብ ቅኔው በጠፋብኝ አንቺን ስመለከት
አምላኬን ካልከፋው ቆሜ ልያዝልሽ ቅኔና ማህሌት

ደግሞ እኮ ችግሩ ጎበዝ ገጣሚነሽ
ምለው ነገር ሁሉ አይደለም ሚከብድሽ
በምን ልሸንግልሽ
ፍቅር እንዲይዝሽ ድክመትሽ ምድነው
ልባም ሴት መማረክ ለካ እንዲ ከባድነው
እውነት ግን ከባድ ነው
በእውቀት ማህደር የሰማይ ጥግ ነሽ
በምድር ደረጃ ደግሞ ልባም ሴት ትሁት ነሽ
ቆንጆ ነሽ
ጠይም ነሽ
ቀጭን ነሽ
ጎበዝ ነሽ
ትሁት ነሽ
ይሄን ሁሉ መሆን ባንድ ገላ ባንድ ሰውነት
እረ እንዴት ተቻለሽ

አው ናፍቀሺኛል
አልናፍቅም ያልኩት ቃሌም ተቀይራል
ተብታባ ብሆንም ከምር ናፍቀሺኛል
ኮልታፋ ብሆንም ቃላት የሚጨንቀኝ
ዛሬ ግን ተናገርኩ ናፈቅሺኝ መሰለኝ
ብሶብኝ መሰለኝ።
አዎ ናፍቀሺኛል

ናፍቆትሽ ይሆን እንዲ የከበደኝ
ቁንጅናሽ መሰለኝ ግርጌሽ ያስቀመጠኝ
ሰው ነሽ እንዳልል የሚገርም ቁንጅናሽ
መላእክት እንዳልል አጥፍተሽ አልተጣልሽ
እምላክስ ቸር ሆኖ እንቺን የመረጠሽ
መደነቅ ጀመረ የሱ ፍጥረት ሆነሽ
ደንግል ሆይ ስሚኝ ነብሴን ተማለጂያት
አንዴ ብቻ ሳይሆን
እድሜ ዘመኔን እሳን ብቻ ልያት

አሜን😊!!!
https://t.me/zzzzaa123
@mikimekonen9

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Jan, 13:55


እናመሰግናለን 😍😍😍🙏

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Jan, 13:52


ይሄ ግጥም

💞
😍
🔥

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Jan, 11:19


ይሄ ግጥም

💔
💔

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

31 Dec, 08:36


ይሄ ግጥም


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

31 Dec, 07:10


🌿🌾ሴት ነሽ

አወ እኔ ሴት ነኝ..
አጎብሰህ ሳይህ ቀና የማደርግህ
እዳይከፋህ ብየ ልቤን የምሰጥህ
ወጠህ እስክትገባ የምጨነቅልህ
እንደ ህጻን ልጅ ሁሌም የማላምንህ
ደስታህን ፈልጌ እኔ እምከፈልህ
አወ እኔ ሴት ነኝ ፍቅርህ ያሸነፈኝ
የናትነት ክብር የተጎናፈኩኝ
እኔ ተጠምቸ አተ እንድጠጣልኝ
ያለኝን ባካፍል ሁሌም ድስ እሚለኝ
ለፍቸ የማድር እኔ ጨዎ ሴት ነኝ
ሴት ነሽ ነው ያልከኝ??
ሴት ስድብ መስሎህ..
ወይስ ትንሽነት?
እዴት ተረዳሀው እስኪ አተ ንገረኝ
እናትህን ወደህ እኔን ከሰደብከኝ
እናትህ እኔ ናት..
እህትህ እኔናት..
እዴት አስበህ ነው ህጅ አች ሴት ያልከኝ..?
ሴት እናትህ ናት
ሴት ውበትህ ናት
ሴት አድማቂህ ናት
ልጅነትህን ደግማ እምታሳይህ
ሴት የሂወትህ ሚስጥር
    ትልቋ ቁልፍ ናት
አክብራት ውደዳት
በክፉ አትያት
ደስታን አትፈጋት
ሰላምህን ስጣት ፍቅርህን ለግሳት
አምላክህ የሰጠህ
    ያተደሴትህ ናት
ላተ ስድብህ መስሎህ
   ሴት  አልካት
አወ ያውም ጀግና ሴት ናት...

ዙፋን ደጀን

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

30 Dec, 11:31


(ለምን እንደ ይሁዳ ? )

ይሄው  ያ...ይሁዳ
የክርስቶስ ጉንጩን
ስሞ እንደሸጠው ሃገር ስላወራው
እኔም ከዚያ ወዲህ
ክህደት እየመሰለኝ ጉንጭ መሳም ፈራው
;
እና በቀደምለት'
ትዝ ይልሽ እንደሆን በዛች' ደማቅ ምሽት
አቅፌሽ አቅፈሽኝ
ከብርዱ ሽውታ፤ ከንፋሱ ሽሽት
ተሟሙቀን
ተጋግለን
ተጠጋግተን
ተጠባብቀን
እርምጃ ሲቀረኝ ሲቀርሽ እርምጃ
ድንገት ተደናብረሽ እንደንቦሳ' ጥጃ
ጉንጭሽን ልትሰጭኝ አንገትሽ ሲሰበር
ለምን እንደይሁዳ
የሚል ቂም አቁሬ ተቀይሜሽ ነበር።
;
ለምን እንደይሁዳ?
ጉንጮችሽን ብቻ አውዝቼ ላርሰው
እስቲ አንዳንድ'ዜ
እንጣበቅ ግለን እንግጠም እንደሰው
አልተፃፈምና
ከንፈር ስሞ እንደጉንጭ አምላክ የሸጠ ሰው።

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

30 Dec, 06:48


ምን አለ

ስለምንህ ብትለመን ተወኝ ስልህ ብትሰማኝ
እኔ እየሸሸሁ አንተ ባትቀርበኝ
ምን አለ ባትወደኝ

ባንተ ልክ አፍቃሪ ባቅም አንደማይኖር
የ'ሱን ህይወት ትቶ ስ'ለኔ የሚኖር
ግና ደሞ ምን ላርግ ልብ አይታዘዝም
ድሮም ሰው ሞኝ ነው ወዳጁን አያውቅም

ሚስጥር አላረኩም ታውቀዋለህ አንተም
ገላ አካላቴን ካንተ ጋር ባደርግም
እንዴትም ብፀልይ እንዴት ብለምንም
አምነህ ተቀበለው በቃ አልወድህም

ምክንያቱም አንተዬ
እኔና ሃገሬ ሞኝ ነን ጅላጅል
ሚገለንን ወደን ሚያድነን ምንጥል!🥺

ምስር🥰
t.me/yemispoems

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29 Dec, 17:35


#አንቺ_ና_እኔ

ከአርዕያም ጥግ ከሰማያት በኩል
ወስደሽ የመለሺኝ ከጨረቃ እኩል

ጨርሰሽ የጣልሺኝ ከሰማይ ወደ መሬት
አዳፍንሽ አካሌን ልቤን ዘግተሺበት

...ከዚያ የምን ኮከብ
ገጥሜ ከራሴ ጋር ጠብ
ያለ አንዳች ሰበብ ያለ አንዳች ምክኒያት
ከሃሳብ ና ዝምታ ጋር ገጥሜ ወዳጅነት

ልንግርሽ ግን ውዴ
ቆርጦሎታል ያልኩት
የመመለስሽን ሃሳብ ክውስጤ ያጠፈዉት

አፈቅርሃለው ባልሺበት አንደበት
  ማለትሽ አይደለም እረስቼሃለው
ይልቅስ ያዘንኩት ቅስሜ እስኪሰበር
የላክሺልኝ ወረቀት ላይ
  ስትይኝ ነው ሰርጌ ላይ እንዳትቀር።

💔
✍️ @YOTORAWIIII

@betagitim
@betagitim

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Dec, 04:19


ባአፍህ አግሰኸኝ
በልቤ አነገስኩህ
በጠቆረው ልብህ በፍቅር አይተኸኝ
ፍቅሬን አሰረከብኩህ
በውሸታም አይንህ በስስት አይተኸኝ
ሳይህ ሳሳውብህ
   ሞልቸም አላይህ
ለስሜት ቀርበኸኝ
ፍቅርህ አሸነፈኝ
የልቤ ሰው ብየ በደማአቁ ጻፍኩህ
አተ የልቤ ጀግና የራሴ ነህ ያልኩህ
እድ ምክር ልስጥህ አድምጠኝ ለዛሬ
   የፍቅሩ መምሬ
የሰጠኸኝ ፍቅር የውሸት ቢሆንም
አስቀምጨህ አለው በልቤ መሀተም
ስሜት ከሰአት ወጭ
     አይቆይ አለመታት
ውሸት ለማምሻ እጅ
      አይሆንም ለንጋት
ማምሻውን አትናፈቅ
እውነት ምረጥና ንጋቷን ተመልከት


        ✍️.........ዙፈን ደጀን

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Dec, 15:32


ይሄ ግጥም

💔
🖤
💛

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Dec, 15:04


በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።

"ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ...ለምሳሌ ሰው ፣ አህያ ወይም የተናኘ ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው" አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ ፍቅረኛው ናት፤ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው?) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች። መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣ የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Dec, 11:59


....አየህ እኔ እንዲህ ነኝ.....
@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Dec, 10:29


❨ካላንቺ ምኖር ያኔ መኖር ሳይመስለኝ
አሁን ግን፣ተደሰትኩኝ
ያጣውሽ ዕለት የጠፋ እኔነቴ ሲገኝ〗

✍️ዳዊት
💔
@betagitim

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Dec, 10:12


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Dec, 08:58



ሳላውቅበት ሳልረዳ
አልገባኝ ወይ አልጠይቅ
  እከፍላለው ትልቅ እዳ
አምላክ ሰቶኝ ልማርበት
እኔ ራሴን እዳውቅበት
ባምላክ ጥበብ እድመራ
እዳልወጣ ከሰው ተራ
መምር ሰጠኝ ባለአደራ
ያመምሩ ጠባአቂየ የሂወት መሰረቴ
ሊመልሰኝ ከስተቴ
እዳልጠፋ እኔ ልጁ
ደረሰልኝ አማላጁ
አቅፎ ያዘኝ በመዳፉ
አስቀመጠኝ ከእቅፉ

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Dec, 08:57


ድፍረት አይሁንና


አንቺ የሳቅሽ ዕለት
አለም ይላል ፍክት
አንቺ የሳቅሽ ጊዜ
ይለቃል አባዜ

እያልኩ እሰብካለሁ ላገኘሁት ፍጡር
የልቤን አውጥቼ ስምሽን ሳሳምር

ቃሉ ሆነና ተገኘች ሄዋን
እንድቶን አጋሩ ከአዳም ጎን
እኔ ሲመስለኝ ግን
አንቺ የመጣሺው ካልታወቀ ፍጡር
ውብም ከተባለ በጣም ከውብ ነገር

ድፍረት አይሁንና ከመላዕክት ጎራ
እነሱን በነካ እጁ አምላክ አንቺን ሰራ

ሲመስለኝ እንደውም
እግዜሩ ሲሰራሽ ብቻውን አይደለም
ያኔ አንቺን ሲያበጅ
ማርያም ተሳትፋለች በጉንጮችሽ ስርጉድ

እናልሽ...........

ፈገግ ያልሽ ለታ ሀሴት ተሰምቶሽ
ገደል የሚፈጥሩት ከመሀል ጉንጭሽ
እነሱን ነው ማርያም የሰራችሽ

#አይፌ

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

26 Dec, 12:09


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

26 Dec, 12:07


       ━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━

              አልናፍቅሽም ወይ

እርግጥ ብትለያኝ ባትሆኚ ከአጠገቤ
ትናንት ብንለያይ ሳትወጪ ከሃሳቤ
ቻው ያልኩሽ እኮ እማ ባፌ ብቻ እኮ ነው
ተለያይተን እንኳን ትናፍቂኛለሽ ምጠራው አንቺን ነው
በሰአት ቅፅበታት በእያንዳንዱ ቦታ
አብረን በሄድንበት የሸኘውሽ ለታ
በተዋወቅንበት ባቀፍሺኝ ያ ሰአት
ባገኘውሽ ጊዜ በሳምሺኝ ቅፅበታት
ልረሳቸው አልቻልኩም እነዛን ደቂቃት
ብቻ ትናንት ተነፋፍቀን አሁን አንቺን ማጣት

አብረን ባንሆን እንካን እኔ ናፍቀሺኛል
የማይደክመው እግሬ ሰፈርሽ ያትታል
አይኔ አማትሮ ደጅ ደጁን ያያል
ሴት ባየው ቁጥር እሳናት እያለ ልቤ ይደነግጣል
እኛ ብንለያይ ፍቅሬ ግን ገርሽቷል
ሰው እንደሞተበት አካሉን አንዳጣ ሃዘኔ በርትቷል
አካላችን ቢለያይ አጃችን ቢላቀቅ
አንቺን እያሰብኩ በፍቅር ስማቅቅ
እና ምን ዋጋ አለው በአካል ተለያይቶ
አንቺን ብቻ እያልኩ በልብ ተቆራኝቶ

አፌ ለካ ዋሽቷል ተያኝ ያልኩሽ ለታ
አሁን እየጠራሽ ጠዋት እና ማታ
ልቤ ግን ልክ ነው ድሮም ያፈቅርሻል
አሁን ተለያይተን እንታረቅ ይላል
ሂይወት ላትገፋ ጭራሽ ላትፋቀቅ
አንቺንስ በድዬ ነፍስ ስጋዬ ላይፀድቅ
እባክሽ ታረቂኝ እኔ ናፍቀሺኛል
ነፍስ ስጋዬ ሁሉ ስምሽን ይጠራል
ልቤ እንኳን ተጣላኝ ስጋዬም በድናል
እሳን ታረቅልን አምጣልን ብለዋል

     እናልሽ የኔ ውድ

እኔ አንቺን በማጣት ስጋዬ ከነፍሴ
ልቤ እረፍት አታ ዝም ብዬ ማልቀሴ
ቁመናሽ ከፊቴ የሳቅሽ ፈገግታ
ደግሞ ስትቆጪ ግልምጫሽ ለአፍታ

