ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media @satenawmedia1 Channel on Telegram

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

@satenawmedia1


ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ, ያልተነገረውን እንነግርዎታለን‼️



Ethiopia | Ethiopianews | Addismereja

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media (Amharic)

ሳተናው ሚዲያ በኢትዮጵያ የሚገኘው አሁኑን በውስጣዊ መረጃ ዘመን የሚባሉ ኢትዮጵያዊያንን በመብት ተስፋ ለሚቀበል፣ በኢትዮጵያ ከተማ ለሚያጋድሩ፣ ብሄራዊ አጀንዳችንን በማፍራት መረጃ ያድርጉና ዘምታ የሚጠቅም ነው። አሁንም የደረሰውን መነሻ የዚህ እዚህ ቻነል ሊኖር መሆኑን እና መረጃ ለመረጃ ይጠቀሙ። የሳተናው ሚዲያ ሰነድ የሆነው፣ የአዛዦ የቴሌግራም ድርጅት ነው፣ እና አዳዲᝪ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ለመድረስ ይለጣል።

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

23 Nov, 09:45


#የጥንቃቄ መልክት

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የተሰጠ ውክልና የለም - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

ለሥራ ዜጎችን እንልካለን በማለት የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።

ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ሚኒስቴሩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና እንደሌለ ገልጿል።

ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣እንግልትና ከሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ዜጎች የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ለማግኘት (lmis.gov.et) የተሰኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

23 Nov, 09:38


#በኮሬ ዞን ደመወዛቸው ያለአግባብ መቆረጡን የተቃወሙ ከ60 በላይ መምህራን ታሰሩ‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ከፍላጎታቸው ውጪ ያለአግባብ ደሞዛቸው መቆረጡን የተቃወሙ ከ60 በላይ የሚሆኑ መምህራን መታሰራቸው ተገለጸ።

የመምህራኑ ደመወዝ ከነሐሴ 2016 ዓ.ም ጀምሮ መቆረጥ መጀመሩን እና እንዲመለስላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውን ተከትሎ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን የታሳሪ መምህራን ቤተሰቦች ለቪኦኤ አስታውቀዋል።

ባለቤታቸው መታሰሩን እና እስሩ ከመምህራኑ ተቃውሞ ጋር የተያያዘ መሆኑን ለጣቢያው የገለጹ ወ/ሮ አስቴር አበበ "ባለቤቴ ታስሮ ነው የሚገኘው፤ ወረዳው ደመወዛችን ይመለስ ብለን ብንጠይቅም እምቢ ብሎናል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህን ተከትሎ ባለቤታቸውን ጨምሮ የታሰሩ በርካታ መምህራን በፖሊሶች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ያስታወቁት ወ/ሮ አስቴር አበበ በድብደባው ቆስለው እስከአሁን ድረስ ህክምና ለማግኘት የተከለከሉ መምህራን መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በወረዳው መምህር የሆኑት አቶ ወረደ ዋኪሶ በበኩላቸው መምህራኑ ከደመወዛቸው ላይ እስከ 25 በመቶ ያለአግባብ መቆረጡን አስረድተዋል።

በዚህም ምክንያት መምህራኑ አቤቱታቸውን በመምህራን ማሕበር አማካኝነት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት እና ለወረዳው አስተዳደር ቢያቀርቡም "የምታመጡት ነገር የለም፤ እኛ የላክናቸው ካድሬዎች አስማምተው በመጡት መሰረት ነው ደመወዛችሁን የቆረጥነው።" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የሳርማሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጎሹ ጌታቸው የመምህራኑን መታሰር አረጋግጠው "መምህራኑ የታሰሩት ሌሎች መምህራን እንዳያስተምሩ በማሳመጻቸው" ነው ብለዋል።
VOA
👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

23 Nov, 07:01


#AddisAbaba ‼️

ለ 614 ጫኝ እና አውራጆች ፍቃድ ተሰቷል።

በከተማዋ 614 የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ህጋዊ ፍቃድ አግኝተዋል ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የምሬት ምንጭ ሆኖ የቀጠለዉ የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀት ህጋዊ አካሄድ እንዲኖረዉ እየተደረገ ነዉ ተብሏል።

