ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ለመነኮሳት ማረፊያ የሚያስገነባውን ባለ አምስት ወለል ሕንጻ(G+5) ግንባታ ባርከው አስጀመሩ።
ጥር ፬/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ለመነኮሳት ማረፊያ የሚያስገነባውን ባለ አምስት ወለል ሕንጻ(G+5) ግንባታ ባርከው አስጀመሩ።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የምትገኘው የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ጥንታዊና ታሪካዊ ከሆኑት ገዳማት መካከል አንዷ ናት።
የገዳሟ አገልጋዮች አባቶች መነኮሳት በመሆናቸው ከተበታተነ ግላዊ ኑሮ ይልቅ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽረ ግቢ ውስጥ የጋራ ማረፊያ (በዓት) እንዲኖራቸው በማሰብ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ አማካኝነት የመነኮሳት ማረፊያ በ1961 ዓ/ም ተገንብቶ እስካሁን ሲጠቀሙበት መቆየቱን በገዳሙ 40 ዓመታት በላይ ያገለገሉት አገልጋይ አስታውሰዋል።
የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ መዊዕ አባ ገብረ ሥላሴ ጠባይ በበኩላቸው የሚሠራው ግዙፍ ሕንጻ ለመነኮሳት ማረፊያ ከመሆኑ በላይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ታሪክን ማስቀጠልና አሻራን ማኖር መሆኑን ገልጸዋል።
የሚገነባው G+5 የመነኮሳት ማረፊያ ሕንጻ በ6 ወራት ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ የተገለጸ ሲሆን ውሉን የወሰደው ላሜድ ኮንስትራክሽ በተባለው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚያደርግ በብፁዕነታቸው ፊት ቃል ገብቷል።
አክለውም ገዳሟ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ተማጸነውባት በሕይወታቸው ዕረፍት ልባቸው መጽናናት ፈውስ ያገኙበት መሆኑን አስተውሰው በአባቶች መነኮሳት አስተባባሪነት የተደረገለት ሰው ሁሉ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሠናያት የቻለው ለማ በበኩላቸው የገዳሙ አስተዳደር ታሪክ ጠብቆና ለነገ ትውልድ የተላላፍን ሥራ ለመሥራት በመነሳቱ እጅግ የሚመሰገነው ያሉ ሲሆን በተለይም መንግሥት እየተገበረው ካለው የኮሪደር ልማት አንጻር የሚሠራው ሕንጻ ቦታ መጠበቁ ለመነኮሳቱ ማረፊያነት ማገልገሉ እንዳለ ሆኖ ለአካባቢው ድንቅ ውበት በመሆን እንደሚያገለግል ተናግረዋል።
ቀጥለውም ገዳሙ ሕንጻውን ሠርቶ ለማጠናቀቅ የተያዘው የ6 ወራት ዕቅድ በእጅጉ የሚደነቅ እንደሆነም ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው ታሪክ ለማስቀጠል የቤተ ክርስቲያንን ሀብት ለመጠበቅ የተደረገው መልካም ሥራ ያደነቁ ሲሆን በዚህም የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ መዊዕ አባ ገብረ ሥላሴንና ማኅበረ መነኮሳቱን አመስገነዋል።
አክለውም ግንባታው የተጀመረው የመነኮሳት ማረፊያ G+5 ሕንጻን በ6 ወራት ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙ በእጅጉ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው ቦታው ተዳፋት ያለው ከመሆኑ አንጻር ሥራው ጥራትና በጥንቃቄ እንዲመራ አሳስበዋል።
በሐመረ ኖኅ በጥቶ ያልተማጸናና መልስ ያላገኘ አይኖርም ያሉት ብፁዕነታቸው በዚህ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ታሪካዊ አሻራ ሁሉም እንዲሳተፍ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
በቤተ ክርስቲያናችን በልማት ሥራዎችና የተለያዩ ክትትል የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ አሠራሩ መስተካከል ይገባዋል ያሉት ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያንን ክብር የምእመናን ታዛዥነንት የካህናት አገልግሎት ታሳቢ በማድረግ ወደ ፊት መጓዝ አለብን ብለዋል።
ለዚህ ሀገረ ስብከቱ በሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኘውን ሕጋዊ ቦታ በባለሙያዎች አስጠንቶ ለአምልኮ፣ለመቃብር እና ለልማት በሚል አቅጣጫ በማስቀመጥ ለማስተግበር በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውሰው የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም አስተዳዳርና መነኮሳት በራሳቸው ተነሳሽነት ይህን ሕንጻ ለመሥራት መነሳታቸው ለነገ የመሥራት ማሳያ ነው በማለት ገልጸዋል።
የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም የመነኮሳት ማረፊያ G+5 ሕንጻ መሠረት ድንጋይ ባለፈው ዓመት በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ ተባርኮ መቀመጡ የሚታወስ ነው።
🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚#ስለአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን"
#ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
#መረጃ ጥቆማ
[email protected] ይጠቀሙ።
በፌስቡክ https://www.facebook.com/AddisAbabaDiocese?mibextid=2JQ9oc
ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች የበይነ መረብ አማራጮች ለመከታታል
በቴሌግራም: https://t.me/AddisAbabaDiocese
በዋትስ አፕ: https://whatsapp.com/channel/0029VaJznc90rGiNUScgwn3U
በዩቱዩብ: http://www.youtube.com/@AddisAbabaDioceseMedia
በቲውተር: https://twitter.com/AADioceseMedia/media
በቲክቶክ:http://tiktok.com/@mediaofaadiocese
መጠቀም ይችላሉ።