      እናልሽ እናቴ 

ይሄን ሁሉ መርሳት እንዳልሆነ ማሰብ
እንዴትስ ይረሳል በአስባቡ ሰበብ
በአልናፍቅሽ ነው ወይ ፀጥታሽ በርትቶ
ትውስታሽን ልከሽ ትዝታሽ አጥቅቶ
እኔው ቁስለኛ ሆኜ ተማራኪ
ሆነሽ ባለድሏ ብስራትን ሰባኪ
በመሃል ምጎዳው ምቆስለው እኔው ነኝ
አንገቴን ደፍቼ እንባዬን አንብቼ አፌ በለጎምታ ይልሻል ታረቂኝ

https://t.me/zzzzaa123
@mikimekonen9


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

26 Dec, 08:48


ተመስገን🙏

✍️ የተክልዬዋ ☦️

@ortopiyaaa
@ortopiyaaa


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Dec, 06:18


ከከበደ ሚካኤል ታሪክ እና ምሳሌ መፅሐፍ የተወሰደ

@ለወዳጆ_ያጋሩ

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Dec, 06:16


እወድሻለሁ ስል ምላሽ ካልሰጠሽኝ
ስኖር በትዝታሽ አንቺ ከረሳሽኝ
እኔ አንቺን ማፍቀሬ ስህተት ከመሰለሽ
ምን አደርገዋለሁ አንዳችም አልልሽ
እኔ እንደወደድኩሽ ውደጂኝም ብዬ

          
ከቶ አላስጨንቅሽ

ውስጤ እየታመመ ልቤም እየደማ
ባዝንም ልመርቅሽ አንዴ ስሚኝማ
ልክ እንደ ሮሚዮ   ከልቡ አፍቃሪ
እንደ በዛብህም ስላንቺ ነዋሪ
ህይወት የሆነ ባል ያድልሽ ፈጣሪ
    
           ቤትሽ ደስታ ይሁን በፍቅር ይሞላ
           የወየበው መልክሽ ተመችቶት ይቅላ
የይስሐቅን አይነት ብሩክ ልጅ ውለጂ
የማቱሳላ'ን እድሜ ከጤና'ጋ ውሰጂ

              ብዬ አልመርቅሽም😡

ማነሽና አንቺ እንዲ ምመርቅሽ
ይሄን ሁሉ ደስታ ይስጥሽ ብዬ ምልሽ
          ይልቅ ስሚኝማ
ውስጤን እንዳደማሽ ልቤን እንዳቆሰልሽ
ከኔ የባሰውን ጅል አፍቃሪ ይስጥሽ።😡😡😡
እኔማ የዋህ ነኝ ሌላ አንዳች አልልሽ


       @henila31

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Dec, 05:45


ተይ ስጭኝ😍

እየዃት በአይኖቼ
አቀፍኳት ከጎኔ አስጠግቼ
ተገለጠ ያ ውብ ከንፈሯ
ጭልምት ዓለምን ሊያበራ

ደግሞ ሲያምርባት....☺️


ቡዝዝ ፍዝዝ ድንግዝ
ከዛ ሳገኛት የሳቅ መቅረዝ
ተደምሮ ሳቋ
በዛ ውብ ፊቷ
ሌት ያበራል እንደፋኖስ
አምሮ ያነቃል እንደ ክፉ ሱስ

እያልኩ እገጥማለሁ እኔ ያንቺ አፍቃሪ
ትሰጭኝ እንደው እያልኩ በተስፋ ኗሪ
     
     ተይ ስጭኝ
     ተይ ስጭኝ

እያልኩ ለምናለሁ
ልብሽን ልቤ ላይ ፅፌ አኑሬያለሁ
ምናልባት አልሰጥ ያልሽ እንደሁ
አልኖርም በዚህ ዓለም እሞትብሻለሁ
እያልኩ እገጥማለሁ እኔ ያንቺ ወዳጅ
ለእናቲቱ ማርያም እጠናለሁ ደጅ

     ተይ ስጭኝ ☺️
      ተይ ስጭኝ 😔


Ayfe 15/4/2017


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Dec, 05:37


ትነግረኝ እንደሆን በጊዜ ንገረኝ
ኋላ ዘግይተህ ከሌላ እንዳታየኝ😁😁
t.me/yemispoems
by ምስር🥰

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

24 Dec, 03:40


ጥያቄን መልሺልኝ

በሞትኩት አንቺ ሴት
በድቅድቅ ጨለማ ምን ይሉታል መብራት፣

እ...ምን ይሉታል
ወፎቹ  ስምሽን ጠርተው ሰውን መቀስቀስ፣
እኔ እንደው ካየውሽ ብኃላ እንቅልፍ ክአይኔም አይደርስ፣
አንቺ ሴት ንገሪኝ...
በየትኛው ድዌ በየትኛው ጋኔል
መላአክ ሁነሽ ነው ወይንስ ሳጥናኤል፣
ንገሪኝ በሞቴ
ዳዊት በሚደግሙት አባትሽ ይዤሻለው
ጽድቅ ልስራ ሃጥያት ...
ሲኦል ወይስ ገነት የት አገኝሻለው።

✍️ዳዊት

@betagitim
@betagitim


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

24 Dec, 03:40


ማግባቷን ክዳለሁ
             :
ዳሯት ፍቅረኛየን
ፍቅረኛየን ዳሯት
እኔም አቅም ሳጣ
አጨብጭቤ ላኳት
     :
እናቷ መረቁ እንትፍ አሉ አባት
እኔም በመሀል ቤት አልኩ ግራ እንደመጋባት
ተገርሜ እያየሁ እናቷ ለሌላው አሳልፋ ስትድራት
አባቷ በደስታ ቆመው ሲመርቋት
ውለዱ ክበዱ ምድርንም ውረሷት እያሉ ሲያወርሷት
ለሀብታም ሰው ድረው ሀብቱንም እንድትወርስ
በአሽሙር ሲነግሯት እሷ መቼ ገብቷት
        :
ቀልቧ ያለው ከእኔው ልቧም ያለው ከእኔው
ሙሽራው ያቀፈው በድን አካላቷን
ስንተያይ እኛ ያስታውቃል መልኳ በውስጧ ማንባቷን
አዝኜ ስታየኝ አዝና እኮ ነው ማያት
እንዲህ ያለ ልብ ከየት አገኘሽ ስላት
ነው አለችኝ ከአንተው ያንተው ፍልቃቂ
ስትስቅ ኑርልን የህይወቴ አድማቂ
በአንተ ደስታ ነው ምኖር ስቀህ ሳይህ ነቂ
ከሌለህማ አንተ ሳትስቅ እንኳ ባይህ
መሞቴን አስታውስ ነገርኩህ ወየሁልህ
      :
የውሸትም ቢሆን ሳቅ
ባንተ ሳቅ ስለሆን ሚሞላው የኔ ሀቅ
             :
ማለቷን አስታወስኩ  አግብታም እያየሁ
እያየሁ ክዳለሁ ወንድሟ ባረገኝ እያልኩ እመኛለሁ
      ማግባቷን ክዳለሁ
                                            :
                                            :
                                    ✍️በቢኒ-መንግሥቱ


@ye_wsit_simet


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

23 Dec, 18:18


@topazionnn
@topazionnn
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

23 Dec, 13:07


ነይ እንቀደስ

እኔና አንቺ ማለት
የዓለም መንገደኛ ብንሆንም ደካማ
አይተወን ጌታችን ለሱም ባንስማማ
ብንኳትንም በምድር ብንል ወጣ ገባ
ዛሬስ እንመለስ ከመቅደሱ እንግባ

   ነይ እንቀደስ ነጩን ልብስ እንልበስ
አለን እንበለው ሳትሞት ረቂቋ ነብስ

አያውረን ስጋ አይተብትበን ምቾት
ከእርሱ ዘንድ ብቻ ነው እውነተኛው ህይወት
ዓለም አታላይ ናት እንዳትወስደን ቀድማ
ከአውደምህረቱ ስር ወንጌሉን እንስማ

ነይ እንቀደስ ነጩን ልብስ እንልበስ
አለን እንበለው ሳትሞት ረቂቋ ነብስ

ፍቅር ማለት ጌታ ፍቅር ማለት እውነት
በፍቃድ በህጉ እንዲኖረን ጥምረት
የዓለምን ስርዓት እንተው እንዘንጋ
በፍቃዱ ያጣምረን እንሂድ እርሱ ጋ

ነይ እንቀደስ ነጩን ልብስ እንልበስ
አለን እንበለው ሳትሞት ረቂቋ ነብስ

እንታጭ ለትዳር ለተክሊሉ ሞገስ
እስኪያደርሰን ለዚያ ምግባር እንላበስ
ሁለትነት ቀርቶ አንድ እስክንሆን ድረስ
በቤቱ እየሄድን ዘውትር እንቀደስ
            ✍️የተክልዬዋ
@ortopiyaaa 
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa

🥰አዳሞች ለሄዋኖቻቹ ሼር አድርጉ🥰

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

23 Dec, 05:44


አይወሳ😑

ጥላቻ ቋጥኝ ነው
ልብ ላይ ተጭኖ ሰላም የሚነሣ
ዘጠኝ ነብስ ያለው
ጠዋት የቀበርከው ማታ የሚነሳ
ማቃጠል ነው አቦ
በነፋስ ተወስዶ ዳግም እንዳይወሳ
አይደለም መኖሩ
ሀውልት አይቁምለት መሞቱም ይረሳ::

By 彡 Řå§ ÅBĮ 彡♋️

@yemispoems

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

22 Dec, 16:03


ገጣሚ መቅደስ ገብረማርያም

💞💞💞

She is so cool

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Dec, 16:49


😔 የሆነ ቀን 😒

ሁለት ገፀባህርይ : የአምላክ ጥማሪ
በአንድ ማርሽ : ጀዋሪ ቀያሪ
አንድ ቀን,በቅፅበተ ሰዓት
ይፈጠራል ልዩነት
ነፍስ ወደ ላይ : ወደ ሰማይ
ከተቀደሰች ፈጣሪዎን ልታይ
ከልሆነም ወደ ማይቀረው ስቃይ
ሀይ ባይ ይባባላሉ ።

ስጋም ወደ ታች : ወደ መነሸዋ
ምንም ሳትይዝ በባዶዋ
በእድሜ ልክ እንደረገጠቻት
ተመልሳ እንደ ማትደርስባት
አቤት መፀየፍ
ላትኖር እልፍ ኣላፍ
የሆነ ቀን : በሆነ ቦታ
በድንገተ ስቅታ😌
ነፍስ ወደ መጣበት ከፍታ
ስጋም ወደ ተነሳበት ዝቅታ
በአንድ ስዕብና እንደ ተጠሩ
በሁለት ስም ይከፈላሉ
ሙት አስክሬን ይባላሉ
መች ? የሆነ ቀን 👌

ቀን ዉለን ተሳስቀን
ትልቅ ተስፋ ሰንቀን
ነገ ህያጅ መሆናችንን
ማን 😮 በነገረን
በሚሆነው ነገር :ብዙ መገረም
ስጋን አልፎ : ነፍስን ማሳመም
ተለዩኝ እረሱኝ
እንደ ሙት ቆጠሩኝ
ብሎ ሰውን መገመት
አያስጥል ከገሃነም እሳት🔥
እንኳን ሰው : የእራስ አካል
ስጋና - ነፍስም: የሚከዳዱበት ቀን ይመጣል
ሁሉን እርሳውና : ውልህን አድስ
የቅድስናን ሱፍህን ልበስ
ወደ አምሳልህ ተመለስ
🙏ተቀደስ

buka

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Dec, 16:48


ነገር ሲገለበጥ
አንችን ያጣው እለት
አለም ተ ደባልቆ አንድ ሆነ ሰው ሁሉ
እነዚያ ሚሊዮኖች በጣት ተቆጠሩ
አንድ ሆኑ አመታት ቢሄዱም አይሄዱም
ለሌላው ቢቆጠር ለኔ አይቆጠርም

አንቺን ያጣው እለት
እባብ በእግሩ ሄደ
በቅሎም ልጅ ወለደ
በግ አድኖ በላ
ያለመደበትን ተደበቀ ተኩላ

አንቺን ያጣው እለት
ግመል ብቻ ሳይሆን ግመሎች አለፉ በመርፌ ቀዳዳ
ያ ፈሪው ዶሮ እንኳን ባ'ቅሙ ቀንድ አወጣ
ነይና መልሽው የአይምሮዬን ጤና
ድሮ እንደነበርኩት ልሁንበት ደህና😔

by ምስር

@t.me/yemispoems

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Dec, 10:20


ይሄ ግጥም

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Dec, 12:13


የት ይሆን
መግቢያችን??

የሚደንቅ ነገር የሚገርም ታምር
ምድርን ሲዘረጋ የሰጠን ከብር
አንድ ውድእ ናቱን መዳኛ አረጎ ሰጦን
ስጋውን በመብል መጠጥ አርጎ ደሙን
እምነትና ተሰፋ ባድ አርጎ አደለን
ባህልና ወጉን እምነቱን አክብረን
የሰው ልጅ ስርአት ሁሉንም ጠብቀን
መገዱን እዳስት መምህር አደለን
አቤት ያዳም ልጆች ወዮታ አለብን
ባልተፈቀደልን እርቃናችን ሄድን
አረ ሴቶች ስሙኝ ወዮታ አለብን
የደረሰች እለት ያች የፍርድ ቀን
የወድ ልብስ መልበስ ሆነና ስራችን
ቻፕስቲክ ሊፒስቲክ ሆኖ ውበታችን
በሰው ሰራሽ ጥፍር በሰው ሰራሽ ቀለም
   ሆኖመዎቢያችን
ይህ አልበቃአለና ሄድነ እርቃናችን
አረ ሴቶች ስሙኝ ወዮታ አለብን
የደረሰች እለት ያች የፍርድ ቀን
ወዶችም እደሴት አብደዎል መሰለኝ
ጀሮጌጡን አርገው ሲዎቡ አየሁኝ
ጸጉራቸው ሹርባ ተሰርተው እደሴት
ዘመናዊነይ ባይ ሁነው ባለ እውቀት
መብላቸውም ቅጠል ሲሻና ሲጋራ
ሞት አይቀርምና ሲወስደን በተራ
የት ይሆን መግቢያችን ያኔ ስንጠራ
ቀሚስ ካባ መልበስ ቀረና ባህሉ
አባቶችን ማክበር ደከማን መደገፍ
   ቀረና ባህሉ
ሸባው አሮጊቷ ብለን እጠራለን
እኛ ዘመናዊ ባለ እውቀት ሁነን
ያኔ ስንጠራ ሲደርስ ስአቱ
ምን ይሆን መልሳችን ያግዜነው ሞቱ
ስንጠየቅ ያኔ ቆመን ካምላክ ፊት
የሰራነው ስራ ሳለን በሂወት
የትኛው ምግባር ነው ሚያወጣን ከሰአት
ከሞትኩኝ በኋላ ብልም ወየወየ
ማረኝ ብል ጌታየ
እሚያወጣኝ ጠፋ
ምግባረ ከቱ ነውና ስራየ
ካሁኑ እንጠቀቅ ፍርድ ቀን ሳትመጣ
የዲያብሎስ እራት ሳንሆን ባላጣ
ስሙኝ ወይዛዝሮች ስሙኝ ወጣቶች
ለዲያብሎስ እራት አንሁን ለሱሟች
ካሁኑ እንጠቀቅ እንግባ ንስሀ
በዛች በፍርድ ቀን
ከተመረጠችው እዲያጠጣን ውሀ

#ገጣሚ_ዙፋን_ደጀን

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Dec, 10:42


🤔
ግራ መጋባቴ እንደዉ ግራ ገብቶኝ፤
ስቋጥር ስፈታ እጅጉን አሳስቦኝ፤

ባስብ ባሰላስል ከልቤ አጣሀት፤
ግራ የገባኝን ግራ ገብቶኝ ተዉኩት።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Dec, 09:05


ገጣሚ _Mearey

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Dec, 08:49


ገጣሚ ሐይማኖት / hayma

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Dec, 17:52


ይሄ ግጥም

💞

💘

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Dec, 17:06


ቀጥረሽኝ....ፈላስፋ አደረግሽኝ


ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡

ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡

እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡

እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡

እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡

እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!