ከአንድ አመት ወዲህ የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት መመሪያ ህግ እንዲወጣ መደረጉ ተነግሯል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ የከተማዋ መታወቂያ አላቸዉ የተባሉ 7228 ወጣቶችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ሰምተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እየመራዉ ነዉ በተባለዉ መመሪያ በእያንዳንዱ እቃዎች የመጫን እና የማዉረድ ሂደት  ላይ የገበያ ጥናት የተደረገበት የዋጋ ተመን ማዉጣቱን የቢሮዉ ምክትል ሀላፊው አቶ ሚደቅሳ ተናግረዋል።

ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ተነሺዎችን ተከትሎ የሚጠየቁ የጫኝ እና አዉራጅ የዋጋ ተመን ክፍያዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ ተነስቶበታል።

ቢሮዉ በዚህ ዙሪያ ያሉ የቁጥጥር ክፍተቶችን ለማስተካከል ምን እየሰራ ነዉ ብለን ላነሳንላቸዉ ጥያቄ " ህጋዊ ማህበራቱ ለባለንብረቶች ንብረት ሀላፊነት እንዲወስዱ በማስገደድ  እንዲሁም የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ክትትል እያደረኩ ነዉ" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በከተማዋ አራብሳ እና ከከተማዋ መውጫ ላይ የሚገኙ ሰፈሮች ህገወጥ  የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀቶች በስፋት መታየታቸዉ ሰምተናል።

ይህንን ተከትሎ ማህበረሰብ ለአገልግሎቱ ህጋዊ ደረሰኝ እንዲጠይቅ ያስፈልጋል ተብሏል።

ሆኖም ህብረተሰቡ ንብረቱን ከጫኝ እና አዉራጅ አካላት ዉጪ በራሱ አቅም የማዉረድም ሆነ የመጫኝ ሙሉ ፍቃዱ ተሰቶታል።

ማህበረሰብ ይህን ያልተከተሉ ማህበራት በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊሲ ኮምሽን ነፃ የስልክ መስመሮችን በመጠቀም ጥቆማዎችን መስጠት የሚችሉ መሆኑን ቢሮዉ አሳዉቋል።

(ethio fm)

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

23 Nov, 05:41


ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተባለ፡፡

“ኦሬሽኒክ” ሚሳኤል በዲንፒሮ የሚገኘውን የሚሳኤል ማምረቻና የጦር መሳሪያ መጋዝን ማቃጠሉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ዩክሬን ረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን ተጠቅማ ሩሲያን እንድታጠቃ የፈቀዱት አሜሪካ እና ብሪታንያ፥ አዲሱ ሚሳኤል የኒዩክሌር አረር መሸከም የሚችልና አውሮፓን ኢላማ ለማድረግ የተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከሩሲያ ጀርመን ለመድረስ 14 ደቂቃ ብቻ እንደሚበቃው የተነገረለት “ኦሬሽኒክ” በ40 ደቂቃዎች ውስጥ በአሜሪካ ያሉ ኢላማዎችን መምታት እንደሚችል ተገልጿል።

ስለሩሲያው አዲስ ሚሳኤል “ኦሬሽኒክ” በቀጣዩ ሊንክ ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3CEGyF7

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

23 Nov, 04:28


አንድ ጊዜ የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ሀገር ቤት እንዳይገቡ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ተመራ ‼️

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ሀገር ቤት እንዳይገቡ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ተገለጸ።ረቂቅ አዋጁ በሀገሪቱ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አጓጓዝ፣ አከመቻቸት፣ መልሶ አጠቃቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ላይ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል ሲሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ ተናግረዋል።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራው ረቂቅ አዋጁ የዜጎችን በንጹሕ እና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል።በተጨማሪም የሀገሪቱን ዕድገት፣ የከተሞችን መስፋፋት እና እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥር የሚመጥን ዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ለመፍጠር እንደሚያግዝም ዋና ዳይሬክተሯ ለኢቢሲ አመላክተዋል።

አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሥራ ሲገባ በዜጎች ጤና እና በስነ-ምህዳር ላይ ከባድ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ የሚገኘውን የፕላስቲክ ምርት ጉዳት ለመቀነስ እንደሚያግዝም አስገንዝበዋል።
Via yenetube

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 17:31


#ኦሮሚያ ክልል ለወታደራዊ ስልጠና የሚደረግ አስገዳጅ ምልመላ መባባሱን ነዋሪዎች ገለጹ ‼️
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ለወታደራዊ ስልጠና በግዳጅ የሚወሰዱ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሰሜን ሸዋ ዞን ያያ ጉለሌ ወረዳ የፍታል ከተማ ነዋሪ ተማሪዎችን እና አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ ሰዎች በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ስልጠና መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

በ #አዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንዲት እናት ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የ17 አመት ልጃቸው ጌታቸው ተድላ ሂሪጎ በመንገድ ላይ ቆሎ እየሸጠ በነበረበት ወቅት በፖሊስ መታሰሩን ለማስለቀቅ 30,000 ብር መክፈል ባለመቻላቸው ልጃቸው ለውትድርና ስልጠና መወሰዱን አስረድተዋል።

በተመሣሣይ በጅማ ዞን ሰጠማ ወረዳ የግጦሽ ቦታ ለባለሀብቶች መሰጠቱን የተቃወሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ቤተሰቦቻቸው እስከ 70,000 ብር እንዲከፍሉ የተጠየቀባቸው ሲሆን መክፈል የማይችሉ ከሆነ ግን “ወታደራዊ ግዳጅ እንደሚጠብቃቸው” ነዋሪዎች ገልጸዋል።
#አዲስስታንዳርድ #Oromia
👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 17:21


#መረጃ ❗️❗️

በአማራ ክልል በተለያዩ መጠለያዎች የተጠለሉ ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያን


ስደተኞች ደኅንነታቸው አደጋ ላይ መውደቁን መናገራቸውን ኒው ሂውማኒተሪያን ድረገጽ ዘግቧል። ስደተኞቹ ታጣቂዎች ጥቃት እንደሚፈጽሙባቸውና የግዳጅ ጉልበት እንደሚያሠሯቸው መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። በደቡብ ጎንደር ዞን ደምቢያ ወረዳ በሚገኘው አለምዋች መጠያ የተጠለሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች፣ የታጠቁ ኃይሎች አካላዊ ጥቃትና ዘረፋ እንደሚፈጽሙባቸው፣ አፍነው እንደሚወስዷቸውና ባንድ ዓመት ውስጥ ዘጠኝ ስደተኞች በጥይት ተመትተው እንደሞቱ ዘገባው ጠቅሷል። በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ሰባት ሕጻናትን ጨምሮ 12 ስደተኞች ታግተው፣ ለማስለቀቂያ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደተጠየቀባቸው የመጠለያው አመራሮች ተናግረዋል ተብሏል።
via wazema

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 17:20


አትሌት ሰውመሆን አንተነህ ''ስፔሻል ዐይን''ተገጠመለት ‼️

አትሌት ሰውመሆን አንተነህ ሙሉ ወጪው ተሸፍኖለት ወደሕንድ ሀገር ተጉዞ ''ስፔሻል ዐይን'' ሊገጠምለት እንደሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለፁ ይታወቃል።

የ17 ዓመቱ አትሌት ሰውመሆን ታሪኩ ፔሩ ሊማ በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአምስት ሺሕ ሜትር ሀገሩን ወክሎ እንዲወዳደር አንደኛ ሆኖ ተመርጦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው ሆቴል ገብቶ በዝግጅት ላይ እያለ ልምምዱን ለመሥራት ወደ ጫካ በወጣበት አንድ ዕለት ፖሊስ ነኝ ካለ አንድ ሰውና ከሁለት ግብራበሮቹ ጋር በተፈጠረ እሰጣ ገባ አንድ ዐይኑን በሽጉጥ ተመትቶ ብርሃኑን እንዳጣ የሚዘነጋ ይታወሳል።

አትሌቱ ከገጠመው ከፍተኛ ጉዳት ለማገገም በዳግማዊ ምኒልክ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምናውን ሲከታተል ቆይቶ፣ በኋላም ሙሉ ወጪም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተሸፍኖ ለተሻለ ሕክምና ወደሕንድ ሀገር እንደሚጓዝ መነገሩም ይታወሳል።

በወቅቱ በሕንድም በመጀመሪያ ዙር ለሰባት ቀን ሕክምና ተደርጎለት እንደሚመለስና ከሁለት ወር በኋላ ''ስፔሻል ዐይን'' ለማስገጠም ተመልሶ እንደሚሄድ ተገልፆ ነበር።

ከሰሞኑም ለዚህ ሕክምና አትሌቱ ወደሕንድ እንዳቀና የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት ለአትሌት ሰውመሆን ''ስፔሻል ዐይን'' እንዳስገጠመለት የሚጠቁም መረጃ በአትሌቱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገፅ ላይ ተጋርቷል።
አትሌቱም ከአጋራው ፖስት ስር''ተመስገን አምላኬ ሁሉም ታሪክ ሆነ።'' የሚል መልዕክት አስፍሯል።