     ✍️✍️✍️በላይ በቀለ ወያ


Any comment @YOTORAWIII

Share @betagitim
Join @betagitim

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

03 Dec, 18:13


ለባለ ጠመኔው

የትውልድ አሻራ የሀገር መሠረት
ዘመን አሻጋሪ የህመም መድሀኒት
የነገ አለኝታ የመበልፀግ ሀውልት
እውቀትን ደራቢ የመኖር ትሩፋት
   የስራውን እሩብ ላልተነገረለት
ለሀገር መስራቹ አንዴ ልቀኝለት

   "ባለመኖር ኖሮ መኖርን የሰጠ
ሀገር ለማስከበር ክብሩን የረገጠ
እውቀትን ሊገዛ ጉልበቱን የሸጠ"

"በረሀ ላይ ወርዶ
                በውሀ ጥም ሲቀጣ
ከሰው በተለየ
                   ነጭ ላብ ለጠጣ"

"የሚበላ ጠፍቶ ራብ ሲደቁሰው
    የጠመኔ ብናኝ ባፉ ለጎረሰው
ሌላው ነገር ቢቀር
       እስኪ አንዴ እናስታውሰው"

"ብዙ ኪሎ ሜትር
            በጭኝጫ ላይ ሄዶ
በበረሃው ነዳድ
                  በረሀ ላይ ነዶ
በውርጭ በውንሽፍር
                   ፊቱ ተጨማዶ
ሀገርን ሲያነሳ
           ከሰው ክብር ወርዶ

ገና በልጅነት
          ከፊቱ ሲጠፋ የልጅነት ወዙ
ቁራሽ እንጀራ እና
ስቃይ መከራ ነው የዚ ሰው ደሞዙ

ለዚህ ብርቱ ጀግና የሀገር ባላደራ
    ታሪክን አስታውሶ ታሪክን ለሰራ
      ሀገር ለገነባ ትውልድን ላኮራ
ሌላው ነገር ቢቀር
like እንለግሰው እንስጠው አሻራ

ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Dec, 15:52


Male Out of Stadium Athlete of the Year Winner 🏆

🇪🇹's Tamirat Tola is your Male Out of Stadium Athlete of the Year 🤩

Via ፦ #AthleticsAwards

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Dec, 15:38


ኢትዮጵያዊነት በ፭ አምዶች የታነጸ የመኖሪያ ዕልፍኝ ነው።

፩ ጥልቅ እና ሠፊ ዕውቀት።
፪ መዛል የሌለበት ትጋት።
፫ በትዕግሥት የታሸ ጀግንነት።
፬ እርኩሠት የሌለበት ቅድሥና።
፭ ግብዝነት የሌለበት ምስጢራዊ ህይወት ።

ኢትዮጵያዊነት ይህ ነውና አናርክሰው።

ምንጭ፦ዝጐራ

    ኢትዮጵያዊነት ወደፊት
ብሔርተኝነት ወደ ኋላ


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Dec, 15:36


በእውቀቱ ስዩም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Dec, 15:35


አላችሁ እንዴ ወገን............🔥???

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Dec, 11:02


እስቲ እዩትና ሀሳባችሁን ጣል ጣል አድርጉልን..........🤝

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Dec, 10:54


#ቶሎ_ለመሞት_ስል

ቶሎ ለመሞት ስል ሲጋራ ጀምርኩ፣
ከኪሴ አውጥቼ ክብሪቱን ለኮስኩ፣
ግና ምን ያደርጋል ሞት ሳልሞት አበድኩ።

     [[[[[#ገጣሚ_ሄኖክ_ፀጋዬ]]]]

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

30 Nov, 05:50


#፳፩

እመቤቴ ማርያም ንጉሡን ወለደች፣
የመለኮት እሳት ወሆዷ አዘለች፣
መድኃኒት ነውና በሆዷ ያረፈው፣
የዓለምን ኃጥአት በደሙ ጠረገው።

✍️ @Henilogy

መላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግስ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን🙏🙏

መልካም በዓል

ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

30 Nov, 04:43


"ማር" በምድርም "ያም" በሰማይ
.
.
.
ሀዘኔ በርትቶ፣
ስትጨነቅ ነፍሴ፣
ፈገግታዬ ጠፍቶ፣
ሲታወወክ መንፈሴ፣
ወድቄ ከፊትሽ፣
አድኚኝ እላለሁ፣
አልቅሼ ከደጅሽ፣
ከሀዘኔ እወጣለሁ፣
ማንስ ብዬ ልጥራዉ?
እናቴ ስምሽን፣
በምንስ ልግለፀዉ?
ጥዑም መዓዛሽን፣
ማር በምድር፣
ያም በሰማይ፣
የሥላሴን ክብር፣
አጉልታ ምታሳይ፣
እሙ ለፀሐይ ጽድቅ፣
የእግዚአብሔር ከተማ፣
ጥምን የምታርቅ፣
ፍቅር ለተጠማ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@topazionnn
@topazionnn

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29 Nov, 10:43


ይህ ሰው ዋሬን ቡፌት ይባላል የካፒታሊስቶች ቁንጮ የዓለማችን ቁጥር 1 በቢሊየን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ባለሃብት ነው። ይህ ሰው አሁን ላይ እድሜው እየገፋ ሲሄድ ሞት እንደቀረበው አውቀ። እናም "ራቁቴን ተወለድኩ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ወሰደ። (ኢዮብ 1:21) የሚለው የመጽሐፍ ቃል ትዝ አለው በገዛ ፈቃዱ ወሰነ የሃብቱን 99.5 ከመቶ ለበጎ አድራጎት ለማዋል ቃል ገባ ይህም 150 ቢሊየን ዶላር ገደማ ማለት ነው። ሐብቴ ለልጆቼ ለዘመዶቼ ሳይሆን ለወደቁት እና ለተራቡት ይሁንልኝ አለ መኖር ማለት ገንዘብ መሰብሰብ በድሎት መኖር እና መሞት ብቻ አለመሆኑን ገብቶታል መኖር ትርጉሙ መስጠት መሆኑ ገብቶታል ዋሬን ቡፌት ይህን ሁሉ የወሰነው በጣም አንባቢ እና የመጽሐፍ ወዳጅ ስለሆነ ነበር በቀን ውስጥም ብዙ ሰዓቱን በንባብ የሚያሳልፍ ባለጠጋ ነበር "የንባብ ኃይልን "እዚህ ጋር ታዩታላችሁ በሉ በቀን 1 ሰዓት ለንባባችሁ ስጡ ለመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ሲጨንቃችሁ ሲከፋችሁ የሕይወትን ቃል ታገኛላችሁ እና አንብቡ ኑሮንስ ለመሻሻል ለቢዝነሳችሁም ለስራችሁ ለእድገታችሁ ቢሆን አንብቡ እናንብ በጎውን እናስብ መልካም ቀን፡፡

Via ፦ Getamesay Haile

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29 Nov, 07:57


ገጣሚ(አቅራቢ) ረድኤት ተረፈ
👉 ዘፈኔ ሆንክልኝ😁🤣😂
Join us
👇👇👇👇👇
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29 Nov, 07:16


ሰላምን ፈለጋ
🦗🦗🦗🦗🦗🦗🦗
በሰወች መካከል ትልቅ ክፍተት መጣ
ትንሽ ተወድሶ ትልቅ ክብር አጣ
አገሬ ኢትዮጵያ ሰላም ላንች ይሁን
ፈቅር ይለግሰን ቸሩ አምላካችን
መሪና ተመሪ መገዱ ጠፍቷቸው
ተመሪ አወቀና መገድ ሊነግራቸው
መሪ አልሰማም አለ መች ተቀበላቸው
አተ መሪ ሁነህ ሰላምን ካሳጣህ
በምን ቀመር ሆኖ አተን ልከትልህ
የወድማችን ደም አተን እየጠጣህ
እናት ደስታን ስትል ሀዘን አሸክመህ
በልጆቿ ሀዘን እናት ደም አልቀሳ
በየትኛው መገድ ላተ እጅ ልሳ
አዉቃለው ታውቃለህ መገዱ መች ጠፋህ
አልገባኝም እኔ...
እናት መግደሉ ነው ?
እምነት ማጥፋቱ ነው?
ወይስ አገር መሸጥ..?
ነው ያተ ስልጣንህ?
አልገባኝም እኔ በምን ልጠይቅህ
ተምሪያለው ብለህ ማዕረግ ተሰጠሀል
እመራለው ብለህ ዳኝነት ይዘሀል
ግን እዴት መረሀው እስኪ ልጠይቅህ
ደምን እያፈሰስክ
እናት እያስለቅስክ
ሰላም ስጠን ሲሉህ ጀግናን እየረሸክ
ይህ ነው ሀላፊነት በምን ልጠይቅህ
ሰላምን ፍለጋ ቢመጣ ትልቁ ወድሜ
እረሽን እሚባል ትንሹ ወድሜ
በምን መልኩ ይሆን እርቁ የሚሆነው
ታናሽና ታላቅ እያጋደልክ ነው
ይህ ነዉ ወይ መሪነት?
እስኪ ልጠይቅህ
ተመሪነህ ብለህ አትናቀኝ እባክህ
ለህዝቤ ነጻነት መገዱን ልገርህ
ነፍጠኛነው ብለህ ወድም ከማሰረሸን
አዴ አድምጠኝና ሰላም ይሰፈንልን....

#ገጣሚ_ዙፋን

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Nov, 16:37


English best and powerful quote

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Nov, 14:55


@topazionnn
@topazionnn
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Nov, 11:35


እስቲ እናንብብ................🙏

የሳኡዲ ዜጋ የሆነው ዶክተር ሰኢድ አልቃህጣኒ ይባላል
ለአስቸኳይ ቀዶ ጥገና ወደ ሆስፒታል እንዲመጣ ጥሪ ይደረግለታል እሱም እየተቻኮለ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል ነገር ግን የተወሰኑ ደቂቃዎች ዘግይቶ ስለነበር ቀዶ ጥገና የሚያደርገው ልጅ አባት ዶክተሩ ላይ በሃይለኛው እየጮሀ ይሰድበው ጀመር " ልጅህ ቢሆን የታመመው አታረፍድም ነበር " እያለ ይጮህበታል
ዶክተሩም ስድብ እና ጩሀቱን ተቋቁሞ ምንም ሳይተነፍስ ቀዶ ጥገና ክፍል ይገባል ለረጅም ሰአት በተደረገ ኦፕሬሽን ታማሚውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ ይወጣል የታማሚው አባትም ይደሰታል ነገር ግን ዶክተሩ ቀዶ ጥገናውን ከጨረሰ በኋላ እየተቻኮለ ወደቤቱ ይመለሳል በእዚህ ጊዜ አብረውት የነበሩት የዶክተሩ ረዳቶች ለታማሚው አባት " ዶክተሩ ልጁ ሙቶበት የልጁን አስክሬን ቤት አስቀምጦ ነው ያንተን ልጅ ለማዳን የመጣው " ይሉታል 💔 አንዳንዴ ሰዎች በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ሳናውቅ ለመፍረድ አንቸኩል .

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Nov, 10:36


😴😴አትሳቅ😴😴
አወ አትሳቅ
ስትስቅ ልቤ ከሁለት መሰጠቅ
ስትስቅ ነብሴ በሀሴት ስትፈነድቅ
ስትስቅ በፍቅርህ ስረታ
ከመገዱ ቁሜ ልሄድ ሳመነታ
አተ ግን ............
ስቀህ ታስቅና ስትሄድ  ተራምደህ
ዳስታን እያለምኩኝ በዛች ጥሩ ሳቅህ
አተን ስመለከት ቁሜ ቀረውልህ
እናም ባትስቅ ተመኘው
ሳቅህን እያሰብኩ እኔ እዴት ልቻለው
አወ አትሳቅ...........
ሳቅህ ህመም ሆነኝ
ሳቅህ  እዳልሄድ አረገኝ
እናም አትሳቅ
ሳቆህን እያነው ልቤ ከሚሰረቅ

#ገጣሚ_ዙፋን

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Nov, 07:22


እስቲ እናንብብ..........🤭😳😳🤭

ዶክተር መሞቷን በማረጋገጥ መቃብር ውስጥ ገብታ ስርዓተ ቀብር ሊፈፀም ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በእህቷ ምክንያት ለተጨማሪ 47 ዓመት በህይወት የኖረችው ሴት......