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 12:04


BreakingNews‼️

መንግሥት ሁለት ታዋቂ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን አገደ

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን ዋዜማ አረጋግጣለች። ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ “CARD” እና “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) ይገኙበታል።
ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል። 

ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል” የሚል ነው። ዋዜማ የደረሳት መረጃ የታገዱት ድርጅቶች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ ቢጠቁምም፣ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም።

ይህ እርምጃ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የእግድ እርምጃው በድርጅቶቹ መሪዎች አካባቢ የተጠበቀ እንዳልነበር ለመረዳት ችለናል።

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን መያዶችን የማገድ ስልጣን ቢኖረውም “የአሁኑ እርምጃ በሕጉ የተዘረዘረውን ቅደም ተከተልና ቅድመ ሁኔታ የሚጥስ ነው” ብለዋል ሌላ የሕግ ባለሞያ። ድርጅቶቹ እግዱን በሕግ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል።

ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ የዋዜማ ምንጮች እገዳው የተላለፈበት ሂደት ለእርሱም ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ድርጅቶቹን እና ባለሥልጣኑን ለማነጋገር እየሞከርን ነው።

[ዋዜማ]

==============================
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 11:33


#መረጃ‼️

ፖለቲከኛው  ጀዋር መሃመድ ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሰቃቂ  ግድያን አስመልክቶ አቋማቸውን አሳውቀዋል

ሰሞኑን ተገደለ ሰለተባለው ወጣት አስተያየት የሰጡት ጀዋር መሃመድ ለዚህ ሁሉ ምንጩ በሃገሪቱ እየተደረጉ ያሉ ጦርነቶች ናቸው ብለዋል ፡፡

ለእነዚህ ሁሉ ጦርነቶች እና ግጭቶች ዋነኛው ተጠያቂ በስልጣን ላይ ያለው  መንግስት ነው ሲሉ ጀዋር መሃመድ  የተናገሩት ፡፡
(አንኳር መረጃ)

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 04:51


በኦሮሚያ ክልል በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሚደረግ ግጭት እና ጦርነት መቀጠሉ የህዝቡን መከራ እና ሰቆቃ አባብሶታል።

የጦርነቱ ገፈት ቀማሽ የሆነው ህዝብ ፤ ግድያ እና መፈናቀልን ጨምሮ ጦርነቱ ያደረሰበት ቀውስ እንዲያበቃ በአደባባይ ድምጹን አሰምቷል።

በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል ከአንድም ሁለት ጊዜ ከሀገር ውጭ የተሞከረው የሰላም ንግግር አልሰመረም ። ህዝቡ ተፋላሚዎች ለሶስተኛ ጊዜ ተገናኝተው ችግሩን በሰላም ይፈታሉ ብሎ በሚጠብቅበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በየራሳቸው መንገድ የአስገዳጅ የአዳዲስ ወታደር ምልመላ እና አፈሳ እያከናወኑ ነው የሚል ስሞታ ይሰማል።

ይህ ደግሞ የሰላም ጥሪ የሚያሳተጋባውን የክልሉን ነዋሪ ተስፋ ከማሳጣት አልፎ ክልሉን ብሎም ሀገሪቱን ለተጨማሪ የቀውስ ዓመታት እንዳይጋብዝ አስግቷል።

  https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 04:22


🍫 እንደ ተመራማሪዎች ከሆነ ጥቁር ቸኮሌት የደም ዝውውር በጣም አስፈላጊ ወደሚባሉ የአንጎል ክፍሎች እንዲፈስ ያበረታታል።

https://t.me/satenawmedia1

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

22 Nov, 04:17


#Bitcoin

የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ98,000 ዶላር በላይ ሆነ።

" የመጀመሪያው የክሪፕቶ ፕሬዝዳንት " የተባሉትና " አሜሪካን የፕላኔታችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ " ያሉት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ከተረጋገጠ በኃላ ቢትኮይን ወደላይ ተተኩሷል።

ዛሬ የተመዘገበው የቢትኮይን ዋጋ በታሪክ ከፍተኛ ሆኗል።

አንድ የቢትኮይን ዋጋ 98,149 የአሜሪካ ዶላር ገብቷል።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት " በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ  " ሲሉ ለክሪፕቶ ማህበረሰቡ መልዕክት አስትላልፈው ነበር።
Via:tikvah

https://t.me/satenawmedia1