በ 1915 በሳውዝ ካሎሪና Essie Dunbar የተባለች ሴት ሰዎች እንደመሰላቸው በ Epilepsy ሕመሟ ምክንያት በደረሰባት አደጋ ሕየወቷ ያልፋል። መሞቷንም ለማረጋገጥ Dr briggs የተባሉ ግለሰብ በቦታው ተገኝተው ከመረመሯት በኋላ There is no signs of life not breathing, nor pulse. በማለት መሞቷን ያረጋግጣሉ። በቀጣዩ ቀን በተደረገው የቀብር ስነስርዓት መገባደጃ ላይ የሬሳ ሳጥኑ ላይ አፈር እየተመለሰ ሳለ ለቀብሩ አርፍዳ የደረሰችው የሟች እህት እህቴን ለመጨረሻ ጊዜ በዓይኔ ሳላያት አትቀብሯትም ብላ አጥብቃ በመለመኗ የሬሳ ሳጥኑ እንደገና ወጥቶ ሲከፈት Essie Dunbar ቀና ብላ እህቷን በፈገግታ ተመለከተቻት። በዚህ ጊዜ ሶስት ቀብር አስፈጻሚዎች በድንጋጤ የቀብር ጉድጓድ ውስጥ የወደቁ ሲሆን ብዙዎች የሙት መንፈስ መስላቸው ከመቃብር ቦታው ፈርጥጠው ሮጠዋል። የእህቷ አጥብቆ መለመን ከተቆፈረላት ጉድጓድ ባያስወጣት ኖሮ Essie Dunbar በተቀበረችበት ትነቃ ነበር ወይስ የመንቃቷ ምክንያት እህቷ ናት???

Essie Dunbar ከመቃብር ከወጣች ቡኃላ ለ ተጨማሪ 47 አመታት በህይወት ኖራለች 🤯🤯

Via ፦ Facebook

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Nov, 04:48


--------

ሁሉም ታጨለኝ ለአዲስ ቀን ህመም ፣ አዲስ ፈተና
መፅናኛ እቺን ታህል አጣሁ ለመኖር ብዬ ደግሞ እንደገና!
ህይወት የዜማ ክሬን በላችው ፣ በጣጠሰችው
ለዓለም ሚያለቅሰውን አንዱን በገና!
ልጅ ይመስል አንሰፈሰፉኝ....
አብረውኝ ሚኮራመቱ ቀሪ አመታቶች
ሀጢያት ይመስል በፀፀት በሉኝ...
እነኛ መኖር አለመቻሎች!
:
እኔ...
አቅም ያጣ ሀዘንተኛውን ንስር መሰልኩ...
ጥንት ኮከብ በሚሸከም ገላዬ
ዛሬ...የራሴ ላብ ከብዶኝ ወደኩ!
በእውር የሌሊት ወፍ ክንፍ ቀናሁ 
ቢራቢሮ በሸፈነው የህዳር ሰማይ
ቦርቆ መብረር ናፍቆኝ አለቀስኩ!
:
በምን ቢጎተት ይሰበሰባል?
ሰው የትጋር ቢተኛ....
ሁሉ ካለፈ ኋላ ከእንቅልፉ ይነቃል?
በየት መንገድ ቢኬድ ነው ከዚህ ሚጠፋው
የት ጋር ቢቆም ነው ሰው የማይከፋው?

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Nov, 08:41


(ሞት ያወሳሳል)

አጀብ ባይባልለት
ባይጨፈር በስራው ትቢያ ባይነሳ
እስቲ አንዳንድ'ዜ
የሞትም ደግነት በጥቂት ይወሳ
;
መኖር ክፉ
መስፈርት አበጅቶ በሃብት በዝና
ከፋፍሎ ከፋፍሎ አራራቀንና
ሰው ከቤተ ዘመዱ
ተነጥሎ ወዲያ መኖር እየናጠው
ይገፋል አለሙን
የብቸኝነቱ መንቆር እየላጠው
;
ሞት ቁምነገረኛው
የመኖርን ክፋት ሰብሮ፣ ሰበሰበ ከየመንገድ
የሩቅን ሰው ባንድ' አሰረ፣ ከስጋው ጋር ከራስ ዘመድ

መኖር ክፉ አራርቆ ሲያረሳሳ
መሞት ደጉ
ደገሰና በሙሾ ስም አወሳሳ


ሲያሰባስብ
የሩቅን ሰው ከየቅል በር
የውነት' የውነት'
ሞት ከመኖር ደግ ነበር።


(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 08:06


@semetnbegtm
         ኦ ሚካኤል...
ፍፁም ትሁት ቢሆን ተሠጠው ልዕልና
ተርበው ለጠሩት የሚመግብ መና
ሞግዚት ነው በዓለም ለሌላቸው ወላጅ፣
ለታመኑት አባት ጠላትን አሳዳጅ
..
ነገድ ብሔር አይለይ ሲቀበል አደራ
ልጆች አሳዳጊ ከፊት እየመራ
ቦታ አይወስነው ጊዜ አይወስነው
                ልጆቹን ሲጠብቅ፣
ስሙ ግርማ ያለው ጠላት የሚያስጨንቅ
የማይሰለች አባት ፍቅሩ የሚጨምር
የሞትን ደብዳቤ በህይወት የሚቀይር
..
ልዑል እምልዑላን ስልጣኑ ከፍ ያለ
ሠልፉን እየመራ ዘንዶውን የጣለ
እሱ ያልረዳው ሠው አይገኝ በዓለሙ
ለአህዛብ አደለም ክርስቲያኖች ስሙ
..
ዓለም ጥበበኛ ያውቅበታል ሴራ
ቆላ ደጋ ብሎ ቢደግስ መከራ
ስጋችሁ አይራድ ፍፁም አትደንግጡ
ሠልፋችሁን ይምራ ልክ እንደ አፎምያ
                   ለሚካኤል ስጡ፣
የዓለምን ሴራ የገንዘብን ድግስ 
                  በእምነት ብለጡ፣
የሚካኤል ልጆች አትፍሩ ቀኑ
                      ቢጨልምም
እንኳን የአዳም ዘር ዘንዶው አልቻለውም!!

        ገጣሚ_ ኤርሚ ግርማ

       @semetnbegtm
       @semetnbegtm

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 06:13


መልካም በዓል🙏
መንፈሳዊ ግጥም


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 06:10


በዓሉን ለምታከብሩ ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረበዓል በሰለም አደረሳቹ አደረሰን ❤️ መልካም በዓል

ቻናላችን በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የበረከት እንዲሆንላቹ ከልብ ይመኛል መልካም በዓል - 🙏🙏

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 05:06


#የኛ_ታሪክ_ግጥም

#መስፍን_ወንድወሰን

ግጥም እንዴት ልግጠም 😏

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 04:22


ቅዱስ ሚካኤል
.
.
.
የአምላክ ባለሟል የአፎምያ ረዳት፤
ሶስናን ያዳነ ከአይሁድ ረበናት፤

ህዝበ እስራኤልን በደመና ጋርዶ፤
እርሱ ያሻገረ እየመራ ወስዶ፤

የባህራን ሞቱን በህይወት የሻረ፤
ለማኑሄ ደስታን ብስራት የነገረ፤

የምስኪናን አባት የድኩማን ምሽግ፤
በኑኅ ሰማይ ላይ ጸሎት የሚያሳርግ፤

ምሕረት የሚለምን የዋህ ባለግርማ፤
ለአምላኩ ምስጋና ድምፁን የሚያሰማ፤

የምስጋና ድምፁን ቃሉን ላደመጡ፤
ከአምላክ ያስታርቃል ደጃፉን ሲረግጡ።
.......................................................
እንኳን አደረሳችሁ🥰🙏🙏🙏
ዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 19:16


የሳቅሽን አቦል ድምቀት
ለዘመናት ሞቄ ሞቄ
እንድታለቅሽ አልፈልግም
ስለ እምባሽ መች አውቄ
የምትስቂው ሙሉ ብርሃን
የተስፋ ቃል ፍንጣቂ
እምባሽ ግና ጽልመት ወሳጅ
ሞት እና ህይወት አስታራቂ
ብደምቅበት በዓለም ሁሉ
ሳቅሽን በገፍ እየቀዳው
ስታለቅሺ ባይ ለአንዴ
እምባሽ ሊሆን
አይኔን ዳዳው

ለዘመናት ያልተሻረ
ህመም ስቃይ ነበረብኝ
ጠብ አድርጎ ቁስሌን ሻረው
ከሳቅ እምባሽ በለጠብኝ

ለዘላለም ብጸልይም
ከሀዘን ችግር እንዳትገቢ
ግና ለቅሶሽ ይናፍቃል
ያምርብሻል ስታነቢ 💧

#mikiyas_feyisa
@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 06:02


#ቀን_መሸኛ_ቅኔ
#መስፍን_ወንድወሰን

ድንቅ ግጥም.....🔥🔥

ለወዳጆ ያጋሩ

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 05:53


አለ  ማፍቀር

ራቅ ብለው ፤በአይን እያዩ
ስሜት በግልፅ፤ ሳያሳዩ
ከተወዳጁ ፤እያወጉ
ቀርቦ ጠረን ፤እየማጉ
በመከተል፤ እንደ ጥላ
በመገስገስ ፤ከእሱ ሗላ
ቃል እያጡ፤ ለመናገር
በዛ ሰው ፊት ፤መደናገር
በሙሉ ቀልብ ፤እያመኑ
የቅርብ እሩቅ ፤እየሆኑ
ሳይገለፅ፤ የልብ እውነት
የሰው ደስታን፤ ላለማጥፋት
ለራስ የከጀሉት ፤ሌላ እቅፍ እያዩት
በዝምታ ፤ታጥረው
ምኞትን፤ ተነጥቀው
እንዲህም፤ አለ ማፍቀር
....
ተስፋ በሌለበት፤ ተስፋ እየቀጠሉ
ለፍቅር እየኖሩ ፤እራስን እየጣሉ
ላልተሰጠ ነገር ፤ዋጋ እየከፈሉ
ማማረርን ይዘው፤ ከአምላክ ከተጣሉ
ሙሉነትን ትቶ ፤ባዶ ሆኖ ከመጥፋት
ከምድር ከሰማዩ ፤ጠልቶ ከመለየት
ለነፃዋ ህይወት ፤ደስታን ማሰንበቻ
ማጣፈጫው ቅመም ፤አለማፍቀር ብቻ።

✍️የተክልዬዋ
#repost

@semetnbegtm
@semetnbegtm

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Nov, 15:29


ስሙኝማ…
ልጅነትን ስሸኝ በሀሳብ አድጌ
ከብቸኝነት ጋር ልላቀቅ ፈልጌ

ትዳር ለመወጠን ካሰብኩኝ በኋላ
ያየሁት እሸት ሁል ሆነ  'ማይበላ

          የሆነ ቀን ለታ
አንድ አለኸኝ ብላ
                  ቃል የገባች እንስት
አንድ አለሽኝ ብየ
                  ቃል የሰጠኋት ሴት
ከብዙ ሁካታ ከጨዋታ መሀል
ከእኔ አስበልጠህ
        ሴት አትወድም አይደል?
ብላ ስትጠይቀኝ መሳቄን አቁሜ
በንዴት በግኜ ደግሞም ተገርሜ
"አትሳሳች ውዴ
ካንች እጥፍ ድርብ ውለታ የዋለች
ለእኔ ደስታ ብላ ደስታዋን የሸጠች
እኔ እንደምወድህ ውደደኝ ያላለች
ካንች በበለጠ
ፍፁም ምወዳት ገራሚ ሴት አለች"
ብየ ቃል ሳወጣ
ገደል ግባ ብላ ገፍታ ጥላኝ ሄደች

በዚህ ቃል ተናዳ ከፊቴ ላይ ሳጣት
ፍቅሯን አራግፌ ከልቤ አወጣኋት

ደግሞ ትናንትና
አንድ አለችኝ ያልኋት
                     የህይወት አጋሬ
"መውደድህ እንዴት ነው
              የት ድረስ ነው ፍቅሬ?
አንዴ ቃል አውጣና
                      በል ንገረኝ ዛሬ"
ብላ ስትጠይቀኝ
በኔ ልብ አዋዋል በፍቅር አደራደር
ከመውደድ ዙፋኔ ከልኬት ማህደር
      ቦታ አደላድየ ላሞግሳት ስጥር
      የሚከተሉትን ቃላት ብወረውር
"ዚች አለም ስኖር ካገኘኋቸው ሴት
    ደስታ ካቋደሱኝ ካለበሱኝ ሀሴት
        ደረጃ ሰጠሁሽ በሁለተኛነት"
                           ብየ ስናገራት
ከእኔ የበለጠ የምትወዳት ካለች
ከርሷ ጋር አብረህ ኑር
                     ብላ ጥላኝ ሄደች
                     የምር ጉደኛ ነች😢
    ይህን ስትናገር በፍቅር አኩርፋ
ለእርሷ ያለኝ ፍቅር ከእኔ በኖ ጠፋ

እናም
         ነገ የማገኝሽ የትዳር አጋሬ
መኖርሽ የምሆን የምትሆኝ መኖሬ
ቀደም አስቢበት በይ ልንገርሽ ዛሬ

ከመንገስሽ በፊት ከልቤ ዙፋን ላይ
ሁለተኛነትሽን በይ አምነሽ ተቀበይ
ወይም
ብቻየን ወድቄ
ሳልቀምሰው ይቅር እንጂ
                           የትዳርን አለም
አንደኛነትንስ
ከእናቴ አስበልጬ
                     የምሰጠው የለም

ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI

@poem_by_poem
@poem_by_poem


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Nov, 13:31


(ዝም የዋጠው ፍቅር)

ረጭ እንዳለ ባሕር
በሚጮህ እርጋታ እንደተንጣለለ
አደብ እንደያዘ
ከዝምታ እልፍኝ እንደተንጋለለ
በውስጡ ግን
አዕላፍት ነፍሳቶች እንዲርመሰመሱ
ቃል አልባ ትርምስ ይዘው እንዲያምሱ
እንደዛ ይመስላል የኔና' አንቺ ነገር
ከባህር ገፄ ውስጥ ጠልቆ ያንቺ ሃገር
የሙት ባህር ያህል ዝም ከወረሰው
ነፍስ የዘራው ፍቅርሽ የሚርመሰመሰው።


(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Nov, 11:01


ያለ ግጣም መግጠም
ሲቆይ ላያጣጥም
ጥቂት ግን ያስጉዛል
ትዝታና ፀፀት በደርዘን ያስይዛል
ልኩ የራቀው አካል ልኩ የራቀው ነፍስ
ሳይሰበር እንዲው መቼም ላይመለስ
ላይ ላዩን እያበራ ውስጡ እየዳመነ
ስንቱ ልብ በቁጭት ከስቶ መነመነ
ያለ ፍቅር ጥምረት የራስን ሰው ጥሎ
እራስን መቅጣት ነው ከናፍቆት ተዳብሎ
አዲስ ግንኙነት እንዲሁ ሰው ይዞ
ምክንያትን ያጣ መድረሻ ቢስ ጉዞ
አይን ወዲ ብሎ ልብ ወዲያ ካለ
ዋጋ የሚያስከፍል ትልቅ ጥፋት አለ

✍️የተክልዬዋ


@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Nov, 14:24


ቺርስ 🥂 ከልባቸው ለሚገጥሙ ገጣሚያን።

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Nov, 14:23


🔥🔥🔥

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Nov, 14:20


ርዕሱን እኔንጃ

ዘመን ዘምኖ ከማዕዘን ሲዘም
አመት ተቆጣጥሮ አመታት ሲከመር
በቡቃያው ሊጭንበት የማቅ ቀንበር
ዘማሚቶች ተርመስምሰው
ምስጦችም ተማምለው
ኩይሳቸውን አጥረው ነበር
መች አወቁት የጠረቡት እንዲሰበር
በክረምት ወቅት በደፍ ዝናብ
የምን ቤት ነው የምን ምኩራብ
ክረምት ከረመ ሰማይ አለቀሰ
አጀብ ነው
ፍትሃት ሊነፍግ እንባውም ቀሰሰ
ጠብ ጠብ ጠብ
ደም አብሮ ይዘንባል
ከአለት ሲናጋ ግጭት ያስተጋባል
ኩይሳውም ይፈርሳል ምስጡ ይራወጣል
ለበጋው ያልቀና በክረምት ይቀጣል

#ገጣሚ_ኤፍራታ_ዳምጤ
(@ephicr7)

@utorrr
@utorrr

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun


ርዕስ እስቲ ምረጡለት ወገን???

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17 Nov, 10:26


'የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጎምጀትም ሁሉ ተጠበቁ '

#በ40 ዓመቷ በጨጓራ ካንሰር ከመሞቷ በፊት በዓለም ታዋቂው ዲዛይነር እና ደራሲ “ክሪስዳ ሮድሪጌዝ” እንዲህ ስትል ፅፋለች።

1. ጋራዥ ውስጥ የአለማችን ውድ መኪና ነበረኝ፣ አሁን ግን በዊልቸር መንቀሳቀስ አለብኝ።

2. ቤቴ ሁሉንም አይነት ብራንድ ያላቸው ልብሶች፣ ጫማዎች እና ውድ እቃዎች ይሸጣል፣ አሁን ግን ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ ጨርቅ ተጠቅልሏል።

3. በባንክ ውስጥ ብዙ ገንዘብ አለኝ።  አሁን ግን ከዚህ መጠን ምንም አልጠቀመኝም።

4. ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነበር አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በሁለት አልጋዎች ተኝቻለሁ።

5. ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል.  አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከአንድ ላብራቶሪ ወደ ሌላ በመንቀሳቀስ ጊዜዬን አሳልፋለሁ

6. በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ ሰጥቻለሁ ነገርግን በዚህ ጊዜ የሕክምና መዝገቦች የእኔ ፊርማ ናቸው።

7. ፀጉሬን ለመስራት ሰባት ፀጉር አስተካካዮች ነበሩኝ ፣ አሁን ግን - በራሴ ላይ አንድ ፀጉር የለኝም።

8 .በግል ጄት ላይ፣ የትኛውም ቦታ መብረር እችላለሁ፣ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በር ለመራመድ ሁለት እርዳታዎች ያስፈልጉኛል።

9. ምንም እንኳን ብዙ ምግቦች ቢኖሩም, አሁን የእኔ አመጋገብ በቀን ሁለት ክኒን እና ምሽት ላይ ጥቂት የጨው ውሃ ጠብታዎች ናቸው::

10. ይህ ቤት፣ ይህ መኪና፣ ይህ አውሮፕላን፣ ይህ የቤት ዕቃ፣ ይህ ባንክ፣ ብዙ ዝናና ዝና፣ አንዳቸውም አይመጥኑኝምነበር። አሁን ግን ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ሊደርሱልኝ እና ሊጠቅሙኝ አልቻሉም፡፡ 

“የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ ..

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

16 Nov, 18:14


ህዝቤ ጠይም ሳለ ሩህሩህ ነበረ
ቀለም ገባው መስል ይቀ'ላ ጀመረ

አማኑኤል ሀብታሙ

ቤተሠባችን ይሁኑ
ይቀላቀላሉን
@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

16 Nov, 18:00


Self-care is also:

• Walking away from draining dynamics
• Creating space between you and chaos
• Protecting your peace because it's precious
• Saying “no” to what doesn't serve your growth
• Setting boundaries that make others uncomfortable

#tips

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

16 Nov, 06:20


ወቸው ጉድ

መተሩጉሙን ጠልተን ከቅኔ ሾለክን
ወርቅ ሲያባዝነን ከሰም ተናጠልን
የኛ አዝማች የኛ ዘማች
እኛው ነጥቀን አለም ቀማች
...........................



@utorrr
@utorrr

#ገጣሚ_ኤፍራታ_ዳምጤ
(@ephicr7)

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

16 Nov, 05:47


#ወለም_ያለው_ዘመን😏😏

ድምፀ መረዋው #መስፍን_ወንድወሰን

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

15 Nov, 15:56


በብዙ አንባቢዎች ሲጠበቅ የነበረው የናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) ሜሎሪና መጽሐፍ ክፍል 3 ለአንባቢያን ቀርቧል።

“ሜሎሪና” ታሪካዊ የሥነልቡና ልብወለድ የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚያወራ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡ በአቀራረቡም #የሥነልቡና_ምክሮችንና ሀሳቦችን
#የሥነ_አመራር ጥበቦችን #ከታሪካዊ_ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል፡፡በተጨማሪም በመጽሐፉ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደ አንድ ገጸ ባህሪ ተካተዋል።

ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ ሀሳቦች

📕 ‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም። ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡ እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።››

📕‹‹...ትዝታ ለብዙ ሰው የዕድሜ ዘመን እስር ቤት ነው። ብዙ ሠዎችም ወደፊት መራመድ እየፈለጉ አስሮ የሚይዛቸው በገዛ አዕምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጡት የትናንት ታዝታቸው ነው።››

📕‹‹አፍሪካ ውስጥ ‹ሕዝቡ› እንደሚለው ቃል በመሪዎች የተነገደበት ቃል የለም። አንዳንዱ መሪ ሕዝቡ የሚለው የገዛ ራሱን እሳቤ ነው። ሌላው ደግሞ ቤተሰቦቹንና ዘመዶቹ ብቻ ነው ሕዝቡ ብሎ የሚቆጥረው።››

📕‹‹በህይወት ስትኖር መቼም ቢሆን ኹሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም፤ ማወቅና መጠንቀቅ ያለብህ ዋናው ቁም ነገር ማስከፋት የሌለብህን ሰው ለይተህ ማወቁ ላይ ነው።››

📕‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha

📕የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል።

💚ሜሎሪና - ስውር ጥበብ
💛ሜሎሪና - ቴሎስ
❤️ሜሎሪና- ሕይወቴ

መጽሐፉን በኹሉም የመጽሐፍ መደብሮችና ከአዟሪዎች እጅ ይገኛል።

Via ፦ Facebook

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

15 Nov, 15:22


ኤፍሬም ስዩም 👉 ይሁዳ😭

ቢሰማ ቢሰማ የማይሰለች ግጥም

Join us
👇👇👇👇👇👇
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

14 Nov, 17:54


When you pursue your purpose:

• Every setback teaches
• Every failure guides
• Every struggle strengthens
• Every step matters

When you listen to fear:

• Every 'what if' haunts
• Every dream dims
• Every regret deepens

The choice is yours.

#tips

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

14 Nov, 14:42


" #የሰከነች_ሰፊና " የምትለውን በራሱ በአያ ሙሌ ድምፅ የተቀዳችውን ሸጋ ግጥም ተጋብዛችኋል! እንዳያልፍችሁ!


@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

14 Nov, 08:37


መለያየት ማለት

#ገጣሚና_አቅራቢ_ኤፍሬም_ስዩም

Share and JOIN us

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

14 Nov, 08:31


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

09 Nov, 16:06


ስማ ስማ...
@topazionnn
@topazionnn

@eliasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

07 Nov, 18:07


ይነጋል
በዔደን እና አየሁ ተፅፎ እንደቀረበ
@ediwub & @ayehu_melkam
@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

07 Nov, 15:29


#እንቆቅልሽ_ቅኔ

የእናትን ስቃይ በቅኔ!😭😭

ምርጥ አቀራረብ!

ለወዳጆ ያጋሩ!!!

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

05 Nov, 15:48


@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

04 Nov, 18:22


⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉༄༄༄⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉

13 Healthy Tips:

1. Family first
2. You are not your job
3. Keep friends close
4. Forgive first
5. Be humble
6. Don’t take people for granted
7. Complain less
8. Be honest
9. Know when to leave
10. Be a mentor
11. Don’t respond to negativity
12. Be teachable
13. Smile more :)

⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉༄༄༄⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉
#health
@ethiopidia
@ethiopidia
@ethiopidia

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

04 Nov, 10:27


ይኧው ከመቅፅበት

ሁለት ሚስኪን ጥንዶች
                   ጊዜ ያጣመራቸው
ጨዋታ ቀልዳቀልድ
                      ቃል ያገናኛቸው
ለመታመን ብለው
                       ለነገ ፍቅራቸው
መፅሀፍ ቅዱስ ይዘው
                      ሲምሉ ባያቸው
ካንተ ውጭ ካንች ውጭ
ብለው ቃል ሲገቡ
                       ሲማማሉ አይቼ
ሁኔታቸው ገርሞኝ
መብላት አምሮኝ
             ነበር ፍርፍር ወጥ ሰርቼ

ፈጣሪ ከዙፋን
ሰማይና ምድርን
                  በቃሉ ቢያፀናም
በቃላት እስትንፋስ
                   ጎባጣ ቢያቀናም
በፍጡር ህግ ግን
               ቃል ፍቅር አይሰራም

ሌላ ሄዋን ሲመኝ ሲሆን አመንዝራ
     ፍቅሩን ችላ ብሎ መሀላ ከፈራ

ሌላ ገላ ሲሻ ቃሉ ከመለሰው
ቃል አክባሪ ሳይሆን
              ፈሪ ነው ይኧ ሰው

እናም የአዳም ዘር ሆይ
               ከፍጥረት ተመራጭ
ሄዋን ውዷ እህቴ
             የአዳም አጥንት ፍላጭ
የፍቅ'ር ልኬቱን ከጌታ ተማሩ
ሰሙን ብቻ ሳይሆን
               ቅኔም አመስጥሩ
ልክ እንደ ክርስቶስ
ፍቅርን በፍቅር እንጅ
                  በቃል አትጀምሩ

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

@poem_by_poem
@poem_by_poem


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

04 Nov, 10:26


(እስከ መኖር)

ከፊደል ገበታ ወድቆ የፈረጠው
የውቀት ጌታውም ጠፈር የረገጠው
ትልቁ ባለሃብት በገንዘብ የፋፋው
የነጣ ድሃውም የሰው ዘር የገፋው
ይሄ ሁሉ ፍጡር፣ አለም እያነሰው
በምድር አዳራሽ የሚርመሰመሰው
የት ድረስ ብትሉት የልቡን እሩጫ
ከ...እስከ..መኖር ነው የሁሉ መቋጫ።

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

03 Nov, 10:32


ኑሮ አልተወደደም
።።።።።።።።።።።።።
ሀገሬው በሙሉ መገንዘብ አቅቶታል
አርቆ መመስጠር ማሰብንም ትቷል
በጭላንጭል እውቀት
         ኑሮ ተወደደ በማለት ተርቷል


እኔ ግን እላለሁ
                  ይህ ፍፁም ውሸት ነው
ለእኔ አልታየኝም
                   መወደድ ምንድን ነው??


           የሰው ነፍስ በነፃ
                                 እየተሸመተ
የአርሶ አደሩ በሬ
             ባልተሳለ ካራ ታርዶ እየሞተ
ትልቁ ቢላ ቤት
          በከባድ መሳሪያ ወድቆ እየነከተ

     እህል ከሜዳ ላይ
                            በእሳት  እየጋየ
ይጠብቃል ያልነው
ሰውን ባውድማ ላይ ወቅቶ እያበራየ
ታዲያ
   ኑሮ ተወደደ
    እንዴት እላለሁኝ ሳይገባኝ ዝም ብየ

እኔ እስከምረዳው እስከማውቀው ድረስ
በተወደደ `ገር
ተበራይቶ አያቅም የሰው ልጅ እንደ ገብስ

      ኑሮ በጋለበት በተወደደ ሀገር
በከንቱ አይባክንም እያ ውድ ነገር

ስለዚህ ዝም በሉ
ውዱ አዳም ታርዶ
             ምድር ስትለብስ በደም
በሬዎቻችን ታርደው
      ጉልበታም ነኝ ያለው
                     ለግብዣ ሲታደም
እህሉ ተቃጥሎ
                የበረደው ሁሉ
                      ዙሪያ ከቦ ሲቆም
        ይህ ሁሉ ሲደረግ
                      አይተነው ባናይም
በዚች ታካሚ ሀገር
        መኖር እንጅ ብርቁ
                       ኑሮ አልተወደደም!!!!
   
belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

@poem_by_poem
@poem_by_poem

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

03 Nov, 08:42


የዘዉትር ምኞቴ
.
.
.
ከምድር ርቆ፤
በሰማይ መንሳፈፍ፤
ከምርምር ረቆ፤
በደስታ መሰለፍ።

ችግር ግሳንግሱን፤
ከመሬት ወርዉሮ፤
ጭንቅና ህመሙን፤
ስቃዩን አባርሮ፤

ከወፎች ዝማሬ፤
በጋራ መቋደስ፤
በምናብ ሀገሬ፤
ተፈጥሮን ማወደስ።
.........................................
በዔደን ታደሰ እንደተፃፈ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Nov, 17:53


EARN WITH PAWS
SIMPLE ,REAL, GOOD REWARD
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=8JQS2VUV

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

02 Nov, 17:01


... ብቻ ግን እነኋት ....

ታቦቷን አልሸኘሁ _ በቅጡ አላወጣሁ አስራት በኩራቷን፤
ለበረከት ብዬ _ መጥረጊያ ጨብጬ አላፀዳሁ ቤቷን፤

(ብቻ ግን እንዲሁ)

ዝናብ ሲመጣብኝ  ልጠለላት ገባሁ
እግሯ ስር ወድቄ ከዶፍ የመረረ ሃዘኔን አነባሁ

(ብቻ ግን እንዲሁ)

ፀሀይ ሲከርብኝ አፀዷ አስጠለለኝ፤
ቀና ብዬ አየኋት             እነኋት፣
ካለም ግለት ይልቅ ፀዳሏ አቃጠለኝ፤

ለምን አለቀስኹኝ!?
እንደ ፈሪ ምርኮ ፊቷ ተንበርክኬ፤
ከቅፅ'ሯ በፊት  ሀዘን ያጠላበት ምን ነበር ታሪኬ!?
   ምን ነበረ መልኬ!?     (እንጃ )

አልቅሼ ሲደክመኝ
ጉሮሮዬን ጠማኝ  ከፀበሏ ጠጣሁ፤ 
(ስሟን ማን ነገረኝ)!!
ብቻ ወደ ሀሩሩ _ብቻ ወደ ጎርፉ
"ማርያም" እያልኹኝ ካለሁበት ወጣሁ::
.
ማርያም
.
ማርያም
.
ማርያም
@topazionnn
@topazionnn

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Nov, 15:32


የዚህ ሳምንት የመፅሐፍ ግብዣዬ

የቀንድ አውጣ ኑሮ


የንባብ አብዮት ይፏፏም 🔥🔥🔥🔥

መልካም ምሽት @Henilogy ነኝ።




@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Nov, 14:44


ቀጥቅጬ የገደልኩት~እባብ የትናንቱ
ሳይተነፍስብኝ~ሳይነካኝ መሞቱ
ተረሳው መሰለኝ...
ዛሬ እንደነደፈኝ~በዛ መጠዝጠዙ
በቃ እንደፈራሁት~ያንተ ነበር መርዙ

ዘማርቆስ

@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Nov, 08:24


ርዕስ:   🎤ከእንባሽ ጋር☺️

ገጣሚ:  ናፍታናን

ድምፅ:   ናፍታናን

ለአስተያየት;  @nafii_junior7

               
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
        
        @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01 Nov, 05:32


#አጭሬን_በ_አጭሬ
የአጫጭር ግጥሞች ስብስብ በድምፅ


የገጣሚ አሌክስ አብርሃም
የገጣሚ በረከት በላይነህ
የገጣሚ በእውቀቱ ስዩም
የገጣሚ አበባው መላኩ
የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም እና
የገጣሚ ይስማዕከ ወርቁ

አጭሬዎች ተካተዋል አንባቢ ሲራክ @siraaq

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

31 Oct, 06:47


(ስረቂኝ ልስረቅሽ)

ነይ እንሰራረቅ
ህግን ገንድሰነው እንጣል ከስሩ
ሌባና ባለቤት ተሳማምተው ይደሩ
ነይና ስረቂኝ
አንቺ ክቡር ሌባ ተሰናድቷል ቤቱ
እጠብቅሻለሁ በናፍቆት ጓጊቼ እኔ ባለቤቱ
ነይና ስረቂኝ
በዘረፋ ስርቆት ባዶ ቤቴን ፍጂው
ከአዳራሹ ዘልቀሽ ነይ ልቤን ውሰጂው።
ነይ ልስረቅሽ ደሞ
አበጃጂ ቤቱን እንቶፈንቶው ይውጣ
ስቀሽ ተቀበይኝ ልሰርቅሽ ስመጣ
እናፋልስ ህጉን
ልብሽን ስሰርቀው ስቀሽ ተሰረቂኝ
ሃገር ልይዘኝ ስል
ንፁ ሌባ ብለሽ አፅድቂና ላኪኝ።
ነይ እንሰራረቅ

(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

31 Oct, 04:51


ምርጥ ግጥም ናት ተጋበዙልኝ። 🔥🔥🔥

የሶስት_ሰው_ቅኔ
#ኤፍሬም_ስዩም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ 👇👇👇
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ሀሙስ የቀን ቅዱስ
መልካም ቀን ይሁንላችሁ።

🙏❤️🙏❤️🙏❤️🙏❤️🙏

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

30 Oct, 17:16


Elevate your mind and spirit.
Release what drains you.
Invest in your wellbeing.
Find time for stillness.
Protect your peace.
Nurture your body.
Move with purpose.
Prioritize deep rest.
Choose growth.
Eat for vitality.
Return to love.
Transform.
Hydrate.
Create.
Heal.
Be.


#tips
dt

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

30 Oct, 13:07


አሪፍ ግጥም ናት ተጋበዙልኝ! 🔥🔥

#ሞት_እያለ
አልሰማሁም አልሰማሁም አላየሁም አልነበርኩም
ለኔ ያርገው ለኔ ያርገው
ምን አገኛት ምን አገኘው
አዪዪ ለካ ሞት ነው
ለኛ ለሁላችን ፍፁም የማይቀረው..

#እባካችሁ_ለወዳጆ_ያጋሩ
ሞትሁላችንም እንሞታለን አትጥላ አትግፋ አትበድል!!

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29 Oct, 23:15


የዝምተኛው ፀሀፊ እንዲሁም የሌሎች ገጣሚያን የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ወደ
https://t.me/poem_by_poem
https://t.me/poem_by_poem
https://t.me/poem_by_poem
ጎራ ብሎ መወዳጀት ብቻ በቂ ነው
ይምጡ እና ይጎብኙን።

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29 Oct, 09:15


(ማጣትም ይቸገር !)

ወሰን አልባ ፍቅር፣
ከልባችን ጎጆ ሞልቶ እየፈሰሰ
ሃገሬው በሞላ፣
ከደጃችን መጥቶ መውደድ እያፈሰ
የፍቅርን አምሳል በኔና አንቺ ስሎ
ሊኖር ሲፍጨረጨር ሁሉም እኛን መስሎ
እኔና አንቺን ግን
መዋደድ ሳያንሰን
መፋቀር ሳያንሰን
ለጋው ፍቅራችንን፣ በማዕበል እያስረጀ
የመለየትን ሞት፣ በኛ እየፈረጀ
እኔን ከአባይ ወዲህ
አንቺን ከአባይ ወዲያ
አርጎ የለያየን፣ ያለ ቅንጣት ተስፋ
አብረን እንርገመው
ማጣት አይኑ ይጥፋ።

ማጣትም ይቸገር፣ ለማኝ እስኪገርመው
ከአባይ ዳሩ መጥተሽ፣ አብረን እንርገመው
አሜን በይ!...
መንገዱ አይግጠም፣ ባርኮት አያግኘው
በሳምንት ሰባት ቀን ድህነት ይጎብኘው
ከጓዳው ሲዘልቁ፣ ባዶ መሶብ ይስፋ
የሰላቢ መዓት፣ ከደጁ አይጥፋ
አሜን በይ!...
የተከለው አይለምልም
ከሩቅ ላየው ይድረቅ ደጁ
ሰይጣንና እግዚሐር በእሱ፣ በመስማማት ይፈርጁ
በርሃብ ዱላ ተለብልቦ
አጥንት ገላው ይገረጣ
በደሳሳው ጎጆ አናት፣ የኮሪደር ልማት ይውጣ።
አሜን በይ!...
መኖር በጣር ሲቃ፣ እየለተመ ይፍጀው
በሰቀቀን ናፍቆት፣ መሞትን ይጎምጀው
በሽታ በፍጥኝ፣ ቀርንቶ ይግረፈው
ፈዋሹ ሲመጣ፣ የሱን ቤት ይለፈው።
አሜን በይ!...
ይግጠመው ይግጠመው፣ የሃገሬ እጣ
ለሆይታው ለሲቃው፣ አንድም አድማጭ ይጣ
ጭቆና ከጫንቃው፣ ወጥቶ ይስፈርበት
ለአቤቱታ ሲጮህ፣ መድፍ ይተኮስበት።
አሜን በይ!...
ይሽሸው ይሽሸው፣ የአካሉ ጥላ
ሃገሩ ትካደው፣ ትደግ እሱን ጥላ
ትጠየፍ ጉንጮቹን፣ ደርሶ እንዳይስማት
እሱ እየገረጣ
ትለምልም ሃገሩ ባረንጓዴ ልማት።
አሜን በይ!..
ማጣትም ይቸገር፣ ለማኝ እስኪገርመው
ከአባይ ዳሩ መጥተሽ፣ አብረን እንርገመው።


(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29 Oct, 09:09


ሰፈራችን ቢራ ቤት አለ ሸምገል ያሉ ጃኬት ሹራብ ያደረጉ ጠና ያሉ ሰዎች በረንዳ ላይ እየጠጡ ቁጭ ብለው ያወጋሉ ...

እኛ ከትምህርት መልስ ኳስ እንጫወታለን !

ሰፈራችን ቤርጎ አለ ጥንዶች  ተቃቅፈው  ተረጋግተው እያወጉ እየተሳሳሙ እየተሽኮራመሙ ፣ አልጋቤት ገብተው ይወጣሉ እኛ እርግጫ ላይ ስለምንሆን ወይ ሲገቡ ወይ ሲወጡ እናያቸዋለን ፦

እቤት ስንገባ ታላላቆቻችን ዜና ጓጉተው ያያሉ ይወያያሉ ዜናውን እያዩ ትክዝ ግርም ይላቸዋል ፦

"ዜና አሁን ምኑ ይታያል ?"
ይላል ልጅነታችን

እኛ ድራማ ፣ፊልም፣ Wrestling ፣ታላቅ ፊልም፣ኳስ፣ ህብረት ትርኢት ለማየት እንጠብቃለን ።

እንቅልፍ አሸንፎ ካልጣለን ፦

ማታ ያየነውን ከጓደኞቻችን ጋ እንቀዳለን ።

"እከሌ እከሌን ወደደ ፣ እከሌ እከሌን ካደችው፣ ካዳት ፣አስረገዛት  ፣እከሌና እከሌ  ተጋቡ፣ ወለዱ" ብለው ያወራሉ እንሰማለን ብዙ ትርጉም አይሰጠንም ።

እኛ ትርጉም የሚሰጠን  ኳስ ፣ እርግጫ ፣ብይ፣ቆርኪ ፣ ሌባ እና ፖሊስ ፣ቃጤ ቃጤ ፣ በረዶ ፣ጠጠር ፣  ሱዚ.... ነበር

ስጋታችን እዛ ሰፈር የተጣላነው ትንሽ ልጅ ፣ በቴስታ የሚማታው ጓደኛችን ፣እምትቧጨረው ጓደኛችን ፣ እዚ ጋ አትጫወቱ የሚሉት ሴትዮ ፣ "ሲጫወቱ አጥሬን መቱብኝ "ብሎ ለቤተሰብ የሚከሰን  ሰውዬ ... ጨዋታ አትጫወቱም አጥኑ የሚል  የቤተሰብ ክልከላእና ጡጫ ፣ ለበዓል የሚገዛልን ልብስ ....

እምንፈራው በተረት የሰማነው አያ ጅቦ ..ስጋታችን በጨለማ  ለሽንት ስንወጣ የምንሰማው ኮቴ ነበር
ማደግ  ያጓጓንም ነበር ።

አደግን ፦

መጠጥን ቀመስነው ...
ቤርጎውን አየነው ...
ዜናውን ተራቆትንበት ...
ተካካድን ....

የማናቀው ነገ አስፋራን ፣ ማደጋችን አስደነገጠን ፣ ትልቅ ሰውዬ ነው ያልነው ሰው እድሜ የኛ ሆነ።

ልጅ ሆነን የምናዉቀው አለም ተቀየረ !!
     ©  Adhanom Mitiku

🔥🔥 ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 🥺🥺

         @eliyasshitahun
         @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Oct, 09:34


ወገን ቻናሉን ሼር እያደረጋችሁ።

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

28 Oct, 06:52


ርዕስ:   🎤እንታረቅ☺️

ገጣሚ:  ናፍታናን

ድምፅ:   ናፍታናን

ለአስተያየት;  @nafii_junior7

               
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
        
        @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

27 Oct, 13:33


(ቅዱስ ነኝ)

የመስቀል ለት' ምሽት፣ ሲለኮስ ደመራ
ከሽህ እቶን እጥፍ፣ እሳቱ ሲያበራ
ሲነድ ሲቃጠል፣ በህይወት ቃል ስፍር
ደሞ ሲታገለው፣ የንፋስ ውሽንፍር
ትዝ ይልሽ እንደሆን...
አንዲት ብጣሽ ብርሃን
ከደመራው ወጥታ
ከእልፍ ምዕመናን፣ እኔን ብቻ መርጣ
ማረፊያ ስትፈልግ፣
ከርማ ከርማ ስትበር
ከደረቴ መሃል ደርሳ አርፋ ነበር።
;
ለምን እኔን መርጣ?
ለምን ከደረቴ ከልቤ አድራሻ?
በፀሎት በምልጃው፣ ሁሉም እሷን ሲሻ?
;
ቅዱስ እንደሆነች ነፍሴ ያለ በደል
እግዚሐር ሲመሰክር
ይሄው አየሽ አይደል።
ቅዱስ ነች ነፍሴ፣
በደልን አታውቅም አለም በሐጥ ቢርስ
ይሄው እስከ አሁን፣
ቅዱስ ነኝ ብዬ እስክበድል ድረስ።
እስክፅፍ ይሄንን
ቅዱስ ሰው ነበርኩት
ቅዱስ ነኝ ስልሽ ነው፣ አሁን የረከስኩት።



(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ለወዳጆ ያጋሩ 👆👆 #ሼር

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

26 Oct, 11:27


#አልፎ_አልፎ_መሞት
#ኤልያስ_ሽታኹን

ሰው
አንድም - በእግዜር፡
አንድም - በመውዜር፡
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል።

ሰው ቢያጣ መንገድ ሰው ቢያጣ ምርጫ፡
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ።

ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ፡
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ።

እኔ ግን፡
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን፡
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን።

ሰው
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት፡
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።


@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

26 Oct, 05:13


የጠነከረው ጥቁር ባልጩት
ምርጥ ግጥም ነው ተጋበዙልኝ

ለወዳጆ ያጋሩ #ሼር #ሼር
👇👇👇👇
@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ለአስተያየት 👉 @henilogy

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Oct, 11:57


ይችህን ጥኡም ግጥም ጋበዝኳችሁ
በጥሞና አድምጧት።
🔥🔥🔥

#የአድዋ_ድል_በስነ_ግጥም
ኢትዮጵያዊ_መሆን_ኩራት ነው!


ወዳጁም ሳቀ ጠላቱም ከሳ፣
ተንቀሳቀሰ ዳኘው ተነሳ፣
አራቱ አሀጉር ለሱ እጅ ነሳ ።
ሄደ ዘለቀ እስከ ጠረፉ፣
የቃኘው ፈረስ የአሞራ ክንፉ።

ለወዳጆም ያጋሩ🇪🇹

@eliyasshitahun @eliyasshitahun
@eliyasshitahun @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Oct, 09:48


ጢም አልባ

ይስማዕከ ወርቁ

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Oct, 09:41


ርዕስ:   🎤ቺርስ😁

ገጣሚ:  ናፍታናን

ድምፅ:   ናፍታናን

ለአስተያየት;  @nafii_junior7

               
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
        
        @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

25 Oct, 08:23


ሆንኩኝ እማምዬ

ሲናፍቀኝ ሽንኩርት፤ ሲናፍቀኝ ጤፉ
ዋጋን ሰበብ አርገው፤ ከቤቴ ሲጠፉ
ኑሮዬ ሲጥለኝ ፤ገንዘብ ሲያንፏቅቀኝ
መፍትሄ ፍለጋ ፤ጭንቄዬ አመጠቀኝ
ሲሰራ ያላለፋ፤ ጥሩ ገቢ ያለው
ግብር ክፈል ብሎ፤ መንግስት ማይጠይቀው
ሳስብ ሳስብ ስራ፤ ያለወጪ አትራፊ
ጥንቁልና አገኘው፤ ሚያበላ በሰፊ
.
ጥቂቱን መፅሀፍ፤ አንብቤ መርምሬ
ለአባብዬም ልኬ፤ ለውል አንድ በሬ
ልምድ ተቀብዬ ፤ሲስተሜን ዘርግቼ
ጀመርኩ ስራዬን ፤ጊቢዬን ከፍቼ
ሲኒዬን ደርድሬ ፤ሳጓራ የሰማ
ጎረቤቴ መጥቶ ፤ሲመክረኝ ባልሰማ
ሴት አትሆን ቢልም፤ መቼም ለዚህ ስራ
ህጉ ያፀደቀውን፤ የእኩልነት አንቀፅ
ሳብራራ በተራ
አምኖኝ ተፀፅቶ ፤ጠይቆኝ ይቅርታ
ካዳሚ ሆነልኝ ፤በሰጠሁት ቦታ
.
ገብያም ጦፈልኝ፤ ተንበርካኪ በዛ
ስነግረው የሆዱን፤ በጉን እየገዛ
በዝቶበት ጊቢዬ ፤ቢመስልብኝ በረት
ሜኑ አዘጋጀው ፤የሚገድብ ስዕለት
ለእጮኛ ፈላጊ ፤ገቢው ዶሮ ጥቁር
ሀብትም ለጠየቀ፤ ይከፍላል በዶላር
መስተፋቅር ያለም፤ ያምጣ ወደል በሬ
ለሌላሁም እንዲ፤ ተርታዬን ዘርዝሬ
ቪአይፒም ለይቼ፤ ጀምሬአለው ስራ
ህዝብ ይጎርፍልኛል ፤ድግምቱን ሊያሰራ
ጣፍጦኝ ገፉሁበት፤ ብትሞላ ጓዳዬ
እየጠነቆልኩ ፤ተጋው በስራዬ
ዲግሪዬንም ትቼ፤ ሲቪዬንም ጥዬ
ሀገር ያደነቃት ፤ሆንኩኝ እማምዬ

(በእርሶ መጀን እማምዬ እያላችሁ👍😁)

✍️የተክልዬዋ 🔥🤝🔥

@semetnbegtm
@semetnbegtm

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

24 Oct, 12:40


የብዕር አሟሟት ሌላ

ገጣሚ ፀጋዬ ገብረመድህን
አንባቢ ሄኖክ ፀጋዬ (
@Henilogy )
No soundtrack

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

24 Oct, 05:00


https://youtu.be/dPguXRYUPpc?si=1E7t2UueHQisSQRb

እሷን ማግኘት ምትፈልጉ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ማግኘት ትችላላችሁ 👉0799154871🙏
0799154871

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

23 Oct, 18:51


@utorrr
@utorrr

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

23 Oct, 15:25


🥂🥂🥂🥂🥂 ቺርስ የጥበብ አፍቃሪያን።


ደህና አመሻችሁ😊

🔥🔥🔥🔥☄️🔥☄️🔥☄️🔥☄️🔥

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

23 Oct, 04:01


በቻሌንጁ ሰበብ የሆዴን አወራሽልኝ ላላችሁ የተረሱ ቺርሶችን ልጨምርላችሁ (የቀጠለ)

ቺርስ 🥂 ለጓደኞቻችን አብረውን ላደጉት ወይም የሆነ ጊዜ ላይ የቅርብና የልባችን ሰው ላረግናቸው በሀዘንና በደስታ ላልተለዩን በቤተሰባችን ውስጥ ጥሩ ስም ላላቸው(እንደሱ/እንደሷ አትሆኑም እያሉ እንድንወቀስ ላረጉን🤨) ስህተታችንን ለሚያርሙ ጉድለታችንን ለሚሞሉ መካሪና መስታወት ለሆኑን ምርጥ የልብ ጓደኞቻችን ቺርስስስ 🥂

በተቃራኒው ደሞ ወዳጅ መስለው ቀርበው (ፍቅረኛ/ጓደኛ ብለን ሾመናቸው ) ጉድ ለሰሩን ሰው እየሳቅ  መውደድ ብቻ ሳይሆን መጥላትና መክፋትም እንደሚችል ላሳዩን መሰበር መናቅ መገፋት ባመኑት መከዳትን ከጀርባ መወጋትን ላቀመሱን ክህደት ወዳጅ ብለን ከምናስባቸውም እንደሚመጣ አሳይተው ላስተማሩን ዛሬ ላይ ጠንቃቃና ብርቱ እንድንሆን ምክንያት ለሆኑን ለወዳጅ መሳይ ጠላቶቻችን በይቅርታ ካለፈ ልብና ከበሰለ አእምሮ ጋራ ቺርስ ብለናል 🥂🥂

እናም በገዛ ገንዘባችን በሽታ ላሸመቱንና ሰላም ለነሱን ችግር ፣ጥላቻ፣ወገንተኝነትን ላስፋፉብን  እኛን ጨርሰው ህፃናቱን ለመረዙልን ለነ ቲክቶክና ዩቲዩብ እንዲሁም ለሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች (ሙሉ ጥፋቱ በነሱ አይወሰንም የኛም አጠቃቀማችን ገዳይ የሆነብን እራሳችንን ከመልክ ባሻገር ምናይበት መስታወት ሳይኖረን የሌላውን ቅሌትና መጥፎ ነገሮች አሳደን እናያለን ቅሌታም የሆንን ጉዶች😑) ይበለን እያልን ላላቸው አንዳንድ ጥሩ  ነገሮች ቺርስስ 🥂

ቺርስ ..ለኛም ምርጥ ምርጥ ነገሮች በሞሉበት መልካም መልካሙን ትተን የቅሌትና የፖለቲካ ዲስኩር ፈልፍለን እየሰማን ቀውሰን ትውልድ ላቀወስነው (ይሄ ነገር ግን 7/4 ሳያስፈልገን አይቀርም የሆነ ጋንጩርማ ህዝቡን ሳይፀናወተው አይቀርም እንጂ እንዴት ይሄ ሁሉ ሰው ፖለቲከኛና ዲስኩራም ይሆናል🤔 )  ብቻ ለኛም እንዲምረን ከህሊና ፀሎት ጋር ቺርስ ( ይሄኛው ያለ አልኮል ነው ቺርሱ ሆ እንዳታስቀስፉኝ ደሞ😁)

ብዙ ጠላት ተነስቶብን በጥላቻ ንግግርና በለሆድ ሟች ሰዎች ዲስኩር እየተወገረ ዛሬም ድረስ ላልጠፋው በአብዛኞቻችን ልብ ውስጥ ላለው ፍቅርና ኢትዮጲያዊነት እንዲሁም መከባበር ዘር፣ ሀይማኖት ሳንመርጥ እንድንዋደድ ላደረገንና በህብረት ለሚያኖረን የጥንት ባህላችን ቺርስስስ 🥂

ደሞ ደሞ ፅፈን(አስበን) ለረሳነው እቅዳችን በዚህ ዓመትማ ብለን ለዛትንበት አዲስ አመት (የአብዛኞቻችን የእስከዛሬ እቅድ ወደ ተግባር ቢለወጡ ኖሮኮ የት ደርሰን ነበር 😒ሀገራችን እራሱ ቻይና ማ ነበረች ምትልበት ቀን ይሄኔ መቶ ነበር🥺 ለማንኛውም ማቀድ ብቻ ሳይሆን መተግበሩም ላይ እንበርታ  )  ተስፋ ለጣልንባቸው ህልሞች ቺርስ 🥂

ለነዛ ወደቁ ደቀቁ ከሱ ጠቆሩ ተሸነፋ ባዶ ቀሩ እያሉ እያሙ ለግመን ከነበረበት መንፈስ ተነስተን እንድንለወጥ ላረጉን ስንደክም የቅናት ሀሜታቸው ሀይል ሆኖን ለሚያስነሳን ስንታክት ንቀታቸው ብርታት ለሚሆነን ምቀኞቻችን ልቦና ይስጥ እያልን ቺርስ 🥂

በመጨረሻም የዋጋ ንረቱን የገቢ እንሰቱ ቢያቀጭጩትም አልበጠስም ብሎ ለሚታገለው  ላልሞላው ኑሮአችን (ላም አለኝ በሰማይ አይነት ተስፋ እየሰጡ ለሚጫወቱብን ለእነገሌ ሳንበላ ያሉትን አምነን እጃችንን ለታጠብነው ለኛም አይዞን ብቻ😞🥺)  ነገን በመልካም ምኞት ለሚጠባበቀው ልባችን "እስኪያልፍ ያለፋል" ብለን ችለን ለምንገፋው ህይወት ቺርስስ 🥂🥂🥂🥂

✍️የተክልዬዋ

@semetnbegtm
@semetnbegtm


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

23 Oct, 03:51


ያለማድነቅ ጥበብ
    

አይንማ ልብማ ማወዳደር ያውቃል
አካልም ሞኝ ነው. . .
ባለቀ ሰውነት ገል ገላ ላይ ይስቃል
ገላዬ ሳቀልሽ አካልሽን አይቶ
በውዳሴ ከንቱ ልቡ ተጎትቶ
ከንቱ ነው አለሜ የመውደድ ዳርቻ
እያደር ያስንቃል አጣምሮም ከአቻ
ገላሽ ከገላዬ
አካልሽ ከአካሌ
ልብሽ ገለመሌ
ሳቅሽ የእነከሌ
ተይው ወዲያ ይቅር ቃላት ምን ያደርጋል
ሙገሳም ነው ከንቱ መንፈስን ያደክማል

ታዝበሽ እንደሆን መኖር ቃሉ ሞተ
ስጋ የለበሰ በስጋት ቃተተ
ከመኖርሽ ጀርባ. . .
. . . በአስሩ ጣቶችሽ የፈረምሽባቸው
ሞቶች ስንት ናቸው?
ሀዘን ስንት ናቸው?
እንባ ስንት ናቸው?
የማያልቅ ፈገግታ የደረብሽባቸው
ታዝበሽ እንደሆን አላፊ አግዳሚውን መሳቅ እያማረው
ነገ የሚል ተስፋ . . .
. . . ከአሁን ልቡ ላይ እንደ እሬት ሲመረው
ከአልሞትም ጋር ትግል. . .
. . . ከአልኖርም ጋር ትግል ሆኖበት መኖሩ
የአሁናዊው ተስፋ ሲነቀል ከስሩ
እያየሽ ካልታዘብሽ ፈገግታሽ ነው ሽፋን
የዛሬን ስቆልኝ ከበላዬ ያልፋል
እናም ሰውነትሽ ገል ገላሽ ላይ ስቆ
ጀርባው ሞት የሆነን መኖርሽን ንቆ
ያልፋል በሚል ተረት . . .
. . .ሊያውም የጅል ተረት ልብሽን ከረታ
ያልፋል አይግረምሽ ደቂቅ ነው ዝምታ
ውዳሴም ከንቱ ነው . . .
ውበትሽ ውበቴ እንደሾህ አበባ እያደር ይረግፋል
ያልፋል በሚል ተረት. . .
. . . ሊያውም የጅል ተረት ኗሪ ሁሉ ያልፋል
ተይው ወዲያ ይቅር . . .
. . . የመደነቅ ሸንጎ ፍርድ አይገኝለትም
ገላ ቀን ጠብቆ ስለሚወድቅ የትም
አይንማ ልብማ የቂል ሀገር ሰው ነው
ሙገሳን ይቸራል ቃል እንኳ ቢያጥረው

  ----ታዳኤል ደሳለኝ----

         ∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

22 Oct, 18:56


-
ጥርስሽ አይደል የሚያስጠላው
አስር ጊዜ አትቦርሺው፤
አይንሽ አይደል የሚያስጠላው
ዙሪያ ኩሉን አታዳርሺው፤
ገላሽ አይደል የሚቀፈው
ነጭ ሎሽን አታብሺው፤
ከናፍርሽ ያምራል እንዲው
እርጥብ ቅባት አታቅምሺው፤
ህሊናሽ ነው የቀፈፈኝ ..
.. ወይራ ነገር አጫጭሺው!

#mikiyas_feyisa
@topazionnn

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

22 Oct, 18:48


---------

አረንጓዴ ሚመስል አተኛኘትሽ መሃል
እግሩን ደረትሽ መሀል የጣለ የፀሀይ ጮራ
ነክቶሽ ነው ቀን የሚጀመር...
ስሞሽ ነው ቀን የሚበራ
:
እኔ የተቀመመ ሲጋራ መሀል
ለስላሳ ቡና እጠጣለሁ...
ጥቃቅን የእጅ ፀጉርሽ እና ብርሀን በሚያደርጉት ጨዋታ እገረማለሁ
ከሁሉ በላይ በዚህ እነቃለሁ!
:
እዚህ ክፍሌ መሀል ባለ ለስላሳ መደብ ላይ ሆነሽ....
ሳቅሽ ሲበተን ፣ ሁሉን ሲነካ
ይቀፈኛል ውጪ ያለው...
ይረሳኛል የሀገሬ ፖለቲካ!
:
ጨለምተኝነቴ ሸሽቶኝ ጠፍቷል
በዓለም ዞሬ ያልተወኝ ሀዘን
በአይንሽ ታይቶ ተረጋግቷል!
እዚህ ከመጣሽ ወዲህ...
መንሰፍሰፍ ከልቤ ገባ...
ያስለቅሰኛል የድሮ ነገር
ያስገርመኛል የደጄ አበባ!
ለማየው ሁሉ...
እንደ አረጋዊ መደመም
ደግሞ እንደ ህፃን ነፍስ መቸኮል
ህይወት'ን ላኮረፍኳት አፀፀትሺኝ
አትሰለችም በአንቺ በኩል።

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

22 Oct, 14:25


#በተናቀ_መድመቅ
ገጣሚ_ረድኤት_አሰፋ

በአምስተኛ ክፍል አማርኛ መፅሐፍ ኑሮዬ ቢመተር፣
ከዚህ ስንኝ በታች ካለው ግጥም ጋራ ይመሳሳል ነበር፣
ምን ንባብ ከዘመናት ባንዱ.........

እንኳን ግጥሙ ድምፁ ይበቃል!!

#ለወዳጆ ያጋሩልን🙏
#ሼር #ሼር #ሼር

@eliyasshitahun @eliyasshitahun
@eliyasshitahun @eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

22 Oct, 14:20


ፍረዱኝ

እሽሽሽ
ዝምታ
   አንዴ ዝም በሉ አትንጫጩ በቃ
  ከጎኑ የሚቆም ባይገዛም ጠበቃ
ፀሀፊ ልማዱ ነው ይወዳል ጨረቃ
እኔ ዝምተኛው
በውስጥ ወሬኛዎች
           ሰላሜን ስላጣሁ
ፍረዱኝ በማለት
       ወደ እናንተ መጣሁ

" ትናንት የነበረው
           ሁሉም ተቀይሯል
የአሜሪካ ዶላር
       በእጥፍ ተመንዝሯል
    ሰላም እና ፍቅር
          ከሀገር ተሰውሯል
ስንቱ እሯጭ ጀግና
        እግሮቹን ተሰብሯል
ቤት አልባው ገጣሚ
          በብሔሩ ታጥሯል
ነፃ አውጭው ግለሰብ
         ወህኒ ተወርውሯል

ትናንት የሀገር ዋልታ የተባለ ቡድን
    አሸባሪ ተብሎ እያየህ ሲታደን

እጆቿን ወደ ላይ በምትዘረጋ ሀገር
ሆደ እንስፍስፍ እናት ሆዷ ሲተረተር
አርሶ አጉራሹ አባት 'ንደወጣ ሲቀር
ስንቱ ሚስኪን ዜጋ
                       በጅምላ ሲቀበር
እልፍ ጨቅላ ህፃን
                     ታርዶ ሲወረወር
   ቆመህ እየታዘብህ
                    ሁሉም ሲቀያየር
አንተ ማን ሆነህ ነው
               ደፍረህ ማትናገር?"

የሚለኝ ሲበዛ በ inbox ብራና
እኔም ለመቀ'የር ወስኛለሁ እና

  ከፅሁፍ በዘለለ
                በድምፅ ልገማሸር
በጥብቅ ስለወሰንሁ
                     ዝምታየን ልሽር
እናንተም ፍረዱ
          በድምፅ ልምጣ ልቅር?

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

@poem_by_poem
@poem_by_poem


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Oct, 15:29


ለዝህች ንፁህ ኢትዮጵያ መልካም ልደት ተመኙላት። መልካም ልደት ክብር ዶክተር እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) 🔥🔥🔥🔥🔥❤️❤️❤️

ዓድዋ
(ጂጂ)
….. ……. …….
የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ
..... ........ ......... .......... ........
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር ሀገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
........ ....... ......... ......... ........
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን
በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
........ .......... ......... ......... ..........
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
......... ........ ........... ....... .........
የጥቁር ድል አምባ አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ ተናገሪ
የድል ታሪክሽን አውሪ
እህህህህህህህህ ተናገሪ

.......... @Henilogy

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Oct, 15:12


የዛሬ መወያያ ርዕስ❤️

#1 ግጥም በኢትዮጵያ መቼ ተጀመረ።



የባለፈውን ጥያቄዎች መልስ በቅርቡ ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ይበርባል🙏

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Oct, 09:52


ከቀን ቀን ካልሽኝ ሥላሴን፣
ሌላ ካልሽኝ ደግሞ ዛሬን።

🎂🎂🎂🎂🔥🔥🔥🎂🎂🎂🎂

     #HENILOGY

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Oct, 06:53


እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል ጊዜ በማንኛውም ሰአት ይለወጣል በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ ምንአልባት ሀይለኛ ትሆን ይሆናል ነገር ግን ጊዜ ካንተ ያበለጠ ሀያል ነው አንድ ዛፍ መቶ ሺህ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺህ ዛፎችን ታቃጥላለች አንድ መጥፎ ስራ ጥሩ ድረጊቶችን ታጠፉለች ዋናው ነገር ሰዎችን የምታከብር በአስተሳስብ ዘመናዊ እና ሁል ጊዜ ጥሩ አመለካከት ያለህ ሁን 👍
                                         

for more Join☞  @tksa_tks

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Oct, 04:42


እብድስ አይመስለኝም
     ...........
ሶላትን ቢሰግድ ቤተ ክርስቲያን ጓሮ
ቢያማትብ ከመስጊድ ዝክሩን ዘክሮ
እሳትና ውሃን አስማምቶ ሲያፈጥር
ያከፈለ እለት ቁርጡን ቢጠረጥር
ከአባቱ ያየውን ከእናቱ ተማረ
በአያቱ ክርስቲያን ወይ ሙስሊም ነበረ
የሰበከው ፍቅር የሰራው በተግባር
አጃሂብ በሚያሰኝ በረቀቀ ምግባር
ቀን ዝክር ቆይቶ ሶላትን በተራ
ከረመዳን በፊት የዋለ ከተራ
ሰላም ለኪ ካለልኩ ኩነኔ ለነብሴ
እንዳይሆን በማለት ውሎ ከቅዳሴ
አመሻሽ ለስግደት ምንጣፍ ሲዘረጋ
እግዜሃር በሚያውቀው ምንይሰጠው ዋጋ
ብቻ እብድ አይመስልም ኩፋሩን ጠምጥሞ
አብሮ ሲሄድ ሲያዩት ከሸሁ ጋር ቁሞ
ብቻ ባልሳሳት አንብቤ ሳስተውለው
ንፁ ኢትዮጵያዊ ይህ ሰው ወሎየ ነው

ባልሳሳት😂😂😂

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Oct, 04:42


እጅ በጆሮ

ህይወት እምሻዉ

🎤ሙሉቀን የጀሚላ

@Mulukenyejmila

ተጨማሪ ትረካ👇

@Terkamulukenyejmila

@Truzmulukenyegmila

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Oct, 15:57


A full moon always rises at sunset
A new moon always rises at sunrise
A first-quarter moon always rises at noon
A third-quarter moon always rises at midnight

#knowledge....

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Oct, 23:21


#እውን መሰላት

አይኖቿን በአይኔ እያየው....
..... መውደዴን በአይን ስነግራት
በኔ ማማለል ጥበብ ከንፈሮቼን ስነክስላት
ቆንጆ እንዳንቺ አላየውም . . . .
.. . . .በእፍታ አይን ውስጥ የገባች
መልክማ እንዳንቺ የለም . . ..
       . . . .ይተዋል ሁሉም ሲሰለች
እያልኩኝ እያሰላሰልኩ. . .
     . . . እጇን ልይዘው በዘዴ
ፍቅርህን ፈራውት አለች እውነት መሰላት እንዴ?

እውነትማ አይመሰላት
ስላየሁ ሁሉም ሲጥላት
ልቧ የዋህ ነው ያምናል አንዲት ቃል የተነፈሰን
ገላዋ መያዝ አይችልም ለመለያየት ያሰበን
እርግጥ ነው የአይኖቿ ማማር የእሩቅ መንፈስ ይስባል
ከንፈሯ ሀሴት ይሰጣል
ሊበተን ያሰበን ሀሳብ ወደ እራሱ ይሰበስባል
እውነት ነው ፍቅራ ብርሀን ነው
ለመርገጥ ያሳሳል በጣም ....
........ገላዋ እርጥብ ጮርቃ ነው
ታዲያ ይሄ ውበቷ ገዝቶኝ እጇን ብዳብስ በዘዴ
ፍቅርክን ፈራውት አለች እውን መሰላት እንዴ!
          (ደፋር)

         ታዳኤል - ደሳለኝ


@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Oct, 13:28


ዛሬ ቅዳሜ ነው🎵 የት አላችሁ እዚህ???👇👇👇👇👇


@kuruethiopiawi777

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Oct, 13:25


እስቲ አንድ ጊዜ ፀጥታ.......ሽሽሽሽሽ



ደራሲያን እራሳችሁን አስተዋውቁ!

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

19 Oct, 05:32


ይሄ ሰው እብድ ነው
አብርሃም ሙሉ ሰው

እቤተክርስቲያን
አውደ ምህረቱ ላይ ፣ ሶላቱን ሰገደ
እመስኪድ ፊት ቆሞ ፣
በትምህርተ መስቀል ፣ ተሳለመ ሄደ
ምንድነው ይሄ ሰው ፣ ሃይማኖት እምነቱ ?
በ'ሱ ልብ አንድ ሆነው ፣ ያፀኑት ሁለቱ
እሳት እና ውሃን
ውሃ እና እሳትን ፣ የያዘ አደባልቆ
ምን የሚሉት ጥበብ ፣ ከማን ዘንዳ አውቆ
ከአማኞች ተራ፣ ተለየ እርቆ ?
...
የኔ መንገድ ብቻ ፣የጽድቅ እየተባለ
ይሄ ሰው እንዴት ነው ፣
ከሁሉም ተስማምቶ፣ መከተል የቻለ ?
ሁለት እግር ያለው ፣ ሁለት ዛፍ ካልወጣ
አንደኛውን መምረጥ ፣ ሆኖ እድል እጣ
ወይም ሁሉን መተው ፣ አማራጭ እያለው
ለሁሉም የሚከብድ፣ ለብቻው ሚቀለው
ወላሂ ! ማርያምን ! ፣ ይሄ ሰው እብድ ነው ፡፡

@topazionnn
@topazionnn

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Oct, 04:39


#በወደደች

አለፈላት ይለኝ ጀመር አልፎባት ሲያስተውላት
ስላላየ.....
ማንም ገብቶ ከልቧ ውስጥ እንደጣላት
መከሩላት ተሰብስበው በራስ ቋንቋ
ከትላንቷ ተዛዘቡ እየሳቀች በመውደቋ
ከህልሟ ውስጥ ያኖረችው ህልም ነበር
ከመኖር ገፅ ተገንጥላ ሳትቀበር
አልሞተችም በአካል አለች ስጋ ለብሳ
ግን አትኖርም....
ካለ እድሜዋ ባመነችው ተገንድሳ

ወንድ ነበር ውበቷን ያደነቀላት
ወንድ ልጅ ነው ውበት ስሯን የነቀላት

ወንድን ነበር በአንዲት ልቧ ያመነችው
በወንድ ነው ሰውነቷን የጣለችው

ወንድ ነበር የቀደሳት
ወንድ ልጅ ነው ያረከሳት

አልሞተችም አለች በአካል ስጋ ለብሳ
ባፈቀረች ስለ ፍቅር በክፉ ወንድ ተገንድሳ

             ታዳኤል ደሳለኝ

@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Oct, 04:38


እንዲህ ነኝ
ለመኖር ነው እንጅ
ኗሪ ነው ለመባል እኔ ኖሬ አላቅም
ለሚገ'ባው እንጅ
ለማንም አድር ባይ ቦታየን አለቅም
ላዝናናኝ ነው እንጅ
ለቀለደ ሁሉ ለይምሰል አልስቅም
በአስተሳሰቡ እንጁ
በልብሱ ለክቼ አዳምን አልንቅም
ችግር ካሰቃየኝ
ከሰረቀ እንጅ ከሚሰራ አልሰርቅም
ለራበው ለማጉረስ
እጆቼን ሰድጀ ከለማኝ አልነጥቅም
በፍቅር ካልሆነ
ስሜት አሸንፎኝ ሱሪን አላወልቅም
ቤቴን ሳላሳምር
ለውዳሴብየ አጥሬን አላጠብቅም
በላይ ዝምተኛው
የራሴን ካልሆነ
የእድለኛን እጣ ተደብቄ አልፍቅም
ደሞ ጉረኛ በሉኝ😡😡😡

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

@poem_by_poem
@poem_by_poem


@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18 Oct, 04:38


ማባዛት(*)

         ሒሳብ በቀመሩ
በህይወት ስሌት ላይ ካርታ መቆመሩ።
አባዝቶ አካፍሎ፣ ዙሪያዬን መርምሮ
    ያጀቡኝን ሁሉ፣ አስልቶ ደምሮ
ካስር' ድምር ውጤት፣ ቁልቁል አሳንሶ
ዘጠኝ አለህ ይላል፣ አንድ እሷን ቀንሶ።
        (ድንቄም ዘጠኝ እቴ)
        እሷን ሲቀንሳት፣
  በዜሮ ተባዝቶ መኖር እንዲጠፋ
       ነፍሴ በስሌቷ፣
ንፋስ እንደምትስም ባዶ ገላን አቅፋ
        (አልገባውም!)
              ;
     ይልቅ በመቀነስ
      አንድ እሷን ቀንሶ
ዘጠኝ አለህ ብሎ፣ ወሬ ከሚነዛ
       በስሌት ቀመሩ
እሷን አስር ጊዜ ለነፍሴ ያባዛ።

      (እንግዳዬሁ ዘሪቱ)

@eliyasshitahun

#ሼር #ሼር